query_id
stringlengths
32
32
passage_id
stringlengths
32
32
query
stringlengths
7
297
passage
stringlengths
137
5.93k
category
stringclasses
6 values
link
stringlengths
28
740
f5fd44ed18e5aed2973c43954a443a26
9b68baa5f0ac122161b9972a3b5a0e8c
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሀምዶክ ጋር ተወያዩ
 በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሀምዶክ ጋር ሀገራቱን በሚያስተሳስሯቸው የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል::ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ፣ በሁለት ቀን ቆይታቸው በሁለቱ አገራት የጋራ ጉዳዮች በተለይም የሀገራቱን የሁለትዮሽና የኢኮኖሚ ትብብር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ የሚመክሩ ሲሆን፤ ትናንትናም ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ተወያይተዋል። በቆይታቸው፣ ሁለቱ መሪዎች ከሁለትዮሽ ትብብር በተጨማሪ በአካባቢያዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩም ይጠበቃል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቀደም ሲል በሱዳን ባደረጉት የሥራ ጉብኝት ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አልቡርሃን እንዲሁም ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።ኢትዮጵያና ሱዳን የሁለትዮሽ እና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ከማጠናከር በተጨማሪ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር በጋራ እየሠሩ መሆኑ ይታወቃል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37324
e82efade8f5062840f4614158c083d81
7afae9fc5555e83e90267407300d4991
በመቀሌና በማይጨው የሞባይል ድምጽ አገልግሎት መጀመሩ ተገለፀ
በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡37 ሰዓት ጅምሮ በመቀሌ ከተማና በማይጨው የተቋረጠው የስልክ አገልግሎት ዳግም ሥራ መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ::ኢትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የሰሜን ሪጅን የቴሌኮም አገልግሎትን ለማስጀመር ሰፊ ሥራዎችና ከፍተኛ ርብርብ ሲካድ መቆየቱን አስታውሶ፤ በአሁኑ ወቅትም በመቀሌና በማይጨው የሞባይል ድምጽ አገልግሎት ማስጀመር ተችሏል ብሏል::የመቀሌ የሞባይል ድምጽ አገልግሎት የተጀመረው አማራጭ ሃይል በመጠቀም ከመሆኑ አንፃር የአገልግሎት መቆራረጥ ሊያጋጥም ስለሚችል ደንበኞች ይህንኑ እንዲገነዘቡም ኢትዮ ቴሌኮም አሳስቧል:: የጥገናና የመሰረተ ልማቶችን መልሶ የማቋቋም ሥራዎችን በማከናወንና ከሃይል አቅርቦት ጋር የተገናኘ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመሥራት የተሟላ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል::ከዚህ ቀደም በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሑመራ፣ በሽራሮ፣ በማይፀብሪና፣ ማይካድራ እና በኮረም አካባቢዎች በከፊል እንዲሁም በአላማጣ ሙሉ ለሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት የተጀመረ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል::ድርጅቱ በሰሜን ሪጅን አገልግሎቱ መቼና እንዴት እንደተቋረጠ እንዲሁም ያቋረጡ አካላት በሚመለከት ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ዝርዝር መረጃና ማስረጃ ማቅረቡን አስታውቆ፤ አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ከዋና ሞባይል ጣቢያ የሚያገናኙና ሁሉም አማራጭ መስመሮች መቆረጣቸውንና የሃይል አቅርቦት መቋረጡ ዋነኛ ተግዳሮት መሆናቸውን መጥቀሱ ይታወሳል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37334
b2d37bb376915991f9a7daa5aed16518
9bbf843129c13d366a18a0fdace12ea3
የጁንታው ግፍ ባገታቸው መኮንኖች አንደበት
ጌትነት ተስፋማርያም ጁንታው በሀገር መከላከያ ሰራዊት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ከአንድ ሺህ በላይ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችን እና መኮንኖችን አፍኖ ወደ መቀሌ ነበር የወሰዳቸው። መቀሌ በመከላከያ ሰራዊት ኮማንዶዎች ስትያዝ እግሬ አውጭኝ ብሎ ሲሸሽ ብቻውን አልነበረም የሸሸው፤ እነዚህኑ ያገታቸውን የሀገር ባለውለታ ሰራዊቶችንም ይዞ እንጂ። ታጋቾቹን በእግር ከቦታ ቦታ እያጓጓዘ አድክሟቸዋል። ምግብና ውሃ ከልክሎ አሰቃይቷቸዋል። በዚህም ምክንያት አብዛኛው ታጋች የሰራዊቱ አመራሮች ተጎሳቁለዋል፤ የታመሙም አሉ። ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ ግን ወገን ለወገኑ ደረሰ። በሄሊኮፕተር እና በድሮን ጭምር የታገዘው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለቀናት ሲከታተል ቆይቶ አመቺ ቦታ ሲያገኝ በጁንታው አመራርና ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ወሰደ። መከላከያ ሰራዊቱ በምድር የሚያደርገውን ጥንቃቄ የተሞላበትን ኦፕሬሽን አጠናከረ። ይህንን የተቀናጀ እርምጃ መቋቋም ያልቻቸው የጁንታው ታጣቂ ግን ተሽከርካሪዎቹን እና ጠብመንጃውን እየጣለ በየጢሻውና ጉራንጉሩ አፈተለከ። በወቅቱ ታፍነው የነበሩ የሰራዊቱ አመራሮች ከደረሰላቸው ሰራዊት ጋር ታጅበው አዴትን ለቀው ወጡ። ከታፋኞቹ መካከል አንዱ የነበሩት የሰሜን ዕዝ ኢንዶክትሪኔሽን ኃላፊ ኮሎኔል አበባው መንግስቱ እንባ እና ሲቃ በተቀላቀለበት ድምጸት ባሳለፏቸው አስከፊ ቀናት የሆነውን ሁሉ አጋርተውናል። ‹‹በመጀመሪያ ደረጃ አፍነው በጦር አውድማ ለምን ሲያንቀሳቅሱን ከረሙ የሚለው ጥያቄ አልተመለሰልኝም። ወይ ሊደራደሩብን አሊያም አማራጭ ሲያጡ ሊጨርሱን አስበው ይሆናል። በወቅቱ ትልቁ ችግር የነበረው ግን ታፋኞችን በምግብ ለመጉዳት የተሸረበው ሴራ ነው›› ይላሉ። በቀን አንድ ዳቦ ይሰጣቸው እንደነበረ በማስታወስ በመጨረሻዎቹ ቀናት ግን እሷም ቀርታ ውሃ እና ማብሰያ በሌለበት በረሃ ጥቂት ዱቄት ብቻ እንደቀረበላቸው ያስታውሳሉ። ዱቄቱን የሚያገነፉበት አንድ ድስት ከሺ በላይ ለሆኑ ሰዎች ቀርቧል። ጨው እና ማባያ በሌለበት ሁናቴ ገንፎው በትግል ተሰርቶ ሲያበቃ ማቅረቢያ እቃ ግን በቦታው አልነበረም። “በወቅቱ ህይወታቸውን ለማዳን በድንጋይ ጥራቢ እና በእንጨት ቅርፊት ባዶውን ገንፎ ለሁለት እና ለሶስት ተቃምሰን ህይወታችንን ለማትረፍ ታግለናል” ሲሉ የነበረውን አስከፊ ሁናቴ በጉንጫቸው እየወረደ ባለው እንባ ታጅበው አስረዱን።ከምግቡ ባሻገር ግን በቆላ በደጋ በግዳጅ በእግር እንዲጓጓዙ መደረጉን አስታውሰው፤ በእግር ጉዞ ብቻ እግራቸው መላላጡን እና ያገኙትን ብትር ለምርኩዝነት እየተጠቀሙ ፍዳ ማየታቸውን ነግረውናል። አንድ ቀን ሙሉ ትልቅ ተራራ ሲወጡ መዋላቸውን አጫውተውናል። ‹‹ብዙ ጊዜ በውትድርና ኑረናልና ብዙ ጊዜ ችግር ሊያጋጥም ይችላል፤ በጁንታው ስር የገጠመን ችግር ግን ከየትኛውም ወቅት ጋር ሊነጻጸር የሚችል አይደለም>> ያሉት ኮሎኔል አበባው መንግስቱ፤ የእራሳቸው ጓደኞች እና የቀድሞ የስራ ባልደረቦች ጭምር ግፉን መፈጸማቸው ደግሞ የበለጠ እንደሚያሳዝናቸው አልሸሸጉም። በመጨረሻ ግን ጁንታው በመከላከያ ሰራዊት እርምጃ አማካኝነት መፈናፈኛ በማጣቱ ንብረቱን ትቶ በየአቅጣጫው መበታተኑን ታዝበዋል። አንዳንድ ባለስልጣናትም ሽርጥ ቢጤ ፊታቸው ላይ በመከናነብ እና ጥቁር መነጽር በማድረግ በዘመናዊ ተሽከርካሪ አብረው ሲከታተሏቸው እንደነበረ የታዘቡት ኮሎኔል አበባው፤ በመጨረሻዋ ሰዓት ግን ሁሉም ከየመኪናው እየዘለለ በየገደላገደሉ ሲያፈተልክ መመልከታቸውን ይገልጻሉ። የጁንታው ቡድን አፍኖ ከወሰዳቸው የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች መካከል አንዱ የሰሜን ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ኮሎኔል ተሾመ ይመር ናቸው። በጁንታው ቡድን ታጣቂዎች ስር የቆዩባቸው ከአንድ ወር በላይ የሆኑ ቀናት መራርነት ከባድ መሆኑን ነግረውናል። በአንድ በኩል በምግብ የሚቀጡበት መንገድ ለአብዛኛው መኮንኖች ጤና መቃወስ ጉልህ ሚና ነበረው። “የጁንታው ታጣቂዎች በመከላከያ ሰራዊት ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ በሚወሰድበት ወቅት ታፋኞችን ይዘው በጦር ቀጠና ውስጥ በእግር እንድንጓዝ ፈረዱብን። አብዛኛው ሰው በምግብና ውሃ ጥም ከመዳከሙ የተነሳ በቅጡ መራመድ እንኳን ቢያቅተውም ነብሱን ለማዳን ግን እየተደጋገፈ እና አፈሩንም ቢሆን እየቧጠጠ ተራራማ ስፍራዎችን ጭምር ሊጓዝ ችሏል” ብለዋል። ከተንቤን ተራራማ ስፍራዎች አንስቶ እዳጋ ሃሙስ እና አዴት ድረስ ብቻ ለአራት ቀናት ታፋኞች በእግር እንዲንቀሳቀሱ የተደረገበትን መንገድ መመልከት ቢቻል ጁንታው ምን ያህል ለሰብአዊነት የማይራራ አረመኔ መሆኑን ያሳያል። በየመንገዱ መጓዝ አቅቷቸው ወደኋላ የሚቀሩትን በዱላ እና በመሳሪያ በመምታት አሳፋሪ ተግባር ፈጽሟል። በተለይ ግን በህግ ማስከበር የጦር ግንባሮች የጁንታው ታጣቂዎች ያፈኗቸውን የሰራዊት አባላት እንደሽፋን በመጠቀም ለማስጨረስ ቆረጠው ነበር። ዶዘር ጭምር በማሰማራትም ለታፋኞች መቀበሪያ የሚሆን ጉድጓድ ሲዘጋጅ እንደነበርም ተመልክተናል። ሰራዊቱ ባይደርስ ምናልባት ከደቂቃዎች በኋላ በህይወት ላይኖሩ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊፈጠር እንደሚችል ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። የወገን ጦር በየጊዜው እኛ ወዳለንበት እየተጠጋ መሆኑን ግን በተለያዩ አጋጣሚዎች እየሰማን በመሆኑ እንደሚደርሱ ተስፋ አድርገናል። የታሰበውም አዴት ላይ ሆነ። በመጨረሻም መከላከያ ሰራዊትም ሆነ አየር ሃይል ሁኔታውን በመገንዘብ ለቀናት ታግሶ በመጨረሻ አመቺ ጊዜ ሲያገኝ በወሰደው ወገን የማዳን እርምጃ የጁንታው ኃይል እግሬ አውጭኝ ብሎ ተበታትኗል በማለት ሁናቴውን ነግረውናል። በወቅቱ በርካታ የጁንታው አመራሮች ግን በዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ሲንቀሳቀሱ እንደነበር እና በመጨረሻም የያዙትን ንብረት እና ፋይሎች እያንጠባጠቡ በየአቅጣጫው መበታተናቸውን አስተውለዋል። “መከላከያ ህዝባዊ ሰራዊት መሆኑን እናውቃለን፤ እንደሚደርስልንም እምነት ነበረን፤ ሌት ተቀን ብሎ የሚከፈለውን መስዋዕት እየከፈለ ደርሶልናል። ለተቋማችንም ሆነ ለመንግስት እኛን በሰላም ከአፈናው ለማውጣት የተደረገው ጥረት ከፍተኛ ዋጋ የተከፈለበት ስለሆነ ምስጋና አቀርባለሁ” ብለዋል። ታጋቾችን ለማዳን የተደረገውን ጥንቃቄ የተሞላበት ጥረት ያደነቁት መኮንኖች፤ በቀጣይ የጁንታውን አመራሮች አድኖ ለመያዝ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እና የሙያ ግዴታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37379
50aa4b275e63504990982310b0e29421
9bb80426b710ca71614c672fc7f6e1d2
በትግራይ እየተዋቀረ ባለው የመንግስት አስተዳደር ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተካተቱ መሆኑ ተገለጸ
በጋዜጣው ሪፖርተሮች አዲስ አበባ:- ከጁንታው መደምሰስ በኋላ በትግራይ ክልል እየተዋቀረ ባለው የመንግስት አስተዳደር ውስጥ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም እየተካተቱ እንደሆነ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አስታወቁ። ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዶ/ር ሙሉ ነጋ እንደገለጹት፤ እየተዋቀሩ በሚገኙ አስተዳደሮች ብዙ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ ነው። መሳተፍም ብቻ ሳይሆን የሽግግሩ መንግስቱ አካል ሆነው እስከ ቢሮ ሃላፊነት ድረስ ይመራሉ። እንደ ዶክተር ሙሉ ገለጻ፤ አረና፣ ትዴፓ እና አሲምባ የመሳሰሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በክልሉ ካቢኔ ውስጥ እንዲገቡ ተወስኗል። ከዚህ በፊት በነበረው የክልሉ ነበራዊ ሁኔታ እነዚህ አካላት በፖለቲካ አመለካከታቸው የተነሳ ሲታሰሩ፣ ሲገደሉና ሲሳደዱ ቆይተዋል። የትግራይ ክልል ሕዝብ በአፈና ውስጥ የኖረ ሕዝብ ነው ያሉት ዶ/ር ሙሉ፤ “በአሁኑ ወቅት ግን ህዝቡ ከታች ጀምሮ እየተሳተፈ ነው፡፡ይህ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ እየሆነ ያለ ነው። ቀበሌ፣ ክፍለ ከተማ እና ሌሎቹንም የአስተዳደር እርከኖች ጭምር ሕዝቡ ነጻ ሆኖ ራሱ እንዲመርጥ ይደረጋል” ብለዋል፡፡ በጁንታው ላይ የተወሰደው ሕግ የማስከበር እርምጃ ለትግራይ ክልል ሕዝብ እንደመልካም አጋጣሚ የሚወሰድ እንደሆነ ያነሱት ዶ/ር ሙሉ፤ በክልሉ የነበረው የዴሞክራሲ ምህዋር ዝግና ጭላንጭል ያልነበረው በመሆኑ በመንግስት የተወሰደው ሕግ የማስከበር እርምጃ ለትግራይ ክልል ሕዝብ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሸጋገር የሚያደርግ መልካም አጋጣሚ ተደርጎ የሚወሰድ ነው ብለዋል፡፡ “ከመጀመሪያው ጀምሮ የሕዝቡ አስተያየትና ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን ያነሱት ዶክተር ሙሉ ፤ “ይሄን ሁኔታ ይበልጥ አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡በትግራይ በአጭር ጊዜ የፖለቲካ ተሳትፎ ምህዳሩ መስፋት አለበት፡፡የሐሳብ ብዝሃነት በነጻት መስተናገድ አለበት፡፡ይሄ ራሱ ትልቅ አጋጣሚ ነው፡፡ከአሁን በኋላ በትግራይ ‘እኔ አውቅልሃለሁ፤ እኔ ብቻ’ የሚል አስተሳሰብ አይኖርም፡፡የመጫወቻ ሜዳውን እና የመጫወቻውን ሕግ እኩል እናደርጋለን” ነው ያሉት፡፡ እንደ ዶ/ር ሙሉ ገለጻ፤ በመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውን ክህደት የትግራይ ሕዝብ እየተገነዘበ መምጣት ጀምሯል፡፡በተደረጉ ውይይቶች እውነታውን ማወቅ እየቻለ ነው፡፡በመሆኑም ጁንታው የፈጸመውን ግፍና በደል እንዲሁም ኢሰብዓዊ ድርጊት ህብረተሰቡ በትክክል እየተገነዘበ መጥቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የትግራይ ብልጽግና ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር አብረሃም በላይ በበኩላቸው፤ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ለህዝብ ያለው ተቆርቋሪነት አሁንም ከህግ ማስከበር ዘመቻው በኋላ እያደረገ ባለው ድጋፍ ማየት ይቻላል ብለዋል። ሰራዊቱ ለህዝብ ያለው ተቆርቋሪነት አሁንም ከህግ ማስከበር ስራው በኋላ የትግራይ ህዝብ እንዳይቸገር ነዳጅ ሳይቀር ከራሱ ቀንሶ ለህዝብ እየሰጠ መሆኑን ነው ዶ/ር አብረሃም ያስታወቁት፡፡ “ህዝቡ የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ሲያገኝ የሚያሳየው ስሜት የተለየ ነው” ያሉት ዶ/ር አብረሃም፤ ይህ የሰራዊቱና የህዝቡ ወዳጅነት በዚሁ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡ መንግስትም በፍጥነት ምላሽ በመስጠት ለትግራይ ህዝብ የምግብና የመድሃኒት ድጋፍ በማድረግ ላይ ነው ያሉት ዶ/ር አብረሃም፤ የትግራይ ህዝብም በፍጥነት ወደ ነበረበት በመመለስ ትግራይን ማልማት አለበት ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37378
84592ffb0facab92fb4c73cf3c3fc7c9
dc21f6224bc2971992d2470ca5b0d116
በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ ነው
የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ጥገናውን ፈታኝ አድርጎታል ዋለልኝ አየለ አዲስ አበባ፡- በትግራይ ክልል በሁሉም አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገለጸ፡፡የህወሓት የጥፋት ቡድን በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ያደረሰው ጉዳት የከፋ መሆኑ የጥገና ሥራውን ፈታኝ እንዳደረገውም ተጠቁሟል፡፡የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም ለማስጀመር በተደረገው ሰፊ ጥረት የክልሉን ዋና ከተማ መቀሌን ጨምሮ በአንዳንድ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ጀምሯል፡፡በቀጣይም ወደ ሽሬ ያሉ አካባቢዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እና ከመቀሌ ወደ ዓድዋ ያሉ አካባቢዎችንም የማገናኘት ሥራ እየተሰራ ነው፡፡በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አቶ ሞገስ፤ መቀሌ ከተማ ላይ እንኳን መስመሮችን ለማገናኘት ያልተቻለበት ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበር ተናግረዋል፡፡አሁን ላይ በክልሉ መቀሌን ጨምሮ አንዳንድ ከተሞች ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጠት የተቻለ ቢሆንም፤ በቀጣይ ሙሉ መስመሩን ከማገናኘት በተጨማሪ ከዋናው መስመር ወጪ መስመሮችም መሰራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡በወጪ መስመሮችም ላይ ጉዳት ስለደረሰ እንደገና እየተሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡እንደ አቶ ሞገስ ገለጻ፤ የጥገና ሥራው በሌሎች አካባቢዎች እንደሚደረገው አይደለም፡፡ምክንያቱም የማስተላለፊያ መስመሮች በቦምብ የተመቱና በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ከመሆናቸው በተጨማሪ በፈንጅ የታጠሩ አካባቢዎችም አሉ፡፡በዚህም የኤሌክትሪክ ጥገና ሥራው እየተሰራ ያለው በኤሌክትሪክ ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ከፀጥታ ኃይል ጋር በመሆን ነው፡፡በዚህም የፀጥታ ኃይሉ ከፈንጅ ነፃ የሆኑ አካባቢዎችን እየለየ ለኤሌክትሪክ ባለሙያዎች ይሰጣል፡፡ሂደቱም ለኤሌክትሪክ ባለሙያዎች ፈታኝና ስጋት ያለበት ነው፡፡ምክንያቱም የኤሌክትሪክ ባለሙያዎች በስነ ልቦና ጫና ውስጥ ሆነው ነው ቀን ከሌሊት እየሰሩ ያሉት፡፡የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን ለመትከል ተራራማና ገደላማ ቦታዎ ውስጥ መግባትን ይጠይቃል፡፡የሰዓት እላፊ የታወጀባቸው አካባቢዎች ስላሉም በቂ ጊዜ ያለማግኘት ችግርም አለ፡፡ሆኖም በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ በመሆንም ክልሉ የአሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑን፣ አቶ ሞገስ ተናግረዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37387
63715925db5c89fdbbdce0d93ee40e34
afd1ca09ff7b6cce831a422b9f82faeb
ጁንታው ከመከላከያ ዘርፎ ለጥፋት ዓላማ ይጠቀምባቸው የነበሩ መሳሪያዎች ተጠግነው ወደ አገልግሎት እየተመለሱ ናቸው
ጌትነት ተስፋማርያምጁንታው ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ዘርፎ ለጥፋት ዓላማው ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ መሳሪያዎች ተጠግነው ወደ አገልግሎት በመመለስ ላይ መሆናቸው ተገለጸ። የምዕራብ ግንባር የጥገና ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል አባተ ተስፋዬ እንደገለጹት፤ ጁንታው ከመከላከያ ሰራዊት ዘርፎ ለጥፋት ዓላማው ሲጠቀምባቸው የነበሩ በርካታ የሀገር ሀብቶች ከየመንገዱ እየተሰበሰቡ ተጠግነው ወደ አገልግሎት በመመለስ ላይ ናቸው። እንደ ሌተናል ኮሎኔል አባተ ገለጻ፤ ጁንታው ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ሲከፍት ታንኮች፣ መድፎች እና በርካታ ከባድ መሳሪያዎችን ዘርፏል። ከባድ መሳሪያዎቹን ከዘረፈ በኋላ ይዞ ለመዋጋት ቢያስብም በመከላከያ ሰራዊቱ ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ እና በአየር ኃይል ኢላማቸውን የጠበቁ እርምጃዎች ምክንያት መሳሪያዎቹን እየጣለ ሊፈረጥጥ ግድ ሆኖበታል። አንዳንድ መሳሪያዎቹን በከፊል ሲያወድም የተቀሩትን ግን በየአስፓልት ዳሩ እና በየጫካው አስቀምጦ እግሬ አውጪኝ ብሏል። ከሃዲው ቡድን ከመከላከያ ሰራዊቱ የደረሰበትን እርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ ከሽሬ አንስቶ እስከ ሽራሮ እና ተንቤን ድረስ በየመንገዱ ያንጠባጠባቸው ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያየ አቅም ያላቸው መድፎች፣ ሎቤዶች እና ቢኤም መሳሪያዎች ተጓጉዘው ወደሽሬ የጥገና ማዕከል እየገቡ ይገኛሉ ያሉት ሌተናል ኮሎኔል አባተ፣ የጥገና ባለሙያዎችም መሳሪያዎቹን በመፈተሽ ዳግም ወደስራ ለማስገባት በመረባረብ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። በርካታ ከባድ መሳሪያዎች እና ተሽከርካሪዎችም ከጥገናቸው በኋላ የተሳካ ሙከራ ተደርጎባቸው ወደስራ መመለሳቸውን ሌተናል ኮሎኔል አባተ ተስፋዬ ተናግረዋል። ለመሳሪያዎቹ ጥገና አስፈላጊው ዝግጅት እና የመለዋወጫ አቅርቦት በሀገር ውስጥ መኖሩን የገለጹት ሌተናል ኮሎኔል አባተ፤ የመከላከያ ሰራዊቱ ንብረቶችን አጠቃላይ የጥገና ስራ ሙሉ በሙሉ በኀገር ውስጥ ባለሙያዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። ጁንታው አስቀድሞ ለጥፋት ዓላማው ዝግጅት በማድረጉ ከባድ መሳሪያዎችን የሚጠግኑ ባለሙያዎችንም ከሰራዊቱ ጋር አፍኖ መውሰዱን አስታውሰው፤ መከላከያ ሰራዊት ባደረገው ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ ባለሙያዎቹን ከጁንታው ቡድን ነጻ ማውጣት መቻሉንም ገልጸዋል። አሁን ላይ ከተለያዩ ከተሞች የተሰባሰቡ የሰራዊቱ ባለሙያዎች አገልግሎቱን በተሳካ ሁኔታ በመስጠት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። እንደ ሌተናል ኮሎኔል አባተ ገለጻ፤ ጁንታው ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ከፈጸመ የሰሜን እዝ የሰራዊቱ ንብረት የሆኑ በርካታ ከባድ መሳሪያዎችን ዘርፎ መውሰዱ ይታወሳል። ከባድ መሳሪያዎቹንም ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ለጥቂት ቀናት ህዝብ እና ሀገር ለማሸበር ሲጠቀምባቸው ቆይቷል። በመከላከያ ሰራዊት በቅንጅተ በወሰዱት እርምጃ መሳሪያዎቹ ተጠግነው ዳግም ለአገልግሎት መብቃታቸው የመልሶ ግንባታ እና የማደራጀት ስራዎች በተሳካ ሁኔታ በመከናወን ላይ ናቸው። ሌተናል ኮሎኔል አባተ እንደገለጹት፤ ጁንታው በሀገር ሀብትና ጉልበት የተሰሩ መንገዶችን ሲቆፍርባቸው የነበሩ ዶዘሮች እና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እንዳይበላሹ የጥበቃ ስራ እየተከናወነ ይገኛል። በጁንታው የተበላሹ መንገዶችም ጊዜያዊ ጥገና ተደርጎላቸው ከባድ ተሽከርካሪዎች የሚፈለግባቸው ግዳጅ እየተወጡ ይገኛል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37380
a48d28ba7e88746db7f0567b145a178c
ad86814e34fc373f38f39d979ab62b4c
ከዶሃው ቻምፒዮና ተምሮ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
 ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ ለቀረው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ከወዲሁ ዝግጅት እንደሚደረግ ተገለጸ። በዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ተሳታፊ ለሆነው ብሄራዊ ቡድንም ገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል። የቶኪዮ ኦሊምፒክ በመጪው ሐምሌ ወር እንደሚካሄድ ይታወቃል። ለዚህ ውድድር ከወዲሁ ትልቅ ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የዶሃው የዓለም ቻምፒዮና አመላካች እንደሆነ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል። ከትናንት በስቲያ ምሽት በዶሃ ለተሳተፈው ልዑክ በተደረገው የሽልማት ስነስርዓት፣ አትሌቶቹ በኳታር ከፍተኛ የሙቀት መጠን ተወዳድረው ያስመዘገቡት ውጤት የሚያስመሰግናቸው መሆኑ ተገልጿል። ይሁን እንጂ ከተስተዋሉት ጥቃቅን ስህተቶች ከፍተኛ ትምህርት በመውሰድ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በሽልማት ስነስርዓቱ እንደተናገረችው፣ በዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና የተመዘገበው ውጤት ጥሩ ቢሆንም የሚያኩራራ ሳይሆን ለቶኪዮ ኦሊምፒክ መንግስት፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲሁም ፌዴሬሽኑ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ሊረባረቡበት እንደሚገባ አመላካች ነው። በ17ኛው የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፈው ቡድን፤ ሁለት የወርቅ፣ አምስት የብር እና አንድ የነሃስ በድምሩ ስምንት ሜዳልያዎች በመሰብሰብ ከዓለም አምስተኛ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁ ይታወሳል። በዕውቅና እና ሽልማት መርሃ ግብሩም ላይ የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገቡ አትሌቶች 40 ሺ ብር፣ የብር ሜዳሊያ ያስመዘገቡ አትሌቶች 30ሺ ብር ተሸላሚዎች ሆነዋል። የነሐስ ሜዳሊያ ያስመዘገበችው ብቸኛዋ አትሌት ጉዳፍ ፀጋየ 20 ሺ ብር እንዲሁም ዲፕሎማ ላገኙና ተሳታፊ ለነበሩ አትሌቶች ማበረታቻ ገንዘብ ተበርክቷል። ለመርሃ ግብሩም በአጠቃላይ ከ2 ነጥብ 25 ሚሊየን ብር በላይ መውጣቱ ታውቋል። በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው ባልቻ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ እንዲሁም የፌዴሬሽኑና የኦሊምፒክ ኮሚቴው ሥራ አስፈፃሚ አባላት ተገኝተዋል። ከሽልማቱ ባሻገር ኢትዮጵያውያን የአትሌቲክስ ባለሙያዎች በዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ዕውቅና ማግኘታቸውም ተጠቁሟል። በዚህም ፈር ቀዳጅ እና ውጤታማ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ በሚል ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ሲመረጡ፤ በርካታ አትሌቶችን ያፈራችው በቆጂ የስመጥር አትሌቶች መፍለቂያ በመባል ተወድሳለች። በተለየ መርሃ ግብር ደግሞ የቴክኒክ ዳይሬክተሩ አቶ ዱቤ ጅሎ በተሳለጠ የአትሌቲክስ አሰራር የዓለም አቀፍ ቬተራን ደረት ፒን እና የምስክር ወረቀት ከዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮ እንደተበረከተላቸው ይታወሳል። አዲስ ዘመን ጥቅምት 12/2012 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=21257
5050d8ae95facf42f0fd00440fb4e679
7e7a341b60c2c65f6e26d90a322f7de3
ቀዩ ትንቅንቅ ድሮም ዘንድሮም ወደ ፊትም አንድ ነው
 ሁለቱን ከተሞች ከአንድ ሰዓት ያነሰ መንገድ ብቻ ያለያያቸዋል። ማህበራዊና ታሪካዊ ዳራዎች ያጠሉበት የማንቸስተርና ሊቨርፑል ከተሞች እግር ኳስ የዘላለም ተቀናቃኝ አድርጓቸዋል። የሰሜን ምዕራብ እንግሊዝን የበላይነት ለመቆጣጠር ሁለቱ ከተሞች ፍልሚያ ያደርጉ ነበር። ማንቸስተር በማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ ትመራለች፤ ሊቨርፑል በወደብ ከተማነት ትንቅንቅ ውስጥ ይገባሉ። ድንገት ግን የማንቸስተር የመርከብ መተላለፊያ መንገድ ታናል ተሠራና መርከቦቹ በቀጥታ ሊቨርፑል ከተማን ዘለው ዕቃዎችን ወደ ማንቸስተር ማጓጓዝ ቻሉ። የሊቨርፑል ነጋዴዎችና ህብረተሰቡ ኑሮው ቀነሰ፤ ሥራ አጦች በረከቱ፤ ቁጣም ተፈጠረ። ያ ክስተት በሁለቱ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ልዩነትን ፈጠረ። ያም የከተማ ተቀናቃኝነት የኢኮኖሚ ሽኩቻ በቀላሉ ወደ እግር ኳስ ሜዳዎች ሰተት ብሎ ገባ። ሁለቱ ክለቦች «የእንግሊዝ ሀያሉ ክለብ እኔ ነኝ» በማለት ዛሬም ድረስ ይቆራቆዛሉ።ማንቸስተር ዩናይትድና ሊቨርፑል በጋራ 124 ዋንጫዎችን ጥርግርግ አርገው የመደርደሪያቸው ማድመቂያ አድርገዋል። ሊቨርፑል እኤአ ከ1975 እስከ 1990 11 የሊግ ዋንጫዎችን ያነሳባቸውን ዓመታት በኩራት ያነሳል። ማንቸስተር እኤአ ከ1993 እስከ 2013 ፍፁም በነገሠባቸውና 13 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ባነሳባቸው ዓመታት በመኩራራት «የእንግሊዝ ሀያሉ ክለብ እኔ ነኝ»ይላል። ዩናይትድ 20 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ሊቨርፑል 18 ዋንጫዎችን በማንሳት በታሪክ ተከታትለው ይጠራሉ። ዛሬም ድረስ ግን ሁለቱ ክለቦች የማይበርድ ውዝግብ ያደርጋሉ። ቀዩ ትንቅንቅ ድሮም ዘንድሮም ወደ ፊትም ተመሳሳይ ነው። እግር ኳስ ለሁለት የሰነጠቃቸው ሁለት ከተሞች ጉምቱ አሰልጣኞች ስድብ ያመርቱበታል፤ ገናና ተጫዋቾች ሁሌም ይተናነቁበታል። ኮከቦቻቸው አንጨባበጥም ያሉበት የእግር ኳስ ጦርነት ከሁለቱም አቅጣጫ እሳት በየዘመኑ ይወረወራል። ጨዋታው የ90 ደቂቃ ብቻ አይደለም። ከዚያ የዘለለ ትርጉም ይሸከማል። በተቀናቃኞቻቸው የሞት ክስተት ላይ እንኳን ሹፈትን ለመፍጠር የማይመለሱ ነውጠኛ ደጋፊዎች የሚታዩበት፤ ታሪክም ወቅታዊ ሁኔታም ጋዝ ሆነው የሚያቀጣጥሉት፤ አሰልጣኞችም ተጨዋቾችም ከስሜት የማይፀዱበት፤ ልጅም አዋቂም እኩል ጎራ ከፍለው የሚሻኮቱበት፣ የፖለቲካም የኢኮኖሚም የስፖርት የበላይነት ጥያቄም ያልተለየው የእግር ኳስ ጦርነት። «ቀዩ ትንቅንቅ።» ሁለቱ ቀያይ ለባሾች አንዱ አንዱን አምርሮ ከመጥላቱ ባሻገር በተራ ጨዋታ መሸናነፍ እንደሞት ይቆጥሩታል። ዋንጫ በሌለበት እንኳን ማሸነፋቸው እንደ ዋንጫ ማንሳት ይቆጠርላቸዋል። «የኔ ፈተና አንድ ብቻ ነው ሊቨርፑልን ሁሌም በሚኩራሩበት ሜዳ መደቆስ፤ ከዛ ቀሪውን እናንተ ትፅፉታላችሁ» በማለት ታላቁ የዩናይትድ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በአንድ ወቅት ለጋዜጠኞች የሰጡት አስተያየት የክለቦቹን ሽኩቻ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። «እኔ ስለ ሊቨርፑሎች ምን አገባኝ?፤ ደጋፊያቸው፤ ስታዲየማቸው ምናቸውም ደስ አይለኝም፤ እነሱን ስናሸንፍ የሚሰማኝን ደስታ እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው» ያለበት የዩናይትዱ ታሪካዊ ተጫዋች ጋሪ ኔቭል ንግግርም የሚዘነጋ አይደለም። የቅርቡ ኮከባቸው ዋይኒ ማርክ ሩኒም ቢሆን «ያደግኩት ሊቨርፑልን እየጠላሁ ነው» ማለቱ እስከአሁን ክለቡን ለቆ እንኳን ጥርስ አስነክሶበታል። ወደ አንፊልድ መንደርም ይህ መሪር ጥላቻ ተመሳሳይ ነው። በአንድ ወቅት ታሪካዊው ኮከባቸው ስቴቭን ጀራርድ ወደ መኖሪያ ቤቱ አንድ የቀረፃ ቡድን ይዞ ሄደ። «እነዚህ የምትመለከቷቸው መለያዎች በርካታ የተቃራኒ ክለብ መለያዎች ሲሆኑ ከጨዋታ በኋላ የተቀያየርኳቸው መለያዎች ናቸው፤ ግን አንድም የዩናይትድ መለያ አታገኙም፤ አንድም የዩናይትድ መለያ ቤቴ አይገባም» ያለበት አጋጣሚ ጥላቻው ከእግር ኳሳዊ ጉዳይ የዘለለ ምክኒያት ያለው አስመስሎት ነበር። ሉዊስ ሱዋሬዝ ፓትሪስ ኤቭራን ያልጨበጠበት፤ ሪዮ ፈርዲናንድና ዳኒ ዌልቤክ ሱዋሬዝን አንተ አትጨብጠንም በማለት አፀፋ የሰጡበት ክስተት የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ተጫዋቾች በቀዩ ትንቅንቅ ስሜታቸውን የሚገልጹበት መንገድ የተለየ ነው። ኳስና መረብ ሲያገናኙ ደስታቸውን ለመግለጽ ሜዳው አይበቃቸውም። ሲበለጡ ሽንፈትን በፀጋ የመቀበል ክህሎታቸው ይከዳቸዋል። ሁሌም ከሜዳ ውጪ የሚጫወተውን ክለብ ለመደገፍ ትኬት ማግኘት ከባድ ነው። ቀድሞ ትኬት ይጠናቀቃል። በጠላት ድንበር ገብተህ እንደመዘመርና እንደ መቦረቅ ምን የሚያስደስት ነገር አለ የሚሉ ደጋፊዎች ብዙ ናቸው። ኦልድ ትራፎርድን ህልም እውን የሚሆኑበት፤ አንፊልድን የታማኝ ደጋፊዎች ህብረ ድምፅ ሌላ ዓለም የሚያስመስላቸው ያኔ ነው። በቀዩ ትንቅንቅ በጨዋታ ወቅት በሚፈጠሩ ነገሮች ሁሉ በብስጭት የተገኘ ነገር ሁሉ ይወረወራል። ፈርጉሰን በሊቨርፑል ደጋፊዎች በእንቁላል ተደብድበዋል። በ2011 የታዳጊዎች ኤፍ ኤ ጨዋታ ተቋርጧል፣ ብዙ ብዙም ነገር ተከስቷል። የሁለቱን ክለቦች የመረረ ጥላቻ የሚያሳይ ሌላም መገለጫ አለ። እኤአ በ1964 ፊል ቼዝናል የተባለ ተጫዋች ከዩናይትድ ወደ ሊቨርፑል ከተዛወረ በኋላ ባለፉት ከሃምሳ አራት ዓመታት በላይ በሁለቱ ክለቦች መካከል አንድም የተጫዋቾች ዝውውር በቀጥታ ተፈፅሞ አያውቅም። ሊቨርፑል በአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ እየተመራ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አምና በማንሳት ወደ ኃያልነቱን ለመመለስ መንገድ ጀምሯል። ከሃያ ስምንት ዓመታት በኋላ ፕሪሚየርሊጉ ላይ መንገሥም ወደ ኃያልነቱ ለመመለስ ትልቅ ዋጋ አለው። ከስምንት ጨዋታዎች ሙሉ ሃያ አራት ነጥብ በመሰብሰብ የመጡበት ወጥ አቋም በታሪካዊው ተቀናቃኛቸው እንደማይገታ የብዙዎች እምነት ነበር። በተለይም ዩናይትድ ከስምንት ጨዋታ ዘጠኝ ነጥብ ብቻ ይዞ እጅግ በደከመ አቋም መገኘቱ ብዙዎች ከትናንት በስቲያ በተደረገው ቀዩ ትንቅንቅ በርካታ ግብ እንዳያስተናግዱ ስጋት ፈጥሮባቸው ነበር። ያምሆኖ ቀዩ ትንቅንቅ ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም አንድ ነውና ዩናይትዶች እንደተፈራው የግብ ናዳ ሳይወርድባቸው አንድ ለአንድ በሆነ ውጤት የሊቨርፑልን መቶ በመቶ የአሸናፊነት ጉዞ መግታት ችለዋል። ባለፉት ስምንት ሳምንታት ለትናንሽ ክለቦች እንኳን ሲያንቀላፉ የነበሩት ዩናይትዶች ለታሪካዊ ተቀናቃኛቸው እንደማይተኙ አሳይተዋል። ይህም የተነቃነቀው አሰልጣኛቸው ሶልሻየር ወንበር ለጊዜውም ቢሆን ረግቶ የሚቆይ አስመስሎታል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 11/2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=21221
5b09f05a2d72c6fa53116393dcf20d25
0d3a92bfdf79b699d7eb03245ba05d17
ጫማ ሰቅለው ጓንት ያነሱ፤ ከሩጫም ወደ ኳስ ያቀኑ ኮከቦች
 ልምምድን አድምቶ በመስራትና በጥንካሬ በመቆየት የመጨረሻዋን መስመር በቀዳሚነት መርገጥ ዋጋው ከደስታም ይልቃል። ሃገርን ማስጠራት እንዲሁም ክብርን መቀዳጀት ደግሞ የስኬታማነት ክፍያው ነው። እንደ አትሌቶቹ ሁሉ፤ ልምምድን በትጋት መልሶ መላልሶ መስራት የግድ ነው፤ በየትኛውም ስፖርት ከውጤት ማድረሱም እውነት ነው። ባሉበት ስፖርት በታማኝነት ጊዜን፣ ጉልበትንና አቅምን አሟጦ መጠቀምም አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ስኬትን ከተቀዳጁበት አንድ ስፖርት ወደ ሌላ በመሸጋገር በድጋሚ ውጤታማ መሆን ይቻላል? ከተጫዋችነት አሊያም ከአትሌትነት ወደ አሰልጣኝነት እንዲሁም ወደ አማካሪነትና ሌሎች ስራዎች መሸጋገር የተለመደ ነው። ጫማ ሰቅሎ የቦክስ ጓንት ማጥለቅ፣ ከመም ወደ እግር ኳስ ሜዳ መሸጋገር እንዲሁም ጓንት ሰቅሎ የበረዶ ላይ ገና ጨዋታ ዱላን ማንሳት ግን አደናጋሪ ነው። ዋናው ጥያቄም እውን እጅግ በተለያዩ ሁለት ስፖርቶች በቀላሉ ስኬታማነትን ማግኘት ይቻላል? የሚለው ይሆናል። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ጥናት ማድረግን ቢጠይቅም፤ ለዛሬ ከአንዱ ወደ ሌላኛው ስፖርት የተሸጋገሩ ስፖርተኞችን እናንሳ። «በርካታ ዋንጫዎችን አንስቻለሁ፤ አሁን ግን ቀበቶ ማግኘት እፈልጋለሁ» በሚል ነበር የተነሳው። ይህ የሁለት ክብሮች ናፋቂ የእንግሊዝን ብሄራዊ ቡድንን ለ14ዓመታት በተለይ የታወቀበትን ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድን ደግሞ ለ12ዓመታት ያገለገለው ሪዮ ጋቪን ፈርዲናንድ ነው። በአራት ክለቦች ሁለት አስርት ዓመታትን በተጫዋችነት ያሳለፈው ፈርዲናንድ፤ በእንግሊዛውያን ዘንድ የምንጊዜም ተወዳጅነትን ካተረፉ ተጫዋቾች መካከል ተጠቃሽ ነው። ስድስት የፕሪምየር ሊግ፣ አንድ የቻምፒዮንስ ሊግ፣ አንድ የፊፋ የክለቦች እንዲሁም ሌሎች ዋንጫዎችን ጨምሮ በርካታ ክብሮችንም በግሉ እና በቡድን አግኝቷል። በ39ዓመቱ የእግር ኳስ ሜዳን ሲሰናበት ግን የቦክስ መፋለሚያ ሪንግን እያሰበ ነበር። በሰቀለው ጫማ ምትክም ጓንት ማጥለቁ መነጋገሪያ አድርጎታል፡፡ በፕሮፌሽናል ቦክሰኛነት በከባድ ሚዛን ለመሳተፍ በሳምንት ከ4-5 ቀናት ልምምድ እንደሚያደርግም አስታወቀ። ነገር ግን በፕሮፌሽናል የቦክስ ማህበር በኩል «ብቁ ነህ» የሚል ማረጋገጫ ማግኘት ሳይችል ቀረ። በዚህ ምክንያትም ማዘኑን «ቦክስ ሰውነት ብቻም ሳይሆን ጠንካራ ልብ ነው የሚፈልገው» ሲል ነበር የገለጸው። የእግር ኳስ ተንታኝ የሆነው አንጋፋው ተጫዋች እንዲያም ቢሆን ፈቃዱን ለማግኘት ጥረቱን እንደማይተውና ጠንክሮ እንደሚሰራ አረጋግጧል። ጃማይካዊው የዓለም ፈጣኑ ሰው ደግሞ ከመም በቀጥታ ወደ እግር ኳስ ማንከባለል የገባ ስፖርተኛ ነው። የሰው ልጅ በዚህን ልክ ይፈጥናል ተብሎ ባይጠበቅም በአጭር ርቀት አትሌቲክስ አዲስ ታሪክ ያስመዘገበው ቁመተ መለሎውና ቀልደኛው ዩሲያን ቦልት ስምንት የኦሊምፒክ ሜዳሊያዎችን ጠራርጎ በመውሰድ ስኬታማ ነው። ቦልት 100 ሜትርን በ9ሰከንድ ከ58 ማይክሮ ሰከንድ፣ 200ሜትርን ደግሞ 19ሰከንድ ከ19ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት የዓለምን ክብረወሰን አርቆ የሰቀለ አስደናቂ አትሌት ነው። ቦልት ከታወቀበት አትሌቲክስ ባሻገር እግር ኳስን እጅግ የሚወድ እንዲሁም የሚመኘውም ስፖርት ነው። የእንግሊዙ ማንቺስተር ዩናይትድ ክለብ ደጋፊ የሆነው አትሌቱ የቀያዮቹ ሴጣን ተጫዋች የመሆን ህልም እንዳለውም ይናገር ነገር። እአአ ከ2017ቱ የለንደን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በኋላም ከአትሌቲክስ ስፖርት ወጥቶ ወደ እግር ኳስ መግባቱን አሳወቀ። የእግር ኳስ ልምምዱን በቅድሚያ የጀመረው በኖርዌይ ክለብ ሲሆን፤ የዓለምን ክብረወሰን ያስመዘገበበትን 9.58 የሚያስታውስ ማሊያ ይለብስ ነበር። ከቆይታ በኋላም የአውስትራሊያውን ሴንትራል ኮስት ማሬነርስ የተባለውን ክለብ ተቀላቀለ፤ በመጀመሪያው የወዳጅነት ጨዋታም ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ቻለ። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ከስፖርት ህይወት ሙሉ ለሙሉ ወጥቶ ወደ ንግድ መግባቱን ይፋ አደረገ። ለበርካታ ጊዜያት ጾታዊ ጥርጣሬ ውስጥ በመግባት አስቸጋሪ ጊዜን መግፋት የግድ የሆነባት ደቡብ አፍሪካዊቷ አትሌት ካስተር ሰመኒያም በቅርቡ ከአትሌቲክስ ስፖርት እግር ኳስን እንደመረጠች አስታውቃለች። በተክለ ቁመናዋ ምክንያት በርካታ ፈተናዎችን ለመጋፈጥ የተገደደችው የ800 ሜትር የኦሊምፒክ ቻምፒዮናዋ ሰመኒያ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ያወጣውን ደንብ ተከትሎ በክስ ሂደት መቆየቷ ይታወሳል። ነገር ግን እሰጣ አገባው እንዳሰበችው ሆኖ ባለመጠናቀቁ፤ በልጅነቷ ታንከባልል እንደነበር ወደ ገለጸችው ኳስ ገብታለች። በሃገሯ የሚገኝን ክለብ የተቀላቀለችው ተጫዋቿ አዲሱ የጨዋታ ዘመን እስኪጀመር በልምምድ ላይ የምትቆይ መሆኗን ተከትሎ «ይሻላል» ባለችው እግር ኳስ ያላትን ብቃት ማስመስከር አልቻለችም። ከሰሞኑ በተሰማ ሌላ ዜና ደግሞ የቀድሞው ግብ ጠባቂ ፒተር ቼክ በጓንቱ ፋንታ የበረዶ ላይ ገና ጨዋታ ዱላ ወደ ማንሳት መሸጋገሩን አስታውቋል። በተለይ በሰማያዊዎቹ እና በመድፈኞቹ ቤት ቆይታው የሚታወቀው ግብ ጠባቂው ጓንቱን ከሰቀለ በኋላ በቀድሞ ክለቡ ቼልሲ የቴክኒክ አማካሪ በመሆን እያገለገለ ይገኛል። ከዚህ ስራው ጎን ለጎንም በልጅነቱ የተጫወተውንና የሚወደውን ይህንን ስፖርት ተቀላቅሏል። እንደ ግብ ደጀንነቱ ሁሉ በዚህ ስፖርትም ስኬታማ መሆን አለመሆኑም ጊዜ ምላሽ ይሰጥበታል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 3/2012ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=20763
c7db0d7bc6599481a89da4dec68e3006
e4d0fdf888fab3127b825320aa3d4175
የሲቲ ካፕ ጨዋታዎች በቅርቡ ይጀመራሉ
የ2012 ዓም ፕሪሚየር ሊግ ቅድመ አቋም መለኪያ ውድድሮች በተያዘው ወር አጋማሽ ይጀመራሉ። የአዲስ አበባ እና የደቡብ ክልል የቅድመ ውድድር ዘመን ጨዋታዎች ዝግጅትም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ክለቦች የውድድር ዘመኑ ከመጀመሩ አስቀድሞ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን እንደሚያደርጉ ይታወቃል። በኢትዮጵያም የተለያዩ ክለቦችን በማሳተፍ ከተማ አቀፍ (ሲቲ ካፕ) ጨዋታዎችን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከመጀመሩ አስቀድሞ ማካሄድ የተለመደ ነው። ረጅም ዓመታትን ካስቆጠሩት ውድድሮች መካከል በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቀዳሚው ሲሆን፤ ዘንድሮም ለ14ኛ ጊዜ ይካሄዳል። በዚህም መሰረት ውድድሩ በተያዘለት መርሐ ግብር ከጥቅምት 22 እስከ ህዳር 7/2012ዓ.ም እንደሚካሄድ ሶከር ኢትዮጵያ በዘገባው ጠቁሟል። በውድድሩም ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መከላከያ፣ ኤሌክትሪክ፣ ወልቂጤ እና ሰበታ ከተማ ተሳታፊነታቸው ተረጋግጧል። የኢኮስኮ እና የኢትዮጵያ መድን ተሳታፊነት አጠራጣሪ ሲሆን፤ ሲዳማ ቡና እና ባህርዳር ከተማ ተሳታፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠበቃል። የዚህን ዓመት ውድድር ልዩ የሚያደርገውም በሽልማት እንዲሁም በተለያዩ ነገሮች ላይ ማሻሻያ በማድረጉ እንደሆነም በዘገባው ተመላክቷል። አሸናፊ በመሆን ዋንጫውን ለሚያነሳው ክለብ ብቻም ሳይሆን በደረጃ ለሚያጠናቅቁት ክለቦችም ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት የሚበረከትላቸው ሲሆን፤ ሌሎች ክለቦችም በተሳታፊነታቸው ብቻ በስጦታ መልክ ገንዘብ የሚበረከትላቸው ይሆናል። የስታዲየም መግቢያ ትኬቶችን እንዲሁም ሌሎች ሥራዎችንም በዘመናዊ መልኩ ለማከናወን ጥረት በመደረግም ላይ ይገኛል። ከዚህም ባሻገር ውድድሩ የመገናኛ ብዙሃን የቀጥታ ሽፋን እንደሚያገኝ ታውቋል፡፡ በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኘው ቴሌቪዥን ጣቢያ ከእጣ አወጣጡ ጀምሮ የተመረጡ ጨዋታዎችን ሽፋን በመስጠት ለህዝቡ የሚያደርስም ይሆናል። ሌላኛው የደቡብ ሪጅናል ካስቴል ዋንጫ ሲሆን፤ ከጥቅምት 15 ጀምሮ በሃላባ ቁሊቶ ከተማ የሚካሄድ መሆኑን የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ጠቁሟል። ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደው ይህ ውድድር አስር ክለቦችን እንደሚያሳትፍ የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። የፕሪምየር ሊጉ ተሳታፊ የሆኑት የክልሉ ክለቦች፤ ሃዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና፣ ወልቂጤ ከተማ እና ሃዲያ ሆሳዕና ተሳታፊ ናቸው። ከከፍተኛ ሊግ ደግሞ ደቡብ ፖሊስ እና አርባ ምንጭ ከተማ ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጅማ አባጅፋር፣ አዳማ ከተማ እና ሰበታ ከተማ በተጋባዥነት እንዲሳተፉ ጥሪ ተደርጎላቸዋል። በከፍተኛ ሊግ ክለቦች መካከል የሚካሄደው ውድድር ደግሞ በቀጣዩ ህዳር ወር የሚካሄድ ይሆናል። በቢጂአይ ኢትዮጵያ ስፖንሰርነት የሚካሄደውን ይህንን ውድድር፤ በሆሳዕና ከተማ ለማድረግ ቢታቀድም ሜዳው በዕድሳት ላይ በመሆኑ ለውጥ ተደርጎበታል። ውድድሩን በተሻለ መልኩ ለማስኬድም ፌዴሬሽኑ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። አዲስ ዘመን ጥቅምት 7/2012 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=20994
b8fd1aeab0da9b2f55ee2a4fd8a691d7
fbb9d925adebcd36b51f6389a0bc0d5a
ጅት ኩን ዶ- የገሃዱ ዓለም ፍልሚያ
 ተወዳጅ ከሆኑ የፍልሚያ ስፖርቶች መካከል ጅት ኩን ዶ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ በኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተለያዩ የፍልሚያ ስፖርቶች በርካታ ተከታዮችን በተለይም ወጣቶችን ከማፍራት አልፈው በዓለም አቀፍና አገር አቀፍ ደረጃ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ወርልድ ቴኳንዶና ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ በዚህ ረገድ ረጅም ርቀት የተጓዙ የፍልሚያ ስፖርቶች ሆነው ይገኛሉ፡፡ በፍልስፍና እንዲሁም በእንቅስቃሴ ደረጃ የተለየና የገሃዱ ዓለም ፍልሚያን መሬት ማውረድ የቻለው ጅት ኩን ዶ በዝነኛው የማርሻል አርት ንጉስና ተዋናይ ብሩስ ሊ እንደተፈለሰፈ ይነገራል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ እንደሌሎቹ የፍልሚያ ስፖርቶች በኢትዮጵያ በስፋት ሲዘወተርና ሲወራለት አይታይም፡፡ ማስተር ኤርሚያስ ገሰሰ ጅት ኩን ዶ ከሌሎች የማርሻል አርት እንቅስቃሴዎች የሚለየው በሳይንሳዊ ፍልስፍናው መሆኑን ይናገራል፡፡ ጅት ኩን ዶ በገሃዱ ዓለም ፍልሚያ ላይ እንደሚያተኩር የሚያብራራው ማስተር ኤርሚያስ፤ ሰዎች ራሳቸውን እንዲሆኑና ራሳቸውን እንዲገልፁ ያስችላቸዋል ይላል፡፡ በስፖርቱ ከሃያ አምስት ዓመታት በላይ ያሳለፈው ማስተር ኤርሚያስ ገርጂና መገናኛ አካባቢ በሁለት ቅርንጫፎች በከፈተው የጅት ኩን ዶ ስፖርት ክለብ በርካታ ወጣቶችን እያፈራ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ከሁለት መቶ በላይ ወጣቶችን እያሰለጠነ ይገኛል። ጅት ኩን ዶ እንደሌሎች የፍልሚያ ስፖርቶች በአገራችን እንዳልተሰራበት ይናገራል፡፡ በስፖርቱ ሙያተኞች ቢኖሩም ፍላጎት ከማጣትም ሊሆን ይችላል በሌሎች መሰናክሎች በአገራችን ስፖርቱን ለማስፋፋት ሲሰሩበት አይስተዋልም፡፡ ጥቂት እንደ ማስተር ኤርሚያስ ያሉ ባለሙያዎች ግን ስፖርቱን ለማስፋፋት ጠንክረው እየሰሩ መሆኑን መካድ አይቻልም፡፡ ጅት ኩን ዶ እንደሌሎቹ የማርሻል አርት ስፖርቶች ሁሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያንቀሳቅሰው ፌዴሬሽን አለው፡፡ የዚህ ስፖርት መታሰቢያነቱ የማርሻል አርት ንጉሱ ቻይናዊው ብሩስ ሊ መሆኑን ማስተር ኤርሚያስ ይናገራል፡፡ በዚህ እንቅስቃሴ ዋናው ትምህርት ፍልሚያ ላይ የሚያተኩር ሲሆን ሰዎች የሚመዘኑትም በፍልሚያ ነው፡፡ሰዎች ምን ያህል ተጋጣሚያቸውን ማጥቃት ይችላሉ፣ ምን ያህልስ ራሳቸውን መከላከል ይችላሉ? የስፖርቱ ዋና መመዘኛ መሆኑን ማስተር ኤርሚያስ ያብራራል፡፡ በዚህ ስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ የነጠላ ወይም አንድ ለአንድ ፍልሚያ፣ ሁለትና ሦስት ለአንድ ፍልሚያ እንዲሁም የቡድን ፍልሚያ የሚታወቁ ሲሆን እንቅስቃሴዎች በባዶ እጅ፣በመሳሪያና ሌሎችም በገሃዱ ዓለም ያሉ ፍልሚያዎችን ያካተተ ነው፡፡ ፍልስፍናውም በጥልቀት የሚሰራው እዚሁ ላይ ነው፡፡ በአገራችን ጅት ኩን ዶ በፌዴሬሽን ደረጃ በጥምር ማርሻል አርት ፌዴሬሽኖች ውስጥ ተካቶ ውድድሮችንም እያካሄደ ይገኛል፡፡ ጅት ኩን ዶ በአገራችን ከጥምር ማርሻል አርት ፌዴሬሽን ተነጥሎ ራሱን ችሎ ለመቋቋም የሰዎች አለማግባባትና የአሰልጣኞች አለመትጋትና የሚጠየቁ መስፈርቶች ውስብስብ መሆን እንቅፋት እንደሆነ ማስተር ኤርሚያስ ያስረዳል፡፡ ጅት ኩን ዶ ራሱን ችሎ በፌዴሬሽን ደረጃ ለመውጣት በተለይም የሚጠየቀው መስፈርት ከባድ መሆኑን ይናገራል፡፡ በአንድ ክፍለ ከተማ ሦስትና ከዚያ በላይ ክለቦችን የሚጠይቅ መስፈርት ከባለሙያ እጥረት ጋር ትልቁ ችግር መሆኑንም ያስቀምጣል፡፡ የስፖርቱ ባህሪ በራሱ አስቸጋሪና ውስጡ መቆየትን የሚጠይቅ መሆኑን የሚያስቀምጠው ማስተር ኤርሚያስ የኑሮ ውጣውረድና ሌሎችም ፈተናዎች ወጣቱን በሚፈለገው መጠን በስፖርቱ እንዲያልፍ አላስቻለውም ባይ ነው፡፡ ይህም ስፖርቱን እንዳይስፋፋ አድርጎታል፡፡ ወርልድ ቴኳንዶን በመሳሰሉ ስፖርቶች በርካታ ወጣቶች በዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ውድድሮች አገራቸውን ወክለው ትልቅ ውጤት ከማስመዝገብ ባሻገር ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን መጥቀም እየቻሉ ነው፡፡ ጅት ኩን ዶ ለሚያዘወትሩት ወጣቶች እንደ ወርልድ ቴኳንዶ ሁሉ አገርን በመወከልና ጥቅም በማግኘት ረገድ ያለውን ተስፋ ማስተር ኤርሚያስ ሲናገሩ ‹‹በፊት ለፊት የሚታይ ነገር የለም፣ነገር ግን የእኛ ጥረት ይሄን ይለውጠዋል፣ አሁን በአገራችን ጥሩ መነሳሳት አለ፤በተለይ በከተማችንና በክፍለ ከተሞች ደረጃ በስፖርቱ ተነሳሽነት አለ፤ ማንኛውንም ስፖርት ለማስፋፋት ባለሙያዎች እየተጠሩና እያወያዩ ነው፣ ይሄን ማሳደግና በፌዴሬሽን ደረጃ ራሱን እንዲችል ማድረግ ከተቻለ ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችንም መፍጠር ይቻላል፣ይህም ወጣቶች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል›› በማለት ስፖርቱ ያለውን ተስፋ ያብራራል፡፡ ኤርሚያስ ገሰሰ ጂምና ማርሻል አርት ማዕከል ወጣቶችን በጅት ኩን ዶ እንቅስቃሴ ከማብቃት ጎንለጎን የበጎ አድራጎት ስራዎችን እንደሚሰራም ማዕከላቱ በሚገኙበት አካባቢ ይታወቃል፡፡ የበጎ አድራጎት ስራ ከማርሻል አርት ስፖርት ጋር አብሮ እንደሚሄድ የሚናገረው ማስተር ኤርሚያስ፤ ወጣቶች ማርሻል አርትን ሲማሩ የስነምግባር ትምህርትም አብሮ እንደሚሰጣቸው ያብራራል፡፡ ይህ የስነ ምግባር ትምህርት መገለጫው በጎ ተግባር ነው፡፡ 1995 ዓ.ም አካባቢ የተማሪ ቤተሰቦች፣በጎ ፍቃደኞችና ሌሎችም በጋራ ሆነው የስፖርቱን እንቅስቃሴ ሲጀምሩ ገንዘብ በማዋጣት ጎዳና ላይ ያሉ ወገኖችን በምግብ፣በአልባሳት ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር በዘላቂነት በማቋቋም መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እየተደረገ ይገኛል፡፡ የበጎ አድራጎት ስራውን ከስፖርቱ ባሻገር ለማስፋት በቅርቡ ‹‹ጳጉሜን 5 የበጎ አድራጎት ድርጅት›› በሚል ስያሜ በማሳደግ እውቅና አግኝቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በየዓመቱም የትንሳዔን በዓል ምክንያት በማድረግ በጎዳና ላይ ያሉ ወገኖችን የመመገብ፣አልባሳትንና ገንዘብ የመስጠት መርሃግብሮችን ያካሂዳል፡፡ መማር የሚችሉ እንዲማሩ፣መስራት የሚችሉ እንዲሰሩ ማድረግም አንዱ ተግባር ነው፡፡ በዚህም የበርካታ ወጣቶችን ሕይወት መለወጥ ተችሏል፡፡አዲስ ዘመን ጥቅምት 3/2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=20759
987f395fb07957dc700562f7aa6eb658
6d84cfd7c86d1084995b22e46a54eca8
የኮርፖሬሽኑ ተምሳሌታዊ የስፖርት ፖሊሲ ትግበራ
በ1990 ዓ.ም. በአገር አቀፍ ደረጃ የወጣው የስፖርት ፖሊሲ ሕዝቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበትና በሚሰራበት አካባቢ ስፖርት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባው ይደነግጋል። ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበትና በሚሠራበት አካባቢ በስፖርት እንቅስቃሴ ተሳታፊ የሚሆንበት መንገድ መመቻቸት እንዳለበት ያስቀምጣል። ከመንግሥት ተቋማት እስከ ታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል በየደረጃው ኅብረተሰቡ ለሚሳተፍባቸው መድረኮች ትኩረት በማድረግ ልሂቃን (ኤሊቶች) የሚፈጠሩበት ዕድል እንዳለም ፖሊስው ያመለክታል። በሌላ በኩል አምራች ዜጋ ለመፍጠር፣ የኅብረተሰቡ ማኅበራዊ ግንኙነት የሚዳብርበት፣ ከዚያም ሲያልፍ ዜጎች ጤንነታቸውን ለመጠበቅና ለመዝናናት እንዲሁም አካላቸውን ለማጎልበትና አዕምሯዋቸውን ለማበልጸግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ታምኖበታል። የስፖርት ፖሊሲውን መሰረት በማድረግ የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በማስፋት ረገድ እየተሄደበት ያለው መንገድ አጥጋቢ አለመሆኑ ተደጋግሞ ይነሳል። በመንግስትም ሆነ በህብረተሰቡ በኩል እንደሚነሳው «ሕዝቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበትና በሚሰራበት አካባቢ የስፖርት እንቅስቃሴ ማድረግ አለበት»በሚል በፖሊሲ ደረጃ ቢቀመጥም ወደ ተግባር ከመለወጥ አንጻር ከፍተኛ ክፍተት መኖሩ ይታመናል። በተለይ በመንግስትና በግል ተቋማት ህብረተሰቡ በሚሰራበት ቦታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ እድል በመፍጠር ረገድ የፍላጎትም ሆነ የግንዛቤ ክፍተቶች እንዳሉ በስፖርቱ አዋቂዎች በኩል ይነገራል። በተቋማት የስፖርቱን ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳን በመረዳት ስፖርታዊ ክንውኖችን የማዘጋጀት ባህሉ በእጅጉ አናሳ መሆኑም አብሮ ይነሳል። መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በኩል የስፖርቱን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በመረዳት የስፖርት ፌስቲቫል የማዘጋጀት ልምድ ባለቤት የሆኑ ተቋማት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ከእነዚህ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል። የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫሉ ዘንድሮ ለ5ኛ ጊዜ ከመስከረም 26 ጀምሮ ለአስር ቀናት ያክል «የኋላውን እያደስን የወደፊቱን ለመገንባት እንተጋለን »በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል። የኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫል በ2002 ዓ.ም እንደተጀመረ መረጃዎች ያመላከታሉ ። ኮርፖሬሽኑ በሚያከናውነው የስፖርት ፌስቲቫል፤ አገር አቀፍ የስፖርት ፖሊሲውን ተግባራዊ ከማድረግ ባሻገር በሰራተኞች መካከል መቀራረብን እንደሚፈጥር ታምኖበታል። የስፖርት ፌስቲቫሉ ጤናው የተጠበቀና አምራች ዜጋን በማፍራት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ማሳያ መሆኑም ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫል አስተባባሪ አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጥንፉ ሙጬ፤ የስፖርት ፌስቲቫሉ በአገር አቀፍ ደረጃ የወጣውን የስፖርት ፖሊሲ መሰረት በማድረግ የተጀመረ መሆኑን ይናገራሉ። ህዝቡ በሚኖርበትና በሚሰራበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ማጉላት እንደሚችል መሰረት ባደረገ መልኩ ተቋሙ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ይገልጻሉ። እንደ አቶ ጥንፍ ገለጻ፣ ስፖርት በተለይ ደግሞ በሰራተኞች መካከል እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ፣ ጤናው የተጠበቀና አምራች ዜጋን ለማፍራት እንዲቻል፣ የሰራተኞችን አንድነት ለማጠናከር ፋይዳው ግዙፍ መሆኑን ያብራራሉ። በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫሉን እነዚህን ውጤቶች መሰረት በማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እንደጀመረ ይናገራሉ። «ፌስቲቫሉ በየሁለት ዓመቱ ቢደረግ የበለጠ ዝግጅት ተደርጎ በጠንካራና ባማረ ሁኔታ ማከናወን ይቻላል »በሚል አስተዳደሩ ወስኖ በየሁለት ዓመቱ ሊካሄድ እንደቻለም ያስታውሳሉ። የኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት በዚህ መልኩ በመቋቋም ባለፉት አስር ዓመታትን መጓዝ ችሏል። በስፖርት ክንውኑ ተቋሙ ውጤታማ መሆን ችሏል? ስንል ጥያቄ ሰንዝረናል። አቶ ጥንፍ ባለፉት አስር ዓመታት በነበረው ስፖርታዊ ክንዋኔ ተቋሙ ውጤታማ መሆኑን ይገልጻሉ። በመጀመሪያ ደረጃ አመራሩና ሰራተኛው መልካም የሆነ ግንኙነት እንዲፈጥሩ አድርጓል። እያደረገም ይገኛል። በአካልም፣ በአዕምሮም የበለፀገ ሰራተኛና አመራር እንዲኖር አስችሏል። ጤናማ ሰራተኛ በመፍጠር ረገድ ውጤት ማምጣት ተችሏል። መታወቅ ያለበት ያለ ጤናማ ሰራተኛ የኮንስትራክሽን ስራ የሚታሰብ እንዳልሆነም ያብራራሉ። የስፖርት ፌስቲቫሉ ሠራተኛውም ሆነ አመራሩን የበለጠ የሚያቀራርብ፣ ሠራተኛው ትርፍ ጊዜውን አዕምሮውንና አካላዊ ብቃቱን የሚያዳብርበት፣ ለተቋሙ ያለውን ወገናዊነት የሚያሳይበት፣ በሌሎች ፕሮጀክቶች ከሚገኙ ሠራተኞች ጋር ለመቀራረብና ለመተዋወቅ መንገድ እየከፈተ እንደሚገኝ ይገልጻሉ። እንደ አቶ ጥንፍ ማብራሪያ፤ የዘንድሮ መድረክ ከእስከ ዛሬው ለየት የሚያደርገው የተሳታፊነቱን ኮታ ለአመራሩ አንድ ሶስተኛውን በመስጠት ዋና ሥራ አስፈጻሚውን ሳይቀር ተሳታፊ ማድረጉ ነው። ስፖርት ፌስቲቫሉ ለአመራሩና ለሰራተኛው እኩል እድል ከመስጠት ባሻገር፤ በሁለቱ አካላት መካከል መቀራረብ እንዲፈጠርና የበለጠ ቀረቤታን መፍጠር እንዲያስችል ነው። ይህን በተግባርም ለመመልከት ተችሏል። የዘንድሮው ውድድር ሴቶችን የበለጠ ተሳታፊ እንዲሆኑ አድርጓል። በመድረኩ ያለፉት ዓመታት ጉዞ ሴቶች ቡድን አልነበራቸውም፤ ዘንድሮ ሁለት ቡድኖች ተቋቁመው በመረብ ኳስና በጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርቶች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ተደርጓል። «የዘንድሮው ፌስቲቫል ልዩ ገጽታው የለውጥ አስተሳሰቦችን ለማስረጽ ጥረት መደረጉ ነው። በውድድሩ ያሉትን ቡድኖች ስያሜን በዚህ ሁኔታ እንዲቃኙ የተደረገ ሲሆን ስያሜዎቹም አሸናፊ፣ ብቁ፣ ታዋቂ፣ ድንቅ፣ ባለራዕይ እና ተስፋ በሚል እንዲሰየሙ ተደርጓል›› ያሉት አስተባባሪው ከዚህ በተጨማሪም ቀደም ሲል ዘርፎች በቡድን ተደራጅተው እርስ በዕርስ የሚያደርጉት ውድድር እንደነበር ተናግረዋል። አደረጃጀቱ እንደ ኮርፖሬሽን ውህደት ባለማምጣቱ አዲስ አደረጃጀት በመፍጠር ወድድሩ እየተካሄደ ሲሆን፤ በመድረኩ የበለጠ መቀራረብና ተቋማዊ ስሜት መፍጠር እንደተቻለ በውድድሩ የአምስትና ስድስት ቀናት ቆይታ ወቅት ለመታዘብ ተችሏል። የስፖርት ፌስቲቫሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቋማዊ ፋይዳውን እያሳደገ መምጣቱን የ5ኛው የቤተሰብ ስፖርት ውድድር እያሳየም ይገኛል። አቶ ጥንፍ ኮርፖሬሽኑ ግዙፍና በርካታ ፕሮጀክቶች ያቀፈ እንደመሆኑ በስፖርት ፌስቲቫሉ ሁሉም ፕሮጀክቶች ተሳታፊ እንዲሆኑ በመስራት የስፖርቱን ግዙፍ ፋይዳ በተቋሙ ምሉእ እንዲሆን ለማድረግ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም አስቀምጠዋል። በ5ኛው የኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት ሲሳተፍ ያገኘናቸው በኮርፖሬሽኑ የፋሲሊቲ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ዜናው ደነቀው በበኩላቸው፤ የስፖርት ክንውኑን እንደ ኮርፖሬሽኑ ሁሉ ሌሎች ተቋማት ተግባራዊ ማድረግ ቢችሉ ያለውን ፋይዳ ይናገራሉ። «በእኛ ተቋም ያለውን ተሞክሮ በሌሎች የመንግስትና የግል መስሪያ ቤቶች ተግባራዊ ማድረግ ቢቻል፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ተጠቃሚ መሆን ይቻላል። ከስፖርቱ የሚገኘውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ማግኘት ይቻላል። በተጨማሪም ኢሊት ስፖርተኞች የሚፈሩበትን አጋጣሚ በማስፋት ረገድ የራሱ የሆነ ድርሻ ይኖረዋል። የአገራችንን ስፖርት በማሳደግ ረገድም የመንግስት ተቋማት ድርሻቸውን እንዲወጡ አጋጣሚውን መፍጠር ይቻላል» ሲል ያብራራል። በኮርፖሬሽኑ የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ከአሰልጣኝነት እስከ ዳኝነት የተሻገረ ተሳትፎን ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲያደርጉ እንደነበረ የገለፁልን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሰራተኛ የሆኑት አቶ አለማየሁ ገብሬ፤ የኮርፖሬሽኑ ተሞክሮን ሌሎች ተቋማት መውሰድ ቢችሉ ያለውን ነጥብ በማሳት ተመሳሳይ ሃሳብ ይጋራሉ። የቤተሰብ ስፖርቱን ከመጠንሰስ እና ቀጣይነት እንዲኖረው ከማድረግ አካያ በተቋሙ የነበሩና ያሉ አመራሮች ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸውም ይናገራሉ። የኮርፖሬሽኑ አመራሮች የስፖርት ፌስቲቫሉ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ከማደርግ አኳያ ያሳዩት ቁርጠኝነት በተለይ ደግሞ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ትልቅ ስራን መስራታቸውን ያስረዳሉ። አቶ አለማየሁ ዋና ስራ አስፈፃሚው ስፖርታዊ ክንውኑ ቀጣይነት ኖሮት በጠንካራ መስመር እንዲጓዝ ከመስራት ባሻገር፤ በውድድሩ ተጫዋች በመሆን የስፖርቱ ተሳታፊ መሆናቸው የሚያስመሰግናቸው መሆኑን ይገለጻሉ። ስፖርቱ ትኩረት እንዲያገኝ ከማድረግ አኳያም አመራሩ ያሳየው ቁርጠኝነት በሌሎች ተቋማት እንደ አርዓያ ሊወስዱት ይገባል ባይናቸው። ኮርፖሬሽኑም በየሁለት ዓመቱ ይህ የስፖርት ባህል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ እንደሚገባው ያስቀምጣሉ። በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የቤተሰብ ስፖርት ፌስቲቫል ተሞክሮ በሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት መውሰድ ቢቻል ዘርፈ ብዙ ውጤቶች እንደ አገር ማትረፍ እንደሚቻል መመስከር ይቻላል። ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በህብረተሰቡ ዘንድ ትኩረት እንዲሰጠው ፖሊሲ ከመቅረጽ ባሻገር ተግባራዊ እንዲሆን እንደ ኮርፖሬሽኑ ሌሎች ተቋማት መስራት አለባቸው።አዲስ ዘመን  ረቡዕ ጥቅምት 5/2012ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=20928
fd5767e1c3d1fc5e23020ee0ddb77de4
7950094d223266e4116e23d57df4ffa9
የኦሊምፒክ ማራቶን የሚካሄድበት ከተማ ሊቀየር ነው
በቅርቡ በተጠናቀቀው የዶሃ ዓለም ቻምፒዮና በሴቶች በተካሄደው የማራቶን ውድድር ከተሳተፉት 68 አትሌቶች መካከል 28ቱ ውድድሩን ማቋረጣቸው የሚታወስ ነው። ለዚህ ምክንያት የሆነውም በዶሃ የነበረው ከፍተኛ ሙቀትና ወበቅ መሆኑ ተነግሯል። ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ የሚቀረው የቶኪዮ ኦሊምፒክም ከፍተኛ ሙቀት እክል ሊሆንበት እንደሚችል ስጋት ተፈጥሯል፡፡ ይህንን ተከትሎም ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የማራቶን እና የእርምጃ ውድድር ቀደም ብሎ ሊካሄድበት ከታሰበው ከተማ ለውጥ ለማድረግ ማሰቡን አስታውቋል። በከባድ ሙቀት ምክንያት በውድድሩ ላይ የሚደርሰውን ተጽእኖ ለመቀነስ ሲባልም በተሻለ መጠን ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ያለው አካባቢ አስፈልጓል። በመሆኑም ቀድሞ ከታሰበው የኦሊምፒኩ ዋና መዳረሻ ቶኪዮ ወደ አገሪቷ ሰሜናዊ ክፍል ለማሸጋገር መታሰቡን የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በድረ-ገጹ አስነብቧል። በ800ኪሎ ሜትር ርቀት በሆካኢዶ ተራራማ አካባቢዎች የሚገኘው ሳፖሮ የተባለው ይህ ስፍራ ውድድሩ በሚካሄድበት ወቅት የአየር ሁኔታው በተሻለ መጠን የሚቀዘቅዝ መሆኑ አትሌቶችን እንደሚረዳቸው ይታሰባል። ስፍራው እ.አ.አ 1972 የክረምት ኦሊምፒክ የተካሄደበትም ነው። የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ፣ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲሁም የማህበሩ የጤና ባለሙያዎችና አማካሪዎች እንዳስታወቁት ኦሊምፒኩ የሚካሄደው በበጋው ወቅት በመሆኑ የቶኪዮ ከተማ የሙቀት መጠን በከፍተኛ መጠን ይጨምራል። ይህም በአትሌቶች ላይ እንዲሁም በውድድሩ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ እንደማይቀር አጽንኦት መስጠታቸውን ተከትሎ የቦታ ለውጥ ለማድረግ መታቀዱ ታውቋል፡፡ ሙቀቱ ከማራቶን እና እርምጃ ውድድሮች ባሻገር የ5ሺ ሜትር እና 10ሺ ሜትር ውድድሮች እንደተለመደው በቀኑ ክፍለ ጊዜ ሳይሆን ሌሊት ላይ ለማካሄድ ሊያስገድድ እንደሚችልም ተነግሯል፡፡ ከረጃጅም ርቀት አትሌቲክስ ባሻገር ላሉ ሌሎች ስፖርቶችም በተመሳሳይ ሙቀቱ አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል የተለያዩ እገዛዎች እንደሚደረጉም ተጠቁሟል። ይህም መጠለያዎችን በማበራከት እንዲሁም የውሃ ማቀዝቀዣ፣ ከፍተኛ የውሃ አቅርቦት እንዲኖርና አትሌቶች ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት በመረዳት ነው። ከዚህ ባሻገር በተያዘው የፈረንጆቹ ወር መጨረሻ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በውድድሩ ስፍራ ለውጥ እንዲሁም በኦሊምፒኩ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ተይዟል። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባች ባደረጉት ገለጻም «የአትሌቶች ጤና እና ደህንነት ቀዳሚው ጉዳይ ነው። አትሌቶችን ከጉዳት ለመታደግም በርካታ ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ ለውጥ ከማድረግ ላይ ደርሰናል፤ ይህም ምን ያህል ትኩረት እንደምንሰጥ የሚያሳይ ነው። ኦሊምፒክ ማለት አትሌቶች በህይወት ዘመናቸው የሚያሳኩት ሁነት ነው፤ በመሆኑም ብቃታቸውን ማሳየት አለባቸው። ለዚህ ሥራም እየተባበረን ያለውን ማህበር ማመስገን ይገባል» ብለዋል። የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፕሬዚዳንት ሰባስቲያን ኮ በበኩላቸው «ከዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና ከ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ አዘጋጆች ጋር በቅርበት ስንሰራ ቆይተናል። አትሌቶች ብቃታቸውን ያሳዩ ዘንድ አስፈላጊውን ሁሉ ልናመቻችላቸው ይገባል፤ በመሆኑም ለማራቶን እና እርምጃ ተወዳዳሪዎች የሚሻል የአየር ሁኔታ ወዳለው ስፍራ ለውጥ ማድረግ አስፈልጓል» ሲሉ አብራርተዋል። አዲስ ዘመን ጥቅምት 7/2012 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=20999
d595fab0de801f045b7f59e5013432ff
ef65a2e4a53ad1e23e40e84560b36c18
ኢትዮጵያዊያን ለ2 ዓመታት የምርጥ አትሌቶች ሽልማት አልታጩም
የጽናት ምልክቱና በ10ሺ ሜትር ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ኢትዮጵያን ወክሎ የዓለም ምርጡ አትሌት ሲሰኝ የመጀመሪያው ነው። በአቴንሱ የዓለም ቻምፒዮና 10ሺ ሜትር እንዲሁም በፈረንሳይ የቤት ውስጥ ቻምፒዮና 3ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ በማጥለቅ አገሩን ባስጠራ ማግስት፣ የጎልደን ሊጉ አሸናፊም በሆነበት ዓመት እአአ 1998 የዓመቱ የዓለም ምርጥ አትሌት በሚል ለመሸለም በቃ። በኃይሌ እግር የተተካው ቀነኒሳ በቀለ ደግሞ ይህንን ክብር በማግኘት ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ለመሰኘት ቻለ። የ5ሺ፣ 10ሺ እና የአገር አቋራጭ ንጉሱ በተከታታይ እአአ በ2004 እና 2005 በወንዶች የዓለም ምርጥ አትሌት በመሆንም ታሪካዊ አትሌትነቱን አስመስክሯል። በወንዶች በኩል ከቀነኒሳ ቀጥሎ ይህንን ክብር ያገኘ ኢትዮጵያዊ አትሌት ባይኖርም በሴቶች በኩል ግን እስከ ቅርብ ዓመታት ለማሸነፍ የቻሉ አትሌቶች ታይተዋል። አትሌት መሰረት ደፋር እአአ በ2007 ይህንን ሽልማት ያሳካች አትሌት ናት። ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ባይቆጠርም እአአ በ2015 ገንዘቤ ዲባባ ሁለተኛውን ክብር እንዲሁም በረጅም ርቀት የዓለም እና የኦሊምፒክ ቻምፒዮናዋ አልማዝ አያና በ2016 የዓመቱ ምርጥ አትሌት በመባል ለመሸለም በቅተዋል። በዓለም ላይ በተለይ በረጅም ርቀት አትሌቲክስ ተጽእኖ ፈጣሪ ከሚባሉ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያናት። በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ዕውቅና በተሰጣቸው ውድድሮች ላይ በግላቸው ከሚሳተፉት አትሌቶች ባሻገር በዳይመንድ ሊግ፣ ዓለም ቻምፒዮና አንዲሁም በኦሊምፒክ መድረክም ሜዳሊያ ያጠለቁ የዝነኛ አትሌቶች ምድርም ናት፤ ኢትዮጵያ። አሸንፎ ሜዳሊያውን ማጥለቅ ብቻም ሳይሆን ሰዓት በማሻሻልና የዓለም ክብረወሰንን በመስበር ጭምር በርካታ ስኬታማ አትሌቶችን ለዓለም አበርክታለች። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም ምርጥ አትሌቶች ሽልማት ማሸነፍ ባይችሉ እንኳን ከመጀመሪያዎቹ አስር እጩዎች በሁለቱም ፆታ መካተታቸው ብርቅ አልነበረም። ባለፈው ዓመትና ዘንድሮ ግን በተከታታይ ከአስሩ እጩዎች ዝርዝር ውስጥ ሳይካተቱ ቀርተዋል። የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለሙያዎች እንዲሁም ከሁሉም አህጉራት በተወጣጡ ተወካዮች በሁለቱም ጾታ በዓመቱ ጥሩ ብቃት ያሳዩ 20 አትሌቶች ቀርበዋል። ዕጩዎቹም በዳይመንድ ሊግ፣ በዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና፣ በዶሃው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና እንዲሁም ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ላይ በሩጫ፣ ዝላይ እና ውርወራ የተሻለ ብቃት ያሳዩ ሲሆኑ ከነዚህ መካከል ለተከታታይ ሁለት ዓመታት አንድም ኢትዮጵያዊ አትሌት ሳይካተት መቅረቱ አስገራሚ ሆኗል። ዘንድሮ እጩ ሆነው ከቀረቡት አትሌቶች መካከል አሜሪካ በርካታ አትሌቶችን በማስመረጥ ቀዳሚዋ አገር ሆናለች። በዓመቱ ከተካፈለባቸው አምስት የ800 ሜትር ውድድሮች አራቱን ያሸነፈው ዶናቫን ብራዜር በእጩነት ከቀረቡት መካከል ይገኛል። አሜሪካዊው አትሌት በቻምፒዮናው ላይ በ800 ሜትር 1:42.34 የዓለም ክብረወሰን የሆነ ሰዓት ከማስመዝገቡም ባሻገር የዳይመንድ ሊጉ አሸናፊ ነው። በዓመቱ በ100 ሜትር ውድድር ተዕእኖ ፈጣሪ የነበረውና የዶሃ ርቀቱን 9 ሰከንድ ከ76 ማይክሮ የገባው ክርስቲያን ኮለመንም ሌላኛው እጩ ነው። የከፍታ ዝላይ አሸናፊው ሳም ኬንድሪክስ፣ የ200 ሜትር ሯጩ ናህ ላይለስ እንዲሁም የርዝመት ዘላዩ ክርስቲያን ቴይለር በእጩነት የቀረቡ አሜሪካዊያን አትሌቶች ናቸው። ባለፈው ሳምንት ማራቶንን ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለት ሰዓት በታች በመግባት ታሪክ ያጻፈው ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌም በእጩነቱ ተካቷል። አትሌቱ ዕውቅና የሌለውን የስፖርት ትጥቅ አምራቹን ኩባንያ ናይኪ ፕሮጀክት የሆነውን ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች የማጠናቀቅ ህልም ከማሳካቱም ባለፈ በለንደን ማራቶን 2:02:37 በመግባት የራሱን ፈጣን ሰዓት በማሻሻል የዓለም ክብረወሰኑን አለማስነጠቁ የሚታወቅ ነው። የአገሩ ልጅ የሆነው ቲሞዚ ቺሩዪት ሌላኛው እጩ ሲሆን፤ በ1ሺ500ሜትር የዳይመንድ ሊግ እንዲሁም የዓለም ቻምፒዮን ነው። በአውሩስ በተካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮን የሆነው ኡጋንዳዊው ጆሹዋ ቼፕቴጊም ከእጩዎቹ ተካቷል። አትሌቱ በ10ሺ ሜትር ቀዳሚ የሆነውን 26:48.36 ሰዓት ሲያስመዘግብ በ500ሜትር የዳይመንድ ሊጉ ቻምፒዮን ነው። የ400ሜትር አትሌቱ ባህሬናዊ ስቲቭ ጋርድነር፣ በዲስከስ ውርወራ የዓለም ቻምፒዮኑ ስዊድናዊ ዳንኤል ስታል እንዲሁም ኖርዌያዊው ካርስቴን ዋርሆልም በምርጫው የተካተቱ ሌሎች እጩዎች ናቸው። ለምርጫው የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ባለሙያዎች 50 በመቶ የሚሆነውን ድምጽ የሚሰጡ ሲሆን 25 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ ሌላው ህዝብ በድረገጾች ድምጹን የሚሰጥ ይሆናል። እጩዎቹን አሸናፊ ለማድረግም በየትኛውም የህዝብ መገናኛ እንዲሁም የማህበራዊ ገጾች ማስተዋወቅ የሚረዳቸው ሲሆን፤ ከወር በኋላ የመጨረሻዎቹ አምስት እጩዎች ይታወቃሉ። አሸናፊው እትሌትም በሞናኮ በሚኖረው ስነስርዓት ላይ ይፋ እንደሚደረግ ይታወቃል። አዲስ ዘመን  ረቡዕ ጥቅምት 5/2012ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=20932
02d6cc6f9be1d90ac9e7eba434e84a3a
52736c8a030923e40abc25f19496c3e6
“ዋናው ነገር የሀገር ጉዳይ ነው፤ እኛ ብንሞትም ብንኖርም ለሀገር ስለሆነ ችግር የለውም፤ ጓደኞቻችን ግን ነፃ አውጥተውናል” – ከታጋቾች መካከል አንዱ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን የመከላከያ ሠራዊት 20ኛ ክፍለጦር አዛዥ
በጋዜጣው ሪፖርተርብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን፣ በጁንታው ቡድን ታግተው ከቆዩ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች መካከል አንዱ ናቸው። ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩ፣ በወቅቱ የጁንታው ታጣቂዎች የሠራዊቱ አባላት ትጥቃቸውን እንዲፈቱ መልዕክት በግዳጅ እንዲያስተላልፍ ሲደረግ “እኔ ትጥቄን ፈትቻለሁ እናንተም ፍቱ፤ እኔን ግን ከዚህ በኋላ አታገኙኝም” ብለው ውስጠ ወይራ መልዕክት አስተላለፉ። አክለውም በኦሮምኛ ለሠራዊቱ ትጥቅ እንዳይፈታ የሚያግዝ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ያስታውሳሉ። መከላከያ ሠራዊቱም ጥቃቱ ከተፈፀመ ማግስት ጀምሮ በመከላከልና የሕግ ማስከበር እርምጃ በመፈፀም ህይወት የማዳን እና አጥፊዎቹን የመቅጣት እርምጃውን ገፋበት። በርካታ የሠራዊቱ አባላት እና አመራሮችም ከብዙ እንግልት በኋላ ከጁንታው እጅ ነፃ ወጡ። ከታጋቾች መካከል አንዱ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ኑሩም በዚህ ወቅት ነው ነፃ የወጡት፡፡ እናም ነፃ ከወጡ በኋላ ሲቃ በተሞላበት ንግግራቸው የነበረውን ሁኔታ አስረድተዋል። “ከሁሉ በፊት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊትም እንኳን ለዚህ ድል አበቃን፤ እኛንም ከአንድ ወር ልፋትና እንግልት በኋላ እንኳን በሰላም አገናኘን። ዋናው ነገር የሀገር ጉዳይ ነው፤ እኛ ብንሞትም ብንኖርም ለሀገር ስለሆነ ችግር የለውም በሚል ተስፋ ቆርጠን ነበር። ጓደኞቻችን ግን ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ ኦፕሬሽናቸውን በመፈፀም ነፃ አውጥተውናል።የተለያዩ ቀናትን ያለምግብ እና ውሃ ሳንጠጣ በርካታ የመሬት ገፆች ላይ ተንገላተናል። በርካታ የሠራዊት አባላትም ይህን እንግልት ተቋቁመን አሁን የደረስንበት ደረጃ በመድረሳችን በታጋቾች እና በራሴ ስም ለመከላከያ ሠራዊትም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ።በአጠቃላይ በሠራዊታችንም ሆነ በህዝባችን ሲከናወን የነበረውን ነገር በተለያየ መንገድ የሰማነው ስለሆነ እኛም ደስ ብሎናል። ለመከላከያ ሠራዊትም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለድል ያበቃችሁን አንድነታችሁን በማጠናከር የቀሩትን ሥራዎችም እንድታጠናቅቁ አደራ ማለት እፈልጋለሁ>> ብለዋል። ለአንድ ወር ከስድስት ቀን በጁንታው ታጣቂዎች ጥቃት ከተፈፀመባቸው በኋላ ታግተው በረሃብና በእንግልት የቆዩት የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች በሠራዊቱ አማካኘነት ነፃ ከወጡ በኋላ ህይወታቸውን ለማትረፍ ለተደረገው ጥንቃቄ የተሞላበት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 4/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37237
8bc7749afc462f0ae290eb4f0d987578
eca8f788162d83578e3a1e7ebe749c82
እንስቶቹ የሠራዊቱ ፈርጦች
ጌትነት ተስፋማርያም ፊታቸው ላይ ሊፒስቲክ፣ ኩል እና የውበት መጠበቂያ ክሬሞች ፈጽሞ አይታዩም። ከዚህ ይልቅ ፊታቸው ላይ የሚታየው የአልበገር ባይነት ወኔ እና ተፈጥሯዊ ውበት ነው። ፀጉራቸውንም ቢሆን እንደወጉ ይሠሩት እንደሆን እንጂ ዛሬም ነገም መተኮስ እና ባማሩ ጌጦች ማስዋብ የሚያስችል ጊዜም ሆነ ዕድሉ የላቸውም። ምክንያቱም ዓላማቸው የሀገር ህልውና ማስከበር እና ወንጀለኞችን ሥርዓት ማስያዝ ነውና፡፡ገደላገደሉን ሲዘሉ፤ ጢሻውን ሲያቋርጡ ነው አብዛኛውን ጊዜያቸውን በግዳጅ ላይ የሚያሳልፉት። ሕብረ- ብሔራዊነትን በአግባቡ በተላበሰው የመከላከያ ሠራዊት ውስጥ የፆታ ልዩነት ሳይገድባቸው በጽናት የቆሙ እንስቶች የሠራዊቱ ብርቱ ክንድ ስለመሆናቸው ደግሞ የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ።ወታደር አስደሳች ታከለ እና ወታደር ታሪኬ ኤርሚያስ የመከላከያ ሠራዊትን የተቀላቀሉት ከሐዲያ እና ጋሞ ዞኖች ነው። ሁለቱም እንስቶች የ20 ዓመት የወጣትነት እድሜ ላይ የሚገኙ የ24ኛ ክፍለጦር አባላት ናቸው። በትግራይ ክልል በተደረገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ አቧራ ለብሰው ኮቾሮ ቀምሰው አፈር ላይም ጋደም ብለው ያሳለፏቸው በርካታ ቀናት መኖራቸውን አጫወቱን እና ታሪካቸውን በይበልጥ ለመስማት ጓጓን። ግርማ ሞገስ ባለው አረማመዷ ታጅባ ታሪኳን ያወጋችን ሴት ወታደር አስደሳች ታከለ፤ የሕግ ማስከበር ዘመቻው ከጅማሮው አንስቶ ላይ መሳተፏን ነገረችን። በተለይ በአከርና በአካባቢው የነበሩ የጁንታው ቡድን ታጣቂዎችን ለይቶ ለሕግ በማቅረብ እና የአካባቢው ኗሪ ሳይጎዳ ግዳጁን ለማጠናቀቅ ጥረት መደረጉን ታስታውሳለች። በወቅቱ ግን ከበአከር አለፍ ብላ ባለች አንድ ተራራማ ቦታ ላይ ስትደርስ ባጋጠማት የመንሸራተት አደጋ ወድቃ ቀኝ እጇ ላይ ስብራት አጋጠማት።አደጋው የማያላውስ እና ጥዝጣዜውም ከባድ ህመም ያለው ቢሆንም ግን “መሣሪያዬን ለማንም አልሰጥም” ብላ የሚመጣውን ሃይል ለመመከት ዝግጅት ማድረጓ አልቀረም። በመጨረሻም አካባቢውን መከላከያ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠረው እርሷም ለህክምና ተወሰደች። እስከ ባህር ዳር ከተማ ድረስ ተጉዛ አስፈላጊውን ህክምና ስትከታተል ግን ትጥቄን ስጡኝ በማለት ከአጠገቧ ሳትነጥል ማቆየቷን አትዘነጋውም። ዓላማዋ ቶሎ ተመልሳ የሕግ ማስከበር እርምጃው ላይ ለመሳተፍ እንደነበር ነግራናለች። አሁን ላይ በመልካም ጤንነት ላይ መገኘቷን በማሳወቅ ልቧ እንደፈቀደው ዳግም ወደግዳጅ ለመመለስ ጥያቄ አቅርባለች። በሠራዊቱ ውስጥ ያለው የሴቶች ተሳትፎ የሚያኮራ ነው የምትለው ወታደር አስደሳች፤ 150 ጥይት ታጥቀው ከወንድ እኩል የሚሮጡ እና የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት የሚፈጽሙ አባላት እና አመራሮችም ለሌሎች እንስቶች ሁሉ የጽናት ተምሳሌት መሆናቸውን ትገልፃለች። ወታደር ታሪኬ ኤርሚያስ በበኩሏ “በከተማ አካባቢ መኖርና መመለስ ሃሳቤ አይደለም። ዓላማዬ ሁሉ ለሀገሬ መታገል እና ለእናት ሀገሬ መኖር ነው” ትላለች። በሠራዊቱ ውስጥ ያለውን የሴቶች ተሳትፎ ስትገልጽም “ሴት ነኝ ብሎ ወደኋላ የሚሸሽ የለም። ሴቶች በውጊያ መሳተፍ ብቻ ሳይሆን ሠራዊቱንም በማበረታታት ጭምር ጥንካሬያቸውን አሳይተዋል፤ ሴቶች ከባድ መሣሪያ ጭምር ይዘው ለሀገር ህልውና ለህይወታቸውን ሳይሳሱ ተሰልፈዋል” ብላለች። ለሀገሯ አይደለም ደሟን ማፍሰስ ህይወቷንም ልታጣ የምትችልበት አጋጣሚ እንደሚኖር የምትናገረው ወታደር ታሪኬ እርሷም በአከር አካባቢ በነበረ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ብሽሽቷ አካባቢ በጥይት ተመታ ቆስላለች። በቆሰለችበት አጋጣሚ ደም ፈሷት ህመም ቢበረታባትም ግና ወኔዋ ሁሉ መሣሪያዋን ይዛ ግዳጇን ለመቀጠል እንደነበር አትረሳውም።መከላከያ ሠራዊት የህክምና ባለሙያዎች በአካባቢው የመጀመሪያ ዕርዳታ አድርገውላት ለተጨማሪ ህክምና ወደባህርዳር እና ሌሎች ከተሞች የተወሰደችው ወታደር ታሪኬ፤ ህክምናዋን ስታጠናቅቅ ግን፤ ስለዚህ አሁኑኑ ወደ ዘመቻ ልሂድ” ብላ መነሳቷን ነግራናለች። ይሁንና ኢትዮጵያ በርካታ ልጆች ስላሏት ተጨማሪ ሥራ ሲያስፈልግ እንደምትጠራ ተገልፆላት ዝግጅት በማድረግ ላይ ነች። ሠራዊቱ ውስጥ ያሉ በርካታ እንስቶች ዛሬም በድንበር እና በተለያዩ የግዳጅ አካባቢዎቸ የጁንታው ቡድን አመራሮችን ለመያዝ ደፋ ቀና ይላሉ። የሠራዊቱ ፈርጦች መሆናቸውንም በተግባር አሳይተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 4/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37235
c8c771d956d1b7cce3f72d0651c27cd6
7b22b49984f7288c115f42a7888d63ef
የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓት አምራቾች ወደአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ለመግባት መዘጋጀት አለባቸው ተባለ
ፋንታነሽ ክንዴአዲስ አበባ፡- በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓት አምራችነት የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ አፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ለመግባት መዘጋጀት እንዳለባቸው ተገለፀ፡፡ኤክስፖርትን ማበረታታት ዓላማው ያደረገ የኤክስፖ ንቅናቄ ከትናንት በስቲያ ተካሂዷል፡፡የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ የተገኙት የኢ.ፌዴ.ሪ. ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የውጭ ንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ በቅርቡ ሙሉ በሙሉ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና አባል ሆናለች፡፡በመሆኑም በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓት አምራችነት የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ አፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ለመግባት መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡እንደ አምባሳደር ምስጋናው ገለፃ፤ ኢትዮጵያ ወደ ነፃ ንግድ ቀጣና ስትገባ ውድድሩ ከአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከጎረቤት ብሎም በአፍሪካ ደረጃ ካሉ አምራቾች ጋር ነው፡፡ስለሆነም በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾች አቅማቸውን በአፍሪካ ያሉ ዕድሎችንም ለመጠቀም በሚያስችል ደረጃ ማሳደግ ይኖርባቸዋል፡፡በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶችን እንደምታስገባ ጠቁመው፤ ይህንን በአገር ውስጥ ምርት መተካት ከተቻለ ትልቅ የውጭ ምንዛሬን የሚቀንስ በመሆኑ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በአገር ውስጥ ምርት መተካት ላይ በስፋት መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ ከ8 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶች እንዲገቡ መደረጉን የጠቀሱት አምባሳደር ምስጋናው፤ ይህንን ወጪ ማስቀረት መቻል በራሱ ትልቅ ሥራ በመሆኑ አቅምን አጎልብቶ ለኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶችንና ምርቶችን በማምረት የአፍሪካን ገበያ ለመጠቀም መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡በዚህ ረገድ በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ያሉ ችግሮችን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ማጥናቱን ተናግረው፤ በተለይ ዘርፉን አንቀው የያዙትን ችግሮች ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡በመድረኩ ላይ የውይይት መነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የጎማና ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክተር ኢንጅነር ዮናስ አባተ በበኩላቸው እንደገለፁት፤ በዘርፉ ውስጥ ከፍተኛ ወጪ ከሚወጣባቸው ምርቶችና ግብዓቶች መካከል ማዳበሪያ፣ ጎማና ፕላስቲክ ለመሥራት እንዲሁም ለሳሙናና ቀለም የሚሆኑ ግብዓቶች ይገኙበታል፡፡በዚህ ረገድ ባለፉት አምስት ዓመታት ከውጭ ግብዓቶችና ምርቶችን ለማስገባት በኬሚካል ዘርፍ ከ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር በላይ፣ በኮንስትራክስን ዘርፍ ደግሞ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር በላይ በአጠቃላይ ከ 9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጓል፡፡የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ኢንስቲትዩት የተቋቋመው ደግሞ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት እንደመሆኑ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ እንዲችሉ ለማለማመድ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ይህንንም ተከትሎ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ 20 ሚሊዮን ዶላር የሚሆኑ ምርቶች ወደ ውጭ ሲላኩ ነበር፡፡በአሁኑ ወቅት ባደጉ አገሮች ካሉ ኢንዱስትሪዎች ጋር ሊወዳደሩ የሚችሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ይዘው የመጡ ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን የገለፁት ኢንጅነር ዮናስ፤ ከባጃጅ እስከ ትራክተር ድረስ ያሉ ጎማዎችን በአገር ውስጥ ማምረት መቻሉንም አስረድተዋል፡፡በኬሚካል ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ ለማደግ ጥረት እየተደረገ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ከተፈጥሮ ጋዝ የፔትሮ ኬሚካል ውጤቶችን አገር ውስጥ ለማምረት እየተሠራ እንዳለም ገልፀው፤ ይህም ከአገር ፍጆታ አልፎ በዓመት እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር ያህል የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚያስችል ምርት ወደ ውጭ መላክ እንደሚያስችል ጠቅሰዋል፡፡“ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪዎችን እንፍጠር” በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው ንቅናቄ መድረክ ዘርፉን ለማነቃቃት፣ እስካሁን የተሄደበትን እርቀት ለማየትና ዘርፉ ላይ ያለውን እምቅ አቅም ለመረዳት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 4/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37247
02cd703e1aa8f1f66f59b112ca7c4ad4
92d883d576e5933be2e285b150f7044d
“ሠራዊቱ የታፈኑትን ነፃ ሲያወጣ ጠላትና ወገንን የለየ ምርጥ ኦፕሬሽን አከናውኗል” – ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ፣ የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ
 ጌትነት ተስፋማርያምሽሬ:- “መከላከያ ሠራዊት በጁንታው ታጣቂዎች አማካኝነት የታፈኑትን የሠራዊቱ አመራርና አባላትን ነፃ ሲያወጣ ጠላትና ወገንን የለየ ምርጥ ኦፕሬሽን አከናውኗል” ሲሉ ከታጋቾቹ መካከል አንዱ የነበሩት የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ ተናገሩ። የሰሜን ዕዝ ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ እንደገለፁት፤ መከላከያ ሠራዊቱ ታጋቾችን እና የጁንታውን ታጣቂ ለመለየት የተጠቀመው እርምጃ የሚደነቅ ነው። በዚህም የሠራዊቱ አመራርና አባላትን በማይጎዳ መልኩ ጥንቃቄ የተሞላበት ኦፕሬሽን በተሳካ ሁኔታ ተፈፅሟል። “መከላከያ ሠራዊታችን እኛ የታፈንነውን አመራርና አባላት ላይ አደጋ እንዳይደርስ ጥንቃቄ በተሞላው መንገድ እርምጃ ወስዷል። በተለይ የጁንታው አመራሮች በቅርበት ይከታተሉን ስለነበር እነርሱን በሚነጥል ሁኔታ በአየር ከፊት ጠባብ መንገድ ላይ ተሽከርካሪዎቻቸውን አቃጥሏል። መከላከያ ሠራዊቱ የጁንታው አመራሮች ወደኋላ ሊመለሱ ሲሄዱ በኋላ በኩልም ተሽከርካሪዎቻቸው ተመተው መንገዱ እንዲዘጋባቸው አድርጓል። በዚህ ወቅት የጁንታው አመራሮች መሄጃ በማጣታቸው የነበራቸውን ተሽከረካሪዎች እና ንብረት እየጣሉና እያንጠባጠቡ ሲበታተኑ መከላከያ ሠራዊታችን ደርሶ አብረውኝ የነበሩትን ሁሉ ታጋቾችን ነፃ አውጥቷል” በማለት የሠራዊቱን እርምጃ አወድሰዋል። ሠራዊቱ የታፈኑትን ነፃ ሲያወጣ ጠላትና ወገንን የለየ ምርጥ ኦፕሬሽን አከናውኗል ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል አዳምነህ፤ እርምጃው መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ደስተኛ የሆነበት እና ጥሩ ሥራ የተከናወነበት እንደሆነም ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። “መከላከያ ሠራዊታችንን በግሌም ሆነ አብረውኝ በነበሩ አመራሮች ስም ላመሰግን እወዳለሁ። በመከላከያ ሠራዊታችን ኮርተንበታል” ብለዋል። በአፈናው ወቅት ስለነበረው ሁናቴ ሲያስረዱም፣ “ስሜቱን መግለጽ ያጥረኝ ይሆናል፤ እናትና አባትህ ይክዱኛል ብለህ በማትጠብቅበት ሰዓት በሠራዊቲ ላይ ክህደት ተፈጽሟል። ቤታችን ነው ሰላም ነው ባልንበት ቦታ በተደራጀ ሃይል የአፈና ሥርዓት ተካሂዷል።የአፈናው ጊዜ በሙሉ በርካታ ውጣ ውረዶች ያሉት ነው፤ ረጅም የእግር ጉዞዎች በቀንም በሌሊትም ያለዕረፍት ነበረው። ዞሮ ዞሮ ህይወታችንን ካተረፉን የመከላከያ ሠራዊት ወንድሞቻችን ጋር ሆነን ታሪኩን በጽሁፍ በሰፊው የምናቀርበው ይሆናል” በማለት ሁኔታውን በአጭሩ አስረድተዋል። ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ በጁንታው ቡድን ታጣቂዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸው የታፈኑት የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት አመራሮች ሽሬ ከተማ ሲደርሱ በሠራዊቱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በርካታ የሠራዊቱ አባላት ታፍነው የሰነበቱ አመራሮቹን እና ጓደኞቻቸውን ሲያገኙም ወደ ሰማይ በሚተኮስ የጥይት ድምጽ እና በጭፈራ ደስታቸውን ገልፀዋል።ህዳር 30 ቀን ከሰዓት በኋላ የጁንታው ቡድን አጋቾች አዴት በተባለ አካባቢ በእግር ሲያጓጉዟቸው የነበሩትን ከ1 ሺህ በላይ የሠራዊቱን መኮንኖች በመልቀቅ በየአቅጣጫው መበታተኑ ታውቋል። ታፍነው የሰነበቱ የሠራዊቱ አመራሮች መንግሥት ላደረገው የህይወት አድን ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 4/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37240
6a62879bfb5ba70325f4c2dbb693aa59
13d43079ba444bde48af02a3c0f8785c
ለምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች 31 ሺህ 500 ኩንታል የስንዴና የታሸጉ ምግቦች ድጋፍ ቀረበ
ጌትነት ተ/ማርያም ሽሬ:- ከምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል 31 ሺህ 500 ኩንታል ስንዴ እና የታሸጉ ምግቦች ድጋፍ መቅረቡን የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አደጋ ምላሽና ክትትል ቡድን መሪ እና በትግራይ ክልል ለሚቀርበው ድጋፍ አስተባባሪ አቶ ታዬ ጌታቸው እንደገለፁት፤ በምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች አፋጣኝ የምግብ ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ስንዴ እና ለህፃናት፣ እናቶችና አረጋውያን የሚሆኑ ፓስታ፣ ሩዝ፣ ዘይት፣ አልሚ ምግብ እና የማብሰያ ቁሳቁሶች ቀርቧል። እንደ አቶ ታዬ ገለፃ፤ መንግሥት ያቀረበውን ድጋፍ ለተፈናቃይ ዜጎች ለማከፋፈል በትግራይ ክልል ከተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በጋራ እየተሠራ ይገኛል። በተለያዩ ማዕከላት ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች አፋጣኝ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ተለይተዋል። ማምረት እና መሥራት የማይችሉ ዜጎች ጭምር ቤት ለቤት የምግብ ድጋፉ ይቀርብላቸዋል። አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብለው የተለዩ 13 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ ድጋፉ እየቀረበላቸው ይገኛል። የሽሬ እንዳሥላሴ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃጎስ በርሄ በበኩላቸው እንደገለፁት፤ ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅለው በሽሬ ከተማዋ የሚገኙ ዜጎች በዩኒቨርሲቲ እና በትምህርት ቤቶች ተጠልለው ይገኛሉ። እንደ አቶ ሃጎስ ከሆነ፤ መንግሥት ችግሩን ተገንዝቦ ለተፈናቃዮች ዕርዳታውን በተጠየቀ ጊዜ ቶሎ በማድረሱ ምስጋና ይገባዋል። ድጋፉን በፍትሃዊነት ለማከፋፈል እንዲቻል በጊዜያዊ አስተዳደሩ ከቀበሌ አንስቶ እስከ ከተማ አስተዳደር ጀምሮ የሰዎች ምደባ ተደርጓል። በከተማ ደረጃ ህብረተሰቡን ለማረጋጋት እና ድጋፎችን ለማከፋፈል አምስት የካቢኔ አካላት እና 25 የወረዳ ምክር ቤት አባላት ተመርጠዋል። በየቀበሌው አምስት አመራር እና 15 ጊዜያዊ የምክር ቤት አባላት አሉ። በተጨማሪ የድጋፍ ክፍፍሉን የሚያስተባብሩ አካላት ከኅብረተሰቡ ተመርጠው በተቻለ መጠን ድጋፉ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ጥረት እየተደረገ ይገኛል። አሁን ላይ ሀብታሙም ድሃውም ሕብረተሰብ የባንክ አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት እኩል የሆኑበት አጋጣሚ አለ የሚሉት አቶ ሃጎስ፤ ይሁንና ችግሩን ቀስ በቀስ ለመፍታት ጥረት በማድረግ በቅድሚያ ግን ህፃናት፣ ጧሪ የሌላቸው አረጋውያን እና በልመና የሚተዳደሩ ዜጎች አስቸኳይ ድጋፉ እንደሚሰጣቸው አስረድተዋል። ድጋፉ ሲዳረስም የመንግሥት ሠራተኞችን ጨምሮ ደመወዛቸው በባንክ ያሉ ነዋሪዎች እና ለሌሎች ዜጎች ድጋፍ ማቅረብ እንደሚቻል ገልፀዋል። ከተለያዩ የፌዴራል ተቋማት የተላኩ ተወካዮች በትግራይ ክልል የሚኖሩ ዜጎች ያሉባቸውን የሰብአዊ ድጋፍ እና አስቸኳይ የመሰረተ ልማት አቅርቦቶች እንዲሁም ተያያዥ ችግሮች በቀጣይነት የሚፈቱበት ሁኔታ ላይ በትግራይ ከተቋቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ተወያይተዋል። ህብረተሰቡ በውሃ በኩል ያለበትን ችግር መፍትሄ እንዲያገኝ ከውሃ መስኖ ሚኒስቴር የመጡ ተወካዮች እንደሚያስተባብሩ ታውቋል። የህፃናት፣ እናቶችን እና አረጋውያን ጉዳዮችን ደግሞ የሴቶችና ህፃናት ሚኒስቴር ተወካዮች ያስተባብራሉ። ቀድሞ በሴፍቲኔት ታግዘው ድጋፍ ሲያገኙ የነበሩ ሥር የሰደደ የምግብ አቅርቦት ችግር ያለባቸውን ዜጎችን ጉዳይ ደግሞ የግብርና ሚኒስቴር እንደሚያስተባብር ታውቋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 4/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37250
dc81574a0f7bdaa0361d7cae713d5a5a
aa80217851fe4a53a40a157545a7b2a6
መንግሥት በትግራይ ክልል የሚያካሂደውን ሁለንተናዊ ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- መንግሥት በትግራይ ክልል የሚያካ ሂደውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ:: ይህ የተገለፀው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ኬንያ እና ማላዊ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በተወያዩበት ወቅት ነው::እንደ ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ዘገባ፤ ውይይቱ ቅዳሜ ህዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም በበይነ መረብ (ቨርቹዋል) የተካሄደ ሲሆን፤ በወቅቱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኬንያ እና ማላዊ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዚህ ፈታኝ ጊዜ ላሳዩት ሀገራዊ ስሜት እና ላደረጉት ድጋፍ አመስግነው መንግሥት በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል የሚያካሂደውን ሁለንተናዊ ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለተሳታፊዎቹ ገልፀውላቸዋል።ሀገራችን ከውስጧ በተነሱ ከሃዲዎች ሉዓላዊነታችንን አደጋ ላይ የጣለውን፣ ጭካኔና አሳፋሪ ድርጊት የተፈፀ መበትን ሁኔታ ለመለወጥ፣ ሕግን ለማስከበር፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ መንግሥታችን ያካደሄው ፈጣንና ውጤታማ ተልዕኮ በሕዝባችን ድጋፍና አብሮነት፣ በቁርጠኛው መከላከያ ሠራዊታችን እና ልዩ ልዩ የፀጥታ አካላት አብሮ በመዋደቅ የተገኘው ድል የሁላችንም ድልና ኩራት ነው ብለዋል።በዚህ ኢ-ሰብዓዊና ጭካኔ በተሞላበት ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ለሕግ እንዲቀርቡም መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንሚሠራም ተናግረዋል። በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግሥትና አቋሞች በማስረዳት፣ ለመልሶ ማቋቋሙ እና ዳግም ግንባታው አስተዋጽኦ በማድረግ መንግሥት በሚያደገርው ጥረት እንዲደግፉም ጥሪ አቅርበዋል።በኬንያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በበኩላቸው፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አገራችን በህወሓት አፍራሽ ሃይል ተገዳ ወደ ሕግ ማስከበር መግባቷን ተከትሎ በኬንያ እና ማላዊ የሚኖሩ ወገኖቻችን ላሳዩት የጋለ ብሔራዊ ስሜት እና ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል። መንግሥት እያካሄደ ያለውን የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን የመጠበቅ እና የዜጐችን ደህንነት የማስከበር ዘመቻ እንዲሳካ በኬንያና ማላዊ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሙያተኞች እና ነጋዴዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቅሰው፤ በገንዘባቸው፣ በእውቀታቸው ባላቸው ግንኙነት የህዝብ አምባሳደር ሆነው ስለአገራቸው አቋምና ፍላጐት ዘብ መቆማቸውን ተናግረዋል። በቀጣይም ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ፣ የተፈናቀሉትን ለማቋቋም እና የፈረሰውን ለመገንባት መንግሥት በሚያደርገው ዲያስፖራው የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርግ ሚሲዮኑ ሙሉ እምነት እንዳለውም አምባሳደር መለስ ገልፀዋል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37305
56d50cbcf1c5844de60c337b1edb2881
00609d533d194e2da9d36915fb627618
መከላከያ ሰራዊት የታደገው የአሲምባው ወጣት
ክብሮም መሰለ ይባላል፡፡ ትውልዱና እድገቱ ትግራይ ክልል አሲምባ አካባቢ ነው፡፡ የ17 ዓመት ታዳጊና የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ አላማውና ምኞቱ ተምሮ እራሱንና ቤተሰቡን መለወጥ ነው፡፡ “በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል” እንዲሉ የጁንታው ታጣቂዎች አንድ ቀን ሌሊት መጥተው እርሱንና ጓደኞቹን በመኪና ጭነውን ወደ ራያ ግንባር ወሰዷቸው፡፡ ለጁንታው ታጣቂ ቡድን ጥይት እንዲያቀብሉና እግረመንገዳቸውን ውጊያ እንዲለማመዱ ተነገራቸው። ሸሽተው የሚሄዱ ከሆነ ደግሞ ተይዘው እንደሚረሸኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው፡፡ ክብሮም በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ያስረዳል፤ ‹‹የህወሓት ታጣቂዎች ሌሊት መጥተው እኔና ጓደኞቼን ከተኛንበት ቀስቅሰው ተሳቢ መኪና  ጭነው ወሰዱን፡፡ ከአንድ ቀን ጉዞ በኋላ ራያ ግንባር መኾኔ ከተማ አጠገብ ካለው የታጣቂዎቹ ምሽግ ደረስን፤ ሃይለኛ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ነበር፤ ለታጣቂዎቹ ጥይት ይዤ ወደ ተኩሱ መሃል እንደገባ አዘዙኝ፡፡ በሰላም ከምኖርበት ቦታና ከቤተሰቦቼ በድንገት ተለይቼ እሳት ውስጥ ስገባ ግራ ገባኝ፡፡ ከፊታችን መከላከያ ሰራዊት ወደእኛ ይተኩሳል፤ ከኋላም የታጣቂው አመራሮች በአይናቸው ይጠብቁናል፤ ሊተኩሱብን ተዘጋጅተዋል፡፡ ወደየትም ማምለጥ አይቻልም”“ያለህ አማራጭ ሳትወድ በግድ ባለህበት መሆን ነው፡፡ የመከላከያ ሰራዊት ጥቃት እየከፋ ሲመጣ በጣም ከመደንገጤ የተነሳ ቦታዬን ለቅቄ ወደ ኋላ ማፈግፈግ ጀመርኩ፡፡ እኔ የሰለጠንኩ ወታደር አይደለሁም፤ የጦርነት ልምድም የለኝም፤ ወጊያ አይቼ አላውቅም ብላቸውም ሊሰሙኝ አልቻሉም፤ ከኋላ ያለው አዛዥ ወደ ኋላ እንዳልመለስ ያስፈራራኛል፡፡ ዝም ብዬው ወደ ኋላ ሸሸሁ፤ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ወገኑ ነኝና ጨክኖ የሚመታኝ አልመሰለኝም ነበር፡፡ ግን ሽጉጡን አውጥቶ ተኮሰብኝ፡፡ የቀኝ ታፋዬ ላይ መታኝ ፤ እዛው ወደቅኩኝ፤ አንድ ሙሉቀን እዛው ተኛሁ፤ ብዙ ደም ፈሰሰኝ፤ ተኩሶ የመታኝ ሰው ኮለኔል ግርማይ በርሄ ይባላል፡፡ ሀሳቡ ሊገድለኝ ነበር እግዚአብሄር ግን ጠበቀኝ”ወጣቱ እንደሚናገረው፤ ህዳር 9 ከቤቱ ወደ ግንባሩ ወሰደውት ህዳር 11 በጥይት መትተው ጫካ ውስጥ ጥለውት ሄዱ፡፡ መከላከያ ሰራዊት ቦታውን ሲቆጣጠረው ከወደቀበት አንስቶ የመጀመሪያ እርዳታ አደረጉለት።  “በልጅነቴ አይጋ አካባቢ ስማር ደብተር እና አስኪብሪቶ እየገዙ፣ ምግብ እያበሉኝ፣ ልብስ እያለበሱኝ፣ ጫማቸውን አውልቀው እየሰጡኝ ያስተማሩኝ የምወዳቸው ባለውለታዎቼ የመከላከያ ሰራዊት አባለት አሉ፡፡ አንዱ ገቢሳ ይባላል አንዱም መለሰ ይባላል አልረሳቸውም፡፡ አብረን እንማር ነበር፡፡ ሁልጊዜ በትምህርቴ እንድጎብዝ ይመክሩኝ ነበር፡፡ ያሳደጉኝ ቤተሰቦቼ ሳይሆኑ እነርሱ ናቸው፡፡ እወዳቸዋለሁ ፤ ይናፍቁኛል፡፡ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ይደውሉልኝ ነበር” ይላል ወጣቱ፡፡ መከላከያ ሰራዊት ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለትግራይ ህዝብ ባለውለታ ነው” የሚለው ወጣቱ፤  “ሁሉም ሰው በሰላም ተኝቶ የሚያድረው በመከላከያ ሰራዊት ነው፡፡ ከጠላት ይጠብቁታል፤ በጉልበትና በገንዘብ ያግዙታል፡፡ ያሁሉ ውለታው ተረስቶ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመፈጸሙ በጣም አዝናለሁ፡፡ ይህንን ድርጊት የፈጸሙ አካላት ተይዘው ፍርድ እንዲሰጣቸው እፈልጋለሁ” ሲልም ነው ስሜቱን የገለጸው።“አሁን እኔ ቆስዬ እያነከስኩ በህይወት አለሁ። እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ ብዙ ጓደኞቼ ሞተዋል፡፡ ከወደቅኩበት አንስተው ያሳከሙኝን የመከላከያ ሰራዊትንም አመሰግናለሁ፡፡ አሁንም እያሳከመኝ ያለውን የቆቦ ወረዳ አመሰግናለሁ፡፡ የትግራይ ወጣቶች ሰላማዊ መንገድን እንዲከተሉ እመክራቸዋለሁ፤ አትሞኙ የቻላችሁትን መንገድ ተጠቅማችሁ ወደ ቤታችሁ ግቡ ማለት እፈልጋለሁ”“የራሳቸውን ልጆች ውጭ እያስተማሩ የደሃ ልጆችን ለሚያስገድሉ አመራሮች ታዛዥ አትሁኑ እላቸዋለው፡፡ ህይወታችሁን አትርፉ እላቸዋለሁ፡፡ የትግራይ ወጣት ከዚህ በኋላ ሰርቶ የሚበላበትና የሚድገግበት ጊዜ ስለመጣ መንግስትን ሊደግፍ ይገባል፡፡ እነዚህ ትግራይን የሚበጠብጡ አመራሮች የመንግስትን በጀት ለራሳቸው የሚጠቀሙ ሌቦች ናቸው፡፡ የትግራይ ህዝብ ፈርቶ ነው እንጂ ሁሉንም ያውቃል፡፡ አነዚህ ሌቦች የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመለየት ነው የሚጥሩት፡፡ ይህ ደግሞ አይሳካም፤ በምንማረው ትምህርት ውስጥ ሳይቀር ልዩነትን ያስተምራሉ፡፡ አንዱ ብሄር በሌላው ላይ ጥላቻ እንዲኖረው ያደርጋሉ፤ በተለይ በታሪክ ትምህርት ውስጥ የሚቀርበው ነገር ችግር የሚፈጥር ነበር፡፡ ለምሳሌ አጼ ቴዎድሮስ እከሌን ገድሎ ስልጣን ያዘ፤ አጼ ሚኒልክ የእከሌን ብሄር አጠቃ የሚል ትምህርት ማስተማር ተገቢነት የሌለው ነው”፡፡ “እንዲህ አይነቱ ትምህርት እውቀትን የሚያስጨብጥ ሳይሆን ክፋትን የሚያስተምር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ህዝቦች አንድነታቸውንና ፍቅራቸውን ጠብቀው ሊሄዱ ይገባል፡፡ የሰዎች ቋንቋ፣ ሃይማኖት ባህል ተጠብቆ በሰላም መኖር ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህ የትግራይ አመራሮች የትግራይን ህዝብ አዋርደውታል፤ አቀርቅሮ እንዲሄድ አድርገውታል፤ ግን ህዝቡን አይወክሉም፤ ነገ የተሻለ ጊዜ ይመጣል ብዬ አስባለሁ፡፡ የትግራይ ህዝብ እነዚህን ሰዎች እንደማይደግፋቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ማወቅ አለበት ›› ሲል ነው ሀሳቡን የቋጨው፤ ክብሮም መሰለ።  በኢያሱ መሰለ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37298
66c24aa93ab528a42b182979c7f8cb3e
a384f0fdce39e09358fd832e26c8f167
የአትሌት ደምሰው ፀጋ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ
 የአትሌት ደምሰው ፀጋ የቀብር ስነስርዓት በትውልድ መንደሩ ጫጫ ክርስቶስ ሳምራ ቤተክርስቲያን ትናንት ስምንት ሰዓት ላይ ተፈፅሟል፡፡ በቀብር ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያን ጨምሮ ፣ ወዳጅ ጓጀኞቹ ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች ፣ የተለያዩ አትሌቶች፣ ማናጀሮች፣ አሰልጣኞች ተገኝተዋል፡፡ አትሌት ደምሰው_ፀጋ በ1980 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን በአንጎለላ ጠራ ወረዳ በጫጫ ቀበሌ በጦጦሴ መንደር የተወለደ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ከ1988—1991 ዓ.ም በጦጦሴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከ1992—1995 ዓ.ም በጫጫ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታተለ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በ1996 ዓ.ም በደብረብርሃን አጠቃላይ 2ኛደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል፡፡ አትሌት ደምሰው ትምህርቱን እየተከታተለ በመረብ ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ እና በገና ጨዋታ የተዋጣለት ስፖርተኛ እንደነበረ የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡ በኋላም በስፖርት መምህሩ ምክር ወደ አትሌቲክስ ስፖርት አመራ፡፡ በ1997 ዓ.ም በዞንና በወረዳ ደረጃ በሚካሄዱ የ3፣5ና 10ሺ ሜትር ውድድሮች ውጤታማ መሆኑን ተከትሎ ወደ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ሊመጣ ችሏል፡፡ አትሌት ደምሰው ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እኤአ በ2006 ማድረግ የጀመረ ሲሆን ከ2006 እስከ 2015 ድረስ በ9 አመት ውስጥ በህመም ምክንያት ወጣ ገባ እያለ 24 ውድድሮችን አድርጓል። ከነዚህ ውድድሮች ውስጥ ሶስቱ ሀገሩን ኢትዮጵያን የወከለባቸው ውድድሮች ናቸው። በኬንያ ሞምባሳ፣ በጃፓን በቶኪዮ በ5ሺ እና በ10 ሺ ሜትሮች እንዲሁም በማራቶን ተሳትፎ ሜዳሊያ አግኝቷል። አትሌት ደምሰው የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ኮርስን የወሰደ ሲሆን፤ የሩጫ ሕይወቱ በፈለገው ደረጃ እንዳያድግ እንቅፋት የሆነበት ሕመም ሲሰማው ወደ ትውልድ መንደሩ እያመራ በርካታ አትሌቶችን በማሰልጠን ማፍራት ችሏል፡፡ አትሌት ደምሰው የአንድ ወንድና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ሲሆን ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ኑሮውን በአሜሪካ አድርጓል፡፡ ባደረበት ፅኑ ህመም ምክንያት ህክምናውን በአሜሪካ ሚሪላንድ ግዛት ሲከታተል ቆይቶ መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። አዲስ ዘመን ለአትሌቱ ቤተሰቦች፣ጓደኞችና የስፖርት ቤተሰቦች የተሰማውን ሃዘን ይገልፃል፡፡አዲስ ዘመን መስከረም 30/2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=20471
955a72c6f9c1dea883d0479f7bee755a
19c3127d858114b296c9b5aacd7a9673
የፌዴሬሽንና የክለቦች ውረድ አትውረድ ድራማ
አጨቃጫቂና አሰልቺ ከነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዚዳንትነትና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት የምርጫ ሂደት በኋላ አፋር ሰመራ ላይ ግንቦት 26 ቀን 2010 ዓ.ም አዲሱ አመራር ወደ ኃላፊነት መምጣቱ ይታወሳል፡፡ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አቶ ኢሳያስ ጅራና ሥራ አስፈጻሚው በሚፋጀው ወንበር ላይ በኃላፊነት ከተቀመጡ ከአንድ ዓመት በላይ እስቆጥረዋል፡፡ ፌዴሬሽኑን ለመምራት ብዙ ውጣ ውረዶችን ተሻግሮ የመጣው ቡድን የፈተናዎች መደራረብ ወደፊት አላስኬድ እንዳሉት ለመታዘብ እየተቻለ ይገኛል። ፌዴሬሽኑን አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገባ በይበልጥ እንቅፋት ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጉዳይ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በእግር ኳሱ ላይ ፖለቲካዊ ጥላ ማጥላቱ ፌዴሬሽኑ የሚያሳልፋቸውን ውሳኔዎች ይበልጥ በርካታ ፈተናዎችን እንዲጋፈጥ ምክንያት ሲሆን ለመታዘብ ተችሏል፡፡ በኢትዮጵያ ኳስና ፖለቲካው በተደበላለቁበት ሁኔታ ፕሪሚየር ሊጉን መሰረት አስይዞ ለመምራት ዳገት ሆኗል። ክለቦች ተዘዋውረው የመጨዋወት ህልውናቸውን እስኪያጡ ደርሰዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ መስመር ለማስያዝ በተለያዩ ጉዳዮች የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች በተደጋጋሚ መሬት ለመውረድ እግር ሲያጥራቸው ይስተዋላሉ።ፌዴሬሽኑ በፕሪሚየር ሊጉ የሚስተዋለውን የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል መፍትሄ ለማምጣት አዲስ የሊግ የውድድር ሥርዓትን (ፎርማት) ተግባራዊ ለማድረግ ያሳለፈው ውሳኔም ተቀባይነት ማግኘት አልቻለም፡፡ ተግባራዊ ለማድረግ የታሰበው የሊግ ውድድር ሥርዓት በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፍ ክለቦችን ቁጥር ከ16 ወደ 24 ከፍ የሚያደርግ መሆኑ ብዙ ውዝግብ ፈጥሯል፡፡ ፌዴሬሽኑ በ2011 የውድድር ዘመን ከፕሪሚየር ሊጉ የወረዱትን መከላከያ፣ደቡብ ፖሊስና ደደቢትን በነሀሴ ወር ይፋ ባደረገው የሊግ አደረጃጀት ለውጥ ምክንያት በሊጉ እንደሚቆዩ ከውሳኔ ደርሶ ነበር።በተጨማሪም ስምንት ከከፍተኛ ሊግ የሚገኙ ክለቦች አካል አድርጓል። የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ተከትሎ ክለቦቹ ዝግጅታቸውን ፕሪሚየር ሊጉን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ሲያደርጉ ቆይተዋል።የክለቦቹ የተጫዋቾች ዝውውርም ይሄንኑ ታሳቢ በማድረግ ዝግጅት ሲያደርጉበት ቆይተዋል። ፌዴሬሽኑ በ24 ቡድኖች አደርገዋል ያለው ውድድር ብዙም ሳይቆይ መሻሩን ተከትሎ ፌዴሬሽኑን አምነው ለፕሪሚየር ሊግ ሲያዘጋጁ የከረሙትን ክለቦች ውሃ በልቷቸዋል፡፡ የፌዴሬሽኑን የውሳኔ ዥዋዥዌ ተከትሎ ቅሬታቸውን በአደባባይ ከገለጹት ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው መከላከያ እግር ኳስ ክለብ ይጠቀሳል። የመከላከያ ክለብ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደረጀ መንግስቱ ክለቡ ከመሰረቱ ጀምሮ ቅሬታ ውስጥ እንደነበረ በማስረዳት ይናገራሉ። በ2011 የውድድር ዘመን መከላከያ 14ኛ ደረጃን በመያዝ ከፕሪሚየር ሊጉ ቢሰናበትም በወልዋሎና ሽረ እንዳስላሴ ጨዋታ ቅሬታን በወቅቱ ለፌዴሬሽኑ አስገብቶ እንደነበር ያስታውሳሉ። ከፌዴሬሽኑ ምላሽ ሳይሰጠው እንደቆየ የሚናገሩት ኃላፊው፤ ክለቡ የፌዴሬሽኑን ውሳኔ በመጠባበቅ እያለ ነሃሴ ወር መጀመሪያ መመሪያ እንደተሰጣቸው ያብራራሉ። ክለቡ በዚህም መመሪያ መሠረት በፕሪሚየር ሊጉ ለመወዳደር ሲዘጋጅ ቆይቶ አዲሱ ፎርማት ዳግም መቀየሩ እርግጥ ሆኗል፡፡ በአዲሱ ፎርማት መሠረት በፕሪሚየር ሊጉ ትሳተፋላችሁ በተባለው መሰረት በፕሪሚየር ሊጉ ለመሳተፍ ክለቡ ዝግጅት እያደረገ ባለበት ወቅት ይህን አይነት ውሳኔ መሰማቱ ክለቡን በከፍተኛ ሁኔታ ቀውስ ውስጥ የሚያስገባው መሆኑን ያስረዳሉ ።«በ24 ክለቦች መካከል እንዲካሄድ የተወሰነው ውሳኔ ስለመታጠፍ አልያም ፤የተወሰነው ውሳኔ ይሄ ነው በሚል የተገለጸልን ነገር የለም» ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ከፌዴሬሽኑ በኩል ስለ ውሳኔው መቀየር እስካሁን አንዳችም ነገር የተባሉት ነገር እንደሌለና በደብዳቤም እንዳላሳወቃቸው ያመላከቱት። ህጋዊ ሆኖ የመጣ ውሳኔ ባይኖርም የሚለወጥ ነገር ከመጣ ግን ክለቡ የራሱን ውሳኔ የሚወስን መሆኑንም ነው ያሳሰቡት። ክለቡ በሚወስደው እርምጃ ዙሪያ ከመናገር የተቆጠቡት ፕሬዚዳንቱ ክለቡ ከፌዴሬሽኑ በኩል ይፋዊ ደብዳቤ ሲደርሰው አቋማቸውን እንደሚያሳውቁ ነው ያስገነዘቡት። የፌዴሬሽኑን የውሳኔ ተለዋዋጭነት ተከትሎ ቅሬታን ካሰሙት ክለቦች መካከል የደቡብ ፖሊስ እግር ኳስ ክለብ ይጠቀሳል። ክለቡ በሊግ አደረጃጀቱ ላይ ለውጥ ተደርጎ ሊጉ በ16 ክለቦች እንዲቀጥል መወሰኑ አግባብ እንዳልሆነ በመግለጽ በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ላይ ቅሬታውን እያሰማ ይገኛል። የክለቡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኢንስፔክተር እታገኝ ዜና ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት ‹‹ለፕሪሚየር ሊጉ ዝግጅት በማድረግ ላይ እያሉ የውሳኔ ለውጥ መደረጉ ያሳዝናል›› ብለዋል፡፡ ‹‹ፌዴሬሽኑ እየበጠበጠን ነው›› ያሉት ኢንስፔክተር እታገኝ በ2012 ዓ.ም በፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ በመሆናቸው ዝግጅት እንዲያደርጉ ደብዳቤ ደርሷቸው ነበር፡፡ የፌዴሬሽኑን ደብዳቤ መሰረት በማድረግ ለፕሪሚየር ሊጉ ዝግጅት ሲያደርጉ በመቆየትም ፕሪሚየር ሊጉ ላይ ተሳታፊ መሆንን ታሳቢ በማድረግ በጀት እንደተያዘ ያብራራሉ፡፡ ‹‹አሰልጣኝም ሆነ ተጫዋቾችን ያስፈረምነው ይሄንኑ ታሳቢ በማድረግ ነው።የፌዴሬሽኑ ውሳኔ እንደ ክለብ ጎድቶናል፣ለምሳሌ የፌዴሬሽኑን ውሳኔ የሰሙ ተጫዋቾች ዛሬ ልምምድ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል። የእነሱም ዝግጅት ለፕሪሚየር ሊጉ እንጂ ለሌላ አልነበረም። በአጠቃላይ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ እኛ ላይ ችግር እየፈጠረ ነው። በተለይ ደግሞ በየጊዜው እያሳየ የሚገኘው የሃሳብ መለዋወጥ አሳዝኖናል›› ይላሉ። በፌዴሬሽኑ የውሳኔ መለዋወጥ ቅሬታ የተሰማቸው ክለቦች ከተጠቀሱት ክለቦች በተጨማሪ እንደሌሉ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፌዴሬሽኑ በእውቀት ሳይሆን በይሆናል መንገድ፤ በስሌት ሳይሆን በስሜት የሚወስናቸው ውሳኔዎች ዋጋ እንዳስከፈላቸው እየተናገሩም ይገኛሉ። በአዲሱ የሊግ አደረጃጀት መሰረት ለፕሪሚየር ሊጉ ዝግጅታቸውን እያደረጉ ባሉበት ሁኔታ እንዲህ አይነት የውሳኔ መዋለል መታየቱ በርካታ ክለቦችን ጎድቷል። ፌዴሬሽኑ የወሰነው ውሳኔ ከመሰረቱ ጥናት ያልተደረገበት መሆኑ ደግሞ የፌዴሬሽኑን ተጠያቂነት ይበልጥ ያጎላዋል። ፌዴሬሽኑ ተጠያቂነትን ባልወሰደበት ሁኔታ ብሎም የፕሪሚየር ሊጉ መጨረሻ ሳይለይለት የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በወርሃ ጥቅምት መጨረሻ እንደሚጀምር በአቋሙ እንደፀና ይገኛል። የውድድር መርሃ ግብሩን በ24 ክለቦች መካከል ለማድረግ ውሳኔ ካስተላለፈ ከቀናት በኋላ ሃሳቡን ቀይሮ በ16 ቡድኖች እንደሚወዳደሩ እርግጥ ሆኗል፡፡ የፌዴሬሽኑን መወላወል ተከትሎ ቅሬታዎች መሰማታቸው ፕሪሚየር ሊጉ በወርሃ ጥቅምት መካሄዱ ብቻም ሳይሆን ፤በዚህ ዓመት ሊጉ ራሱ ስለመካሄዱ ጥርጣሬ እንዳለ ጭምር እየተነገረ ይገኛል። ፌዴሬሽኑ ፕሪሚየር ሊጉን ማካሄድ ይችል ይሆን? የሚለውን ጥያቄ የስፖርት ቤተሰቡ በከፍተኛ ጉጉት እየተጠባበቀ ይገኛል። ይፋዊ ያልሆኑ ሰሞኑን እየተሰሙ የሚገኙ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ግን መከላከያ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማደግ 99% እድል አለው። ለዚህም መከላከያ ከወረደ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሽሬ እንዳስላሴ ይወርዳሉ የሚሉ መላ ምቶች ገፍተው እየወጡ ነው፡፡ ለዚህም በቂ ማስረጃዎች አሉ። ይህ ከሚሆን መከላከያን ማሳደግ ቀላሉ መፍትሄ ነው። መከላከያ የሰራዊት ክለብና በአገሩ ተጫዋቾች ብቻ የሚኮራ ወይም የሚያምን ቡድን ስለሆነ ‹‹ቢያድግ›› የሚቃወም አይኖርም የሚሉ ስፖርት ቤተሰቦች በርካታ ናቸው። ጥያቄው ግን አምና ወደ ፕሪሚየር ሊግ አድጎ የወረደው የደቡብ ፖሊስ ጉዳይስ ይሆናል? መልሱ ቀላል ይመስላል፣ ለመከላከያ የሚወሰነው ለደቡብ ፖሊስም ይሰራል። ከከፍተኛ ሊግ አደጉ ለተባሉት ክለቦች ወደመጡበት እንዲወርዱ ደብዳቤ መላኩ ደግሞ ይሄን ሃሳብ ውሃ እንዲያነሳ ያደርጋል::አዲስ ዘመን መስከረም 30/2012 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=20468
20855d71be44f3b9fd704d8085392729
3ba0946220cfcea15bd95e2f3871c129
ኮሚሽኑ የማዘውተሪያ ስፍራዎችን ቁጥር 40ሺ ለማድረስ አቅዷል
የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በአገሪቷ የሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በዓይነት፣ በመጠንና በቦታ በተጨባጭ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ቆጠራማድረጉን አስታወቀ። ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ለሚገኙ ማዘውተሪያዎች አቅጣጫ መጠቆሚያ (ማፒንግ) በማዘጋጀት ላይም ይገኛል። ኮሚሽኑ ለአገሪቷ ስፖርት እድገት እንደ ምክንያት የሚነሳውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረት የመፍታት እንዲሁም ሕጋዊ ይዞታ እንዲያገኙ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል። በዚህም መሠረት በ2007 ዓ.ም 12ሺ428 የነበሩትን የማዘውተሪያ ስፍራዎች፤ በተያዘው ዓመት መጨረሻ ወደ 40ሺ ለማሳደግ አቅዶ እየሰራ ነው። በ2011 የበጀት ዓመት በተደረገው ቆጠራም 21ሺ ማዘውተሪያዎች በአገሪቷ እንዳሉ ታውቋል። እነዚህ ማዘውተሪያዎች የይዞታ ማረጋገጫ እንዲሁም የደረጃ የመለየት ሥራ የተደረገባቸው ሲሆኑ፤ ያሉበትን ቦታ የሚያሳዩ የአቅጣጫ መጠቆሚያ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል። ከጠቅላላው የማዘውተሪያ ስፍራዎች መካከል መንግሥት በከፍተኛ ወጪ የሚገነባቸው ግዙፍ ስታዲየሞችም ይገኙበታል። ከእነዚህ መካከል ብሔራዊ ስታዲየም አንዱ ሲሆን፤ ወደ ሁለተኛው ዙር ግንባታው ለመግባት በጨረታ ሂደት ላይ እንደሚገኝም ነው ኮሚሽኑ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያስታወቀው። በተለያዩ ክልሎች እየተገነቡ ያሉ ስታዲየሞች የቁጥጥርና ክትትል ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝም ተመልክቷል። ኮሚሽኑ ከማዘውተሪያዎች ባለፈ በማስፈጸም አቅም ግንባታ፣ የተተኪ ስፖርተኞችን ችግር በመቅረፍ፣ በማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሁም ኅብረተሰቡን በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ በማድረግ ረገድ ባለፈው ዓመት ዓበይት ተግባራት ማከናወኑንም ገልጿል። ከተግባራቱ መካከል አንዱ የማስፈጸም አቅም ግንባታን የሚመለከት ሲሆን፤ ከዚህም ጋር በተያያዘ ከአገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት ጋር በጋራ እየራ ይገኛል። የስፖርት ማህበራቱ ዓመታዊ ጉባኤያቸውን በወቅቱ እንዲያደርጉ በመከታተል፣ እንዲሁም የሚወጡ ደንቦች ከአገሪቷ፣ አህጉር እንዲሁም ዓለም አቀፍ የስፖርት ማህበራት ጋር የተናበቡ መሆናቸውንም ያረጋግጣል። የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርት ኮሚቴዎች እንዲደራጁና እንዲጠናከሩም አድርጓል። የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰትን በተመለከተም መንስኤውን በጥናት በመለየት የፖለቲካ ችግሩን በከፍተኛ አመራሮች ግንኙነት በተወሰነ ደረጃ መፈታቱ ተጠቁሟል። በጥናቱ የተለዩ ሌሎች ችግሮችንም ከባለድርሻ አካላት ጋር መግባባት ላይ ለመድረስ የሚያስችሉ መድረኮች ተዘጋጅተዋል። የተሰጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም በሚመለከተው አካል ተግባራዊ እንዲሆን የማስተግበር፣ የመከታተልና የመገምገም ሥራዎች ተከናውነዋል። ኮሚሽኑ አገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት ዕቅዳቸውን በብቃት እንዲያሳኩ ድጋፍ ማድረጉም በሪፖርቱ ተጠቁሟል። 27ቱም ማህበራት የተደረገው የበጀት ድጋፍም ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ ነው። በዓመቱ በተካሄዱት የታዳጊ ወጣቶች ምዘና እና የተማሪዎች ውድድር፣ በባህርዳር በተካሄደው የአፍሪካ ብስክሌት ቻምፒዮና፣ የሴቶች ጨዋታ እንዲሁም ለፓራሊምፒክና ዴፍሊምፒክ ስፖርቶች በድምሩ ከ45 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓል። ለ12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ዝግጅት እንዲሁም ተሳትፎ 38 ሚሊዮን ብር ጥቅም ላይ ውሏል። ከዚህም ባሻገር ኮሚሽኑ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ የወጣቶች ኦሊምፒክ፣ ከ16 እና 18ዓመት በታች ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያም ተካፋይ በመሆን ሜዳሊያዎችን እንድታስመዘግብ ድጋፍ አድርጓል። በአገሪቷ የሚታየውን የተተኪ ስፖርተኞች ችግር በመቅረፍ በኩልም የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል። ታዳጊዎች በ17 የስፖርት ዓይነት በ2ሺ የሥልጠና ጣቢያዎች፣ ከአምስት በላይ በሚሆኑ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት እንዲሁም በሁለት አካዳሚዎች ላይ ሥልጠናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ የሥልጠና ፕሮግራሙ ከታለመለት ዓላማ አንጻር ውጤታማ ባለመሆኑ ያለበትን ደረጃ እና ያስገኘውን ውጤት የማረጋገጥ ሥራ ተከናውኗል። ዓመታዊው የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድርም በአርባምንጭ ከተማ ተካሂዷል። ኅብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚሰራበትና በሚማርበት አካባቢ በስፖርት ተሳታፊ በማድረግ ረገድም ባለፈው ዓመታት የተሻሉ ጅምሮች ታይተዋል። በአገር አቀፍ ደረጃ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት የእግር ጉዞ እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብሮችን ማዘጋጀት ተችሏል። በዚህም ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቁጥር ያለውን ሕዝብ ማሳተፍ መቻሉን በሪፖርቱ ተጠቁሟል።በተያዘው በጀት ዓመትም የስፖርት ችግሮችን በጥናት ለመለየት፣ የፌዴራል ስፖርት ምክር ቤት ጉባኤን ለማካሄድ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ቁጥር ለማሳደግ እንዲሁም ሕጋዊነታቸውን ማረጋገጥ፣ በስፖርት ለሁሉም መርሃ ግብሮች ኅብረተሰቡን በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማሳተፍ፣ ስፖርታዊ ጨዋነትን በዘላቂነት ለማስፋት፣ የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠናን በጥናቱ መሠረት ለመምራት እንዲሁም የሽልማትና ዕውቅና መድረኮችን ለማዘጋጀት ታቅዷል። አዲስ ዘመን ጥቅምት 1/2012 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=20621
4c9116dcf33cae2678dffc6e133c2bc7
00c2229ea9ea47a9f7f89dee1a557fe8
ቀንም ሌትም ከሠራዊቱ ጎን ያልተለዩት ሐኪሞች
ጌትነት ተስፋማርያም ኮሎኔል ዶክተር ተረፈ ንጉሴ በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር ዘመቻ የጤና አገልግሎት እንዲሰጥ ከአዲስ አበባ በተላከው የህክምና ቡድን ውስጥ አባል ናቸው። በመከላከያ ሠራዊት ምዕራብ ዕዝ የፈውስና ክብካቤ ኃላፊ ሆነው እየሠሩ ይገኛል። ከህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምረው መከላከያ ሠራዊቱ በሚንቀሳቀስባቸው እና ግዳጅ በሚፈፅምባቸው አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው።በጁንታው አማካኝነት በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የተፈፀመው ጥቃት የህክምና ባለሙያውን አስቆጭቶታል፤ ቁጭቱን ለመግለፅም በሙያው ለማገልገል በወኔ ተነስቷል። ሐኪሙም ከሠራዊቱ ጋር ቢዋጋ ደስ ይለዋል፤ ይሁንና ህይወት ማዳኑም ትልቅ ሥራ ነውና ሙያውን እያሳለጠ እንቅልፍ ሳይበግረው ለሠራዊቱ አጋር በመሆን ላይ እንደሚገኝ ነገረውናል። ያሉበት ቦታ ኔትወርክ የሌለበት ቢሆንም የተገኘው ቤተሰብ ናፈቀኝ አሊያም ገንዘብ አስፈለገኝ ብሎ ሲያማርር አይስተዋልም። ለግዳጅ የወጣው የህክምና ባለሙያ ተንቀሳቃሽ ሆኖ በየቦታው መሪ ሳይፈልግ ምን እናድርግ ብሎ ለመፍትሄው ይሮጣል፤ ለማስተባበርም ቀላል የሆነ እና በወኔ የሚሠራ ባለሙያ ነው የታየው። የህክምና ባለሙያው የሚተኛባቸውን አነስተኛ ፍራሾች እንኳን ለታካሚዎች አውጥቶ በመስጠት ጭምር እያገለገለ መሆኑን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።ተረኛ ነኝ የሚባል ንግግር በሐኪሙ ዘንድ የለም። በተለያየ ምክንያት ወደ ማዕከላት መጥተው የህክምና ዕርዳታ የሚፈልጉ ወታደሮችን ቀን ብቻ ሳይሆን ምሽት ላይም አገልግሎት በመስጠት ሐኪሞች ሌሊቱን ጭምር ቆመው በሥራ ያሳለፉባቸው ጊዜያት በርካታ መሆናቸውን አውግተውናል። ሁሉም በትብብር ለመጣበት ሀገራዊ ዘመቻ በጋራ ተሰልፏል የሚሉት ኮሎኔል ዶክተር ተረፈ፤ ረጅም ሰዓት ቆመው በማገልገላቸው ድካም የሚታይባቸውን ሐኪሞች በግድ ጎትተው ያሳረፉበት ወቅት መኖሩን ይናገራሉ። የህክምና ባለሙያዎቹ ስሜት ግን ለሀገሩ ክብር ሲል ሲዋደቅ ለሚውለው ወታደር 24 ሰዓት ሙሉ የህክምና አገልግሎት መስጠት ነውና እረፉ ሲባል እንኳን የማይስማሙ በርካታ ባለሙያዎች መኖራቸውን ነው የነገሩን። ቆስለው እንኳን የሕግ ማስከበር እርምጃውን ሳናጠናቅቅ አንመለስም የሚሉ የጦር መሪዎች እና የሠራዊት አባላት መኖራቸውን ያስታወሱት ኮሎኔል ዶክተር ተረፈ፤ ከፍተኛ የህክምና ዕርዳታ እያስፈለጋቸው የህክምና ባለሙያዎችን የሚያበረታቱ ሰዎች መኖራቸውን ማየታቸው ከትውስታዎቻቸው መካከል ዋነኞቹ መሆናቸውን ነው ያስረዱን።<<አሁን ላይ ዋናው የሕግ ማስከበር እርምጃ ቢጠናቀቅም የማጥራት ሥራ ነው እየተከናወነ የሚገኘው፤ ይሁንና ዋናውን የጁንታ አመራር ለማግኘት የተወሰነ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። እኛ የህክምና ባለሙያዎች በትግራይ ክልል አዲሱ መስተዳደር ተረክቦ እራሱን እስኪችልና መረጋጋት እስኪፈጠር የሚሰጠንን ግዳጅ በአግባቡ ለመወጣት ሁሌም ዝግጁ ነን። ብዙ ጊዜ ይወስዳል ብዬ ባላስብም ሁኔታው እስከፈቀደ ድረስ በሙያዬ ለማገለገል ዝግጁ ነኝ>> ብለዋል። የህክምና ባለሙያው ሌተናል ኮሎኔል በላይነህ በሪሁን የምዕራብ ዕዝ ቀዶ ጥገና ክፍል ኃላፊ ናቸው። የሠራዊቱ አጋር ለመሆንና በሙያቸው ለመደገፍ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም መነሻቸውን ከባህር ዳር ከተማ ማድረጋቸውን ያስታውሳሉ። ሠራዊቱ በተንቀሳቀሰባቸው አካባቢዎች ሁሉ ከጎንደር ጀምሮ እስከ ዳንሻ፣ ሑመራ እስከ ሽራሮ፣ አዲሃገራይ እና ሽሬ እንዲሁም ሽሬ ከተሞች እየተንቀሳቀሱ የህክምና ባለሙያዎችን በማስተባበር አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው። የሕግ ማስከበር እርምጃው የጦር መሣሪያ ልውውጥ ያለው ነውና ቁስለኛ መኖሩ አይቀርም። እርሳቸውና የሥራ ባልደረቦቻቸው ቁስለኞችን በማከም ህይወት የማስቀጠል ሙያ ተግባራቸውን ወደውና ፈቅደው እየተወጡ እንደሚገኝ ነግረውናል። በሁለት ቡድን ተከፍሎ የህክምና ዕርዳታ እየሰጠ የሚገኘው ቡድን ባረፈባቸው ቦታዎች ሁሉ ግዳጁን በብቃት እየፈፀመ ይገኛል። የጁንታው ቡድን የጥፋት ተልዕኮ የተደራጀ እንደነበር ያስታወሱት ሌተናል ኮሎኔል በላይነህ፤ ሽራሮ አካባቢ የነበረን ትልቅ ሆስፒታል ንብረት በሙሉ ዘርፎ መውወሰዱን ነግረውናል። ንብረቱን ብቻ ሳይሆን ሰዎችንም በመጫን በቦታው የነበሩ የህክምና ባለሙያዎችን ጭምር አፍነው መውሰዳቸውን ነግረውናል። አካባቢውን መከላከያ ሲቆጣጠረው አንድ ባዶ የአስክሬን ሳጥን ብቻ መገኘቱን በትዝብት መልክ አጋርተውናል። የህክምና ባለሙያው ሠራዊቱ ላይ የተፈፀመው ጥቃት እና የደረሰው በደል ሲያይ ማንም ሳይቀሰቅሰው በቁጭት እና በሞራል የህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ አድርጓል። ሐኪሙም የራሱን መኝታ ብቻ ሳይሆን የዝናብ ልብሱንም ጭምር ለሠራዊቱ በመስጠት ታካሚው አረፍ የሚልበትን መንገድ ሁሉ እያመቻቸ መሆኑን ይናገራሉ። ቀንም ማታም በሥራ ላይ ከማሳለፍ ባለፈ የምግብ ሰዓቱን የሚያስታውስ የህክምና ባለሙያ አለመኖሩን ነው ያጫወቱን። በህክምና ማዕከላቱ የጽዳትም ሠራተኞች አለመኖራቸው ቢታወቅም ሐኪሞች የጤና አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ ክብሬ ተነካ ሳይሉ የህክምና ማዕከላቸውን ወለል እና ግድግዳ በማጽዳት ጭምር ግዳጃቸው በውጤት እንዲጠናቀቅ እየተጉ መሆናቸውን ያስረዳሉ። ምንም እንኳን የመብራት አገልግሎት ባይኖርም <<የህክምና ባለሙያው ግን ይህ ችግር አለብኝ ብሎ ሳይማረርና እና ሥራውን ሳያስተጓጉል በሻማና በእጅ ባትሪ አገልገሎት እየሰጠ ይገኛል፤ እንደ ህክምና ባለሙያ በግንባር ተገኝቼ በሰጠሁት አገልግሎት እጅግ ደስተኛ ነኝ >> ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 5/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37306
ceb7fa0f5bd55bc03fa5655eeb2af8d7
ba423af6511abb3fd29996df2ac6a138
ናይኪ የኦሪገን ፕሮጀክቱን ዘጋ
 ግዙፉ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ ናይኪ በአሜሪካ ፖርትላንድ ኦሪገን ያለውን የአትሌቲክስ ፕሮጀክት መዝጋቱን አስታወቀ። የፕሮጀክቱ አሰልጣኝ የሆነው አልቤርቶ ሳላዛር ከአበረታች መድኃኒት ዓለምአቀፍ ሕግጋቶች መጣስ ጋር ተያይዞ ከሳምንት በፊት ከማንኛውም ስፖርት ለአራት ዓመታት መታገዱ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ ናይኪ ፕሮጀክቱን ለመዝጋት እንደወሰነ ረነርስ ወርልድ ከትናንት በስቲያ ምሽት ዘግቧል። አሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር በፕሮጀክቱ የሚያሰለጥናቸውን አትሌቶች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ አበረታች መድኃኒት እንዲጠቀሙ ያደርጋቸዋል በሚል ከስፖርቱ መታገዱን ተከትሎ በፕሮጀክቱ የታቀፉ አትሌቶች ጥያቄ ውስጥ መግባታቸው አልቀረም። የናይኪ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ፓርከር ለረነርስ ወርልድ እንደገለፁት፣ የፕሮጀክቱ አትሌቶች ባልተረጋገጠ አሉባልታ ከአበረታች መድኃኒትተጠቃሚነት ጋር ስማቸው መነሳቱ ያላቸውን እምቅ አቅም ተጠቅመው በልምምድና ውድድሮች ላይ ትኩረት እንዳያደርጉ ተፅዕኖ ስለሚፈጥርባቸው ፕሮጀክቱን መዝጋት አስፈላጊ ሆኗል። ስለዚህም ናይኪ ኩባንያ የፕሮጀክቱን አትሌቶች በሚፈልጉትና ትክክል ነው ብለው በሚያምኑት አሰልጣኝና የሥልጠና ሂደት እንዲከታተሉ በማድረግ ድጋፉን ከውጪ ሆኖ እንደሚቀጥልበት ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል። የፕሮጀክቱን በርካታ አትሌቶች የሚያሰለጥኑት ፒት ጁሊያን ከአበረታች መድኃኒት ጋር በተያያዘ ስማቸው የማይነሳ ከመሆኑም ባሻገር የዓለም አትሌቲክስ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዳላቸው ይነገራል። የናይኪ ኦሪገን ፕሮጀክት ሲዘጋ የእኚህ አሰልጣኝ ዕጣፈንታ ምን እንደሚሆን የተገለፀ ነገር የለም። በቅርቡ በተጠናቀቀው የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በአስር ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ ማሸነፍ የቻለው ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻን ጨምሮ የአስርና አንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር ቻምፒዮኗ ትውልደ ኢትዮጵያዊት የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን የናይኪ ኦሪገን አትሌቲክስ ፕሮጀክት ሰልጣኞች ናቸው። ነገ በሚካሄደው የቺካጎ ማራቶን የሚወዳደሩት አሜሪካውያኑ ጋለን ሩፕና ጆርዳን ሃሴይም የዚሁ ፕሮጀክት ፍሬዎች ናቸው። የሦስት የዓለም ቻምፒዮናዎችና የሁለት ኦሊምፒኮች የአስርና አምስት ሺ ሜትር ቻምፒዮኑ እንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህን በነገው የቺካጎ ማራቶን ለአሸናፊነት የሚጠበቅ የቀድሞ የናይኪ ኦሪገን አትሌቲክስ ፕሮጀክት ውጤት መሆኑ ይታወቃል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነው የአትሌቲክስ ስፖርት አሠልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን ከቦታ ቦታ ማዘዋወርን (Trafficking) ጨምሮ የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴውን በማወክ (Tampering) እና በተለያዩ የፀረ-ዶፒንግ የሕግ ጥሰቶች ተጠርጥሮ ጉዳዩ በአሜሪካ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (USA­DA) ሲጣራ ቆይቷል። በዚህም መሠረት ግለሰቡ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ለአራት ዓመታት በስፖርቱ ውስጥ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጥሎበታል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና የስፖርት ባለሞያዎችም ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ከአሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር ጋር የሚኖራቸውን ቀጥተኛም ይሁን ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት ማቋረጥ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት ማሳሰቡ ይታወሳል።አዲስ ዘመን ጥቅምት 1/2012ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=20624
2848b1dabe94c4f76abb540ff0b9eaf4
9a110306f18f577fcc7289b9cc971da7
ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች የማጠናቀቅ ተስፋ
 በማራቶን የዓለም የሁለት ጊዜ ቻምፒዮኑ ኬንያዊ ኢሉድ ኪፕቾጌ በሳምንቱ መጨረሻ ማራቶንን ከ2ሰዓት በታች የመግባት ሙከራውን በኦስትሪያ ቬና ያደርጋል። ኪፕቾጌ እ.አ.አ በ2018 የበርሊንን ማራቶን የገባበት 2፡01.39 የሆነ ሰዓት የዓለም ክብረወሰን ሲሆን፤ ይህንን በማሻሻል 1ሰዓት ከ59 ደቂቃ የመግባት ሙከራ ያደርጋል። አትሌቱ ለሙከራው እንዲሁም «የሰው ልጅ ዓቅም አይወሰንም» የሚለውን አባባል በተግባር ለማሳየት የሚችልበት አቋም ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል። ናይኪ የተባለው የስፖርት ትጥቅ አምራች የተያዘው ይህ ፕሮጀክት ሙከራውን ከዓመታት በፊት የጀመረ ሲሆን፤ ዛሬ በቬና በያዘው ቀጠሮም ይሳካል የሚል እምነት አሳድሯል። አትሌቱ ለሩጫው ያመቸው ዘንድ ልዩ የመሮጫ ጫማ የተዘጋጀለት ሲሆን፤ ከተማዋም በዛፍ የተከበበችና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ያላት በመሆኑ አትሌቱ ያሰበውን ለማሳካት ይረዳዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት አትሌቱ በጣሊያኗ ሞንዛ ከተማ ባደረገው ሙከራ በ26 ሰከንዶች ዘግይቶ ዓላማውን ማሳካት አልቻለም ነበር፤ አሁን ግን የከተማዋ የቦታ አቀማመጥ እንዲሁም አሯሯጮች የተዘጋጁ በመሆኑ ሰዓቱን እንደሚያሻሽል ተስፋ ተጥሎበታል። ኢሉድ ኪፕቾጌ ሙከራውን በተመለከተ በሰጠው አስተያየትም «ከሁለት ሰዓት በታች የመግባት ሙከራውን ለማድረግ ተዘጋጅቻለሁ። ዝጅግቴም ጥሩ ነበር፤ ይህንንም በተግባር አሳይቼ የሰው ልጅ አቅም ገደብ እንደሌለው አስመሰክራለሁ» ሲል ለኒውስ 24 ገልጿል። ከአትሌቱ ጋር በአሯሯጭነት በሙከራው ላይ የሚሳተፉት 41አትሌቶች የታወቁ ሲሆን ዘ ዋሽንግተን ፖስትም ታዋቂዎቹን በስም ጠቅሷል። በ1ሺ500 ሜትር የዓለም ቻምፒዮን የሆነው አሜሪካዊው ማቲው ሴንትሮዊትዝ፣ በዶሃው የዓለም ቻምፒዮና የ5ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ ተሸላሚው ሰለሞን ባረጋ፣ በ3ሺ ሜትር የዓለም ቀዳሚው ሰዓት ባለቤት ኡጋንዳዊው ሮናልድ ሙሳጋላ እንዲሁም ሌሎች ጠንካራ አትሌቶች ተካፋይ ይሆናሉ።አዲስ ዘመን ጥቅምት 1/2012 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=20630
205d5d34d86d496c575c77cdecdf9bd5
a071e81cbeaccb65aa0ebb3fbd281ef2
‹‹በሐዋርያት መካከል ራስ ወዳድ ሆኖ አምላኩን የሸጠ እንዳለ ሁሉ በሕዝብ መካከልም ይሁዳዎች ይጠፋሉ ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም››ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ
ጽጌረዳ ጫንያለው አዲስ አበባ፡- በ12ቱ ሐዋርያት ራስ ወዳድ ሆኖ አምላኩን የሸጠ እንዳለ ሁሉ በሕዝብ መካከልም ዳግማዊ ይሁዳዎች ይጠፋሉ ብሎ ማሰብ ትክክል እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ አስታወቁ። ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በ12ቱ ሐዋርያት መካከል ሐዋርያዊ ተልዕኮ ተሰጥቶት ከተላከበት ሥራ ይልቅ ራሱን ወዶ አምላኩን የሸጠ ይሁዳ እንዳለ ሁሉ በሕዝብ መካከል፣ የተዘሩ የዲያቢሎስ የግብር ልጅ የሆኑ ዳግማዊ ይሁዳዎች መኖራቸው የማይቀር ነው።ለዚህም ማሳያው ብሔርንና የአገር ባለውለታን እየነጠሉ በጅምላ የጨፈጨፉት የህወሓት ጁንታዎች ተጠቃሽ ናቸው። ግን እነዚህ አካላት ትግሬ በመሆናቸው የትግራይ ሕዝብን ይወክላሉ ብሎ ማሰብ የተሳሳተ ምልከታ ነው። የትግራይ ሕዝብ አማኝና ኢትዮጵያዊነቱን አጥብቆ የሚወድ እንደሆነ በርካታ እናቶች ምስክር እንደሚሆኑ የተናገሩት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ በቤተ እምነት ውስጥ ሳይቀር ምሽጉን አድርጎ ሕዝብ ለማስፈጀት ሲጥር የነበረው ደግሞ ሌላው ጎራ ነው ብለዋል። እነዚህ አካላት እምነት አልባና ክፉ ሀሳብ ያላቸው ይሁዳዎች ናቸው። ምክንያቱም በሕዝብ ውስጥ መሸሸግና እርስ በርስ ማጠላላት ዋነኛ ተግባራቸው መሆኑን ገልጸዋል። የትግራይ ሕዝብ ይህንን አደረገ ብሎ ከአማራው ጋር ለማጋጨት ብዙ እኩይ ተግባራትን ሲፈጽሙ እንደነበር አመልክተው፣ ሕዝቡ ይህንን ተረድቶ ከሥራቸው ታውቋቸዋላችሁ እንደተባለው ሊያውቃቸው ይገባል ብለዋል። ምንም በማያውቁት በጁንታው ቡድን ለሞቱት ሁሉ እግዚአብሔር ነብሳቸውን በአጸደ ገነት እንዲያኖረው የተመኙት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ፤ ሁኔታው የተደረገው ለኢትዮጵያውያን አስባለሁ ከሚል ለኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ እታገላለሁ ከሚል ቢሆንም ተግባሩ ይህ እንዳልሆነ በግልጽ ታይቷል። ይህን እኩይ ተግባሩም ጥቁር ጠባሳ ሆኖ ሲዘከር ይኖራል። አስተማሪ ሆኖ እንዲያልፍ ግን ሁሉም የበኩሉን ማድረግ እንደሚጠበቅበት አስታውቀዋል። ጁንታው ሃይማኖታዊ መሰረት የሌላቸው፣ ሰብዓዊ ርህራሄ ያልፈጠረባቸው ከግል አልፎ ለቡድን ጥቅምና ሥልጣን የሚስገበገቡና የሚጥሩ አካላት የሞሉበት እንደሆነ የሚያነሱት ጠቅላይ ጸሐፊው፤ 98 በመቶ ሃይማኖተኛ የሆነባት አገር ውስጥ ይህ ለምን ይሆናል የሚለውን እንደማይቀበሉትና እንደ ጁንታው ዓይነት ሃይማኖት አልባ ክፉ ቡድኖች መኖራቸውን ሁሉም ማሰብ እንደሚገባው ጠቁመዋል። እነዚህ አካላትም ሃይማኖትን እንደ ምሽግ እንደዋሻ የሚጠቀሙ ስለሆኑ እነርሱን ከሃይማኖት ጋር አስተሳስሮ ማንሳት ተገቢነት የሌለው ነውም ብለዋል። በማንኛውም ሃይማኖት አስተምሮ መግደል ሀጥያት ቢሆንም እነዚህ አካላት ግን ከመግደል ያለፈ ተግባር ፈጽመዋል ያሉት ሊቀትጉሃን ቀሲስ ታጋይ፤ ጉራፈርዳ ላይ በሄዱበት ጊዜ በንጹሀን ጭፍጨፋ የህወሓት ጁንታ እጅ እንዳለበት ነዋሪዎቹ እንዳስረዷቸው አስታውቀዋል። ይህ ዓይነት ተግባር በየቦታው እየፈነዳ ያለው ሰላም ከማይወዱ፣ ሁልጊዜ ሥልጣን ላይ ብቻቸውን መቀመጥ ከሚፈልጉ፤ ሌላው ሲሰራና ሲለወጥ የሚያማቸው፤ ከእነርሱ ውጭ በአገር ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይ እንዲኖር የማይፈልጉ በመሆናቸው እንደሆነ አስረድተዋል። እንደ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ገለጻ፤ እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያ ላይ ቢሳካላቸው ተረጋግተው የሚቀመጡ አይደሉም። አፍሪካ ብሎም ዓለምን በእኛ ሥር አድርገን ካልገዛን ከእኛ ውጪ መሆን የለበትም የሚሉና ጦርነት ለማንሳት የሚቃጣቸው ናቸው። በዚህም አሁን እንደ አገር የተሰራው ሥራ የአገርን ክብር ከመመለስም በላይ ነው። በተለይ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ከማስጠበቅ አኳያ ትልቅ ፋይዳ አለው። የጭፍጨፋው ምንጭ አላማው ከሥልጣን እኔ ለምን ገሸሽ ተደረኩ የሚል ነው። ከዚያ ውጪም በሥልጣን ላይ እያሉ ብዙ የተለመዱ ክፉ ተግባራትን ሲሰሩ መኖራቸው ሊያመጣባቸው የሚችለውን ተጠያቂነት ፍርሀትም ሌላው ምክንያት እንደሆነ ጠቁመዋል። ለአብነት ከሕግ ውጪ ፈላጭ ቆራጭ ነበሩ፤ በሕገወጥ መንገድ ሀብት ሲያከማቹ እንደነበር አስታውቀዋል። የእነርሱ ልብ በዲያቢሎስ እጅ የገባና የእርሱን አመራር የተከተለ ነው። የዲያቢሎስ የግብር ልጅ መሆን ደግሞ ፈሪሀ እግዚአብሔርን ከማስነጠቅም በላይ ሰብዓዊነት የሚባለው ነገር ትዝ እንዳይል ያደርጋል። ከጠንካራው ይልቅ ደካማውን እየመረጡ እንዲያጠቁና እናቶች እንዲያዝኑ አድርገዋል። ከዚያ ከፍ ሲልም በክፋት መንፈስ የተደፈነ ልብ ስለያዙ በአስከሬን ቀልደዋል እንደ ጀግና ፎክረዋል። ከተረዱት ተግባሩ የወራዳና ወራዳነት ምግባር ነው ብለዋል። እንደ ሊቀትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ማብራሪያ፤ እነዚህ አካላት አገር ከሀዲነት ብቻ አይገልጻቸውም። ከዚያ በላይ አገር የገደሉ ናቸው። ነጭ የደም ሴልን ገሎ አለሁ ማለት ከመሞት አይተናነስምና። ስለዚህም ሕዝቡ ከእነዚህ ተኩላዎች በሁለት ነገር መጠንቀቅ ይኖርበታል። የመጀመሪያው እነዚያ ክፉ ሰዎች የሰሩትን ተግባር ሕዝብ ለሕዝብ ጦርነት እንዲያውጅ በመፈለግ የተደረገ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ይህንን ዘግናኝ ተግባርም ሁሉም ማህበረሰብ በነቂስ ወጥቶ ማውገዝና እነርሱን እንደማይገልጽ ማስገንዘብ ይኖርባቸዋል። ሌላው እያንዳንዱ ሰው የእነርሱ ሽንፈት ማስፈጸሚያ እንዳይሆን መጠንቀቅ ይኖርበታል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37168
a8b17a6387ffe4a51085f99bd11b2b99
ee8a561dd540e30fb28c2402cc6f8e55
“የማይካድራውን የዘር ጭፍጨፋ የፈጸሙ ኃይሎች በምድራዊ ፍትህ ተመጣጣኝ ቅጣት አይገኝላቸውም”-ኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ
ሶሎሞን በየነ አዲስ አበባ:- በማይካድራ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ወንጀል የፈጸሙና ያስፈጸሙ ኃይሎች ተይዘው ለፍርድ ቢቀርቡ እንኳን በምድራዊ ፍትህ ተመጣጣኝ ቅጣት እንደማይገኝላቸው ኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ አስታወቁ።ኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ የማይካድራ ጭፍጨፋን አስመልክተው በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በማይካድራ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ወንጀል የፈጸሙና ያስፈጸሙ ኃይሎች ተይዘው ለፍርድ ቀርበው ተገቢውን ፍትህ ማግኘት እንደሚገባቸው ጠቁመው፤ ያም ቢሆን ግን እነዚህ ኃይሎች በንፁሃን ዜጎች ላይ የፈፀሙት የጅምላ ጭፍጨፋ በድርጊት አፈጻጸምም ሆነ በተጎዱ ሰዎች ብዛት፣ እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈፀሙ አሰቃቂ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ሁሉ በእጅጉ የከፋ አረመኔያዊ ተግባር ነው።ፈጣሪ በሰማይ ቤት ዋጋቸውን ይከፍላቸው ካልሆነ በስተቀር ተይዘው ለፍርድ ቢቀርቡ እንኳን በምድራዊ ፍትህ ተመጣጣኝ ቅጣት አይገኝላቸውም ያሉት ኡስታዝ አብዱልገፋር፣ የእስልምና ሃይማኖት አስተምሮ አላህ! “አንተ ሰላም ነህ፤ ሰላምም ከአንተ ነው” በሚል እንደሚጀምር አስታውቀዋል።በአንድ ፈጣሪ ስር ያሉ ሁሉም ፍጡራን የእርሱን ህግና ስርዓት ተከትለው ተናበውና ተሳስበው በሰላም እንዲኖሩ እምነቱ ያዛል ያሉት ኡስታዝ አብዱልገፋር፤ በመሆኑም አይደለም ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ቀርቶ አዕዋፍን፣ እንስሳትን፣ ነፍሳትን ወዘተ በምድር ላይ ህይወት ያለውን ሁሉ ያለምንም ምክንያት መንካት፣ ማሰቃየት፣ ማንገላታት፣ መምታት፣ መግደል በእስልምና አስተምሮ የተወገዘ መሆኑን አመልክተዋል።ከዚህ አንጻር በማይካድራ ከተማ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ወንጀል ጠንካራ እምነት እና ፈጣሪያቸውን ይፈራሉ ከሚባሉት ኢትዮጵያዊያን ቀርቶ ከኢ-አማንያን የማይጠበቅ አረመኔያዊ ተግባር መሆኑን ኡስታዝ አብዱልገፋር ገልጸው፤ በማይካድራ የተፈጸመው ጥቃት “ክስተቱ እጅግ አስደንጋጭ ይሆናል ተብሎ የማይገመትና በሰው ዘር ላይ የተፈጸመ አረመኔያዊ ድርጊት ነው” ብለዋል። “አይደለም በጅምላ ሰዎችን መግደል ቀርቶ የአንድን ሰው ህይወት በምንም አይነት ምክንያት ተነሳስቶ ማጥፋት በአላህ ዘንድ ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ ከዚህ በፊት የሞቱትን፣ በህይወት ያሉትንና ለወደፊትም የሚፈጠሩትን የሰው ልጆች ሁሉ እንዳጠፋ ተደርጎ የሚቆጠር ነው” ያሉት ኡስታዝ አብዱልገፋር፤ “ጭፍጨፋው ዘርንና ማንነትን መሰረት ያደረገ፤ በገመድ በማነቅ፣በስለት በመውጋትና በሌሎች መሰል አሰቃቂ መንገዶች መፈጸሙ ባለፉት አመታት አገሪቱ የተገነባችበትን የጥላቻና የቂምበቀል ፖለቲካ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ እንደሆነ አመልክተዋል። ድርጊቱ ከሞራልም፣ ከሰብአዊነትም፣ ከምድራዊም ሆነ ከሰማያዊ ህግ አንጻር የተወገዘ ነው ያሉት ኡስታዝ አብዱልገፋር፤ ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት በንጹሃን ላይ የፈጸሙ ኃይሎች ከምስረታቸው ጀምሮ ውስጣቸው በክፋት የተጠነሰሰ፣ ሃይማኖት የሌላቸው፣ ሰብዓዊነት የማይሰማቸው፣ በጥላቻ፣ በቂም፣ በምቀኝነት፣ በክፋት መንፈስ የሰከሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በንጹሃን ዜጎች ላይ ይህን አሰቃቂ ድርጊት የፈጸሙ ኃይሎች ተይዘው ለፍርድ ቀርበው ተገቢውን ፍትህ ማግኘት እንደሚገባቸው ቢያምኑም፤ እነዚህን ኃይሎች ዓላህ በሰማይ ቤት ዋጋቸውን ይከፍላቸው ካልሆነ በስተቀር ተይዘው ለፍርድ ቢቀርቡ እንኳን በምድራዊ ፍትህ ተመጣጣኝ ቅጣት እንደማይገኝላቸው ገልጸዋል። የድርጊቱ መንስኤ ባለፉት ዓመታት እንደዋዛ የተረጩ የጥላቻና የቂም በቀል አስተምሮዎች፣ የትምህርት ፖሊሲው፣ ወጣቱ በስነ ምግባር አለመቀረጹ የመሳሰሉት ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑ ጠቅሰው፤ ይህን አሰቃቂ ወንጀል የፈጸሙ ኃይሎችን አድኖ ህግ ፊት የማቅረብ ሂደቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ጥፋቱ እንዳይደገም የአገሪቱ አንድነትና የህዝብ ደህንነት ያገባኛል የሚል ማንኛውም የማህበረሰብ ክፍል በችግሩ መንስኤና መፍትሄው ላይ ፍርጥርጡን አውጥቶ ተወያይቶ ዘላቂ መፍትሄ ማስቀመጥ፣ የትምህርት ፖሊሲውን መፈተሽ፣ ወጣቱን በስነ ምግባር ማስተማርና ማረቅ፣ ህብረተሰቡን ከቂምና ከጥላቻ ፖለቲካ አላቆ በአዲስ መልክ መገንባት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37169
02c27f73ec66e0cba44d904869c39102
4c32cc4d3d1d74f75fe747b2dcde9c55
በአማራ ክልል በመኸር ወቅት 65 በመቶ ምርት መሰብሰቡ ተገለጸ
ወርቅነሽ ደምሰው አዲስ አበባ፡- በዘንድሮ ዓመት በአማራ ክልል በመኸር ወቅት በሰብል ከተሸፈነው 4ሚሊየን 282 ሺህ 517 ሄክታር መሬት እስካሁን 65 በመቶ ያህሉ ምርት መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግሥቴ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በክልሉ በዘንድሮ ዓመት በመኸር ወቅት 4ሚሊየን 282ሺህ 517 ሄክታር መሬት በሰብል የተሸፈነ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት ወደ 2ሚሊየን 800 ሺህ156 ሄክታር መሬት (65 በመቶው) የደረሰ ምርት መሰብሰብ ተችሏል።በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሆነ የሰብል አሰባሰብ የሚካሄድበት ወቅት እንደመሆኑ፤ በተለይም ለዘር የሚሆኑ የጤፍ፣ የስንዴና የበቆሎ ምርጥ ምርቶች ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተስፋሁን፤ ለዚህም የደረሱ ሰብሎች ለመሰብሰብ የሚረዱ 104 የሚሆኑ ኮምባይነሮችን በመጠቀም ሰብል እየተሰበሰበ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በኮምባይነሮች ከ19ሺህ 481 ሄክታር በላይ ማሳ ላይ ያለ ሰብል የታጨደ ሲሆን፤ ከዚህም 715 ሺህ 698 ኩንታል ምርት ተሰብስቧል። ኮቪድ ጋር ተያይዞ ሰብል አሰባሰብ ሂደት በርካታ የሰው ኃይል ለመጠቀም አስቸጋሪ መሆኑ ኮምባይነሮቹ እጅግ ጠቃሚ ናቸው የሚሉት ምክትል ኃላፊው፤ በተለይ በኩታ ገጠም በሆኑ ማሳዎች ላይ የተዘሩ ሰብሎችን ለመሰብሰብ ኮምባይነሮቹ ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑን ተናግረዋል።ይሄም በሰው ጉልበት ከ10 እስከ 20 ቀናት የሚወስድ የምርት አሰባሰብ ሂደት ከአንድ እስከ ሁለት ባሉት ቀናት ውስጥ እንዲሰበሰብ ማድረግ ማስቻሉን ተናግረዋል። ክልሉ ዘንድሮ በኮቪድ ወረርሽኝ፣ በአንበጣ መንጋ፣ በጎርፍ ክስተት፣ በመሬት መንሸራተትና በጦርነት ውጥረት ውስጥ ከመቆየቱ አኳያ የሰብል አሰባሰብ ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን የገለጹት አቶ ተስፋሁን፤ ደጋማ የሆኑ አካባቢዎች ያሉ ሰብሎች ገና ያልደረሱ በመሆናቸውም አጠቃላይ የሰብል ስብሰባውን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች በልማት ግንባር እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።ሂደቱም በየቀኑ እየተገመገመ ስለሆነ አፈጻጸሙ ጥሩ መሆኑን ተናግረዋል።እንደ አቶ ተስፋሁን ገለጻ፤ በወቅታዊ የሀገራዊ ጉዳይ ከክልሉ ለህግ ማስከበር ዘመቻ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ሰብል ለመሰብሰብ በተደረገ ጥረት 24ሺህ 845 ተሳታፊዎች በማሳተፍ 84 ሺህ ሦስት መቶ 97 ሄክታር መሬት ምርት ተሰብስቧል።ለአብነትም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደርና ምዕራብ ጎጃም ሰብል ከመሰብሰብ አልፎ እስከ መውቃት ድረስ ባለ ቁርጠኝነት እየተሰበሰበ ሲሆን፤ አሁን ላይ ለህግ ማስከበር ዘመቻው ከሄዱት ውስጥ አንዳንዶቹ እየተመለሱ መሆኑንም ጠቁመዋል።በዘንድሮ የምርት አሰባሰቡ ላይ ከኮቪድ ቫይረስ ጋር ተያይዞ የታየውን ችግር መነሻ በማድረግ አልፎ አልፎ የጣለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በመኖሩ የደረሱ ሰብሎች እንዳይበላሹ ቀደሞ ለመሰብሰብ እንዲቻል ከግብርና ባለሙያዎች ጋር በመወያየት መሰራቱን አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል። ዋና ዋና የደረሱ ሰብሎችን ቀድሞ መሰብሰብ እንጂ እንደድሮ ከምሮ ማስቀመጥ እንደማያዋጣ ጠቁመው፤ የተሰበሰበው ሰብል እንደደረቀ ወቅቶ ምርቱን መሰብሰብ በአውድማ ቦታ የሚፈጠሩ ችግሮችን ስለሚቀንስ ከድሮ በተለየ መልኩ ሰብሉን ቶሎ ለማስገባት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።እንደ አቶ ተስፋሁን ገለጻ፤ አርሶ አደሩ ሰብሉን ሲሰበስብ ድግስ በማብዛት ወይም ተረጋግቶ ከመሰብሰብ አልፎ ያለንበትን ሁኔታ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ካጨደ በኋላ በፍጥነት ወቅቶ ሰብሉን በእጁ መያዝ አለበት። ምክንያቱም ይሄን ሲያደርግ በምርቱ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ በተባይ መበላት፤ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ መታደግ ይችላል። ይህ እንዲሆን ደግሞ በየደረጃው ያለ የግብርና ተቋምና ባለሙያዎች እገዛ ማድረግ እንዳለባቸው ነው አቶ ተስፋሁን ያሳሰቡት።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37175
c1705fb4d2b2c225d2ee40d9a7088e9a
3fb9620c0131d312cc0de9766f2e81f7
በትግራይ ክልል የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች ስርጭት እንደሚካሄድ ተገለጸ
አንድ ሚሊየን ለሚጠጉ ስደተኞችም ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዘ ሲሆን፤ ከዛሬ ጀምሮም ይሰራጫል ተብሏል። በተያያዘም አንድ ሚሊየን ለሚሆኑ ስደተኞች አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ተገልጿል።መድኃኒቱና የሕክምና መገልገያው ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ወደ መቀሌ፣ አዲግራትና ሽሬ ከተሞች በመጓጓዝ ላይ መሆኑ ታውቋል። በስፍራው እንደደረሰም በተለያዩ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች የሚሰራጭ ይሆናል። ወደ ስፍራው በመጓጓዝ ላይ ካሉት መድኃኒቶች መካከል ለስኳር ሕሙማን እንዲሁም ለእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶች ይገኙበታል።የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎቹ ስርጭት በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ በኩል በመጓጓዝ ላይ መሆኑ ታውቋል። ከዚህ ቀደም ለምዕራብና ደቡባዊ የትግራይ ዞኖች በአማራና አፋር የኤጀንሲው ቅርንጫፎች በኩል መድኃኒት መሰራጨቱ ይታወቃል።በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የእለት ደራሽ ምግብና የተለያዩ ቁሳቁሶች በመዳረስ ላይ ሲሆኑ፤ የዕለት ደራሽ እርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት ከ12ሺ በላይ ኩንታል ስንዴ በ30 የጭነት መኪናዎች አማካኝነት ወደ መቀሌ የተጓጓዘ መሆኑ ይታወቃል።የመሰረተ ልማት ተቋማት መልሶ ግንባታ እየተካሄደ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም የኤሌክትሪክና የቴሌኮም አገልግሎት ወደ ስራ እየገቡ መሆኑም ታውቋል።በተያያዘ ዜና፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የስደተኛ መጠለያ ውስጥ ለሚገኙ ከተለያዩ አገራት ማለትም ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራና ከሱዳን ተሰደው ለመጡ ሰዎች በ26 የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወደ አንድ ሚሊየን ለሚጠጉ ስደተኞች አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።ኢትዮጵያ በምትከተለው ፖሊሲ አንጻር ስደተኞች ከስደተኞች መጠለያ ወጥተው ህግን በተከተለ አሰራር በፈቀዱት ቦታ እንዲኖሩ እያደረገች በመሆኗ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊየን በላይ ስደተኞች ተጠልለው እንደሚገኙ መረጃው አመላክቷል።ሆኖም የተሳሳተ መረጃ በመያዝ ኤርትራውያን ስደተኞች ከማይ ዓይኒ እና ሀሩሽ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ህጋዊ አሰራርን ሳይከተሉ ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያው የገለጸው። በአሁኑ ወቅት የህግ ማስከበር ዘመቻው በተጠናቀቀበት ትግራይ ክልልም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የስደተኛ ማቆያዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በሰላማዊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አመልክቷል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37181
38cea2c9f67a34dbdefc7e01e9b1dff3
36e1f77ada3ed983522ac57275c8b5cc
ኤጀንሲው ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ላደረጉ 22ሺ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር አስታወቀ
ሞገስ ተስፋአዲስ አበባ፡- በተያዘው በጀት ዓመት ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ላደረጉ 22ሺ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር የፌዴራል ከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ገለጸ።የፌዴራል ከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ አቦዘነች ነጋሽ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ኑሯቸውን ጎዳና ላይ አድርገው ሕይወታቸውን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገፉ 22ሺ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጠራል።የፌዴራል ከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና በፓይለት ፕሮጀክት ለዜጎች የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ሰፊ ሥራ እየሰራ መሆኑን አመልክተው፤ ከዚህም ጎን ለጎን ኑሯቸውን ጎዳና ላይ ላደረጉ ዜጎች አስፈላጊ የሚባሉ ሥልጠናዎች እንደሚሰጡ አስታውቀዋል። ባለፈው ዓመት ስድስት ሺ ለሚሆኑ ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ላደረጉ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የገለጹት ኃላፊዋ፤ ዘንድሮ ግን ክፍተቶች በጥናት ተለይተው ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን፣ ከመንግሥትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የጋራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።በተለይ በሥራ ዕድል ፈጠራ ትግበራው ላይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ የሚከታተል ኮሚቴ የሚመለከታቸውን አካላት በማካተት መቋቋሙን የጠቆሙት ወይዘሮ አቦዘነች፤ ፕሮጀክቱን በበላይነት የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደሚመራው አስታውቀዋል።ባለፉት አምስት ዓመታት በአጠቃላይ ለ604ሺ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ገልፀው፤ በተያዘው በጀት ዓመትም በሀገሪቱ ባሉ 83 ከተሞች የከተማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በመዘርጋት 480 ሺ 880 ዜጎች በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሯ ገልፀዋል።
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37186
6635d51e88b0befc7bcc6545d4638f64
e74f6d544b227b7ff92ae4f8a9f0471b
የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር ከአክሲዮን ሽያጩ ቃል ከተገባለት ውስጥ ስድስት ቢሊዮን ብር መከፈሉን ገለጸ
ፍሬህይወት አወቀ አዲስ አበባ፡- በምስረታ ላይ ያለው የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር ከአክሲዮን ሽያጩ ቃል ከተገባለት ስምንት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ውስጥ ስድስት ቢሊዮን ብር መከፈሉን ገለጸ።ማህበሩ ባለ አክሲዮኖች ውክልና እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል። የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መላኩ ፈንታ፣ የማህበሩ የአክሲዮን ሽያጭ መጠናቀቁን አስመልክተው እንደተናገሩት፤ የአክሲዮን ሽያጩ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ከአክሲዮን ሽያጩ ቃል የተገባለት ስምንት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር እንደሆነና ከዚህ ውስጥም ስድስት ቢሊዮን ብር መከፈሉን ተናግሯል። ከአገልግሎት ክፍያ ጋር በተያያዘም አራት መቶ ሁለት ሚሊዮን ብር መገኘቱን አስታውቋል።በአክሲዮን ሽያጩ ላይ መንግሥት አስተዋጽኦ እንደነበረው የጠቀሱት አቶ መላኩ፤ ባንኩ የሕዝብ እንደመሆኑ በአክሲዮን ግዥው ሁሉም ብሔር ብሔረሰብ ተሳታፊ እንደነበር አመልክተዋል። ኅብረተሰቡን ጨምሮ በሽያጩ ላይ ተሳታፊ ለነበሩ አስር ባንኮችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።ይሁን እንጂ የባለአክሲዮኖች ውክልና አሰጣጥን በተመለከተ ከኅዳር አንድ እስከ ኅዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም የውክልና አሰጣጡ በሰነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ መሰጠቱን ያነሱት አቶ መላኩ፤ ከ185 ሺ ባለአክሲዮኖች መካከል 75 ሺ ወይም 41 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ብቻ ውክልናቸውን የሰጡ መሆናቸውንም አመልክተዋል። ለዚህ ደግሞ ባለአክሲዮኖች ወይም ወኪሎች በአካል ተገኝተው ውክልና የሚሰጡበት የንግድ ሕግ ቢኖርም ወቅታዊ ሁኔታው ለዚህ ምቹ አለመሆኑን ገልፀዋል።ሆኖም በተቀመጠው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ባለአከሲዮኖች ሙሉ በሙሉ ውክልና መስጠት ያልቻሉና ይህም ምስረታውን ወደ ኋላ እየጎተተው እንደሆነ ያነሱት አቶ መላኩ፤ ባለአክሲዮኖች እስከ ታኅሣሥ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ውክልናቸውን እንዲሰጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። የባንኩ አደራጅ ጊዜውን ሰውቶ እያገለገለ እንደመሆኑ፣ ባለአክሲዮኖችም የአንድ ቀን ጊዜ ወስደው በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ በሰነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ በመገኘት ውክልናቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። የውክልናውን ሂደት ተከትሎም ጉባኤው የሚካሄድበትን ጊዜ የሚያሳውቁ መሆኑን ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37180
a42aca4c5fc62ecbdb687d27a2e1e0f7
296c5b62524d0f434eab00106dc7fbc5
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአሠልጣኝ ሳላዛር እንዲርቁ ተጠየቀ
እኤአ 2015 የቢቢሲ ፓናሮማ የተሰኘው ፕሮግራም በአሜሪካ የሚገኘው የናይኪ ኦሪገን የአትሌቲክስ ማሰልጠኛን በተመለከተ ያቀረበው ዘገባ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ነበር። ከአሜሪካው ፕሮፑብሊካ ድረ ገፅ ጋር በጋራ በመሆን በተሰራው በዚህ ፕሮግራም ላይ በአትሌቲክስ ማሰልጠኛው በከፍተኛ ሁኔታ የአበረታች መድሃኒት እንደሚሰጥ በተደረገው ምርመራ እንደተደረሰበት አጋልጧል። በማሰልጠኛው ተገቢነት ያልሆኑ ተግባራት እንደሚካሄዱም ዘገባው በወቅቱ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም። እኤአ ከ2011 ጀምሮ የፕሮጀክቱ አስተዳዳሪ የነበሩት አሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር የመጀመሪያ ተጠያቂ አድርጎ ዘገባው አቅርቧቸዋል። አራት የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሸናፊ የሆነው እንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ የዚህ ማዕከል ፍሬ መሆኑን የምርመራ ዘገባው መጠቆሙን ተከትሎ ጉዳዩ ከስፖርትም በዘለለ ሊጦዝ ችሏል። የፓናሮማ ዘገባን ተከትሎ የአሜሪካው የፀረ አበረታች መድሃኒት ኤጀንሲ ጉዳዩን በመያዝ የ61 ዓመቱ ሳላዛር ፍርድ ቤት ሳይውል ሳያድር እንዲቆም አድርጓል። ኤጀንሲው ሰውዬውን ተጠያቂ ለማድረግም መረጃዎችን በማሰባሰብ ዓመታትን ተሻግሯል። የተለያዩ መረጃና ማስረጃዎችንም ሲያሰባስብ ቆይቷል። የአሰልጣኙ ጉዳይ በተለይ ከ ሞፋራህ ጋር የተያያዘ መሆኑ በብዙ መልኩ አነጋጋሪ መሆን የቻለ ሲሆን ከትናነት በስቲያ በኤጀንሲው ይፋ የተደረገው መረጃ ጉዳዩን እንደ አዲስ መነጋገሪያ አድርጎታል። ቢቢሲ የኤጀንሲውን መረጃ ዋቢ አድርጎ አሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር ከአራት ዓመት ምርመራና ከሁለት ዓመት የፍርድ ቤት ክርክር በኋላ ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን ዘግቧል። አሰልጣኙ የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን ከቦታ ቦታ ማዘዋወርን ጨምሮ የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴውን በማወክ እና በተለያዩ የፀረ-ዶፒንግ የህግ ጥሠቶች እንደፈጸመ መረጋገጡን አስታውቋል። የዩኬ ስፖርቶችን የሚቆጣጠረው ዩኬ አትሌቲክስ፣ የራሱን ምርመራ ማካሄዱን የጠቀሰው ዘገባው፤ በናይክ እየተከፈላቸው በርካታ የሳላዛር አትሌቶችን የሚያክሙት ዶክተር ጄፍሪ ብራውን ደግሞ ለአራት ዓመት መታገዳቸውን ዘግቧል። ቢቢሲ የሞ ፋራህ ቀድሞ አሠልጣኝ፣ አልቤርቶ ሳላዛር፣ ከአበረታች መድሀኒት ጋር በተያያዘ ከስፖርት ለአራት ዓመት መታገዱን ባስነበበው በዚህ ዘገባው፤ ፋራህ ከሳላዛር ጋር የተለያየው በ2017 መሆኑን ጠቅሶ ከአበረታች መድሃኒት ጋር በተያያዘ አለመሆኑን ገልጿል ከማለት ውጪ፤ ፋራህ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ጥፋተኛ ይሁን አይሁን ምንም ያለው ነገር የለም። ከተለያዩ አገራት አትሌቶች ጋር በቅርበት እንደሚሰራ የሚነገርለት አሰልጣኝ ሳላዛር ጥፋተኝነትን ተከትሎ አገራት አትሌቶቻቸውን ከአሰልጣኙ እንዲርቁ እያስገነዘቡ መሆኑም ተሰምቷል። ኢትዮጵያዊያን አሰልጣኞችና የስፖርት ባለሙያዎችም ከአሠልጣኙ ሊርቁ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅህፈት ቤት በላከው መግለጫ አስታውቋል። «ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና የስፖርት ባለሞያዎች ከአሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር ጋር የሚኖራቸውን ቀጥተኛም ይሁን ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት ማቋረጥ አለባቸው» ሲልም አሳስቧል። በአለም ዓቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ህግና በአገራችን የፀረ- ዶፒንግ መመሪያ አንቀፅ 2 ነጥብ 10 መሠረት በህግ ጥሰት ቅጣት ከተላለፈባቸው ግለሰቦች ጋር ያልተገባ ግንኙት መፍጠር በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣትን እንደሚያስከትል አስገንዝቧል። የአገራችን አትሌቶች በተለያየ መልኩ ከአሠልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር ጋር እንደሚሠሩ የገለጸው ጽህፈት ቤቱ፤ በግለሰቡ ላይ የተጣለው ይህ የቅጣት ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ያላቸውን ቀጥተኛም ይሁን ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት እንዲያቋርጡ ጥሪውን አስተላልፏል። ከዚህ ባሻገር የስፖርት ባለሞያዎችም ይሁን ሌሎች አካላት ከዚህ ግለሠብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማቋረጥ እንደሚኖርባቸው አስገንዝባል። «ስፖርተኞችም ይሁን ሌሎች ባለሞያዎች የተቀመጠውን ህግ በመተላለፍ ቀደም ሲል የነበራቸውን ግንኙነት ለማስቀጠልና አዳዲስ ግንኙነቶችን ለመፍጠር እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ከሆነ ፅህፈት ቤታችን ጉዳዩን በማጣራት አስፈላጊውን የህግ እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል» በማለት ፅህፈት ቤቱ ሁሉም አካላት የፀረ-ዶፒንግ ህጎችን በማክበርና በማስከበር ንፁህ ስፖርትን ለማስፋፋት ጥረት ማድረግ እንደሚገባም አብራርቷል።አዲስ ዘመን መስከረም 22/2012ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=19910
966b502ad483af2fba04563d85963a76
61f3b44bdb05ca6a80e8857f9b35b92c
«ወንጀለኛው ጁንታ ዋናው ዓላማው ኢትዮጵያን ማፈራረስና ለዓመታት ይዞ የቆየውን የዝርፊያ ፍላጎቱን ማስቀጠል ነበር» አቶ ብናልፍ አንዷለም የብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
ማህሌት አብዱልአዲስ አበባ፡- ወንጀለኛው ጁንታ ዋነኛ ዓላማውና የሴራው ማጠንጠኛ ኢትዮጵያን በማፈራረስ የራሱን የአገዛዝ ሥርዓት በማስቀጠል ይዞ የቆየውን የአፈናና የዝርፊያ ፍላጎት ማስቀጠል እንደነበር የብልጽግና ጽሐፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ገለፁ። አቶ ብናልፍ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት፤ ወንጀለኛው ጁንታ ከዝርፊያ ውጪ ሌሎች መንገዶችን ማየት የማይችልና የራሱንም ሃሳብ መልሶ የሚክድ የማፍያ ቡድን ነው። ለምሳሌ ቀደም ሲል በኢህአዴግ ውስጥ በጋራ አንድ አጀንዳ ላይ ተወያይቶና ውሳኔ ካሳለፈና የውሳኔዎቹ ሃሳብ በመግለጫ ከወጣ በኋላ፣ ለብቻው ወጥቶ እንደገና ሌላ መግለጫ ያወጣል።በወቅቱ የሚያወጣው መግለጫ ደግሞ የኢህአዴግን ውሳኔ የተቃረነ ነበር። በጋራ መድረክ ተስማምቶ ሲያበቃ ለብቻው መግለጫ ካወጣባቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ውዝግብ ወደ እልባት እናምጣው የሚለው አጀንዳ ይጠቀሳል። የፕራይቬታይዜሽን ጉዳይም ሌላው አወዛጋቢ ጉዳይ ሲሆን፤ የልማት ድርጅቶችን ደረጃ በደረጃ አዋጭነታቸው እየታየ አንዳንድ ተቋማት ወደ ግል ሴክተር እንዲዛወሩ የተወሰኑ ውሳኔዎችንም አብሮ ነበር የወሰነው። ይህንንም በጋራ ከወሰነ በኋላ በሚቀጥለው ቀን በመቃወም እንደገና መግለጫ አውጥቷል።ከዚህም ውጪ በሀገሪቱ የተካሄደውን የፖለቲካ ሪፎርም ለማደናቀፍ ጁንታው በከፍተኛ ሁኔታ ሲንቀሳቀስ እንደነበርም አቶ ብናልፍ ተናግረዋል። ለአብነትም፣ ኢህአዴግ የሚመራበት አብዮታዊ ዴሞክራሲ በሚል ፍልስፍና ርዕዮተ ዓለም ደግሞ ጠላትና ወዳጅ ብሎ የሚለይ ነው። ሰዎችን በአመለካከታቸው ብቻ ይሄኛው ጠላቴ ነው፤ ሌላኛው ደግሞ ወዳጄ ብሎ የሚያስቀምጥ መሆኑ በሕዝቦች መካከል የጥላቻ ግድግዳ ፈጥሮ ኖሯል። ይህ አስተሳሰብ እንዲስተካከል ግን ፈጽሞ ፍላጎት አልነበረውም።የሚገርመው ግን ጠላት ወይም ወዳጅ ከሚለው ውጪ ሌላ ሦስተኛ መንገድ አለ ብሎ አለማመኑ እንደሆነ የገለፁት አቶ ብናልፍ፤ በዚህ ርዕዮተ ዓለም አንድ ዜጋ ምንም ዓይነት አስተሳሰብ ይኑረው ገለልተኛ ሆኖ መኖር አይፈቀድለትም ብለዋል። ይህም አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲካ ንቃት፤ የአገሪቱ የዓለምአቀፍ ሁኔታ በፍፁም አያስኬድም የሚል አቋም በአብዛኛዎቹ የለውጡ ኃይሎች ዘንድ ተይዞ እንደነበር እና ጁንታው ግን ይህ ሊዋጥለት እንዳልቻለ ተናግረዋል።እንደ አቶ ብናልፍ ገለጻ፤ ጁንታው በኢኮኖሚ ረገድ በመላ አገሪቱ በሚባል ደረጃ ኢፍትሃዊ የሆነ አሠራር ነበር ሲከተል የነበረው። ይሄ ቡድን በሁለት ዓይነት መንገድ ነበር ኢ-ፍትሃዊነቱን ሲያስፋፋ የነበረው። አንደኛው ሕጋዊ የሆኑትን የመንግሥት ተቋማት በመጠቀም ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በልማት ድርጅቶች አማካኝነት የሚደረግ ዘረፋ ነው። ለምሳሌ በአማራ ክልል የመንገድ ፕሮጀክቶችን የሚመሩት የጁንታው አካላት ስለነበሩ እንዲህ ዓይነት ፕሮጀክቶች በሚያዙበት ጊዜ ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ይካሄድ እንደነበር አቶ ብናልፍ ጠቅሰዋል።በኢንቨስትመንት ሰፋፊ የእርሻ ቦታ ባላቸው አካባቢዎች ላይ የእነሱ ተላላኪ፣ የእነሱ ዘመድ፣ የእነሱ የቅርብ አስፈፃሚ የሆኑ ሰዎችን የኢንቨስትመንት ፍቃድ እንዲያወጡ አድርገው በኢንቨስትመንት ስም እርሻ እንዲወስዱ ሲያደርጉ እንደነበር በመጥቀስ፤ ቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ክልሎች ላይ የፈፀሙት ምዝበራ ለዚህ አብነት የሚሆን ማሳያ ነው ብለዋል።አቶ ብናልፍ እንዳሉት፤ ይህ ቡድን በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በራያና በመሳሰሉት አካባቢዎች ያሉ ሕዝቦች ድምጽ እንዳይሰማ አጀንዳ እያስቀየረ ነው የኖረው። አሁን የተፈጠረው አዲሱ ነገር ጥያቄው ከዚህ በኋላ መታፈን አይችልም የሚለው ነው። ይሄ አፋኝ ቡድን ላይመለስ ወደመቃብሩ ወርዷል፤ ስለዚህ የመጨረሻ የሞት ሞት ያደረጉት ትግል ይህንን የሕግ ማስከበርና አገር የማዳን ዘመቻ የመሬት ማስመለስ ዘመቻ ነው በሚል አገናኝተው ቀላል የማይባል መደነጋገሪያ ፈጥረዋል። ሆኖም ሃቁና እውነቱ ተደብቆ አይቆይም።ሆኖም የእነዚህ ሰዎች ጥያቄ የመብት ጥያቄ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። እዚያ አካባቢ ያለ የእርሻ መሬትም በተግባር ሄዶ ሲታይ አማራም ሆነ ትግሬ ሄዶ ሊያርስ ይችላል፤ ዋናው ነገር እሱ አይደለም፤ ዋናው ነገር የሰው ልጆች ክብር ነው፣ ብለዋል አቶ ብናልፍ።የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች በመከፋፈልና በጠላትነት እንዲተያዩ በማድረግ በጋራ የመሰረቱትን የአንድነት እሴታቸውን እያፈረሰ በልዩነቶቻቸው ላይ ሲሰራ እንደኖረና የልዩነቶቻቸው አንኳር አድርጎ የወሰደው ደግሞ አማራ የሚባል ጨቋኝ ብሔር አለ የሚል ትርክት ላይ ተመስርቶ እንደሆነም አቶ ብናልፍ ጠቅሰዋል።አቶ ብናልፍ እንደገለጹት፤ ከነዚህ ሁሉ ሴራዎች ጀርባ የነበረው ደግሞ የደህንነት መዋቅሩ ነው። ይህ መዋቅር ወንጀለኛው ጁንታ ባስቀመጣቸው ሰዎች የሚመራ ስለነበር ሁሉም ነገር በምስጢር ነው የሚደረገው። አብዛኛው የፖለቲካ አመራር አያውቀውም ነበር። ለምሳሌ፣ ድብቅ እስር ቤቶች አሏቸው፤ ግን ሌላው አመራር አያውቃቸውም ነበር። እናም የሚፈልጉትን ሰው በድብቅ እስር ቤት ውስጥ አስገብተው ከፍተኛ የሆነ ኢሰብዓዊ ድርጊት ይፈፅሙባቸው ነበር።እንደሚታወቀው፣ ደግሞ በአብዛኛው እስር ቤት የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች በብዛት ነበሩ፤ የኦሮሞ ተወላጆችን ከኦነግ ጋር አብረው የሽብር ተግባር ሲፈፅሙ ነው የያዝኳቸው ይላል፤ በአማራ ክልል በኩል ያሉትን ደግሞ የግንቦት ሰባት ተላላኪዎች ናቸው እያለ ነበር መከራና ግፍ ሲያደርስባቸው የነበረው። አቶ ብናልፍ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሰራዊት የተሰጠውን ግዳጅ በጥንቃቄና በብቃት በመወጣቱ ሂደት ንፁሃን እንዳይጎዱ በማድረግ ረገድ ጥፋተኛውን ኃይል ብቻ ነጥሎ በመምታት ሕግን ለማስከበር የወሰደው እርምጃ ትልቅ አድናቆት ሊሰጠው የሚገባ ነው። በታሪክ መዝገብ ሊመዘገብ የሚገባ ትልቅ ክስተትም ነው።ከሃዲው ቡድን ሽንፈቱ አይቀሬ መሆኑን እየተገነዘበ ሲሄድ የያዛቸውንና ምሽግ የሰራባቸውን ቦታዎች እየለቀቀ በሚሄድበት ጊዜ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን እያፈረሰ እንደሄደ የጠቆሙት አቶ ብናልፍ፤ ለምሳሌ መከላከያ ሰራዊት አልፎና ተሻግሮ እንዳይሄድ መንገድ ሲቆርጥና ሲያፈርስ ነበር፤ አየር ማረፊያዎችን ከጥቅም ውጪ አድርጓል፤ ስልክና ኤሌክትሪክ የመሳሰሉትን መሠረተ ልማቶች ቆራርጧል፤ ብለዋል። እነዚህን መሠረተ ልማቶችም ተጠግነው ቶሎ አገልግሎት የሚሰጡበትን መንገድ ለመፍጠር እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37187
67f7fa7a529338dcf50deb182071c338
b6a2b362f7fbad9d11d86a286df71cf3
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሀገሪቱን የአሥር ዓመት ብሔራዊ ዕቅድ አጸደቀ
– የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ረቂቅ አዋጅንም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል በጋዜጣው ሪፖርተርአዲስ አበባ፡- የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ92ኛው መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን፤ በዚህ ውሳኔውም ኢትዮጵያን ወደ ዕድገት ማማ በማስፈንጠር አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን የሚያስችላት የኢትዮጵያ የአሥር ዓመት ብሔራዊ ዕቅድ ማጽደቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት፤ ዕቅዱ በተለይም በሰላም ግንባታ እና ተቋማዊ ሕዳሴ ላይ የሚያተኩሩ አሥር ምሰሶዎች አሉት። በተጨማሪም፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኅትመት እና የብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን መተዳደሪያ ሆኖ የሚያገለግለውን እና ለበይነ መረብ ሚዲያ የሕግ ማዕቀፍ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚተገበረውን የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል። የዘርፉን ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች የሚተነትነው አዋጅ፣ የመረጃ እና የፕሬስ ነጻነት ተግባራዊነትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚደግፍ ነው።የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በበኩሉ በፌስቡክ ገጹ እንዳመለከተው፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት በሁለት ጉዳዮች ላይ የተወያየ ሲሆን፤ የመጀመሪያው የልማት እቅድ ፍኖተ ካርታ ብልጽግና 2013 – 2022 ሰነድ ላይ ነው። የልማት መሪ እቅዱ አገር በቀል የልማት አቅጣጫን የተከተለ፣ በዘርፎች መካከል ሊኖር የሚገባውን ትስስር የሚያጎለብት፣ የቀጣይ አስር ዓመታት የሚያተኩርባቸውን የልማት ምሰሶዎች እና የትኩረት መስኮች የለየ ነው።ይህ ሰነድ፣ የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ የሚያስችል ብሎም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን ለማድረግና የአፍሪካ ብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን የሚያስችል እቅድ ነው። ይሄው እቅድ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን ተከትሎ በእቅዱ ላይ በመወያየትና ግብዓቶችን በማከል ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል።በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የመገናኛ ብዙኃን ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። ይህ ረቂቅ አዋጅ የዜጎችን ሃሳብ በነጻነት የመግለጽ መብት የሚያረጋግጥ፣ የመገናኛ ብዙሃን በተቋምነታቸው የአሰራር ነጻነት እንዲኖራቸው እና የሃሳብ ብዝሃነት የማስተናገድ አቅም እንዲያጎለብቱ የሚያስችል ነው። ከዚህ ባለፈ የቴክኖሎጂ እድገት የደረሰበትን የሚዲያና ብሮድካስት ቴክኖሎጂ እውቅና የሚሰጥ፣ በገለልተኝነት ዘርፉን የሚመራ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነ ተቋማዊ ስርዓት ማጎልበት የሚያስችል ነው። ምክር ቤቱም ረቂቅ አዋጁ ላይ በጥልቀት ተወያይቶ ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 3/213
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37174
f267b704577ebce4379e77b8a619d468
498568db91277d14cfe37932d8f15210
ፌዴሬሽኑ በአራት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ
 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከትናንት በስቲያ በተቋሙ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከጠዋቱ አራት ሰዓት እስከ ምሽት አንድ ሰዓት የቆየ ስብሰባ አድርጓል። በ2011 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የመጣው አመራር በቆይታው ምን ምን ጉዳዮችን ሰራ፣ ምንስ ሳይሰራ ቀረ እንዲሁም ሥራዎችን በምን ደረጃ ሲከታተል ቆየ በሚል አጠቃላይ ውይይት መደረጉን ፌዴሬሽኑ ገልጿል። ከዚህ ቀደም በተቋሙ የታዩ ክፍተቶች በምን ደረጃ መስተካከል ይኖርባቸዋል፣ በሥራ አስፈጻሚው መካከል የነበረው አለመናበብ እና በቀጣይ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት እንዲሁም የግል ግምገማ በማድረግ በአራት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መተላለፉን አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን የተሳታፊ ክለቦችን ቁጥር በተመለከተም ውሳኔ አስተላልፏል። ፌዴሬሽኑ መስከረም 05 ቀን 2012 ዓ.ም የውድድር ዓመቱ በሁለት ምድብ ተከፍሎ 24 ክለቦች እንደሚሳተፍ ያስተላለፈውን ውሳኔ በመሻር፤ በ16 ቡድኖች መካከል ውድድሩ እንዲካሄድና በምን አግባብ መመራት እንዳለበት ከክለቦች ጋር በቅርብ ውይይት እንዲካሄድ ውሳኔ መተላለፉን አስታውቋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ ሌላው በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን የገለጸው ፌዴሬሽኑ፤ በአንድ የውድድር ዘመን ሁለት ጊዜ ፎርፌ ለተጋጣሚ ቡድኖች የሰጠ ቡድን ከውድድር እንደሚሰረዝ አስታውቋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ባለፈው የውድድር ዓመት ሁለት ጊዜ በወጣለት መርሃ ግብር መሰረት ጨዋታዎች ላይ አለመገኘቱን ፌዴሬሽኑ ከታዛቢዎች ሪፖርት ተመልክቷል። በዚህም የሊግ ኮሚቴ ውጤቱን ለመወሰን የውድድር ክፍል በወቅቱ ባለማሳወቁ ውሳኔው ሂደት ያልጠበቀ እንዲሆን አድርጎታል ተብሏል። ስህተቱን በፈጠረው ሰራተኛ ላይ የዲሲፕሊን ቅጣት እንዲተላለፍበትም ተወስኗል። ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብም በፕሪሚየር ሊጉ እንዲቆይ እና በ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንዲወዳደር ውሳኔ ላይ መደረሱን በመግለጫው ተጠቅሷል። በአንደኛ ሊግ ተሳታፊ የነበረው ቦሌ ገርጂ እግር ኳስ ክለብ በፀጥታ ችግር ቡድኑ ወደ ጨዋታ ስፍራ መጓዝ ባለመቻሉ የተሰጠው ፎርፌ ቡድኑ እንዲሰረዝ ምክንያት እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ውድድር ክፍል ላይ በነበረው የአሰራር ክፍተት ቡድኑ አለመጓዙ ሥራ አስፈጻሚው ስለተረዳ ቡድኑ ላይ የተሰጠው ውሳኔ እንዲሰረዝ እና በአንደኛ ሊግ እንዲወዳደር መወሰኑን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። ሥራ አስፈፃሚው በእለቱ ውሳኔ የሰጠበት ሌላው ጉዳይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ይመለከታል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለኳታር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ወደ ሌሴቶ ሲያቀና ላጋጠመው እንግልት ምክንያት የሆኑ ሰራተኞች በጽህፈት ቤቱ በኩል በሰራተኞች አስተዳደር በዲሲፕሊን እንዲጠየቁ እንዲሁም በጽህፈት ቤት ኃላፊው የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው መደረጉ ታውቋል።አዲስ ዘመን መስከረም 22/2012ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=19916
8bef807bcd4b8bc6a6611b8dc29bef9b
5ebe622281648a071c818ac6b0df3fb3
የ10ሺ ሜትር ድልና ኢትዮጵያ ለ10 ዓመታት ተለያይተዋል
 በዓለም አትሌቲክስ ታሪክ አስር ሺ ሜትር ውድድር ለኢትዮጵውያን የተለየ ቦታ አለው። የዓለም ሕዝብም ይህን ርቀት የኢትዮጵያውያን የባህል ስፖርት አድርጎ እስከ መቁጠር ደርሷል። ማርሽ ቀያሪው ምሩፅ ይፍጠር በሞስኮ ኦሊምፒክ በርቀቱ ካስመዘገበው ድል አንስቶ ኃይሌ ገብረሥላሴና ቀነኒሳ በቀለ በኦሊምፒክም ይሁን በዓለም ቻምፒዮና ደጋግመው ድል በማድረግ ኢትዮጵያ የርቀቱ ንጉሥ መሆኗን አስመስክረዋል። ከምሩፅ ይፍጠር በኋላ ኢትዮጵያ በርቀቱ ንጉሥ ለማግኘት በርካታ ዓመታትን መጠበቋ ባይዘነጋም ከኃይሌ ገብረሥላሴ ጀምሮ የመጣው የአትሌቲክስ ትውልድ የርቀቱን የኢትዮጵያ የበላይነት አስጠብቆ ቆይቷል። እ.ኤ.አ 2011 ደቡብ ኮሪያ ዴጉ ካስተናገደችው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ወዲህ ግን ኢትዮጵያውያን ካለፉት ስምንት ዓመታት በላይ የርቀቱን ዙፋን ለሌላ አገር አትሌቶች ለማስረከብ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሯል። በዴጉው የዓለም ቻምፒዮና አትሌት ኢብራሒም ጀይላን እንግሊዛዊው ሞ ፋራህን መቼም በማይረሳ ሁኔታ ካሸነፈ ወዲህ ኢትዮጵያ በርቀቱ እንደቀድሞዎቹ ጀግኖች አልሸነፍ ባይና እስከ መጨረሻ ታጋይ አትሌት ለዓለም ማሳየት አልቻለችም። ይህም ሞ ፋራህ በርቀቱ በሦስት የዓለም ቻምፒዮናዎችና በሁለት ኦሊምፒኮች እንዲነግሥ ምክኒያት ሆኖታል። በነዚህ ዓመታት ኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ የጣለችባቸው ወጣትና ባለተሰጥኦ አትሌቶች በብዛት መፈጠር ቢችሉም የፋራህ ተከታይ ሆነው የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ከማጥለቅ በዘለለ የርቀቱን ክብር ወደ ቤቱ መመለስ አልተቻላቸውም። ፋራህ ካለፈው የለንደን የዓለም ቻምፒዮና በኋላ ከህመም ውድድሮች ራሱን ማግለሉን ተከትሎ ዓለማችን በአስር ሺ ሜትር ውድድር አዲስ ንጉሥ ስትጠብቅ ቆይታለች። ከለንደን ቻምፒዮና በፊትና በኋላ በርቀቱ ትልቅ ተሰጥኦ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወጣት አትሌቶች በብዛት መፈጠራቸውን ተከትሎ አስር ሺ ሜትር ዳግም የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዙፋን የመሆኛው ትክክለኛ ጊዜ እንደደረሰ በርካቶች ተስፋ አድርገው ነበር። ከትናንት በስቲያ በተጠናቀቀው የዶሃው የዓለም ቻምፒዮናም የትኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት የርቀቱን ዘውድ እንደሚደፋ በጉጉት ሲጠበቅ ነበር። ኢትዮጵያ በዚህ ርቀት ፈጣን ሰዓት ያላቸው ወጣትና ልምድ ያካበቱ አትሌቶችን ከማሰለፏም በላይ በርቀቱ ያላት ታሪክ ዳግም ወደ ድል የምትመለስበት ጊዜ አሁን እንደሆነ ብዙዎች እምነት አሳድረው ነበር። ልምድና ብቃት ከድንቅ የሩጫ ክህሎት ጋር የተላበሰው ሐጎስ ገብረሕይወት፣ ቁመተ መለሎው ባለተሰጥኦ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እንዲሁም ጠንካራው አትሌት አንዱዓምላክ በልሁ የርቀቱን ድል የመመለስ ተስፋ የተጣለባቸው አትሌቶች ናቸው። እነዚህ አትሌቶች እንዳላቸው ብቃት ተባብረው የቡድን ሥራ ሠርተው ድሉን ወደ ቤቱ ማምጣት ግን ሳይችሉ ቀርተዋል። ኢትዮጵያም የአስር ሺ ሜትር ድል ከእጇ ከወጣ ይህ አራተኛ የዓለም ቻምፒዮና ሊሆን ችሏል። ለአስር ዓመታት ከእጃችን ለመውጣት የተገደደው የአስር ሺ ሜትር ከዚህ በኋላ ለመመለስ ስንት ዓመት እንደሚፈጅ መገመት አይቻልም። ምክኒያቱም ዶሃ መልካምና የተሻለ አጋጣሚ ነበርና። በርቀቱ ተፎካካሪና ተመሳሳይ ታሪክ ያላት ኬንያም አልተሳካላትም። ያልተጠበቀውና ትኩረት ያልተሰጠው ዩጋንዳዊው አትሌት ጆሹዋ ቺፕቴጌ በዓለም ቻምፒዮና ታሪክ ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት በ26:48.37 አስመዝግቦ ለአገሩ አዲስ ታሪክ ፅፏል። ወጣቱና ወደ ፊት ባይባል እንኳን በቅርቡ ትልቅ ተስፋ እንዳለው ያስመሰከረው ዮሚፍ ቀጄልቻ በርቀቱ ገና ለሁለተኛ ጊዜ ቢወዳደርም 26:49.34 በሆነ ሰዓት የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ማስመዝገብ ችሏል። ይህም ኢትዮጵያ በቻምፒዮናው በሁለት ወርቅ፣አራት ብርና አንድ ነሐስ ሜዳሊያ ከዓለም አምስተኛ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ሆና እንድታጠናቅቅ አስችሏታል። ባለፈው መጋቢት በዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና በወጣቶች ምድብ ወርቅ ማጥለቅ የቻለው ዩጋንዳዊ ኮከብ ሆኖ ባመሸበት የዓለም ቻምፒዮና የመዝጊያ ውድድር ኬንያዊው ሮኔክስ ኪፕሩቶ 26:50.32 በሆነ ሰዓት የነሐስ ሜዳሊያ ሲያጠልቅ ለድል ሲጠበቅ የነበረው ሐጎስ ገብረሕይወት በ27:11.37 ሰዓት ዘጠነኛ ደረጃን ይዞ መፈፀሙ አስደንጋጭ ነበር። በአንፃሩ የርቀቱን ድል ለመመለስና የቡድን ሥራ ለመሥራት ጥረት ሲያደርግ የነበረው አንዱዓምላክ በልሁ 26:56.71 በሆነ ሰዓት አምስተኛ ደረጃን ይዞ ፈፅሟል።አዲስ ዘመን  መስከረም 27/2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=20279
d1177dee215d508e195aefd579b9dbff
b8fde660af1681300e9f7507f352768f
‹‹ኅብረተሰቡ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ትብብሩን ካጠናከረ የኦነግ ሸኔ መጥፊያው ሰዓት አጭር ይሆናል›› – ኮሚሽነር ጀኔራል አራርሳ መርዳሳ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
አስቴር ኤልያስአዲስ አበባ፡- በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የኅብረተሰብ ክፍል ከክልሉ ጸጥታ ኃይል ጋር የመስራት ትብብሩን አጠናክሮ ከቀጠለ በክልሉ እየተንቀሳቀሰ ሽብር የሚፈጥረው ኦነግ ሸኔ መጥፊያው ሰዓት አጭር እንደሚሆን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል አራርሳ መርዳሳ ገለጹ። ኮሚሽነር ጀኔራል አራርሳ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ እንደ ኦነግ ሸኔ ያሉ አሸባሪ ኃይሎች በጂ.ፒ.ኤስ በሚወሰድ ርምጃ ብቻ ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ የሚያስችል ለውጥ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቅ አይደለም። ትልቁ ነገር እነዚህን ኃይሎች የማስወገድ እና ዕድሜያቸውን የማሳጠር ሥራ ነው። ይህ ደግሞ በዋናነት ስኬታማ የሚሆነው የየኅብረተሰቡ ተሳትፎ ሲታከልበት ነው። ኅብረተሰቡ ከክልሉ ጸጥታ ኃይል ጋር በመሆን የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ የሚቀጥል ከሆነ ሽብር ፈጣሪው ኦነግ ሸኔ መጥፊያው ሰዓት አጭር ይሆናል። የኅብረተሰቡ አንዱ ሥራ እነዚህን ቡድኖች የጥፋት ኃይሎች መሆናቸውን ተገንዝቦ ሴረኞቹን የማጋለጥ ሥራ መስራት ነው ያሉት ኮሚሽነር ጀኔራል አራርሳ፣ ሁለተኛው ደግሞ ኅብረተሰቡ ራሱ ተደራጅቶ እነዚህን ኃይሎች የመመከት ሥራ ማከናወን መሆኑን ተናግረዋል። ኅብረተሰቡ በእነዚህ ሥራዎች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ተባብሮና አብሮ ርምጃ በመውሰዱ ላይ ከተሳተፈ የኦነግ ሸኔ ዕድሜ እንደሚያጥር አመልክተዋል። እንደ ኮሚሽነር ጀኔራል አራርሳ ገለጻ፤ ኅብረተሰቡ በዚህ ሥራው ያለማቅማማት ከተባበረ ኦነግ ሸኔ ሊወገድ ይችላል። በአሁኑ ወቅት ኅብረተሰቡ የጀመረው እንቅስቃሴ አበረታች ነው። ካለውም የጸጥታ ኃይል ጋር ያለውም ትብብር ጥሩ የሚባል ነውና ይህ እገዛው በዚሁ ከቀጠለ ኦነግ ሸኔን የማስወገድ ሥራ መስራት ብዙም የሚከብድ አይደለም። አሁን የጀመርነው ርምጃ የመውሰዱን ሥራ ሕዝቡ በሎጂስቲክ እንዲሁም እውነታውን በመናገሩ በኩል ከሰራ የተሻለ ውጤት ይኖራል ያሉት ኮሚሽነር ጀኔራሉ፣ ጸረሰላም ኃይሉ ኦነግ ሸኔ ከኅብረተሰቡ የሚያገኘው ድጋፍ ሙሉ ለሙሉ የሚቋረጥ ይሆናልና ከዚህ በኋላ ብዙ እንደማይቆይ አስረድተዋል። ስለሆነም ኅብረተሰቡ አሁን የጀመረውን ትብብርና ለሰላም መስፈን እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል። የኦሮሞ ብሔርም ይሁን በክልሉ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች በትብብር በመሆን ለማንምና ለምንም የማይበጁትን ጸረ ሰላም ኃይሎች ለማስወገድ በቅንጅት እና በጋራ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል። ስለዚህም ማህበረሰቡ የማጋለጡን ሥራ ያለምንም ርህራሄ አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ከጸጥታ ኃይሉ ጋርም በመሆን ተባብሮ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 2/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37098
2e5531fe9d0552b81df72c40ed60e3e1
eef95f755e8cc42585c4f8b7d00f152b
በትምህርት ቤቶች በኮቪድ 19 ዙሪያ እየተደረጉ ያሉ ጥንቃቄዎች
ሞገስ ተስፋ ጭር ብለው ለስምንት ወራት የቆዩት ትምህርት ቤቶች ውበትን ተላብሰዋል፡፡ ከአምስተኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ትምህርት ተጀምሯል፡፡ እኛም በሁለት ትምህርት ቤቶች ቅኝት አድርገናል፡፡ አፄ ናኦድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ስንዘልቅ ገና ከበሩ የሙቀት መከሊያ፣ የእጅ ንፅሀና መጠበቂያና ሳኒታይዘር በተገቢው ቦታ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ተማሪዎች የአፍና የአፍንጫ ጭንብላቸውን አድርገው ዕውቀት ወደሚገበዩበት ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ይገባሉ፡፡ መምህራን ነጭ ጋዋናቸውን አድርገው የቀለም ልጆቻቸውን በዕውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ለመቅረፅ ዝግጅታቸውን አጠናቀው አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሳቸውን ይዘው እያስተማሩ ነው፡፡ እኛም ይህንኑ ሁነት የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ወደሚማሩበት ክፍል ዘልቀን ተመልክተናል፡፡ ተማሪ አማኑኤል ማሬ የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ነው። የ2013 ዓመተ ምህረት ትምህርት መጀመሩን በጉጉት ሲጠብቅ እንደነበረ ገልፆልናል፡፡ ተማሪ አማኑኤል እንደሚለው ለሥምንት ወራት ከትምህርት ገበታ ርቆ በመቆየቱ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮብኝ ነበር፣ አሁን ላይ ሁሉም ተማሪ የትምህርትን መጀመር በጉጉት ሲጠብቀው ስለነበር ዕውቀት ወደምንገበይበት ቤት መመለሳችን በጣም ደስታ ተሰምቶናል ይላል፡፡ ወደትምህርት ቤት ሲገቡ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚያስችሉ ማለትም የአፍና የአፍንጫ ጭንብል በማድረግ እጅን በመታጠብ ወደ መማሪያ ክፍላቸው ከገቡ በኋላም እያንዳንዱ ተማሪ ሳኒታይዘረት እና አልኮል እንደሚጠቀሙ አማኑኤል ይናገራል፡፡ ተማሪዎች እንዳይዘናጉ በትምህርት ቤቱ ሚኒ ሚዲያ አማካኝነት የተለያዩ መልዕክቶችን በማዘጋጀት ሁሉም በንቃት ራሱን ከቫይረሱ እንዲጠብቅ ከሰልፍ ሥነ ሥርዓት ጀምሮ በእረፍትና ምሳ ሰዓት እንደሚተላለፉ የገለፀልን ተማሪ አማኑኤል አስተማሪዎቻቸው የሚሰጧቸውን መመሪዎች በመቀበል ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ በመከላከል ትምህርታቸውን በአግባቡ እየተከታተሉ እንደሆነ እኛም ክፍል ውስጥ በመዘለቅ ታዝበናል፡፡የአፄ ናኦድ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርት የሆኑት ወይዘሮ ፀሐይ ካሳ እንደገለፁልን፣ የትምህርት አጀማመራቸው ቀድመው የትምህርት ቤቱን ግቢ ለተማሪዎች ምቹና ተስማሚ እንዲሆን የግቢ ማስዋብ ሥራ ሰርተዋል፡፡ ከዚያም ለኮሮና ቫይረስ መከላከል አስፈላጊ የሆኑ የእጅ ማስታጠቢያ እስከ መፀዳጃ ቤት ደረጃቸውን የጠበቁ በማድረግ ዝግጅት እንዳደረጉ ይገልፃሉ፡፡ ይህ ሲሆን ሳሙና፣ ሳኒታይዘርና አልኮል ምቹ በሆኑ ቦታዎች በማስቀመጥ ሲሆን ተማሪዎችም ሳይዘናጉ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ሁሉም መምህራን በኃላፊነት ስሜት እየሰሩ ነው ሲሉ ገልፀውልናል፡፡ እንደ ርዕሰ መምህሯ ገለፃ፣ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ለሥምንት ወራት ርቀው ስለቆዩ ወደትምህርት ቤት በሚመጡበት ወቅት አምሯቸው ብሩህና ንቁ ሆነው እንዲማሩ ለማድረግ ሰፊ ቅድመ ዝግጅት አድርገው ስለተቀበልናቸው ለትምህርታቸው የሰጡት ትኩረት ከፍተኛ ነው፡፡ ከወረዳ ስድስት ጤና ጽሕፈት ቤት ጋር በጋራ በመሆን የጤና ባለሙያዎች ተመድበው ሙቀት በመለካት ለተማሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ነግረውናል። ወደ ትምህርት ያልተመለሱ ተማሪዎችን በመለየት እና ወደወላጆቻቸው በመደወል ትምህርት እንዲጀምሩ ለማስቻል የሚረዱ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። ለዚህም ማህበራዊ ድረ ገጾችን ጭምር እየተጠቀሙ ነው፡፡በተመሳሳይ መልኩ በምኒልክ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተገኝተን በትምህርት ቤቱ ያለውን እውነታ ለመታዘብ ችለናል። ሳሙኤል መንግሥቱ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነው። ‹‹ትምህርት በመጀመሩ ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ለሥምንት ወራት ከትምህርት ገበታችን ስላራቀን አላስፈላጊ ቦታ እንድንውል በማድረግ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሮብን ነበር፡፡ ስለሆነም አሁን ላይ ትምህርታችን በፈረቃም ቢሆን መጀመራችን ትልቅ እፎይታን ሰጥቶናል›› ሲል ስሜቱን አጋርቶናል፡፡ በምኒልክ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ሲሳይ አለሙ በበኩላቸው፣ የመማር ማስተማሩ ሂደት ከሁለት ቀናት በፊት ከዘጠነኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚገኙ ተማሪዎችን ተቀብለው ጀምረዋል። ኮሮናን ለመከላከል ሲባል 12ኛ ክፍል በአንድ ክፍል 24 ተማሪዎች በ24 ወንበር ምደባ በ44 ክፍል ተደልድለው በአንድ ፈረቃ ሰኞ፣ ረቡዕና አርብ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው፡፡ በሁለተኛው ፈረቃ ደግሞ ዘጠነኛ፣ አስረኛና አስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች ተደልድለው ትምህርት ጀምረዋል፤ የክፍል ጥምርታውም በክፍል 24 ሲሆን በ46 ክፍሎች ማክሰኞ፣ ሐሙስና ቅዳሜ ጥንቃቄ በተሞላበት ማስተማር መጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ተገኝተን ባደረግነው ምልከታ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ የእጅ ማስታጠቢያ ገንዳ፣ ሳሙና፣ ሳኒታይዘርና የመሳሰሉት ቁሳቁሶች ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ ቦታ ተቀምጠዋል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም ተማሪ በርቀት ሆኖ ስለቫይረሱ መተላለፊያ መንገዶችና ሊወስዱት ስለሚገባቸው ጥንቃቄ የሚያስገነዝቡ መልዕክት የያዙ ማስታወቂያዎች መኖራቸው ተገቢ መሆኑን ታዝበናል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 1/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37051
2f9e657a4a685a91dbaf2f0c78190dba
134bb8a457e992c5a409ea4debcccc51
ወታደሮችን በሲኖ ትራክ እስከመጨፍለቅ የዘለቀው የጁንታው የክፋት ጥግ
ኢያሱ መሰለሃምሳ አለቃ ደረጀ አንበሳ በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ የጥገና ባለሙያ ናቸው። በሙያቸው አገራቸውን ሌት ተቀን ከማገልገላቸውም በላይ እንደማንኛውም የመከላከያ አባል ለትግራይ ሕዝብ በችግሩ ጊዜ ከጎኑ በመቆም አጋርነታቸውን ሲገልጹ ኖረዋል። የሕዝብና የአገር ከለላና መከታ የሆነው የኢፌዴሪ መከላከያ አባል እንደመሆናቸው አንድም ቀን በአገር ልጅ የባንዳነት ተግባር ይፈጸምብኛል ብለው አስበውም አያውቁም። ይሁንና በእናት ጡት ነካሾች ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ከምሽቱ አራት ሰዓት ያልታሰበ ጥቃት ተፈጸመባቸውና ያለምንም ጥፋታቸው ተይዘው ለእስር መዳረጋቸውንና ቀላሚኖ እስርቤት መታሰራቸውን ይገልጻሉ። «ከቀላሚኖ እስር ቤት ወደ አግቤ በመቀጠልም ከትንሽ ቀን በኋላ ወደ ተንቤን መምህራን ኮሌጅ ወሰዱን። የመከላከያ ሠራዊትን የከባድ መሳሪያ ድምፅ ሲሰሙ የ90 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ አስጀመሩን። ልክ 40 ኪሎ ሜትር እንደተጓዝን ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ሲኖ ትራክ መኪና ከኋላችን መጣ። ተጓዡ ወደ 1,200 ሰው ነበር። ከአስፋልት እንድንወጣ ካለመፈቀዱም በላይ ከአስፋልቱ መሀል ከወጣን ልዩ ኃይል ተኩሶ ይመታን ነበር። ከግራና ከቀኝ ገደላማ የሆነ ጠባብ ቦታ ላይ ስንደርስ ሲኖ ትራክ መኪና ልከው ከኋላችን ነዱብንና የሚገድለውን እየገደለ፣ ያቆሰለውን እያቆሰለ ሄደብን። እኔንም አንድ እግሬን አገኘኝና እግሬ ከተሰበረ በኋላ ተንከባልዬ ጉድጓድ ውስጥ ገባሁ። እዚያው ጉድጓዱ ውስጥ ከተጎዱ ጓደኞቼ ጋር ተኝቼ አደርኩ። ሲኖ ትራኩ ቢያንስ እስከ 50 ሜትር የተጓዘው በሰዎች ላይ ነበር። በዚህም ግማሹ ሞተ፣ ግማሹ ቆሰለ የቀረውም ወደገደል ገባ። እንግዲህ የራሳችን ወገን ነው እንዲህ ዓይነት በደል የፈፀመብን። ይህ ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ድርጊት ነው። ስንት ዓመት ሙሉ አብረናቸው ኖረን በመኪና ሲጨፈልቁን በጣም ነው የተሰማኝ፤ በጥይት ቢገድሉኝ ይሻል ነበር» ይላል:: በወቅቱ ሴቶችም ሕፃናትም አብረውን ነበሩ ማን እንደሞተ ማን እንደተረፈ አንኳን አላውቅም ያለው ወታደሩ «በወቅቱ በሕይወት የተረፉትም ተበታተኑ፤ አንዳንዶቹም ቆስለው ወደጫካው ገቡ፤ የሞቱትም እዚያው ቀሩ አምስት የምንሆን ሰዎች እዚያው አድረን ከሞቱት ሰዎች መሀል በሕይወት ወጣን። የሞቱ ልጆችን እንኳን ለመለየት አልቻልኩም፤አጠገቤ ነው እየጮሁ የሞቱት፤ ምንም ልረዳቸው አልቻልኩም። በወቅቱ እኔም በሁለት እግሬ መቆም አልችልም ነበርና በጉልበቴ ዳዴ እያልኩ ነው የወጣሁት» ሲል የወቅቱን አሳዛኝ ሁኔታ ይገልፃል:: «እኛኮ ከሌሊቱ 11 ሰዓት እየተነሳን አጨዳ የምናጭድ፤ ኮሮና ገባ ሲባል ብር እያዋጣን የምንደግፍና ከደመወዛችን እየቆረጥን የልማት ሥራዎችን የምንሰራ ነን። እኛ ለትግራይ ሕዝብ ልማት ወደኋላ ብለን አናውቅም። ይሁንና ጁንታውና የእሱ ተላላኪዎች በሰው ላይ የማይፈፀም ድርጊት ነው የፈፀሙብን። ሰብስበው በቦምብ ቢያቃጥሉን ወይም በጥይት ቢገድሉን ይሻል ነበር። የውጭ ጠላት እንኳን በመኪና ሰውን ደፍጥጦ አይገድልም። ድርጊቱ ከተፈፀመብን በኋላ በመኪና መንገድ ላይ ስንሄድ እየተሸማቀቅን ነው።  ጭንቅላታችን ራሱ ተጎድቷል::» ሌላው ተመሳሳይ ድርጊት የተፈፀመበት አምሣ አለቃ ወንድማገኝ ወልደገብርኤል ነው። እሱ እንደሚገልፀው በልዩ ኃይል እና በሚሊሻ ታጅበን በእግር እየተጓዝን ሳለ ከአስፓልቱ እንዳትወጡ አሉን እኛም ፈንጂ ያለ መስሎን የአስፋልቱን መሀል ይዘን መጓዝ ጀመርን። ጨለምለም ሲል ከኋላችን ሲኖትራክ መኪና መጣ፤ ከፊት ለፊት ተኩስ ተከፈተብን፤ እንዳንመታ ብለን ሁላችንም ተኛን፤ በዚህ ወቅት ሲኖ ትራኩ እየጨፈለቀን ሄደ። ግማሹ እየተንከባለለ ወደገደል ገባ፤ ተገጭተን የተረፍነው በማግስቱ ተነሳን፤ ብዙዎች ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ሞቱ፤ አንዳንዶቹም ቆሰሉ፤ አሽከርካሪው ለመትረፍ የሚሞክሩ ሰዎችንም ዚግዛግ እየነዳ ነበር ሲጨፈልቃቸው የነበረው። በእግራችን መሄድ አቅቶን ጅብ ይብላን ብለን እዚያው ከተኛን በኋላ ታፍነው በመከላከያ ሰራዊት እርዳታ የተለቀቁ እስረኞች እየረዱን የተወሰነ ርቀት ከተጓዝን በኋላ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ደርሰው ወደዚህ አመጡን። ሲሉ የደረሰባቸውን ግፍ አስረድተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 2/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37097
35822d09ba75703b5648fd81a07527f7
0546740a4bdf5ddc543cce63c85e1183
የጁንታው ግፍ የማንነት ጥያቄ ባነሱ ዜጎች አንደበት
ኢያሱ መሰለ ወጣት ሞገስ ዳርጌ የራያ አላማጣ ተወላጅ ሲሆን የማንነት ጥያቄ በማንሳቱ ብቻ ከሥራ ቦታው ታፍኖ በማይጨው ገጠራማ አካባቢ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ ለሦስት ወር ከቆየ በኋላ ወደ መቀሌ እስር ቤት መዛወሩን ይናገራል። በማይጨው ቆይታው የደረሰበትን አካላዊና ሞራላዊ ጥቃት እንዲህ ያስረዳል። በእስር ቤቱ ውስጥ እጅና እግሬ ታስሮ ነው የተወረወርኩት፤ በተለይ እግሬ የታሰረበት እስከ አሁን ምልክቱ አለ፤ ቀንና ሌሊቱን አላውቀውም፤ አንዳንዴ ከዋሻው እያወጡ አንድ ትልቅ የወይራ ዛፍ ላይ አስረው ያሰቃዩኛል፤ ሲፈልጉ ሽንታቸውን ይሸኑብኛል፤ ስለራያ ማንነት የሚከራከሩ ሰዎችን ጠቁመን ይሉኛል፤ እነርሱ ሊያስሯቸው በሚፈልጉ ሰዎች ላይ መስክር ይሉኛል፤ ከመሰከርክባቸው ሃምሳ ሺ ብር እና ቦታ እንሰጥሃለንም ይሉኝ ነበር። እነዚህ ሰዎች ያልሰሩኝ ሥራ የለም፤ አሪዎስ እንኳን እንደነሱ የክፋት ሥራ አልሰራም። በምድር ላይ ያለውን የክፋት ሥራ ሁሉ በእኔ ላይ ፈጽመዋል፤ ያልደረሰብኝ ነገር የለም፤ ሽንት ቤት ውስጥ አስረውኛል፤ ሲፈልጋቸው አንገቴ ላይ ሰንሰለት አስገብተው ዛፍ ላይ አስረው ወደ ላይ ይጎትቱኝና ልሞት ስል ይለቁኛል፤ እንደገና ደግሞ አስረው ይጎትቱኛል፤ ጉድጓድ ቆፍር ይሉኛል፤ መቆፈር ሲያቅተኝ ይመቱኛል፤ ይሰድቡኛል፤ እስከ አንገቴ ድረስ በቁመቴ ልክ ጉድጓድ ውስጥ ቀብረውኝ እንገድልሃለንም ይሉኛል። ይህ አልበቃ ብሏቸው ማይጨው ማረሚያ ቤት ወሰዱኝ፤ ቀጥለውም መቀሌ ማረሚያ ቤት አስገቡኝ፤ በኋላም መንግሥት ሕግ የማስከበር ርምጃ ሲወስድና መቀሌ አቅራቢያ ሲደርስ ወደ ተንቤን ወሰዱን፤ በዚህ ወቅት ምግብም ውሃም አልነበረም። አንድ ጊዜ አንድ እንጀራ ለአራት ከሰጡን በኋላ እስከ ሁለት ቀን ሳንበላ እንቆያለን፤ መከላከያ ሰራዊቱ አሁንም ተንቤን ሲደርስ ሊረሽኑን አሰቡ። ጌታቸው ረዳ፣ አለም ገብረዋህድ እና የክልሉ የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ተክኤ ምትኩ በወልቃይት፣ በራያ፣ በትግራይ ደምሒት አባላት ላይ ሞት ፈርደውብን ሄዱ። ከዚህ በኋላ ስልሳ ሰዎች ተመርጠን፤ የሁለት ሰዎች እጅ አንድ ላይ እየታሰረ ወደ በረሃ ተወሰድን። ከዚያም አንድ ሸጥ ውስጥ አስገብተውን ካስቀመጡን በኋላ ውሳኔ የተላለፈበት ወረቀት እንዲመጣ ሰዎችን ላኩ፤ በወቅቱ የአላማጣ ተወላጅ የሆኑና የታጣቂ ቡድኑ አባል የነበሩ የማውቃቸው ሰዎች ነበሩ። እነዚህ ሰዎች አመራር ስለነበሩ በዚህ ባለቀ ሰዓት ለምን ይገደላሉ ብለው ሲከራከሩ ነበር። ግድያው የዘገየውም በዚሁ ምክንያት ይመስለኛል። ይሁንና የውሳኔ ወረቀቱን እንዲያመጡ የተላኩ ሰዎች ወረቀቱን ይዘው ሲመለሱ በመከላከያ ሰራዊት ተያዙ። ያገቱን ታጣቂዎችም መከበባቸውን ሲያውቁ ትተውን ሸሹ። ሌላው የጁንታውን እኩይ ተግባር ከደረሰበት አንጻር የሚያስረዳው፣ አቶ ጥጋቤ እሸቴ፤ የወልቃይት ጠገዴ ሳንጃ ወረዳ ነዋሪ ሲሆን፤ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነው። የማንነት ጥያቄ ከሚያቀርቡ የወልቃይት ተወላጆች አንዱ በመሆኑም በ1998 ዓ.ም በህወሓት ጁንታ ታጣቂዎች ተይዞ መቀሌ ከተማ መታሰሩን ይናራል። ከዚያም ወደ ማይጨው እስር ቤት ተዛወረ። ከማይጨው እንደገና ወደ መቀሌ ማረሚያ ቤት ተወስዶ እያለ የጁንታው ታጣቂዎች በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ መንግሥት ሕግ የማስከበር ርምጃ ሲወስድ የጁንታው ታጣቂዎች መቀሌ ማረሚያ ቤት ያሉትንና በፖለቲካ ጉዳይ የሚፈልጓቸውን እስረኞች ወደ ተንቤን ይዘዋቸው እንደሸሹ ይናገራል። ከአስራ አምስት ዓመት የአፈና ቆይታ በኋላ በመከላከያ ሰራዊት አማካኝነት ነፃ የወጣው አቶ ጥጋቤ፣ የእስር ቤት ቆይታውን እንዲህ ያስረዳል። በእስር ቤት ውስጥ የደረሰብኝ አሰቃቂ በደል መቼም ከህሊናዬ አይጠፋም፤ እንዳልሞት ብቻ ትንሽ ምግብ ይሠጡኛል፤ አንገቴን ያንቁኛል፤ ልሞት ስል ይለቁኛል፤ ይገርፉኛል፤ እስከ አንገቴ ድረስ አፈር ውስጥ ቀብረውኝ ሳንገድልህ የምንጠይቅህን ንገረን ይሉኛል፤ ያሰቃዩኛል ይሰድቡኛል። አንዳንድ ጓደኞቻችንን ማታ ወስደው ባዶ ቤት ውስጥ ካስገቧቸው በኋላ ጧት ራሳቸውን አንቀው ገደሉ እያሉ አስክሬናቸውን ያሳዩናል። ብዙ ሰዎችን እንዲህ እያደረጉ ገድለዋቸዋል። በመጨረሻም የመከላከያ ሰራዊት ጥቃት ሲበረታባቸው ደርግ በዚህ በኩል እየመጣባችሁ ስለሆነ በዚህ በኩል ሂዱ ብለው መንገድ አመላከቱን። እኛ ግን እነርሱ ያሳዩንን መንገድ ትተን በተቃራኒው ሄድን። በመኪና ተገጭተውና ገደል ተወርውረው እግራቸውና ጭንቅላታቸው የቆሰሉ አስራ አንድ ሰዎችንም አገኘን። እነርሱን ተራ በተራ እየተሸከምን ወደ ኋላ ስናፈገፍግ መከላከያ ሰራዊቱ ከሞት አፋፍ አትርፎን ወደ መቀሌ ይዞን መጣ፤ ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 2/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37101
a9b57e943d40771592c4cd6e84cbd008
fdf965603852d7008c13201e1ae7b0da
«ጁንታው ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ አልነበረም» -አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀመንበርና በፌዴራሊስት ኃይሎች የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ
ዳግማዊት ግርማአዲስ አበባ፡- የህወሓት ጁንታ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ ያልነበረ፤ ዴሞክራሲን የማያውቅ መሆኑን የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀመንበርና በፌዴራሊስት ኃይሎች የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ ገለጹ። አቶ ቶሎሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፣ የህወሓት ጁንታ ከመጀመሪያውኑ በአገሪቱ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ዝግጅት፣ ዓላማ እና ፍላጎት አልነበረውም። በባህሪውም የዴሞክራሲያዊ እሴቶች አይታይበትም ነበር። ቡድኑ ጠመንጃ አንግቦ ጫካ እንደገባ ሁሉ ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህም እንደ መፈክር ይዞት የመጣውን የዴሞክራሲ ሥርዓት ወደ ጎን በመተው ሕግና ሕገ መንግሥቱን በመጨፍለቅ ስለዴሞክራሲ የሚያቀነቅኑ ቡድኖችን ሆነ ግለሰቦች በማፈን፣ ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ እንዲሁም በመግደል በጫካ አስተሳሰቡ አምባገነናዊ ሥርዓት እንዲሰፍን ማድረጉን አስታውቀዋል። ጁንታው በ1983 ዓ.ም አምባገነኑን የደርግ ሥርዓት ገርስሶ በትረ ሥልጣኑን በጨበጠበት የመጀመሪያ ሰሞን ላይ መልካም አስተዳደር እገነባለሁ፣ ዴሞክራሲ አሰፍናለሁ፣ ሕዝባዊ መንግሥትን እመሰርታለሁ ብሎ ሲምልና ሲገዘት እንደነበር አስታውሰው፤ በሥልጣን ዘመኑ በተጨባጭ ቃሉን ማክበር እንዳልቻለ አመልክተዋል። በሚፈለገው ደረጃ ዴሞክራሲያዊ ባይሆንም በ1987 ዓ.ም ሕገመንግሥት መርቀቁና ተግባራዊ መደረጉ፣ የፌዴራል አደረጃጀቶች፣ የክልሎች የራስ አስተዳደር አስተዳደሮች መመስረታቸውን የጠቆሙት አቶ ቶሎሳ፣ በወቅቱ ከደርግ አምባገነናዊ ሥርሥት የተሻለ የሚመስል ጭላንጭል ጅምሮች ቢታዩም፤ ሳይቆይ ግን ቡድኑ ሕግና ሕገ መንግሥቱን በመጨፍለቅ አምባገነን መሆኑን ገልጸዋል። የህወሓት ጁንታው ሕዝቡ ከስጋትና ከፍርሃት ቀጣና ወጥቶ መብቱን እንዳይጠይቅ ሥልጣኑን ለማራዘም እሱ ከሌለ ኢትዮጵያ አንድነቷን ይዛ እንደማትቀጥል፤ የብሔርና የሃይማኖት ግጭቶች እንደሚስፋፉ ኢትዮጵያም የሱማሌ ዕጣ እንደሚገጥማት ይሰብክ እንደነበር አስታውሰው፣ ይህ ደግሞ መቼም ሥልጣን ለመልቀቅ ዝግጁ አለመሆኑና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ጠል መሆኑን እንደሚያሳይ አመልክተዋል። እንደ ኃላፊው ማብራሪያ በአገራችን ባለፉት ዓመታት በተደረጉ ምርጫዎች ቡድኑ በሀገሪቱ ዴሞክራሲን የማስፈን ፍላጎት ስላልነበረው በ1987 ዓ.ም ጥሩ የሚመስል ጅምር ቢታይም ጅምሩ የ1997 ዓ.ም በድምፅ ዝርፊያ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን አስታውቀዋል። በዚህ ምርጫ ሕዝቡ ጁንታው ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ደንታ እንደሌለውና የራሱን አምባገነናዊ ሥርዓት እንደዘረጋ በግልጽ የተረዳበት ወቅት ነበር ብለዋል። ጁንታው በመጀመሪያ በማዕከል የታጠረ የይስሙላ ዴሞክራሲን የማከፋፈል ባህሪ እንደነበረ ጠቁመው፣ ክልሎች የዴሞክራሲ መብታቸውን በነፃነት እንዳይተገብሩ የአፈና መዋቅር እስከ ቀበሌ ድረስ በመዘርጋት ብቻውን ያሻውን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቀዋል። ከሀብት ብዝበዛ በተጨማሪ አስነዋሪ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶችን ሲፈጽምና ሲያስፈጽም እንደነበረ አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 2/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37107
6fd7019ac36036a9b29cc7dc8a329c33
6eea84e686c0ad551bf7da60ed3c2f2f
የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ለአገራዊና ክልላዊ ለውጡ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበረው ተገለጸ
ዋለልኝ አየለአዲስ አበባ፡- የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት (አብመድ) በ2010 ዓ.ም በአገሪቱ እና በአማራ ክልልውስጥ ለመጣው ለውጥ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበረው ተገለጸ::ድርጅቱ በአዲስ አበባ ያስገነባውን ስቱዲዮ አስመረቀ::ድርጅቱ ትናንት ስቱዲዮውን ባስመረቀበት ወቅት በክብር እንግድነት የተገኘኑት የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው እንደገለጹት፤ አብመድ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በወቅቱ የክልሉ አመራሮች ያደርሱት የነበረውን በደል እየዘገበ የሕዝብ ዓይንና ጆሮ ሆኗል:: ‹‹እኛ እንዳይጋለጡ የምንፈልጋቸውን ነገሮች በማጋለጥ ትህነግ በጎንደርና ባህርዳር ላይ ያደርስ የነበረውን ግፍ ለሕዝብ አድርሷል›› ያሉት አቶ ላቀ፤ በወቅቱ ሁለት ፈተናዎችን ተቋቁሞ ይሰራ እንደነበር አመልክተዋል::ህወሓት ያኔ ሙሉ ጥርስ የነበረው በመሆኑ ከሱ የሚመጣው ጫና አንደኛው ፈተና ነበር ያሉት አቶ ላቀ፣ ሌላው ደግሞ በራሱ በክልሉ አመራሮች ይደርስበት የነበረው ጫና እንደነበር አስታውሰዋል:: የአብመድ ጋዜጠኞች እነዚህን ጫናዎች ተቋቁመው በክልሉ ሕዝብ ላይ ይደርስ የነበረውን ግፍና ኢፍትሀዊነት ለሕዝብ ማድረሳቸውን ገልጸው፤ ዛሬ ወያኔ ከወደቀ በኋላ ብዙዎች ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ማለት ቢችሉም፤ አብመድ ግን ከነሙሉ ጥርሳቸው በነበሩበት ጊዜ ፊት ለፊት ሲታገላቸው እንደነበር አስታውቀዋል::ድርጅቱ ላለፉት 40 ያህል ዓመታት አማራን እንደ ጠላት ተደርጎ የተሳለበትን ትርክት የሚያስተካክል ሰፊ ሥራ መሥራት እንደሚጠበቅበት ያመለከቱት አቶ ላቀ፣ የአማራ ሕዝብ እና የአማርኛ ቋንቋ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ቋንቋዎች ጋር ሆኖ ለኢትዮጵያ ያበረከተውን አስተዋጽኦም ማስተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል::አማራ ከሌላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የተለየ ዕጣ ፈንታ እንደሌለው፤ የአማራ አርሶ አደር ከተበደለም ከተጠቀመም ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር እኩል እንጂ ለብቻው የሚሆን ነገር እንደሌለ ተናግረዋል::በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የመላው ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት ፕሬዚዳንት አቶ ማሙሸት አማረ በበኩላቸው፤ አብመድ እየተደረገ ባለው የሕግ ማስከበር ሂደት ውስጥ ለሰራው ትልቅ ሥራ አመስግነዋል::በጦርነቱ ቦታ ላይ ተገኝቶ የሕዝብ ልሳን ሆኗል::በአገሪቱ ላይ ሲሰራ የነበረውን ግፍ ለሕዝብ አሳይቷል ብለዋል::የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው፤ አብመድ በአዲስ አበባ የቀጥታ ማሰራጫ ስቱዲዮ መገንባቱ ከክልሉ ውጪ ላሉ ሕዝቦች ልሳን ለመሆን እንደሚያግዘው አስታውቀዋል::በቀጣይም በአዲስ አበባ የራሱ የሚዲያ ኮምፕሌክስ እንደሚኖረው ጠቁመዋል። ድርጅቱ በቀጣይ በሁሉም ክልሎች የዘገባ ወኪሎች እንደሚኖሩት ያመለከቱት አቶ አገኘሁ፣ በአዲስ አበባ ጨምሮ የአማራ ክልል አዋሳኝ በሆኑ ክልሎች የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች እንደሚጀመሩ አመልክተዋል::ድርጅቱ ወደ ኮርፖሬት እንደሚያድግም ተናግረዋል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 1/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37042
21d9d4b4e72555d88dd437c1598a3001
d6f021d4d0542f82ad5522a1151c1337
የዘንድሮ ምርጫ በሕዝብ ዘንድ ሊኖረው የሚችለውን ተቀባይነት የሚያጎሉ ምልክቶች እየታዩ መሆኑ ተገለጸ
ዋለልኝ አየለአዲስ አበባ፡- የዘንድሮ ምርጫ ከዚህ በፊት ከነበሩት ምርጫዎች በተሻለ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ሊኖር እንደሚችል የሚጠቁሙ የነፃነት ምልክቶች እየታዩ መሆኑን አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ገለጹ። የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ በቀጣዩ ምርጫ ዙሪያ የደረሰበትን የውሳኔ ሀሳብ አስመልክቶ ያነጋገርናቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ በኃይሉ ተሰማ እንደገለጹት፤ ከዚህ በፊት በነበሩት ምርጫዎች ግልጽ የሆኑ ጫናዎች ይደረጉ ነበር። ይሄን ነው መምረጥ ያለብህ የሚሉ አስገዳጅ ትዕዛዞች ይሰጡ ነበር። ነገር ግን አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ሰዎች የሚፈልጉትን የፖለቲካ አመለካከት ማራመድ እንዲሁም ያለምንም መሸማቀቅ ሀሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ ሁኔታ እየታየ ነው ።በተጨማሪ መንግሥትም በተደጋጋሚ የዘንድሮ ምርጫ ከዚህ በፊት ከነበሩት ምርጫዎች በተሻለ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግሯል። በአገሪቱ ውስጥ ጥቃት በመፈጸምና በማስፈጸም የአገሪቱን ሰላም ሲያውኩ የነበሩት በህወሓት ጁንታ እና በኦነግ ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለው የሕግ ማስከበር እርምጃ ለምርጫው የተሻለ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። ምርጫው በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትና ታማኝነት ያለው እንዲሆንም እንዲህ ዓይነት የጥፋት ቡድኖችን ሥርዓት ማስያዝ ተገቢ እርምጃ ከመሆኑ በላይ የዜጎችን ሥጋት በማስወገድ ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ ያስችላል ብለዋል። ‹‹በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ ማድረግ የሚቻለው መንግሥት ከዚህ በፊት ይደረግ ከነበረው ትምህርት ከወሰደ ነው›› የሚሉት ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ መምህር ዮሐንስ ግሩም ናቸው። ከዚህ በፊት በተደረጉ ምርጫዎች በሃይማኖት ተቋማት ሁሉ ግፊት ይደረግ ነበር። ከላይ እስከ ታች ያሉ አመራሮች አንድ ፓርቲ ብቻ እንዲመረጥ ጫና አድርገዋል። ምርጫ በሚደረግ ቀን እዚህ አስገቡ እየተባለ ነፃነት አልነበረም፤ መንግሥት ለእነዚህ ችግሮች በበለጠ ትኩረት ስጥቶ ከሰራ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ ማድረግ ይቻላል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል። ከዚህ በፊት በተደረገው ምርጫ የታዩ ጥፋቶች ከተቀረፉ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ ማድረግ ይቻላል። በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ ለማካሄድ ፍትሐዊ የሆነ የመገናኛ ብዙኃን የሰዓት ድልድል ማድረግ እንደሚገባ መንግሥት ቀደም ብሎ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ከጀመረው የምክክር መድረክ መገንዘብ ይቻላል ብለዋል። የመገናኛ ብዙኃን እንደየ ፖለቲካዊ ፍላጎታቸው ለፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ለሕዝብ በወቅቱ ማድረስ እንዳለባቸውና መንግሥትም ፍትሐዊ የአየር ሰዓት ድልድል ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል። ከዚህ በፊት የነበረው ወቀሳ ከአየር ሰዓት ድልድል ጀምሮ ለሁሉም ሕዝብ ግልጽ የሆነ አድሎ ይደረግ ስለነበር ነው። ‹‹በመገናኛ ብዙኃን ድልድል ብቻ ሳይሆን የታዛቢዎችና የአስመራጮችም ገለልተኝነት መኖር አለበት፤ ይህ ከሆነ ምርጫው በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ሕዝቡ ራሱ ያምናል›› ብለዋል። የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከኅዳር 25 እስከ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው፤ የ2013 ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ እና በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው እንደሚሆን የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና ዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም መግለጻቸው ይታወሳል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 2/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37106
611feb678af2d30b2cd6543bf4fd59c5
2182a280dd5d17057eea76fa8654969e
የክለቦች ስያሜና ውዝግብ ያስነሳው የፌዴሬሽን ማሳሰቢያ
በኢትዮጵያ እግር ኳስ በተለይም በፕሪሚየር ሊግና ከፍተኛ ሊግ ክለቦች መካከል በሚካሄዱ ውድድሮች ስታዲየሞች ስፖርት ለሰላም፣ ለጤንነት ከሚለው መርህ አፈንግጠው የሁከት መናኸሪያ መሆንን ፋሽን አድርገውታል።ካለፉት ሁለትና ሦስት ዓመት ወዲህ እግር ኳሱ በብሔርተኝነት ጥላስር ወድቆ ስታዲየሞች ኳስ ሳይሆን የፖለቲካ አጀንዳ ማንከባለያ ሲሆኑ ታዝበናል። መንግሥትም ሆነ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በአደገኛ ሃዲድ ላይ እየተጓዘ ለሚገኘው የስፖርታዊ ጨዋነት ጉዳይ ጥናትን መሠረት ባደረገ መልኩ መፍትሄ ማበጀት በይደር ሊተዉት የማይገባ ጉዳይ እንዳልሆነ እውን ነው። በተለይ እግር ኳሱን በሚመራው ብሔራዊ ፌዴሬሽን መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል የማያሻማ የመፍትሄ እርምጃዎችን አምጥቶ ወደመሬት ማውረድ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።ፌዴሬሽኑ ለስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ብርቱ ችግር ናቸው ብሎ የለያቸው ምክንያቶችና ያቀረባቸው የመፍትሄ አቅጣጫዎች ግን ሌላ ችግር እየመዘዙ ይገኛሉ። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለስፖርታዊ ጨዋነት ችግር ብሎ ከጠቀሳቸው ምክንያቶች ውስጥ የክለቦች ስያሜ አንዱ መሆኑም ለውዝግቦች መነሻ እየሆነ ይገኛል፡፡ፌዴሬሽኑ በ2012 ዓ.ም ስያሜያቸው ብሔር ተኮር የሆኑ የእግር ኳስ ክለቦች የስም ለውጥ ማድረግ እንዳለባቸው ማሳሰቡ ይታወሳል።ፌዴሬሽኑ የስያሜ ለውጥ በአምስት ክለቦች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ፤ ከወዲሁ ቅሬታዎች በርትተዋል። ፌዴሬሽኑ ለስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት ናቸው በሚል አምስት ክለቦች ስያሜያቸውን እንዲቀይሩ ማሳሰቢያ ማውጣቱን ተከትሎ በክለቦቹ ተቃውሞ ገጥሞታል።መቐለ 70 እንደርታ ወደ መቐለ ከተማ፣ ፋሲል ከተማ ወደ ጎንደር ከተማ፣ ጅማ አባጅፋር ወደ ጅማ ከተማ፣ ስሁል ሽረ ወደ ሽረ ከተማ እንዲሁም ሀዲያ ሆሳዕና ወደ ሆሳዕና ከተማ ስማቸው እንዲቀየር የተሰጠውን ማሳሰቢያ ክለቦቹ ውድቅ በማድረግ ማሳሰቢያውን እንደማይቀበሉት የተለያዩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ፖለቲካዊ ይዘት ያለው የፋሲል ከነማ ስያሜ ሳይሆን የፌዴሬሽኑ ጥያቄ እንደሆነ ክለቡ በማህበራዊ ገፁ አቋሙን አስታውቋል። ‹‹ፋሲል ከነማ ለጎንደር ሕዝብ መገለጫው ነው፣ የዛሬ 52 ዓመት የነበረን ስያሜ ዛሬ ቀይሩ ማለት መልዕክቱ ሌላ ነው›› በማለትም የፌዴሬሽኑን ማሳሰቢያ ክለቡ እንደማይቀበለው አረጋግጠዋል።ከተመሰረተ ከግማሽ ምዕተዓመት በላይ ያስቆጠረው ፋሲል ከነማ የተጫዋቾቹ መለያ ስም አፄዎቹ ይባላል፤ በተመሳሳይ የደጋፊዎች መለያ ስም አፄያውያን ይባላል። ስለዚህ ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን መለስ ብሎ ሊመለከት ይገባል በማለት ክለቡ ያለውን አቋም አሳውቋል።በጉዳዩ ዙሪያ ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየታቸውን የሰጡት የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ ዘዋሉ ይሄንኑ አቋሙን እንዲህ ሲሉ አረጋግጠዋል። ‹‹የፋሲል ከነማ ራዕዩ፣ ሕልም እና አቋሙ ስፖርት ብቻ ነው። ስያሜውም የጎንደር ከተማ መገለጫ በሆነው በዩኔስኮ በተመዘገበውና የኢትዮጵያ ቅርስ በሆነው የፋሲል ግንብ አሰሪ እና የኢትዮጵያ ንጉስ በሆኑት በአፄ ፋሲለደስ የተሰየመ እንጂ ሌላ ፖለቲካዊ አጀንዳ የሌለው ፍፁም ኢትዮጵያዊ ክለብ ነው››።ፋሲል ከነማ የጎንደር ከተማ ሕዝብና የክለቡ ደጋፊዎችም ይህንን የፌዴሬሽን ውሳኔ እንደማይቀበሉት ፌዴሬሽኑ እንደሚያውቀውም ቡድን መሪው ተናግረዋል። ጉዳዩ የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብን በእንደዚህ ዓይነት ነገሮች ችግር ውስጥ በማስገባት የስፖርት ክለቡን አንገት ለማስደፋት የሚደረግ ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው ውሳኔ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ፖለቲካዊ ይዘት ያለው የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ስያሜ ሳይሆን የፌዴሬሽኑ ድፍረት የተሞላበት ‹‹ስም ቀይሩ›› የሚል ውሳኔ መላውን ኢትዮጵያዊ ስፖርት ወዳጅ እና የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በፅኑ የሚቃወሙት መሆኑን ተናግረዋል።በመሆኑም ክለቡ የስያሜ ለውጥ ለማድረግ በምንም መልኩ ፈቃደኛ እንዳልሆነ አብራርተዋል።የክለቡ የቦርድ አመራሮች በቅርቡ ስብሰባ እንዳላቸው የጠቆሙት ቡድን መሪው ፌዴሬሽኑ ጥቅምት መጀመሪያ ላይ በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ይሄንኑ አቋም ይዘው እንደሚመጡም እምነት አላቸው፡፡በተመሳሳይ የስያሜ ለውጥ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው ከተነገረው ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው የጅማ አባጅፋር ክለብ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሱልጣን ዛኪር፣ ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በኩል በጉዳዩ ዙሪያ ምንም ዓይነት የደረሳቸው ደብዳቤ እንደሌለ ተናግረዋል።‹‹እኛም የሰማነው በጭምጭምታ ነው። ይፋዊ የሆነ ነገር አልሰማንም። ክለቡ ከስያሜ ጋር ተያይዞ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር አለበት የሚል እምነት የለንም›› ያሉት ሥራ አስኪያጁ የስያሜው ባለቤት ሕዝብ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ክለቦች ከስያሜያቸው ጀምሮ ምንም ዓይነት የብሔርተኝነትና የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት ባለመሆናቸው ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን ሊቀይር እንደሚገባ በመግለፅም በጉዳዩ ማዘናቸውን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተሰጡ የሚገኙ አስተያየቶች የአንዱ ክለብ ደጋፊ ከሌላው ደጋፊ ሲጋጭ፣ ሲቋሰል፣ ሲጨካከን የነበረው ወቅታዊ የአገሪቱን ፖለቲካ በተከተለ መልኩ እንደነበር ይዘረዝራሉ።ክለቦች ከመጡበት ክልል አኳያ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችና የሚፈጠሩ መፋጠጦች፤ በተቃራኒው ደግሞ የወንድማዊነት፣ የወገንተኝነት አዝማሚያዎች በዚህ መልክ የተቃኙ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር። ለዚህም እንደማሳያ የሚቀመጠው ቻምፒዮኑ መቐለ 70 እንደርታ፣ ከስሁል ሽረ፣ ከደደቢት ብሎም ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ክለቦች ጋር እርስ በእርስ ሲገናኙ የሚስተዋለው የስታዲየም ድባብ የአንድነትና የወንድማማችነት መሆኑ ነው።በተመሳሳይ በፋሲል ከነማ፣ ባህርዳር ከነማ፣ ወልዲያ ከነማ ደጋፊዎች መካከል ያለውን ወንድማዊ ስሜት መጥቀስ ይቻላል።በ2011 የውድድር ዓመት በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል ክለቦች መካከል በሚካሄዱ ጨዋታዎች የነበረው ሁኔታ ተቃራኒ መሆኑን መመልከት ይቻላል።ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የስፖርታዊ ጨዋነት ምንጩ የክለቦች ብሔር ተኮር ስያሜ ከመያዛቸው መሆኑን ጠቅሶ «ብሔር ተኮር የሆኑ የእግር ኳስ ክለቦች ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ ስያሜያቸውን እንዲያስተካክሉ ይደረጋል» የሚለውን ውሳኔ ከዚህ አንጻር መልሶ ሊመለከት ይገባል የሚሉ የስፖርት ቤተሰቦች በርካታ ናቸው። ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ካንሰር የሆነው ብሔር ተኮር ስያሜ ሳይሆን ብሔር ተኮር እሳቤ መሆኑን ሊሰመርበት እንደሚገባ በተደጋጋሚ ይነሳል።ብሔር ተኮር ስያሜን የያዙ ክለቦች ያውም በሌሉበት ስያሜው ተቀይሮ አመለካከት ሳይቀየር ለውጥ ማምጣት እንደማይቻልም የሚያሰምሩበት ወገኖች አሉ። ፌዴሬሽኑ መሬት ያለውን እውነት ተቀብሎ አመለካከት ላይ መስራቱ አንዱና ዋነኛው መፍትሄ ሊሆን ይገባል። ሌላው በጎሰኝነት፣ ብሔርተኝነት በሽታ ውስጥ የሚገኘውን እግር ኳስ ለመታደግ በተለያዩ መድረኮች ሲነሱ የነበሩ የመፍትሄ ሃሳቦችን ዞር ብሎ መመልከቱም ጠቃሚ ይመስላል፡፡የኢትዮጵያ ስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ የዘር ልዩነት እንዲጠፋ የኦሊምፒክና የዓለም አቀፍ የስፖርት ማኅበራት ደንብና መመሪያዎች እንዲከበሩ ማድረግ አንዱና ዋነኛው መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል።አዲስ ዘመን ረቡዕ መስከረም 14 / 2012  ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=19256
c89a2f7e1f013fb539bf7060b691b3e3
50f62ba170ff10bda28e8097fbd8bf73
ከጀግናው አንደበት፣ ለአዲሶቹ ጀግኖች
በ25 ዓመታት የውድድር ዘመኑ፤ በርካታ የኦሊምፒክና የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ሜዳሊያዎችን እንዲሁም 27 የዓለም ክብረወሰኖችን በእጁ አስገብቷል። በረጅም ርቀት የመም ተወዳዳሪዎችም ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፤ ከገጹ ፈገግታ የማይነጥፈው ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ። በስድስት ዓለም ቻምፒዮናዎች ተሳትፎው አራት የወርቅ፣ ሁለት የብርና አንድ የነሃስ በጥቅሉ ሰባት ሜዳሊያዎችን ለሃገሩ አበርክቷል። እአአ 1993 የስቱትጋርት ቻምፒዮና የመጀመሪያ ተሳትፎው ሲሆን፤ በ10ሺ ሜትር የወርቅ በ5ሺ ሜትር ደግሞ የብር ሜዳሊያ ነበር ያጠለቀው። ከሁለት ዓመታት በኋላም ጉተንበርግ በተዘጋጀው ቻምፒዮና በ10ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያውን መድገም ችሏል። በአቴንስ እና ሴቪላ በተካሄዱት ውድድሮችም በተመሳሳይ የወርቅ ሜዳሊያውን የግሉ አድርጓል። እአአ የ2001 የኤድመንተን ቻምፒዮና የመጀመሪያውን የነሃስ ሜዳሊያ ሲወስድ፤ በመድረኩ የመጨረሻ ተሳትፎውን ያደረገበት የፓሪሱ ቻምፒዮናም አትሌቱን በብር ሜዳሊያ ነው ያሰናበተው። አሁን ኃይሌ ራሱን ከውድድሮች ካገለለ ዓመታትን አስቆጥሯል። ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት መንበሩን በቃኝ ብሎ ቢያስረክብም አገራቸውን ወክለው ለመሮጥ ከተዘጋጁ አትሌቶች ጎን አይጠፋም። በስድስት ጊዜ የዓለም ቻምፒዮና ተሞክሮውን ነገ በሚጀምረው የኳታር የዓለም ቻምፒዮና ኢትዮጵያን ለሚወክሉ አትሌቶች እንደሚከተለው ያካፍላል። «ዓለም ቻምፒዮናን፤ በዓለም ላይ ያሉ ምርጥ አትሌቶች የሚሳተፉበት መሆኑ ለየት ያደርገዋል። በዳይመንድ ሊግ እና ሌሎች ውድድሮች ላይ የሚገኙት ጥቂቶች ሊሆኑ ይችላሉ፤ በዓለም ቻምፒዮና ግን በዓለም ላይ ‘አሉ’ የተባሉ አትሌቶች የሚሰባሰቡበት ነው»። ጠንካራ አትሌቶች የሚገናኙበትና የምርጦች ምርጥ የሚመረጥበትም ይኸው ውድድር በመሆኑ በአትሌቶች ዘንድ በልዩነት ይታያል። አትሌቶች ሃገራቸውን የሚወክሉበት እንዲሁም ሃገራት ባስመዘገቡት ውጤት በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ደረጃ የሚያገኙበት በመሆኑም፤ ስፖንሰር አድራጊ ተቋማትም ጭምር ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጡት አንጋፋው አትሌት ይጠቁማል። ሃገሩን ወክሎ በጥረቱ ውጤት ካስመዘገበባቸው ቻምፒዮናዎች ሁሉ እስካሁንም ከትውስታው ያልተሰረዙ ገጠመኞችም አሉት። «ከተካፈልኩባቸው ቻምፒዮናዎች ሁሉ እስካሁንም የማዝንበት አጋጣሚ የደረሰው በስቱትጋርት ነው። እአአ የ1993ቱ ቻምፒዮና በ5ሺ ሜትር አሸናፊነት አምልጦን የብር ሜዳሊያ ነበር ያገኘነው» ሲል ቁጭቱን ይናገራል። ገጠመኞቹ እነዚህ ብቻም አይደሉም ኃይሌ ይቀጥላል፤ «እአአ 2001 ኤድመንተን ላይ እኔና አሰፋ መዝገቡ ማሸነፍ በምንችለው ውድድር ላይ የፈጸምነው ስህተት ነው። በተለይ እኔ ለአምስተኛ ጊዜ አሸናፊ እንደምሆን በማመኔ መዘናጋት አሳይቼ ነበር፤ ባልተጠበቀ ሁኔታ ግን አንድ ኬንያዊ አትሌት አሸነፈን። ይህም እስካሁን እንደ እግር እሳት ነው የሚለበልበኝ» በማለት በድንገት ከመሃላቸው ፈትልኮ ወርቁን ስላጠለቀው ጥርሰ ፍንጭቱ ኬንያዊ አትሌት ቻርልስ ካማቲ ያስታውሳል። ከተካፈለባቸው ቻምፒዮናዎች ሁሉ አንጋፋውን አትሌት በተለየ የሚያስደስተው እአአ 1995 በስዊድን ጉተንበርግ የነበረው ተሳትፎ ነው። በዚህ ውድድር ላይ የመጨረሻውን 200ሜትር፤ የወቅቱ ጠንካራ አትሌቶች ከነበሩት፤ ፖል ቴርጋት፣ ካሊድ ካህ እና ሳላ ኢሱ ለማምለጥ ያደረገው ጥረት ያስደስተዋል። አጨራረሱን ሲያስታውስም ምናልባት ከ800ሜትር ሯጮች በላይ የፈጠነ እንደነበር ነው የሚገልጸው። ከትውስታው መልስም ነገ በዶሃ በሚጀመረው ቻምፒዮና ስለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አስተያየት ሰጥቷል። ከዳይመንድ ሊግ ውድደሮች በመነሳት በወንድም በሴትም በተለይ በ10ሺ ሜትር ጥሩ ጥሩ አትሌቶች አሉ። በዚህ ውድድር ላይ ግን ብልጠት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። በተለይ የመጨረሻዎቹ ሜትሮች ላይ የተለየ ነገር ካላደረጉ ልፋታቸው ሁሉ ገደል ነው የሚገባው። የመጨረሻው 100ሜትር ቀላል አይደለም በጣም ብዙ ነገር ነው የሚያበላሸው፤ በመሆኑም እዚህ ላይ አእምሯቸውንና ሰውነታቸውን መጠቀም አለባቸው። ብልጠት ካልታከለበት ሰውነት ብቻውን አሸናፊ አያደርግም፤ ብልጥ ከሆኑ ግን ሰውነትም ቢደክም ማሸነፍ ይቻላል በማለት የይቻላል ተምሳሌቱን ይናገራል። ቡድኑ ወደ ዶሃ ከመጓዙ ከሁለት ቀናት አስቀድሞም የብዙዎች ተምሳሌት የሆነው አትሌቱ ልምምድ በሚያደርጉበት አዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝቶ ምክርና ተሞክሮውን አካፍሏል። «ውድድር ‘እንዲህ ነው፤ እንዲያ ነው’ አይባልም ሁሉም የሰራውን ነው የሚያመጣው። ስታዲየሙ የሚያቀዘቅዝ መሳሪያ ስለተገጠመለት እዚህ ካለው አየር የተለየ አይሆንም። ከዚህ ባለፈ በአትሌቶችም ሆነ አሰልጣኞች መካከል አብሮነት አስፈላጊ ነው፤ የእናንተ አብሮ መሆን ብዙ ነገር ይቀይራል። የእናንተ በጋራ መስራት ከውጤትም በላይ ነው፤ ህዝቡም የሚፈልገው ይሄንኑ ነው። ሁሌም ሩጫ ስትሮጡ መጠንቀቅ ያለባችሁ የመጨረሻዎቹን 500 እና 600ሜትሮች ነው። ሌላውን ርቀት ሳትጨናነቁና ሳትፈሩ ዘና ብላችሁ ሸፍኑ። በመካከለኛ ርቀትም ቢሆን ሩጫውን ማንበብ የግድ ነው፤ መዘናጋት አያስፈልግም» ሲልም አስገንዝቧል። ቀጥሎም፤ «አንዳችሁ ለሌላችሁ ውጤት አስፈላጊ እንደሆናችሁ እንዳትዘነጉ። ልብ አድርጉ፤ አሰልጣኞችም ሆናችሁ አትሌቶች ‘እኔ ውጤት ላምጣ እንጂ ስለሌላው አያገባኝም’ ማለት የለባችሁም። ሌላው ማስታወስ ያለባችሁ እናንተን የሚመለከቱ ብዙ ሺ ታዳጊዎች አሉ፤ ውጤት ሁለተኛ ነገር ነው ዋናው እርስ በእርሳችሁ የምታሳዩት ስነ-ምግባር ነው። እናንተ ውጤት ስላመጣችሁ ብቻ መደሰት ሳይሆን ሌላውንም መደገፍ በተመሳሳይ አስፈላጊ ነገር ነው። አሰልጣኞች፣ የቡድን መሪዎችና ቴራፒስቶችም ከልምምዱ ባሻገር ስነ-ምግባር ላይም ማተኮር አለባችሁ»ም ብሏል። በመጨረሻም ለብሄራዊ ቡድኑ መልካም ውድድር እንዲሆን ተመኝቷል።አዲስ ዘመን  መስከረም 15/2012 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=19334
de145a9d2c684352171808298fe88db4
90afe926eb1e877881423a6f6c57ef1c
በትግራይ ክልል ለተስተጓጎለው የቴሌኮም አገልግሎት የክልሉ ልዩ ኃይል ተሳታፊ እንደነበር ተገለጸ
ክፍለዮሐንስ አንበርብርአዲስ አበባ፡- ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ከ37 ደቂቃ ላይ በሰሜን ሪጅን ትግራይ ክልል ለተቋረጠው የቴሌኮም አገልግሎት የክልሉ ልዩ ኃይል ተሳታፊ እንደነበር ተገለፀ። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፣ በሰሜን ሪጅን የቴሌኮም አገልግሎት ላይ የደረሰውን የአገልግሎት መቋረጥ አስመልከተው ትናንት በስካይ ላይት ሆቴል ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፤ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን ሪጅን አገልግሎት ተቋርጧል። ይህም በመቀሌና በሽሬ የሚገኙ ዋና ጣቢያዎችን አማራጭ የመገናኛ መስመሮች በሙሉ በመቁረጥና የኮመርሻል ኃይል አቅርቦት ከጥቅም ውጪ በማድረግ የተፈፀመ ነው። የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት እንዲቋረጥም ሲደረግ በዕለቱ የግቢ ጥበቃ ላይ የነበሩትን የቴሌኮም ሠራተኞችን በኃይል ከግቢ እንዲወጡ በማድረግና አካባቢው በልዩ ኃይል በመጠበቅ የተከናወነ እንደነበር አስታውሰዋል። በዕለቱ በሰሜን ሪጅን ላይ የቴሌኮም አገልግሎት መቋረጡን የሚያሳይ መረጃ በማዕከል ከሚገኘው የኔትወርክ መቆጣጠሪያ ሲስተም ለቴክኒክ ቡድንና ለከፍተኛ አመራሩ መድረሱን ያስታወሱት ሥራ አስፈጻሚዋ፤ በወቅቱ ግን ችግሩን ይህ ነው ብሎ በቅጽበት መናገር እንዳልተቻለ አስረድተዋል። ሆኖም በሂደት በተደረገ ምርመራና በተንቀሳቃሽ ምስል በተደገፈ መረጃ መረዳት የተቻለው አገልግሎቱን ሆን ተብሎ እንዲቋረጥ ተደርጓል። ችግሩ ከታወቀ በኋላም ሁኔታዎችን የመከታተልና ተጨማሪ አገራዊ አደጋ እንዳይከተልም አስፈላጊው እርምጃ ተወስዷል። እንደ ሥራ አስፈፃሚዋ ገለፃ፤ በአሁኑ ወቅት የተስተጓጎለውን የቴሌኮም አገልግሎት እንደገና እንዲጀምር ጥረት እየተደረገ ሲሆን በዳንሻ፣ ተርካን፣ ሁመራ፣ ሽራሮ፣ ማይፀብሪ፣ ማይካድራ፣ ኮረም በከፊል አገልግሎት የጀመረ ሲሆን በአላማጣ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎቱ ተጀምሯል። ሆኖም በመላ ክልሉ የቴሌኮም አገልግሎት ለማስጀመር በሚደረገው ጥረት የኃይል መቋረጥ፣ የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች መቆራረጥና የሰው ኃይል ለማሰማራት ምቹ ሁኔታ አለመኖር አገልግሎቱን ወደቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ ፈታኝ ሆኗል። አገልግሎቱን ማቋረጥ የሚችሉ ግለሰቦች የተሳተፉበት መሆኑንና የክልሉ ልዩ ኃይልም በዚህ እኩይ ተግባር ተሳታፊ መሆኑን ከሥፍራው የደህንነት ካሜራዎች በተቀረፀ ተንቀሳቃሽ ምስል መረዳት የተቻለ መሆኑን የገለፁት ሥራ አስፈፃሚዋ፤ ከድርጊቱ ጋር የተያያዙ በርካታ ጉዳዮች በምርመራ ላይ መሆናቸውን ጠቁመው በቀጣይ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረጉ አረጋግጠዋል። ከኢትዮ ቴሌኮም የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በመላ አገሪቱ ከ16ሺ በላይ ቋሚ ሠራተኞች ያሉት ተቋም ሲሆን ዘርፈ ብዙ አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን የቴክኖሎጂ ሥራዎችን በማከናወን አገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚተጋ ተቋም ነው።አዲስ ዘመን ታህሳስ 2/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37110
06752989b7107cb8d817a2dbc19342ad
179bcc778abc5e6be98522e961d47c0d
ለሁሉም ክፍት የሆነ የወርልድ ቴኳንዶ ውድድር ተጠናቀቀ
 ከሁለት መቶ በላይ ስፖርተኞች የተሳተፉበት ለሁሉም ክፍት የሆነ የወርልድ ቴኳንዶ ውድድር ተጠናቀቀ፡፡ በብሔራዊ ስፖርት ፌዴሬሽን አዳራሸ በተካሄደው ውድድር ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ስፖርተኞች ተሳታፊ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ጥር 2012 ዓ.ም ሞሮኮ ላይ የሚካሄደውን የኦሊምፒክ ማጣሪያ የቴኳንዶ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፋ ስፖርቶችን መምረጥና በተለያየ ጊዜ በቴኳንዶ ውድድር ዕድል ያላገኙ ስፖርተኞችን በማሳተፋ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ ማድረግ የውድድሩ ዓላማ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከውድድሩ ጎን ለጎን ከ300 በላይ የወርልድ የቴኳንዶ ስፖርተኞች ከ1ኛ እስከ 4ኛ የዳን ዕድገት ፈተና የተሰጣቸው መሆኑንም ፌዴሬሽኑ አሳውቋል፡ ፡ ውድድሩ በሁለቱም ፆታ የተካሄደ ሲሆን በወንዶች ከ58 ኪሎ ግራም በታች፣ ከ68 ኪሎ ግራም በታች እና ከ80 ኪሎ ግራም በታች ተከፍሎ ተካሂዷል፡፡ በሴቶች ደግሞ ከ49 ኪሎ ግራም በታች፣ ከ67 ኪሎ ግራም በታች እና ከ67 ኪሎ ግራም በታች መካሄዱ ተገልጿል፡፡ በዚህም መሠረት በውድድሩ ፍጻሜ በወንዶች ከ68 ኪሎ ግራም በታች ጀማል ሀጂ ከኦሮሚያ ክልል የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሲሆን ገመቺስ ኤፍሬም ከአዲስ አበባ ብር ሜዳሊያ ማጥለቅ ችሏል፡፡ ዮሐንስ ለማ ከኦሮሚያ ክልልና አብዱል ፈታ ሠፋ ከአዲስ አበባ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል፡፡ በወንዶች ከ58 ኪሎ ግራም በታች ፍጹም ዘውዴ ከአዲስ አበባ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያሸንፍ፣ ባስልኤል ደረጄ ከደቡብ ክልል የብር ሜዳሊያ፣ አብዱራህማን ሰፋ ከአዲስ አበባ እና ሁሴን ሀጂ ከኦሮሚያ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል፡፡ በወንዶች ከ80 ኪሎ ግራም በታች በተካሄደው ውድድር ሲያንሰው ዘኪ ከደቡብ ክልል የወርቅ ሜዳሊያ ወስዷል፡፡ በረሳ አብዲሳ ከኦሮሚያ ክልል የብር ሲያሸንፍ፣ ስንታየው ዘመድኩን ከኦሮሚያ እና ቁምላቸው ፈንቴ ከአማራ የነሐስ ሜዳሊያ ማጥለቅ ችለዋል፡፡ በሴቶች ከ49 ኪሎ ግራም በታች ውድድር ሰብለ ፈለቀ ከአማራ ክልል የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ስትሆን ሶፊያ በለጠ ከኦሮሚያ ክልል የብር ሜዳሊያ ማጥለቅ ችላለች፡፡በዚሁ ውድድር አጸደ አድማሱ ከኦሮሚያ እና ማስተዋል ታረቀኝ ከአማራ የነሐስ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በሴቶች ከ57 ኪሎ ግራም በታች መቅደስ አስማረው ከአዲስ አበባ የወርቅ ሜዳሊያው ባለቤት ስትሆን ምህረት ሞላ በተመሳሳይ ከአዲስ አበባ የብር ሜዳሊያውን አጥልቃለች፡፡አሜን ሚኤሴ እና አያንቱ ሚኤሴ ከኦሮሚያ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በሴቶች ከ67 ኪሎ ግራም በታች አያና አሠፋ ከደቡብ የወርቅ፣ መስከረም ሽፈራው በተመሳሳይ ከኦሮሚያ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያሸንፉ፣ ረድኤት ጌታቸው ከአዲስ አበባ እና ወርቄ ሚልኬሳ ከኦሮሚያ የነሐስ ተሸላሚ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል::አዲስ ዘመን  መስከረም 16/2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=19535
fbaf1eefa4f17a9626b3038c01dd0baf
b9c6c9b3e8930733dc8ee1bea1c2b446
ኮ ዳግም የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
 የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሆነው ባለፉት አራት ዓመታት የቆዩት እንግሊዛዊው ሴባስቲያን ሎርድ ኮ በድጋሚ ተመርጠዋል። የኦሊምፒክ የቀድሞ የ1ሺ500 ሜትር ቻምፒዮኑ ኮ በዶሃ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በተካሄደው የአባል አገራት ጉባኤ ለአንድ የኦሊምፒክ ዓመት በመሪነት እንዲቀጥሉ ዕድል እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡ ኮ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ስልጣን የመጡት እአአ በ2015 ሲሆን፤ በስልጣን ላይ በቆዩባቸው ጊዜያትም በሩሲያ የአበረታች ቅመሞች ጉዳይ እንዲሁም በቅርቡ ከደቡብ አፍሪካዊቷ አትሌት ካስተር ሰመኒያ ጋር በገቡት እሰጣ ገባና በጠንካራ ውሳኔ ሰጪነታቸው ይታወቃሉ። በተለይ ከአበረታች ቅመሞች ጋር በተያያዘ የሰሯቸው ስራዎች እንደሚያስደስታቸውም ነው የሚናገሩት። በዚህ ምርጫ ላይም 203ቱም አባል አገራት ያለ አንዳች ማቅማማት ሙሉ ድምጻቸውን እንደሰጧቸው የሮይተርስ ዘገባ ያሳያል። የሁለት ጊዜያት የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱ ኮ ዳግም መመረጣቸውን ተከትሎም «ቀላል የሚባል ቆይታ አልነበረም፤ አራቱ ዓመታት ከባድ ነበሩ። ማሰብ ያለብን ስፖርቱን ስለማሳደግና የስፖርት ቤተሰቡን ስለማርካት ነው። አሁን ስፖርቱ ባለበት የአንድነት ስሜት እኮራለሁ፤ አሁንም ጥሩ የምንሰራበት ጊዜ ላይ እንገኛለን» ሲሉም ገልጸዋል ። ኮ የማህበሩን የመሪነት ስፍራ የተቆናጠጡት እአአ በ2015 በቤጂንግ የዓለም ቻምፒዮና ሲሆን፤ ዩክሬናዊውን የቀድሞ ምርኩዝ ዝላይ ባለክብረወሰን ሰርጄ ቡቡካን ሰፊ በሆነ ድምጽ በመርታት ነበር። ከእርሳቸው በፊት ቦታውን ለ16ዓመታት የያዙት ካሜሩናዊው ላሚን ዲያክ ለሩሲያ አትሌቶች ሽፋን ይሰጣሉ በሚል ምክንያት በፈረንሳይ ፖሊሶች ክስ ተከፍቶባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ የዓለም አትሌቲክስ የስራ አስፈጻሚ አባላት 13 ወንበር ያለው ሲሆን፤ በደንቡ መሰረትም ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ ስድስት የሚሆኑት ሴት መሆን ይገባቸዋል። በዚህም መሰረት ጉባኤው አዲስ ሴት ምክትል ፕሬዚዳንት መርጧል። የምክትልነት መንበሩን የተቆናጠጡት ኮሎምቢያዊቷ አንጋፋ አትሌት ዚሜና ሬስትሬፖ ናቸው። የ50ዓመቷ ሬስትሬፖ እአአ 1992ቱ የባርሴሎና ኦሊምፒክ በ400ሜትር ነሃስ በማጥለቅ የመጀመሪያዋ ሴት ኮሎምቢያዊት አትሌት ናቸው። መመረጣቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ላይም «ይህ ለእኔ እና ለአገሬ ትልቅ አጋጣሚ ነው። እንደማስበው ከሆነ ከበፊቱ ይልቅ አሁን እኛ ሴቶች የተሻለ ዕድል እያገኘን ነው፤ በምክር ቤቱ ሰባት ሴቶች አለን። ይህ በጣም ትልቅ ቁጥር ነው፤ በዚህ ደግሞ ደስተኛ ነኝ» ማለታቸውን ዘገባው አስነብቧል። ፕሬዚዳንት ኮ የምክትላቸውን መመረጥ ተከትሎም « የቀድሞዋ አትሌት ዚሜና ስፖርቱን ለማሳደግ በምናደርገው ጥረት ጥሩ ይረዱናል። ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም ተጨማሪ የምክር ቤት አባል በማግኘታችን ደስተኛ ነኝ፤ ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው» ብለዋል።አዲስ ዘመን  መስከረም 16/2012 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=19544
736e9e7d2a2f55669c95f89d5f7499bf
8fd978e852b0b7198ec9947d908ae603
አወዛጋቢው መዋቅር በተሻረበት ዝግ ስብሰባ ምን ተባለ?
የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከወትሮው በተለየ በአጨቃጫቂ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ መቆራረጥ እንዲሁም በአሰልቺ የውድድር መርሐ ግብር ሳይጠናቀቅ ተጠናቋል። የ2012 ፕሪሚየር ሊግን ችግር የጸዳ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ የሚናገረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፤ መስከረም 5 ቀን 2012 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ፕሪሚየር ሊጉን በተወሰነ ደረጃ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለቶች የፀዳ ለማድረግ አዲስ የውድድር ሥርዐት ወይም መዋቅር መዘርጋቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ፌዴሬሽኑ በወቅቱ እንዳስታወቀው ፤ በ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24 ቡድኖች በሁለት ምድብ ተከፍለው ውድድራቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አወል አብዱራሂም፤ ሊጉ በሁለት እንዲከፈል የተደረገበት ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል መፍትሄ እንዲሰጥ በማሰብ መሆኑን ነበር በጋዜጣዊ መግለጫው የተናገሩት። በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተግባራዊ የሚደረገው አዲሱ የሊግ አደረጃጀት ወቅታዊ የአገሪቱን ሁኔታ መሰረት ያደረገ መሆኑን አስቀምጠዋል። በዋናነት የሊግ አደረጃጀት መለወጥ ምክንያት የሆነው በክለቦች መካከል የተፈጠረ አለመግባባት ሲሆን፤ ለጊዜው መገናኘት የሌለባቸውን ክለቦች በተቻለ መጠን አለማገናኘት እንደ መፍትሄ ተወስዷል። በዚህም ባለፈው ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ውድድር ሲገናኙ በስፖርታዊ ጨዋነት ችግር ተስተውሎባቸዋል የተባሉ ቡድኖች ለአብነትም ወላይታ ድቻ፣ ሲዳማ ቡና እንዲሁም የአማራ ክልል ከትግራይ ክልል ክለቦች ጋር እንዳይገናኙ ለማድረግ ነበር የታሰበው። ፌዴሬሽኑ በውድድር ዓመቱ ተግባራዊ ሊያደርገው የነበረው አዲሱ የሊግ አደረጃጀት ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጥያቄዎች ማስነሳቱ አልቀረም። በተለይ እግር ኳስ የሠላም መፍጠሪያና አንድነትን ማጠናከሪያ መድረክ ሆኖ ሳለ አዲሱ የሊግ አደረጃጀት ህዝብን ከህዝብ የሚያራርቅ እንደሆነ ትችቶች ሲሰነዘሩበት ሰንብቷል።በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመሳሰሉ አንጋፋ የአዲስ አበባ ክለቦች የፌዴሬሽኑን ሃሳብ በፅኑ ሲቃወሙ ታይቷል። እነዚህ ክለቦች ጉዳዩን ወደ መንግስት እስከ መውሰድ ደርሰውም ማስቆም ችለዋል። በጉዳዩ ላይ በሸምጋይነት ጣልቃ የገባው የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ከትናነት በስቲያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተመካክሮ ፌዴሬሽኑ ተግባራዊ ለማድረግ ያሰበውን የሃያ አራት ክለቦች ሊግ መዋቅር ማገዱ ተሰምቷል። ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽነሮች ጋር ምክክር ያካሄደው ስፖርት ኮሚሽን ፌዴሬሽኑ ያሰበው አዲሱ መዋቅር እንዲታገድ ሲወስን በዋናነት ምክንያት ተደርጎ የቀረበው አዲሱ መዋቅር ጥናት ሳይደረግበት ወደ ተግባር እንዲለወጥ በመደረጉ መሆኑ ታውቋል። ስፖርት ኮሚሽን ያዘጋጀውን ስብሰባ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶክተር ሒሩት ካሳው በሰብሳቢነት፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር፣ የዘጠኙ ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የስፖርት ኮሚሽን አመራሮች እንዲሁም የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ተሳታፊ ያደረገ ነበር። በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ በ2011 ዓ.ም በእግር ኳሱ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች ምን እንደሆኑ በዝርዝር አስረድተዋል ።አቶ ኢሳያስ ሁኔታውን በማስረዳት እየተፈጠሩ ያሉ አለመግባባቶችን ለመቀነስ እንደመፍትሄ በጊዜያዊነት በሁለት ምድብ የተከፈለ 24 ቡድኖች የሚካፈሉበት ውድድር ማዘጋጀት እንዳስፈለገ ተናግረዋል። በስብሰባው ታዳሚ የነበሩት አንዳንድ የፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ አባላት መካከል አቶ አሊሚራና አቶ አበበ ገላጋይ «በፌዴሬሽኑ የተላለፈው ውሳኔ ክለቦች ሳይማከሩበት እና ጥናትን መሠረት ያላደረገ መሆኑን በወቅቱም በሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ወቅት አጽንኦት ሰጥተን ተናግረን ነበር። ሆኖም እኛም በማናውቀው መልኩ የተወሰነ ውሳኔ ነው» በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል። ይህም በፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚዎች መካከል መግባባት እንደሌለ ያሳበቀና ትዝብት ላይ የጣላቸው ጉዳይ ሆኗል። በክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች በኩል በተለይ የአማራና የትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ፣ የፌዴሬሽኑ ውሳኔ በእጅጉ ተኮንኗል። በውድድሩ የሚሳተፉት ቡድኖች ሆነው የአማራና ትግራይ ክልል ክለቦች እንዳይገናኙ የተወሰነው ውሳኔን እንደማይቀበሉትም አበክረው ሲገልጹ ተደምጠዋል።እግር ኳስ የሠላም እና የማቀራረቢያ መድረክ መሆኑን አስረግጠው በመናገርም የፌዴሬሽኑን ውሳኔ እንደማይቀበሉት አሳስበዋል። የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥናት በማስጠናት በውስጥ ውድድር ተካሂዶ በኋላም በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ውድድሩ ይጠናቀቅ በማለት ያቀረበው ሃሳብ የሚያስመሰግን ሆኖም ተነስቷል። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ግን እንደ መፍትሄ ከመቀበል ይልቅ የራሱን መንገድ መከተሉ ስህተት መሆኑ ተጠቁሟል። በተጨማሪም ፌዴሬሽኑ ከክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ጋር ተቀራርቦ የመስራት ችግሮች እንዳሉበት ተነግሯል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ በበኩላቸው ፤በፕሪሚየር ሊጉ 24 ቡድኖች መሳተፋቸውን እንደማይደግፍ እና ከኦሊምፒክ መርህ አንጻር ክልሎች እና ህዝቦች እንዳይገናኙ ማድረግ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። የኢፌዴሪ ባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ሚኒስቴር ዶክተር ሒሩት ካሳው፤አለም ዓቀፍ የእግር ኳስ ማህበር ፊፋ ላስቀመጠው ደንብ እና ህግ ተገዥ በመሆን አባል አገራቱም ለተቀመጠው መመሪያ ተገዥ እንዲሆኑ በማድረግ እያስተዳደረ በመገኘቱ ተፈሪና ተቀባይነት ያለው ተቋም መሆን እንደቻለ አስታውሰዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፊፋ ላወጣው ደንብና መመሪያ ተገዥ በመሆን እግር ኳሱን መምራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን የሃሳብ ልዩነት በውስጥ እንዲፈታና፤ 24 ቡድኖች በሁለት ምድብ ተከፍለው የሚጫወቱበት መዋቅር ለጊዜው እንዲቆም በስተመጨረሻ ውሳኔ ላይ ተደርሷል። በቀጣይም ክለቦች በተገኙበት ውይይት በማድረግ ዘላቂ መፍትሄ እንዲቀርብ ተወስኗል። ስፖርት ኮሚሽኑም ጉዳዩን በጥንቃቄ እንደሚከታተለው በማስታወቅ ስብሰባው ተጠቃሏል።አዲስ ዘመን  መስከረም 15/2012 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=19340
9193695982a17db79576514d0eb8ebcd
a9ef27f05d1dcba8ea0b969dcced82fa
‹‹የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት›› ቀጣዩ የውዝግብ ምዕራፍ
 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጥድፊያ ውሳኔ ላይ በመድረስ የሚስተካከለው የለም ቢባል አልተጋነነም። በአጭሩ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ‹‹የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት›› እንደሚባለው ዛሬ በጥድፊያ ይወስናል ነገ ይሽረዋል። እሱ ባይሽረው እንኳን ሌሎች በተቃውሞ እንዲሽረው ያደርጉታል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንደ አዲስ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ካለፉት ሃያ ዓመታት በላይ የተወዳዳሪ ክለቦችን ቁጥር ሲቀያይር ታይቷል። የተወዳዳሪ ክለቦች ብዛት በሚቀያየርበት ወቅት በጥናት አለመደገፉም ዘወትር ከተቃውሞ ነፃ ሆኖ አያውቅም። ዘንድሮም ከስፖርታዊ ጨዋነትና ከስቴድየም ግጭቶች ጋር በተያያዘ ለጊዜውም ቢሆን መፍትሄ ይሆናል በሚል ፌዴሬሽኑ የተሳታፊ ክለቦችን ቁጥር ወደ ሃያ አራት አሳድጎ በሁለት ምድብ ለማካሄድ ማሰቡ ከዚህም ከዚያም ተቃውሞ አስነስቶበት በመንግሥት ጣልቃ ገብነት ከመታገድ አልዳነም። በቀጣይም ክለቦች ተወያይተው አዲስ መዋቅር እንደሚሰራ ይጠበቃል። ያም ሆኖ የውድድር ዓመቱ ከመጀመሩ በፊት ባለው ጥቂት ጊዜ ምን ዓይነት ጥናት ተጠንቶ ወደ ተግባር እንደሚገባ የሚያውቁት የእግር ኳሱ አመራሮች ብቻ ናቸው። ይህም ቀጣይ ሌላ የውዝግብ ምዕራፍ እንደሚከፍት ስጋት ያላቸው የስፖርት ቤተሰቦች ከወዲሁ በጉዳዩ ላይ ትኩረት እንዲሰጡ አድርጓል። ወትሮውንም ቢሆን የተሳታፊ ክለቦች ብዛት ከ12 ወደ 14፣ ከ14 ወደ 16 ያደገበት አሳማኝ ምክንያት አልነበረውም። የሊጉ ክለቦች ቁጥር 16 መሆኑ የአገሪቱን አቅም ያገናዘበ እንዳልሆነ ብዙዎች ይስማማሉ በምክንያትም ይሞግታሉ። ፊፋም ከ16 ይልቅ 14 ክለቦች ያሉት ፕሪሚየር ሊግ ቢሆን መልካም ነው ሲል ምክረሃሳብ እንደሰጠን ይሰማል። የሊጉ ክለቦች ቁጥር 14 በነበረበት በ2004 ዓ.ም. መቀመጫቸውን ሸገር ላይ ያደረጉ ክለቦች ብዛት ሰባት ነበር። የሊጉን እኩሌታ ቁጥር መያዛቸው በሌሎች የክልል ክለቦች ላይ የማይገባ የፉክክር ጥቅም ያስገኝላቸው ነበር። በሰንጠረዡ ግርጌ የጨረሰው ፊንጫ ስኳር በመኪና እየተዟዟረ ተዳክሞ ሲጫወት፣ ሰባቱ ክለቦች ብዙሃኑን የሊግ ጨዋታዎች ያለጉዞ ድካም በአዲስ አበባ ያካሂዱ ነበር። በዚያ ዓመት በሰንጠረዡ እስከ አራተኛ የነበረውን ቦታ ይዘው ያጠናቀቁት የአዲስ አበባ ክለቦች መሆናቸው አያስገርምም። በሊጉ በጨዋታ የሚቆጠረው አማካይ የጎል መጠን 2.34 የነበረ ሲሆን እስካለፈው 2011 ድረስ ይህን ያህል ጎል በአማካይ የተመዘገበበት ዓመት ከዚያ ወዲህ አልታየም።አምና ደደቢት በደረሰበት ከባድ የፋይናንስ ችግር ምክንያት ስብስቡን በማሳሳቱ የሊጉ እጅግ ደካማው ቡድን በመሆን በዘጠኝ ዓመታት ከታየው ሁሉ መጥፎውን የጎል ዕዳ ይዞ ወርዷል። ይህም የሊጉን የጎል ብዛት ያለምክንያት አሳድጎታል።የ14 ክለቦች ሊግ ከ16 ክለቦች ሊግ የተሻለ ንጻሬ እንዳለው በርካታ ምክንያቶችን መደርደር ይቻላል። በጨዋታዎች መካከል በቂ የማገገሚያ ጊዜ የሚሰጥ መርሐግብር ስለነበር በንጽጽር ያልተዳከሙ ተጫዋቾች በየጨዋታው የመገኘታቸው ዕድል ከፍ ያለ ስለነበር የጨዋታውም ግለት የተሻለ እንደሚሆን ጥርጥር አይኖርም። ‹‹የሊግ ክለቦች ቁጥር የሚጨመርበትና የሚቀነስበት በጥናት የጎለበተ ስፖርታዊ ምክንያት መኖር ነበረበት›› የሚሉ የስፖርት ቤተሰቦች ሌላው ቢቀር በዓመት የ58 ጨዋታ ልዩነት ስለፈጠረ፣ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ከሊጉ መርሃግብር ጋር ተጣጥሞ የመከናወኛ ጊዜ በማጣቱ ለዛ ቢስ እንዲሆን ምክንያት ሆኗል።የሊጉ ተወዳዳሪዎች ብዛት በመደበኛነት 16 ሲደረግ የሊጉ አማካይ የጎል መጠን እያሽቆለቆለ መምጣቱን ባለሙያዎች በስታትስቲካዊ መረጃ አስደግፈው ያስቀምጡታል። በሊጉ የአዲስ አበባ ክለቦች ብዛት በቀነሰ ቁጥር የቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ግብ የማስቆጠር አቅም እየወረደ ሊሄድ መገደዱን እዚህ ጋር ያነሳሉ።በስምንት ዓመት ውስጥ የቅዱስ ጊዮርጊስ የዓመቱ መጨረሻ የግብ ክፍያ ከ39 ወደ 10 አሽቆልቁሏል። የሊጉ የጨዋታ አማካይ ጎል መጠንም ከ2004 እስከ 2010 ባለው የጊዜ ርቀት በጨዋታ በአማካይ በ0.48 ጎል ቀንሷል። ያለግብ የሚጠናቀቁ ጨዋታዎች ብዛት እየጨመረ፣ የሊጉ አዝናኝነት እየቀነሰ ሲመጣ ግን ያስተዋለው የለም።ኢትዮጵያ ቡና የሊጉ ቻምፒዮን ከሆነበት ከ2003 ዓ.ም ወዲህ በየጨዋታው የሚሰበስበው አማካይ ነጥብ ከ2.1 ወደ 1.3 አሽቆልቁሏል። በሊጉ ላይ ሰባት የአዲስ አበባ ክለቦች በነበሩበት 2003 እና ሦስት ብቻ በቀሩበት በ2011 መካከል ቡና በአማካይ በየጨዋታው የ0.8 ነጥብ ማሽቆልቆል አሳይቷል። በተመሳሳይ በጎል መጠንም ቢሆን በሁለቱ ዘመናት መካከል በጨዋታ 0.8 ጎል ቀንሷል። ሊጉ በዚሁ መልኩ ከቀጠለ፣ ሁለት የሸገር ክለቦች ብቻ በቀሩበት በ2012 የኢትዮጵያ ቡና ዕጣ ምን ይሆናል?የአስራ አራት ጊዜ ቻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስም ቢሆን ከፍተኛ ጎል ካስቆጠረበት ከ2006 ወዲህ በአምስቱ ዓመታት ‹‹የጎል ምርቱ›› ቀንሶበታል። ቢያንስ የ27 ጎሎች ልዩነት አሳይቷል። ይህ የሆነው በአምናው ውድድር ‹‹ፈረሰኞቹ ሦስት ጨዋታዎችን ባለመጫወታቸው ነው›› የሚል ሙግት ሊነሳ ይችላል። ነገር ግን ሦስቱን ጨዋታዎች ቢጫወቱና በእያንዳንዳቸው ስምንት፣ ስምንት ጎሎችን ቢያስቆጥሩ እንኳን ልዩነቱ የሚጠብ አይሆንም። በ2006 አንድ ክለብ 26 ጨዋታዎች ሲጫወት፣ 30 ጨዋታዎች ከሚያደርግበት 2011 ጋር በአራት ጨዋታ እንደሚያንስም ልብ ይሏል። የጨዋታዎች ቁጥር በዝቶ የጎሉ መጠን ይህን ያህል ዝቅ የሚልበት አንድ አንገብጋቢ ምክንያት ከሌለ በስተቀር በጤና እንዳልሆነ ግልጽ ነው።በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በደርሶ መልስ የሚደረገው ውድድር ከ22 ዓመት በፊት በ1990 ዓ.ም ሲጀመር ይገመት የነበረው አደጋ ማለትም ሕዝቡን በጎሳ አደራጅቶ እርስ በርስ ያባላል የሚለው አደጋ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተግባር እየታየ ነው። አዲስ መዋቅር በተግባር ላይ ይዋል ከተባለ ይህንን አደጋ የሚያስወግድ መሆን አለበት እንጂ ያንኑ አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆን የለበትም። በተለይ በ2010 ዓ.ም እና በ2011 ዓ.ም የታዩትን ዓይነት ሁከቶች እንዲቀጥሉ ዕድል መክፈት የጤነኝነት ሊሆን አይችልም። የሊግ ጥራት የሚለካዉ የክለቦችን ቁጥር በመጨመር አይደለም። አካባቢያዊ እና ተቋማዊ የሆኑ መሠረታዊ ጥያቄዎችን የሊግ ውድድርን ችግር ሳያጠኑ ክለቦችን ወደ ፕሪሚየር ሊግ በማሳደግ ማምለጥ አይቻልም። ይህ ውሳኔ የፉክክር መርህን የሚጣረስ ፣ ክለቦች ለተዋረዳዊ ውድድር ያላቸውን ክብር እንዲዘነጉ የሚያስገድድም በመሆኑ ጊዜ ወስዶ ማየት ተገቢ ነው።አዲስ ዘመን መስከረም 17/2012  ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=19619
135e033700da3fc818f3247ff8a75edc
bab702c661a4cb7ff3acbe61468e4ddb
ቀነኒሳ በ2 ሰከንድ የማራቶን ክብረወሰን አመለጠው
የረጅም ርቀትና የአገር አቋራጭ ንጉሱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከረጅም ጊዜ ጉዳት ተመልሶ የማራቶን የዓለም ክብረወሰንን ለመስበር ተቃርቧል። ትናንት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን ቀነኒሳ ርቀቱን 2፡01፡41 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ በጀርመኗ መዲና ለሁለተኛ ጊዜ ነግሷል። ቀነኒሳ እ.አ.አ በ2016 የበርሊን ማራቶን ሲያሸንፍም የዓለም ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግቦ እንደነበረ ይታወሳል። ቀነኒሳ እ.አ.አ ለመጀመሪያ ጊዜ 2015 የፓሪስ ማራቶንን የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር ካሸነፈ ወዲህ በርቀቱ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት አትሌት ቢሆንም በተደጋጋሚ በሚገጥመው ጉዳት ውድድሮችን አቋርጦ ለመውጣት ሲገደድ ታይቷል። ለረጅም ጊዜ ከጉዳቱ ለማገገም ሲጥርም በርካታ ውድድሮች አምልጠውታል። ያምሆኖ ትናንት ከወደቀበት ተነስቶ ታሪክ መስራት እንደሚችል በማሳየቱ የዓለም መገናኛ ብዙኃንን ቀልብ ስቧል። በኳታር ዶሃ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ኢትዮጵያ እስከ ትናንት ድረስ የጠበቀችውን ውጤት ማምጣት ባለመቻሏ ቅር የተሰኙ የስፖርት ቤተሰቦችም በቀነኒሳ ድል ተፅናንተዋል። በኬንያዊው ድንቅ አትሌት ኢሉድ ኪፕቾጌ ተይዞ የሚገኘው የዓለም የማራቶን ክብረወሰን 2፡01፡39 ሲሆን ይህን ክብረወሰን ሌላ አትሌት እንደማይደፍረው ሲነገር ቆይቷል። ቀነኒሳ በትናንቱ ውድድር ምናልባትም ውሃ አንስቶ ለመጠጣት ያባከናት ሽርፍራፊ ሰከንድ ዋጋ አስከፈለችው እንጂ ይህን ክብረወሰን ማሻሻል እንደሚችል አስመስክሯል። ከቀነኒሳ ጎን ለጎን የዘንድሮው የበርሊን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የነገሱበት ሆኗል። ቀነኒሳን ተከትሎ ብርሃኑ ለገሰ 2:02:48 በሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ሲሳይ ለማ በ2:03:36 ሰዓት ሦስተኛ ሆኗል። በሴቶች መካከል በተካሄደው ውድድርም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። እሸቴ በክሪ የኢትዮጵያን ክብረወሰን 2:20:14 በሆነ ሰዓት በማሻሻል ጭምር ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ የቀድሞ የዓለም ቻምፒዮኗ ማሬ ዲባባ 2:20:21 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆናለች። ኬንያዊቷ ሳሊ ቺፕየጎ 2:21:06 ሰዓት ሦስተኛ፣ ሔለን ቶላ በ2:21:36 ሰዓት አራተኛ ሆነው ውድድሩን ጨርሰዋል። በውድድሩ ትልቅ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷት የነበረችው የቀድሞ የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮኗ አትሌት መሠረት ደፋር እስከ ሰላሳ ኪሎ ሜትር ገደማ ከመሪዎቹ ተርታ ሆና ብትታገልም ደረጃ ውስጥ ገብታ ማጠናቀቅ አልቻለችም።አዲስ ዘመን  መስከረም 19/2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=19710
b23332e8be51da4773c59a1c82db6a5b
69792fba0f88c8b013f2cf6fc8102db5
ከአስቆጪ ውጤት ጋር የተገኘች መፅናኛ
የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከተጀመረ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል። ኢትዮጵያ ትልቅ ውጤት የምትጠብቅበት የሴቶች አስር ሺ ሜትር ውድድር ከትናንት በስቲያ ምሽት ተካሂዶም በአትሌት ለተሰንበት ግደይ አማካኝነት የብር ሜዳሊያ ሊመዘገብ ችሏል። ቻምፒዮኗ አልማዝ አያና በመጨረሻ ሰዓት በጉዳት ምክንያት በውድድሩ መሳተፍ አለመቻሏን ተከትሎ ዓለማችን የርቀቱን አዲስ ቻምፒዮን በጉጉት ስትጠብቅ ነበር። ኢትዮጵያ በርቀቱ ብዙ ልምድ በሌላቸው አትሌቶች ለተሰንበት ግደይ፣ሰንበሬ ተፈሪና ነፃነት ጉደታ የተወከለች ቢሆንም የተለመደው የወርቅ ሜዳሊያ መመዝገብ አልቻለም። ይሁን እንጂ ወጣቷ አትሌት ለተሰንበት የወርቅ ሜዳሊያውን ለማጥለቅ ያደረገችው የአልሸነፍ ባይነት ትግል መፅናኛ የሆነውን የብር ሜዳሊያ ማምጣት ችሏል። በውድድሩ ከኢትዮጵያውያንና ከኬንያውያን አንፃር ብዙም የአሸናፊነት ግምት ያልተሰጣት ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን 30:17.33 በሆነ ሰዓት ማሸነፍ ችላለች። ከሦስቱ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ የሆነችው ነፃነት ጉደታ ውድድሩን ባቋረጠችበት አጋጣሚ ሰንበሬ ተፈሪና ለተሰንበት ሌሎቹን ተፎካካሪዎች ለመቁረጥ ትልቅ ጥረት አድርገዋል። ሆኖም ሰንበሬ ወደ ኋላ በመቅረቷ ለተሰንበት በጊዜ ለመምራት ጥረት አድርጋለች። ይህም በውድድሩ መጨረሻ ዋጋ አስከፍሏት በሲፈን ሃሰን የወርቅ ሜዳሊያውን እንድትነጠቅ ምክንያት ሆኗል። ለተሰንበት ወርቁን ላለመነጠቅ ያደረገችው ጥረት አድናቆት ሳይቸረው የሚታለፍ አይደለም። ርቀቱን 30:21.23 በሆነ የራሷ ምርጥ ሰዓት ሁለተኛ በመሆን አጠናቃ ለአገሯ ያስመዘገበችው የብር ሜዳሊያም በቻምፒዮናው የመጀመሪያና ትልቅ ክብር የሚሰጠው ነው። በውድድሩ ትልቅ የአሸናፊነት ግምት አግኝታ የነበረችው ኬንያዊት ሔለን ኦቢሪ ጭምር ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን ሲሳናት ታይቷል። ሆኖም የአገሯ ልጅ አግኒስ ቲሮፕ 30:25.20 በሆነ ሰዓት ሦስተኛ በማጠናቀቅ የነሐስ ሜዳሊያውን አጥልቃለች። ሰንበሬ ተፈሪ በስድስተኛነት ውድድሩን ፈፅማለች። ኔዘርላንድስ ለበርካታ ዓመታት ገንዘቧን በማፍሰስ ከሥልጠና ጀምሮ በተለያዩ መንገዶች ስታዘጋጃት የቆየችው አትሌቷ ሲፈን ሃሰን አሁን ፍሬ ማፍራት ችላለች። በአሰልጣኝና ሥልጠና ጋር በተያያዘ ሰፊ ክፍተቶች በኢትዮጵያውያን ዘንድ መኖሩንም ከውድድሩ ለመታዘብ ተችሏል። በርካታ የስፖርት ቤተሰቦችም የለተሰንበትን ጥረትና ያስመዘገበችውን የብር ሜዳሊያ በማድነቅ በርቀቱ የተለመደው የወርቅ ሜዳሊያ አልማዝና ጥሩነሽ ከሌሉ የለም ማለት ነው? በሚል ቅሬታቸውን በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛ መረቦች ሲገልፁ ለመታዘብ ተችሏል። ከዚሁ ከዓለም ቻምፒዮና ጋር በተያያዘ በመጀመሪያው ቀን በተካሄደው የሴቶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያን የወከሉት ሹሬ ደምሴ፣ ሩቲ አጋና ሮዛ ደረጄ ሦስቱም ውድድሩን አቋርጠው መውጣታቸው ይታወሳል። በዶሃ ያለውን ከፍተኛ የሙቀት መጠንና ወበቅ ለመቀነስ ታስቦ ለመጀመሪያ ጊዜ በእኩለ ሌሊት የተካሄደው የማራቶን ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያኑን ጨምሮ ሃያ ስምንት አትሌቶች አቋርጠው ለመውጣት ተገደዋል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድሩን ማቋረጥ ብቻም ሳይሆን በመኪና ተጭነው እስከመሄድና ሆስፒታል እስከ መግባት እንደደረሱ በስፍራው ያሉ ታዛቢዎች ተመልክተዋል። ሆኖም ኬንያዊቷ ሩዝ ቺፕጌቲች አስቸጋሪውን ሙቀት ተቋቁማ የወርቅ ሜዳሊያ ማጥለቅ ችላለች። ያለፈው ቻምፒዮና አሸናፊዋ በትውልድ ኬንያዊ የሆነችው የባህሬን አትሌት ሩዝ ቺሌሞ ሁለተኛ ስትሆን ናሚቢያዊቷ ሄሌሊያ ጆሃንስ ሦስተኛ ሆና ጨርሳለች። ከኬንያውያን አትሌቶች ጋር ተፎካካሪና ተመጣጣኝ ብቃት እንዲሁም ፈጣን ሰዓቶችን ይዘው ወደ ውድድር የገቡት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የነበረውን ጫና ተቋቁመው እስከ ውድድሩ ግማሽ እንኳን መሄድ አለመቻላቸው በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ በርካታ ጥያቄዎችን እያስነሳ ይገኛል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከኬንያውያን ጋር ተመሳሳይ አቅም ያላቸው እንደመሆኑ ከሥልጠና ጋር ተያይዞ የሚመጣ ችግር ውድድሩን ለማቋረጥ እንዳስገደዳቸው የሚናገሩም በርካታ ናቸው። የአየር ፀባዩ ለሁሉም አትሌቶች እኩል እንደመሆኑ በሥልጠና ወቅት ውድድር ላይ ከሚኖረው የአየር ፀባይ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ስፍራን መርጦ ዝግጅት ቢደረግ ይህ ሁሉ እንደማይከሰት ምክንያታዊ አስተያየት ያላቸውም የስፖርት ቤተሰቦች ጥቂት አይደሉም። አዲስ ዘመን  መስከረም 19/2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=19706
71bcea8ae0dc0c87e46e19572189b292
8783d01e57a66da3bce79909914663e3
የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳሊያ ተስፋዎች
 ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ስፖርት በተለይ ከምትታወቅባቸውና ውጤታማም ከሆነችባቸው ርቀቶች መካከል ይጠቀሳል፤ 5ሺ ሜትር። ከሁለት ዓመታት በፊት በለንደን በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ኢትዮጵያ በአትሌት ሙክታር እንድሪስ አማካኝነት የርቀቱ ቻምፒዮን መሆኗ ይታወሳል። በቅርቡ በተጠናቀቀው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይም በተመሳሳይ የዓለም ፈጣኑ ሰዓት የተመዘገበው በኢትዮጵያዊ አትሌት መሆኑ ይታወቃል። ይህም ከተጀመረ ዛሬ አራተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የዶሃ ዓለም ቻምፒዮና ላይ የርቀቱን ቀዳሚ የአሸናፊነት ግምት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እንዲያገኙ አድርጓል። በዚህ ውድድር ተጋባዥ ከሆነው ቻምፒዮኑ ሙክታር ባሻገር፤ ጥላሁን ኃይሌ፣ ሰለሞን ባረጋ፣ እንዲሁም አባዲ ሃዲስ አገራቸውን የሚወክሉ አትሌቶች ናቸው። ይሁን እንጂ አባዲ ሃዲስ ማጣሪያውን ማለፍ አልቻለም። ቀሪዎቹ አትሌቶች በግላቸው ያስመዘገቧቸው ሰዓቶች በርቀቱ ከሚሳተፉት አትሌቶች ሁሉ ፈጣን መሆኑ፤ የርቀቱ ክብር ዘንድሮም ከምሥራቅ አፍሪካውያኑ እጅ እንደማይወጣ ያመላከተ ሆኗል። በሦስት ቻምፒዮናዎች ላይ በተከታታይ መንገስ የቻለው እንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ ዘመን ከማብቃቱ ጋር በተያያዘም ሜዳሊያው የኢትዮጵያውያን ስለመሆኑ ግምታቸውን የሚያስቀምጡም በርካታዎች ናቸው። ኢትዮጵያ በቻምፒዮናው እስካሁን ድረስ ወርቅ አለማስመዝገቧን ተከትሎም እነዚህ ወጣት አትሌቶች የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳሊያ ተስፋ ሆነዋል። ሞ ፋራህን በመጨረሻው የመም ውድድሩ የረታው የዓለም ቻምፒዮኑ ሙክታር እድሪስ በዚህ ቻምፒዮና ላይ ተጋባዥ ቢሆንም በጉዳት ምክንያት በዛሬው ውድድር ተሳታፊ ላይሆን እንደሚችል ተገምቶ ነበር። ይሁን እንጂ ሙክታር ማጣሪያውን አልፎ ዛሬ በፍፃሜ ተፋላሚ እንደሚሆን አረጋግጧል። የሁለት ጀግና አትሌቶችን ስም አጣምሮ የያዘው ወጣቱ አትሌት ጥላሁን ኃይሌ በቀለ ለአሸናፊነት ከሚጠበቁት መካከል አንዱ ሲሆን፣ በሮም ዳይመንድ ሊግ ያስመዘገበው 12:52.98 የሆነ ሰዓት በዛሬው ውድድር ላይ የሚካፈሉት አትሌቶች ሁሉ ፈጣኑ ነው። በለንደኑ ቻምፒዮና በርቀቱ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ሌላኛው ወጣት አትሌት ሰለሞን ባረጋም በዚህ ውድድር የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ያገኘ አትሌት ነው። አትሌቱ እአአ በ2018 ያስመዘገበው ፈጣን ሰዓት 12:43.02 ከርቀቱ ተሳታፊዎች ሁለተኛው ምርጥ ሰዓት ነው። ሰለሞን የዓለም ቻምፒዮና ተሳትፎው ይህ ሁለተኛው መሆኑ የተሻለ ልምድ እንደሚያስገኝለት የሚታመን ሲሆን፤ ለፈጣኑ ሰዓት ያለው ቅርበትም የወርቅ ሜዳሊያውን ለማጥለቅ የሚሮጥ ያሰኘዋል። ባህሬናዊው ብርሃኑ ባለው 12:56.26 ሰዓት በማስመዝገብ ኢትዮጵያውያኑን አትሌቶች የሚከተል ከመሆኑ ባሻገር ለኢትዮጵያውያኑ ፈተና እንደሚሆንባቸውም ይጠበቃል። ኮማንደር ቶሌራ ዲንቃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ5ሺ እና 10ሺ ሜትር አሰልጣኝ፤ ርቀቱ በዓለም ላይ ፈጣን ሰዓት ባላቸው አትሌቶች የተዋቀረ መሆኑን ይጠቁማሉ። አዳዲስና ጥሩ ሰዓት ያላቸው ወጣት አትሌቶች ተሳታፊ የሚሆኑበትም ነው። በተጨማሪም ሁሉም አትሌቶቹ በዓመቱ ዳይመንድ ሊግ ላይ ርቀቱን በደንብ የሸፈኑ አትሌቶች መሆናቸው ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚረዳቸው በዝግጅታቸው ወቅት ለአዲስ ዘመን ገልጸዋል። በዓለም ቻምፒዮና በ5ሺ ሜትር የኢትዮጵያ ታሪክ እ.አ.አ 1991 ቶኪዮ ላይ ይጀምራል፤ በወቅቱ ፊጣ ባይሳ ኬንያዊውን አትሌት ተከትሎ በመግባት የብር ሜዳሊያ ነበር ያገኘው። ከሁለት ዓመታት በኋላም በስቱትጋርት ኃይሌ ገብረስላሴ እና ፊጣ ባይሳ ተከታትለው በመግባት የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች ሆነዋል። እ.አ.አ 2001 ኤድመንተን ላይ በተካሄደው ቻምፒዮና ሚሊዮን ወልዴ ሦስተኛውን የብር ሜዳሊያ እስካስመዘገበበት ጊዜ ድረስም ኢትዮጵያ በሦስት መድረኮች ከሜዳሊያ ሰንጠረዥ መግባት አልቻለችም ነበር። እ.አ.አ 2003 ቀነኒሳ በቀለ የነሐስ፣ ሄልሲንኪ በስለሺ ስህን የብር፣ በርሊን በቀነኒሳ የወርቅ፣ ዴጉ በደጀን ገብረመስቀል የነሐስ፣ ሞስኮ እና ቤጂንግ ሐጎስ ገብረሕይወት ብርና ነሐስ እንዲሁም ለንደን ላይ ሙክታር እድሪስ የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቁ አትሌቶች ናቸው። በርቀቱ ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬንያ በርካታ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ቀዳሚ ስትሆን፤ 14ሜዳሊያዎችን ወደ ካዝናዋ አስገብታለች። አምስት ሜዳሊያዎች ያሏት እንግሊዝ ደግሞ በወርቅ ሜዳሊያ ብዛት ሁለተኛ ስትሆን፤ በተከታይነት ኢትዮጵያ 2የወርቅ፣ 5የብር እና 4የነሐስ በጥቅሉ 11ሜዳሊያዎችን በወንድ አትሌቶች በማግኘት ሦስተኛ ስፍራ ላይ ተቀምጣለች። በዓለም ቻምፒዮናው የርቀቱ ክብረወሰን እ.አ.አ በ2003 የተመዘገበው 12:52.79 ሲሆን፤ ኬንያዊው አትሌት ኢሉድ ኪፕቾጌ ደግሞ የሰዓቱ ባለቤት ነው። ሌላው ዛሬ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚካፈሉበት ርቀት የ3ሺ ሜትር መሰናክል ሴቶች ምድብ ነው። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር እ.አ.አ 2013ቱ የሞስኮ ቻምፒዮና ነበር የነሐስ ሜዳሊያ በአትሌት ሶፊያ አሰፋ ያስመዘገበችው። ሶፊያ በዚህ ርቀት በ2012ቱ የለንደን ኦሊምፒክም ሦስተኛ የወጣች ቢሆንም፤ ቀድማት የገባችው አትሌት የአበረታች ቅመም ተጠቃሚነቷ በመረጋገጡ የብር ሜዳሊያውን ሶፊያ እንድትወስድ ተደርጓል። በዘንድሮው ቻምፒዮና ላይ አትሌት መቅደስ አበበ፣ ሎሚ ተፈራ፣ ዘርፌ ወንድምአገኝ እና አገሬ በላቸው ኢትዮጵያን ይወክላሉ። የ3ሺ ሜትር መሰናክል አሰልጣኝ ተሾመ ከበደ፤ አትሌቶቹ በራባት የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ ተሳታፊ በመሆናቸው ረዘም ላለ ጊዜ በሳምንት ስድስት ቀን በቀን ደግሞ ለሁለት ጊዜ በዝግጅት ላይ መቆየታቸውን ተናግሯል። በሄንግሎ በተካሄደው የሰዓት ማሟያ ውድድር ላይ የተመዘገበው ጥሩ ሰዓት መሆኑን የጠቆሙት አሰልጣኙ፤ በርቀቱ ያለውን ታሪክ ለመቀየር ቡድኑ ወደ ዶሃ ያመራ መሆኑንም አስረድተዋል። በዚህ ርቀት ኬንያውያን አትሌቶች ስኬታማ ሲሆኑ ባትሬክ ቼፕኮች ደግሞ በለንደን ቻምፒዮን መሆኗ አይዘነጋም። አትሌቷ ከ2018 ጀምሮ በተሳተፈችባቸው 17 ውድድሮች 15ቱን ያሸነፈች ጠንካራ አትሌት ስትሆን፤ በተያዘው ዓመት ያስመዘገበችው 8:55.58 የሆነ ሰዓት ደግሞ ፈጣኑ ነው። 9:03.71ሰዓት ያላት ኖራህ ጀሩቶ በ3ሺ ሜትር መሰናክል የአሸናፊነት ግምት እንዲሁም ፈጣን ሰዓት ያላቸው ኬንያውያን አትሌቶች ሁለተኛዋ ናት። እ.አ.አ የ2015 ቻመፒዮኗ ሃይቪን ኪያንግ 9:03.83 በሆነ ሰዓት ሦስተኛዋ ፈጣን አትሌት ናት። ለንደን ላይ ቻምፒዮን የነበረችው አሜሪካዊቷ ኤማ ኮቡርን አራተኛው ፈጣን ሰዓት ያላት ስትሆን፤ ከኬንያውያኑ አትሌቶች ጋር ብርቱ ፉክክር እንደምታደርግም ይጠበቃል።አዲስ ዘመን  መስከረም 19/2012 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=19713
6a703c0af8604f02a53b3b537a818e33
0f0a6a632413451380dd334c3e369165
የትግራይ ክልልን መልሶ ለመገንባት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ ፦ የትግራይ ክልልን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።ራሱን ተጋሩ የኢትዮጵያውያን ድርጅት ብሎ የሚጠራው የሲቪክ ተቋም፣ በትግራይ ወቅታዊና መጻኢ ጉዳዮች ዙሪያ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የሲቪክ ማህበራት ጋር ትናንት ውይይት ባደረገበት ወቅት ፣የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሐንስ ጎይቶም በክልሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ግልፅ እና አሳታፊ ለማድረግ በማሰብ ውይይት ማድረግ ማስፈለጉን ገልጸዋል።ለውጡን ተከትሎ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች እንዲፈቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ችግሮቹ እንዲፈቱ እና አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኙ ለማድረግ መሆኑንም አመልክተዋል።ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሃገር ሽማግሌዎች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ዜጎችን ያካተተ የመማክርት ጉባኤ መቋቋም ስላለበት ለባለድርሻ አካላት ለማስገንዘብ መድረኩ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።የትግራይ ህዝብ በተጀመረው የለውጥ ጉዞ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፍትህ እንዲቀዳጅ ተባብረን መስራት አለብን ብለዋል ።በውይይቱ ላይ የተገኙት የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤል በበኩላቸው፣ በትግራይ በሚደረገው መልሶ የማቋቋም ተግባር በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ እና የሲቪክ ማህበራት የበኩላቸውን ለመወጣት እያደረጉ ያሉት እንቅስቃሴ የሚያበረታታ መሆኑን አስታውቀዋል።የሲቪክ ማህበራትም በቀጣይ በክልሉ በሚደረጉ የለውጥ ጎዞዎች የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልፀው ፣ፓርቲውም ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ በበኩላቸው፣ የህወሓት ጁንታ በትግራይ ክልል ለሶስት አስርት አመታት ያደረሰውን ችግር መፍታት የሚቻለው ተቀራርቦ በመነጋገር መሆኑን ጠቁመዋል።የትግራይን ህዝብ ችግር መፍታት የሚቻለው የፖለቲካ ፓርቲ በማቋቋም ብቻ ሳይሆን የሲቪክ ማህበራትንም በማደራጀት እንደሆነ አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36994
a8290b7bbb0ded99215b51c3ada24a2e
d7cb4187783600e58e161037eb074f58
የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት 23 የጸረ-ሰላም ኃይሎች ላይ እርምጃ ወሰደ
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ ፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን 23 የጸረ ሠላም ኃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የዞኑ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ኮሎኔል አያሌው በየነኝ ጠቅሶ እንዳስታወቀው ፣ በዞኑ ዳንጉር ወረዳ ልዩ ስሙ ቁጥር 3 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሠላምን ሲያውኩ በነበሩ ኃይሎች ላይ በተወሰደው እርምጃ 23 ጸረ-ሠላም ኃይሎች ተደምስሰዋል ።የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የክልሉ የጸጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ ከተደመሰሱት የጸረ-ሠላም ኃይሎች በተጨማሪ ለጥፋት ሲጠቀሙበት የነበረ ሶስት የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ስር ውሏል።በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የጥፋት ቡድን በሠላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጥ በክልሉ መንግሥት ጥሪ መቅረቡን ያስታወሱት ኮሎኔል አያሌው ፣ በተሰጣቸው እድል መጠቀም ካልቻሉ በዋናው ጁንታ ላይ የተወሰደው አይነት የማያዳግም እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።ህብረተሰቡም እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የአካባቢውን ሠላም በተደራጀ መንገድ በመጠበቅ ረገድ የጀመረውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ።አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37000
197b769d2b92d417947ace78890cd354
3d5a7780d31b8c66bb4d1771ab497853
የኤሊዳአር በልሆ የመካከለኛ መስመር የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ ፦ የኤሊዳአር በልሆ ወረዳ የመካከለኛ መስመር የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ተጠናቆ ተመረቀ፡፡ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ፣ የኤሊዳአር በልሆ ወረዳ የመካከለኛ መስመር የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ተጠናቆ ተመርቋል ፤በቅርቡ ስራ ይጀምራል ፡፡የጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱ አሊ በምረቃው ወቅት ፣ፕሮጀክቱ ተጠናቆ አገልግሎት ላይ መዋሉ ለጉምሩክና ኢሚግሬሽን አገልግሎት የላቀ ጥቅም ይሰጣል ብለዋል። ከዚህ በፊት የጉምሩክና ኢሚግሬሽን አገልግሎት ሥራዎች በጄኔሬተር ይሰጥ እንደነበር አስታውሰው ÷ ስራዎችን በተያዘለት ጊዜና በተገቢው መንገድ ለማከናወን ይቸገሩ እንደነበር አመልክተዋል፡፡የፕሮጀክቱ መጠናቀቁ ስራዎቻቸውን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን እንደሚረዳቸውም ጠቁመዋል፡፡የኤሊዳአር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የአቅም ግንባታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብደላ ሱሌ በበኩላቸው አገልግሎቱ በወረዳዋ የኢኮኖሚ መነቃቃት እና ለወጣቶችም የስራ እድል እንደሚፈጥር አስታውቀዋል፡፡በምርቃቱ ላይ የተገኙት የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ አቶ ያሲን አሊ ፣ ፕሮጀክቱ በተያዘለት በጀትና በሚፈለገው ጊዜ መጠናቀቁ ለስራው መቀላጠፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አስታውቀዋል።የኤሌክትሪክ መስመሩ ኢትዮጵያ በጅቡቲ ድንበር ከምትጠቀምባቸው ወደቦች አንዱ የሆነው የታጁራ ወደብ ምስረታ ጋር ተያይዞ የተዘረጋ ነው ፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36987
513340dcaba7baec0509b236c8f0cf1c
4099760581eae7ad92611cc84892caaa
በመከላከያ የተጋድሎ ጀብድ፤ በጋዜጠኞች የጦር ሜዳ ምስክርነት የደመቀው መድረክ
ግርማ መንግሥቴአዲስ አበባ፡- በእብሪተኛው የህወሓት ጁንታ ቡድን ምክንያት ተገድዶ ወደ ሕግ ማስከበር እርምጃ የገባው የመከላከያ ሰራዊት ያስመዘገበው ድል እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በየግንባሩ በመሰለፍ ላበረከቱት አስተዋፅኦ የተዘጋጀ መድረክ በመከላከያ የተጋድሎ ጀብድ፤ በጋዜጠኞች የጦር ሜዳ ምስክርነት የደመቀ ሆኖ አልፏል።የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማስመልከት “በሕግ ማስከበር ዘመቻ በግንባር ለተሰለፉ የሚዲያ ባለሙያዎች የተዘጋጀ የእውቅናና የውይይት መድረክ” በሚል መሪ ሀሳብ በትናንትናው ዕለት በካፒታል የእውቅናና ውይይት መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደተገለፀው፤ ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመሰለፍ ወቅታዊ መረጃን ለሕዝብ በማድረስ በኩል ከፍተኛ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ለቆዩ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ጋዜጠኞች የእውቅናና የምስክር ወረቀት ሽልማት የተሰጠ ሲሆን፤ የመከላከያ ሰራዊቱም የሕግ ማስከበርና ህልውናንና ሉዓላዊነትን የማስቀጠል ኃላፊነቱን በብቃት የመወጣቱ ተግባር የልእልናው እና የአገራችን ከፍታ ማሳያ መሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡በመርሐግብሩ ላይ በመገኘት ሽልማቱን የሰጡት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንደ ተናገሩት፤ መከላከያ ሰራዊቱ ተገዶ ወደ እዚህ አይነቱ ውጊያ የገባ ቢሆንም አስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ ከፍሎ የሕግ የበላይነትን አስከብሯል፤ የአገር ሉዓላዊነትንና ማንነትን አስጠብቋል። በዚህም ሊኮራና ሊመሰገን ይገባዋል፡፡መከላከያ ሰራዊታችን በከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት የሰራዊታችን ብቻ ሳይሆን የአገራችንና ሕዝባችን ሞራልና ክብር በከፍተኛ ደረጃ ከፍ ብሏል ያሉት አምባሳደር ሬድዋን፤ ከመከላከያ ጋር በመሰለፍ መረጃን በፍጥነት ተደራሽ ሲያደርጉ የነበሩና በመድረኩ እውቅናና ሽልማትን ላገኙ ጋዜጠኞችንም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።በጁንታው ላይ የተገኘው ድል ከፍተኛ ቢሆንም በዚህ ብቻ ልንዘናጋ አይገባም የሚሉት አምባሳደሩ፤ ወደ ፊት ገና ብዙ የሚቀሩን ስራዎች አሉና ለእነሱም እንደዚሁ ከወዲሁ ልንዘጋጅ እንደሚገባም ተናግረዋል።ሌላውና በመድረኩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሲሆኑ፤ በወቅቱም፣ “ይህ ድል ከህፃናት ጀምሮ እስከ አዋቂዎች ድረስ ከፍተኛ ስሜትንና አንድነትን የፈጠረ፤ የሰራዊታችን፣ ህዝባችንና አገራችን የድምቀትና ልእልና ጫፍ ላይ ያደረሰ ስለሆነ ከዚህ እንዳይወርድ፤ ፖለቲከኞቻችንም፣ አክቲቪስቶቻችን ሁሉም ከዚህ በኋላ ወደ መንደር፣ ወደ ጠባብ አስተሳሰብ እንዳታወርዱን አደራ” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በእውቅናና ውይይት መድረኩ ላይ ጋዜጠኞችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተወካዮች ያጋጠሟቸውን የጦር ሜዳ አሳዛኝ፣ አስደናቂ፣ አስደማሚ፣ አሳፋሪ የጁንታውን ተግባራትን ያቀረቡ ሲሆን፤ መድረኩ እጅግ አሳዛኝ፣ አስተማሪና ታሪካዊ ሆኖ ለማለፍ በቅቷል።የመርሐ ግብሩ አዘጋጅ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ይህን መድረክ ማዘጋጀት ያስፈለገው የጥፋት ኃይሉ ባደረሰው አገር የማፍረስና ሉዓላዊነትን የማጥፋት ተግባርን የመከተውን ሰራዊታችንና ከጎኑ የተሰለፉ ጋዜጠኞችን በማመስገን እውቅናና የምስክር ወረቀት ለመስጠት በማሰብ ሲሆን፤ ይህም የድርጅቱን 80ኛ ዓመት በምናከብርበት በዚህ ወቅት እንደመሆኑ መሰል መርሀ ግብሮች የሚቀጥሉ ይሆናል።በፕሮግራሙ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፤ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት በጦር ሜዳ ለተሰው ጋዜጠኞች፤ ፎቶ ጋዜጠኛ ዘውዱ ጥላሁን ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ ሀይሉ ለገሰ እና ዋሲሁን ገብረ ሚካኤል ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ታውሰዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37004
1c5d3ebe89de508613594e29fe345341
50c5421c8f0f361ef5252c2141ee2181
«የጥፋት ኃይሉ ዕድሜ ልኩን ሽብር ሲሰራ፣ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ሲያወድም የኖረ ነው » ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ ሙሉ
ግርማ መንግሥቴ አዲስ አበባ፡- የህወሓት የጥፋት ኃይል ዕድሜ ልኩን ሽብር ሲሰራ፣ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ሲያወድም የኖረ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ ሙሉ አስታወቁ። ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፣ የጥፋት ኃይሉ ዕድሜ ልኩን ሽብር ሲሰራ፣ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ሲያወድም የኖረ ቡድን በመሆኑ ሕግና ሕጋዊ አካሄዶች በሙሉ አይጥሙትም። እሱ እየተመራ ያለው ባረጀና ባፈጀ አስተሳሰብ በመሆኑ ለአዳዲስ አስተሳሰብና አሠራር ፍፁም ዝግ ነው። በዚህም ነው ወደ እንደዚህ ዓይነት ጥፋት ውስጥ ሁሉ ሊገባ የቻለው። ቡድኑ ከጠ/ሚ አብይ ወደ ስልጣን መምጣት ወቅት ጀምሮ ምንም ዓይነት ምቾት ተሰምቶት አያውቅም የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ፣ እሳቸው ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የጥፋት ኃይሉ ሲሰራ የቆየው የሽብር ተግባር ብቻ መሆኑንም አመልክተዋል። እንደ ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ ከሆነ፣ ቡድኑ ወደ መቀሌ ሄዶ ከመሸገ ወዲህ ሲያከናውናቸው የነበሩ ተግባራት ሁሉ ሕገወጥና ከፌዴራል ሥርዓቱ ያፈነገጡ ናቸው። ከእነዚህ ተግባራት እንዲቆጠብ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጀምሮ በሁሉም አካል ቢመከርና የተለያዩ ዕድሎች ቢሰጡትም በፍፁም የሚገባው እና ወደ ትክክለኛና ሕጋዊ መስመር ለመግባት ፈቃደኛ አይደለም። ቡድኑ ለራሱ ባለው እጅግ የገዘፈና እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ የሚል ስሜት እራሱን ችግር ውስጥ መክተቱን ጠቁመው፣ ይህ ለራሱ የነበረው የተሳሳተ አመለካከት የተሰጡትን ብዙ ዕድሎች እንዳይጠቀምባቸው አድርጎታል ብለዋል። ጁንታው በዶክተር አብይ የሚመራው የፌዴራል መንግሥት የሚሰራቸውን ጥሩ ጥሩ ሥራዎች ሁሉ በማደናቀፍ፣ በማጣጣልና በማንኳሰስ ሥራ ላይ ተጠምዶ ነው የቆየው የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ፤ ሕግና ሕግን ተከትሎ ወደ መስመር መግባት የሚፈልግ ቡድን እንዳልሆነና ወደ መስመር እንዲገባም መንግሥት እየወሰደ ያለው የሕግ የበላይነትን የማስከበር እርምጃ ተገቢ መሆኑንም ተናግረዋል። ሕጋዊ ያልሆነ ምርጫ፣ ሕጋዊ ያልሆነ ካቢኔ ምስረታ እና ሌሎች ሕጋዊ ያልሆኑ ሥራዎችን ሁሉ ሲሰራ በሂደት ወደ ሕጋዊነት ይመለሳል ተብሎ ቢጠበቅም ጭራሽ እያበላሸና እየባሰበት መሄዱን፤ አሰቃቂና ዘግናኝ ተግባሩም መከላከያ ሰራዊቱን እስከ ማጥቃት መዝለቁን የሚናገሩት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ ይህም ሊሆን የቻለው ቡድኑ ለራሱ ሰጥቶት ከነበረው ሁሉ አወቅነት ደረጃና ይህም በፈጠረው እብሪቱ ምክንያት እንደሆነም አስታውቀዋል። የውጭ ጣልቃ ገብነትን በተመለከተም ቡድኑ የአንድ ክልል አስተዳደር ነው፤ ያ ክልል ደግሞ በፌዴራል መንግሥት ስር ነው። በመሆኑም ሊተዳደርም ሆነ ወደ ሕጋዊ መስመር ሊመጣ የሚገባው በፌዴራል መንግሥቱ አማካኝነት ነው እንጂ በሌላ ጣልቃ ገብ አካል ባለመሆኑ መንግሥት በዚህ በኩል የወሰደው አቋም የሚደነቅ እንደሆነ አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 1/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37041
510d5fa9eec095116d6ec532caad09b3
6ea29065d64eec213c9ecd80a8c49a2d
ብርጋዴር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴን ጨምሮ 1 ሺ ያህል የሰሜንእዝ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ተለቀቁ
 አዲስ አበባ (ኢዜአ)፡- የህወሓት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋዴር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴን ጨምሮ 1 ሺ ያህል የሰሜን ዕዝ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖችን የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በሰሩት የጋራ አሰሳ አስለቀቁ። የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ ተሰማ ትናንት እንደገለጹት፤ የህወሓት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን ምሽት ላይ የእራት ግብዣ ብሎ ከጠራ በኋላ አፍኖ በመውሰድ አግቷቸው ቆይቷል።የጁንታው ኃይል መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖቹን በሸሸበት ቦታ ሁሉ ይዟቸው ሲጓዝ ቆይቶ በቀድሞው የትጥቅ ትግል ወቅት የማዘዣ ቤዝ በነበረው አዴት በሚባል ቦታ አግቷቸው እንደነበር አመልክተው፣ የጁንታው ታጣቂ ኃይል መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖቹን በዚያ አካባቢ መደበቁ በአሰሳና በጥናት እንደተደረሰበት አስታውቀዋል።የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ባደረጉት የጋራ አሰሳ እና እርምጃ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጁንታው ማስለቀቅ መቻላቸውን ገልጸዋል።ሰራዊቱ ያስለቀቃቸው 1 ሺህ ያክል የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች አሁን ላይ ሰራዊቱን መቀላቀላቸውን ሜጀር ጀኔራል መሀመድ ጠቁመዋል። ሰራዊቱ ከጁንታው ካስለቀቃቸው መካከል የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋዴር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴም አመልክተዋል።የጁንታውን አባላት የማደን ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹት ሜጀር ጀኔራል መሀመድ፣ የመጨረሻ ምዕራፍ በሆነው ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ የተደበቀውን ጁንታ አስሶ የመያዙ ሥራ በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ የጋራ ቅንጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። ወደፊትም የጁንታውን ቡድንና ወንጀለኞቸን ለሕግ የማቅረብና የማደን ሥራ ውጤት በየጊዜው ለሕዝብ እንደሚገለፅ አስታውቀዋል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 1/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37040
73fe8e232b943032e98f01a38e626c3f
746d737a7ba4c3a470bcc1eb978ef358
ሕዝቦች ትናንት በአንድነት ለአንድ ሀገር መሰረት መጣላቸው ዛሬ ሀገር አፍራሽ የሆነን ቡድን መመከት እንዳስቻላቸው ተጠቆመ
 ሞገስ ጸጋዬአዲስ አበባ፡- ሕዝቦች ትናንት በአንድነት ለአንድ ሀገር መሰረት መጣላቸው ዛሬ ሀገር አፍራሽ የሆነ ቡድንን መመከት እንዳስቻላቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አስታወቁ::መንግስት ሕግ ለማስከበር በወሰደው ስኬታማ እርምጃ ዙሪያ ያነጋገርናቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ነዋሪ የሆኑት አቶ አያሌው አስናቀ፤ በሌሎች ሀገራት ታጥቀው ጫካ የገቡ ቡድኖችን ትጥቅ ለማስፈታት ብዙ እየደከሙ እንደማይሳካላቸው ገልጸው፣ በአገራችን ግን ለሀያ ሰባት ዓመታት ያክል መንግስት ሆኖ በሕዝብ ሀብት ጡንቻውን ያፈረጠመውን የህዋሓት ጁንታ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሕዝቦች አንድነት መደምሰሱ እጅግ የሚያኮራ ተግባር መሆኑን አስታውቀዋል::በአድዋ ላይ ትናንት የታየው ሀገራዊ አንድነት ጀግንነት ዛሬም ጁንታው በሀገር አንድነትና በሀገር ህልውና ላይ የደቀነውን አደጋ በመቀልበስ ዳግም መታየቱን ጠቁመው፣ ምንም እንኳ ጥቃቅን የውስጥ ችግሮች ቢኖሩብንም እነዚህ ችግሮች ከሀገር በላይ የሚሆኑ እንዳልሆኑ አመልክተዋል:: ጁንታው ሀገር ለማፍረስ ኃይል እና መሳሪያ አደራጅቶ እንደመነሳቱ ፣ ችግሩ ብዙ ኪሳራ ሳይደርስብን መመከት መቻሉ እድለኞች ነን ብለዋል ። የትግራይን ሕዝብ ጨምሮ መላው ሕዝብ የጁንታውን ድርጊት በማውገዝ ለሰራዊቱ ያሳየው ድጋፍ ቡድኑ እንዳሰበው ግጭቱ ወደ ሕዝብ እንዳይወርድ አድርጎታል ፤እንዳሰበው ቢሆንለት ኖሮ ችግሩ ለሀገሪቱ ከባድ ፈተና ሆኖ እንደነበር አመልክተዋል::አቶ አያሌው እንዳሉት፣ጁንታው በተሳሳተ ግንዛቤ የሕዝቡ አንድነት እንዲሸረሸር እና መንግሥት ላይ እምነት እንዳይኖረው ለማድረግ ብዙ ሰርቷል ።የለውጥ ኃይሉ ለብሔር ብሔረሰቦች ስጋት ነው በማለት ሆን ብሎ የብሔር ግጭት ለመፍጠር ሲሰራ ቆይተዋል። እውነታው ግን እሱ እንደሚለው ሳይሆን ሕዝቦች ይበልጥ ወንድማማችነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያግዝ ነው ::ሌላኛው አስተያየት ሰጭ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግዥ ባለሙያ የሆነው ወጣት አብነት ነጋ በበኩሉ ፣ የህወሓት ጁንታ ጊዜ ወስዶ እንደመደራጀቱ ሕዝቡ በአንድነት ባይቆም ኑሮ ያሰበው ይሳካለት ነበር ብለዋል ::‹‹በርግጥ ሀገራችን በርካታ ጊዜ ብዙ ፈተናዎች አጋጥመዋት በሕዝቦችዋ የተባበረ ክንድ ፈተናዎችን መመከት መሻገር ችላለች›› ያለው አስተያየት ሰጭው፣ ሕዝቡ ከሰፈሬ ውጣልኝ ማለቱን ትቶ የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ የሆነውን የህወሓትን ጁንታ በተባበረ ክንዱ ማስወገድ እንዳለበት አመልክቷል ::ዜጎች ወደፊትም በጋራ በመቆም ከመሰል ችግሮች ሀገሩን መጠበቅ እንዳለበት ያስታወቀው ወጣት አብነት ፣ መንግሥትም እንደ ሀገር የተዛቡ ነገሮችን በማስተካከል የሕዝቡ አንድነት የሚጠናከርበትን መንገድ ለማምጣት በርካታ ስራዎችን ሊሰራ ይገባል ብሏል::በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ የወረዳ ስምንት ነዋሪ ምስላቸውን ለመስጠት ፍቃደኛ ያልሆኑት አስተያየት ሰጭ ወይዘሮ በለጡ አሞኘ በበኩላቸው፣ሕዝቡ አሁንም ወደፊትም አንድ ነው::በጋራ በመቆሙ ሀገራችንን ከጠላትና ከአፍራሽ ቡድን ታድጓታል::ወደፊትም አንድነቱን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል::የተማረውም ያልተማረውም ከመከፋፈል አስተሳሰብ ተላቆ በጋራ በመቆም ሀገራችንን ወደ ምትለማበት ጎዳና መምራት ያስፈልጋል ብለዋል::አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36993
5b511b26b7adefcc23100d3841299527
7b29c7b006110846fb80b90bd028b1e1
በትግራይ ክልል የብሔራዊ አደጋ ስጋት ምላሽ ሥራዎች በተገቢው መንገድ እየተከናወኑ ነው
ጽጌረዳ ጫንያለውአዲስ አበባ፡- በትግራይ ክልል የብሔራዊ አደጋ ስጋት ምላሽ ሥራዎች በተገቢው መንገድ እየተከናወኑ መሆናቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን ለመቀበል የሚያስችል ሥራ እየሰራ መሆኑንና ለተመላሾቹ መጠለያ ካምፕ እየተገነባ መሆኑን ገለጸ::የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ በትግራይ ክልል የብሔራዊ አደጋ ስጋት ምላሽ ሥራዎች በተገቢው መንገድ እየተከናወኑ ነው። በደቡብ ትግራይ ለ24 ሺ፤ በምዕራብ ትግራይ ለ10 ሺ ዜጎች መድረስ ተችሏል።በክልሉ ቀደም ሲልም በሴፍትኔት የሚረዱ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች እንደነበሩ የጠቆሙት አቶ ምትኩ ፣ እነርሱን ጨምሮ አሁን በተፈጠረው ችግር ሰላም በተገኘባቸው አካባቢዎች ላይ ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠሉንና ከ20 እስከ 30 በመቶ የሚደርሱ የከተማ የቀን ሠራተኞችም ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስታውቀዋል:: ኮሚሽኑ የሚመራው የሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ባለሙያዎችን ያካተተ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል መኖሩን ያመለከቱት ኃላፊው፣ የማዕከሉ መመስረት ችግሮች በቀላሉ መፍትሄ እንዲያገኙ እያደረገ ነው ብለዋል። በተመሳሳይ በሰላም ሚኒስቴር የሚመራ የብሔራዊ አደጋ ምላሽ ሰጪ ቡድን መኖሩን ጠቁመው፣ ቡድኑ ለሚያጋጥሙ ችግሮች አፋጣኝ ምላሾች በመስጠት ሥራዎች እንዲቀሉ እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል:: በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮች አገሪቱን ልማት ላይ እንዳታተኩር አድርገዋታል የሚሉት ኮሚሽነሩ፤ መንግሥት ከሰው ነብስ የሚበልጥ የለም ብሎ ልማቱን ይዞ ለሚከሰቱ ችግሮች ምላሽ እየሰጠ ያለበት ሁኔታ የሚያስመሰገን ነው ብለዋል:: በተለይ በተለያዩ ምክንያቶች አዳዲስ ተፈናቃዮች ሲከሰቱ መልሶ ወደ መደበኛ ኑሯቸው ለማስገባት የሚያደርገው ርብርብና ቁርጠኝነት በየትኛውም አገር ላይ ይሆናል ተብሎ የማይታሰብ እንደሆነ አመልክተዋል::እንደ አቶ ምትኩ ገለጻ፣ በእስካሁኑ ችግሮቻችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለዋል::ሆኖም ብዙ አደጋ ሳይደርስባቸው ከተፈናቀሉት 94 በመቶ የሚሆኑን ወደ መደበኛ ሕይወታቸው መመለስ መቻላቸውን አስታውቀዋል::ቀሪው ስድስት በመቶ (እስከ ሦስት መቶ ሺ) የሚደርሱት በመጠለያና በየዘመድ ቤት ተጠልለው የሚገኙ መሆናቸውን አመልክተው፤ ለነሱም የሚሰጠው ድጋፍ ባሉበት የቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል:: አሁን በትግራይ ክልል የተፈጠረው ችግር ቀደም ሲል አጋጥሞን በስኬት ከተወጣነው አንጻር ሲታይ ብዙ ይፈትነናል የሚል ግምት የለም ብለዋል:: እስከ አሁን የነበሩት ክስተቶች በ50 ዓመት ታሪክ ውስጥ ሆነው የማያውቁ ናቸው ያሉት አቶ ምትኩ፣ በቅርቡ የተከሰተውን የአፋር አካባቢ የጎርፍ ችግር ብናይ በ30 ዓመት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ እንደሆነ የሚነገርለት ነው::ነገር ግን ሁሉም የከፋ አደጋ ሳያደርሱ አልፈዋል፡፡ በተለይም ከሰው ሕይወት መጥፋት ጋር ተያይዞ ኢሊኖ ያደረሰው ድርቅ እንደ ከ1977 ዓ.ም 750 ሺ ሰው አልነጠቀንም:: እንደ 1966 ዓ.ም 250 ሺ ሰውም አልሞተብንም::እንዲያውም በተቃራኒው የአንድም ሰው ሕይወት ሳያልፍ ችግሩ እልባት አግኝቷል ብለዋል:: ለዚህ ደግሞ መሠረቱ የመንግሥት አደጋን መከላከልና ምላሽ መስጠት አቅም ከጊዜ ወደጊዜ እየጠነከረ መምጣት እንደሆነ አመልክተዋል:: ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን ጉዳይ በዋናነት የሚመለከተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ቢሆንም ሲመለሱ መቀበሉና ተገቢውን ድጋፍ የማድረግ ሥራ የኮሚሽኑ በመሆኑ ድንበር አካባቢ የመጠለያ ካምፕ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል::አዲስ ዘመን ታህሳስ 1/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37039
3c4292895cdf4ae66104509b521b433b
d8db09dc7b9243a39bc0c34650866e94
ጥቂት ስለ ዶሃው ዓለም ቻምፒዮና
በሩጫ፣ ዝላይ እና ውርወራ ስፖርቶች የዓለምን ምርጥ አትሌቶች ለመመልከት የአትሌቲክስ ቤተሰቡ በሳምንቱ መጨረሻ በምዕራብ እስያዊቷ ሃገር ኳታር ይከትማል። የተወዳጁን አትሌቲክስ ስፖርት ታላቅ ድግስ የተረከበችው ዶሃም መሰናዶዋን አጠናቃ እንግዶቿን በመቀበል ላይ ትገኛለች። ሃገራትም በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናው ስማቸውን ለማስጠራት የሚያደርጉትን ዝግጅት በማጠቃለል ላይ ናቸው። ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ከሰሞኑ እንዳስታወቀው ከሆነም 209 ሃገራት 1 ሺ 900 አትሌቶቻቸውን በቻምፒዮናው እንደሚያሳትፉ ማረጋገጫቸውን ሰጥተዋል። ከእነዚህ ስመጥርና ጠንካራ አትሌቶች መካከልም ከሳምንታት በፊት በተጠናቀቀው ዳይመንድ ሊግ አሸናፊ የሆኑት 30 አትሌቶች ተካፋይ በመሆን በዓለም ታላቁ ውድድር ላይም ታሪክ ለማስመዝገብ መዘጋጀታቸውን ድረ ገጹ ጠቁሟል። በዚህ ቻምፒዮና የታሪክ መዝገብ በደማቅ ቀለም የሰፈረችው ውጤታማዋ አሜሪካዊት የአጭር ርቀት አትሌት አሊሰን ፍሊክስም የክብረ ወሰኗን ቁጥር ለመጨመር በዶሃ ትገኛለች። አትሌቷ 11 የወርቅ፣ 3 የብር እና ሁለት የነሃስ በድምሩ 16 ሜዳሊያዎችን በእስካሁኑ የዓለም ቻምፒዮና ተሳትፎዋ ሰብስባለች። እ.አ.አ በ2005ቱ የሄልሲንኪ ቻምፒዮና ለመጀመሪያ ጊዜ የተካፈለችው ፍሊክስ፤ የዶሃው ዓለም ቻምፒዮና ሰባተኛ ተሳትፎዋ ነው። በዚህ ቻምፒዮና ከሚሳተፉት አትሌቶች ሁሉ በእድሜ ትልቁ በሚል የተመዘገበው አትሌት ደግሞ ስፔናዊው የርምጃ ተወዳዳሪ ጀሱስ አንጌል ጋርሲያ ነው። እ.አ.አ የ1993ቱ የስቱትጋርት ዓለም ቻምፒዮና ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው የ49 ዓመቱ አንጋፋ አትሌት 13ኛ ተሳትፎውን በዶሃ ያደርጋል። የፊታችን አርብ የሚጀመረው 17 ኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በኳታር ዋና ከተማ በሚገኘው ከሊፋ ስታዲየም የመክፈቻ መርሃ ግብሩን ያደርጋል። ውድድሩ በመልካም ሁኔታ እንዲካሄድም ከዓለም ዙሪያ 4 ሺ የሚሆኑ በጎ ፈቃደኛ ሰራተኞች ተሰባስበዋል። ስዊድናዊው የ2004 ኦሊምፒክ የከፍታ ዝላይ ቻምፒዮን ስቴፈን ሆልምም የዚህ ቻምፒዮና የክብር አምባሳደር መሆኑን ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር አስታውቋል። ሃገራት ብሔራዊ ቡድኖቻቸውን በማሳወቅ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ሁሉም በቻምፒዮናው ቁንጮ ለመሆን የሚያደርገው ፉክክርም የዓለም ህዝብ በጉጉት የሚጠብቀው ነው። ኢትዮጵያም ቡድኗን ያሳወቀች ሃገር ስትሆን የ5 ሺ ሜትር ወንዶች እና የ10 ሜትር ሴቶች ቻምፒዮናዎቹ ሙክታር እድሪስ እና አልማዝ አያና በቡድኑ መካተት ርቀቶቹን ከወዲሁ ተጠባቂ ያደርገዋል። በዘንድሮው ዳይመንድ ሊግ የ3 ሺ ሜትር መሰናክል አሸናፊው ጌትነት ዋለ እንዲሁም በውጤታማነታቸው ዓለምን ያስደነቁት ወጣቶቹ ሳሙኤል ተፈራ፣ ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ ሰለሞን ባረጋ፣ ጥላሁን ኃይሌ፣ ሃጎስ ገብረህይወት፣ ለተሰንበት ግደይና ሌሎችም አዲስ ታሪክ ያስመዘግባሉ የሚል ግምት አግኝተዋል። ከዚህ በተጨማሪ የተጠባቂዋ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ከውድድሩ መገለልም ሌላኛው መነጋገሪያ ሆኗል።  ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=18548
ae149c83396f821895e369ed001cb675
af27354ff145be1667e02c18a4275e89
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሚለይበት መንገድ ይፋ ሆኗል
 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዘንድሮውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር አሸናፊ የሚለይበትን መንገድ ይፋ አድርጓል። ፌዴሬሽኑ በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኩባንያ ምስረታን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። በዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ 24 ቡድኖች በሁለት ምድብ ተከፍለው ውድድራቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል። በውድድሩም ከምድባቸው በአንደኝነት የሚያጠናቅቁ ሁለት ቡድኖች ለዋንጫ በገለልተኛ ሜዳ ሁለት ዙር ተጫውተው የጨዋታው አሸናፊ የሊጉን ዋንጫ የሚያነሳ ይሆናል። አሸናፊው ቡድን በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ሲሳተፍ ሁለተኛ ሆኖ የሚያጠናቅቀው ቡድን ደግሞ ኢትዮጵያን በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይወክላል። የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ደግሞ ኢትዮጵያን በሴካፋ ወክሎ እንደሚወዳደር ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። በሀገር ውስጥ ያሉ የእግር ኳስ ውድድሮችን ለመምራት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኩባንያን ለመመሥረት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ፌዴሬሽኑ በዚህ ወቅት ገልጿል። አሁን ላይም የክለቦችን ገቢ ለማሳደግ፣ ከደጋፊ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ፣ ዘመናዊ የትኬት ሽያጭ ለመጀመርና የክለቦችንና ደጋፊዎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሷል። አዲስ ዘመን መስከረም 6 / 2012
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=18148
955c57a123d247a6a911645f1e50c412
290aaa7572dc3025c6077041f3700371
«መከላከያ ሰራዊታችን ያሳየን የኢትዮጵያዊነትን ልክ ነው» – ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
አስቴር ኤልያስአዲስ አበባ፡- መከላከያ ሰራዊታችን በሶስት ሳምንት ውስጥ በታላቅ ጀብዱ የኢትዮጵያዊነታችንን ልክ እንዳሳየን የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ አስታወቁ ፡፡ዶክተር ቢቂላ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት ፤ በትግራይ ክልል ተሸሽጎ የከረመው ጽንፈኛው የህወሓት ስግብግቡ ጁንታ በአገር   መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ መንግስት የሕግ ማስከበሩን ተግባር ባከናወነበት ወቅት የአገር መከላከያ ሰራዊት ትልቅ ጀብድ በመፈጸም የኢትዮጵያዊነትን ልክ አሳይቶናል ።መከላከያ ሰራዊቱ በሶስት ሳምንት ውስጥ በሰራው ጀብዱ በእርግጥም ታላቅነቱንም አስመስክሯል ፡፡ መከላከያ ሰራዊቱ፤ ‹በአገሬ ከመጣህማ እኔን ታርዳለህ እንጂ ትጥቄን አትፈታም፤ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና በአገሬ ማንነት ከመጣህ ትጨርሰኛለህ እንጂ በዘር አትከፋፍለንም የሚል የጀግንነት ጥግ አሳይቷል “ ያሉት ዶክተር ቢቂላ ፤ በተለይም ውስጥ ያሉ አመራሮች ትጥቃቸውን ፈተው ላለመስጠት ያደረጉት ተጋድሎ ታላቅ ነው ብለዋል።ሌላ ኃይል እስኪደርስላቸው ድረስ አንገት ለአንገት ተናንቀው የታገሉ መሆናቸውንም አስታውቀዋል ። ከድሉ ጀርባ ያለው የአገር አንድነት መለከያ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን እንደሆነም ጠቁመዋል ። እንደ ዶክተር ቢቂላ ገለጻ፤ በዚህም ብቻም ሳይሆን ወደ ፊትም ትልልቅ አገራዊ ፈተናዎች ቢከሰቱ እንኳ መከላከያ ሰራዊቱ ያልቃታል እንጂ አገሩን እንደማያስደፍር ማረጋገጥ ተችሏል።ይህን ጀግንነቱንም በማየት ከኋላው 115 ሚሊዮን ሕዝብ ተገልብጦ ኢትዮጵያ ተነካች በማለት ለመከላከያው ያለውን ድጋፍ ገልጿል፡፡ የአገር መከላከያ ሰራዊትን ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከዳር መጥተው ያቋቋሙትና ከየትኛው ብሔርና ኃይማኖት ነህ ሳይል አብሮ የሚኖር የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ነው ያሉት ዶክተር ቢቂላ፣ ጁንታው ፤ ዜጎች እንደ አይናቸው ብሌን የሚያዩዋትን ኢትዮጵያን ለማጠልሸት ፤ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፣ የአገራዊ አንድነት ምልክት በሆነው መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አመልክተዋል ፡፡ ከኢትዮጵያዊነት መገለጫዎች አንዱ መከላከያ ሰራዊታችን ነው ያሉት ኃላፊው ፣ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የማይታይ ኢትዮጵያ የለም ያሉት ዶክተር ቢቂላ፣ ይህንን ሰራዊት በዘር ለይተው ማጥቃታቸውንም አመልክተዋል።ይህም የተንኮልና የክፋት ሥራቸው ለታሪክ የሚቀመጥ ነው ብለዋል፡፡ ዩኒቨርስቲን፣ ፌዴራል መንግስትን፣ መከላከያን መንካት ኢትዮጵያ መንካት ነው። የአይንን ብሌን መንካት እንደሆነ ያመለከቱት ዶክተር ቢቂላ፣ ከዚህ ድል ጀርባ ያለውን መከላከያ መንካት ማለት የኢትዮጵያውያን አንድነትና መስተጋብርን መንካት እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡ ከዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ሙሉ ቃል ገጽ 6 ይመልከቱ ፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36927
963ae9295029377872ebff7d6e33aa9b
e942551dd0fa34e4e889740649e5d299
ባህልና ስፖርት በኢሬቻ ሩጫ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት ሲታሰብ አንዱ አቅጣጫ ያመዝናል። የአበበ ቢቂላ፤ እሸቱ ቱራ፣ ቶለሳ ቆቱ፣ ፊጣ ባይሳ፣ ኃይሌ ገብረስላሴ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ገዛኸኝ አበራ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ስለሺ ስህን፣ ጥሩነሽ ዲባባና ቤተሰቧ እንዲሁም የበርካቶች መገኛ፤ የኦሮሚያ ክልል። ክልሉ የረጅም ዓመታት የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ስፖርት የጀርባ አጥንት ስለመሆኑም አያጠያይቅም። አሁንም የኦሊምፒክ፣ የዓለም ሻምፒዮና እንዲሁም የበርካታ ውድድሮች ድምቀት እንደሚሆኑ ተስፋ የሚጣልባቸው አትሌቶች በመፍራት ላይ ይገኛሉ። አትሌቲክስና ክልሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው ለማለት የሚያስደፍረውም ለስፖርቱ ምንጭ በመሆኑ ነው። በህዝቡም ዘንድ እንደ ባህል የሚታየው ስፖርቱ፤ አንድ የኢኮኖሚ ምንጭ እስከመሆን ደርሷል። ይህ ከህዝቡ ጋር ከፍተኛ ትስስር ያለው ስፖርት ለባህላዊ ሁነት ማድመቂያ እንዲሁም መልዕክት ለማስተላለፍ ተመራጭ ነው። በኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ ዋጋሪ፤ የኢሬቻ በዓል አከባበር ወቅት ወጣቶች የሩጫ፣ የፈረስ ጉግስ እና ሌሎች ውድድሮችን የማድረግ ባህል እንዳላቸው ያስታውሳሉ። ይህም የሚያሳየው ሩጫ የበዓሉ አንድ አካል እንዲሁም የሩጫ ስፖርት ለኦሮሚያ ህዝብም ባህል መሆኑን ነው። በተለይ በዚህ የሽግግር ወቅት በህዝቦች መካከል ጥርጣሬ የበዛበት እንደመሆኑ፤ በሩጫው የሰላምና አንድነትን መልዕክት ለማስተላለፍ እንዳስፈለገ ያስረዳሉ። ትናንት «እሬቻ የሰላምና የአንድነት ተምሳሌት» በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው የሩጫ ውድድርም የዚህ ማሳያ ነው። ከ150 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ እንዲሁም ስለ እሬቻ በዓል ህዝቡ እንዲያውቅና ባህሉን እንዲረዳ ለማድረግ በአዲስ አበባ በተካሄደው የእሬቻ የሰላም ሩጫ ላይ በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ተገኝቷል። መነሻና መድረሻውን በመስቀል አደባባይ ያደረገው የጎዳና ላይ ሩጫው፤ 10 ኪሎ ሜትር የሸፈነ ነበር። በሩጫው ላይ እንዲሳተፉ ለሁሉም የአትሌቲክስ ክለቦች ጥሪ የቀረበ ሲሆን፤ ከ500 በላይ የሚሆኑ አትሌቶች ከኦሮሚያ፣ ድሬዳዋ፣ አዲስ አበባ፣ ከደቡብ እንዲሁም ከአማራ ክልል ተካፋይ ሆነዋል። በወንዶች መካከል በተካሄደው ውድድር የስሁር ኮንስትራክሽን አትሌቱ በሪሁን አረጋዊ አሸነፊ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ እንዲሁም የ50ሺ ብር ሽልማቱን ወስዷል። ያለፈውን ዓመት በጉዳት ከወድድር ርቆ የቆየው አትሌቱ፤ ብርቱ ተፎካካሪ አለመኖሩ ለአሸናፊነቱ እንደረዳውም ገልጿል። ኃይለማሪያም ኪሮስ እና ደጀኔ ደበላ ደግሞ ከመብራት ኃይል እና ኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ስፖርት ክለብ ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል። በሴት አትሌቶች በኩልም ኦብሴ አብደታ ከለገጣፎ ለገዳዲ ክለብ አሸናፊ ሆናለች። በግሏ የተሳተፈችው አትሌት መስታወት ፍቅሩ ሁለተኛ ስትሆን፤ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲዋ አንቻለም ሃይማኖት ሦስተኛ በመሆን የነሃስ ሜዳሊያቸውን አጥልቃለች። ከአንድ እስከ ሦስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን ያጠናቀቁ አትሌቶችም ከሜዳሊያው ባሻገር፤ የ50ሺ፣ 30 እና 20ሺ ብር ማበረታቻ ተበርክቶላቸዋል። የኦሮሚያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊና የሩጫው ኦርጋናይዘር አቶ ነጋ ቱጂባ፤ ሩጫው ከታሰበው ሰዓት ዘግይቶ ቢጀመርም በመልካም ሁኔታ መጠናቀቁን ይገልጻሉ። የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ በዓለም ደረጃ የገነባው የአትሌቲክስ ስፖርት፤ ከአበበ ቢቂላ ጀምሮ ያለው ታሪክ በርካታ አትሌቶች የወጡት ከኦሮሚያ ክልል መሆኑን ያሳያል። አትሌቲክስ ከኦሮሞ እሴት ጋር ሊያያዝ የሚችል በመሆኑም፤ ኢሬቻና አትሌቲክስን በማገናኘት ህዝቡ በእኔነት ስሜት እንዲደግፈውና እንዲያሳድገው ያደርጋል። በየዓመቱ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓልም ስፖርታዊ ውድድሩ ይበልጥ ውበት የሚሰጠው ይሆናል። የኦሮሚያ ክልል የኢትዮጵያ አትሌቶች ምንጭ ቢሆንም በዚህ ወቅት ግን ውጤቱ እየቀነሰ መምጣቱ ይታያል። የዚህን ምክንያትም በመገምገም ወደ ቀድሞ ስፍራው ለመመለስ ህዝባዊ መሰረት ማስያዝ የግድ ይሆናል። መሰል ውድድሮች በየዞኑ እና ወረዳው ማካሄድ ቢቻል፤ ህዝቡ ስፖርቱንና አትሌቶችን በባለቤትነት ስሜት በመደገፍ ወደ ምንጭነቱ መመለስ እንደሚቻልም ኃላፊው ይጠቁማሉ። በዓሉም በሰላምና በፍቅር ያለ ኃይማኖትና መሰል ልዩነት የሚያከብር በመሆኑ ይህንን አጠናክሮ መቀጠል ለስፖርቱ የራሱን ሚና የሚጫወት ይሆናል። አሁን በ50ሺ ሰው የተጀመረው ውድድር ወደፊትም ተጠናክሮ ለማስቀጠልና ቁጥሩንም ለማሳደግ ጥረት ይደረጋል። ሩጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እንዲሁም ለተሳታፊዎችም ኃላፊው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አዲስ ዘመን መስከረም 12/2012 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=18983
1d567949b293b5b724159f281bac754f
e26dbdab69feafd4c2387a7952da6bfb
“ባለፉት 27 ዓመታት በንግዱ ዘርፍ እኩል የሆነ የተሳትፎ ዕድል አልነበረም ” አቶ ክቡር ገና የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤት ሥራ አስኪያጅ
ለምለም መንግሥቱአዲስ አበባ፦ ባለፉት 27 ዓመት በነበረው የንግድ ሥርዓት እኩል የሆነ የተሳትፎ እድል እንዳልነበረ የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤት ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።የህወሓት ጁንታው ንብረት የሆኑ ድርጅቶች ባልተገባ መልኩ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን ድጋፍ ያገኙ እንደነበር ጠቁመዋል ።ሥራ አስኪያጁ አቶ ክቡር ገና በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት ፣ ባለፉት 27 ዓመታት የነበረው ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ፍትሐዊ ተሳትፎ ያላቸው የንግድ ድርጅቶች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታ አልነበረም ። ጉዳዩ ዛሬ እንደ አዲስ ይነሳ እንጂ በጉዳዩ ላይ ብዙ ተብሏል፡፡ለሕዝብም አዲስ ነው ብለው እንደማያምኑና እርሳቸው ቀድሞ የንግድ ምክር ቤት በአሁኑ ደግሞ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ተብሎ የሚጠራው ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ በማህበራቸውም ሆነ በተለያየ አጋጣሚ ሁሉ ለግሉ ዘርፍ ከአድሎ ነጻ የሆነ አሰራር እንዲኖር ክፍተቶችን በማሳየት ብዙ ርቀት መሄዳቸውን አስታውሰዋል። ሰሚ ባለመኖሩ እኩል ተሳትፎ ሳይፈጠር አሁን ላይ መደረሱን አመልክተዋል ፡፡ለንግድ ድርጅቶች መቋቋም ዋና መሰረቱ አድሎ የሌለበት ምቹ አሰራር መዘርጋት እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ክቡር፤ የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጁንታ ቡድን የሆኑ አካላት ንብረት የሆኑ ድርጅቶች ባልተገባ መልኩ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን ድጋፍ ያገኙ እንደነበር አመልክተዋል። በቦርድ ስም የሚሰየሙ የመንግሥት ኃላፊዎች እነዚህ የንግድ ድርጅቶች፣ መረጃ እንዲያገኙ ፣ከባንክ በፈለጉ ጊዜ መበደር እንዲችሉ፣ ብድር በወቅቱ ለመመለስ እንዳይገደዱ የሚያደርግ አሰራር የተዘረጋበት ሥርዓት እንደነበር ገልጸዋል። ይህ አይነቱ አሰራር ለብዙዎች አዲስ እንዳልሆነና ሲተችም እንደነበር ያመለከቱት አቶ ክቡር ፣ ይህም የግሉን ዘርፍ ክፉኛ እንደጎዳውና ከውድድር እንዳወጣው አስታውቀዋል ። የንግዱ ማህበረሰብ ከራሱ አልፎ ለሀገርም ሚናውን እንዲወጣ አድርጎታል ከተፈለገ ፍትሐዊ አሰራርን ማስፈን እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡መንግሥታት የሕዝብን ጥቅም እናስቀድማለን ቢሉም ይህንን ቃላቸውን በተግባር ሲያውሉት አለማየታቸውን የጠቆሙት አቶ ክቡር፤የራሳቸው ጥቅም የሚያሸንፋቸው መንግሥታትን ማስተዋላቸውን ተናግረዋል፡፡ችግሩ ዓለምአቀፋዊ ቢሆንም አፍሪካ ላይ ባለው የአቅም ውሱንነት ችግሩ የከፋ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡በችግሮች ዙሪያ በተለያዩ ወቅቶች በሚመቻቹ መድረኮች ማህበሩ የሚሰጣቸው ምክረ ሀሳቦች ተቀባይነት እንደሌላቸውና የሚደመጥም እንዳልነበር ያመለከቱት አቶ ክቡር ፣ አንዳንዶች ከሚፈልጉት ጋር ተነጋግረው በሚፈልጉት መንገድ ጉዳያቸውን ማስጨረስ የሚችሉበት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ማህበራትም ሆኑ መንግሥታት ሚናቸው የንግዱ ማህበረሰብ ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለክፍተቶች መፍትሄ መስጠት እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ክቡር ፣ ባለፉት 27 ዓመታት ይህ ሲሆን አልታየም ፤ የንግድ ድርጅቶች ባልተገባ መንገድ ከውድድር ውጪ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የንግድ ድርጅቶች ከማነቆ የተላቀቁ አለመሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36939
4ea432386b1c8633f17942caea0ad463
2a5446191df16283bcf344034798dea7
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት በኃይል ገመድና ኬብል ስርቆት መቸገሩን አስታወቀ
በኃይሉ አበራአዲስ አበባ:- የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት የኃይል ገመዶች እና ኬብሎች ስርቆት መቸገሩን አስታወቀ። በዚህም ተገልጋዮቹ መንገላታቸውና ኮርፖሬሽኑም ለተደጋጋሚ ኪሳራ መዳረጉን ገለጸ።የአገልግሎት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሙሉቀን አሰፋ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ፣የኃይል ገመዶች እና ኬብሎች በሌቦች ተቆርጠው በመወሰዳቸው ምክንያት ሰሞኑን ከመሿለኪያ ሚኒሊክ አደባባይ እና ከጦርኃይሎች ስቴዲየም ያለው መስመር በከፊል አገልግሎቱ ተቋርጧል። በዚህም ደንበኞቹ ለችግር ተጋልጠዋል።እስካሁን 750 የሚደርሱ የኃይል ኬብሎች እና 15 የኃይል ማሰራጫ ገመዶች ስርቆት እንዳጋጠመ የገለጹት ኢንጂነር ሙሉቀን ፣ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ማበጀት ባለመቻሉ አገልግሎቱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸዋል።የኃይል ገመዱን ያገኙ የሚመስላቸው ሌቦች የፋይበር ኦፕቲክስ ገመዶችን ጭምር ስለሚቆርጡ ፣ እነዚህን መልሶ ለማግኘትና ለመጠገን ቢያንስ አንድ ሙሉ ቀን የሚፈልግ መሆኑ የጥገና ስራውን አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል። በዚህም የተነሳ አገልግሎቱን በከፊል ለማቋረጥ መገደዱን አስታውቀዋል። የህብረተሰቡ እንግልትና ችግር ሳይጨምር በቀን እስከ 200 ሺ ብር የሚገመት ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑንም ጠቁመዋል።ባለፉት ሶስት ቀናት ከቃሊቲ እስከ ስታዲየምና ከሀያት እስከ ስቴዲየም ብቻ አገልግሎት ለመስጠት መገደዱን ያመለከቱት ኃላፊው፣ አሁን ላይ በቀን ሳይቀር የመሰረቅ ችግር እያጋጠመው እንደሚገኝም ገልጸዋል። ከዚህም ውጭ ጥገና የተደረገለትን ሆነ ብለው አላቀው የሚሄዱበት ሁኔታ መኖሩንም አመልክተዋል ።ችግሩን ለመፍታት በቅንጅት ለመስራት እስከ ፖሊስ ኮሚሽን ድረስ የተሄደበት ርቀት ቢኖርም ዘላቂ መፍትሄ ባለመገኘቱ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መሄዱን አስታውቀዋል ።የባቡር መስመሮቹ አስፈላጊው ጥገና ተደርጎላቸው ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጡ ገልጸዋል።ከወቅታዊው የጸጥታ ሁኔታ አንጻር የ24 ሰአት ጥበቃ ለማድረግ ኮርፖሬሽኑ ተጨማሪ የጥበቃ ኤጀንቶችን በተመረጡ ቦታዎች መመደብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ ይገኛል ብለዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36934
c01e61c86156eb49c8a4810f61e35608
448c275a5c3d8b1ff665d57b478366df
አርሶ አደሮቹ ወደ መደበኛ የስራ እንቅስቃሴያቸው መመለሳቸውን ገለጹ
ኢያሱ መሰለ ኦፍላ፡- በደቡባዊ ዞን ኦፍላ ወረዳ ሀየሎ ቀበሌ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ሰላም በመስፈኑ ወደ መደበኛ ህይወታቸው መመለሳቸውን ገለጹ ።የጁንታው ታጣቂዎች መንደራቸው ውስጥ በመመሸጋቸው ከአካባቢያቸው ርቀው ለመሄድ ተገደው እንደነበር አመለከቱ ።ከሁለት ሳምንት ቆይታ በኋላም የሕግ ማስከበር ሥራው በአጭር ጊዜ በመጠናቀቁ ወደ መንደራቸው ተመልሰው ምርታቸውን በመሰብሰብ ላይ ያገኘናቸው የኦፍላ ወረዳ ሃየሎ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ቄስ መላከ ብርሃን ከበደ ግርማይ እንዳስታወቁት ፣ የጁንታው ታጣቂዎች በግራካሶና አካባቢው በመመሸጋቸው ቤተሰቦቻቸውንና ያሏቸውን እንሰሳት ይዘው ለመሸሽ ተገደው ነበር ።ሕግ የማስከበር እርምጃው በአጭር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ በመሆኑ አዝመራ በመሰብሰቡ ላይ እንደሚገኙ የጠቆሙት ቄስ መላከ ብርሃን ከበደ፣ እስካሁን ሰብል በመሰብሰብ ያጋጠማቸው ችግር እንደሌለ አስታውቀዋል ፡፡አርሶ አደሩ አምርቶና ለፍቶ ከመብላት ውጭ ሌላ ዓላማ የለውም ያሉት ቄስ መላከ ብርሃን ፣ የተለመደ ስራን ለማከናወን ሰላም ያስፈልገዋል ፤ በኣካባቢው ሰላም በመኖሩም ተጋግዘው ምርታቸውን በማስገባት ላይ ነን ብለዋል ።ሌላው በስራ ላይ ያገኘናቸው የኦፍላ ወረዳ ሃየሎ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ሃይሌ አበራ አርሶ አደሩ ሰርቶ ለመኖርም ይሁን አምርቶ ለሌሎች ለመትረፍ ሰላም ያስፈልጋል ብለዋል።በሰላም እጦት ምክንያት ለሁለት ሳምንት አካባቢውን ለቀው መሄዳቸውን ተናግረዋል።የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአካባቢውን ሰላም በማረጋጋት ወደ ቀደመ ህይወታችን መልሶናል ያሉት አርሶ አደሩ ፣ አዝመራቸውን ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበት በወቅቱ ለመሰብሰብ መቻላቸውንም ገልጸዋል።በደርግ ሥርዓተ መንግሥት በአካባቢው በነበረው ጦርነት እናታቸውን ፣ ወንድማቸውን፣ ባለቤታቸውንና በርካታ ንብረታቸውን እንዳሳጣቸው የተናገሩት አስተያየት ሰጪው ጦርነቱ መጥፎ ጠባሳ ጥሎባቸው ያለፈ በመሆኑ ዳግም በአካባቢያቸው እንዲከሰት የማይፈልጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።የትግራይ ሕዝብ ዘመኑን ሙሉ በጦርነት እንዳሳለፈ የተናገሩት አርሶ አደሩ፣ ይህም ለተለያዩ ችግሮች ዳርጎታል ብለዋል።መንግሥት ሕግ ከማስከበር አንጻር እየወሰደ ያለው እርምጃም ተገቢ እንደሆነና በተለይም የአርሶ አደሩን እንግልት እንደሚቀንስ ገልጸዋል።ገበሬ አርሶ የሚያበላና ፣ ለመንግስት የሚገብር እንደሆነ የተናገሩት አቶ ሃይሌ በስራ የሚደክመው ሳያንሰው ጽንፈኞች በሚፈጥሩት ችግር ምክንያት ሊጉላላ አይገባም ብለዋል።የጥፋት ቡድኑ በሰላማዊ መንገድ እጁን መስጠት እንዳለበትና የቡድኑ ታጣቂ የሆኑ የአርሶ አደር ልጆችም ከወላጆቻቸው ጋር ሆነው አምርተው እንዲኖሩ መክረዋል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36940
79d8fe50fe58d4feea41c4b87c510458
1a245c7d28c6fab54bdf13a138112772
“አገራዊ ለውጡ ከተጀመረ አንስቶ ሕዝቦችን ያራራቁ ግንቦች እየፈረሱ ናቸው” ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ አገራዊ ለውጡ ከተጀመረ አንስቶ ሕዝቦችን ያራራቁ ግንቦች እየፈረሱ መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታወቁ ። ኢትዮጵያ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚንቀሳቀስባትና የዜጎች ክብር የሰፈነባት፤ ሁሉም የየራሱን ማንነት በነጻነት የሚያንጸባርቅባት እንድትሆን ተግቶ መስራት እንደሚያስፈልግ አመለከቱ ። በአገር አቀፍ ደረጃ 15ኛውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ትናንት በአዲስ አበባ በተካሄደ ውይይት ፣ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዳስታወቁት ፣የለውጥ ጉዞው የኢትዮጵያ ሕዝቦች በአብሮነትና በአንድነት ወደ ብልጽግና ጎዳና እንዲሻገሩ የሚያስችል ነው። ሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚንቀሳቀስባት፣ የዜጎች ክብር የሰፈነባት የተሻለች አገር እንድትሆን ተግቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ያመለከቱት አቶ ደመቀ ፣ እያንዳንዱ ብሔር ፣ብሔረሰብ የየራሱ ቋንቋ፣ ባህልና ትውፊትና ታሪክ በነጻነት የሚስተናገዱባት ስልጡን ምድር እንድትሆን ጠንክሮ መስራት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል። ሁሉም በወንድማማችነት፣ በመተሳሰብና አንዱ ለሌላው ጠበቃና ዋስትና በመሆን ለሕብረ ብሔራዊ አንድነቱ ዘብ እንዲቆምም ጠይቀዋል።የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አደም ፋራህ በበኩላቸው ፣ከለውጡ በኋላ በአገሪቷ በብዙ ዘርፎች እመርታዊ ለውጦች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። ከለውጡ በፊት ከፍተኛ የዴሞክራሲ እጦት፣ ሥራ አጥነትና የሰብዓዊ መብት በሰፊው ይስተዋል እንደነበር ጠቁመዋል።ይህ ሁሉ ችግር ተደምሮ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ለውጥ እንዲመጣ መታገላቸውንና የለውጡ አመራርም የተሻሉ ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሓመድም፤ ከለውጡ በኋላ የተሻሉ ሁኔታዎች መምጣታቸውን ፤ ሌላው ቢቀር በዚህ ወቅት ሕዝቦችን የሚያቀራረቡ ትርክቶች መጀመራቸውንና ከፋፋይ አስተሳሰቦች እየቀነሱ መምጣታቸውን አስታውቀዋል።በተጨማሪም ሚዛናዊ የፖለቲካ ውክልና እየመጣ መሆኑን አመልክተው ፣ ከዚህ በፊት አጋር ተብለው እንደ ሁለተኛ ዜጋ የሚታዩ ክልሎች ከሌሎች ጋር እኩል በመሆን አንድ ላይ ተቀምጠው በሀገር ጉዳይ ላይ መምከርና መወሰን መቻላቸውን ጠቁመዋል ።የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ፤በተለያዩ ሁኔታዎች አመቺ ያልሆኑ ሕጎች መሻሻላቸውን አንስተዋል።ከተሻሻሉት ሕጎች መካከል ጥቅል የሆነውን የሕገ መንግሥት ድንጋጌ ለአተገባበር በሚያመች መልኩ መሻሻሉን ጠቅሰዋል።የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ የአሜሪካን ሕገ መንግሥት ዋቢ አድርገው የሕገ መንግሥት መሻሻል ያለውን ጥቅም አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36979
6d8fbb065835a7f3195b6a6c39b481b2
c29936a6c5eba2a874aeba66862c83a7
«ጁንታውና ኦነግ ሸኔን የሚያመሳስላቸው ዓላማቸውን በኃይል ለማስፈጸም የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው» – አቶ ቶሌራ አደባ የኦነግ ቃል አቀባይ
አስቴር ኤልያስአዲስ አበባ፡- የህወሓት ጁንታው እና ኦነግ ሸኔ የሚያመሳስላቸው ዓላማቸውን በኃይል ለማስፈጸም የሚያደርጉት እንቅስቃሴ መሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ አስታወቁ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በንጹኃን ኢትዮጵያውያን ላይ እየተወሰዱ ያሉ እኩይ ተግባሮች ከባህላችንም ከባህሪያችንም ውጭ የሆኑ እንደሆኑ አመለከቱ ።የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ፣ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለረጅም ዓመታት ተጋብተውና ተዋልደው እንዲሁም ልዩነት ቢኖራቸውም ተቻችለውና ተከባብረው የኖሩ ሕዝቦች ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን እየታዩ ያሉ እንቅስቃዎችና እየተወሰዱ ያሉ እኩይ ድርጊቶች ከአሁን በፊት ያልተለመዱ ናቸው። የዚህ አኩይ ተግባር ዋና አራማጅ የህወሓት ጁንታ ነው ፣ ኦነግ ሸኔም በተመሳሳይ መልኩ ዓላማውን በዜጎች ላይ በኃይል ለመጫን እየታተረ ነው ።ሁለቱም ቡድኖች የእኔን መንገድና ሐሳብ ተቀበል፤ ካልተቀበልክ መኖር አትችልም እንደሚሉ አቶ ቶሌራ አመልክተው፣ በመጀመሪያም ቢሆን በኃይል የመጣው ወያኔ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጋጋለው የሕዝቦች አመጽ ከያዘው ስልጣን በኃይል ሲያስወግደው ያጣውን ስልጣን አሁንም በድጋሚ በኃይል ለመያዝ ትግል ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመዋል። ኦነግ ሸኔ የሚባለው ቡድን ደግሞ ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወደ አገር ቤት ሲገባ አፈንግጦ የቀረ ቡድን ነው ፤ ያፈነገጠበትም ምክንያት ሰላማዊው መንገድ አያዋጣኝምና የትጥቅ ትግሉን እቀጥልበታለሁ በሚል አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም  አቋም እንደሆነ ገልጸዋል። ቃል አቀባዩ፣ ኦነግ ሸኔ ዓላማዬንና የፈለኩትን ነገር በጠበመንጃ አፈሙዝ አስገኛለሁ፤ ሕዝቡም ደግሞ በግዴታ እኔን መደገፍ አለበት ብሎ የሚደግፉትን እየተውና ሌሎቹን እያስፈራራ እንዲሁም እያስገደደ በኃይል ወደስልጣን ለመምጣት የሚሰራ ቡድን መሆኑ ከህወሓት ጁንታ ጋር ያመሳስላቸዋል ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የበለጠ ሊያቀራርባቸው የሚችለው ጉዳይ በሕዝቦች መካከል መቃቃር እና ቅራኔ ሲኖር ዓላማ ጭነን ለማሳካት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርልናል ማለታቸው እንደሆነም አስታውቀዋል። በመሰረቱ እየተካሄደ ባለው የሕግ ማስከበር ዋናው ሰንኮፉ ከተነቀለ የኦነግ ሸኔ ጉዳይ ያን ያህል ስጋት እንደማይሆን ያመለከቱት ቃል አቀባዩ ፣ የሕዝቦች ንቃተ ህሊና ከትናትናው ይልቅ ዛሬ የተሻለ ነው ። ነገ ደግሞ ይበልጥ ይጎለብታል ። በተለይ ደግሞ ሕዝቡ ጥቅሙንና መብቱን በአግባቡ እያወቀ ሲመጣ የትኛውም ኃይል ከአሁን በኋላ በኃይልና በጠመንጃ አፈሙዝ አስገድዶ ሐሳቤን ተቀበል ቢል ተቀባይነት እንደማይኖረው አመልክተዋል። የጁንታው ለአብነት መውሰድ ከተቻለ የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ነው፤ መለየት አይቻልም በማለት ሲናገሩ ነበር ያሉት ቃል አቀባዩ፣ እሱ ደግሞ ትክክል እንዳልሆነ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በተጨባጭ በተግባር ለማየት ተችሏል ብለዋል። የጁንታውን ቡድን ዓላማ በማስፈጸም ላይ ያሉት አንድም በጥቅም የተሳሰሩ ሁለትም ተገድው እንዲዋጉ የተደረጉና መሄጃ እና አማራጭ ያጡ እንደሆኑ ጠቁመዋል ። ጁንታው ለአገራችንም ሆነ ለሕዝባችን ጠቃሚ ነው ብለው አምነውበት የሚታለሉ አሉ ብሎ መገመት እንደሚከብድ አስታውቀዋል። በዚህ አይነት ወደሥልጣን መምጣትም ሆነ ተቀባይነትን ለማግኘት የሚደረግ ሙከራ ከአሁን በኋላ ቦታ እንደሌለው የጠቆሙት አቶ ቶሌራ፣ እነዚሕ ኃይሎች ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ስጋት ናቸው የሚል ነገር ጨርሶ እንደማይታየው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለረጅም ዓመታት ተጋብተውና ተዋልደው እንዲሁም ልዩነት ቢኖራቸውም ተቻችለውና ተከባብረው የኖሩ ሕዝቦች ናቸው ፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን እየታዩ ያሉ እንቅስቃዎችና እየተወሰዱ ያሉ እኩይ ድርጊቶች ከአሁን በፊት ያልተለመዱ እንደሆኑ ጠቅሰዋል። በተለይም ደግሞ የኦሮሚያ ሁኔታን በሚመለከት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሕዝቦች ሁሉ ኦሮሚያ ውስጥ ያሉ ሕዝቦች ናቸው ማለት ይቻላል ብለዋል። እንደ አቶ ቶሌራ ከሆነ ፤ በመሰረቱ የዚህ አይነት ዓላማ አራማጆች እነማን ናቸው በሚባልበት ጊዜ ዋነኛ ተጠያቂ የሚሆነው የህወሓት ጁንታ ነው። ቡድኑ ከመጀመሪያውኑ ጀምሮ ሕዝቦች በእኩልነትና በመፈቃቀር ላይ ተመስርተው እንዲኖሩ የሚፈልግ አልነበረም። ጥላቻና ቅሬታ ተባብሶ በቅሬታዎች መሃል እሱ እድሜውን ለማራዘም የሚተጋ ቡድን ነው።አሁንም ቢሆን በቅርቡ በማይካድራ የተፈጸመው ሁኔታ በሕዝቦች መካከል ጥላቻና ጥርጣሬ እንዲሁም መገዳደል ሰፍኖ ሕዝቦች ተፋጅተው ወደ እርስ በእርስ ጦርነት አምርተው አገሪቱ እንድትፈርስ አስበው ያደረጉት ነው ብለዋል። በአንድ ቀን ተነስተው የፈጸሙት ነገር ሳይሆን ረጅም ጊዜ አቅደው የሰሩበት እንደሆነም አመልክተዋል። በዛ አካባቢ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ክልሎች የዚያን አይነት ሁኔታዎች እንዲፈጠሩና ዓላማቸውንም በኃይል ለመጫን እንደሚሰሩ የታየ ጉዳይ ነው። የጠነከረችና ሕዝቦች በእኩልነት ተቻችለው የሚኖሩባት የበለጸገች አገር እንድትገነባ ፍላጎታቸው ስላልሆነም ያንን ለማስቀጠል በማሰብ ከባህላችንም ፤ ከባህሪያችንም ውጭ የሆኑ የጭካኔ እርምጃዎችን ወስደዋል ብለዋል። አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36933
c13afaa2654954ccf4229e2b4a95c15e
95ddb9a2da4c1130e7a8dab4f657ca91
የትግራይ ክልል ወደቀደመው መረጋጋትና ሰላም እየተመለሰ መሆኑ ተገለጸ
ፋንታነሽ ክንዴ አዲስ አበባ፡- የትግራይ ክልል ወደቀደመ ሰላሙና መረጋጋት እየተመለሰ መሆኑን የትግራይ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁልሚካኤል አስታወቁ::በክልሉ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ 50 ሚሊዮን ብር መመደቡን ገለጹ:: አቶ ነብዩ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በህወሓት ጁንታ ወደ አለመረጋጋት ገብቶ የነበረው የትግራይ ክልል አሁን ላይ ወደቀደመ ሰላምና መረጋጋቱ እየተመለሰ ይገኛል:: ችግሩ ከተፈጠረበት ዕለት ጀምሮ ጉዳዩ ሀገራዊ ጉዳይ ተደርጎ ከፍተኛ ርብርብ እንደተደረገበት እንደሚገኝ ያስታወቁት አቶ ነብዩ ፣ የተገኘው ውጤት ነገሮች በጋራ ሲሰሩ ምን ያህል አመርቂ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል ያሳየ ነው ብለዋል ::አሁን ላይ በክልሉ መደበኛ ሕይወት እየተጀመረ ነው፤ የፈረሰው አስተዳደር በጊዜያዊ አስተዳደር እየተተካ ነው ፤ ሕዝቡም እየተወያየ ይምራኝ የሚለው እና ራሱ የመረጠው አካል እንዲመራው እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል::በአክሱም፣ በሽሬ ፣ በአላማጣ በአጠቃላይ ምዕራብ ትግራይና ደቡብ ትግራይ መቀሌ ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ላይም ሕዝቡ እየተወያየ መሪውን እየመረጠና ወደመረጋጋት እየተመለሰ መሆኑን አብራርተዋል::አገልግሎት ሰጭ የመንግሥት ተቋማትን ወደ ስራ እየተመለሱ መሆኑንም ገልጸዋል::ከመሰረታዊ አገልግሎትና ከሰብዓዊ ድጋፍ ጋር ተያይዞ ተቋርጠው የነበሩ አገልግሎቶች ቶሎ ወደ ሥራቸው እንዲገቡ ለማድረግ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት እርብርብ እያደረጉ መሆኑን የገለጹት አቶ ነብዩ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ የትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ 50 ሚሊዮን ብር በመመደብ የመማር ማስተማር ሂደቱን ወደመደበኛ እንቅስቃሴ ለመመለስ እየተሰራ እንደሆነም አስታውቀዋል::ኮቪድን ከመከላከል አንጻርም ወደ 700ሺ የሚሆን የፊት መሸፈኛ ጭምብል በነጻ ለተማሪዎች እንዲታደል ተወስኖ እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቁመዋል። እንደ አቶ ነብዩ ማብራሪያ፤ ክልሉን ወደነበረበት ለመመለስ ሁሉም አካላት የተቀናጀ ሥራ እየሰሩ ነው፤ የትግራይ ብልጽግናም የሚጠበቅበትን እየተወጣ ይገኛል::በዚህም መሰረታዊ አገልግሎቶች ስራ እንዲጀምሩ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል ። ጉዳት የደረሰባቸውን እንደ መንገድና ድልድይ የመሳሰሉ የልማት አውታሮች እንዲጠገኑና ለሕዝቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል::በዚህ ረገድ መንግስት በዋናነት የፈረሰውን የቀድሞ አስተዳደር በአዲሱ አስተዳደር በመተካት ሕዝቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ እና ቀጣይ ልማቶቹን እንዲያረጋግጥ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል ::የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ በትግራይ ክልል የተከሰተው ችግር እንዴት እንደተፈጠረና እንዴት እንደተቀለበሰ ትኩረት ሰጥቶ መገምገሙን ያስታወቁት አቶ ነብዩ፤ ትግራይን መልሶ ለማልማትና ለመገንባት ጠንካራ ሥራ መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ መቀመጡንም አስታውቀዋል::ከዚህ ባሻገር የትግራይ ህዝብ ከጁንታው ጎን ባለመሆኑና ሊደብቀው ስላልፈቀደ የሕግ ማስከበር ስራው በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅና መከላከያው ድል እንዲቀዳጅ የማይተካ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም የተፈጠረውን ችግር ለመቀልበስ በተከናወኑ እልህ አስጨራሽ ስራዎች ውስጥ ለነበረው ሚና ሥራ አሥፈጻሚው ለትግራይ ሕዝብ እውቅና መስጠቱን ገልጸዋል::የጁንታው ውድቀት ማለት የትግራይ ሕዝብና ወጣት ውድቀት ማለት እንዳልሆነ ያስታወቁት አቶ ነብዩ ፣ ወጣቱ ለውጡ የራሱ መሆኑን ተገንዝቦ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንዳለበት አመልክተዋል ::ወንጀለኞችን በአጭር ጊዜ ለሕግ ለማቅረብና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሕዝቡ በተለይም የትግራይ ወጣት ቀደም ሲል ሲያደርግ እንደነበረው የራሱን የማይተካ ሚና መወጣት እንደሚኖርበት አስታውቀዋል ።አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36977
4816ad0bfd6978fae99bedb44d053e56
0936fede6a9edaa60fd22703f84a7545
በሃገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ነባር አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጣ
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ ፦በሃገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነበሩ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ::ከኮሚሽኑ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ፣ተጠርጣሪዎቹ መንግስት እና ሕዝብ የጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው መቀመጫቸውን ትግራይ ክልል በማድረግ የህወሓት ፀረ-ሰላም እና ፀረ-ሕዝብ ከሆኑ ከፍተኛ አመራሮች ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ ነበር ::ከዚህ ባለፈም በጽንፈኝነት አስተሳሰብ በመነሣት በኃይል ወደ ስልጣን የመምጣት ፍላጎትን ካነገቡ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ተልዕኮ በመቀበል በሀገር ውስጥ ሌሎችን በማደራጀት ሀገር የመበተን፣ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር እና ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ውስጥ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ መንገድ በመሳተፍ ሕዝብ በመንግሥት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው በማድረግ በሃገር ክህደት እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ በተለያዩ የአመራር ደረጃ ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች የመያዣ ትዕዛዝ እንደ ወጣባቸው አስታውቋል::የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው ተጠርጣሪዎች1. ኮማንደር ሰለሞን አብርሃ ብስራት2. ኮማንደር ኃይለማርያም ብርሃኔ ገብረማርያም3. ምክትል ኢንስፔክተር ክብሮም ገብሩ ገብረእግዚአብሄር4. ምክትል ኢንስፔክተር አረጋዊ ገብረሂወት አስፋው5. ረዳት ኢንስፔክተር ገዛኢ ገብረሂወት ገብረስላሴ6. ረዳት ኢንስፔክተር ተስፋ ኪሮስ ግደይ7. ረዳት ኢንስፔክተር አርአያ ገብረአናንያ ኪዳኑ8. ረዳት ኢንስፔክተር ሰለሞን ወላይ ወልደአብዝጊ9. ዋና ሳጅን ሀይላይ ወልዱ ገብረማርያም10. ዋና ሳጅን ሀፍቱ ካህሳይ አብርሃ ናቸው።በመሆኑም መላው ህዝብ በተለይም ሰላም ወዳዱ የትግራይ ሕዝብ፣ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የጁንታው የህዋሓት የጥፋት ቡድን ተፈላጊዎች አባላትን አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ተግባር በያሉበት የድርሻቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል::በቀጣይም የጁንታው ርዝራዥ ቡድን ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በመግለጽ በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚያደርግ ኮሚሽኑ አስታውቋል::አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36978
3ed3d087c544bb0e340312db820a7adf
25570f171a72b5c5ba245470f43cb525
የሰብዓዊ መብት አከባበር ላይ የነበረውን ችግር ለመቅረፍ በህግ ማዕቀፎች ላይ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ተገለጸ
ዋለልኝ አየለአዲስ አበባ፡- በሰብዓዊ መብት አከባበር ላይ የነበረውን ችግር ለመቅረፍ በሕግ ማእቀፎች ላይ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር ጽሕፈት ቤት ገለጸ::በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይበቃል ግዛው በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የሰብዓዊ መብት የሕግ ማዕቀፎችን ለማሻሻል ረቂቅ ሰነድ ተዘጋጅቷል። ሰነዱ በክልሎች የሚታዩ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን በአግባቡ የሚለይ ነው::የድርጊት መርሐ ግብሩ ሦስተኛው ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበሩት የተሻለ ለማድረግ እየተሰራ ነው:: ከለውጡ በፊት የነበሩት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ሰፊ ፈተና የነበረባቸው ናቸው ያሉት አቶ ይበቃል ፣ አንደኛውና ሁለተኛው የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብሮች አፈጻጸም በነበረው ፖለቲካዊ ዓውድ አመርቂ አልነበረም ብለዋል ። የአፈፃፀም ውስንነቶች እንደነበሩበትም አስታውቀዋል ::ከለውጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ሦስተኛው ረቂቅ ሰነድ ብዙ ማሻሻያዎችን መያዙን ያመለከቱት ኃላፊው ፣ ለውጡ ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር ምቹ ሁኔታ የፈጠረ በመሆኑ የረቂቅ ሰነዱ ይዘት በለውጡ ዓውድ የተቃኘ ነው ብለዋል:: እንደ አቶ ይበቃል ገለጻ፤ ከሕግ አንፃር ሰብዓዊ መብቶችን ይበልጥ ለማስከበር እንዲያስችሉ አዳዲስ የህግ ማዕቀፎች ይወጣሉ::መንግስት በዓለም አቀፍ ግዴታዎች ውስጥ ሊፈጽማቸው የሚችል ኃላፊነቶች ይኖሩታል::በፖለቲካዊና የሲቪል መብቶች፣ በሴቶችና ህጻናት፣ በአረጋውያን መብቶች ላይ አዳዲስ የአሰራር ሥርዓቶች ይዘረጋሉ::ሰብዓዊ መብት ሲባል በብዙዎች አዕምሮ የሚመጣው የፍትሕ ተቋማት ላይ ቢሆንም ሰብዓዊ መብት በሁሉም ቦታ ያለ ነው የሚሉት አቶ ይበቃል ፣ ይህን ለማስፈጸም በተዘጋጀው ረቂቅ የድርጊት መርሐ ግብር ላይ በርካታ ተቋማት እንዲካተቱ ተደርጓል::የመሰረተ ልማት ሥራዎች ሁሉ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ያለባቸው ናቸው:: ሰብዓዊ መብት የማይመለከተው የመንግስት ተቋም ስለሌለ ለሁሉም ኃላፊነት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡ ‹‹ከዚህ በፊት ነበረው አሰራር የፖለቲካ ቁርጠኝነት ከፍተት ይታይ ነበር›› ያሉት አቶ ይበቃል፤ በማዘጋጀትና በመወሰን ሂደት የመንግስት መፍቀድ አለመፍቀድም መሰናክል ሆኖ እንደነበር አመልክተዋል::በዚህም ምክንያት ከዚህ በፊት የነበሩትን መርሐ ግብሮች በታሰበላቸው ዓላማ ለማስኬድ አልተቻለም::ከለውጡ ወዲህ የፖለቲካ ቁርጠኝነት በመታየት የድርጊት መርሐ ግብሩ በሰፊው እንዲሻሻል ተደርጓል ብለዋል::ለድርጊት መርሐ ግብሩ በቂ መዋዕለ ንዋይ እንደሚመደብ በውይይቱ ላይ የተገለጸ ሲሆን፤ የድርጊት መርሐ ግብሩ ግብዓቶች፤ የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት፣ ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች፣ የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች፣ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች እና የመንግስት ተቋማት ዓመታዊ ሪፖርቶች ይሆናሉ::አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36986
e2a1a2f5450be9794c34a047836a107b
4f87aa6ba96d9ceb5ed21c6dc556b1ff
የፍቺው ጥቁር ጥላ በተወዳጁ ሊግ ላይ
 በርካታ እግር ኳስ አፍቃሪያን የዓለማችን ምርጡ ሊግ ሲጠቁሙ ‹‹የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን በማስቀደም የሚስተካከለው የለም›› በማለት ሽንጣቸውን ይዘው ይሞግታሉ። ምንም እንኳን የግል የምርጫ ልዩነት እንደተጠበቀ ቢሆንም አንዱን በመለየት ሂደት በመላው ዓለም የሚገኙ የእግር ኳስ አፍቃሪያንን ቀልብ በመሳብ፣ አንድም የገቢ ምንጭ አንድም የመዝናኛ አማራጭ ሆኖ ብዙዎችን እያዝናና ስለመሆኑ ምስክር በማቅረብ ሊጉን ከማንኛውም ሊግ ያስበልጡታል። ባሳለፍነው አመት በአውሮፓ ታላቅ የእግር ኳስ መድረኮች በሻምፒንስ ሊጉና የዮሮፓ ዋንጫም የፍፃሜ ተፋላሚዎች ከእንግሊዝ መሆናቸው ዋቢ በማድረግም ሊጉ የጠንካራ ክለቦች ባለቤትና የአለማችን ምርጡ ስለመሆኑም ያሰምሩበታል። በተጫዋቾች የአልሸነፍ ባይነት የታጋይነት ስሜት ፈጣን፤ መከላከልንና በአብዛኛው አካላዊ ጥንካሬን መሰረት ያደረገው ሊግ፣ በእያንዳንዱ ውድድር አመት አስቀድሞ ከማይገመቱና በደረጃ ግርጌ ያሉ ክለቦች በደረጃው አናት የሚገኙ ከለቦችን ሲያሸንፉ የሚታይበት መሆኑም የደጋፊዎቹን ቀልብም ለመግዛቱና ዓለምዓቀፍ ትኩረት ለመሳቡ ዋነኛው ምክንያት ሆኖ ይጠቀሳል። በተለይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የቴሌቪዥን ስርጭት ተደራሽነትና ጨዋታዎች የሚተላለፍበት ሰዓትም ይበልጥ ምቹ መሆንም የብዙዎች ምርጫ እንዲሆንና በርካታ የስፖንሰር አድራጊ ተቋማትን ቀልብ እንዲስብ ስለማድረጉም ይታመናል። ብሪታኒያ እኤአ በ2016 ‹‹ከአንድነት ይልቅ ልዩነቱ ይበጀኛል›› በሚል በህዝበ ውሳኔ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ለመፋታት ከወሰነች ማግስት አንስቶ ታዲያ የፍቺው አጀንዳ በአገሪቱ እግር ኳስ በተለይ በተወዳጁ ፕሪሚር ሊጉ ውድድር እጣ ፈንታ ላይ ከፍተኛ ስጋትን አጭሯል። በእርግጥ አገሪቱ ባለፉት ሶስት ዓመታት በብሬግዚት ጣጣ ስትቃወስ ብትቆይም ከህብረቱ የመፋታት ፍላጎትን ግን እንዳቀለለችው አልቀለላትም። በአገሪቱ ታሪክ ሁለተኛ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ቴሪሳ ሜይም የፍቺ አጀንዳ ማስፈፀም አልሆነላቸውም።በጉዳዩ ላይ ከፓርላማ አባላት ጋር ከስምምነት መድረስ ተስኗቸው በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸውን ለመልቀቅም ተገደዋል። ስልጣናቸውንም ለሃምሳ አምስት አመቱ ቦሪስ ጆንሰን አስረክበዋል። የብሬግዚት አቀንቃኙ የቀድሞ የለንደን ከተማ ከንቲባና የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንም የለንደንን ከህብረቱ የመፋታት ውጥን እንደሚያሳኩና የሀገሪቷን አንድነት እንደሚያስጠብቁም ቃል ገብተዋል። ካለስምምነት ከህብረቱ መፋታትን አዋጭ አድርገው የሚመለከቱት ጆንሰን፣ በመጪው የፈረንጆቹ ጥቅምት መጨረሻ አገራቸውን ከህብረቱ ለማፋታት ቆርጠው ተነስተዋል። ጉዳዩንም የሞት ሽረት አድርገው ገፍተውበታል። ምንም እንኳን የፍቺውን ፍላጎት የሚደግፉት ቢኖሩም፤ ‹‹ያለምንም ስምምነት ፍቺውን የመፈፀም አደጋ ከባድ ነው፤ ይሕን ለማስቀረትም አማራጮችን መቃኘት ያስፈልጋል›› በሚል ስጋታቸውን የሚያስቀመጡ በርካቶች ሆነዋል። በአለም ኢኮኖሚ እድገት አምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠቸውን አገር ኢኮኖሚ በእጅጉ እንደሚጎዳ የሚያሳስቡም አልጠፉም። ገና ከወዲሁ የፓውንድ አቅም መዳከምና ታላላቅ ኩባንዎችም በፍቺው ጣጣ መተማመኛ ማጣታቸውን ሲገልፁ መደምጣቸውም ለዋቢነት ይነሳል። የብሬዚዳት ቀውስ የአገሪቱን በርካታ ኢንዱስትሪዎች እንደመነካካቱ ተወዳጁ የአለማችን ፕሪሚየር ሊጉም ከሰለባዎቹ መካከል ዋነኛው ስለመሆኑ የሚያስገነዝቡ ባለሙያዎች ቁጥርም ከፍተኛ ነው። በተለይ የፍቺው ቀነ ቀጠሮ እየቀረበ በመጣ ቁጥር ስጋቶችም አብረው ከፍ ሲሉ እየተስተዋለ ይገኛል። አገሪቱ በመጪው የፈረንጆቹ ጥቅምት መጨረሻ ከህብረቱ ከተፋታች በተወዳጁ የአለማችን ፕሪሚየር ሊግ ላይ ከሚስተዋሉ ጥቁር ጥላዎች መካከል አንዳንዶቹ ከወዲሁ ተገምተዋል።፡ የሊጉ ተሳታፊ ክለቦችና የተጫዋቾች ዝውውር ላይ የሚያደርሰው ጫናም ከሁሉ ቀድሞ ተጠቅሷል። በተለይ ‹‹በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ከወገብ በላይ ሆነው የሚያጠናቀቁና በተጫዋቾች ዝውውር ገበያው ቀንደኛ ተዋናይ በመሆን ስኬታማ የሚሏቸውን ተጫዋቾች በማስፈረም የሚታወቁ ክለቦች፣ ከፍቺው በኋላ ፍላጎታቸውን በቀላሉ ለማሳካት ይቸግራቸዋል››ተብሏል።በሰዎች ላይ የሚደረጉ ማናቸውም በነፃነት ተንቀሳቅሶ የመስራት ገደቦችም የክለቦቹ ዋነኛ ፈተና እንደሚሆኑም ተመላክቷል። ከብሬግዚት በኋላ ማንችስተር ዩናይትድና አርሰናልን የመሳሰሉ ክለቦች ምርጫ የሆኑት የጀርመን፣ ፈረንሳይና ስፔን ተጫዋቾች እንግሊዝ ምድር እግር ኳስን ለመጫወት የስራ ፈቃድ ማግኘትና መስፈርቶችን ማሟላት ግድ እንደሚላቸውም ታውቋል።ይሕም በተጫዋቾች ብቻ የማይወሰንና አሰልጣኖችንም የሚመለከት ይሆናል። በአለም በኢኮኖሚ እድገት አምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠቸው አገር ኢኮኖሚ በእጅጉ ተንገጫግጮ በተለይ የፓውንድ የመግዛት አቅም የሚዳከም ከሆነ ደግሞ ክለቦች የሚፈልጓቸውን ተጫዋቾች ፊርማ ለማግኘት እንዲቸገሩ ማድረጉ አይቀሬ ነው። የመገበያያ ገንዘቡ አቅም ማጣትን ተከትሎም ተጫዋቾች ልፋታቸውን የሚመጥን አቅም ያለው ገንዘብ አለማግኘታቸውን ታሳቢ በማድረግ በእንግሊዝ ምድር እግር ኳስን ለመጫወት ፍላጎት እንዳይኖራቸው ያደርጋል። ለመጫወት እንዲወስኑ ለማግባባት ደግሞ የፕሪሚር ሊጉ ክለቦች ተጨማሪ ገንዘብን ለመክፈል ኪሳቸው መግባት ግድ ይሆንባቸዋል። ተጫዋቾች ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለመምጣትና ለመቆየት ዳተኛ ከሆኑ ደግሞ በአልሸነፍ ባይነት ተጋድሎ በሚታወቁት ክለቦች መካከል የተፎካካሪነት ስሜት እንዲቀንስ በማድረግ የሊጉን ተወዳጅነት ያደበዝዘዋል። ምርጥነቱን ሊያስነጥቀውም ይችላል። ይሕም በተለይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የቴሌቪዥን ስርጭት ተደራሽነት ምክንያት የሰበሰባቸውን በርካታ የስፖንሰር አድራጊ ተቋማት ቀልብ በማስነፈግ፣ አስተማማኛና ከፍተኛ የገንዘብ አቅሙን በእጅጉ ያዳክመዋል። ዋጋውንም ዝቅ ያደርገዋል። የብሬግዚት ጣጣ ክለቦች የውጭ አገር ተጫዋቾች ለማስፈረም እንዲቸገሩና ሂደቱንም ውስብስብ በማድረግ በተጓዳኝ የውጭ አገራት ተጫዋቾች ቁጥር ለመቀነስ ሊያስገድዳቸውም ይችላል።መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ እኤአ በ1992 በፕሪሚር ሊጉ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች መካከል 70 በመቶ እንግሊዛውያን ነበሩ።ይሕ አሃዝ እያደር አሽቆልቁሎ ባሳለፍነው ውድድር አመት ከ26 እስከ 27 በመቶ ደርሶም ታይቷል። የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር (ኤፍ.ኤ) በአንድ ክለብ ከ25 ቡድን አባላት ውስጥ የሚገኙ አገር በቀል ተጫዋቾች ቁጥር ከፍ እንዲል ሲተጋ ቆይቷል።የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦችም 12 አገር በቀል ተጫዋቾችን ማስመዝገብ እንዳለባቸውም በፖሊሲው ያስቀምጣል። ይሕ ህግ በተቀመጠበት የሊጉ ክለቦች በፍቺው ጥቁር ጥላ ምክንያት እንደቀድሞው የውጭ ተጫዋቾችን በቀላሉ ለማስፈረም ካልቻሉም ወደ አገር በቀል ተጫዋቾ ማተኮሩና ለታዳጊዎች ልማት ትኩረት መስጠታቸው አይቀሬ ነው። ይሕ ደግሞ በሊጉ የሚጫወቱ እንግሊዛውያን ተጫዋቾችን ቁጥር ከፍ እንዲልለት ፍላጎት ላለው ማህበር ዋነኛ ፍላጎት ነው። አዲሱ የማህበሩ የቴክኒክ ዳይሬክተር ለስ ሪድም የብሬግዚት ጣጣ በርካታ እንግሊዛውያን ተጫዋቾች በተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ የመጫወት እድልን እንደሚሰጥ እምነት አላቸው። በአሁን ወቅት በሊጉ የሚጫወቱ እንግሊዛውያን ተጫዋቾች ቁጥር ከ32 እስከ 34 በመቶ ከፍ ማለቱን የሚጠቁሙት ዳይሬክተሩ፣ ማህበሩ ይሕ አሃዝ ይበልጥ እንዲጎለበት ፍላጎት እንዳለውም ያስምሩበታል። ‹‹ጠንካራ ፕሪሚየር ሊግ ያስፈልገናል፤ ይሕ እንዲሆን የምንፈልገውም ለአገሪቱ እግር ኳስ ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ስለሆነ ነው›› የሚሉት ዳይሬክተሩ፣ ሊጉ የአለማችን ጠንካራና ምርጡ ሆኖ እንዲቀጥል፣ ሳቢና ማራኪ ከመሆኑ ባሻገር በምጥጥንም የተሻለ እንዲሆን ፍላጎታቸው ስለመሆኑም አፅኖት ሰጥተውታል። ለዚሕ ውጥን እውን መሆን ደግሞ ሊጉ ለወጣት እንግሊዛውያን ተጫዋቾች እድል መስጠቱ ግድ መሆኑን አስ ምረውበታል። በአሁን ወቅትም ክለቦች ታዳጊዎችን ለማፍራት እየታተሩ ሰለመሆኑና በቼልሲ ክለብ ላይ ለአንድ አመት የተወሰነው የተጫዋቾች ዝውውር ቅጣት በእስታንፎርድ ብሪጅ የነበረውን ባህል በእጅጉ እንደቀረው የሚጠቁሙት ዳይሬክተሩ፣በአሁኑ የፍራንክ ላምፓርድ የቼልሲ ቡድን አባላት ውስጥ ታሚ አብረሃም ማሶን ማውንትን የመሳሰሉ ወጣቶችን መተዋወቃቸውም አንድ ጅምር ሰለመሆኑ ነው ያስገነዘቡት። በአጠቃላይ በብሬግዚት ጣጣ ክለቦች የውጭ ተጫዋቾችን በቀላሉ ማግኘት ሊያስቸግራቸው ቢችልም፤ በተቃራኒው ትኩረታቸውን ወደ አገርው ውስጥ እንዲመልሱ ስለሚያደርጋቸው በርካታ እንግሊዛውያን ተጫዋቾች በሊግ የመጫወት እድልን እንደሚያገኙም ተማምነዋል። በርካታ የእግር ኳስ ሳይንስ ባለሙያዎች በአንፃሩ በአገር ውስጥ ተጫዋቾች ብቻ የሚካሄድ ሊግን መናፈቅ አግባብ አለመሆኑንና ለተወዳጁ ሊግ ተወዳጅ ሆኖ መዘልቅ አዋጭ አለመሆኑን አስገንዝበዋል።የሊጉ አስተዳዳሪ አካላትም ከዚህ የተሳሳተ እሳቤ መውጣት እንዳለባቸው አፅኖት ሰጥተውታል። ምንም እንኳን በአሁን ወቅት የብሬግዚት አጀንዳ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ከፊት ቢደቀኑበትን በርካቶች ግን ከወዲሁ ከፍቺው በኋላ የሚሆነው አስግቷቸዋል። ተወዳጁ የአለማችን ሊግም ዕጣ ፈንታውን የሚወስንለት የፍቺው ቀነ ቀጠሮ እስኪደርስ ተወዳጅ ሆኖ ይዘልቃል።አዲስ ዘመን  ጳጉሜን 5 /2011 ታምራት ተስፋዬ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=17599
fee782a584a4b7e35a86a4fb4072e68f
2e51be1280c61c3ae0d231e83ceee824
የማንጎ ምርት “ኋይት ስኬል “ በተባለው ነፍሳት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት መሆኑ ተገለጸ
ሞገስ ጸጋዬአዲስ አበባ፡- የማንጎ ምርት “ኋይት ስኬል” በተባለ ነፍሳት በመጠቃቱ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት መሆኑን በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ተመራማሪና መምህር ዶክተር አዳነ ተስፋዬ አስታወቁ::ከችግሩ የተነሳ አርሶ አደሮች ማንጎ ለማምረት ያላቸው ፍላጎት እንደቀነሰ መሆኑን ጠቆሙ ።ዶክተር አዳነ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት በርካታ የተክል አይነቶች መነሻቸው በማይታወቁ በሽታዎች በመጠቃታቸው የተነሳ ምርታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ነው::በተለይ ማንጎ በሀገራችን የተለያዩ ቦታዎች በስፋት የሚመረት ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ምርቱ በተባይ በመጠቃቱ አርሶ አደሮች ከማምረት እየተቆጠቡ ነው ::ማንጎ በበሽታ ከተጎዳና ምርታማነቱ ከቀነስ ቢቆይም ሊታደገው የሚችል መፍትሔ አልተበጀለትም የሚሉት ተመራማሪው፣ በግብርና ሚኒስቴር በኩልም ችግሩ ተገቢውን ትኩረት እንዳላገኘ አመልክተዋል ። በፍጥነት ከመድረስ አኳያ ማንጎ ተመራጭ የገበያ ምርት መሆኑን የጠቆሙት ተመራማሪው ፣ የተሻሻለ ዝርያ ባለመዘጋጀቱ የተነሳ በርካታ አርሶ አደሮች በማንጎ ፈንታ ሌላ ዝርያዎች ወደ ማምረት እየተሸጋገሩ ነው ብለዋል::በርካታ አርሶ አደር ባለበት ሀገር ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት ባለመስጠቱ አርሶ አደሮች ከማምረት እየተቆጠቡ ነው::በዘርፉ የሰለጠኑ ባለሙያዎች ቢሆን ወደ ሌላ የስራ መስክ እየሄዱ ነው ፤ይህ ደግሞ ለበሽታው ጥሩ አጋጣሚ እንደፈጠረለትም አስታውቀዋል:: በዘርፉ ለሚደረጉ ጥናቶች የሚበጀተው በጀት በጣም አነስተኛ መሆኑን ያመለከቱት ተመራማሪው ፣ በዚህ የተነሳ በዘርፉ ተገቢው ጥናት ባለመደረጉ በቀላሉ መከላከል የሚቻሉ በሽታዎች ስር ሰድደው ሰፊ ችግር እያስከተሉ መሆኑን ገልጸዋል::አርሶ አደሩ በራሱ አቅም በሽታዎችን ለመከላከል በርካታ ጥረቶችን ቢያደርግም ችግሩን መቋቋም እንዳልቻለ አመልክተዋል::ከውጭ ሀገር የሚመጡ ተመራማሪዎችንና ኢንቨስተሮችን መርምሮ ማስገባት ያስፈልጋል የሚሉት ዶክተር አዳነ፣ በርካታ በሽታዎች የሚመጡት ከውጭ ሀገር መሆኑ ገልጸዋል። የበሽታውን ስርጭት እንዳይስፋፋ ከክልል ወደ ክልል ያለውን የችግኝ ዝውውር መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል::ጉዳዩን በተደጋጋሚ ለመንግስት ቢያሳውቁም ትኩረት ከመነፈጉ በላይ የማንጎ ምርት ቀደም ካለው ጊዜ ጋር ሲወዳደር በግማሽ ቀንሷል ፤ በጥራት ደረጃም የወረደና በገበያም ተፈላጊነቱ እየቀነሰ መጥቷል፤ እንዲሁም ወደ ውጭ ይላክ የነበረው ምርት አሁን ሙሉ በሙሉ ቆሟል ብለዋል ::አዲስ ዘመን ህዳር 30/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36988
535c4e91ddf5cfef0825ba0313c68f0a
abd08fed3e3251044daeddc15ee4096a
ዋልያው ወደ ቀጣዩ ዙር አ
 የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በ2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ለ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታውን ከቀናት በፊት ባህርዳር ላይ ከሌሴቶ ጋር የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን፣ በጨዋታው ከተጋጣሚው የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ማሳየት ቢችልም እድሎች በመፍጠርና የተፈጠረውን እድልም በአግባቡ መጠቀም ባለመቻሉ ያለ ምንም ግብ ማጠናቀቁ ይታወሳል። ብሔራዊ ቡድኑ በሜዳውና ደጋፊው ፊት ነጥብ መጣሉ በቀጣይ መልስ ጨዋታ አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገባ ያስገደደው ቢሆንም፤ ወደ ሌሴቶ አቅንቶ በሳምንቱ መጨረሻ ከሌሴቶ አቻው ጋር ያደረገው ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችሏል። ከባህር ዳሩ ጨዋታ በተለየ ሶስት ተጫዋቾችን በመቀየር ወደ ሜዳ የገቡት ዋልዎቹ፣ ‹በጨዋታው ኳስን ከኋላ መስርተው በመልሶ ማጥቃት በቁጥር በዝተው በመሄድ እድሎችን ለመፍጠር ለመጫወት ሲሞክሩ ታይተዋል። መከላከልን ምርጫቸው አድርገው ወደ ሜዳ የገቡት የሌሴቶ አዞዎች በአንፃሩ አልፎ አልፎ ከመሃል ሜዳ በረጅሙ በሚላኩ ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ቢሞክሩም የዋልያውን ተከላካይ ክፍል ጥሰው መግባት አልሆነላቸውም። ሁለቱም ቡድኖች ይሕ ነው የሚባል ጠንካራ የግብ ማግባት እድሎችን መፍጠር ሣይችሉ፤ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል። በሁለተኛው አጋማሽ በአንፃሩ ሁለቱም ብሄራዊ ቡድኖች ወደ ተጋጣሚያቸው ሜዳ ክልል በመዝለቅ ተጭነው ለመጫወት ሞክረዋል። ሁለተኛው አጋማሽ ከተጀመረ ከአምስት ደቂቃ በኋላ ቢኒያም በላይ ከቀኝ መስመር በኩል ያሻገራት ኳስ በሌሴቶው ተከላካይ ንካይ ኔትሪሊ ተጨርፋ አዞዎቹ በራሳቸው ላይ ግብ እንዲያስቆጥሩ ምክንያት ሆናለች። ግብ ከተቆጠረባቸው በኋላም የአጨዋወት ዘይቤያቸውን በመለወጥ ተጭነው ለመጫወት የሞከሩትና በተደጋጋሚ ወደ ዋልያው ግብ ክልል የተመላለሱት ሌሴቶዎች፣ ግብ ለማስቆጠር ብዙም ደቂቃ አልፈጀበቸውም። ግብ ከተቆጠረባቸው ከአምስት ደቂቃ በኋላ ያገኙትን ቅጣት ምት ሴፖ ሴትሩማንግ ወደ ግብ አክርሮ የመታት ኳስ የመስፍን ታፈሰን እግር በመጭረፍ ከዋልያው መረብ ላይ አርፋለች። ጨዋታው አንድ አቻ መሆኑን ተከትሎ ዋልያዎቹ ይበልጥ ወደ መከላከሉ ፊታቸውን ያዞሩት ሲሆን፣ አዞዎቹ በአንፃሩ ተጨማሪ ግብ ለማግኘት ይበልጥ ተጨነው ለመጫወት ሞከረዋል። ከአንድም ሁለት ጊዜ ለግብ ቀርበው የግቡ አግዳሚ የመለሰባቸው አጋጣሚም ተስተውሏል። ሰዓት እየገፋ በሄደ ቁጥር ጫና እየበዛባቸው የመጡት በተለይ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ መረጋጋት የተሳናቸው ሌሴቶዎች፣ ኢትፒሰን ብሄራዊ ቡድን መከላከል ጥመረት በማፍረስ ግብ ማስቆጠር ባለመቻላቸው ጨዋታው በአንድ አቻ ውጤት ሊጠናቀቅ ግድ ብሎታል። ይህንን ተከትሎም ዋልያው ከሜዳው ውጪ ባስቆጠረ በሚል የሌሴቶ አቻውን በመርታት በ2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል። የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ ድልድል ውስጥ መግባቱንም አውቋል። ዋልያዎቹ ምንም እንኳን ከጨዋታው ነጥብ በማግኘት ወደ ምድብ ድልድሉ መግባት የሚስችላቸውን ውጤት ማግኘት ቢችሉም፤ በተጋጣሚያቸው ሜዳ የሚያሳዩት አለመናበብና የፈጠራ ብቃት እጥረት ግን ዋነኛ ክፍተታቸው መሆኑ ሳይጠቁም አይታለፍም። በዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታዎች አሸናፊ የሆኑ 14 ቡድኖች ለዋናው የማጣሪያ ጨዋታ ከተመደቡት 26 ቡድኖች ጋር ተቀላልቀለው ይፋለማሉ። እነዚህ የ40 ሀገራትም እያንዳንዳቸው በአራት ቡድኖችን በያዙ 10 ምድቦች ተደልድለው ይጫወታሉ። የየቡድኖቹ አላፊ 10 ቡድኖች የመጨረሻውን ማጣሪያ ያከናውናሉ። ከ10 ቡድኖች አሸናፊ የሚሆኑት አምስቱ የ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ላይ አፍሪካን ወክለው የሚሳተፉ ይሆናሉ።አዲስ ዘመን  ጳጉሜን 5 /2011 ታምራት ተስፋዬ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=17596
b94f69f2eff35068db4f923b5ac48af4
84c71ae22eb4e729a69d1a90175d2916
የማህበሩ ቅሬታ ከመግለጫ እስከ ፍርድ ቤት
የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን «በኢትዮጵያ አሁን ያለው የሊግ አደረጃጀት በፋይናንስ ረገድ ክለቦች ላይ ያለው ተጽዕኖ ምንድነው?» በሚል ርዕስ አንድ ጥናት አስጠንቶ ነበር። የፌዴሬሽኑ ጥናት እንዳመለከተው፤ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚገኙት አጠቃላይ ክለቦች በየዓመቱ ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ ያደርጋሉ። ክለቦቹ ይህንን ገንዘብም ለተጫዋቾች ወርሃዊ ደመወዝ፣ ለምግብ፣ ለመኝታ፣ ተዟዙሮ ለመጫወትና ለትራንስፖርት ወጪ እንደሚያወጡም ገልጿል። ከህዝብ፣ ከግብር ከተሰበሰበ ገንዘብ፣ ከክልል መስተዳድሮች በሚሰጥ በጀት ያለ ተጠያቂና ውጤት ተኮር ዓላማ ለተጫዋቾች የሚወጣው በሚሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብ እጅጉን ያስደነግጣል። የክለቦቹ ገደብ አልባ ወጪ በብዙ መልኩ አነጋጋሪ በመሆን ለዓመታት የተሻገረ ሲሆን፤ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ለዚህ ጉዳይ ልጓም ይሆናል ያለውን መፍትሄ አመላክቷል። ባሳለፍነው ነሐሴ 3 ቀን 2011 ዓ.ም የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የክልል ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎችና የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራሮች በተገኙበት ቢሾፍቱ በተደረገው ጉባዔ ለዚሁ ችግር መፍትሄ የሚያመጣ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል። ፌዴሬሽኑ በዚህ ውሳኔው የተጫዋቾች ደመወዝ ከ50 ሺህ ብር በላይ እንዳይሆን ህግ አውጥቷል። ይህ መመሪያ ጸድቆ ተግባር ላይ ቢውልም ከወዲሁ የተቃውሞ ድምጾች እየተሰሙበት ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉት ቦለር አሶሴሽን በውሳኔው ተገቢነት ላይ ጥያቄን ካነሱት አካላት መካከል ይጠቀሳል። ማህበሩ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን ባስተላለፈ ማግስት ውሳኔው ተገቢነት እንደሌለው በመግለጽ ቅሬታውን ሲያሰማ ቆይቷል። ከሰሞኑ መመሪያው የተጫዋቾችን ሰብአዊ መብት የሚነካ በመሆኑ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑን ፍርድ ቤት ለማቆም መሰናዶ መጀመሩን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉት ቦለር አሶሴሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ እንደነገሩን ፤ ማህበሩ ለዚህ ውሳኔ የበቃው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተደጋጋሚ ደብዳቤዎች ቢላኩለትም ምላሽ ባለመስጠቱ ነው። የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉት ቦለር አሶሴሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ምን መሰረት ይዞ ውሳኔ እንዳሳለፈ አቶ ግርማ አስረድተዋል። «ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ በመጀመሪያ ደረጃ የተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ መመሪያ ሲያወጣ የራሱን መመሪያና የፊፋን መተዳደሪያ ደንብ የጣሰ እንደሆነ ያምናል ። መስከረም 27 ቀን 2004 ዓ.ም. በወጣው የፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ በአንቀጽ አምስት የአባላት የጋራ ጥቅም እንዲሁም በአንቀጽ 11፣ 46 እና 47 የአባላት መብቶችና የዓለም አቀፍ የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት ከሚከተሉት ሕጋዊ አሠራር ያፈነገጠ ነው» ብለዋል።ፕሬዚዳንቱ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን ያስተላለፈው ከስፖርት ኮሚሽን ጋራ በአብሮነት መሆኑን አንስተዋል። ስፖርት ኮሚሽን በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የፌዴሬሽኑ አባል አለመሆኑ፣ በፌዴሬሽኑ ደንብ ላይ የተገለጸው የተጫዋቾች መብት አለመጠበቁ፣ አንቀጽ 47 ላይ የተደነገገው የስፖርት ግልግል ጉባኤ አለመተግበሩ ህጋዊ መሰረት የሚያሳጠው መሆኑን በመግለጽ ሞግተዋል። ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ በተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ መመሪያ ሃገር አቀፍና አለም ዓቀፍን መተዳደሪያ ደንብ ከመጣስ ባሻገር፤ የኢትዮጵያን የፍትሐብሄር ህግ የጣሰ ድርጊት እንደሆነም አመልክተዋል።የፌዴሬሽኑ ውሳኔ ላይ ተቃውሞ እንዳለው የተናገረው የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ዳዊት እስጢፋኖስ ፤ ፌዴሬሽኑ በግለሰብ ላይ እንዲህ ዓይነት ውሳኔ የማሳለፍ መብት እንደሌለው ገልጿል፡፡ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ የፈፀመው ድርጊት ህጋዊ መሰረት እንደሌለውና መተዳደሪያ ደንቡን የሚጥስ እንደሆነ በተደጋጋሚ በደብዳቤም ጥያቄ አቅርበው በአፋጣኝ መልስ ሊሰጥ እንዳልቻለ ያስታውሳል። ማህበሩ ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ለጥያቄያቸው እስከ መስከረም አንድ ቀን 2012 ድረስ መልስ ካልሰጠ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ከውሳኔ ላይ መድረሱን አስታውቋል። ዳዊት እስጢፋኖስ፤ ለብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ጥያቄያቸውን አስገብተው ምላሽ እየጠበቁ እንደሚገኙ፣ ከፌዴሬሽኑ ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸውና አብሮ መስራት ሲባል ግን በዚህ መልኩ አለመሆኑን ጠቅሷል። የፌዴሬሽኑ ዋናው ክፍሎች ተጫዋቾች በመሆናቸውም የተጫዋቾች መብት ማስጠበቅ ይኖርበታል። የተጫዋቾችን መብት ባላከበረና ባልጠበቀ ሁኔታ፣ ሳያማክርና መግለጫ ሳይሰጥ ውሳኔ ማሳለፍ አግባብነት የሌለውና ትክክል እንደሆነ በመግለጽ የብሄራዊ ፌዴሬሽኑን ድርጊት ኮንኗል።የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ ሌላው አባል አቶ ኤፍሬም ወንድወሰን በበኩሉ‹‹ማህበሩ አላማው የተጫዋቾችን መብት ማስከበር ነው ፤ በተጫዋቾች ላይ ቀደም ሲል ሲደርሱ የነበሩ የተለያዩ የመብት ጥሰቶች ነበሩ ፤ አሁን ግን ከመንግስት የተሰጠን ፍቃድ በመጠቀም በተጫዋቾች ላይ የሚደርሱ የመብት ጥሰቶችን ለመከላከል እንሰራለን›› ካሉ በኋላ፤ ማህበሩ ፍቃድ ካገኘ በኋላ እርሱን ያላማከለ ውሳኔ ተወስኖ የሞራል ጉዳት መድረሱን አብራርተዋል።አቶ ኤፍሬም «በተደጋጋሚ ለፌዴሬሽኑ ጥያቄዎች ቢቀርቡለትም ከዝምታ ውጪ ምላሽ አልሰጠም። ማህበሩ ካሉት የህግ ሰዎች ጋር ተመካክሮ ቀጣይ መንገዶችን መጓዝ እንዳለበት ከውሳኔ ደርሷል። በመሆኑም ሁላችንም ወደምንዳኝበት ፍርድ ቤት ጉዳዩን ይዘን የምንሄድ ይሆናል። ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ለመነጋገር በሩ ክፍት ነው። እስከ መስከረም አንድ ቀን 2012 ዓ.ም በዚሁ ፍላጎቱ የሚፀና መሆኑንና ምላሽ ከሌለ ወደ ህግ የሚጓዝ ይሆናል» ሲል ሃሳቡን ቋጭቷል።ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ከመግለጽ በስቀር የማህበሩን እንቅስቃሴ በተመለከተ ምንም አይነት ማብራሪያም ሆነ መግለጫ ሲሰጥ አልተደመጠም።አዲስ ዘመን  ረቡዕ ጳጉሜ 6/2011ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=17791
b37ede3694e261b09d89445c6cfec29d
3355d97fdb4db0ca1259dddc07721d7b
መንግሥት የወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ በመደገፍ በቴልአቪቭ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፡- በእስራኤል የሚኖሩ የቤተ እስራኤል ማኅበረሰብ አባላት፣ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮ ጵያውያን መንግሥት በህወሓት ጁንታ ላይ የወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ እና የመከላከያ ሠራዊት ያደረገውን ተጋድሎ በመደገፍ በቴልአቪቭ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከቴል አቪቭ፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከቤርሼባ እና ከሌሎችም የእስራኤል ከተሞች የመጡ ናቸው ።ሰልፉን ያዘጋጁት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጁንታውን በመደገፍ እና በመንግሥት የተወሰደውን የሕግ ማስከ በር እርምጃ በመቃወም ሰልፍ ያደረጉ ሰዎች ጥያቄ እንዳስቆጣቸው አስታውቀዋል።በእስራኤል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ረታ ዓለሙ ለሰልፈኞች ባስተላለፉት መልዕክት “መንግሥታችን የወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ እና ለመከላከያ ሠራዊታችን ያላቸውን አክብሮት ለመግለጽ ድጋፍ ስላደረጋችሁ በመንግሥት ስም አመሰግናለሁ” ብለዋል።ሕግ የማስከበር ዘመቻው በድል መጠናቀቁ ትልቅ ስኬት መሆኑን ጠቅሰው፣ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት መሰረት በሕግ የሚፈለጉትን የጁንታው አባላት ለሕግ ለማቅረብ መንግሥት የሚያከናውነው ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።በቀጣይ የመንግሥት ዋና ትኩረት የትግራይ ሕዝብ አሁን ካለበት ሁኔታ እንዲወጣ የመልሶ ግንባታ ማከናወን፣ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ የተሰደዱ ዜጎችን ወደነበሩበት ቀዬ መመለስ መሆኑን አስታውቀዋል ። እነዚህን ተግባራት በመደገፍ ከመንግሥት ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።የድጋፉ ተሳታፊዎች ባወጡት የአቋም መግለጫ፣ በሰሜን እዝ ላይ በተፈጸመው ከባድ ክህደት እና ጥቃት ልባችን አዝኗል፤ የጁንታውን ቡድን ለፍትህ ከማቅረብ በተጨማሪ ቡድኑ በሕግ ሊታገድ እንደሚገባ ጠይቀዋል።  ሰልፈኞቹ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት በወቅቱ ያሰባሰቡትን 17 ሺህ 200 የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ለኤምባሲው አስረክበዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 27/2013 ዓ. ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36809
8e04de283dfcc20c52d079eb684a1a93
91e8a25d1b4900c76dea8d3aac9bfba7
የወታደሯ የሶስት ቀናት የከርሰ ምድር ውስጥ ቆይታ
አዲስ አበባ፦ መ/ወ/ር ተስፋነሽ ጋቢሳ ትባላለች። የመከላከያ ሠራዊታችን ልዩ ኃይል አባል ናት። ጁንታው በከፈተው ውጊያ ለመፋለም በራያ ግንባር ከክፍሏ አባላት ጋር ተሰልፋ በርካታ ግዳጆችን በድል ተወጥታለች።ጠላት ለዓመታት ያዋጋኛል ብሎ እንዳዘጋጀው በወታደራዊ ጠበብቶቹ በግንባሩ መሪ ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ እና ሌሎች አመራሮች የተመሰከረለት ልዩ ቦታው አዲ ቀይህ የተባለው ቦታ ላይ ለ3 ቀናት በተደረገው ፍልሚያ በጀግንነት እየተዋጋች ሳለ ያልጠበቀችው ገጠማት። በዚህ ቦታ ላይ ጠላት ሙሉ ኃይሉን ተጠቅሞ መዋጋት በመጀመሩ እንደ ሌሎች ምሽጎች በቀላሉ መስበር ካለመቻሉም ባሻገር፣ ጠላትን ለመደምሰስ የገባውን የወገን ጦር ለመቁረጥ መልሶ ማጥቃት በማድረጉ፣ ወገን የኃይል ሚዛኑን ለማመጣጠንና ሌሎች ወታደራዊ ጥበቦችን ለመጠቀም ሲባል ከጠላት ከበባ ሰብረው እንዲወጡ ሲደረግ ፣ መ/ወ/ር ተስፋነሽ በጠላት ቀጣና ተቆርጣ ትቀራለች። ወ/ር ተስፋነሽ ወገን አሸንፎ ሞሽጉን እንደሚሰብር ሙሉ እምነት ስለነበራት ፣ የታጠቀችውን ስናይፐር ጨምሮ መሬቱን ቆፍራ ራሷን ጉድጓድ ውስጥ ትቀብራለች። አፈሩን በእጆቿ በላይዋ ላይ በመመለስ ከመሬቱ ጋር በሚገባ ትመሳሰላለች። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች ብዙ የጁንታው ታጣቂዎች በላይዋ ላይ እየተረማመዱ ከወዲያ ወዲህ ይመላለሱባታል። መማረክን ከሞት በላይ የምትፈራውና ድሉን ሳታይ መሞት የማትፈልገው ጀግናዋ መ/ወ/ር ተስፋነሽ ያላት አማራጭ ሁሉንም ችላ ዝም ማለት ብቻ ነበር።በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለች ጁንታው ከአጠገቧ ላይ ዲሽቃውን ጠመደ ፣ አንዱ የዲሽቃው ዎሳ እግር ከተቀበረችበት አቅራቢያ ላይ አረፈ።በቃ ድሽቃው ቦታውን ሳይለቅ ከአቅራቢያዋ እየተኮሰ 3 ቀናት አስቆጠረ ። በነዚህ ቀናት ራሷን እንደሙት ያለምንም እንቅስቃሴ ትንፋሿን አምቃ በከርሰ ምድር ሳለች ከፍተኛ ውጊያ ከተካሄደ በኋላ ሰራዊታችን ሞሽጉን ሰብሮ ድል ማድረጉን የዲሽቃው ዎሳ እግርም እሷ ካለችበት ጉድጓድ  አካባቢ መነሳቱን አወቀች። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ራሷን ከቀበረችበት በማስነሳት አካባቢውን ስትመለከት ጀግኖች ጓዶቿ ጁንታውን አባረው ቦታውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውታል። እሷ ብታውቃቸውም እነሱ ግን ሙሉ ሰውነቷ ከአፈር ስለተመሳሰለ አላወቋትም ነበርና ‘ እጅ ወደ ላይ ‘ የሚል ድምፅ ሰማች። እሷም እጆቿን አንስታ ‘ ወገን ነኝ ‘ የሚል ድምፅ በደስታ ብዛት ተውጣ አሰማች። እነሱም ወደ ኋላ በመውሰድ ከ 3 ቀናት በኋላ እህልና ውሃ እንድትቀምስ አድርገው ተመልሳ ጁንታውን ለደምሰስ እየተፋለመች ትገኛለች።አዲስ ዘመን ህዳር 27/2013 ዓ. ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36810
5d8e889ba17ce00a2eec50208d57f5fd
0fe83c1bf1490f10892e71df04a6b9a9
“ጁንታው የትግራይን ህዝብ መውጪያ መግቢያ ከማሳጣት ባለፈ የጠቀመው ነገር እንደሌለ ጠንቅቆ ያውቃል” – ዶክተር አረጋዊ በርሄ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
እፀገነት አክሊሉአዲስ አበባ፦ ጁንታው የትግራይን ህዝብ እግር በእግር እየተከታተለ መውጪያ መግቢያ ከማሳጣት ባለፈ የጠቀመው ነገር እንደሌለ ጠንቅቆ እንደሚያውቅ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አስታወቁ።ሊቀመንበሩ ዶክተር አረጋዊ በርሄ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳስታወቁት ፣ ጁንታው እስከ አሁን ህዝቡ በድርጅቱ ቁጥጥር ስር አድርጎ እያንዳንዷን እንቅስቃሴውን እየተቆጣጠረ መውጪያ መግቢያ አሳጥቶ ነው የኖረው ። አሁን ግን የተጎናጸፈውን ድል በመጠቀምና ነጻነቱን በአግባቡ በማጣጣም የመንግሥትን እገዛ ተጠቅሞ እራሱን ወደልማት ያስገባል።የትግራይ ህዝብን በኢኮኖሚ በፖለቲካ ተጠቃሚ አደርጋለሁ ሲባል መጀመሪያ ሊመጣ የሚገባው ነገር ህዝቡን ማስቻል፤ መብቱን መጠበቅ፤ ተደራጅቶ እንዲንቀሳቀስ ማመቻቸት ነው ያሉት ዶክተር አረጋዊ ፣ ይህ ከሆነለት በአጭር ጊዜ ውስጥ በራሱ መንገድ ኑሮውን በማሻሻል መሰረታዊ ለውጥ ማምጣጥ እንደሚችል አስታውቀዋል።መንግሥት መሰረተ ልማቶችን በማሟላት፤ ለወጣቱ የሥራ እድል በመፍጠር በተለይም ደግሞ የጀመረውን ህግን የማስከበር ሥራ በመላ አገሪቱ በማድረግ የትግራይም ወጣት ሌላ ክልል ሄዶ በነጻነት እንዲሰራ በማመቻቸት በኩል ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ አመልክተዋል።ጁንታው ለትግራይ ህዝብ የማያስብ መሆኑን በዚህ ጦርነት እንኳን እራሱን ለማትረፍ ሲል በህዝብና በመንግሥት መሰረተ ልምቶች ላይ ያደረሰውን ውድመትን ማየት ይቻላል ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ የአክሱም የአየር ማረፊያን ጨምሮ ሌሎች በርካታ መሰረተ ልማቶችን አውድሞ መሄዱን አመልክተዋል ።ጊዜያዊ አስተዳደሩም እነዚህን የወደሙ መሰረተ ልማቶችን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆኑ ወደቦታቸው መመለስ ይጠበቅበታል፤ እኛም ማህበራዊ መሰረታችን ትግራይ ክልል የሆንን ፓርቲዎች ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር በጋራ ለመስራት ባለን አቅም ሁሉ ተዘጋጅተናል ብለዋል ።በክልሉ ሥራውን የጀመረው ጊዜያዊ አስተዳደር የህዝቡን አስከፊ ህይወት ለመለወጥ እንደሚሰራ ተስፋ አለኝ ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ክልሉን እንደገና ለመገንባትና ከዚህ በፊትም አጥቶት የነበረውን መሰረተ ልምት ለማሟላት እንደ ፓርቲ ህዝቡን በማስተባበር ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችንም በማድረግ እንደሚሳተፉም አስታውቀዋል።የትግራይ ክልል ከዛሬ 46 ዓመት በፊት ጀምሮ በጦርነት እጅግ የተጎዳ አካባቢ ነው፤ ህዝቡም በእርዳታ ስንዴ የሚኖር የተስተካከለ የመጠጥ ውሃ እንኳን ያላገኘ ነው ያሉት ዳክተሩ፣ ጁንታው በስሙ እየነገደ የሚያጋብሰውን ሃብት ስለተመቸውና እራሱን አንደላቆ እንዲሁም ልጆቻቸውን እጅግ በተቀናጣ ምቾት ውስጥ ማኖር ስለቻሉ ብቻ ስለ ህዝቡ ደንታ ቢስ ሆነው መቆየታቸውን ጠቁመዋል።ይህ መሆኑ ደግሞ ሌላውም የአገሪቱ ህዝብ የእነሱን መንደላቀቅ ሲያይ ህዝቡም በዛው ልክ ተመችቶት የሚኖር እየመሰለው መቆየቱን ጠቁመው፣ ነገሩ ሁሉ የተገላቢጦሽ ነው። የገዢዎቹና የህዝቡ ኑሮ ሰማይና ምድር ነው ። ይህንን ማስተካከል ደግሞ የቀጣይ የቤት ሥራችን ይሆናል ብለዋል።የህግ ማስከበሩ ጉዳይ ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው ያለው ያሉት ዶክተር አረጋዊ ፣ ጁንታው ሁሉም በሚባል መልኩ ከአዲስ አበባ ሸሽተው እንደሄዱት ሁሉ መቀሌ ላይም ሴራ ሲጠነስሱ ከርመው በአሁኑ ወቅት እዛም ስላልሆነላቸው በመሸሸና የሚደበቁበትን ጥግ በመፈለግ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።የመከላከያ ኃይላችንም ከህዝቡ ጋር እየተባበረ እነሱን ይዞ ለፍርድ ለማቅረብ አደን ላይ ነው ። የእነሱ ቡድን አባል የሆነችው ሴትም እጇን ሰጥታለች፤ በቀጣይም ሁሉም እጅ ይሰጣሉ ፤ አንሰጥምም ቢሉ ከመሞት ሌላ አሁን ላይ ምንም አማራጭ እንደሌላቸው ጠቁመዋል።“ የጁንታው ቀንደኛ አባላት በቁጥር ትንሽ ቢሆኑም በርካታ የጥቅም ተጋሪዎች፣ አገልጋዮች፣ ተባባሪዎች እንዲሁም ቤተሰቦችና ታማኞች በትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን በመላ አገሪቱ አሉ፤ ይሁን እንጂ ህዝቡ ማን ምን እንደሆነ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ የባሰበትን ለጸጥታ አስከባሪ አሳልፎ በመስጠት ሌላውን ደግሞ በራሱ መንገድ አርፎ እንዲቀመጥ በማድረግ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። እኛም እንደ ፓርቲ በተለይም ሌቦቹና ዘራፊዎቹ ህግ ፊት እንዲቀርቡ ለማድረግ ከፍተኛ የሆነ ትብብርን ለማድረግ ተዘጋጅ ተናል” ብለዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36856
5295a780375d0f4a60d711e1b7eafade
28e202f6a933aac1f44e611e6488e6ed
የጁንታው የጭካኔ ጥግ – በወታደሮችና በፖሊስ አባላቱ አንደበት
ኢያሱ መሰለአስር አለቃ ቤቴልሄም በዛ ትባላለች። የ11ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል ነች። የከሀዲው ህወሓት ጁንታ ታጣቂዎች በሰሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት  ደርሶባታልም፤ የጁንታው ጭካኔ እንኳንስ በወገን ላይ ቀርቶ በሰው ልጅ ላይ ሊታሰብ የማይችል መሆኑን ትናገራለች።‹‹ሁኔታው ከመፈጸሙ በፊት በሰራዊቱ ውስጥ የጁንታው ተላላኪዎች የሆኑ የሻለቃው አባላት እየተደበቁ በየቀኑ ይሰበሰቡ ነበር። የዋርዲያ ተራቸውን ጠብቀው ስለማይሰሩም የተቀረው ወታደር ያለእረፍት የእነርሱንም ጭምር ሲሸፍን ቆይቷል። የተቀረው ሰራዊት ቀን ቀን አንበጣ እንዲያባርር ይደረጋል። ደምም ሰጥተናል። በብዙ ሌሎች ነገሮችም ማህበረሰቡን እንደግፋለን” ትላለች አስር አለቃ ቤቴልሄም።ጥቃቱ በተፈጸመበት እለትም ቀኑን በሙሉ አንበጣ ሲያባርሩ ውለው ጎናቸውን ለማሳረፍ ጋደም ባሉበት ቅፅበት ነው አብረዋቸው በኖሩ በሰራዊቱ ውስጥ በነበሩ ከሀዲ የጁንታው ተላላኪዎች ከጀርባ የተወጉት::አስር አለቃ ቤቴልሄም ትናገራለች፤ “በዕለቱ ከሌሊቱ አምስት ሰዓት ተኩል ከውጭ ወደ ውስጥ የጥይት ሩምታ ተከፈተብን። ከውስጥ ደግሞ እነዛ አስቀድመው ሲሰበሰቡና ሲያሴሩ የቆዩት የጁንታው እኩይ አላማ ፍፃሚ የሰራዊቱ አባላት የገዛ ጓደኞቻቸው የሆኑ የሌላ ብሄር ተወላጆችን እየመረጡ በተኙበት በጥይት መምታት ጀመሩ።ከተኛንበት እየተጣደፍን ወደ ውጭ ወጣን፤ ትጥቃችን ወዳለበት መጋዘን ሄድን። የመሳሪያ ግምጃ ቤቱ ግን ተቆልፏል። የመጋዘኑን ቁልፍ የያዘውን ወታደር አስቀድመው ገድለውታል” ትላለች አስር አለቃ ቤቴልሄም።በእለቱ ዋርድያ ላይ የነበሩ የሰራዊቱ አባላት በኮሎኔል ሀጎስ መገደላቸውን የምትናገረው አስር አለቃ ቤቴልሄም፤ “ባዶ እጃችንን ስለሆንን እራሳችንንለመከላከል አልቻልንም። ጥቂት ሰዎች ብቻ ነበሩ የሚከላከሉት። ብዙዎችን ገደሉ። እጅ የሰጡትንም ጭምር ገደሏቸው” ትላለች።የጁንታው ታጣቂዎች ግፍና ጭካኔ የትየለሌ መሆኑን የምተናገረው አስር አለቃዋ፤ “አንድ የአራተኛ ክፍለ ጦር አባል የነበረ ወታደር እጁን ከሰጠ በኋላ በታንክ ደፈጠጡት። መትረፍ የሚችሉ ቁስለኞችን ሳይቀር ገደሏቸው። ሬሳቸውን ሳይቀብሩ የራሳቸውን ሰዎች ሬሳ ብቻ አንስተው ሄዱ” ስትል ነው የጓዶቿ በከሀዲ የሰራዊቱ አባላትና በጁንታው ታጣቂዎች የተፈጸመባቸውን ግፍ የምትናገረው።ከዚህ ሁሉ ግፍና ጭካኔ በኋላ የተረፉትን እንድነ አስር አለቃ ቤቴልሄም ያሉ የሰራዊቱ አባላትን የጁንታው ታጣቂና ከሀዲ የሰራዊቱ አባላት በሲኖትራክ ጭነው አጉላ ወደተባለ ትምህርት ቤት ወስደው እንዳጎሯቸው ትናገራለች፤ “በህይወት የተረፉና ከሻምበል በላይ የነበሩ የኦሮሞና የአማራ ተወላጅ የሆኑ የጦር መኮንኖችን ለብቻቸው አስቀመጧቸው። ትኩረታቸው በነሱ ላይ ነበር። እስከ አሁንም የት እንዳደረሷቸው አላውቅም።ሴቶችን ለብቻችን በአንድ ክፍል ውስጥ አጎሩን። ሞባይላችንን፣ ልብሳችንንና ያለንን ዶክመንት፣ ገንዘባችንን ሁሉ ዘረፉን። ያለምግብና ውሃ ለሶስት ቀን ወንበር ላይ እየተኛን አሳለፍን። አንዳንድ የወታደር ሚስት የሆኑ ነዋሪዎች ምግብ ሊሰጡን ሲሞክሩ ይከለክሏቸው ነበር። በረሀብ የተነሳ በጣም ተዳከምን። በመጨረሻ ጥሬ እየቆነጠሩ ይሰጡን ጀመር”እፍኝ ቆሎ እየሰጡ አጉረው ለሁለት ሳምንት ያቆይዋቸውን የሰራዊት አባላት እጃቸውን ጠርንፈው አስረው ወደ መቀሌ እንዳመጧቸው ትናገራለች፤ “መቀሌ የእንስሳት ጤና ኮሌጅ ውስጥ አስቀመጡን። ስድብ፣ እርግጫና ማንጓጠጥ ይደርስብን ነበር።ሌላ አካባቢ የሴቶችን ጡት እንደቆረጡም ሰምተናል። በእኛም ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈጸም መዘጋጀታቸውን እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊቱ የሰጡ የጁንታው ታጣቂዎች ተናግረዋል። ህዳር 21 እቅዳቸውን ለመፈጸም ሲዘጋጁ ህዳር 20 የመከላከያ ኮማንዶዎች ደርሰው ነጻ አውጥተውናል” ስትል በሰራዊቱና በፈጣሪ ታምር መትረፋቸውን ተናግራለች።ጁንታው ለእኩይ አላማው ያልተባብረውን ሁሉ ከማጥፋት የማይመለስ ጨካኝና ከሀዲ ነው ያለችው አስር አለቃ ቤቴልሄም፣ በትግራይ የኩያ ተወላጁን ወታደር ተጋድሎም ታስታውሳለች “የአራተኛ መካናይዝድ አባል የሆነ የኩያ አካባቢ ተወላጅ ከእኛ ወገን ቆሞ ያደረገውን ተጋድሎ ማንሳት ያስፈልጋል። ልጁ ታንከኛ ነው፤ ታንክ ውስጥ እንዳለ እጅህን ስጥ ይሉታል። እኔ የቆምኩት ለኢትዮጵያ ስለሆነ እጄን አልሰጥም ብሎ በታንክ መዋጋት ጀመረ። ታንክ ከታንክ ጋር ገጠሙና ተረባርበው ገደሉት”።ሌላዋ የአይን ምስክር ኮንስታብል አለምነሽ ገመዳ የሰባት ወር እመጫት ናት። የፌዴራል ፖሊስ አባል ስትሆን የጁንታው ታጣቂዎችና የሰራዊቱ ከሀዲ አባላት ለእሷና መሰል እመጫቶች እንኳን እንዳልራሩላቸው ትናገራለች።ኮንስታብል አለምነሽ ምድብ የጥበቃ ሥራዋ አክሱም አየር መንገድ ውስጥ ነው። ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ አየር መንገዱ ውስጥ በጥበቃ ሥራ ላይ ባሉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ የተፈጸመውን ክህደት ስታነሳ እንባዋን መቆጣጠር አትችልም።“እኔ የሰባት ወር እመጫት ስለነበርኩ መሳሪያዬን ለሌሎች ሰጥቼ ማረፊያ ቤት ውስጥ አራስ ልጄን ይዤ ተቀምጬ ነበር። ጋንታ አመራሩ የጁንታው ተላላኪ ነው። ላካስ ከታጣቂዎች ጋር ተመካክሮ ጨርሷል። በጫካው በኩል አድርገው ወደ ጊቢው ገቡና እጅ ስጡ አሉ። እርሱ ቶሎ ብሎ መሳሪያውን ሰጣቸው። ሌሎቹአንሰጥም ብለው አፈገፈጉ። ከዚያም ተኩስ ተጀመረ። አንድ ኃይል አመራር ከማማው ላይ ሆኖ ለመከላከል ሞከረ። መጨረሻም እጁን እንዲሰጥ አደረጉት። እጁን ከሰጠ በኋላ ግን በረንዳው ላይ እጁን በሰንሰለት አስረው በዱላ ጨፈጨፉት›› ትላለች ኮንስታብል አለምነሽ።ኮንስታብል አለምነሽ በከሀዲዎች የተፈጸመው ግፍ ዛሬም ድረስ ከአይኗ አልጠፋ ብሎ አይኖቿ በእንባ እንደተሞሉ ሳግ እየተናነቃት ነበር ሁኔታውን የነገረችን። “ከዚያ ወደ እኔ መጡ ቤቴን ዘግቼ እንደተቀመጥኩ የጥይት እሩምታ አወረዱብኝ፤ ውጪ አሉኝ ህጻን ልጅ ስለያዝኩ አልወጣም አልኳቸው። ጨካኝ ናቸው ለአራስ ልጄ እንኳን አልራሩም::አስገድደው ገቡና ቤቱን ፈተሹ ፤ አንድም ነገር ሳልይዝ ባዶ እጄን አስወጡኝና ልጄን እንዳቀፍኩኝ በሶምሶማ ሩጪ አሉኝ፤ ከእኔ ጋር ሌላም አንድ ልጅ የያዘች ሴት ነበረች። እርሷ ግን ጭንቅላቷ አካባቢ ተመታ ደሟን እያፈሰሰች ሩጪ ተባለች። ሁለታችንም ህጻን ልጅ ይዘናል፤ እሩጡ እያሉ አስሮጡን።ስላሴ ወደሚባል ቤተክርስቲን ጫካ ውስጥ ወሰዱንና የሞቱ የነሱን ታጣቂዎች ተሸከሙ አሉን። ልብሳችንን ጫማችንም አስወልቀው በባዶ እግራችን አስኬዱን፤ እንደዚ አድርገው ወደ ሽሬ አመጡን፤ እጅ የሰጡ አመራሮቻችንንም ገደሏቸው። በተለይ ኦሮሞና አማራን እየለዩ አስቀሯቸው። የደቡብ ተወላጆች ላይም አይናቸው ላይ በርበሬ እየጨመሩ ያሰቃይዋቸው ነበር። በረሀብም የሞቱ አሉ። የሞቱትን አስፋልት ላይ ሲጎትቷቸው ነበር፤ አንዳንዶቹን አፍነው የት እንደወሰዷቸው አናውቅም።ከባለቤቴ ጋር እስከ ሽሬ ድረስ አብረን ከመጣን በኋላ እርሱን እዛው አስቀሩት፤ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም” ከዚህ በላይ ኮንስታብል አለምነሽ መናገር አልቻለችም፤ እንባዋንም መግታት ተሳናት።አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36859
3e56b2ae4fe384321162171dd2507d38
0877b6d1607b930836c3eaf89064bcb0
«ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ያሳዩት ድጋፍ በሀገር ሉዓላዊነት ላይ የማይደራደሩ መሆኑን ያረጋገጠ ነው» – አቶ ብናልፍ አንዷለም የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ
አዲስ አበባ፡- የህወሓት ጁንታ በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ክህደት ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ በነቂስ በመውጣት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያሳዩት ድጋፍ በሀገር ሉዓላዊነት ላይ የማይደራደሩ መሆኑን ያረጋገጠ መሆኑን የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ አስታወቀ፡፡የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከህዳር 25 እስከ 26/ 2013 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በተወያየባቸው አጀንዳዎች እና ባስተላለፋቸው ውሳኔዎች ዙሪያ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ የህወሓት ጁንታ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ የሚከት የክህደት ተግባር ፈጽሟል ፡፡የቡድኑን የክህደት ተግባር ተከትሎ መንግሥት ሀገር የማዳንና ህግ የማስከበር ዘመቻ ማካሄዱን ያመለከቱት አቶ ብናልፍ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በመከላከያ ላይ የተፈጸመውን የክህደት ተግባር በነቂስ ወጥቶ ከማውገዝ ጀምሮ ለመከላከያ ሰራዊቱ የተለያዩ ድጋፎች በማድረግ ከጎኑ መቆሙን ያረጋገጠበት መንገድ እጅግ የሚያኮራ ነው ብለዋል፡፡ህዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ ያሳየው መነቃነቅ የሀገር ሉዓላዊነትን ለማፍረስ ለሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ምንም አይነት ትዕግስት የሌለው መሆኑን ያረጋገጡበት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ብናልፍ፤ ህዝቡ ያሳየው አኩሪ ድጋፍ ለመከላከያና ህግ ለማስከበር ለተንቀሳቀሱት ለሌሎች ኃይሎች ትልቅ ስንቅና ትጥቅ የሆነ እንደነበር የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መገምገሙን አብራርተዋል፡፡ከመከላከያ ጎን በመሆን የጥፋት ቡድኑን ጥቃት በመከላከልና መልሶ በማጥቃት የጥፋት ቡድኑ ውርደትና ሽንፈት እንዲከናነብ ላደረጉ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ፣ ለአፋር ልዩ ኃይል ፤ እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና የትግራይ ህዝብ ከመከላከያ ጎን በመሆን ላሳየው ድጋፍ ሥራ አስፈጻሚው ያለውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡የህወሓት ጁንታ በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ክህደት ተከትሎ የፌዴራል መንግሥት የወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃና ኢትዮጵያውያን ከጫፍ ጫፍ በመነቃነቅ ያሳዩት ድጋፍ በሉዓላዊነታቸው ላይ ለሚመጣ ማንኛውም ጉዳይ መቼም እንደማይደራደሩ ያስመሰከሩበት እንደሆነም አመልክተዋል ፡፡ህግ የማስከበር ዘመቻው እና ህዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ በመውጣት ያሳየው መነቃነቅ የሀገሪቷ ሉዓላዊነት እንዲጠበቅ፤ የአገር መከላከያ ሰራዊት አገር ከመፈራረስ እንዲድን፤ ኢትዮጵያዊነትም ጎልቶ እንዲወጣ ማድረግ ችሏል ያሉት አቶ ብናልፍ ፣ ይህ ህግ የማስከበር ዘመቻም ኢትዮጵያዊነት አሸንፎ የወጣበት ዘመቻ ነው ብለዋል፡፡እንደ አቶ ብናልፍ ማብራሪያ፤ የህግ ማስከበር ሥራውእየተጠናቀቀ ነው፡፡ የጥፋት ቡድኑን የሚያስተባብሩ በህግ የሚፈለጉ አካላትን ከጉድጓድ በማውጣት ለፍርድ እንዲቀርብ የፓርቲያቸው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ እና የተቋረጡ አገልግሎቶች እንዲጀምሩ፣ የወደሙ መሰረተ ልማቶች እንዲገነቡ የሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴው አቅጣጫ ማስቀመጡን አመልክተዋል፡፡በየአካባቢው የሚካሄዱ የልማት፣ የዴሞክራሲ እና የሰላም ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አቅጣጫ ማስቀመጡንም አቶ ብናልፍ ገልፀዋል።ሀገራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮችን በተመለከተም ብሄረ መንግስት እና ሀገረ መንግስት በመገንባት ሂደት ውስጥ ፅንፍ የወጡ አስተሳሰቦች እንደሚስተዋሉ የተመ ለከተው ሥራ አስፈፃሚው፤ ይህንን ለማስተካከል ህዝቡ ፖለቲካዊ ንቃት እንዲኖረው መሰራት እንዳለበት መገምገሙንም አስታውቀዋል።ከዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች አንፃር በተለይም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ አኳያ፣ ከአባይ ፖለቲካ ጋር በተያያዘ የህዳሴ ግድብ እንዳይጠናቀቅ እና የሚፈለገው ደረጃ ላይ እንዳይደርስ የሚከፈቱ ፕሮፖጋንዳዎች ላይ በዝርዝር ውይይት ተደርጎ ግልፅ አቅጣጫ መቀመጡንም ጠቁመዋል።ምርጫን በተመለከተም የ2013 ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድም ሆነ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ እንዲሆን አቅጣጫ መቀመጡን አመልክተዋል።የብልጽግና ፓርቲ የሚጠበቅበትን ሁሉ አሟልቶ በዚህ ሂደት ውስጥ ለማለፍ ዝግጅት ማድረጉንም አስታውቀዋል።የብልጽግና ፓርቲ ምርጫውን ለማሸነፍ ማኒፌስቶ አዘጋጅቶ ወደ ምርጫ ቅስቀሳ የሚገባ መሆኑንም በመግለጫው አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ሕዳር 28/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36858
ad74aedacfe773e682c0a08ea6a0d377
87ea4e3f9e090c416b7a7575077aac91
የወንጀለኛው ጁንታ የንግድ ድርጅቶች የአገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ መጉዳታቸው ተገለፀ
ተገኝ ብሩአዲስ አበባ፡- ወንጀለኛው የህወሓት ጁንታ የንግድ ድርጅቶች በህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ መጉዳታቸውን ምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ አዲሱ እጥፉ አስታወቁ። የሀገሪቱን ሀብት ከመበዝበር ወደ ውጭ ለማሸሽ መሳሪያ እንደነበሩም ጠቆሙ።አቶ አዲሱ እጥፉ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገ ለጹት፦ የህወሓት ጁንታው የንግድ ድርጅቶች በሀገ ሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያሳደሩት አሉታዊ ተፅዕኖ እጅግ የከበደ ነው።ተቋማቱ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በበላይነት በመቆጣጠርና በህገወጥ መንገድ በመዝረፍ የአገሪቱን ሀብት ወደውጭ ሲያሸሹ ነበር።የንግድ ተቋማት አሰራራቸው ብቻ ሳይሆን አጀማ መራቸውም ህገ ወጥ እንደነበሩ የገለፁት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው፣ ተቋማቱ ላለፉት በርካታ ዓመታት በማናለብኝነት ሀገሪቱን ሲመዘብሩ መቆየታቸውና የአገሪቱን ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን አስታውቀዋል።ጁንታው የፖለቲካ የበላይነት ለመያዝ የኢኮኖሚ የበላይነት ማረጋገጥ አለብኝ ብሎ የሚያምን ድርጅት መሆኑን የተናገሩት ባለሙያው፣ በህገወጥ ተቋማቱ አማካኝነት ይህንን እምነቱን ተጨባጭ ለማድረግ የሄደበት መንገድ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አመልክተዋል።ተቋማቱ በተጠና መልክ የተሳሰሩና በሰንሰለት መልክ የተደራጁ ሁሉም ለአንድ አላማ የተቋቋሙ እንደሆኑ የሚናገሩት ባለሙያው፣ አንዱ ተቋም የአንደኛው ግብዓት አቅራቢ በመሆን ለሌላው በመሸጥና ኢኮኖሚውን በተለያየ መልኩ በመቆጣጠር የበላይነቱን ተቆጣጥረውት ቆይተዋል ብለዋል።የህወሓት ጁንታ በነበረው የፖለቲካ የበላይነት ተጠቅሞ የአገሪቱ የወጪና የገቢ ንግድ ሆን ተብሎ ከእነዚህ ድርጅቶች ጋር የተያያዙ እንዲሆኑ ማድረጉን ያመለከቱት ባለሙያው፣ ተቋማቱ ያለገደብ የባንክ ብድ ርና የውጭ ምንዛሪ ያገኙ እንደነበር ገልፀው” ይህ ደግሞ ከሌላ ህጋዊ ድርጅቶች በተለየ መልኩ ኢኮኖሚውን እንዲቆጣጠሩ እድል እንዲሰጣቸው አስታውቀዋል ።የድርጅቱ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ በ2003 ዓ.ም ለአሜሪካ ድምፅ “የህወሓት ተቋም የሆነው ኤፈርት የአገሪቱ ቁጥር አንድ ሀብታም ድርጅት ነው” ማለታቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል።ተቋማቱ ከልማት ባንክና ከንግድ ባንኮች በብድር መልክ የወሰዷቸው ገንዘቦች እንደማይመልሱና የተበላሸ ብድር እየተባለ እንደሚመክን ያስረዱት አቶ አዲሱ፣ እነዚህ ተቋማት አትራፊ መሆናቸውና እጅግ ትልልቅ ገንዘቦች ማዘዋወራቸው እየታወቀ ተቋማቱ ኪሳራ ላይ ናቸው በሚል የተበደሩትን ገንዘብ ሳይመልሱ እንዲቀሩና የመንግሥት ገንዘብ እንዲመዘበር ሆን ተብሎ ሲሰራ መቆየቱን አስታውቀዋል።በህጉ መሰረት አንድ ተቋም መክሰሩ ታውቆ የተበ ደረው ብድር መመለስ እንደማይችል ሲረጋገጥ ብድሩ ተበላሸ እንደሚሰኝ ገልፀው ፣የህወሓት ጁንታው ተቋማት ግን አትራፊ መሆናቸው እየታወቀ የተበደሩትን ገንዘብ እንዳይመልሱ የተለያዩ ምክንያቶች ያቀርቡ እንደነበር ጠቁመዋል።ጤነኛ የንግድ ህግ ተከትለው ይሰሩ የነበሩ ተቋማት በቡድኑ ህገወጥ ድርጅቶች በደረሰባቸው ጫና ከገበያ እንደወጡና በአንፃሩ ደግሞ በቡድኑ የሚተዳደሩ ተቋ ማት በአገሪቱ ግዙፍ የገንዘብ ዝውውር የሚያደርጉና በህገወጥ መንገድ የከበሩ እንደነበሩ አስታውቀዋል። ተቋማቱ ከአገሪቱ በተለያየ መንገድ የዘረፉት ገንዘብ ወደውጭ በማሸሽ ሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲገጥማትና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዋ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዲፈጠር ምክንያት እንደነበሩ ገልጸዋል።ከአመሰራረታቸው ጀምሮ ህገወጥ በሆነ መልኩ የተቋቋሙት የህወሓት ጁንታው የንግድ ተቋማት በአገሪቱ ላይ የፈጠሩት ኢኮኖሚያዊ ጫና ከፍተኛ መሆኑንም ገልፀዋል። ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት የንግድ ሥራ ውስጥ መሳተፍ የለበትም ያሉት አቶ አዲሱ ተቋማቱ በ1952 ዓ.ም የወጣውን አገራዊ ህግ በሚፃረር መልኩ የተቋቋሙና በህገወጥ መልኩ ሲሰሩ የቆዩ ናቸው ብለዋል።በመንግሥት ቁጥራቸው 34 የሚሆኑ የንግድ ቋማት ተለይተው የተገለፁ መሆኑንና ጉዳያቸው በህግ ሂደት ላይ ቢሆንም የድርጅቱ የንግድ ተቋማት ግን ቁጥራቸው ከዚያ እጅግ እንደሚበልጥና በመንግሥት በኩል በትክክል ተለይተው ከህገወጥ ተግባራቸው ሊገቱ እንደሚገባም አመልክተዋል ።ተቋማቱ ለመንግሥት ግብር በስርዓት የማይከፍሉና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች መሬቶችን በመውሰድ እና መልሶ በመሸጥ ለህገወጥ ተግባራቸው መጠቀሚያ ያደርጉ እንደነበር ጠቁመዋል።ዓለምአቀፉ የፋይናንስ ሀቀኝነት ድርጅት በፈረ ንጆች በ2010 ይፋ ባደረገው ሪፖርት መሰረት የጁን ታው ድርጅቶች ከአገሪቱ ከ17 ቢሊዮብ ብር በላይ በማሸሽ በውጭ ሀገር በሚገኙ የተለያዩ ባንኮች ላይ አስቀምጠዋል። ይህ ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱንና እስካሁን ይፋ የተደረገ ሪፖርት ብቻ መሰረት በማድረግ ከአገሪቱ በተለያየ መንገድ የዘረፉት ከ36 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ በተለያዩ አገራት ባንኮች ላይ ማስቀመጣቸውን አስታውቀዋል።ተቋማቱ የአገሪቱ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችን በመሸጥና ወደውጭ በማሸሽ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ሲፈጽሙ መቆየታቸውንም የገለጹት አቶ አዲሱ፣ ተቋማቱ ገለልተኛ በሆነ መልኩ ተጣርተው አገሪቱ ላይ ያደረሱትን ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ በመመርመር ተጠያቂ ሊደረጉ እንደሚገባ አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36864
e0cf12fbb24a55db64f90a4d45c35c30
a2bd802a466bfda3bf1ee879cd3ab7dc
«ጁንታው ሕጋዊ የንግድ ውድድርን ማዛባት ብቻ ሳይሆን ተፎካካሪዎችን የማጥፋት አካሄድ ይከተል ነበር » – አቶ ውብሸት ሙላት የህግ ባለሙያ
ወርቁ ማሩአዲስ አበባ ፦ ወንጀለኛው የህውሓት ጁንታ ሁሉንም የቢዝነስ ተቋማት በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ ካለው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ ማንኛውም የንግድ ውድድር እንዳይኖር ከማድረግ በዘለለ ተፎካካሪ ሊሆኑ የሚችሉ የግልና የመንግስት የንግድ ተቋማትን እስከማጥፋት መሄዱን የሕግ ምሑሩ አቶ ውብሸት ሙላት አስታወቁ ።አቶ ውብሸት በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ ይህ ቡድን ወደ ስልጣን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው መስክ አግላይ ብቻ ሳይሆን ሌላውንና ከሱ ውጭ የሆነውን የሚያስወግድ እና አፋኝ ነበር ። በኢኮኖሚውም መስክ በኢትዮጵያ ትልቁ ኢንቨስተር ይህ ቡድን ነበር ፤ከፌደራል መንግሥት በላይ የኢኮኖሚ አቅም የፈጠረ ነው ።አንድ ቡድን በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው የበላይ ከሆነ እና በዚያ ላይ ያለው አስተሳሰብ አግላይ ከሆነ አገርን አደጋ ላይ ይጥላል የሚሉት አቶ ውብሸት፤ አገር ማፍረስን ጨምሮ የፈለገውን እንዲያደርግ እድል ይሰጠዋል፤ በወንጀለኛው ጁንታ የሆነው ይኸው ነው ብለዋል ። ትልቅ ገንዘብ ለማግኘት ሲታሰብ አንዱ አባላቸው ይነገረውና እንዲዘጋጅ ይደረጋል። ዝግጅቱን ሲጨርስ እሱን የሚያበረታታ ሕግ እንዲወጣ ይደረጋል የሚሉት አቶ ውብሸት ፣ለምሳሌ ከውጭ ያለቀረጥ ተሽከርካሪ ማስገባትና የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚሰራ ድርጅት ፈቃድ ለመስጠት አስበው እንደሆነ። ይህ ቀድሞ ባሰቡት መሰረት የነሱ ሰው እራሱን እንዲያዘጋጅ ይደረጋል ።ዝግጅቱን ከጨረሰ በኋላ የጊዜ ገደብ የተቀመጠለት መመሪያው እንዲወጣ ይደረጋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ያዘጋጁት ሰው ቀድሞ የሚፈለውን ነገር ከውጭ ያዛል በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ተጠቃሚ ያሆናል። ይህን መንገድ በተደጋጋሚ ሲሰሩበት የነበረ እንደሆነ ጠቁመዋል። በአንድ ወቅት የልማት ባንክ ገንዘብ ተበድረው ሲያልቅ ሁሉም ባንኮች ለልማት ባንክ 27 ከመቶ ብድር እንዲሰጥ እንደተደረገ አቶ ውብሸት ያስታውሳሉ። በዚህ ወቅት ልማት ባንክ ያበደራቸው በሙሉ የጁንታው ቡድን አባላት መሆናቸውንም ይናገራሉ። ቡድኑ በርካታ የጭካኔ መገለጫዎች አሉት ያሉት አቶ ውብሸት፤ ከነዚህም ውስጥ አንዱ በድርቅ ከተጎዱና በሞት አፋፍ ላይ ከነበሩ ሰዎች መንጋጋ ላይ ፈልቅቆ ምግብ እስከመውሰድ የደረሰ ወንጀሉ አንዱ ነው ብለዋል ። ይህም ቡድኑ ቅንጣት ታክል ሰብዓዊነት የሌለው ለመሆኑ ትልቁ መገለጫ እንደሆነም አመልክተዋል ። ለዚህም በ1977 ዓ.ም በተከሰተው ድርቅ ለሰብዓዊ እርዳታ የመጣውን ድጋፍ መዝረፉን ጠቁመዋል።ከዚህም አልፎ በሴፍቲኔትና በተለያዩ ምክንያቶች ለእርዳታ የሚሰጡትን ሁሉ ያለ ይሉኝታ እንደሚወስድም ተናግረዋል። እንደ አቶ ውብሸት ገለጻ፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ወደግል ሲዞሩም ከፍተኛ ደባ ተፈጽሟል። በደርግ ጊዜ የተወረሱ፣ ወይም ደርግ በራሱ የገነባቸውም ተመሳሳይ ሸፍጥ ነው የተፈጸመባቸው፤ ሰዎች ባዶኣቸውን ይመጡና ከዚያ ይህንን ለሚገዛ ሰው የባንክ ብድር ይመቻቻል፤ ከዚያ የጨረታ አሸናፊ ይሆናሉ። ከዚያ የሆነ ባንክ እዲከፍልላቸው ይደረጋል። ከሆነ አመት በኋላ የግላቸው ይሆናል። በዚህ መሰረት ከዜሮ የትልቅ ሆቴል እና ፋብሪካ ባለቤት፣ ከዜሮ ሚሊየነር የሆኑ በርካታ የጁንታው ቡድን አባላት አሉ ። የቀደሙ ፋብሪካዎችንም ዘርፈው በመውሰድ ለራሳቸው ድርጅት ማቋቋሚያ እስከማድረግ የዘለቁበትም ሂደት ነበር። ለአብነትም መስፍን ኢንጂነሪንግ የተመሰረተው ከፓዌ በተዘረፈ ሃብት ነው። ደርግ ፓዌ ላይ የገነባው ትልቅ ፋብሪካ ነበር። ይህ ቡድን ኢትዮጵያን መቆጣጠር ሲጀምር እንዳለ ነቃቅሎ ሁሉንም ወስዷል። ከዚያ በኋላ ደግሞ መስፍን ኢንጂነሪንግን ለማጠናከር እነማሩ ብረታ ብረት፣ አምቼ የመሳሰሉትንና አቅም የነበራቸውን ድርጅቶችን ማክሰሩን ጠቁመዋል ። በሌላም በኩል በከፍተኛ ሁኔታ የንግድ ሥርዓቱ ውስጥ ገብተው ውጤታማ የነበሩትን የስታር ቢዝነስ ግሩፕ እና ሌሎች በርካታ የመከኑ የንግድ ድርጅቶችን ማንሳት እንደሚቻል የጠቆሙት አቶ ውብሸት ፣ በፋይናንስ ሴክተሩ አቢሲኒያ ባንክን ጭምር በርካታ ተቋማት የነሱ አባላት አክሲዮን እንዲገዙ በማድረግ በነሱ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጋቸውን አመልክተዋል። በተቋሙ ውስጥ የነበሩ ሰዎችንም የተለያዩ ምክንያት እየፈለጉ ስምንት እና ዘጠኝ ጊዜ አስረዋቸዋል። አያት ሪል ስቴትንም ማንሳት ለዚህ ትክክለኛ ማሳያ እንደሆነም አስታውቀዋል ። አንዳንድ ድርጅቶቻቸው ሕገወጥ ስራ ላይም ተሰማርተው እንደነበር አቶ ውብሸት ጠቁመው፣ ለአብነትም ሱር ኮንስትራክሽን በአማራ ክልል ከሰራው መንገድ ይልቅ የሰራው ምሽግ ይበልጣል ብለዋል።  በቅማንትና በአማራ ክልል መካከል በተፈጠረው ግጭት በርካታ ድርጅቶች ነዳጅ የሚያመላልሱ መስለው መሳሪያ ሲያመላልሱ እንደቆዩና በየቦታው በነዚህ ድርጅቶች ውስጥ የተገኘው የጦር መሳሪያም የዚህ ማሳያ እንደሆነ ጠቁመዋል። የሽብር ድርጊትን ፋይናንስ የሚያደርጉት እነዚህ ድርጅቶች እንደነበሩ በርካታ ማሳያዎች እንዳሉ አስታውቀዋል። የወንጀለኛው ቡድን አባላት ህይወት እርሻ መካናይዜሽን በሚል ሁመራ አካባቢ እርሻም እንደነበራቸው የጠቆሙት አቶ ውብሸት፤ ይህንን ስንመለከት እነዚህ ሰዎች በእርሻ ስም አደንዛዥ እጽ ሲያለሙ እንደነበርም መገመት ይቻላል ብለዋል። በተለይ ሰሞኑን ወንጀለኛው ጁንታ ሲባረር የተያዘው በርካታ አደንዛዥ ዕፅ ከዚህ ሊሆን ስለሚችል ይህ በአግባቡ መፈተሽ እንዳለበትም አሳስበዋል። በአገራችን የተፈጠሩት በርካታ ግጭቶችን ስንመለከት የፋይናንስ አቅም ይፈልጋሉ ያሉት አቶ ውብሸት ፣ ይህ ገንዘብ ከየት ነው የሚገኘው ካልን ከነዚህ ድርጅቶች ለመሆኑ ግልፅ ነው ብለዋል ። የጁንታው ድርጅቶች በደምብ መታየት ፤ እስከዛሬ ለፈፀሙትም መጠየቅ አለባቸው ብለዋል ። አቶ ውብሸት እንደገለጹት፣ ከተወሰነ ዓመታት በፊት ፓናማ ፔፐርስ በሚል የወጣ አንድ ማስረጃ አንዳንድ የዚህ ቡድን ድርጅቶች በመሳሪያ ዝውውር ስራ ላይ መሰማራታቸውን መጠቆሙን ተናግረዋል። ይህ ደግሞ ቡድኑ ድርጅቶቹን ከሃገር አልፎ ጎረቤት ሃገራትን ለማበጣበጥ ሲጠቀምባቸው እንደነበረ የሚጠቁም እንደሆነ አስታውቀዋል። በአገራችንን የጦር ሕግጋት ያልወጣው ለዚህ ነበር የሚሉት አቶ ውብሸት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የጦር መሳርያ በገፍ ነበር የሚሸጠው፤ ይህንን ግን ማነው የሚሸጠው፤ እንዴት ነው ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የሚለው እስካሁን በቂ ምላሽ ያላገኘ ጥያቄ እንደሆነ ገልጸዋል ። ይህ ቡድን ከሃገሪቷ አልፎ ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋትም ካንሰር እንደነበር ያስታወቁት አቶ ውብሸት፤ይህንን በአግባቡ በማጥናት ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድንም ከዚህ ቡድን ማንፃት ያስፈልጋል ብለዋል ። አንድ ድርጅት ሕገወጥ ተግባር ውስጥ ተሰማርቶ ከተገኘ ይከሰሳል። እንደሁኔታውም ንብረቱ በመንግስት ሊወረስ ይችላል፤ ካልሆነም በገንዘብ ቅጣት ሊቀጣ ይችላል። እነዚህ ድርጅቶችም የፈፀሙት ወንጀል በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ሊወረሱ ይገባል።አመራሩን በመቀየርና ዓላማውን በማስተካከል ወደጤናማ የንግድ ስርዓት ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል። በቀጣይም ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይከሰቱ እያንዳንዱን ሥራ ሕግን መሰረት አድርጎ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል። ፋይናሽያል ኢንተለጀንስ፣ ሽብርን ፋይናንስ የማድረግ እንቅስቃሴ መኖር አለመኖሩን መከታተል፤ እነዚህ አይነት የንግድ ድርጅቶች ሕግን ተከትለው በውድድር መንፈስ እየሰሩ መሆን አለመሆናቸውን መከታተል፤ ይህንንም ሊቆጣጠሩና ሊከታተሉ የሚችሉ ጠንካራ አቅም ያላቸው ተቋማትን መገንባት፣ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠርም እግር በእግር እየተከታተሉ ወደ ሕግ ማምጣት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል ። ይህ ሲሆን አጠቃላይ ሀገራዊ ሥርዓቱን ጤናማ እንደሚሆን አስታውቀዋል ።አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36925
9599580e86b5611aefbf3aefd925435d
dcbaa0d20e115ad3890cf2d4a5c32fc7
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመመስረትና መልሶ የማደራጀት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ
ኢያሱ መሰለመቀሌ፡- በትግራይ ክልል ህግን የማስከበር ሶስተኛው ምእራፍ ከተጠናቀቀ በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደር የመመስረትና መልሶ የማደራጀት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገለጸ።የትግራይ ብሄራዊ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እንደገለጹት ፣ ህግን የማስከበር እርምጃውን በጥንቃቄ በማከናወን ወደ ቀጣዩ ምእራፍ መሸጋገር ተችሏል። ጊዜያዊ አስተዳደር የመመስረትና መልሶ የማደራጀት ሥራ መጀመሩን በመግለጽም በሽሬ ፣ እና በአክሱም የተለያዩ ቀበሌዎችንና ወረዳ አስተዳደሮችን መልሶ የማደራጀት ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል።ለጊዜያዊ አስተዳደሩ የተመረጡ ሥራ አስፈጻሚዎች ሥራ መጀመራቸውን ያስታወቁት ዶክተር ሙሉ ፣ በመቀሌ ከተማ ህዝቡ ወደ መደበኛው ሥራው እንዲመለስ፣ የመንግሥት ተቋማት ሥራቸውን እንዲያከናውኑና የንግድ ተቋማትም ሥራቸውን እንዲጀምሩ የማድረግ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።ወጣቶች ተደራጅተው ከመከላከያ ጎን እንዲቆሙ የልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲሰጡም እየተሰራ መሆኑን የገለጹ ትዶክተር ሙሉ፣የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች የመንግሥትን እገዛ ሲጠባበቁ እንደነበር ጠቁመዋል።በከተሞች አልፎ አልፎ የሚታየውን ዘረፋ ለማስቆም ከጸጥታ ኃይሉ ጋር እየተሰራ ነው ፤ በጸጥታ ስጋት ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ሸሽተው የሄዱ ሰዎችን ወደ ነበሩበት የመመለስ እና የማረጋጋት ሥራ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳዩ እንደሆነ ገልጸዋል።መከላከያ ሰራዊት መቀሌንና ሌሎች ከተሞችን የተቆጣጠረ በመሆኑ ህብረተሰቡ ያለምንም ስጋት ወደሚኖርበት አካባቢ በመምጣት ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን አመልክተዋል።የህግ ማስከበሩ ሥራ ለትግራይ ህዝብ ከፍተኛ ጥቅም ይዞ የሚመጣ እንደሆነ የገለጹት ዶክተር ሙሉ ፣ህዝቡ ከነበረበት ጫና ወጥቶ በነጻነት እንዲንቀሳቀስ ያስችለዋል ብለዋል።የክልሉን የካቢኔ አባላት የማዋቀር ሥራ እንደሚሰራና እንደ ባንክ ፣ቴሎኮም፣ መብራት የመሳሰሉት አገልግሎት ሰጪ ቋማትን ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመተባበር የማስጀመሩ ሥራ ትኩረት ተሰጥጦታል ብለዋል።የሥራ እንቅስቃሴ ከመቋረጡ ጋር ተያይዞ የምግብ እጥረት ሊፈጠር ስለሚችል እርዳታዎችን የማስተባበር ሥራዎች እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013  ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36880
a7b9f6d8e527478e1a5541c49408a22b
64972bbb6a333db06518402c6ce4f4f3
ባለ ከዘራው ኮሎኔል
ጌትነት ተስፋማርያምፊታቸው ላይ የአልበገርም ባይነት ስሜት ጎልቶ ይነበባል፤ እያነከሱም ቢሆን ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳሉ። መገናኛ ራዲዮናቸውን እና የምርኩዝ ከዘራቸውን ይዘው የጁንታው ቡድን አመራር ያለበት ቆላ ተንቤን አቅራቢያ በምትገኝ ሰዋራማ ስፍራ ላይ ጦሩን እየመሩ ይገኛል።ኮሎኔል ሻምበል በየነ ይባላሉ። በቆሙበት የውጊያ ትዕዛዝ እየሰጡ ኮስታራ ፊታቸውን ወደእኛ ዘወር አደረጉ። ቆስለው አልታከምም በማለት በወኔ እየመሩ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አመራር መሆናቸውን ሰማንና ታሪካቸውን እንዲያካፍሉን ጠየቅናቸው።ድንገተኛ ፈገግታ እያሳዩ ቀድሞም የጁንታው አባላት ውጊያ ሰራዊቱ ላይ ሊከፍቱ እንደሆነ ጥርጣሬ ነበረኝ በማለት በተረጋጋ ስሜት ትውስታቸውን ማጋራት ጀመሩ። እኔ የ31ኛ ክፍለጦር ምክትል የኦፕሬሽን አዛዥ ነበርኩ ዋና አዛዡ ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ቀደም ብሎ የተወሰኑ አባላትን ሽሬ ድረስ ወስዶ ሲሰበስብ የሆነ ነገር ሊፈጥር እንደሚችል አስበው እንደነበር።ማታውኑ ችግር ሊኖር እንደሚችል በማመን በግሌ ዝግጅት አደረግኩ። ስዘጋጅ በባንክ አካውንቴ የነበረውን ጥቂት ገንዘብ በቤተሰብ አዞርኩ። ከዚያም ጥቃት ለማድረስ ከበባ ሲፈጽሙብኝ ተከብቤያለሁ በሚል ለበላይ አካላት ሪፖርት አደረኩ ።በመከላከያ ላይ ጥቃት ሲፈጸምም የክፍለጦሩ አዛዡ ከድቶ የጁንታውን ቡድን ተቀላቀለ። በዚህ ጊዜ የክፍለጦር ኮሚቴ ወይም ከበታች አዛዦች አባላት ጋር በመሆን ግብግብ ፈጸምን። እኔም ከፊቴ ያለውን በጥይት መትቼ ጣልኩ። እኔ ጋር የተጀመረች የመከላከል ተኩስ እስከታችኛው የሻለቃ አመራር ድረስ እየተደማመጠ የመከላከል እርምጃውን ወሰደ።በኋላም የካምፑን ከበባ አጠናቅቄ ስወጣ ደግሞ የልዩ ኃይል ከውጭ ጠበቀኝ የሚሉት ኮሎኔል፤ እነሱንም ጥሼ በመውጣት ከስምንተኛ ሜካናይዝድ ጦር ጋር ተቀላቀልኩ ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ያስታውሱታል።በወቅቱ እግራቸው ላይ በጥይት መመታታቸው እምብዛም ቁብ አልሰጡትም። በዚያ ሁኔታ ላይ እያሉ ወደኤርትራ በማፈግፈግ በዚያ ከሚገኘው እና በጁንታው ታጣቂ ጥቃት ደርሶበት ከሚገኘው ጦራቸው ጋር ተገናኙ። ጦሩን አደራጅተው በመመለስ ሽራሮ ፣ሽሬ፣ አዲ አደራይ፣ አዲነብሪ እና በርካታ ቦታዎች በማስለቀቅ የህግ ማስከበር እርምጃቸውን በብቃት መወጣትም ቻሉ።ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ከታፋቸው የሚፈስ ደም እንደ ነበር በቅርበት የሚያውቋቸው ወታደሮች ይናገራሉ። ቁስሉን በየሶስት ቀኑ በጦር ሜዳ አካባቢ እየታከምኩ አንዷ ጥይት ወጣች የሚሉት ኮሎኔል ሻምበል፤ ምርኩዝ ይዘው ግዳጃቸውን መወጣታቸውን ነግረውናል። ዋና አዛዡ ግን የጁንታውን ቡድን በመቀላቀል ለጁንታው አመራር ሽፋን ለመስጠት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።አሁን ላይ ቆላ ተንቤን ላይ ወንጀለኛ ለማስመለጥ እና ወንጀለኛ ለመያዝ ዋናው እና ምክትል አዛዡ ፊት ለፊት ተፋጠዋል። ምክትል አዛዥ ዋናውን ከነጀሌዎቹ እያባረረ እርምጃ እየወሰደበት ይገኛል። ከሚመሩት ጦር ጋር በርካታ ሀገር የከዱ ጄኔራሎችን እያባረሩ ቆላ ተምቤን ላይ ያደረሱት ኮሎኔል ሻምበል፤ እዚህ በመድረሴ ትልቅ ደስታ ይሰማኛል ሲሉ በኩራት ይናገራሉ።ቆላ ተምቤን ላይ የመሸገውን የከሃዲው ቡድን አመራር አባላት ለህግ ሲቀርቡ በተሻለ ህክምና በጥይት የተመታውን እግራቸውን ሊታከሙት እንደሚችሉ እንደተወርዋሪ ኮኮብ መሳይ ብልጭታ ባለው ፈገግታቸው ታጅበው በለሆሳስ ነገረውናል። ቦታው ላይ ቆስለውም ቢሆን ጦሩን እየመሩ መገኘታቸው ለሰራዊቱም ብርታት መሆኑን አልሸሸጉንም።በእጃቸው ከዘራቸውን ጨብጠው የሚንቀሳቀሱት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፤ በጉዳት እያሉም ቢሆን በህግ ማስከበር እርምጃ የጁንታውን አመራሮችን ለመያዝ ፀሐይ ውርጭ ሳይሉ በመታገል ላይ ናቸው። ይህም ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችን በየጊዜው አታጣም የሚባለው ብሂል እውነት መሆኑን ያረጋገጠ ነው። አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013  ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36881
efc7f5fc6f05ad3b71e0dcc809b8b87a
70a5fbff9786f76b2c0b9ffb32a2b3cc
ወደ ሕዝብ ባለመተኮስ የተገለጸ ቃል ኪዳንና ጽናት!
ኢያሱ መሰለ ሻለቃ ዘላለም ብዙነህ በሰሜን አየር ምድብ የአየር መከላከል እቅድና ስልጠና ቡድን መሪ ነው።ዋናው የስራ ድርሻው ጠላት የአየር ጥቃት እንዳያደርስ መከላከል እና የምድር ኃይሉ እንዳይጎዳ ድጋፍ መስጠት ነው።ሰሜን አየር ምድብ ከመጣም ከ17 ዓመት በላይ ሆኖታል።ሻለቃ ቡዙነህ እንደሚያስረዳው ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ ከ2010 ዓ.ም በኋላ ለውጡ ያልጣማቸው ኃይሎች አዳዲስ ባህሪ አምጥተዋል።ከፌደራል መንግስት የሚተላለፉ መመሪያዎችን ያለመቀበልና ሰራዊቱን ከፋፍሎ የመመልከት ሁኔታዎችም ይስተዋሉ ነበር። የእነሱን ሀሳብ የማይቀበለውን የአየር ኃይል አባል የብልጽግና ፓርቲ  ደጋፊ ነው በማለት ያጥላላሉ።በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉም ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ ምንም ባላሰቡት ሁኔታ መቀሌ በሚገኘው የሰሜን አየር ምድብ መኖሪያ ቤት የተኩስ ሩምታ ተከፈተ፤ ምንድ ነው ብለው ሲጠይቁም የሴራው ተባባሪ የሆኑና ጉዳዩን የሚያውቁ አባላት ልምምድ ነው እያሉ ያዘናጓቸው እንደነበር ያስታውሳል።‹‹ሌሊቱን ሙሉ ሳንተኛ አድረን ልክ አስራ ሁለት ሰዓት ሲደርስ ልዩ ኃይሎች ወደ ግቢው መግባት ጀመሩ።በተለይም የአማራና የኦሮሞ ተወላጅ አባላትን ከቤታችን እያወጡ እያመናጨቁና እየገረፉ ወሰዱን።ወደ ማጎሪያ ቤት ከወሰዱን በኋላ በብሔር ከፋፈሉን።ደቡብን ለብቻ ፤ አማራና ኦሮሞን በአንድ ላይ አድርገው አጎሩን።ሚሳኤል የመተኮስ ልምድና እውቀቱ እንዳለኝ  ስለሚያውቁ እኔን ለብቻዬ ወሰዱኝና እንድተኩስላቸውና ከእነርሱ ወገን እንድቆም ጠየቁኝ።እኔ ከምንም በላይ ቃል የገባሁት የሀገሬን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ሕዝቤን ለመጠበቅ ነው፤ ከሀገር በላይ ክብር የለም ፤ ስለዚህ መልሼ ሀገሬን አልወጋም አልኳቸውና 20 ዓመት የታገልኩበትን የትግል ዓላማ በአንድ ቀን እንደማላፈርሰው ነገርኳቸው።ሙያዊ እገዛ አድርግልን ፤ ተኩስልን፤ አሉኝ።እምቢ ስላቸውም በዚህና በዚያ መሳሪያ ደቅነውብኝ አስፈራሩኝ፤ ሰደቡኝም።ከፈለጋችሁ ግደሉኝ አልኳቸው።ከመሃላቸው አንዱ በጥፊ መታኝና ውጣ አለኝ።ከወጣሁ በኋላ ለሚሊሺያዎች አስረከቡኝ።ሚሊሺያዎቹ እግሬን በዱላ ሰባብረው ጣሉኝ፡፡እረ ባካችሁ ተውኝ እያልኩ ብማጸናቸውም ትንሽ እንኳን ሊራሩልኝ አልፈለጉም።ቀጥቅጠው ጥለውኝ ሲሔዱ በዳዴ እየተሳብኩ ቤቴ ገባሁ።ቤት ከገባሁ በኋላም እንደገና መጥተው እንድተኩስላቸው ጠየቁኝ እግሬ መጎዳቱን አሳየኋቸውና እንደማልችል፤ ቃል ኪዳኔንም እንደማላፈርስ ደግሜ ነገርኳቸው።ኮሌኔል በላይ የሚባል ሰው ፈቃደኛ ከሆንኩና ከተኮስኩ እንደሚያሳክመኝ ነገረኝ።እኔ ግን ከፈለግህ ግደለኝ አልኩት።ሚሳኤል ማስወንጨፊያው ሶስት ቦታ ላይ ማለትም መሶቦ፣ አዲግራትና አክሱም ነው ያለው።የሚሳኤሉ ዋና ታርጌት ተዋጊ አውሮፕላኖችን መጣል ነው፤ እስከ 25 ኪሎሜትር ይጓዛል።ወደ ባህር ዳር ይተኩሱት የነበረው ግን ሚሳኤል ሳይሆን ሮኬት ነው።ሮኬቱን ተሽከርካሪ ላይ አጥምደው ቦታ እየቀያየሩ ነበር የሚተኩሱት።ለምሳሌ መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ አካባቢም እየመጡ ይተኩሱ ነበር።አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ወደ ሌላ ቦታ ወስደው ሲተኩሱት ይሰማል።ጦርነቱ እየተባባሰ ሲመጣ ወደ ግንባር ሄዱ።ከዚያም መከላከያ ሰራዊት ከተማውን ሲቆጣጠረው መረጋጋት ጀመርኩ።ምንም አይነት ህክምና ሳላገኝ ማታ ማታ እየታሸሁ አሁን ትንሽ ተሽሎኛል።አድራጎታቸው በጣም ያማል ፤እስከአሁንም አዕምሮዬ ትክክል አይደለም።እህል በማጨድ፣ አንበጣ በማባረር ፣ ኮሮናን በመከላከልና በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ድጋፍ ሲያደርግ የነበረን ሰራዊት ክብሩ ተገፎ ውርደት ደርሶበታል።በተፈጸመብን የጭካኔ ተግባር ምክንያት እስከ አሁን ራሴን እያመመኝ ነው ፤ ጤነኛ አይደለሁም።መከላከያ ሰራዊት ለሀገሩ የገባው ቃል ኪዳን አለ።ሕዝብና መንግስት የሰጠውን ኃላፊነት የመፈጸም አደራ አለበት።ትግል ውስጥ ስገባ ልንሞትም ነው።እኛ እንደሻማ ቀልጠን ሌሎች ብርሃን እንዲወጣላቸው ቃል ገብተናል።በዚህ ቃል ኪዳናችን እንጸናለን፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 29/2012 ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36926
1b65bec753dc94af4d099de8adca7ff5
b5036da2c8f6d454bcc519588e773b20
የሳምንቱ እግር ኳስ ወሬዎች
 ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ በርካታ መረጃዎች ወጥተዋል። በተለይ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመት ፋሲል ከተማን በመያዝ ስኬታማ ጊዜያትን ያሳለፈው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በይፋ ሰበታ ከነማን ለማሰልጠን የመስማማቱ ዜና ጆሮ ገብ ሆኖ በርካታ የስፖርት ቤተሰብን ሲያነጋግር መቆየቱ ይታወሳል። ዛሬ የአሰልጣኝ የዝውውር ዘገባን ጨምሮ ትኩረት የሳቡ የስፖርት ዘገባዎችን የምናስነብብ ሲሆን ዘገባዎቹን ለማዘጋጀት የተለያዩ ዋቢዎችንና በዋናነት የሶከር ኢትዮጵያ ድረ ገፅ ተጠቅመናል። ባህር ዳር ከተማ በኢትዮጵያ እግር ኳስ የዝውውር መስኮት ላይ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘው ባህር ዳር ከተማ ሰለሞን ወዴሳን ስድስተኛ ፈራሚ ማድረጉ ተሰምቷል። ከሀዋሳ ከተማ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በወጣት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጊዜ ተጠርቶ መጫወት የቻለው እና በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በመድን የአማካይ ተከላካይ ሥፍራ ጥሩ ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረው ሰለሞን ወዴሳ የጣና ሞገዶቹን በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅሏል። ከተከላካይ አማካይነት በተጨማሪ በተከላካይ ስፍራ የሚጫወተው ይህ ተጫዋች ከሃያ ቀናት በፊት በወላይታ ድቻ ለመጫወት የተስማማ ቢሆንም ዝውውሩን ሳያጠናቅቅ በመቅረት ወደ ባህር ዳር ማምራቱ ታውቋል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ሰበታ ከተማ ውበቱ አባተን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታውቋል። የውድድር ዓመቱን በፋሲል ከነማ ያሳለፉትና ከቡድኑ ጋርም የኢትዮጵያ ዋንጫን ያነሱት አሰልጣኝ ውበቱ ከፋሲል ጋር ከተለያዩ በኋላ ከበርካታ ክለቦች ጋር ስማቸው ሲያያዝ ቢቆይም ወደ ሰበታ ለማምራት መስማማታቸው የሚታወስ ነው። በዚህም መሠረት ነሐሴ 25 በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰበታ ከተማ አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸው በይፋ ተነግሯል። ዓለምገና በሚገኘው ዓለም ሆቴል ከጠዋቱ 3:00 የቡድኑ አመራሮች በተገኙበት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከሰበታ ከተማ ጋር ስለሚኖራቸው ቆይታ እና ስምምነት ዝርዝር እንዲሁም ቀጣይ እቅድ ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል። የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ላለፉት ሳምንታት በኤርትራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ውድድር ሲጠናቀቅ ዩጋንዳ የዋንጫ አሸናፊ ሆናለች። ሩዋንዳ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃ ይዛለች። ከትናንት በስቲያ 7 ሰዓት 30 የተካሄደው የብሩንዲ እና ሩዋንዳ የደረጃ ጨዋታ ሲሆን መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ ለአንድ ተጠናቆ ወደ መለያ ምት በማምራት ሩዋንዳ 4ለ2 በማሸነፍ ሦስተኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች። ቀጥሎ የተካሄደውና 10 ሰዓት የተጀመረው የፍፃሜው ጨዋታ በዩጋንዳ እና ኬንያ መካከል ተከናውኖ ዩጋንዳ ከፍፁም ብልጫ ጋር 4ለ0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች። የዩጋንዳ ጎሎች የተቆጠሩት በኦግዋ ዴቪስ፣ ትራቪስ ሙታይባ እና ኬዩኔ አባስ ነው። የኤርትራው ተመስገን ተስፋይ ግምት አግኝቶ ከነበረው የዩጋንዳው ትራቪስ ሙታይባ በመብለጥ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተሸልሟል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በፕሪሚየር ሊጉ ለሚጫወት ማንኛውም ተጫዋች ከነሐሴ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የደመወዙ ጣሪያ ታክስን ጨምሮ ብር ሃምሳ ሺ ብር እንዲሆን 15 የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቢሾፍቱ ላይ መወሰናቸው ይታወቃል። ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን እንዲያስፈጽም ክለቦች በወሰኑት መሠረት ፌዴሬሽኑ በቁጥር 2/ኢ.እ.ፌ አ-4/1069 ነሐሴ 08/12/2011 ዓ.ም በጻፈው የሰርኩላር ደብዳቤ ክለቦች በዚህ ውሳኔ መሠረት የተጫዋቾችን ውል እንዲፈጽሙ መግለጹ ይታወቃል። ሆኖም ግን የተወሰነውን ውሳኔ በአግባቡ ከመፈፀም ይልቅ የተወሰኑ ክለቦች በተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ውል እየተዋዋሉ እና እያፀደቁ በተቃራኒው ግብር የማይከፈልበት ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ ለተጫዋቾች ክፍያ እየፈጸሙ እንደሆነ ከተለያዩ ጠቋሚ የመረጃ ምንጮች ጥቆማዎች ደርሰውናል። በመሆኑም ፌዴሬሽኑ ይህንን ሕገ ወጥ ድርጊት ከተጫዋቾች ጋር በመመሳጠር በታክስ ስወራና ሕገ ወጥ በሆነ ተግባር ላይ የተሰማራችሁ ካላችሁ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን፤ መንግሥት በራሱ የሚወስደው እርምጃ እንደተጠበቀ ሆኖ ፌዴሬሽኑም በዚህ ሕገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርቶ በተገኘ ክለብ፤ የክለብ አመራርና ተጫዋቾች ላይ ከስፖርቱ ዓለም እስከማገድ የሚደርስ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ለክለቦች በላከው ደብዳቤ አሳውቋል። (መረጃው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ነው )አዲስ ዘመን ነሐሴ 26/ 2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=17119
46ff1fa973a29a5a2e50f527079cd6d7
75207efb00aeedaa377a37d80443880e
‹‹ሰዎችን በጅምላ መግደል ሃይማኖታዊ ተጠያቂነቱ ከፍ ያለ ነው›› ሸህ ሱልጣን ሃጂ አማን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
እስማኤል አረቦአዲስ አበባ፦ ሰዎችን በብሄራቸው ወይም በሃይማኖታቸው ምክንያት በጅምላ መግደል የኢትዮጵያውያን ወግና ባህል ካለመሆኑም በላይ ከፍ ያለ ሃይማኖታዊ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሸህ ሱልጣን አማን አስታወቁ።ሸህ ሱልጣን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ሰላም በእስልምና ከፍተኛ ቦታ አለው። የሃይማኖት ሰዎች ሲገናኙ ‹‹አሰላም አለይኩም›› ወይም ሰላም ለአንተ ይሁን የሚል ሰላምታ ተለዋውጠው ነው ወደቀሪ ጉዳያቸው የሚገቡት። ይህ ከሰላም በፊት የሚቀድም ጉዳይ እንደሌለ የሚያመላክት ከመሆኑም ባሻገር ሰላም ከሌለ ሀገር የለም፤ ልማት የለም፤ በአግባቡ አምልኮንም ማከናወን አይቻልም የሚልም መልዕክት አለው።“ነፍስን ማጥፋት በእስልምና በጣም የተወገዘ ነው። አንድን ነፍስ ማጥፋት ዓለምን እንደማጥፋት ነው። እንኳን የሰው ነፍስን ቀርቶ ያለ አግባብ የነፍሳትን ነፍስ ማጥፋት በእስልምና በጣም የተወገዘ ነው። ይሁን እንጂ አሁን በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ ሰዎችን በጅምላ የመግደል ተግባሮች እንደሃይማኖት አባት በጣም የሚወገዝ ነው” ብለዋል።‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን ተባብረን፤ ተቃቅፈን ፤ ተዋደን ብሄርና ሃይማኖት ሳይለየን በሰላም ስንኖር የቆየን ህዝቦች ነን። አሁን ግን በተለያዩ ቦታዎች ዘግናኝ የሆኑ ግድያዎችና ጭፍጨፋዎችን እያየን ነው ያሉት ሸህ ሱልጣን ሃጂ አማን፣ ይህ ከኢትዮጵያውያን አማኝነትና ባህልና እሴት አንጻር በጣም የሚያሳፍርና እኛን የማይገልጽ እንደሆነ አመልክተዋል። ፖለቲከኞች ሃይማኖትንና ብሄርን ሽፋን አድርገው በሳለም ለዘመናት የኖረውን ህዝብ ሲያባሉትና ሲያጫርሱት እየተመለከትን ነው›› ያሉት ፕሬዝደንቱ ፣ በየቦታው የሚታዩ ግጭቶችና ግድያዎች መንስኤያቸው ከሃይማኖትና ብሄር ይልቅ ፖለቲካ መሆኑን ጠቁመዋል። ሸህ ሱልጣን እንደሚሉት ፖለቲከኞች የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈጸም ሲሉ አንድን ብሄር ከሌላው ጋር ወይም ሃይማኖትን ከሃይማኖት ጋር እያጋጩ የሚፈጽሙት ድርጊት እንጂ ኢትዮጵያውያን እንደዚህ አይነት ታሪክም ሆነ ስነልቦና የላቸውም። “ኢትዮጵያን መዋደድ ፤ መፋቀር ፤ መከባበርና መተሳሰብ እንጂ የእልቂትና የጭፍጨፋ ስነልቦና የላቸውም። ይህ በሁሉም ሃይማኖት የተወገዘና በወዲያኛውም ዓለም የሚያስጠይቅ ነው። አሁን በማይካድራም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች እየሰማነው ያለው ዘርን መሰረት ያደደረገ ጥቃትና ጭፍጨፋ እንደሃይማኖትም ፤ አንደ ኢትዮጵያን ወግና ልማድ በጣም የሚያሳፍርና አንገት የሚያስደፋ ነው። ይህ ጸያፍ ድርጊት ሃይማኖት አለኝ የሚል የሰው ፍጡር የሚፈጽመው አይደለም” ብለዋል ። ብሄርን ወይም ሃይማኖትን መሰረት አድርገው የሚፈጸሙ ጅምላ ግድያዎች አረመኔያዊና ጸያፍ ድርጊት በመሆኑ ሊወገዝ የሚገባው ነው ያሉት ሸህ ሱልጣን፣ ሰው ካጠፋ በበህላዊ ሽምግልና ወይም ሀገሪቱ በምትመራበት ህግ መዳኘት እንጂ ዘርን መሰረት አድርጎ በሚወሰዱ የጅምላ ግድያዎች ፍትህን አረጋግጣለሁ ወይም አንድን አካል እጎዳለሁ ብሎ መነሳት ከጤናማ አእምሮ የሚመነጭ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ይህን ድርጊት የሚፈጽሙ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች  ኢትዮጵያውያን ናቸው ብሎ ለመናገርም አያስደፍርም ያሉት ሸህ ሱልጣን፣ ይህ ኢትዮጵያውያንን የሚገልጽ አለመሆኑን፤ ሰዎችን በጅምላ መግደል የሚያስከትለው ሃይማኖታዊ ተጠያቂነት ከፍ ያለ መሆኑንም ጠቁመዋል። ‹‹እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ኢትዮጵያን ተዘዋውሬ አይቻታለሁ። ከሶማሌ እስከ አፋር፤ ደቡብ ፤አማራን፤ ኦሮሞን ፤ጋምቤላና ቤኒሻንጉልን ሁሉንም ተዘዋውሬ ተመልክቻለሁ። በዞርኩባቸው አካባቢዎች በሙሉ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንግዳ ተቀባይ፤ አዛኝና ተከባብሮ የሚኖር ነው” ብለዋል። አሁን፤ አሁን ፖለቲከኞች በሚፈጥሩት ውዥንብር ሰዎች በሃይማኖትና በብሄር በመከፋፈል አንዱ አንዱን ውጣልኝ ሲል ይሰማል። አልፎም ግድያ ሲፈጸም እናያለን። ስለዚህም ፖለቲከኞች የሚፈጽሙት ተግባር ከኢትዮጵያውያን ወግና ባህል ውጭ በመሆኑ ህዝቡ ተባብሮ በቃችሁ ሊላቸው እንደሚገባም አመልክተዋል። ስር እየሰደደ የመጣውን ዘረኝነትና በእሱም የተነሳ እየተስፋፋ ያለውን ግጭት፤ መፈናቀልና ግድያ ለዘለቄታው ለማስወገድ የሃይማኖት አባቶች ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸውና የሃይማኖት አባቶች ተከታዮቻቸውን ከሃይማኖታዊ ትምህርት ጎን ለጎን የኢትዮጵያውያንን የቆየ የመተሳሰብ፤ የመተጋገዝና የአብሮነት እሴቶችን በማስተማር ህዝቡ እሴቶቹን ጠብቆ እንዲጓዝ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አስታውቀዋል። በተለይ ለወጣቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት ወጣቱ ሃይማኖቱን እንዲከተል፤ ወግና ባህሉን እንዲያከብርና ሀገሩን እንዲወድ ማድረግ ከሃይማኖት አባቶች የሚጠበቁ ተግባራት ናቸው። ብሄርተኝነት ወደ ጥፋት እንጂ ወደ ሰላም እንዳልወሰደ፤ ወደ ድህነት እንጂ ወደ ልማት እንዳላሻገረ፤ እርስ በእርስ ወደ መተላለቅ እንጂ ወደ ትብብርና አንድነት እንዳላመጣና፤ እንደማያመጣም የሃይማኖት አባቶች በስፋት ማስተማር እንዳለባቸው አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36736
f80256f3211853fc53402904f0666e4e
4c1a47f74e3ffbc3801ee865164143ae
ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅት ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ከተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅት ኃላፊዎች ጋር የበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል። ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው፣ በውይይቱ ላይ ሬና ገላኒ፣ በተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት የሰብዓዊ ድጋፍ ዳይሬክተር፣ ዶክተር ካትሪን ሶዚ፣ በተባበሩት መንግስታት አስተባባሪና የሰብዓዊ ድጋፍ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተካፍለዋል። ሚኒስትሯ በሰሜናዊ የኢትዮጵያ ክፍል በተካሄደው የህግ ማስከበር ሂደት እንዲሁም ከወታደራዊ ህግ የማስከበር ሂደት ቀድሞ ሰላምን በሰለጠነ መልኩ በውይይት ለማምጣት ስለተሄደው ረጅም ርቀት ሰፊ ገለጻ አድርገዋል። በሰላም ማስከበር ሂደቱም ንጹሃን እንዳይጎዱና መሰረተ ልማት እንዳይፈርስ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ የተሞላበት ዘመቻ እንደተካሄደ አስረድተዋል። ሬና ገላኒ በበኩላቸው ስለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው በኢትዮጵያ መንግስት ንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ የተደረገውን ጥረት አድንቀዋል። በመጨረሻም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሁልጊዜውም ሰብዓዊና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን ከመንግስት ጋር በገባው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36744
a8f015a0cba47c436da0fd1be665cb29
96dbec9a5f9b43778316d366efabed7c
የህግ ማስከበሩን ተግባር ዓላማ ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ለማስረዳት የተከናወነው የዲፕሎማሲ ስራ ውጤታማ እንደነበር ተገለጸ
በጋዜጣው ሪፖርተር አዲስ አበባ፦ ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል የነበረውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ዓላማ ለዓለም ለማሳወቅ የሰራችው ዲፕሎማሲ ስኬታማ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑንም ገለጸ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በትግራይ ክልል የነበረውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ዓላማ ለዓለም ለማሳወቅ የተሰራውን የዲፕሎማሲ ስራ አስመልክቶ ትናንት በሰጡት መግለጫ ፣ የፌዴራል መንግስት ሲያከናውን የነበረውን ህግ የማስከበር ተግባር ዓላማ ለዓለም መሪዎች ለማስረዳት የተሰሩ የዲፕሎማሲ ስራዎች ስኬታማ እንደነበሩ አስታውቀዋል። በአፍሪካና አውሮፓ በአካል፣ በበይነ መረብ፣ በስልክና ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የህግ ማስከበሩን ዘመቻ አላማ ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ የማስረዳት ስራ መከናወኑን ያመለከቱት ቃል አቀባዩ፣ በተለይም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በጎረቤትና በአውሮፓ አገሮች ባደረጉት ጉብኝት ውጤታማ ነበር ብለዋል። በዲፕሎማሲ ስራው ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ የመጡ ለውጦችን ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ማስረዳት መቻሉን ጠቁመው ፣ የህወሓት ጁንታው አመራሮች ለውጡን መጻረራቸውንና ወደ ለውጡ እንዲመለስ የፌዴራል መንግስት የሰጣቸውን ሰፊ እድል ማሳየት መቻሉን ገልጸዋል። የጁንታው አባላት የተሠጣቸውን እድል ከመጠቀም ይልቅ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በገንዘብና በአደረጃጀት የሽብር ስራዎችን ሲደግፉ እንደነበር ማስረዳት መቻሉን ጠቁመው ፣ ህገ ወጥ ቡድኑ በሰሜን እዝ ላይ በፈጸመው ጥቃት ህግ ለማስከበር የተወሰደው እርምጃ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን በማስረዳት ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ መከናወኑን አብራርተዋል። ህግ የማስከበር ተግባሩ ንጹሃን ዜጎችን ሳይጎዳ መጠናቀቁን ከሩሲያ፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌይና ሌሎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በስልክ ውይይቶች መደረጋቸውን አንስተዋል። በውይይቱም ድርድር ማድረግን በተመለከተ ህጋዊ ከሆነው ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር እየተደረገ መሆኑንና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የማስረዳት ስራ መከናወኑን ገልጸዋል። ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከአገሪቱ መንግስት ጋር እየተሰራ መሆኑንም ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36749
afc797e9271f7470f6070087d8451c45
2ac01a4dd6767242f3eb4c1898a2f9ee
ለተመራቂ ሥራ ፈላጊዎች የበይነ መረብ የሥራ ዓውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው
ዋለልኝ አየለ አዲስ አበባ፦ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ለሚመረቁ ሥራ ፈላጊዎች የበይነ መረብ የሥራ ዓውደ ርዕይ እንደሚካሄድ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን አስታወቀ። ዓውደ ርዕዩ አካላዊ ቅርርብን በማስቀረት ኮቪድ-19 ወረርሽኝን የሚከላከልና ሥራ ፈላጊዎችን ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር የሚያገናኝ እንደሆነም ገልጿል። በሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን የኮምኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት አማካሪ ወይዘሮ ተወዳጅ እሸቱ በተለይም ለአዲስ ዘመን ትናንት እንደገለጹት፤ የንግድ ሥራ ክፍል የሆነው ደረጃ ዶት ኮም ከኢፌዴሪ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም የበይነ መረብ የሥራ ዓውደ ርዕይ ይካሄዳል። በዓውደ ርዕዩም የጅማ፣ የባህርዳር፣ የአዲስ አበባ እና ሌሎች አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች ይሳተፋሉ። እንዲህ አይነት የሥራ ዕድል ዓውደ ርዕይ በሌላው ዓለም ብዙ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚረዳ ያመለከቱት አማካሪዋ ፣ በኢትዮጵያም የተሻለ የስራ አድል ለመፍጠር ያስችላል በሚል ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን አስታውቀዋል። በደረጃ ዶት ኮም አነሳሽነት ከዚህ በፊት በየከተሞች እየተዞረ በአካላዊ ቅርርብ የስራ እድል ለመፍጠር ይሰራ እንደነበር ጠቁመው ፤ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ብዙ ሰዎችን ማሰባሰብ ባለመቻሉ ስራውን በበይነ መረብ ዓውደ ርዕይ እየተካሄደ መሆኑን አመልክተዋል። አገልግሎቱን በበይነ መረብ መሰጠቱ የአገልግሎቱን ተደራሽነት እንዳሰፋው የገለጹት አማካሪዋ፣ በበይነ መረብ አገልግሎት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንደገባ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎችን ማሳተፍ ተችሏል ብለዋል። ‹‹የሥራ ዕድል ፈጠራ አጀንዳው የመንግስት ኃላፊነት ብቻ አይደለም›› ያሉት ወይዘሮ ተወዳጅ፤ የግል ባለሀብቶችና ሌሎች ቀጣሪዎች ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። መንግስት በግል አስቀጣሪዎች የሚሰሩ የስራ ፈጠራ ስራዎችን እንደሚደግፍም ተናግረዋል። የደረጃ ዶት ኮም ፕሮግራም ዳይሬክተር ወይዘሪት ሲሃም አየለ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ደረጃ ዶት ኮም ከማስተር ካርድ ፋንውዴሽን በሚያገኘው ድጋፍ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ጋር በመተባበር አዲስ ተመራቂዎችን ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር ያገናኛል፤ ያስቀጥራል። ከተቀጣሪዎች ምንም አይነት ክፍያ አይቀበልም። ደረጃ ዶት ኮም ከአንድ ሺህ በላይ ተመራቂዎችን ከ80 ቀጣሪ ድርጅቶች ጋር ማገናኘቱን የገለጹት ወይዘሪት ሲሃን፣ ህዳር 29 በሚከፈተው ዓውደ ርዕይ ከአራት ሺህ በላይ ተመራቂዎች እንደሚሳተፉም አስታውቀዋል ። እንደ ወይዘሪት ሲሃን ገለጻ፤ ደረጃ ዶት ኮም ከቀጣሪ ድርጅቶች እና ከተመራቂዎች ጋር ማገናኘቱ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሥርዓተ ትምህርት ቀረጻ ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎችን ማግኘት ማስቻሉን ጠቁመዋል። እንደ አሰራር ቀጣሪ ተቋማቱ ከተመራቂ ተማሪዎች ላይ ያጡትን ክህሎት ለደረጃ ዶት ኮም ያሳውቃሉ ያሉት ወይዘሪት ሲሃም ፣ ደረጃ ዶት ኮም በበኩሉ ተመራቂ ተማሪዎች በተመረቁበት ሙያ አጡት የተባለውን ክህሎት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሳውቃል ብለዋል። ደረጃ ዶት ኮም ከ25 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተመራቂዎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ክህሎትን በተመለከተ ሥልጠና መስጠቱን አስታውቀው ፣ በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 14 የሙያ ማበልጸጊያ ማዕከላት ማቋቀሙን ገልተጸዋል። ለስድስት ሺህ ተመራቂዎች የሥራ ዕድል ማስገኘቱን አመልክተዋል። የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሦስት ሚሊዮን ወጣቶች የሥር ዕድል የመፍጠር እቅድ እንደነበረው ይታወሳል።አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36756
77717d7779fc607edb8dbbe99dd9c144
94f66ef32285d318390727037fce6729
አሁንም አፍላ ወጣቶቻችንን እየነጠቀን ያለው የኤች አይ ቪ ቫይረስ
አስመረት ብስራት የተለያዩ ተስፋ የሚሰንቁበት፤ ነገን በብሩህ መንፈስ የሚመለከቱበት፤ ሁሉንም ነገር ማየት መሞከር በሚያስደስትበት የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ወጣቶች ናቸው። በዘወዲቱ ሆስፒታል የማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ድጋፍ በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ ከኤች አይቪ ቫይረስ ጋር ግብ ግብ መገጠም ግድ ሆኖባቸዋል። ገሚሱ እድሜያቸው ለአካለ መጠን ሳይደርሱ የጀመሩት ግንኙነት ለዚህ ቫይረስ ሰለባ የዳረጋቸው፣ ገሚሱ ደግሞ ከወላጆቻቸው የተላለፈባቸው ናቸው። እነዚህ ህፃናትና ወጣቶች አፍላነታቸው በእድሜ ልክ በሽታ መጠቃታቸው እጅግ ልብ የሚነካ ነው። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፌዴራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤትና ሌሎች አጋር ድርጅቶች የ2013 ዓ.ም የዓለም ኤድስ ቀን አከባበር አካል የነበረውን የሆስፒታሉ ጉብኝት ላይ የተመለከትናቸው ህፃናትና ወጣቶች ምንም ያህል በሽታውን ተቀብለውት በጥንካሬ ቢኖሩም የበሽታው ስርጭት ግን ምን ያህል አስከፊ እንደነበር ለመመልከት ያስቻለ ነው። በአዲስ አበባ የስርጭት መጠኑ ከሶስት በመቶ በላይ መሆኑን በፕሮግራሙ ላይ አግኝተን ያናገርናቸው በዘውዲቱ ሆስፒታል የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አስቴር ሸዋአማረ፣ ዛሬም በከፍተኛ ሁኔታ በቫይረሱ ከተያዙ መካከል ሴቶችና አፍላ ወጣቶች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ ብለዋል። በከተማዋ ኤች አይቪ በደማቸው የሚገኙ ግለሰቦች 109 ሺ በላይ መሆናቸውን ያስታወሱት ዶክተሯ፣ ከእነዚህ መካከል እድሜያቸው ከ 15-24 የሚሆን ወጣቶች ከፍተኛ ቁጥር መያዛቸውን ጥናቶች እንደሚያሳዩ ተናግረዋል። በሀገራችን 76 በመቶ የሚሆኑ ወጣት ሴቶች ስለ ኤች አይ ቪ እውቀት የሌላቸው መሆኑን ነው ያስረዱት። በዝግጅቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ እንደሚሉት አዲስ አበባ ከጋምቤላ ቀጥሎ በከፍተኛ ሁኔታ የኤች አይቪ ስርጭት የሚታይባት ከተማ ናት። በጋምቤላ የኤች አይቪ የስርጭት መጠን ወደ አምስት በመቶ የሚጠጋ መሆኑን አስታውሰው፣ አንዳንድ የሀገሪቱ ከተሞች ላይም የስርጭት መጠኑ ከፍ ማለቱን ጠቅሰዋል። ዶክተር ደረጀ እንደሚሉት በከተማዋ በአፍላ ወጣቶች ያለው የኤች አይቪ የስርጭት መጠን ከፍ ማለት ምክንያት መዘናጋት ነው። የተለያዩ አካላት ኤች አይቪ ላይ የሚሰጡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች መቀዛቀዛቸው በአዲሱ ትውልድ የስርጭት ምጣኔው ከፍ እንዲል ምክንያት መሆኑን ነው የሚያስረዱት። የኤችአይቪ መከላከያና መቆጣጠያ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶክተር ፅጌረዳ ክፍሌ እንደሚሉት በከተማዋ ያለውን የኤች አይቪ የስርጭት መጠን አሳሳቢ የሚያደርገው በአፍላ ወጣቶች መካከል ያለው የስርጭት መጠን ከፍተኛ መሆኑ ነው። ለዚህም ኃላፊዋ እንደ ምክንያትነት የጠቀሱት ከስራ አጥነት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ነው። “ስራ አጥነት ለኤች አይቪ የሚያጋልጡ ስፍራዎች እንዲውሉ ገፊ ምክንያት ነው” የሚሉት ዶክተሯ በከተማዋ ያሉ የኢንዱስትሪና የሆቴሎች መስፋፋት ሌላው እንደምክንያት ያነሱት ነው። በከተማዋ የመጤ ባህሎች መስፋፋትም እንደሚታይ የገለጹት ሲስተር ብርዛፍ የራቁት ዳንስ ቤት፣ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት፣ ጫት፣ ሺሻና ቡና ቤቶች መበራከታቸው ለኤች አይቪ መስፋፋት አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየው የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ለመሰማራት ከተለያዩ ከተሞች የሚመጡ ወጣቶች ቁጥር ከፍ ማለትም የስርጭቱ መጠን ከፍ እንዲል እንዳደረገው አብራርተዋል። ጽህፈት ቤታቸው በከተማዋ ለኤች አይቪ ተጋላጭ ብሎ የለያቸውን የከተማዋ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሲዘረዝሩ በትምህርት ቤትም ሆነ ውጭ ያሉ ወጣቶች፣ የቀን ሰራተኞች፣ የከባድ መኪና የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ በወህኒ ቤት የሚገኙ ታራሚዎች፣ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦች፣ እና በቅርቡ በተደረጉ ጥናቶች እንደታየው ደግሞ ባሎቻቸውን በፈቱ ሴቶች የስርጭት ምጣኔው ከፍ ያለ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶቹ በብዛት በሚገኙባቸው አካባቢዎች የትምህርት ስራውን ሊያውኩና ወጣቶቹን ለኤች አይቪ ሊያጋልጡ የሚችሉ መዝናኛዎችን ከትምህርት ቤት መራቅ አለባቸው የሚል አቋም ይዞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመስራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል። የዓለም ጤና ድርጅት እኤአ በ2030 አዲስ በቫይረሱ የሚያዝ ግለሰብ መኖር የለበትም የሚል ራዕይ አስቀምጧል። በኢትዮጵያ የኤች አይቪ የስርጭት መጠኑ 0.9 በመቶ ነው።አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36743
dc357bf174dd19be7d469ca3ceba7708
2f6d160f6c44a0641f7bebb94db4a4b8
ለዓመታት የክልሉ ኢንቨስትመንት ላይ ማነቆ የነበረው የመሬት ካሳ አዋጅ ተሻሽሎ ሊተገበር ነው
ክፍለዮሐንስ አንበርብር አዲስ አበባ፡- የክልሉን ኢንቨስትመንት ለማፋጠን የወጣው የመሬት ካሳ አዋጅ ተሻሽሎ ሊተገበር ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨትመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨትመንት ቢሮ የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ አዲስ ለዝግጅት ክፍሉ እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል የነበረው የመሬት ካሳ አዋጅ የክልሉን ኢንቨስትመንት ላይ ማነቆ ሆኖ መቆየቱን ጠቁመው በአሁኑ ወቅት ቀደም ሲል የነበረው የመሬት ካሳ አዋጅ ተሻሽሎ ሊተገበር ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡ ለአርሶ አደር የሚከፈል ካሳን አስመልክቶ እንዲወጣ የታሰበው አዋጅ በፌዴራል መንግስት ዘንድ አንድ ዓመት ቆይቷል፡፡ ወደ ክልል ከመጣ በኋላ ደግሞ ወራት ተቆጥረዋል የሚሉት አቶ ያየህ ፣ የአዋጁ ተግባራዊ አለመሆን ባለሀብቶችን በፍጥነት ለማስተናገድ እንቅፋት ሆኗል ብለዋል፡፡ እንደ ኃላፊው ገለፃ፤ ክልሉ በፍጥነት መመሪያ አውጥቶ ከሚመለከታቸው አካላትን ጋር ባለመወያየቱና ወደ ሥራ ባለመግባቱ ከተማ አስተዳደሮችና የልማት ኮሪደሮች ባለሀብቶችን ለማስተናገድ ተቸግረዋል፡፡ ይህ አሰራር በአሁኑ ወቅት መፍትሄ ሊሰጠው ተቃርቧል። አዋጁ ተግባራዊ ሲሆን በሳምንታት የኢንቨስተሩን ጥያቄ መመለስ ይቻላል፡፡ አርሶ አደሩም በአሁኑ ወቅ ምርት እየሰበሰበ ሲሆን በወቅቱ ካሳ ካልተከፈለው ወደ መሬት ማረስ እና ማለስለስ ብሎም ዘር መዝራት ስለሚገባ በሚቀጥለው ዓመትም ተመሳሳይ ችግር የሚፈጥር መሆኑን የጠቀሱት ሃላፊው፤ በመሆኑም በፍጥነት አዲሱን አዋጅ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ወደ ሥራ መግባት እንደሚገባ በከፍተኛ አመራሮች መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡ ለዓመታት የክልሉ ኢንቨስትመንት ላይ ማነቆ የነበረ የመሬት ካሣ አዋጅ ተሻሽሎ ወደ ሥራ ሲገባም በክልሉ ከፍተኛ መዋዕዋለ ንዋይ የሚያፈሱ ባለሀብቶች እንደሚኖሩና ከፍተኛ የሆነ የኢንቨስትመንት ፍሰት እንደሚኖርም እምነታቸው እንደሆነ አስታውቀዋል ፡፡ የደብረብረሃን ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃን ገብረሕይወት በበኩላቸው፤ የአዋጁ መዘግየት በከተማው እና በአካባቢው በሚካሄደው ኢንቨስትመንት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ጠቁመዋል፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት ወደ ከተማዋ የሚጎርፉ የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ባለሀብቶችን ለማስተናገድ እና የሚፈልጉትን አገልግሎት በወቅቱ ለመስጠት ፈታኝ ሆኖ መቆየቱን ጠቁመው፤ በተደጋጋሚ ከዞን እስከ ክልል ችግሩ እንዲፈታና ለሚመለከታቸው ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡ አዋጁ በመዘግየቱ ባለሀብቶች በፈለጉት መንገድ ኢንቨስትመንት እንዳያካሂዱ ያደረጋቸው ሲሆን ከወረዳ እስከ ዞን ለሚገኙ አስተዳደሮችም ፈተና እንደነበርና አርሶ አደሩን ካሳ ከፍሎ መሬት እንዲለቅ የሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስቸጋሪ ሆኖ መቆየቱንም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36750
3eb2b928a5bd97e1c7c0bdc6ca63e059
6bca1c46416cf87db3aa37a7feab0d58
የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ
ጌትነት ምህረቴ ”አንድ በሬ ሸጬ ስድስት ዓመት በመቀሌ የታሰረውን የልጅ ልጄን በደከመ አቅሜ ሄጄ አስፈትቻለሁ። ከተፈታ በኋላም አፋኙ የህወሓት ጁንታ በሚደረግበት ጫናና ክትትል ተማሮ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሄዷል። የልጅ ልጄ ያለበትን ቦታና ምን እንዳጋጠመው ስለማላውቅ የበረሃ ራት ሆኖ ይሆን ብዬ እየተጨነኩ ነበር። አምና ግን ሳውዲ መግባቱን ስለሰማሁ ደስታዬ ወደር የለውም” የሚሉት ወይዘሮ ከፍያለች በላይ ናቸው። ንት ሁኗታል። ከተማዋ ነጻነቷን በመቀናጀቷ እፎይታ ከተሰማቸው ነዋሪዎች መካከል አንዷ ወይዘሮ ከፍያለች በላይ ናቸው። አፋኙ ቡድኑ በማንነታቸው ምክንያት በእኚህ አዛውንት ላይ ከፍተኛ ማንገላታት፣ ሰቆቃና ግፍ ፈጽሞባቸዋል። ማንነቴን አልሸጥም እኔ የወልቃይት አማራ ነኝ አባቴ፣ አጎቶቼ ይግባኝ ሲኖራቸው መቀሌ ሳይሆን ደባርቅና ዳባት ሄደው ሲያስፈጽሙ ነበር ብዬ በአደባባይ በመናገሬ እያረስኩና እያሳረስኩ ልጆቼን ያሳደኩበትን መሬቴን ተነጥቄያለሁ ይላሉ ። ሁለት ልጆችና አንድ የልጅ ልጃቸውን በግብርና ሥራ ያስተዳድራሉ። ልጆቼም ብዙ መከራና መገፋት ደርሶባቸዋል። በተለይ ቃፍታ ከተማ የመንግሥት ሥራ ሲሰራ የነበረው የልጄ ልጄ 600 ብር አጥፍተሃል ተብሎ ስድስት ዓመት መቀሌ ወስደው አስረውታል። ይኸው በዚህ ደካማ አቅሜ የማሳርስበትን በሬ ሸጬ 10ሺ ብር ዋስትና ከፍለው ማስፈታታቸውን ያስታውሳሉ። የምንኖርበት ቃፍታ ሁለት ህግ ነው ያለው የሚሉት ወይዘሮ ከፍያለች፣ የወልቃይት አማራ ከፍተኛ ልዩነትና ጫና ይደረግበት ነበር። ለዚህም ብር ያጠፋና ነብስ ያጠፋ ሰው እኩል ፍርድ የሚሰጥበት ሁኔታ እንዳስተዋሉ ገልጸዋል። የእሳቸው የልጅ ልጅ የመንግሥት ሥራ በሚሰራበት የወረዳው የፋይናንስ መስሪያ ቤት 600 ብር አሳስተሃል ተብሎ 6 ዓመት የተፈረደበት ሲሆን ሌላው የትግራይ ተወላጅ ደግሞ የሰው ህይወት አጥፍቶ 6 ዓመት የተፈረደበት መሆኑን በመግለጽ የዳኝነት ልዩነቱን በአብነት ጠቅሰዋል። ከሀዲው ቡድን አማራን ይጠላል፤ በግልጽም የወልቃይት መሬቱን እንጂ እናንተን አንፈልጋቸውም ይል ነበር የሚሉት ወይዘሮ ከፍያለች ፤ በርካታ የወልቃይት አማራ ወጣቶች በሚደርስባቸው በደል፣አፈና፣መገለልና ጫና ምክንያት አገር ጥለው ለስደት መዳረጋቸውን ነግረውናል። ታስሮ የተፈታውም ሆነ ሁለት ልጆቻቸው በከ ሀዲው ህወሓት ይደርስባቸው የነበረውን ጫናና በደል አንገፍግፏቸው አገር ጥለው መኮብለላቸውን ያወሳሉ። ላለፉት 30 ዓመታት በወልቃይት አማራዎች ላይ የሚደ ርሰው ጫና፣ በደል፤ ልዩነት አይጣል የሚያስብል መሆኑን የሚገልጹት ከፍ ባለ ምሬት ነው። ለልጆቻቸው ብቻ ሳይሆን ለእሳቸውም ጭምር ጆሮ ጠቢ ይመደብባቸው እንደነበርም ይናገራሉ። ላለፉት 30 ዓመታት ምን አወራን ፣ ዛሬ ደግሞ ምን ሊያደርጉን ነው ብለን እንደነግጣለን እንጂ እንደጉም ይጠፋሉ ብለን አስበን አናውቅም የሚሉት አዛውንቷ፤ የከሀዲው የህወሓት ጁንታ በውስጡ እንጥፍጣፊ ርህራሄ የሌለው መሆኑ ንጹሀን ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ከእነሱ ጋር አብረዋቸው የሚሰሩ ሰዎችን ጭምር ሳይቀር ገድለዋቸው ነው የፈረጠጡት፤ ይህ የሚያሳየው ዞሮ ዞሮ ግፍ የሚሰራ ሰው የእጁን እንደሚያገኝ ነው ብለዋል። አሁን ነጻ ወጥተናል፤ ከሀዲውና አፋኙ የህወሓት ጁንታን ተገላግለናል። ይህን ነጻነትና እፎይታ በዘላቂነት ለማስቀጠል የከተማው ነዋሪም ሆነ መንግሥት እጅና ጓንት ሆነው መስራት ይኖርባቸዋል። እኔም በጸሎት አግዛለሁ ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተውናል። አደራጀው ጫሉ የሚባለውን ትንሽ ወንድማቸው በአፋኙ የህወሓት ጁንታ የተገደለባቸው መሆኑን የሚገልጹት የጸገዴ ወረዳ ከተማ ንጉስ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አዲሲ ቀለብ ፤ የአማራ ነጋዴና ገበሬ እሱ ቤት ተሰብስበው ነው የአማራ ማንነትን የሚጠይቁት በሚል ደብድበው ገድለው ወደ ገደል እንደጣሉት በቁጭት ይናገራሉ። “የወንድሜን ሞት ሲያረዱኝ ሴት ልጄ አራስ ነበረች፤ ገደል ገብቶ ሞተ ብለው አስከሬኑን ደጃፌ ላይ ጥለውት ሄዱ፤ በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ወቅት አደራጀው ወንድሜ አንተ ነህ የማትተካ እንጂ ነገ የአማራን መብት የሚያስጠብቅ ትንታግ ትንታጉን እንተካዋለን ብለሽ አልቀሰሻል ተብዬም በትግራይ ልዩ ሃይል በሰደፍ መመታታቸውን ይናገራሉ ። ከአንድ ወር በላይም ታስሬያለሁ፤ የሚሉት ወይዘሮዋ፣ ከዚያ አስከፊ አስተዳደርና አገዛዝ በመከላከያ ሰራዊትና በአማራ ልዩ ኃይል ነጻ በመውጣታቸው ደስታቸው እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸውልናል። “ ድቅድቁ ጨለማ አልፏል ፤አሁን ጸሐይ ወጥቶልናል፤ ይህን የተገኘውን ነጻነት ተንከባክቦ መጠበቅና ማስቀጠል ከጸገዴ ወረዳ ህዝብ ይጠበቃል። እኔም በማንኛውም መልኩ ለማገዝና ለመተባበር ሙሉ ፈቃደኛና ደስተኛ ነኝ” ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተውናል።አዲስ ዘመን ህዳር 27 ቀን 2013 ዓ ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36795
d17b7325632e078e1abca2b6752f205f
60b5f8fac26de81c0207b2afb0d06adb
በቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመጨረሻ ምሽግ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል
የጁንታው የአመራር ቡድን የታየባቸው ቦታዎች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው ጌትነት ተስፋማርያም ተንቤን:- በቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመ ጨረሻ ምሽግ በሀገር መከላከያ ሰራዊት በሶስት አቅጣጫ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደበት እንደሚገኝ ተገለጸ። በቆላ ተምቤን የጁንታውን አመራር ለመያዝ የሚ ደረገውን ዘመቻ እየመሩ ያሉት በመከላከያ ሰራዊት የ31ኛ ክፍለ ጦር ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ኮሎኔል ሻምበል በየነ እንደገለጹት፤ ከመቀሌ ቢሮው ለቆ የሸሸው የጁንታው አመራር በቆላ ተንቤን የመጨረሻ ምሽጉ ላይ ይገኛል። የመከላከያ ሰራዊትን የጁንታውን የመጨረሻ ምሽግ በተለያዩ አቅጣጫዎች ከቦ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። ቆላተምቤን ወርቅ አምባ ከተማ ላይ የመጨረሻ ምሽጉን ያደረገውን የጁንታውን አመራር ለመያዝ አሊያም ለመደምሰስ መከላከያ ሰራዊት በመረጃ የተደገፈ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ያሉት ኮሎኔል ሻምበል፤ ከአድዋ መስመር የመጣው ሰራዊት አካባቢውን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ እንደሆነ እና ከሃውዜን እና መቀሌ መስመር ያለውም ወደ ቦታው በከፍተኛ ወኔ እየተጠጋ እንደሚገኝ ገልጸዋል። መከላከያ ሰራዊቱ ወርህ የሚባል ትልቅ ወንዝ መሻገር አይችልም በሚል አካባቢ የጁንታው ታጣቂዎች ማጥቃት ቢፈጽምም ሰራዊቱ ወደ አካባቢው ተጠግቶ ከወርቅ አምባ 10 ኪሎ ሜትር ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል። እንደ ኮሎኔል ሻምበል ከሆነ፤ በቆላ ተምቤን ወርቅ አምባ አካባቢ የመሸገው ጁንታው በምድር ከሚወሰድበት እርምጃ ባለፈ በአየር ጭምር እርምጃ ተወስዷል። በአየርና በድሮን አውሮፕላኖች በተወሰደ እርምጃ ወርቅ አምባ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ሰባት የጁንታው ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ወድመዋል። በአካባቢው የነበሩ የጁንታው የቀድሞ ባለስልጣናትም በየአቅጣጫው ተበታትነዋል። <<ከአጥፊው ቡድን ጋር በርካታ ሀገር የከዱ ጄኔራሎች፤ የፖለቲካ እና የአስተዳደር አመራሮች እንደሚገኙም በቂ መረጃ ተገኝቷል>> ያሉት ኮሎኔል ሻምበል፤ ከተገኘው መረጃም ከጁንታው አመራር ከዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል አንስቶ እነ ጌታቸው ረዳ፣ ስዩም መስፍን፤ አቦይ ስብሃት እና በርካታ የአጥፊው ቡድን አባላት በአካባቢው እንደሚገኙ እንደታወቀ ገልጸዋል። ከመከላከያ የከዱ ጄኔራል ከበደ እና ጄኔራል ጆን የሚባሉ ተፈላጊዎች የጁንታውን አመራር ሽፋን በመስጠት ላይ መሆናቸውን አመልክተው፣ሰራዊቱ የጁንታው ዋና አመራርና አጃቢዎችን እንዲሁም የኮማንዶ አባላቱን በብረት ለበስ ከቦ እንደሚገኙም ገልጸዋል።የጁንታው ቡድን ከአመራር እስከ ደጋፊ ሃይሉን አሰባስቦ ቆላ ተምቤን መገኘቱን የገለጹት የግንባሩ አዛዥ፤ በአካባቢው ኮማንዶዎቹን በማሰማራት አይደፈርም በሚል ሲኩራራበት የነበሩ 10 ዙር ምሽጎች በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ከመግባታቸውም በላይ በአካባቢውም በቀንና ማታ ጭምር እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አስታውቀዋል። የመከላከያ ሰራዊቱም የጁንታውን አመራር ከተቻለ ለመያዝ አሊያም ለመደምሰስ የሚያስችለውን እርምጃ በማካሄድ ላይ መሆኑን የተናገሩት ኮሎኔል ሻምበል፤ <<የጁንታው አመራር እና የመጨረሻ ቡድን ቀለብ፣ ውሃ እና ነዳጅ አልቆበታል። ስለሆነም በቅርብ ጊዜ በዝርዝር የተያዙ የጁንታው አመራር አባላትን እና ተበታተኖ የሚገኘውን ወንጀለኛ የመልቀም ሥራ ይከናወናል>> ብለዋል። የጁንታው አመራር የሚፈልጋቸው ከተሞችን ውጊያ እንዳይካሄድባቸው እየለቀቀ ከሄደ በኋላ ለምን ቆላ ተምቤን ላይ መሽጎ ተቀመጠ የሚለው ግልጽ እንዳልሆነ የተናገሩት ኮሎኔል ሻምበል፤ አድዋን አክሱምን እና መቀሌ ከተማ የህግ ማስከበር እርምጃ እንዳይካሄድባቸው እየለቀቀ መሬት ይዞ እንኳን ሳይተኩስ መውጣቱን ገልጸዋል። ሽሬ ላይ ደግሞ ውጊያ ገጥሞ ህዝብ ለማስጨረስ ቢፎክርም አልተሳካለትም። አሁን ላይ በተንቤን ውጊያ እንዲካሄድ የፈለገው ጁንታው ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የተንቤን ህዝብ መብራት እንዳያገኝ እና በመሰረተ ልማት እንዳይጠቀም ሲያደርግ በመቆየቱና ህዝቡም ይህንን በተደጋጋሚ በግልጽ ይቃወም ስለነበር ህዝቡን ለጥቃት ለማጋለጥ ሊሆን እንደሚችል ማብራሪያ ሰጥተዋል። እንደ ኮሎኔል ሻምበል ከሆነ፤ የጁንታው አመራር አሁን ላይ በተንቤን በመመሸግ ፣ውጊያ እንዲካሄድ እና የተንቤን ህዝብ እንዲያልቅ ያለውን ፍላጎት በግልጽ አሳይቷል። መከላከያ ሰራዊቱ ግን ለይቶ በሚወስደው እርምጃ ህዝብን ከጥቃት በመከላከል የጁንታው መገኛዎችና መዳረሻን ዒላማ ባደረገ ሁኔታ በመረጃ የተደገፈ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። ሰራዊቱ በሚወስደው እርምጃ የጁንታው ታጣቂ የነበሩ ወጣቶች ተይዘዋል። ከተያዙ ሰዎችም የሚገኙ ተጨማሪ መረጃዎችን በመያዝ የህግ ማስከበሩ ሥራ በተጠናከረ መንገድ እየተከናወነ ይገኛል ፤ የጁንታ አመራር በቅርቡ ለህግ ቀርቦ ፍርዱን እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 27/2013 ዓ. ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36796
98aa0d1f7f05a5ebb96e6599ee7d78c9
1000ce23464869ee4562c77450f4c2a3
የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂ ፒ ኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው
ክፍለዮሐንስ አንበርብር ፊንፊኔ፡- በኦሮሚያ በየጊዜው እያጋጠመ ለሚ ገኘው የህይወትና ንብረት ውድመት በህወሓት ጁንታ እና ተላላኪዎቹ የሚፈፀም መሆኑንና ይህንንም ለማስወገድ ብሎም የቡድንን ዕድሜውን ለማሳጠር በ‹ጂ ፒ ኤስ› ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መምሪያ አስታወቀ።የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መም ሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር እንዳለ ቁምላቸው ለበሪሳ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የህወሓት ጁንታ እና የኦነግ ሸኔን ሴራ ለማክሸፍና ዕድሜ ለማሳጠር ‹‹ጂ ፒ ኤስ›› ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ መሆኑን አብራርተዋል። እነዚህ አካላት ዜጎችን ለምን እንደሚገድሉ እን ደማያውቁ በመጠቆም በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋልም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል። ቴክኖሎጂው እነዚህ አካላት ያሉበትን ቦታ ለመከታተል የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል።በዚህ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የኦነግ ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸውን የተናገሩት ኃላ ፊው፤ በሠላማዊ መንገድ እጅ ለማይሰጡና የኃይል አማራጭ ለመጠቀም የሚሞክሩት ላይ ደግሞ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሆነ አስታውቀዋል ። እነዚህ ጸረ ሠላም አካላት አባ ቶርቤ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሱ መሆኑን አመልክተው ፣ ኦሮሚያ ክልልን የግጭትና ጦር አውድማ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ሠላማዊ ዜጎችን መግደል ሥራቸው አድርገው መቆየታቸውንም አመልክተዋል። ማንኛውንም የፖለቲካ አመለካከት ያለው አካል በዴሞክራሲያዊ መንገድ የፖለቲካ አስተሳሰቡን ለህዝብ መሸጥ ይጠበቅበታል ያሉት ኮማንደር እንዳለ፤ ከዚህ ውጪ ሰላም በማደፍረስና ሠላማዊ ዜጎችን በመግደል ስኬታማ መሆን እንደማይቻል አስረድተዋል። የኦሮሚያ ፖሊስም ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ የሆነና የዜጎችን ሠላም ለመጠበቅ የተቋቋመ ነው ያሉት ምክትል ኮማንደር ፣ በየትኘውም ሁኔታ የዜጎችን ሰላም ችግር ውስጥ የሚከቱ ተግባራትን አይታገስም ብለዋል። መንግሥትም ለዜጎች ሠላምና ደህንነት መቃወስ ምክንያት የሆኑ እንደ የህወሓት ጁንታና ፣ አባ ቶርቤ፣ ሸኔ እና ሌሎችንም ወደ ህግ ለማቅረብ ከመቼውም በላይ ጠንካራ ሥራ እየሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል።ቀደም ሲል እነዚህን አካላት በህግ ጥላ ሥር ሆነው እንዲዳኙ የተለያዩ ሥራዎች ቢሰሩም አሁንም ዜጎችን እየገደሉ በመሆኑ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የማጽዳት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት የክልሉ የፖሊስ ኃይል በቴክኖ ሎጂው በመታገዝ የተላላኪዎችን ሁኔታ በማወቅ ብሎም የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ በመከታተል ወደ ህግ ለማቅረብ አስፈላጊውን ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። እነዚህ አካላት ዜጎችን ከመግደል በዘለለ የንግድ እንቅስቃሴ በማስተጓጎል ሽብር ለመፍጠር እየተሯሯጡ መሆኑን ጠቁመው፣ የነዚህን አካላት ዕድሜ ለማሳጠር በትጋት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል ። ዜጎችም ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ጎን በመቆም እነዚህን ፀረ ሰላም አካላት እንዲፋለም ጥሪ አቅርበዋል፤ ፖሊስ ከመቼውም በላይ ሰላም ለማስከበር ዝግጁ መሆኑን ምክትል ኮማንደር እንዳለ አረጋግጠዋል።አዲስ ዘመን ህዳር 27/2013 ዓ. ም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36804
9694ffbe58b7cc9190093cfd1f5b99b1
c3fae79d34159583181167afa5e35c47
አረንጓዴው ጎርፍ በሌላ የታሪክ ምዕራፍ
ኢትዮጵያ እግራቸው እንደ አቦሸማኔ የሚወረወር፣ እንደ ንሥር የሚበሩ፣ ጽናትንና ብርታትን ከአልሸነፍም ባይነት እልህ ጋር ያዋደዱ፣ ተስማምተው እየተማከሩ ከኋላና ከፊት አገርና ህዝብን አስከትለው የሚሮጡ፣ የርቀት መጠን ለክተው ሳይጠበቅ የሚፈተለኩ፣ ለሰንደቅ ዓላማና ለሕዝብ ፍቅር የተገዙ አትሌቶች እናት ናት። ከአገሩ አልፎ ለመላው አፍሪካ ህዝቦች የአሸናፊነት ተምሳሌት ሆኖ በታሪክ የሚዘከረው ሻምበል አበበ ቢቂላና ማሞ ወልዴን ጨምሮ ሌሎችም አትሌቶች፣ በአህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ ውጤታማ በመሆን ከወርቅ እስከ ነሐስ በማምጣት፣ ለሚወዷት አገራቸውና ሕዝባቸው ልዕልና እና ክብር የአሸናፊነት ዓርማ ሆነዋል። ሰንደቅ አላማዋንም በዓለም አደባባይ በተደጋጋሚ ከፍ አድርገው አውለብልበዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ ሲዘከርም በርካታ አይረሴ፣ ደማቅና ወርቃማ ዘመናትን ማስታወስ አይከብድም። ከሁሉ በላይ ግን ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች የማንኛውንም አገር አትሌት ጣልቃ ሳያስገቡ በሚያሳዩት የአጨራረስ ብቃትና ውጤት ያገኙት ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› (ዘ ግሪን ፍለድ) መጠሪያና ታሪክ ቀድሞ የሚታወስና በአብዛኞች ዘንድ መቼም የማይዘነጋ ነው። ይህን ሁነት የተመለከቱ ታላላቅ የዓለም መገናኛ ብዙኃንም በአረንጓዴው መለያ መላውን ዓለም ያስደመሙት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እውነትም ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› እንጂ ለገድላቸው ሌላ ተቀጽላ እንደማይገልጻቸው ሲናገሩም ተደምጠዋል። ከግል ይልቅ የቡድን ሥራ በትልቁ የሚንፀባረቅበት፣ አንዱ በሌላው ተንኮልና ሸፍጥ የማይሰራበት፣ እውነተኛ ወንድማማችነትና አጋርነት የሚስተዋልበት የአገሪቱ አትሌቶች ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› የሚል ስያሜ ከ1970 እስከ 1980ዎቹ መጀመሪያ በነበሩት የውድድር ዓመታት ውስጥ መነሻውን አሃዱ ስለማለቱም መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዋናነት ለአረንጓዴው ጎርፍ ስያሜ ትልቁን ውለታ ከዋሉት መካከልም የሞስኮ ኦሊምፒክ በአምስትና አስር ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ የድርብ ድል ባለቤቱ ማርሽ ቀያሪው ‹‹ይፍጠር ዘ ሺፍተር›› ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር፣ በዚሁ የሞስኮ ኦሊምፒክ በአስር ሺ ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ ያስመዘገበው መሐመድ ከድር፣ ሻምበል እሸቱ ቱራ፣ ከበደ ባልቻ፣ ደረጀ ነዲ፣ ዮሐንስ መሐመድ፣ ብርሃኑ ግርማ፣ ግርማ ወለደሃናን ጨምሮ ሌሎችም ድንቅ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የጎላውን ስፍራ እንደሚዙ አንዳንድ ባለሙያዎች መረጃዎችን ጠቅሰው ይጠቁማሉ። የአረንጓዴው ጎርፍ ይበልጡን ጎሎቶ የወጣው ግን በታላላቅ አትሌቲክስ መድረክ እ.ኤ.አ በ2003 በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው ሻምፒዮና ላይ ነው። በዚህ መድረክ በአስር ሺ ሜትር ወንዶች ቀነኒሳ በቀለ፣ ኃይሌ ገብረ ስላሴ እና ስለሺ ስህን በድንቅ የቡድን ሥራ ዓለምን ባስደመመ መከባበርና የወንድማማች ፍቅር የማንኛውንም አገር አትሌት ጣልቃ ሳያስገቡ ተከታትለው በመግባት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የአረጓዴው ጎርፍ ታሪክን ይበልጥ ማጉላታቸው ይታወሳል። እ.ኤ.አ በ2005ቱ ሄልሲንኪ በተካሄደው ሻምፒዮና ደግሞ አረንጓዴ ጎርፉ በወንዶች ብቻ ሳይሆን በሴቶችም ቢሆን ቀጣይ ስለመሆኑ ያስመሰከረና የኢትዮጵያም አትሌቲክስ ስፖርት ሥምና ታሪክ እንዲታወስ የላቀ ሚና ተጫውቷል። በዚሁ መድረክ በሴቶች አምስት ሺ ሜትር በጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰረት ደፋር እና እጅጋየሁ ዲባባ አማካኝነት የአረንጓዴው ጎርፍ ስም ይበልጡን ደምቋል። ከዚህ የብርቅ እንስት አትሌቶቻችን አኩሪ ታሪካ በኋላ የአረንጓዴው ጎርፍ ገድል መልሶ ለማግኘት አምስት ሻምፒዮናዎች መጠበቅ ግድ ያለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ከዓመታት በኋላም በቤጅንጉ ሻምፒዮና በአልማዝ አያና፣ ሰንበሬ ተፈሪ እና ገንዘቤ ዲባባ አማካኝነት ዳግም አሳክቶታል። በቤጂንግ 15ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ማጠናቀቂያ ላይ በተካሄደው የአምስት ሺ ሜትር ሴቶች ፍጻሜ አልማዝ አያና 14 ደቂቃ:26:83 የሆነ ሰዓት የወርቅ፣ ሰንበሬ ተፈሪ 14:44:07 በሆነ ሰዓት፣ የብር እንዲሁም ገንዘቤ ዲባባ 14:44:14 በሆነ ሰዓት የነሐስ ሜዳሊያ ለሀገራቸው አስገኝተዋል። በጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰረት ደፋር እና እጅጋየሁ ዲባባ አሃዱ የተባለው ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ››ን የእንስት አትልቶቻችን ታሪክ በማስቀጠል አገሪቱ በድንቅ ክህሎትና አቅም የካበቱ በድላቸውም የሰንደቅ ዓላማቸውንና የሕዝባቸውን ልዕልና ከፍ ያደረጉ አትሌቶች ሃብታም ስለመሆኗ አስመስከረዋል። በዚሁ መድረክ አልማዝ ያስመዘገበችው ሰዓት የሻምፒዮናው ክብረ ወሰን ሆኖ መመዝገቡ ደግም ድሉን ይበልጥ ጣፋጭ ያደርገዋል። ባለፉት ሳምንት በሞሮኮ ራባት በተካሄደው የ12ኛው በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች አትሌቶች የማንኛውንም አገር አትሌት ጣልቃ ሳያስገቡ በድንቅ የአጨራረስ ብቃትና ውጤት ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› (ዘ ግሪን ፍለድ) ታሪክ በአፍሪካ ምድር ላይ ደግመውታል። በዚህ መድረክ በሴቶች አስር ሺ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትለው በመግባት በበላይነት አጠናቀዋል። አትሌት ፀሐይ ገመቹ 31 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ ከ92 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ለሀገሯ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። አትሌት ዘይነባ ይመር 31 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ95 ማይክሮ ሰከንድ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ስታስገኝ፤ አትሌት ደራ ዲዳ 31 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ ከ78 ማይክሮ ሰከንድ ሶስተኛ ሆና በመግባት የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። በዚህ መድረክ የአረንጓዴውን ጎርፍ ታሪክ በአንድ የውድድር ርቀት ብቻም አልተገደበም። እንደ አስር ሺ ሜትር ሁሉ በሴቶቹ ግማሽ ማራቶን ውድድር ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትለው ገብተዋል። አትሌቶቹ ፍልሚያውን በበላይነት ከማጠናቀቅ በላይ በአንድ መድረክ በሁለት የርቀት አይነቶች የአረንጓዴውን ጎርፍ እንዲፈስ በማድረግ አዲስ ታሪክን ሰርተዋል። አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው 1ሰአት፡10 ሰከንድ.26ማይክሮ ሰከንድ ወርቅ፣ አትሌት ደጊቱ አዝመራው 1ሰአት፡ 10 ሰከንድ 31ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ስታስገኝ፣ አትሌት መሠረት በለጠ 1ሰአት፡12 ሰከንድ.08 ማይክሮ ሰከንድ ሶስተኛ ሆና በመግባት የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› ከአሸናፊነትም በላይ ለአሁኑ የአትሌቲክስ ተዋንያን በአስተማሪነቱ ትልቅ ታሪክ ያለው ሆኖ የዘለቀ ሲሆን፣ ተተኪዎችም በተለያዩ ታላላቅ አትሌቲክስ መድረኮች እያስቀጠሉት ስያሜውም ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች ልዩ መጠሪያቸው ሆኖ እንደትናንቱ ዛሬም ቀጥሏል።አዲስ ዘመን ነሐሴ 28/2011 ታምራት ተስፋዬ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=17298