query_id
stringlengths
32
32
passage_id
stringlengths
32
32
query
stringlengths
7
297
passage
stringlengths
137
5.93k
category
stringclasses
6 values
link
stringlengths
28
740
13252a2fff8e1e3acf854c4a4bda9ea1
158a420e99406f5cc7b148cc3e62c38a
«ታላቁ የህዳሴ ግድብ ህይወታችንን ለመክፈልም የተዘጋጀንበት ትልቁ ፕሮጀክታችን ነው» – ጄኔራል አደም መሐመድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
አዲስ አበባ ፦ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ህይወታችንን ለመክፈልም የተዘጋጀንበት ትልቁ ፕሮጀክታችን ነው ሲሉ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ አስታወቁ። የግድቡ ጉዳይ የልማታችን እና የህልውናችንም ጉዳይ እንደሆነም አመለከቱ ።ጄኔራል አደም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ህይወታችንን ለመክፈልም የተዘጋጀንበት ትልቁ ፕሮጀክታችን ነው ብለዋል። ለሰራዊቱ አንዱ የሉዓላዊነታችን መገለጫ እንደሆነም አመልክተዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ሰራ ዊቱ የህዳሴውን ግድብ በዓይነ ቁራኛ የሚያየው እንደሆነ ገልጸዋል።መላው ህዝባችን የህዳሴ ግድብ ተገድቦ ለኢኮኖሚያችን የሚኖረውን አዎንታዊ አስተዋጽዖ በሚገባ ተረድቶ ፍጻሜውን በጉጉት እንደሚጠብቀው ሁሉ ሰራዊቱም የግድቡን ግንባታ ፍጻሜ በጉጉት እየጠበቀው መሆኑን ገልጸው በተለያዩ መንገዶች ለግንባታው ከአንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ማበርከቱንም አስታውቀዋል ።በህዳሴ ግድባችን ላይ ከውስጥም ከውጪም ሊቃጡ የሚችሉ ማንኛውንም ጥቃቶች ለመከላከል ከፍተኛ ጥረትና ሰፊ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ያመለከቱት ጀነራሉ፣ እስካሁን ግንባታው ያለምንም እንከን እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።“የህዳሴ ግድቡን ጉዳይ እንደ ሰራዊት አንዱ የሉዓላዊነታችን መገለጫ አድርገን ስለምናየው፤ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ከፍተኛ የትኩረት አቅጣጫችን ነው። አመራሩም፤ አባሉም፤ በዛ አካባቢ ግዳጅ ተሰጥቶት የሚንቀሳቀስ ማንኛውም አካል ሌት ተቀን ግድቡን እየጠበቀ እስካሁን የመጣበት ሁኔታ አለ” ብለዋል ። ፕሮጀክቱ ሲታሰብ ጀምሮ ግብጾች ግንባታውን ለማደናቀፍ ያልሰሩት ስራ የለም ያሉት ጀነራል አደም፤ ፋይናንስ እንዳናገኝ አድርገዋል፤ ከዛ በላይ ህዳሴው ግድብ እንዲጓተት በተለያየ ምክንያት ሰርተዋል ብለዋል። ግብጾች እንኳን እንዲህ አይነት ግድብ መገደብ ይቅርና በተለያዩ ቦታዎች የምንሰራቸውን የውሃ ማቆር ስራዎች እስከመከታተል የሚደርሱ ከመሆናቸው አንጻር ስራቸው የሚጠበቅ እንደነበረ ገልጸዋል።በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተለያየ መንገድ የውክልና ጦርነት፣ የውክልና ግጭት በማካሄድም አገር ውስጥ ባለ ቡድን ጭምር ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን አመልክተው፤ ከባቢ አገራትንም እንደ መነሻ በመጠቀም ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲዋን ለማዳከም ከጎረቤት አገሮች ጋር በጥርጣሬ እንድትተያይ በርካታ ስራዎች እየሰሩ የመጡበት ሁኔታ መኖሩንም አስታውቀዋል።ግብጾች አባይን ውሃ የህልውናችን ጉዳይ ነው እንደሚሉት፤ ለእኛም የልማታችንም፤ የህልውናችንም ጉዳይ መሆኑን ማወቅ ይጠበቅባቸዋል ። ሰራዊታችንም እነዚህን ሁሉ ነገሮች በጥንቃቄ ያያቸዋል ያሉት ጀነራል አደም ፣ ከዚህ የተነሳም የግድቡን ግንባታ ሰራዊቱ በልዩ ሁኔታ የምንከታተለው፤ የምንጠብቀው፤ ከገንዘባችንም፣ ከጉልበታችንም በላይ ህይወትን እየከፈልንበት ያለ፤ ለመክፈልም የተዘጋጀንበት ትልቁ ፕሮጀክታችን ነው ብለዋል፡፡ ከጄኔራል አደም መሐመድ ጋር ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ ሙሉ ቃል በ11ኛው ገጽ ይመልከቱ አዲስ ዘመን ሐምሌ 19 ቀን 2012 ዓ.ም  በወንድወሰን ሽመልስ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36038
e9bda6f772e2840ceec8ce940e5e6cb4
9bf3ae802b605878d936d3ee9c678220
በአደንዛዥ አስተሳሰብ የተመረዙ ወጣቶች ለአገሪቷ ሥጋት እንዳይሆኑ ሊሰራበት ይገባል
 አዲስ አበባ፡- በርካታ ወጣቶች በአደንዛዥ እና በተበላሸ አስተሳሰብ በመበረዛቸው ለአገር ተስፋ ሳይሆን ሥጋት እየሆኑ መምጣታቸውን የተለያዩ ምሁራን ገለጹ። በወጣቶች ስብዕና ዙሪያ የተጠናከረ ስራ መስራት ይገባል። የሱስና ሱሰኝነት ተጋላጭነት ቅነሳ ህክምናና መልሶ ማገገም ስልጠና ባለሙያው ወጣት ኤሊያስ ካልዕዩ እንደገለጸው፤ ወጣቱ በተበላሸ አስተሳሰብ መመረዙ አዳዲስ ሥራዎችን ከመሥራት ይልቅ በተሠራው ላይ አቃቂር ማውጣት፤ የሚሠራን አካል መተቸት፣ ራስን እንደ አዋቂ አድርጎ መቁጠር የሚታዩ ችግሮች ናቸው። ‹‹የእኔ ብሔር አንደኛ የሌላው ሁለተኛ›› የሚለው ሐሳብ መነሻው የአደንዛዥ አስተሳሰብ ውጤት መሆኑን ጠቅሰው፤ የአስተሳሰቡ ስፋት ወጣቱን ገንዘብና ቁሳቁስ ከሰው አብልጦ እንዲወድ፣ የሰውን ክቡርነት እንዳይቀበል የሚያደርግ የአስተሳሰብ ዝንፈት ባለቤት እንዲሆን አድርጎታል። ይህ ደግሞ አገርን አደጋ ውስጥ እንድትገባ እያደረገ መሆኑን አስረድቷል።‹‹አደንዛዥ አስተሳሰብ ማለት ግለሰቦች ስለራሳቸው፣ ስለማህበረሰባቸው፣ ስለአገራቸው፣ ስለሚጠቀሙት ነገር ያላቸው አስተሳሰብ የተዛባ መሆን እና የተዛባ መረጃና እውቀትን እንደ እውነት አድርጎ መቀበል መጀመር ነው›› የሚለው ባለሙያው፤ ወጣቱ አሁን አፀያፊ ነገሮችን ማድረግ የጀመረው የአደንዛዥ አስተሳሰብ ሰለባ በመሆኑ ነው። ስለዚህ መንግሥት፣ ማህበረሰቡና ግለሰቦች በወጣቱ አዕምሮ ልማት ላይ ሊሠሩ ይገባል ሲል አሳስቧል። በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር መምህር ሃሳቡ ተስፋ እንደሚናገሩት፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በወጣቱ ዘንድ ነውር የሚባል ነገር ጠፍቷል። ለዚህም ዋና መንስኤው በጥላቻ የተሞላ አዕምሮ ባለቤት እንዲሆን በመደረጉ ነው። ወጣቱን የማያገናዝብ፣ አስቦና አሰላስሎ ነገሮችን የማይመለከት እንዲሁም ምክንያታዊ ባለመሆኑ ለአገር ተስፋ ሳይሆን አደጋ ፈጣሪ ሆኗል። ይህ ደግሞ ሀገር ተረካቢነቱን ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል። ወጣቱ ከሰውነት ተራ ወጥቶ በሪሞት እንደሚታዘዝ ማሽን እየሆነ መምጣቱን የሚያነሱት መምህሩ፤ አሁን በስሜት እና በተበላሸ አስተሳሰብ እየተመራ በመሆኑ ማወቅ የሚገባውን ያህል እየጠየቀና እያወቀ አይደለም ብለዋል። ወጣቱ መብትና ግዴታውን በሚገባ ስላልተገነዘበ በተነዳበት መንገድ እየሄደ ነው ያሉት መምህሩ መንግሥት መብትና ግዴታን ማሳወቅ፣ ጥፋት ሲያጋጥምም በሕግ አግባብ ተጠያቂ ማድረግ እንዳለበት ገልጸዋል። ለሚስተዋለው ችግር የመማር ማስተማሩ ዘዴና የልጆች የአስተዳደግ ሁኔታም ትልቅ አስተዋፅኦ ስላለው የትምህርት ሥርዓቱ መስተካከል እንዳለበት ጠቁመዋል። ‹‹ግዴታ ያለመብት ሊኖር ይችላል፤ መብት ግን ያለግዴታ አይኖርም›› የሚሉት የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር መምህሩ፤ ሞጋች ማህበረሰብ ባለመፈጠሩና መብቱን ብቻ በማየቱ አሁን ያለው ወጣት ከመሥራት ይልቅ የሌላውን ሀብት ሲያይ ዓይኑ የሚቀላ፤ ለእኔ ብቻ የሚል፤ የመንጠቅ መብት የተጠናወተው እየሆነ መምጣቱን አንስተዋል። በማያውቋቸው ሴረኞች በመንጋ አስተሳሰብ እየተመራ ንብረት ከማውደም አልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ ሰው ወደመግደሉ እየገባ ነው። በመሆኑም መንግሥት ወጣቱ ላይ መሥራት እንዳለበት ሲሉ መክረዋል። ማህበረሰቡ ልጆቹን ሲያሳድግ ሕግና ሥርዓት ባለው መልኩ ባለመሆኑ የሌላውን ዜጋ መብት ጭምር እየተጋፋ እንዲሄድ እንዳደረገው ጠቁመው፤ ይህም በማህበረሰቡ ዘንድ ሊሠራበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 19 ቀን 2012 ዓ.ም በ ጽጌረዳ ጫንያለው
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36043
29f39ddb1ee2fac50575b44ef2c0c3ec
48e84f4f2b42e9e1cc0d21726bd83ef8
አዎን! ግድቡ የኔ ነው
የማያረጅ ውበት የማያልቅ ቁንጅናየማይደርቅ የማይነጥፍ ለዘመን የፀናከጥንት ከፅንሰ አዳም ገና ከፍጥረትየፈሰሰ ውሃ ፈልቆ ከገነት።ነበር ያለችው እጅጋየው ሽባባው አባይ በሚለው ዜማዋ። እውነት አባይን በቅርበት ለተመለከተው የሆነ ውስጥ የሚነካ የተለየ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርግ ውብ የተፈጥሮ ፀጋ ነው። አባይ ጣና ላይ ሲፈስ ጥቁር ቀለሙን ፅፎ ውሃው ሳይቀላቀል ሲያልፍ፤ ከጣናም ከወጣ በኋላ በዝምታ የባህር ዳር ከተማን አቋርጦ ሲወርድ ለተመለከተው እንደልብ ወዳጅ ሆድ እያባባ የሚሰናበት ያህል ልብ ይነካል። ከዚህ ቀጥሎ ጢስ አባይ ሲደርስ ደግሞ ከላይ ተወርውሮ ሲወርድ፤ ከዛ ተመልሶ ደግሞ ጭስ የመሰሉ ትናንሽ የውሃ ነጠብጣቦችን ይዞ ሲመለስ ለተመለከተው ልብን በሃሴት ጮቤ የሚያስረግጥ ውበት ያሳያል።እንኳን ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ሀገራችንን ሊጎበኙ ለመጡ ቱሪስቶች ይቅርና ከማህፀኗ ለፈለቅኩት ለኔ እንኳን ሳይቀር ሀገሬ ድንቅ ምድር እንደሆነች የፈጣሪ ውብ ስራ አንደሆነች ማመልከቻ ነው። ስለአባይ ማንሳት ከጀመርኩ ማቆሚያ የለኝም። አሁን ደግሞ ከሁሉ የሚልቀው ጉባ ላይ የከተመው ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሀገር ኩራት እውነተኛ የኢትዮጵያዊነት ወኔን የሚቀሰቅስ ነው።የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ̋እንኳን ደስ አላችሁ የመጀመሪያው ዙር የግድቡ የውሃ ሙሌት ስራ በስኬት ተጠናቋል” ብለው ለህዝቡ ሲያበስሩ ልቤን ፈንቅሎ የወጣው ስሜት ከልቤ የምወደውን አባይ ሳሞጋግስ አንድውል አድርጎኛል።ከቢሮዬ ወጣ ብዬ የህዝቡን ሁኔታ መመልከት ጀመርኩ። በእግሬ ትንሽ እርምጃዎችን ከተራመድኩኝ በኋላ ሰብሰብ ብለው የሚጨዋወቱ የእድሜ ባለፀጎች አጠገብ ደረስኩ። ፈቃዳቸውን ጠይቄ መቅረፀ ድምፄን ወደእነርሱ ጠጋ አደረግኩ።አቶ ታደሰ ሲሳይ ይባላሉ፤ የ63 ዓመት እድሜ ባለፀጋ ናቸው። ጡረተኛ መሆናቸውን የሚናገሩት አባት የአንድ ወር የጡረታ አበላቸውን አዋጥተው የግድቡን እድገት እንደ ህፃን ልጅ ከስር ከስር ሲከታተሉ መቆየታቸውን ይናገራሉ። “ከባልንጀሮቼ ጋር በተገናኘን ቁጥር ግድቡ እንዴት ሆነ? ምን ሰማችሁ? እንባባል ነበር” የሚሉት አቶ ታደሰ” ዛሬ ቀኑ ደርሶ የመጀመሪያውን ውሃ ለመያዝ መቻሉ ከአድዋ የማይተናነስ ድል ነው ብለዋል። እኔ እንኳን ባልደርስበት ለልጅ ልጆቼ የሚተላለፍ ግድብ ላይ አሻራዬን ስላኖርኩ ኩራት ይሰማኛል” ብለዋል። አቶ ጌታነህ አበባው በአንድ የግል ኮሌጅ ውስጥ በጥበቃ ስራ የሚተዳደሩ አባት ናቸው “ፈጣሪ እድሜ ሰጥቶኝ ይሄን ለማየት በመቻሌ እራሴን እንደ እድለኛ እቆጥረዋለሁ” ብለዋል። “ከኛ እኩል ካላቸው ላይ ቆጥበው ይሄን ቀን ለማየት ሲጓጉ የነበሩ ጓደኞቻችን ዛሬ በህይወት የሉም። እነርሱን ከጎናችን ብናጣቸውም ግን በነበራቸው አቅም ታሪክ ፅፈው እንዳለፉ እያሰብን እንጽናናለን ሲሉ ተናግረዋል። በውትድርና ሙያ ሀገራቸውን ሲያገለግሉ የኖሩት አቶ ይደርሳል ብርሃኔ የሀገር ዳር ድንበርን በማስከበር ስራ ላይ ከኖሩበት ጊዜ በላይ የልማት አርበኛ ሆነው የቻሉትን ያህል ገንዘብ አዋጥተው የግድቡን መጠናቀቅ የድል ብስራት የሚጠባበቁበት ጊዜ እንደሚበልጥባቸው ገልፀው፤ በድሉም ወደር የሌለው ደስታ እንደተሰማቸው ይናገራሉ። ሌላዋ እናት ወይዘሮ ምህረት ልመንህ ይባላሉ፤ የ72 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ናቸው፤ በመንግስት ስራ ላይ ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ በጡረታ ጊዜያቸው ሀገርን በአንድ ድምፅ የሚያነጋግር ድል መገኘቱ የማይቆጣጠሩት ደስታ እንደሰጣቸው ተናግረዋል። ወይዘሮዋ እንደሚሉት ከሚመሩት እድር አባላቶቹን በማስተባበር የአስር ሺ ብር ቦንድ እንደገዙ አስረድተው፤ ህብረተሰቡ ከእለት ጉርሱ ቀንሶ ያዋጣው ገንዘብ ወደ ስራ ተቀይሮ ውጤት ላይ ሲደርስ ከማየት የበለጠ ደስታ የለም ብለዋል።የእድሜ ባለፀጎቹ በአንድ አይነት ሃሳብ ግድቡ የኛም የአረጋውያኑ መጦሪያ የልጆቻችን ሀብት ማፍሪያ በመሆኑ “ አዎ ግድቡ የኛም ነው” ብለን አስተዋጽኦችንን በህይወት እስካለን እንቀጥላለን ብለዋል።“አዎ ግድቡ የኔም ያንችም የእነሱም የሁላችንም ነው”።አዲስ ዘመን ሐምሌ 20/2012አስመረት ብስራት
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36098
71a28e2b89868a93b4cd4fd5a9c81423
bb1a45b513212f30ba42f2b4e35b6a58
የብልጽግና ጉዞውን ከዳር ለማድረስ አመራሩ ግንባር ቀደም ሚናውን መወጣት እንዳለበት ተጠቆመ
አዳማ ፡- የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ከዳር ለማድረስ አመራሩ ግንባር ቀደም ሚናውን መወጣት እንዳለበት የክልሉ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ አመለከቱ ። ጨፌ ኦሮሚያ በአምስተኛው ዙር የስራ ዘመኑ አምስተኛ ዓመት ጉባኤ የባለስልጣናትን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቋል። የክልሉ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ ትናንትና ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር፣ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ከዳር በማድረስ የክልሉንና የሀገሪቱ እድገት ማረጋገጥ የሚቻለው አመራሩ በትጋትና በቁርጠኝነት ሲሰራ እንደሆነ አመልክተዋል። በአሰራር ላይ እንቅፋት የሚሆኑ ጉዳዮችን አስቀድሞ በመለየት አፋጣኝ ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ የተናገሩት አፈ ጉባኤ፣ በተለይም የክልሉን ሰላምና ጸጥታ በማስከበር ምቹ የስራ ሁኔታ መፍጠር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነ አስታውቀዋል። ጨፌው በትናንትና ውሎው የክልሉን ጠቅላይ ኦዲት መስሪያ ቤት፣ ፍርድ ቤት እና የጨፌውን የ2012 ዓ.ም አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም አድምጧል። የጨፌው አባላት በኦዲት የተገኙ ውጤቶች የክልሉን እንቅስቃሴና እድገት የጎዱ መሆናቸውን ጠቅሰው ይህን በተመለከተ የተወሰዱ ርምጃዎች አለመጠቀሳቸው ሪፖርቱ ሙሉዕ እንዳይሆን አድርጎታል ብለዋል። በወቅቱም ፍርድ ቤቶች የህግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ እና ፍትህን እንዲያረጋግጡ በርካታ ሀሳቦች ተንጸባርቀዋል። በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች፣ የፍትህ ስርዓቱን በጥቅም ለማዛባት የሚሞክሩ የውጭ ደላሎችና የውስጥ ጉዳይ አስፈጻሚዎችን አደብ ማስገዛት እንደሚያስፈልግ ተመልክቷል። ጨፌው ለ2013 ዓ.ም በረቂቅ ደረጃ የቀረበውን የ 90 ቢሊዮን ብር በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ከዚህ ውስጥ 61 ነጥብ 2 ቢሊዮኑ ብር ከፌዴራል መንግስት የሚሰጥ ሲሆን 28 ነጥብ 8 ቢሊዮኑ ደግሞ ከክልሉ ገቢ የሚሰበሰብ መሆኑ ተገልጧል። በተጨማሪም ጨፌው የክልሉን የመጠጥ የውሃ ሃብት አጠቃቀም በተመለከተ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል እንዲሁም የ2012 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጁን በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል። ከቅዳሜ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ይህ ስብሰባ አስራ አንድ የሚደርሱ አጀንዳዎች የዳሰሰ ሲሆን፣ ትናንት ማምሻውን የባለስልጣናትን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቋል። በዚሁ መሰረት፤ ዶክተር መንግስቱ ሁሪሳ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ታረቀኝ ቡልቻ የመሬት አስተዳደር ሃላፊ፤ ወይዘሮ መስከረም ደበበ የኦሮሚያ ገቢዎች ባልስልጣን ሃላፊ፣ አቶ አህመድ ሰይድ ኢብራሂም የህብረት ሥራ ኤጀንሲዎች ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን ተሹመዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 20/2012በኢያሱ መሰለፎቶ በጸሀይ ንጉሤ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36097
18899017fbafa07d7201a1ede093d47e
b96ec47b8fd164aa94cfcfd109197b06
የግድቡን ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ለመጨረስ በዲፕሎማሲው መስክ በተጠናከረ መልኩ መንቀሳቀስ እንደሚገባ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፡- የህዳሴውን ግደብ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ በመጨረስ ወደስራ ለማስገባት በዲፕሎማሲው መስክ በተጠናከረ መልኩ መንቀሳ ቀስ እንደሚገባ ተጠቆመ። በመጀመሪያው ዙር የተያዘው ውሃ ለኢትዮጵያ የመደራደሪያ አቅም እንደ ሚፈጥር አስታወቁ።በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለምአቀፍ ትምህርት መምህር እና የትምህርት ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሞገስ ደምሴ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የህዳሴውን ግደብ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ አልቆ ወደስራ እንዲገባ በዲፕሎማሲው መስክ በተጠናከረ መንቀሳቀስ ይገባል።የዲፕሎማሲው ስራ እውቀቱ እና ክህሎቱ ባላቸው ሰዎች እንዲሳተፉ እና የሚፈለገው ውጤት እንዲመጣ ዲፕሎማሲው ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይጠይቃል ሲሉ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለምአቀፍ ትምህርት መምህሩ አስገነዘቡ።በግድቡ ዙሪያ የጀመርናቸውን ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ የዲፕሎማሲ ስራ በጣም ወሳኝ ነው የሚሉት መምህሩ ፤ ይፋዊም ይፋዊም ባልሆኑ የዲፕሎሚሲ ስራዎች አሁን ካለው ከፍ ባለ ደረጃ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ አመልክተዋል። በተለይም ይፋዊ ላልሆኑ የዲፕሎማሲ ስራዎች ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።ይፋዊ ያልሆነ ዲፕሎማሲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና ባህልን መሰረት ያደረገ እንደሆነ የሚያስረዱት መምህሩ ፤ ይህም ባንድ ወቅት ታይቶ የሚጠፋ ሳይሆን ተከታታይነት ባለው መንገድ በደንብ ተጠንቶ ሊተገበር እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡ በመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት ኢትዮጵያ የተከተለችው መንገድ ብሄራዊ ጥቅም አስገኝቷል የሚሉት መምህሩ ፤ ወደፊትም ለሚኖረው ድርድር ግብፅ እና እና ሱዳንም በአንድ ልብ ወደ ድርድሩ እንዲመጡ ያስገድዳቸዋል ብለዋል። በመጀመሪው ዙር የተያዘው ውሃ ለኢትዮጵያ የመደራደሪያ አቅም የፈጠረ እንደሆነ ገልጸዋል። ከአሁን በኋላ ያለውን ድርድር በጥሩ ሁኔታ እንዲጠ ናቀቅ የማስፈንጠሪያ አቅም መሆኑንም ገልጸዋል። የህዳሴ ግድቡን ፕሮጀክት ከአድዋ ጦርነት ጋር የሚመሳሰል የህዝብ አንድነት የታየበት መሆኑን ጠቁመው፣ ይህ አንድነት በዘላቂነት እንዲቀጥል መንግስት ተጠናክሮ መስራት እንደሚኖርበት መክረዋል። በሀገር ህልውና እና በዴሞክራሲ መካከል ያለውን ሚዛናዊነት የመጠበቅ አካሄድ መኖር አለበት የሚሉት ዶክተር ሞገስ፤ የሀገርን ህልውና ባገናዘበ መልኩ የዴሞክራሲው ምህዳሩን ማስፋት እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል። የውስጥ አለመግባባቶችና የውስጥ ሽኩቻዎች ለውጭ ሃይሎች ሀገራችንን እንዲያተራምሱ እድል የሚከፍት መሆኑን ገልጸው ፣ የዴሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት አንድነታችንን እያጠናከሩ መሄድ ይገባናል ብለዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 20/2012ሙሉቀን ታደገ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36104
983b0b0b72c2c587ffa212bcd1760b7e
2ba7283ba305ed5b50329e4cb74b87f3
«መንግሥት ከፍተኛ ገንዘብ እያፈሰሰ ሰው እንዲደባደብ መድረክ አያመቻችም»- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
 አዲስ አበባ፡- ‹‹በአገሪቱ የሚስተዋሉ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግሮች እልባት የማያገኙ ከሆነ መንግሥት ከፍተኛ በጀት እየመደበ ሰው የሚደባደብበት መድረክ አያመቻችም፤ አስፈላጊውን ዕርምጃ ይወስዳል» ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሳሰቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2011 በጀት ዓመት የመንግሥት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በትላንትናው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል። መንግሥት በአገሪቱ ለሚስተዋለው የስፖርታዊ የጨዋነት ችግር እልባት በመስጠት ረገድ በቀጣይ ምን ዓይነት አቅጣጫዎችን ሊከትል አስቧል የሚል ጥያቄም ከምክር ቤቱ አባላት ቀርቦላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጥያቄው በሰጡት ምላሽም «ስፖርት ባለባቸው አገራት የማይስተዋል ችግር፤ስፖርቱ በሌለበት በእኛ አገር እየተስተዋለ ነው፤ ስፖርት በባህሪው መንደር አይደለም፤የስፖርት ሜዳ ኳስ በጥበብና በዕውቀት ይንከባለልበታል እንጂ ፖለቲካ አይንከባለልበትም፤ይሁንና በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ፖለቲካ ስታዲየም ገብቷል» ብለዋል። በአገሪቱ አንድም ስታዲየም ያለው፤ማልያ ሸጦና በግሉ ስታዲየም ተጫውቶ ራሱን ችሎ የሚንቅሳቀስ ክለብ አለመኖሩን ጠቅሰው፣ እያንዳንዱ ከለብም መንግሥት እጁን ቢሰበስብ አንድ ወር መዝለቅ የማይችል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡ ክለቦች በመንግሥት ድጎማ እየተንቀሳቀሱ መልሰው መንግሥት ላይ ችግር ሲፈጥሩ እንደሚስተዋል አብራርተዋል። ነገሮች በዚህ ከቀጠሉ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ የበላይ አኳል /ፊፋ/ ሳይቀር ዕርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚችል ተናግረው፣ አስቀድሞ በርካታ ዕርምጃዎች እንደሚወሰዱ አመልክተዋል፡፡ በአህጉርም ሆነ በዓለም አቀፍ መድረኮች ተስፋ እያሳየ ላልሆነ ስፖርት መንግሥት ከፍተኛ ገንዘብ እያፈሰሰ ሰው እንዲደባደብ መድረክ  አያመቻችም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ‹‹ገንዘብም ወጣትም አይከስርም፤ነገሮች በጊዜ የማይስተካከሉ ከሆነም መንግሥት እጁን ይይዛል» ብለዋል። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ሰው ስታዲየም የሚገባው ድጋፍ ለመስጠት እንጂ የፖለቲካ አቋምና ብሄርን ለማንፀባረቅ ሲኮራረፍም ለመሰዳደብ አይደለም፡፡ ስፖርትን ከፖለቲካ አፅድቶ መጠቀም ያስፈልጋል። ስፖርትን ከብሄር፤ከፖለቲካ ነፃ ለማውጣትና ህግና ስርዓትን ተፈፃሚ በማድረግ ረገድም ፌዴሬሽኑ በርካታ ተግባራት ማከናወን ይጠበቅበታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገሪቱ ስፖርት ላይ ከሚስተዋሉት የጨዋነት ችግሮች በተጓዳኝ በወር አንድ ቀን የሚካሄደው የማስ ስፖርት በተለይ ሰዎችን ከማቀራራብ፤ለጤና የሚወጣ በጀት በመቀነስና የተነቃቃ ትውልድ በመፍጠር ረገድ የሚያበረክተው ፋይዳ ጉልህ መሆኑን አመላክተዋል። በተመረጡ ቦታዎች ከመኪና ፍሰት በፀዳ ሁኔታ አዲስ አበባ ላይ የሚካሄደው ስፖርታዊ ሁነትም፤በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ብቻ መወሰን እንደሌለበት ጠቅሰው፣ በሌሎች አገራት እንደሚካሄደው ጎን ለጎን ጥበባዊ ትዕይንቶችን ማቅረብ እንዳለበትም አስረድተዋል።አዲስ ዘመን ሰኔ 25/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13411
162f13481563279e70af61e9a8d64858
aff080184d2729ee21ea6bedba8739ad
በዳይመንድ ሊጉ ኢትዮጵያውያን አልቀናቸውም
ሰባተኛ ዙር የዳይመንድ ሊግ ውድድር በሳምንቱ መጨረሻ በአሜሪካ ዩጂን ከተማ በተለያዩ ርቀቶች ሲካሄድ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም። በተለይ ተጠባቂ በነበረውና በርካታ ስመጥር አትሌቶችን ባሳተፈው የሴቶች ሦስት ሺ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሰፊ የማሸነፍ ዕድል ቢሰጣቸውም ውጤቱ ግን የተገላቢጦሽ ሆኗል። ያልተጠበቁ አትሌቶች ከፊት ሲሆኑ ተጠባቂዎቹ ወደኋላ በቀሩበት በሴቶች መካከል የተካሄደውን የሦስት ሺ ሜትር ውድድር ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና ለኔዘርላድ የምትሮጠው ሲፋን ሃሰን ቀዳሚ ሆና አጠናቃለች። አትሌቷ ውድድሩን ለማጠናቀቅ የወሰዳባት ሰዓት 8 ደቂቃ ከ18 ሴኮንድ ከ49 ማይክሮ ሴኮንድ ሆኗል። ይህም የግሏና የውድድሩ የዓመቱ ምርጥ ሰዓት ሆኖ ተመዝገቧል። አትሌቷ ከቀናት በፊት በሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ ርዕሰ መዲና ራባት በተካሄደው የዳይመንድ ሊጉ ስድስተኛው ዙር የ1ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር አሸናፊዋን ገንዘቤ ዲባባ ተከትላ በሁለተኝነት ውድድሩን ማጠናቀቋ ይታወሳል። የሦስት ሺ ሜትር ውድድሩን ሲፋንን ተከትላ ጀርመናዊቷ ኮንስታንዜ ሃልፈን ሁለተኛ ወጥታለች። 8 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ ከ07 ማይክሮ ሴኮንድ ውድድሩን ጨርሳ የገባችበት ሰዓት ሆኗል። ኢትዮጰያዊቷ አትሌት ለተሰንበር ግደይ ሦስተኛ ሆና አጠናቃለች። ውድድሩን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ሰዓትም 8 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ ከ27 ማይክሮ ሴኮንድ ነው፤ ይህም የሯሷ ምርጥ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦላታል። በውድድሩ ሰፊ የማሸነፍ ግምት አግኝታ የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ አራተኛ ስትሆን 8 ደቂቃ ከ21 ሴኮንድ ከ29 ማይክሮ ሴኮንድ የገባችበት ሰዓት ሆኗል። ገንዘቤ ከቀናት በፊት ሞሮኮ ርዕሰ መዲና ራባት በተካሄደው የዳይመንድ ሊጉ ስድስተኛው ዙር የ1ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር 3 ደቂቃ ከ55 ሴኮንድ ከ47 ማይክሮ ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ቀዳሚ ሆና ማጠናቀቋ ይታወሳል። አትሌት ገንዘቤ እ.አ.አ በ2015 በፈረንሳይ ሞናኮ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ የ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር 3 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ ከ8 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት በርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት መሆኗም አይዘነጋም። በውድድር ዓመቱ የአምስት ሺ ሜትር ውድድርን በበላይነት ተቆጣጥራ የቆየችውንና በ8 ደቂቃ ከ23 ሴኮንድ ከ60 ማይክሮ ሴኮንድ የሦስት ሺ ሜትሩ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤት የነበረችው ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ በዩጂን ስድስተኛ ሆና አጠናቃለች። ኢትዮጵያውያኑ ፋንቱ ወርቁ ዘጠነኛ፤ሰንበሬ ተፈሪ አስራ አንደኛ፤ ሃዊ ፈይሳ አስራ ሦስተኛ ሆነዋል። ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ውድድር ተመልሳ የመጀመሪያ ፉክክሯን ያደረገችውም የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮኗ ዓለም የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤቷ ኢትዮጵያዊት አትሌት አልማዝ አያና ውድድሩን 18ተኛ በመሆን አጠናቃለች። አልማዝ አያና ከሁለት ዓመት ቀድሞ በህንዱ ደልሂ ግማሽ ማራቶን ከተሳተፈች በኋላ በውድድሮች ላይ ሳትሳተፍ መቋየቷ ይታወሳል። ውጤቷ ባያምርም አትሌቷ ከረጅም ጊዜ የጉዳት ቆይታ በኋላ ተመልሳ ያሳየቸው አቋም ለቀጣይ ውድድር ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን በርካቶች ተስማምተውበታል። የሦስት ሺ ሜትር ፈጣን ሰዓት 8 ደቂቃ ከ06 ሴኮንድ ከ11ማይክሮ ሴኮንድ ሆኖ መመዝገቡ ይታወቃል። የሰዓቱ ባለቤትም ቻይናዊቷ ጁዋንግ ዋንግ ስትሆን ያስመዘገበችውም እኤአ 1993 ላይ በተካሄደ ውድድር ነው። ጠንከር ያለ ፉክክር የተስተዋለበትና በወንዶች መካከል የተካሄደው የሁለት ማይል ውድድር በዩጋንዳዊው አትሌት ጆሹዋ ቼፕቴጊ ቀዳሚነት መቋጫውን አግኝቷል። አሜሪካዊው ፖል ቺሊሞ ሁለተኛ ሲሆን ኢትዮጵያዊው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ደግሞ ሦስተኛ ሆኖ ገብቷል። ውድድሩን ለማጠናቀቅ የወሰደበት ሰዓትም፤8ደቂቃ ከ08 ሴኮንድ ከ69 ማይክሮ ሴኮንድ የገባበት ሰዓት ሆኖ ተመዝገቧል። ሰባተኛ ዙር የዳይመንድ ሊግ ውድድር ሌላኛው መርሐ ግብርም በሴቶች መካከል የተካሄደው የስምንት መቶ ሜትር ውድድር ነው። ውድድሩም፤ከፆታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (አይኤኤኤፍ) ጋር ውዝግብ ውስጥ የቆየችውና በመጨረሻ ወደ ውድድር የተመለሰችው ደቡብ አፍሪካዊቷ አትሌት ካስተር ሴሜኒያ አሸናፊነት መቋጫውን አግኝቷል። የሁለት ኦሎምፒክና ሦስት የዓለም ሻምፒዮና ባድል የሆነችው ሴሜኒያ፤ በስምምንት መቶ ሜትር ለአራተኛ ጊዜ ያለመሸነፍ ጉዞዋን በማስቀጠሏም አድናቆትን አግኝታለች። በዚህ ርቀት ጥሩ ብቃት በማሳየት ላይ የምትገኘው ሀብታም ዓለሙ አምስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። በአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና ሰሜን አሜሪካ በሚገኙ 14 ከተሞች የሚካሄደው የ2019 የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለስምንተኛ ጊዜ በስዊዘርላንድ ሉዛን የፊታችን ዓርብ ይካሄዳል። ውድድር በቀጣይም፤በሞናኮ፤ ለንደን፤በርሚንግሃም ኸፓሪስና ዙሪክ ቀጥሎ በጳጉሜ መጀመሪያ በቤልጂየም መዲና ብራሰልስ በሚካሄደው ውድድር የሚጠናቀቅ ይሆናል። የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በዘንድሮው የዳይመንድ ሊግ ውድድር በአጠቃላይ የስምንት ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ሽልማት ማዘጋጀቱ ይታወሳል። በሁለቱም ጾታዎች በተመሳሳይ በ16 የተለያዩ የውድድር ዓይነቶች በእያንዳንዱ ርቀት የአጠቃላይ አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶች የ50 ሺህ ዶላርና የዳይመንድ ሽልማት ያገኛሉ። ከዚህም በተጓዳኝ በእያንዳንዱ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ የ100 ሺህ ዶላር ሽልማትም ተዘጋጅቷል። በተጨማሪም በእያንዳንዱ ርቀት አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶች ከመስከረም 17 እስከ 26 ቀን 2012 ዓ.ም በኳታር መዲና ዶሃ ለሚካሄደው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያለማጣሪያ የሚያልፉ ይሆናል። አዲስ ዘመን ሰኔ 25/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13413
b91e0ab75a612557fc064ad725e082ec
e5b6c5071d41efd8a45bc242365270c3
የክብደት ማንሳት ብሔራዊ ቡድኑ በመጪው ወር ወደ ልምምድ ይገባል
በሞሮኮ አዘጋጅነት 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ ድምቀት ተደርገው ከሚቆጠሩ የስፖርት ዓይነቶች የክብደት ማንሳት ስፖርት ይጠቀሳል። ከፍተኛ ፉክክር በሚታይበት ስፖርት ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች ትሳተፋለች። የኢትዮጵያ ክብደት ማንሳት እና ሰውነት መገንባት ፌዴሬሽን በመድረኩ ሀገሪቱን የሚወክሉ ተጫዋቾችን ለመምረጥ ከሰኔ 19 እስከ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በጃን ሜዳ ሀገር አቀፍ ሻምፒዮና አካሂዷል። ሻምፒዮናው ወንዶች ከ55 እስከ 102 ኪሎ ግራም በሴቶች ከ45 እስከ 71 ኪሎ ግራም ባሉት የክብደት ዘርፎች ተካሂዷል።በአህጉር አቀፍ ውድድሩ ሀገርን የሚወክሉ ተጫዋቾችን ለመመልመል በተካሄደው ሻምፒዮና ላይ የትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ሐረሪ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ተሳታፊ ሆነዋል። አጠቃላይ የተሳታፊ ቁጥሩም በወንድ 40 በሴት 25 በድምሩ 65 ተወዳዳሪዎች ነበሩ። ሻምፒዮናው ለአራት ተከታታይ ቀናት በድምቀት ሲካሄድ ቆይቶ ባሳለፍነው ቅዳሜ በተካሄዱ አራት የፍጻሜ ውድድሮች ተጠናቋል። በመዝጊያው ዕለት አራት የፍጻሜ ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን፤ በወንዶች 102 ኪሎ ግራም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተወዳዳሪ ቢኒያም አክሊሉ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን ተመስገን ቶማስ ከኦሮሚያ ክልል የብር ሜዳሊያ አግኝቷል። በ96 ኪሎ ግራም ወንዶች የኦሮሚያ ክልሉ አዲሱ አለማየሁ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያገኝ ምህረትአብ በቀለ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፣ ሃይልነት አወቀ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ያገኙ ተወዳዳሪዎች ናቸው።በተጨማሪም የ89 ኪሎ ግራም ወንዶች የሐረሪ ክልሉ ተወዳዳሪ ሳሙኤል በዛብህ፤ መስፍን ኃይሉ ከኦሮሚያ ክልል እምነት ደጉ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የብር እና የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘት ችለዋል። በሴቶች ደግሞ በ71 ኪሎ ግራም የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ተወዳዳሪዋ ምንተአምር ታደሰ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች። ከትግራይ ክልል የመጣችው ቤተልሄም መሳይ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ስታገኝ ፤ የአዲስ አበባዋ አበባ ማዳ ሦስተኛ በመሆን የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።በከፍተኛ ድምቀት ታጅቦ የተጀመረው ሻምፒዮና ድምቀቱን ጠብቆ በአጠቃላይ ውጤት በወንዶች የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በአራት ወርቅ ሜዳሊያ፣ በሴቶች የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁለት ወርቅ እና በአንድ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነዋል። ድሬዳዋ ከተማ የስፖርታዊ ጨዋነት የጸባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።የኢትዮጵያ ክብደት ማንሳት እና ሰውነት መገንባት ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበበ አሽኔ እንደገለጹት፤ የሻምፒዮናው አላማ በነሐሴ ወር 2011 ዓ.ም በሞሮኮ ርዕሰ ከተማ ራባት በሚካሄደው 12ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ ነው። በመላው አፍሪካ ጨዋታ በሚኖረን ተሳትፎ ውጤትና ሜዳሊያዎችን ለማስመዝገብ ብቻም ሳይሆን፤ ውድድሩ ሀገራችን በስፖርቱ በምን ደረጃ ላይ እንዳለች የምንለካበት መልካም አጋጣሚም ጭምር መሆኑን አስረድተዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በነበረው ሻምፒዮናው ላይም ብሔራዊ ቡድኑን የሚወክሉ ጠንካራ ተወዳዳሪዎች የታዩበት መሆኑን ተናግረዋል።በሁለቱም ጾታዎች በሻምፒዮናው ጥሩ ተፎካካሪ የሆኑና በአፍሪካ ከሚገኙ ተወዳዳሪዎች ተቀራራቢ ውጤት ያስመዘገቡ ተወዳዳሪዎች ለመላው አፍሪካ ጨዋታ ይመረጣሉ። ፌዴሬሽኑ ያስቀመጠውን መስፈርት መሠረት በማድረግ በሻምፒዮናው ላይ በተመዘገበው ውጤት ተጫዋቾቹን በቅርብ ቀናት በመምረጥ ይፋ የሚደረግ ይሆናል። አስፈላጊውን መስፈርት እና መለኪያ ያሟሉ በወንድ አምስት፣ በሴት ሁለት ተወዳዳሪዎች ተመርጠው በፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት ክልሎች እንዲያውቁት እንደሚደረግና ከሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ልምምድ እንደሚገቡም አስታውቀዋል።በሻምፒዮናው ተሳታፊ በኩል ደግሞ ከተሳትፎ አንጻር የተሻለና ጥሩ ፉክክር እንደታየበት መሆኑን ተናግረዋል። የሻምፒዮናው መዘጋጀት ተወዳዳሪዎች ያሉባቸውን ጉድለቶች ለመሙላት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል። በአገር አቀፍ ደረጃ ስፖርቱን የሚመራው ፌዴሬሽን የውድድር አማራጮችን ከማስፋት አኳያ እንዲሁም ሥልጠናዎች ከማዘጋጀትና ክልሎች የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁስ ከማሟላት አንጻር ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠበቃል። ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች አንጻር ሲታይ ስፖርቱ ላይ ገና ብዙ መስራት እንደሚጠበቅና ለዚህም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በጋራ መስራት እንዳለባቸው አመልክተዋል።በሻምፒዮናው የትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ የሐረሪ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉበት ነበር። በሌላ በኩል የአማራ፣ ሶማሌ፣ አፋር እና ጋምቤላ ክልሎች በበጀት እጥረት እና በዝግጅት ማነስ በሻምፒዮናው ሳይሳተፉ ቀርተዋል።አዲስ ዘመን ሰኔ 26/2011 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13491
e8c645a5af45d9eb2cab4794ce7cd548
3c7a29db0e8079a9638229cc8bcafacb
በዓለማችን ታላላቅ ሊጎች ጥቋቁር ኮከቦች
አፍሪካ የምርጥ ደጋፊዎች እንብርት የመሆኗን ያህል የድንቅ ተጫዎቾች ባለሀብትም ነች። ከልጅነት ጀምሮ በየመንደሩ ባዶ እግራቸውን እግር ኳስ የሚጫወቱ፤ ራሳቸውን ለኳስ ፍቅር አሳልፈው የሰጡና ለእግር ኳስ ፍቅር የሚታመኑ በርካታ ተጫዋቾችን ወልዳለች። በድንቅ የእግር ኳስ ጥበብ የተካኑ በሙያቸው ብዙዎችን ያስደመሙ፣ ከአህጉሪቱም ተሻገረው በታላላቅ ሊጎች ድንቅ ችሎታቸውን ያስመሰከሩ ጥበበኞችንም አፍርታለች። እኤአ1992/93 የውድድር ዓመት በፈረንሳዩ ኃያል ክለብ ማርሴይ ከነገሠው ጋናዊው አቢዲ ፔሌ፤ አንስቶ እ ኤ አ በ1995 በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት ባሎንዶር ክብርን እስከተቀዳጀው ጆርጅ ዊሃ፤አፍሪካውያን የኳስ ጠቢባን በተለያዩ የአውሮፓ መድረኮች ችሎታቸውን አሳይተዋል። በአርሰናል ቤት አይረሴ ዘመን ያሳለፈው ናይጄሪያው ኑዋንኮ ካኑ፤ በእንግሊዝ ምድር በቦልተን ወንደረረስ የነገሠው ጄጄ ኦካቻ፤በጀርመኑ ኃያል ክለብ ባየር ሙኒክ በርካቶችን ያስጨበጨበው ጋናዊው ሳሚ ኩፎር እንዲሁም በባርሴሎናና ኢንተር ሚላን ድንቅ የነበረው ካሜሮናዊው ሳሙኤል ኤቶና በቼልሲዎች መለያ ድንቅና ተአምራዊ ገድሎችን የሠራው አይቮሪኮስታዊው ዲዲየር ድሮግባ ተጠቃሾች ናቸው። የሚገባቸውን ያህል ክብርና እውቅና ማግኘት ባይችሉም በአሁኑ ወቅት የአህጉሪቱ እግር ኳስ ጥበበኞች በዓለማችን ሁሉም ማዕዘናት በተለያዩ ታላላቅ ሊጎች በመጫወት አገራቸውንና ስማቸውን ከፍ አድርገው እያስጠሩ ይገኛሉ። ብቃት ሲለካ የቆዳ ቀለም የልዩነት ተረኮች ስህተት ስለመሆናቸው በማስመስከር፤ የማንነት ሚዛንን አመጣጥነው የኃያልነት ትርጓሜ የቀየሩ፤በተለይ በፊት መስመር ተሰላፊነት ሚና የሚጫወቱ ውድ የአህጉሪቱ ኮከቦች፤ ክለቦችን ከሽንፈት መታደግና አሸናፊ ከማድረግ ባለፈ ሻምፒዮን እንዲሆኑ ማስቻላቸውን ቀጥለዋል። በተለይ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት የአህጉሪቱ ኮከቦች ከደመቁባቸው ታላላቅ የእግር ኳስ መድረኮች መካከል ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቀዳሚ ሆኖ ይጠቀሳል። የአርሰናሉ የፊት መስመር ተጫዋች ፔር-ኤሜሪክ ኦባሚያንግ፤የሊቨርፑሎቹ ሞህ ሳላህ እና ሳዲዮ ማኔ፤በውድድሩ የካበተ ልምድ ካላቸው ከማንችስተር ሲቲው ሰርጂዎ አጉዌሮና ከቶተንሃሙ ሃሪ ኬን በላይ ከፍተኛ ግብ በማስቆጠር የሊጉ የኮከብ ግብ አግቢነት ክብርን በጋራ ተቀዳጅተዋል። በተለይ በጀርመኑ ቦርሲያ ዶርቱመንድ ቆይታው ምርጥ የፊት መስመር ተጫዋች መሆኑን በሚገባ አሳምኖ ያረጋገጠው ጋቦናዊው አጥቂ ፔር-ኤሜሪክ ኦባሚያንግ፤ በ56 ሚሊየን ፓውንድ ከሁለት ዓመት በፊት መድፈኞቹን ከተቀላቀለ ወዲህ ድንቅ ችሎታውን እያሳየ ይገኛል። ተጫዋቹ በወቅቱ የጀርመን ቆይቷውን ለመቋጨት መወሰኑ ስህተትና እንደ ቡንደስሊጋው በፕሪሚየር ሊጉ ግብ ማስቆጠር ከባድ ሊሆንበት እንደሚችል በርካቶች ቢገምቱም ተጫዋቹ ግን ይህ እሳቤ የተሳሳተ ስለመሆኑ ለማረጋጋጥ ብዙም አልተቸገረም። አርሰናል ከኤቨርተን ጋር ባደረገው ጨዋታ በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ የመድፈኞቹን መለያ መልበስ የቻለው ኦባሚያንግ፤ ክለቡ ጨዋታውን 5ለ1 ሲያሸንፍ በመጀመሪያ ጨዋታው የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል። በውድድር ዓመቱ አስር ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ አራት ለግብ ያለቀላቸው ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ ማጋራት ችሏል። ተጫዋቹ በተለይ በ2018/19 የእንግሊዝ ፐሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመት ድንቅ ግብ የማግባት ችሎታ እንዳለው ይበልጥ ያስመሰከረ ሲሆን፤ለመድፈኞቹ በ36 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 22 ግቦችን አስቆጥሯል። አምስት ለግብ ያለቀላቸው ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። ተጫዋቹ ያስቆጠራችው ግቦችም የሊጉን ኮከብ ግብ አግቢነት ክብር እንዲቀዳጅ አስችለውታል። በአሁኑ ወቅትም በዓለማችን ታላቁ ሊግ የአገሩንና የራሱን ስም ከፍ አድርጎ እያስጠራ ይገኛል። ሌላኛው በአሁኑ ወቅት በታላቁ ሊግ ድንቅ ችሎታቸውን በማስመሰከር ላይ የሚገኘው የአህጉሪቱ ፍሬ ጥበበኛው ሰይዲ ማኔ ነው። ከ2014/15 የውድድር ዓመት ጀምሮ በሊጉ ባለሁለት አሃዝ ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ የማይሳነው ሴኔጋላዊው ኮከብ ማኔ፤ በተለይ በ2016 ከሳውዝሃፕተን ሊቨርፖሎችን ከተቀላቀለ ወዲህ ስሙ እጅጉን ከፍ ብሎ መሰማት ጀምሯል። በሜዳ ላይ ታታሪነቱና የተቃራኒ ቡድን ተከላካዮች በማስጨነቅ የሚታወቀው ሴኔጋላዊው ኮከብ፣ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከክለቡ ጋር የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ በማንሳት ማጣጣም የቻለ ሲሆን፣ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ግብ አግቢነት ክብርን በመቀዳጃት የወርቅ ጫማውንም ተሸልሟል።ብቃቱንና አስተዋፆኦውን በየጊዜው እያጎለበተ የሚጓዘው ሴኔጋላዊ ተጫዋች፤የብቃቱንና የአስተዋፅኦውን ያህል ባይዘመርለትም ሊጉን ከሚያደምቁት ድንቅ አፍሪካውያን ተጫዋቾች አንዱ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት በድንቅ የእግር ኳስ ጥበብ ችሎታ ከተካኑ እና በሙያቸው ብዙዎችን ካስደነቁ አፍሪካውያን ኮከቦች መካከል በግንባር ቀደምትነት ስሙ ይነሳል። ግብፃዊው ሞሃመድ ሳላህ። የ26ዓመቱ ግብፃዊው ኮከብ በመጀመሪያ ዓመት የአንፊልድ ቆይታም በ38 ጨዋታዎች 32 ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ይህም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሠላሳ ግቦች በላይ በማስቆጠር በታሪክ ብቸኛው ተጫዋች እንዲሆን አስችሎታል። ምትሐተኛው ግራ እግር ባሳልፈነው የውድድር ዓመት መጀመሪያ ደካማ የሚባል አቋም ማሳየቱን ተከትሎ «የአንድ ውድድር ዓመት አንበሳ» በሚል በበርካታ ወገኖች ትችት ቢሰነዘርበትም፣እያደር ብቃቱን በማረጋገጥ በብቃቱ የማይዋዝቅ ስለመሆኑ አስመስክሯል። በእግር ኳስ ጥበብ ልህቀቱ ዓለምን ያስደመመውና ሁልጊዜም ግብ ማስቆጠር የማይሳነው ሳላህ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ክለቡ ሊቨርፑል የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ከፍ አድርጎ እንዲስም የላቀ ሚና ተጫውቷል። በግሉም ፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ግብ አግቢነት ክብርን በመቀዳጃት የወርቅ ጫማውን አጥልቋል። በአሁኑ ወቅት በዘመናዊ እግር ኳስ ከሚጫወቱ ከፊት መስመር ተጫዋቾች ተመራጭ መሆኑ የሚመሰከርለት ሳላህ፤ የእግር ኳስ ጥብብ ችሎታውን ያህል ዓለም ስለእርሱ የምትዘምረው በጣም ዝቅ ባለ ድምፅ ስለመሆኑም ይገለጻል። ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውጪ በአሁኑ ወቅት በሌላ ማዕዘን በማንፀባረቅ ላይ ከሚገኙ ጥቁር ኮከቦች መካከል ስሙ ጎልቶ የሚነሳው ሌላኛው ተጫዋች ኒኮላስ ፔፔ ነው። በፈረንሳዩ ክለብ ሊል ድንቅ ተጫዋች መሆኑን እያስመሰከረ የሚገኘው አይቮሪኮስታዊው ኮከብ ፤ባሳለፍነው የውድድር ዓመት 19 ግቦችን ሲያስቆጥር፤11 ለግብ የተመቻቹ ኳስችን ለቡድን አጋሮቹ ማቀበል ችሏል። «እርሱን በተቃራኒ መለያ መግጠም እጅግ አድካሚና ፈታኝ ስለመሆኑ ብዙዎች የሚመሰክሩለት የ23 ዓመቱ ፔፔ፤ክለቡ በፈረንሳይ አንደኛ ሊግ በሁለተኝነት እንዲጨርስ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። በፈረንሳይ ሊግ አንድም «ምርጡ የአፍሪካ ተጫዋች ነህ» የሚል ክብር ተቀዳጅቷል። የተጫዋቹ ወቅታዊ ብቃትም የበርካታ ወገኖችን አድናቆት እንዲያገኝ ከማስቻሉ በተጓዳኝ የታላላቅ የአውሮፓ ክለቦችን ቀልብም እንዲሰርቅ አርጎታል። ተጫዋቹም በቀጣዩ የውድድር ዓመት ወደ እንግሊዝ በማቅናት ሊቨርፖሎችን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል። ሞሮኮአዊው ሀኪም ዚያችም በአሁኑ ወቅት አፍሪካ ምርጥ ተጫዋቾች ባለቤት ስለመሆኗ እያስመስከረ የሚገኝ ወጣት ኮከብ ነው። በሆላንዱ ክለብ አያክስ በሚያሳየው ድንቅና ውበት ያለው እግር ኳስ ችሎታው የበርካቶችን ቀልብ በቀላሉ ያገኘው ዚያች፡፡ ክለቡ የኤርዲቪዜዎን ዋንጫ እንዲያነሳ የላቀ ሚና ተጫውቷል። ባሳለፍነው የውድድር ዓመት 21 ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ 24 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ አጋርቷል።ይህም የክለቡ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋችነት ክብርንም አስግኝቶለታል። አሁኑ ላይ በርካታ ክለቦች ተጫዋቹን በዓይነ ቁራኛ በመከታተል የተጠመዱ ሲሆን፤ ተጫዋቹም ስሙ ከአርሰናል ጋር በጥብቅ እየተዛመደ ይገኛል። ሴኔጋል ዳካር ውስጥ የተወለደው የ27 ዓመቱ ተጫዋች ምቤይ ዲያን በቱርክ ሊግ ገናና ስሙን እየገነባ ነው። በውድድር ዓመቱ 29 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 30 ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ የቻለ ሲሆን፣ ይህ የግብ የማስቆጠር ብቃቱ ሲመዘንም በእያንዳንዱ 81 ደቂቃ አንድ ግብ ማስቆጠር እንደሚችል አረጋግጦለታል። በቱርክ ሱፐር ሊግ ለጋላታ ሰራይ የሚጫወተው ኮከብ፤ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ክለቡ ካስቆጠራቸው ግቦች መካከል 45 በመቶ የሚሆኑት ከእርሱ እግር ስር የወጡ ስለመሆናቸውም ተመላክቷል። ተጫዋቹ ለአራት ዓመት የሚያቆየው የውል ስምምነት ከኢስታንቡሉ ኃያል ክለብ ጋር ቢኖረውም፣ በርካታ አውሮፓውያን ኃያላን ክለቦችም ተጫዋቹን የግላቸው ለማድረግ አሰፍስፈዋል። በጀርመን ቡንደስሊጋ ለሆፈኒየም የሚጫወተው አልጄሪያዊው ኢሻክ ቤልፎዲልም፣ በአሁኑ ወቅት በድንቅ እግር ኳስ ችሎታቸው ዓለምን ማነጋጋር ከጀመሩ አፍሪካውያን ኮከቦች አንዱ ነው። ተጫዋቹ ባሳለፈነው የውድድር ዓመት ለክለቡ 28 ጨዋታዎች ላይ የመሰለፍ ዕድል አግኝቶ 16 ግቦችን ከመረብ አዋህዷል። አምስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለጓደኞቹ አመቻችቶ አቀብሏል። የተለያዩ የሜዳ ላይ ኃላፊነቶችን በብቃት የሚወጣውና «የትም ቦታ ተሰልፎ ቢጫወት ግብ ማስቆጠር አይከብደውም» የሚባልለት ኮከብ፤በቡንደስሊጋው ከፍተኛ ግብ ካስቆጠሩ ሦስት ተጫዋች መካካል ስሙን አፅፏል። በቤልጂየም ሊግ ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ላይ የሚገኘው ሌላኛው አፍሪካዊ ኮከብ ማብዋና ሳማታ ነው። ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ውስጥ የተወለደው ተጫዋቹ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ለከለቡ 28 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 20 ግቦችን በስሙ አስመዝገቧል። የቀድሞው የአርሰናሎች ምልክት ቴሪ ዳንኤል ሄነሪ አድናቂ የሆነው ተጫዋቹ፣ በቅርቡ በቤልጂም ሊግ ከተከሰቱ አፍሪካውያን ተጫዋቾች መካከል ‹‹አንተ ምርጡ ነህ» በሚል የኮከብነት ክብር ማግኘት ችሏል። የሚገባቸውን ያህል ክብርና እውቅና ማግኘት ባይችሉና በምዕራባዊያኑ ተፅእኖ ስር ለመደበቅ ቢገደዱም በአሁኑ ወቅት እነዚህ የአህጉሪቱ እግር ኳስ ጥበበኞች በዓለማችን ታላላቅ ሊጎች አገራቸውንና ስማቸውን ከፍ አድርገው እያስጠሩ ይገኛሉ።አዲስ ዘመን ሰኔ 25/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13415
0a32546d2dc29b98922abdf668579bd4
9a596f852833f52f5e8b5742265b6392
ጥንቃቄን የሚሹት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለቱ ሳምንታት
የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፍጻሜውን ሊያገኝ የሁለት ሳምንታት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል። ሊጉ ከወርሃ ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ዘጠኝ ወራት ቆይታን አድርጓል። በብዙ ውጣ ውረዶች በመታጀብ ከፍጻሜ አፋፍ ላይ መድረስ ችሏል። በውድድር ዓመቱ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር ተያይዞ የነበረው ውጥንቅጥ የስፖርቱን መልክ አጉድፈውት የተጓዙ ሳንካዎች ነበሩ። በስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል እየማቀቀ ያለው እግር ኳሱ በተለይ በዘንድሮው የውድድር መድረክ አውዱን ቀይሮ የፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃ እስከመሆን የተጓዘም ነበር።በእግር ኳስ ጨዋታዎች የተዋጣለት ፉክክር ከመመልክት ይልቅ ወደ አምባጓሮና ወደ ግጭት የሚያመሩ ስሜቶች በስፋት ተንጸባርቆበታል። የስፖርቱን ህልውና ፈታኝ ምዕራፍ እስከ ማድረስ በተጓዘ ችግር ውስጥ በመሆን ለሻምፒዮናነት የሦስት ክለቦች እጆች ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎችን ይጠብቃሉ። እነርሱም የዘንድሮው የሊጉ አዳጊ ክለብ መቐለ ሰባ እንደርታ፣ ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና ናቸው።የመሪነቱን ጉዞ ፋሲል ከነማ እና መቐለ ሰባ እንደርታ በእኩል 53 ነጥብ በመያዝ በግብ ክፍያ ተበላልጠው መሪና ተመሪ ሲሆኑ፤ ሲዳማ ቡና በ52 ነጥብ ጥሩ ተከታይ ሆኗል። የውድድር ዓመቱን ሻምፒዮናነት ክብርን ለማግኘት በሚደረገው ግስጋሴ ላይ አዲስ መልክ እንዲኖር ያደረገው 28 ኛው ሳምንት፤ በተለይ ፋሲልና መቐለ ከነማን ፍጥጫ ከፍ እንዲል ያደረገው ነበር። በ28 ኛው ሳምንት ፋሲል ከነማ ነጥብ መጋራቱን መቐለ ደግሞ ማሸነፍን ተከትሎ ለሻምፒዮናነት የሚደረገው ፍጥጫ እንዲካረር ያደረገው አጋጣሚ ተፈጥሯል።ባሳለፍነው እሁድ ወደ አዳማ ያቀናው ፋሲል ከነማ ከባለሜዳው አዳማ ጋር 1 ለ 1 በመለያየት አንድ ነጥብ በመያዝ ተመልሷል። ፋሲል በጨዋታው ከእረፍት በፊት ሙጂብ ቃሲም በፍጹም ቅጣት ምት በማስቆጠር የሻምፒዮናነት ክብር ግስጋሴው ከፍ ያለ ተስፋ የታየበት ቢመስልም፤ባለሜዳዎቹ አዳማ ከነማ ከእረፍት መልስ ቡልቻ ሱራ በግንባሩ በመግጨት አቻ አድርጓቸዋል። ይሄንኑ ተከትሎ የተጠበቀው የፋሲል ከነማ ተስፋ ሊናድ ግድ ብሎታል።ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ነጥቡን ወደ 53 ከፍ ማድረግ ቢችልም፤ የመቐለ ሰባ እንደርታ ደቡብ ፖሊስን መርታትን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ሻምፒዮናነቱን ቀድሞ ለማረጋገጥ የነበረው ግስጋሴ ተጨናግፎበታል። በ28 ኛው ሳምንት ደቡብ ፖሊስን በሜዳቸው ያስተናገዱት መለቐ ሰባ እንደርታዎች 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት በማሸነፍ ሦስት ነጥብ ማግኘት የቻለ ሲሆን፤ ከፋሲል ከነማ ጋር የነበረውን የነጥብ ልዩነት እኩል በማድረግ የሻምፒዮናነት ግስጋሴውን እጅግ አጓጊ መልክ እንዲኖረው አስችሏል። ክለቡ በጨዋታው ያስቆጠራቸውን አራት ግቦች ጋናዊው አጥቂ ኦሴይ ማውሊ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤልና ያሬድ ብርሃኑ አንድ አንድ ግብ አስቆጥረዋል።ክለቡ ተጋጣሚው ላይ የወሰደው የግብና የጨዋታ የበላይነት ከፊት ለፊቱ ያሉትን ሁለት ጨዋታዎች በድል የመወጣት አቋም እንዳለው የፈተሸበት መሆኑን ተመላክቷል። ከፋሲል ከነማ በእኩል 53 ነጥብ ተቀምጦ በግፍ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። 52 ነጥብ በመሰብሰብ በአንድ ነጥብ ተበልጦ ሦስተኛ ደረጃን የያዘው ሲዳማ ቡና በ28 ኛው ሳምንት ድሬዳዋ ከተማን በመርታት ሦስት ነጥብ ከመሪዎቹ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 1 ዝቅ እንዲል ማድረግ ችሏል።የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሊግ ኮሚቴ ባስቀመጠው የውድድር መርሃ ግብር መሠረት 29ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፤ የ30 ሳምንትና የመጨረሻው ጨዋታዎች ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ይካሄዳል። በዚህ መሠረት አጼዎቹ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ስሁል ሽረ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የአጼዎቹን እግር የሚከተለው መቐለ ሰባ እንደርታ በበኩሉ ከድሬዳዋ፣ ከመከላከያ የሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታዎች ከፊት ለፊቱ የሚጠብቁት ይሆናል።መሪው ፋሲል ከነማ በ29 ኛው ሳምንት ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርገው ጨዋታ በእጅጉ ፈታኝ እንደሚሆን ተጠባቂ ሆኗል። በፕሪሚየር ሊጉ የሻምፒዮናነት ታሪክ ውስጥ ግዙፉን ድርሻ የያዘው ሳንጃው ለአጼዎቹ እጁን በቀላሉ እንደማይሰጥ ከወዲሁ መላምቶች ይሰማሉ። በሌላ ወገን ደግሞ የሻምፒዮናነት ፍላጎትንና ወኔን የታጠቁት አጼዎቹ ሳንጃውን በመርታት የተመኙት የሻምፒዮናነት ዘውድን ለመጫን የሚዋደቁ መሆኑን ተከትሎ የጨዋታው አሸናፊነት ግምት እንዲሰጣቸው አድርጓል። አጼዎቹ በ29 ኛው ሳምንት የሚኖራቸው ነጥብ ተከትሎ የመጨረሻው ምዕራፍ በሆነው 30ኛው ሳምንት ላይ ላለመውረድ ከሚታገለው ስሁል ሽረ ጋር ወሳኙን የሜዳ ላይ ቆይታ የሚያደርጉ ይሆናል።ከአጼዎቹ ጋር አንገት ለአንገት የተያያዘው መቐለ ሰባ እንደርታ በ29 ኛው ሳምንት ላለመውረድ ከሚጫወተው ከመከላከያ ጋር ይጋጠማል። መቐለ በዚህ ጨዋታ በቀላሉ ሙሉ ነጥብ ይዞ ለመውጣት ፈተና እንደሚገጥመው ይገመታል። መከላከያ ከሊጉ ላለመውረድ የሚያደርገው የሞት የሽረት ትግል የመቐለን የሻምፒዮናነት ግስጋሴን ሊገታ እንደሚችል በማስረጃነትም ቀርቧል። የመውጣትና የመውረድ ስሜትን በያዘው በዚህ ጨዋታ ውጤት ተንተርሶም በ30 ኛው ሳምንትን ከድሬዳዋ ጋር በሚኖረው ጨዋታ የሻምፒዮናነት ዕጣ ፈንታው የሚለይ ይሆናል። የሻምፒዮናነት ሚዛንን የተሸከመው ሲዳማ መውረዱን ካረጋገጠው ደደቢት ጋር 29 ኛ ሳምንት ጨዋታውን የሚያደርግ ሲሆን፤ በጨዋታው ሙሉ ነጥብ ይዞ ለመመለስ ሰፊ ዕድል እንደሚኖረው ይገመታል። ምናልባትም በጨዋታው ካሸነፈ በ30ኛው ሳምንት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር በሚኖረው ጨዋታ አሸንፎ ሻምፒዮና የመሆን ወኔን እንዲይዝ የሚያደርገው አጋጣሚ ይሆናል።በአጠቃላይ የፋሲል ከነማና መቐለ ሰባ እንደርታ የነጥብ እኩልነትና የሻምፒዮናነት ግስጋሴ ትንቅንቅ ከወዲሁ አነጋጋሪና ጥንቃቄን የሚሻ መሆኑን የስፖርት ቤተሰቡ ስጋቱን እየገለጸ ይገኛል። እግር ኳሱ አውዱን ቀይሮ ፖለቲካዊና ብሔርን ወካይ ከሆነ የሰነበተ መሆኑን ተከትሎ፤ ጨዋታዎች ከዳኘነት ጋር ተያይዞ ጥንቃቄን የሚሹ እንደሆኑ ተገልጿል። ባለሜዳ ቡድኖች ዳኞች፣ ተጋጣሚ ተጫዋቾች እና ከእንግዳ ቡድን ደጋፊዎች ጋር የሚኖራቸው ሰላማዊ ግንኙነት አስቀድሞ ቅድመ ዝግጅት ሊደረግ ይገባል። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ፣ ክልሎችና የጸጥታ አካላት ቀሪዎቹን ጨዋታዎች በንቃትና ፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት በሰፈነ መልኩ እንዲከናወኑ ከማድረግ አኳያ ከባድ ኃላፊነት እንዳለባቸው ቀድመው መረዳትና መዘጋጀት ሌላው መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ ይሁን። የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ለሻምፒዮናነት በሚደረገው ግስጋሴ ውስጥ ደግሞ ደቡብ ፖሊስ በሃያ ስምንት ነጥቦች አስራ አራተኛ፤ ስሁል ሽረ በሃያ ሰባት ነጥቦች አስራ አምስተኛ እንዲሁም ደደቢት በአስራ ሦስት ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ በመያዝ፤ ለመውረድና ለመውጣት የሚያደርጉት እልህ አስጨራሽ ጨዋታ እንደሚሆን ይጠበቃል። በሌላ በኩል የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ፉክክር የመቀሌው አማኑኤል ገብረሚካኤልና የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በአስራ አምስት ግቦች አንደኛና ሁለተኛ ሲሆኑ፣ የፋሲሉ ሙጂብ ቃሲም በአስራ አራት ግቦች ሦስተኛ ደረጃን ይዟል።አዲስ ዘመን ሰኔ 26/2011 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13493
0ff83f6f42abe2c89a2c376babb8c052
5fa632e088eb300de7df74b39f53f8e4
አካዳሚውምርጥ ስፖርተኞችን የማፍራት ተልዕኮውን እያሳካ መሆኑ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ምርጥ ስፖርተኞች የማፍራት ተልዕኮውን እያሳካ መሆኑን ተገለጸ። ለአራት ዓመታት በ9ኝ የስፖርት ዓይነቶች በአሰላ ጥሩነሽ ዲባባ እና በአዲስ አበባ የማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን 105 ስፖርተኞችም በትናንትናው ዕለት አስመርቋል።የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ አንበሳው እንየው ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ አካዳሚው ምርጥ ስፖርተኞች የማፍራት ተልዕኮውን እያሳካ ሲሆን ውጤታማነቱ ሰልጣኞች በሚያስመዘግቧቸው ውጤቶች የሚለካ ነው። አካዳሚው ፓራሊምክን ጨምሮ ሥልጠናውን በሚሰጥባቸው አስር የስፖርት ዓይነቶች ከአገር አቀፍ ውድድሮች ባሻገር፤ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ተመልምለው በአህጉርና በዓለም አቀፍ መድረኮች መሳተፍ የቻሉ በርካታ ስፖርተኞች ማፍራት እንደተቻለው ገልጸዋል። በዘንድሮው ዓመት በነበሩ አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች በመሳተፍ የነበራቸው ውጤታማነት ለዚህ እንደ ማሳያ የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል።እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ማብራሪያ፤ በዚህም መሠረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሦስት ሺ ሜትር መሰናክል በራባት ሞሮኮ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ አንደኛ የሆነው የኢትዮጵያ የርቀቱ ባለ ክብረ ወሰን ጌትነት ዋሌ፣ በሁለት ሺህ መሰናክል እና በ4 ኪሎ ሜትር ሀገር አቋራጭ ዘንድሮ ቦነስ አይረስ ላይ በተካሄደው የዓለም የታዳጊዎች ኦሎምፒክ የወርቅ ባለቤት የሆነው አብርሃም ስሜ፣ በማራካሽ ሞሮኮ በ4 ኛው ኢንተርናሽናል ፓራሊምፒክ አትሌቲክስ ውድድር የተሳተፈው ገመቹ አመኑ በ1 ሺ500 ሜትር ወርቅ፣ በ 800 ሜትር ነሐስ ማምጣት ችሏል። ዝናሽ አሰፋ በዚሁ መድረክ በ200 ሜትር እና በ400 ሜትር ወርቅ አስመዝግባለች።በዓለም አቀፍና በአህጉር አቀፍ መድረኮች የአካዳሚው ፍሬ የሆኑ ስፖርተኞች እያስመዘገቡ የሚገኙት ውጤት አካዳሚው ከተቋቋመበት አላማና ራዕይ እኩል እየተጓዘ ስለመሆኑ ምስክር መሆኑን አመልክተዋል። አካዳሚው ባለፉት አራት ዓመታት በ9ኝ የስፖርት ዓይነቶች በአሰላ ጥሩነሽ ዲባባ እና በአዲስ አበባ የማሰልጠኛ ማዕከል ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን 105 ስፖርተኞችንም እንዳስመረቀ ተናግረዋል።ተመራቂዎቹ ሥልጠናቸውን ላለፉት አራት ዓመታት ሲከታተሉ መቆየታቸውን ገልጸው፤ ተመራቂዎቹ ለጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል 7ኛ ዙር 49 ሰልጣኞች ሲሆኑ ለአዲስ አበባ ካምፓስ ደግሞ የ 3 ኛ ዙር 56 ሰልጣኞችን መሆናቸውን አብራርተዋል። ሥልጠናውና ምርቃቱ በሀገሪቱ ቀጣይ የስፖርት ውጤታማነት ላይ ጉልህ ድርሻን እንደሚጫወቱ እምነታቸውን ገልጸዋል።የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ርስቱ ይርዳው በምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአካዳሚው ላለፉት አራት ዓመታት ያገኛችሁትን እውቀት፣ ክህሎት እና ስፖርታዊ ሥነ ምግባር በምትቀላቀሏቸው ክለቦች እና ተቋማት ይበልጥ ልታጠናክሩ ይገባል። ተመረቃችሁ ማለት የነገ ተስፋ መሆናችሁ አመላከታችሁ እንጂ ምርጥ ስፖርተኞች የመሆን ጉዟችሁ አጠናቀቃችሁ ማለት አይደለም። የስፖርት ሥልጠና እና የመደበኛ ትምህርት ጉዞአችሁ በምትቀላቀሏቸው ክለቦ፣ የስፖርት እና ሌሎች ተቋማት ዘንድ ከፍ ወዳለ እርከን ልታደርሱት ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ በ2006 ዓ.ም እንዲሁም የጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል በ2002 ዓ᎐ም ሥራ መጀመራቸው አይዘነጋም።አዲስ ዘመን ሰኔ 26/2011 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13496
d326c5d95769b7990da5b387ffa48af8
c19d28341ab07707ef2740c4af380372
‹‹ሙሌቱ ለነባርም ሆነ ለአዳዲስ ኢንቨስተሮች ከፍተኛ የሞራል ስንቅ ይሆናል››አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ
 አዲስ አበባ፦ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ፕሮጀክቶቻቸውን እንዲያስፋፉና አዳዲሶቹም ወደ አገሪቱ እንዲያማትሩ ከፍተኛ የሞራል ስንቅ እንደሚሆን ጀግናው አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገብረ ስላሴ ተናገረ፡፡ሙሌቱን አስመልክቶ የጋዜጣው ሪፖርተር ያነጋገረው በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የተሰማራው ጀግናው ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ፣ ህዳሴ ግድቡ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት የታላቅ ድል መጀመሪያ ነው፣ በተግባሩም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል›› ብሏል፡፡የውሃ ሙሌቱ የኤሌክትሪክ ሃይል ማግኘት ፈተና በሆነበት አገር በተለይ በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ለቀጣይ ስራዎች ስንቅና ማበረታቻ እንደሚሆን ያመላከተው ሃይሌ፣ የሙሌቱ ብስራት ‹‹ነገ ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ የሃይል ችግር ፈተና ሆኖ እንዳይቀጥልና እኔ እና ሌሎችም በርካታ ኢንቨስተሮች ካለ ጭንቀት በልበ ሙሉነት ስራችንን እንድንቀጥል መተማመኛ የሚለግስ ነው›› ብሏል። አገሪቱም የውስጥ ፍላጎትን ከማርካት በተጓዳኝ በሽያጭ መልክ ለሌሎችም እንድትተርፍና ተጠቃሚነቷን እንድታጎለብት ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አስገንዝቧል፡፡‹‹እንደ አንድ የአትሌቲክስ ስፖርተኛ በጥሩ ብቃት ከአንድ ኦሎምፒክ ወደ ሌላ ኦሎምፒክ ከአንድ ድል ወደ ሌላ ድል፣ ከአንድ ክብረ ወሰን ወደ ሌላ ክብረ ወሰን መተላለፍ አለብን›፣ ህዳሴ ላይ የፈፀምነው ገድል መንደርደሪያችን እንጂ መቋጫችን ባለመሆኑ በተግባሩ ሳንኩራራ ሁለተኛውንም ሶስተኛውንም ሙሌት ማፋጠን እና እስከመጨረሻው በመዝለቅ በሙሉ አቅም ኤሌክትሪካችንን ማመንጨት ይገባናልም›› ብሏል፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በህገወጦች የሚፈፀሙ ተግባራት መሰል የደስታ ዜናዎችን እንደሚያደበዝዙ የጠቆመው ሃይሌ፤ የህገወጦቹ ተግባር የአገሪቱን ገፅታ የሚያበላሽ በተለይ ኢንቨስተሮችን ተስፋ የሚያስቆርጥ እንደመሆኑ ሊታረም እንደሚገባም አስገንዝቧል፡፡መንግስትም በህገወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩትን በቃችሁ በማለት ህግ የማስከበር ኃላፊነቱን በአግባቡ መፈፀም እንዳለበት አፅንኦት የሰጠው ሃይሌ፤ ይህ እስካልሆነም ግድቡን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶች ኪሳራ እንደሚሆኑ መረዳት አግባብ መሆኑንም አመላክቷል፡፡በአሁኑ ወቅትም በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚከሰት ሁከት ለጥፋት ከመነሳት ይልቅ ቆም ብሎ የሚያስብና “ለምን” የሚል የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የሚያወድም ሳይሆን የራሱ መሆኑን በመረዳት የሚጠብቅና የሚንከባከብ ትውልድ መፍጠር እንደሚያስፈልግም አፅንኦት ሰጥቶታል፡፡የህዳሴ ግድቡ ትሩፋት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ተጠቃሚ የሚያደርግና ጥቅሙም ለመቶና ለሁለት መቶ አመት የሚዘልቅ እንደመሆኑ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚሉ አንዳንድ አካላትም በዚሁ አቋማቸው ዙሪያ ቆም ብለው ማሰብ እንደሚገባቸውም አመላክቷል፡፡የኢትዮጵያውያን የጋራ አሻራ የሆነውን ታላቁ የህዳሴ ግድብ መደገፍ የምርጫ ሳይሆን የግዴታም ጉዳይ በመሆኑ ከቀደመው በበለጠ የሁሉም ተሳትፎ መጠናከር እንዳለበትና ህዝቡም ሆነ ባለሀብቶች የጀመሩትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸውም አትሌት ሃይሌ ጥሪ አቅርቧል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 16/2012ታምራት ተስፋዬ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35871
e694b2481e6f90cda55bc0a7c7837b6c
a1bd21ac55738d44ddaecd0f3c97d67b
አባይን በሀገሩ ያሳደሩ አርበኞች ድልና ተስፋ
 አዲስ አበባ፡- አባይን በሀገሩ ለማሳደር የዘመቱት አርበኞች የላባቸውን ዋጋ ፣ የእጆቻቸውን የስራ ውጤት ማየት በመጀመራቸው በጉባ ተራሮች ግርጌ ታላቅ ደስታና ፈንጠዝያ ፈጥሯል። ዓይናቸው የውሃ ሙሌቱ ከፈጠረው አዲስ መልክዓ ምድር ጋር እየተለማመደ ነው። ተራሮች ደሴት ፈጥረዋል። አባይ በተራሮች ግርጌ ተነጥፏል፤ አንዳንዴም ከወዲህ ወዲያ እየተንሸራሸረ የመኖሪያውን ጓዳ ጎድጓዳ ይጎበኛል። አንዳንዴም በግድቡ አናት ላይ ካልዘለልኩ ይላል። ግን አይዘልም፤ በሀጋሩ ልጆች ሙያና ፋይናንስ ትብብር አባይ በሀገሩ አድሯል ይላሉ በህዳሴው ግድብ ላይ አሻራቸውን ያሳረፉ አርበኞች። ኢንጂነር ታደሰ መልሰው ከወሎ ዩኒቨርሲቲ በመካኒካል ምህንድስና ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ ለተከታታይ አራት ዓመታት በህዳሴው ግድብ ላይ ሲሰራ ነበር። ኢንጂነር ታደሰ ይህን በሚያክል ሜጋ ፕሮጀክት ላይ በተለይም በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ አሻራውን በማሳረፉና በሙያው አስተዋጽኦ ማበርከቱ ደስተኛ አድርጎታል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ግድቡ ውሃ ተሞልቶ ሲመለከት ደስታውን የሚገልጽበት ቃላት አጥሮታል። ተጨባጭ ውጤት ማየቱም ቀሪውን ስራ ለመስራት ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሆነው ይገልጻል። ልክ እንደ እርሱ ሰራተኛው በሙሉ በደስታ ማዕበል ውስጥ እየዋኘ መሆኑን የጠቀሰው ኢንጂነር ታደሰ፤ በተለይም የውጭ ሃይሎች የውሃ ሙሌቱን ለማደናቀፍ ያደረጉት ሙከራ መክሸፉ ትልቅ ድል ነው ይላል። የህዳሴው ግድብ የኤሌክትሪክ ፣ የመስኖና የዓሳ እርባታ ፍላጎትን ከማርካት ባለፈ ካለው አቀማመጥ አንጻር የቱሪስት መስህብና ልዩ የመዝናኛ ቦታ መሆን እንደሚችል ያለውን ተስፋም አመላክቷል። ውሃ መያዝ ተጀመረ ማለት ተስፋችን እውን ሆነ ማለት እንደሆነም ጠቅሷል። ኢንጂነር አበባው ይሁን በኤሌክትሪካል ምህንድስና ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተመርቆ በህዳሴው ግድብ መስራት ከጀመረ አራት ዓመታን አስቆጥሯል። በሃይድሮ ኤሌክትሪክ ስቲል ስትራክቸር ስራ ውስጥ ሴፍቲ ኦፊሰር ሆኖ በመስራትም ላይ ይገኛል። የህዳሴው ግድብ ውሃ ሙሌት እንደ አንድ ኢትዮጵያዊም ሆነ አሻራውን በግድቡ ላይ እንዳሳረፈ ሙያተኛ ወደር የሌለው ደስታ እንደፈጠረበት ይገልጻል። ለዘመናት ብዙዎች ሲቆጩበት የነበረውን የአባይ ወንዝ እጅ ካሰጡ አርበኞች መካከል አንዱ መሆኑና ‹‹ አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል›› የሚለውን ምሳሌዊ አነጋገር ታሪክ ያደረገ ስራ መስራቱ እንደሚያኮራውም ይናገራል። የህዳሴው ግድብ ውሃ ሙሌት በተለይም በግድቡ ስራ ላይ ለተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ድል እንደሆነ የገለጸው ኢንጂነሩ፤ የውሃው ሙሌቱን ለማደናቀፍ ሲሯሯጡ ለነበሩትም ተስፋ ያስቆረጠ ነው ብሏል። በበረሃው ሀሩር ላቡን እያንጠፈጠፈ ሲሰራ ለነበረው ሰራተኛ ሳምንቱ የተለየ ወቅት እንደነበር የጠቀሰው ኢንጂነር አበባው፤ የውሃው ሙሌቱ የአካባቢውን መልክዓ ምድር ወደ ገነት የቀየረና የመጪዋን ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ ያሳየ ነው ይላል። ከምንም በላይ ፕሮጀክቱ በእቅዱ መሰረት ስራዎችን ማከናወኑ ለቀጣይ ስራዎች ሰራተኞችን የሚያነሳሳ መሆኑንም ይጠቅሳል። በጉጉት ለሚጠብቀው የኢትዮጵያ ህዝብም ትልቅ የምስራች እንደሆነ በማስረዳት። የውሃ ሙሌቱ የፈጠራቸው ደሴቶች ቀልብን የሚስቡ መሆናቸውና በረሃማው መልክዓ ምድርም ወደ ልምላሜና ነፋሻማነት የመቀየር እድሉ የሰፋ እንደሆነ የጠቀሰው ኢንጂነር አበባው፤ የተፈጠረው ሃይቅ ለበርካታ አገልግሎቶች የሚውል እንደሆነም ይጠቅሳል። ኢትዮጵያ የውጭ ጣልቃ ገብነትን ወደ ጎን ትታ በመርሃ ግብሯ መሰረት ሙሌቱን ተፈጻሚ ማድረጓ ዛሬም እንደ ጥንቱ ሉአላዊነቷን፣ መብቷንና ክብሯን ያስጠበቀች ሀገር እንድትሆን አድርጓታል። የህዝቦቿንም ተስፋ አለምልሟል ይላል። ህዳሴው ግድብ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሰው ኢንጂነር አበባው፤ ህዝቡ ድጋፉን አጠናክሮ በመቀጠል ህልሙን እውን ማድረግ ይኖርበታልም ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 16/2012 ኢያሱ መሰለ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35855
93a01e131875cf2d54b99bec4ff9c805
dd5ad1e11cd0afe49e44af8f36a9ddb5
በአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም እስካሁን ከ3ነጥብ5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል
አዲስ አበባ፡- ዘንድሮ በተጀመረው የአምስት ቢሊዮን ችግኞች ተከላ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም እስካሁን ከ3ነጥብ5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያትኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገለጹ፡፡ኢትዮጵያውያን የጋራ ቤታቸውን በጋራ መገንባት ላይ በማተኮር የጀመሩትን ድል ለማስቀጠል እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡አቶ ንጉሱ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ሂደትን አስመልክተው ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ ዘንድሮ በተጀመረው የአምስት ቢሊዮን ችግኞች ተከላ የአረንጓዴ አሻራ እስካሁን ከ3ነጥብ5 ቢሊዮን  በላይ ችግኞች መተከላቸውን ፤ ቀሪ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ገደማ ችግኞችም ካለው ምቹ ሁኔታ አኳያ በቀሪ ጊዜያት እንደሚተከሉ አስታውቀዋል ፡፡ መርሃ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያመነጩት ሀሳብና በባለቤትነትም የሚመሩት እንደመሆኑ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ተገኝተውም ተክለዋል፡፡ ባለፈው ዓመት የተተከሉትንም አርአያ ለመሆን ሲንከባከቡ ቆይተዋል ብለዋል ። በዚህ ዓመት ደግሞ ይህ ስራ ሲሰራ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴን ግድብ ለመጀመሪያ ጊዜ ውሃ ሙሌት ማከናወን እንደተቻለም አስታውቀዋል ፡፡ በዚህ ወቅት የሚተከለው ችግኝ አንደኛ፣ የአየር ንብረቱን በማሻሻል በቂና ተመጣጣኝ ዝናብ እንዲገኝ የሚያስችል ሲሆን፤ ግድቡ በደለል እንዳይሞላ የሚያደርግ ነው፡፡ ችግኝ መትከል ደግሞ የአስር ዓመቱ የአረንጓዴ ልማት እቅዱ አንድ አካል የተደረገ እንደመሆኑ አረንጓዴ ልማቱን እውን ለማድረግ ይሄን ስራ አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል፡፡“አሁን የምንገኘው በደስታ ላይ ነው” ያሉት አቶ ንጉሱ፤ የደስታ ምንጩ ደግሞ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ውሃ በመያዝ በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዓባይን ወደ አገሩ እንዲመለከት የሚያደርግ፤ ከአገር ውስጥ አልፎም ለታችኛው ተፋሰስ አገራት ለልማት የሚጠቅም እና  ኢትዮጵያ ዓባይን ተመልካች ብቻ ሳትሆን ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንድትሆን ያስቻለ ታሪክ የጻፍንበት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ወቅቱም ይሄ ታሪክ የተጻፈበት የደስታ ወቅት ስለሆነ እንኳን ደስ አላችሁ/አለን ማለት እወዳለሁ፤ በማለት የደስታ ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ አንደኛ፣ ግድቡን ማጠናቀቅ ይጠበቅብናል፡፡ ሁለተኛ፣ በዲፕሎማሲው መድረክም በትክክል ኢትዮጵያን ግብጽና ሱዳን ብቻ ሳይሆኑ ሌላውም ዓለም እንዲረዳት በማድረግ የፍትሃዊ ተጠቃሚነት መብታችንን ማስከበር እና ይሄንን የማስገንዘብ ትልቅ ኃላፊነት አለብን፡፡ ሶስተኛም፣ የገነባነውን ግድብ በደለል እንዳይሞላ አረንጓዴ ልማቱን ማፋጠን ይኖርብናል፡፡ ለዚህ ደግሞ የእርከን ስራን ጨምሮ ችግኝ ተከላውን በማፋጠን ያስቀመጥነውንም ግብ ማሳካት ይኖርብናል ሲሉም አሳስበዋል፡፡ግድቡንም በገንዘብም በሞራልም፣ በእውቀትም ተደጋግፈን ማጠናቀቅ፤ ከዛም ባሻገር ምሑራን፣ የህግ ባለሙያዎች፣ የቴክኒክ ባለሙያዎችና ሌሎችም የዲፕሎማሲ ስራው ላይ የሚያደርጉትን ተጋድሎ በአገር ውስጥም በውጪም የምንኖር ኢትዮጵያውያን መደገፍና የበኩላችንን አስተዋፅዖ ማበርከት ይጠበቅብናል፡፡ የኢትዮጵያን ጥቅም፣ ትክክለኛ ፍላጎትና መብት በመግለጽ፤ የማስረዳት፣ የመከራከርና የመሟገት እና ለፍትህ የመቆም ስራ መስራት አለባቸው፡፡ በችግኝ ተከላው ተሳትፎም ታሪክ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡እነዚህን ሁሉ ለማድረግ ግን የአገራችንን ሰላም መጠበቅ፤ አንድነታችንን ማስቀጠል እና በፍቅር በሰላምና በአንድነት ሊያጋጩን የሚችሉ ጥቃቅን ነገሮችን ወደጎን በመተው የጋራ ቤታችንን በጋራ መገንባት ይገባናል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 18/2012ወንድወሰን ሽመልስ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35942
9bea146ff43d4e5799c75745abab8117
7e5c22c8201e68628b6d41e77587aa7b
‹‹ትህነግ የተለያዩ ማንነቶችን ጨፍልቆ አንድ ማንነት ለመገንባት እየጣረ ነው››አቶ አገዘው ህዳሩ የራያራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት
ህውሃት በትግራይ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ማንነቶችን በመጨፍለቅ አንድ ማንነት ለመገንባት ጥረት እያደረገ መሆኑን የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ አገዘው ህዳሩ አስታወቁ፡፡ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ህልፈተ ህይወት በኋላ የህወሃት አፈና መጠናከሩንም ገልጸዋል፡፡የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ አገዘው ህዳሩ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለጹት በትግራይ ውስጥ የተለያዩ ማንነቶች ያላቸው የራያ ፤የኩናማ ፤የሳሆ ፤የአገው እና የኢሮብ ሕዝቦች ቢኖሩም ሕውሓት እንደእርሳቸው አባባል ትህነግ ሁሉንም በአንድ ቅርጫት ውስጥ በመጨፍለቅ አንድ ማንነት ለመፍጠር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡የራያ ህዝብ ከታሪክ አንጻር ትስስሩ ሰፊ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ራያ ከኦሮሞ ማህበረሰብ ፤ከአማራ፤ከአገው ጋር ውህድ ማንነት ያለው ሲሆን በታሪክ ሂደትም የራሱን ማንነትን የፈጠረ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ሆኖም ግን የራያንም ሆነ በትግራይ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ማንነቶችን ባለመቀበል ትህነግ በህዝቦች ላይ የተለያዩ በደሎችን በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡የራያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የራያ ማህበረሰብ የሚገኝበት አካባቢ በሙሉ እና በራያ ወረዳዎች የህዝቡን ማንነት እንዲገነባ ከምርጫ ቦርድ ፍቃድ የተሰጠው ቢሆንም ፓርቲው በራያ ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ በትህነግ በርካታ ማስፈራሪያዎችና ጥቃቶች እየደረሱበት መሆኑን አቶ አገዘው ያስረዳሉ፡፡ የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲንና ሌሎች ትህነግን የሚቃወሙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ባንዳ የሚል ተቀጽላ በማውጣት የማሸማቀቅ ስራ በመስራት ላይ መሆኑን የገለጹት አቶ አገዘው በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ 12 ከሚደርሱ ፓርቲዎች ውስጥም የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በግንባር ቀደምትነት ባንዳ ተብሎ መፈረጁንም ጠቁመዋል ፡፡የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በግንባር ቀደምትነት ባንዳ ተብሎ በህወሃት የተፈረጀበትንም ዋነኛ ምክንያትን አቶ አገዘው ሲስረዱ ‹‹ የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጠንክሮ ከወጣ ተመሳሳይ የማንነት ጥያቄ ያላቸው የአገው፤የኩናማ፤የሳሆ፤የውጅራትና የኢሮብ ማህበረሰቦች ትግላቸውን ማፋፋማቸው አይቀርም፡፡ስለዚህም የራያን የማንነት ጥያቄ ማፈን እና ጥያቄውንም የሚያነሱትንም እያሳደዱ ማጥፋት በዋነኝነት ትህነግ የሚከተለው ስልት ነው፡፡›› ሲሉ አብራርተዋል፡፡በራያና አላማጣ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን የራያራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ደጋፊዎች ናችሁ በማለት የማንገላታትና በልዩ ልዩ የማሰቃያ መንገዶች ተማረው አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን የተናገሩት የፓርቲው ፕሬዚዳንት የራያ ማንነትን የሚያቀነቅኑ ግለሰቦችን አድኖ ከመግደል አንስቶ የማህበረሰቡን ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለሰቦችን ስልታዊ በሆነ መንገድ የመግደልና የማጥፋት ስራዎችን ሀገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሲከወን መቆየቱንም አብራርተዋል፡፡አቶ አገዘው አክለው እንደሚገልጹትም የራያ ማንነት ከዳር ለማድረስም ‹‹ስበር›› በሚል መጠሪያ ተደራጅቶ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርገውን ወጣት በገፍ በማሰርም ጥያቄውን ለማፈን ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ባለፉት ሁለት ዓመታት ስበር ባደረገው እንቅስቃሴም በመደናገጥ የተለያዩ የኃይል እርምጃዎችን ወስደዋል፡፡ ከ17 በላይ ወጣቶች ተገድለዋል፡፡ከ2ሺ በላይ ወጣቶች አሁንም ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡በአሁኑ ወቅትም ምርጫ እናካሂዳለን በሚል ቅስቀሳ ምርጫውን የሚያደናቅፍ ግለሰብም ሆነ ቡድን እርምጃ እንደሚወሰድበት በግልጽ እየዛቱ ነው፡፡በራያ ወረዳዎች ማለትም በጨርጨር፤በመሆኒ ፤አላማጣ፤ወፍላ ወረዳዎች በአንድ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ሰላሳ ሰዎችን በማዋቀር ህብረተሰቡን እንዲሰልሉ እየተደረገ ነው፡፡የተወሰኑት ተቃዋሚዎችን በእነሱ አጠራር ባንዳዎችን መንጥሮ የሚያወጣ ፤ሌላው ደግሞ ጸጉረ ልውጥ አሳሽ፤የተቀረው እነሱ እንጀምረዋለን ብለው የሚያስቡት ጦርነት ሲጀመር ምግብና ውሃ የሚያስተባብር ቀሪው ደግሞ ሙትና ቁስለኛ የሚያነሳ አድርገው አደራጅተውታል፡፡በተጨማሪም ትራንስፖርትና ሌሎች ሎጅስቲኮችን የሚያቀርብ ቡድንም የዚሁ አካል ተደርጎ ተዘጋጅቷል፡፡በአጠቃላይ ትህነግ ተከበሃል በሚል ውዥንብር ወጣቱን ለጦርነት እየመለመለ ይገኛል፡፡በተለይም ከሃጫሉ ህልፈት በኋላ የትህነግ አፈና በእጅጉ መጨመሩንና በሃጫሉ ሞት የቀየሱት ሴራ ባለመሳካቱ ወደ ስልጣን እንመለሳለን ብለው ሲነዙት የነበረው ፕሮፖጋንዳ በመክሸፉ ሕዝቡም እንደታዘባቸውና ድጋፉንም እየነፈጋቸው መምጣቱን በመረዳታቸው ሙሉ ለሙሉ ከቁጥጥራቸው ሳይወጣ በአፈና እንዲገዛላቸው ለማድረግ እየሞከሩ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡አቶ አገዘው አክለውም ቀድሞውንም የሚቃወማቸውን አካባቢ እስከግድያ ድረስ የሚደርስ እርምጃ በመውሰድ ጸጥ ብሎ እንዲገዛና እንዲሸበርም ልዩ ኃይሎችንና ሚሊሺያዎችን በማዟዟር የጦር አቅማቸውን ለማሳየት እየሞከሩ ነው፡፡ይባስ ብሎም ለሚሊሺያው ቀለብ እንዲሰፍርና ለሚሊሺያው ደመወዝ ጭምር እስከ አምስት መቶ ብር ድረስ እንዲያዋጣ ግዴታ እየተጣለበት ይገኛል፡፡ገንዘብ የለኝም ያለ ጤፍና ስንዴ በመስፈር እንዲያስረክብ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡የቃለ መጠይቁን ሙሉ ሙሉ ሃሳብ በገጽ 6 ይከታተሉ፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 18/2012እስማኤል አረቦ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35937
ce2a207ff100b677034a44bdb9fb9a4a
9074ac2ef85731ee43a9d1352448665b
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የወደሙ ኢንቨስትመንቶች መልሰው እንደሚገነቡ አስታወቀ
አዳማ፡- የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ህልፈት ተከትሎ በተፈጸመ ሴራ የወደሙ ኢንቨስትመንቶች መልሰው እንደሚገነቡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ፡፡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ትናንት በአዳማ ከተማ ኦሮሚያ ሥራ አመራር አካዳሚ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ህልፈት ምክንያት በማድረግ በተፈጸመ ሴራ የወደሙ ኢንቨስትመንቶች መልሰው ይገነባሉ ብለዋል፡፡ መንግስት የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋትና ታፍኖ የኖረው ህዝብ እንዲተነፍስና ብሶቱን እንዲናገር የሰጠውን ነጻነትና ያሳየውን ትዕግስት ለዓላማቸው ማሳኪያ የተጠቀሙ ጸረ ሰላም ኃይሎች ጥፋት ማድረሳቸውን ጠቅሰዋል፡፡ እነዚህ ኃይሎች የኦሮሞን ህዝብ ስሜት ቀስቅሰው ክልሉን የጦርነት አውድማ ለማድረግ መሞከራቸውን የጠቀሱት ወይዘሮ ጫልቱ ያደረሱት ጥፋት ቀላል ነው ባይባልም ከውጥናቸው አንፃር ሲታይ ግን ጥቂት ነው ብለዋል፡፡ በተለይም ኢንቨስትመንት ለክልሉና ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ምን ያህል አስተዋጽኦ እያበረከተ እንዳለ የተረዱት እነዚህ ኃይሎች ሆን ብለው ባለሃብቱን ለማስበርገግና ዜጎችን ከስራ ለማፈናቀል አልመው መስራታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በክልሉ ከትንሽ እስከ ትልቅ የንግድና የኢንቨስትመንት ተቋማት እንደወደሙ የገለጹት ምክትል ፕሬዚዳንቷ እነዚህን የኢንቨስትመንት ተቋማት ለመገንባት የፌዴራል መንግስት ፣ የክልሉ መንግስትና ባለሃብቶች ተረባርበው ወደ ነበረቡት ይመልሷቸዋል ብለዋል፡፡ የክልሉ ህዝብ አቃፊ ፣ ስራ ወዳድና መልካም ሰብዕና እንዳለው የተናገሩት ፕሬዚዳንቷ የተፈጠረውን ክስተት እንደጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም በሰዎች አዕምሮ ውስጥ መጥፎ ስዕል የሚስሉ አካላት መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ባለሀብቱ ይህ ክስተት ለውጡን ለማደናቀፍና በአቋራጭ ወደ ስልጣን መምጣት በሚፈልጉ አካላት የተፈጸመ ድራማ መሆኑን ተረድቶ ያለምንም የስነ ልቦናና የጸጥታ ችግር ስራውን ማከናወን እንዳለበት አሳስበዋል:: በዘንድሮው ዓመትም በርካታ የኢንቨስትመንት ማሻሻያዎች፣ መመሪያና ደንቦች ጸድቀው ወደ ስራ እንደተገባ የገለጹት ፕሬዚዳንቷ በመጪው ዓመትም በክልሉ ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልግ ባለሃብት ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ክልሉ የሕግ የበላይነትን በማስከበር ለነዋሪውና ለባለሃብቱ ዋስትና እንደሚሰጥና አሁን የተጀመረው ህግን የማስከበር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ፕሬዚዳንቷ ገልጸዋል፡፡ ኢንቨስትመንት ኢኮኖሚን ለማሳደግና የስራ እድልን በመፍጠር ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት የጠቀሱት ወይዘሮ ጫልቱ አሁን የግል ባለሃብቱን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ እንዳለ አስረድተዋል፡፡ ባለሃብቱም በሚሰራበት አካባቢ ካለው ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦ መስራት እንዳለበትና ህዝቡ የፈሠሠው መዋዕለ ንዋይ የኔነው ብሎ እንዲያምን ማድረግ ይገባዋል ብለዋል፡፡ የሥራ ዕድል በመፍጠርም ይሁን ማህበራዊ አገልግሎት በመስጠት ህዝቡ የልማቱ ተጠቃሚ መሆኑን ማሳየት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በክልሉ ለሚገኙ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች ልዩ ጥበቃ የማድረግ ስራ ለመተግበር እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውንም ፕሬዚዳንቷ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በጥፋት ላይ የተሰማሩ አካላትን እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አካላትን ተከታትሎ ለፍርድ በማቅረብ ህጋዊ እርምጃ የማስወሰዱ ስራ እንደተጀመረ ጠቅሰዋል፡፡ በውይይቱ ላይ ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ በርካታ ባለሃብቶች የተሳተፉ ሲሆን አብዛኛዎቹ ባንጸባረቁት ሃሳብም መንግስት የህግ የበላይነትን እንዲያስጠብቅና ላፈሰሱት መዋዕለ ንዋይም ዋስትና እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ በውይይቱ ላይ በክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የግብርና ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ እና የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ተመሳሳይ ሀሳቦችን አቅርበዋል፡፡ የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃይሉ ጀልዴም የዓመቱን የኢንቨስትመንት ሥራ አፈጻጸምና ቀጣይ አቅጣጫዎችን አሳይተዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 18/2012ኢያሱ መሰለ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35939
c18a3d5ca1607906c0f5b0687d5de9e2
86c4f1f2f3b4db38800229d82a7a1f4e
” ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ የላቸውም “ጄኔራል አደም መሐመድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
 አዲስ አበባ፦ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ እንደሌላቸው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ አስታወቁ። የሰራዊቱ ወታደራዊ ቁመና የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና የሕዝቡን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል እንደሆነም አመለከቱ። ጄኔራል አደም መሐመድ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ከህግ ውጪ ሆኖ፤ በተለይ በሕዝቦች መካከል ቁርሾ በመፍጠር፤ ግጭት በመፍጠር፤ በሃይማኖትና በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎች እየተፈረጁ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ እንደማይኖራቸው አስታውቀዋል።ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ፤ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ፤ ጎሳን ከጎሳ የሚያጋጩ ስራዎች ሆነ ተብለው የሚሰሩ ከሆነ፤ አድገው ወደ ዘር ማጥፋት፣ ወደ እልቂት የሚያመሩ በመሆኑ መንግስት እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል ። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ መንግስት እርምጃ መውሰድ ካልቻለ የመንግስትነት ተልዕኮው ምን ሊሆን ይችላል? እንደዚህ አይነት ጥፋቶች አድገው እንደ ሩዋንዳና ሌሎች አገሮች እንደሆኑት የሚጠብቅ ከሆነ ሕገመንግስታዊነቱ በምን ይገለጻል ሲሉም ጠይቀዋል ፡፡” ግልጽ መሆን ያለበት መንግስትና የመከላከያ ሰራዊት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ እና አገርን የሚበትንና የሚያዳክም ማንኛውም ህገወጥ የሆኑ ተግባራትን እያየ ዝም አይልም ፡፡ ይህን ማስቆም በህገመንግስቱ የተሰጠው ኃላፊነት ነው ። የሰራዊቱም ተልዕኮ ይሄ ነው፡፡ መንግስትም ቢሆን የሀገርን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ኃላፊነት ፤ ግዴታም አለበት” ብለዋል ፡፡ የመከላከያ ሰራዊቱ የኢትዮጵያውያን ሰራዊት ነው ፤ተልእኮውም የሚመነጨው ከህገ መንግስቱ እንደሆነ ያመለከቱት ጄኔራል አደም ፣ ህገ መንግስቱ የሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ይወጣል ለዚህም ዝግጁ ነው ብለዋል ። የሰራዊቱ ተልእኮ የሚመነጨው ከህገ መንግስቱ በመሆኑም ተልእኮውን ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ርዕዮተ ዓለም ጋር አይይዞ ማየት እንደማያስፈልግ ገልጸዋል ። ህዝቡም እንደዚህ አይነት አስተሳሰቦችን ሊታገል እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የመከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያውያንን እኩል ሊያገለግል የሚችል ተቋም ሆኖ እየተገነባ መሆኑን አመልክተው፣ የጸጥታ ተቋማት የማንም ፓርቲ ዕሴት ወይም ሀብት ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ሀብት ናቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በአንድ ፓርቲ ፕሮግራም ሊቀረጽና ሊገነባ የማይገባው እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ በኢትዮጵያውያን ዕሴቶች፣ በአገር ሉዓላዊነት፣ ደህንነትና ብሔራዊ ጥቅም ተመስርቶ መገንባት ያለበት ተቋም ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በሰራዊቱ ውስጥ ለነበሩ በርካታ የሰራዊት የግንባታ ጥያቄዎች ብዙ ኪሳራዎች እንደነበሩ ጠቁመው፤ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ የተቋም ግንባታ ላይ የተቀመጡ አስተሳሰቦችን በግለሰብ ደረጃ አለመቀበል እንደ ኃጢያት ይቆጠር ነበር፡፡ በዚህም የከሰርናቸው ኪሳራዎች አልነበሩም ማለት አይቻልም ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም አንዱን ጠባብ ብለህ ታባርራለህ፤ ወይ ትከስሳለህ፡፡ ወይ አንዱን ትምክህተኛ ብለህ ትጠረጥራለህ፤ ታባርራለህ፤ ወይ ትከስሳለህ ነው ያሉት፡፡ የሰራዊቱም ጥንካሬ ከአንድ ፓርቲ የፖለቲካ ጥንካሬ የሚነሳ መሆን የለበትም፡፡ ከአንድ ፓርቲ የፖለቲካ ጥንካሬ የሚነሳ ከሆነ፤ ፓርቲው ሲጠነክር አብሮ የሚጠነክር ይሆናል፡፡ ሌላውን እያዳከመ የሚኖርም ይሆናል፡፡ ያ ፓርቲ ሲደክም፣ ነገ በሌላ መንገድ ወደ ስልጣን የሚመጣ ኃይል ደግሞ የሚንደውና የሚያፈርሰው መሆን የለበትም:: ይሄ ተቋም የአገር እናየሕዝብ ተቋም ሆኖ በትውልዶች መገንባት መቻል አለበት ብለዋል፡፡ ፓርቲዎች በራሳቸው በሚያደርጉት ጭቅጭቅና ንትርክ ይሄንን ተቋም መጠቀሚያ የሚያደርጉበት ሁኔታ ከተፈጠረ የሆነ ፓርቲ ወደስልጣን በመጣ ቁጥር እየወደቀና እየፈረሰ እንደገና የሚገነባ ይሆናል፡፡ እየፈረሰ እየተገነባ የሚሄድ ተቋም ደግሞ ይህችን ታላቅ አገር አይመጥንም ብለዋል ጄኔራል አደም፡፡ የመከላከያ ሰራዊቱ ከለውጡ በፊትም ሆነ በኋላ የልማት እና የሰላም ጀግና ሆኖ እየተንቀሳቀሰ እንደነበር ያመለከቱት ጄኔራል አደም፤ በዚህ በኩል ትልቅ ዝናና ስም ያለው ሰራዊት ነው፡፡ አሁንም በውስጥም ሆነ በውጪ ያሉ ማንኛውንም የሀገር እና የህዝብ ስጋቶችን በመከላከል ከፍተኛ ስራ እየሰራ ነው ብለዋል። በአገር ውስጥ ሰላምና መረጋጋትን በማረጋገጥና በማስከበር ሚናው ከፍተኛ እንደሆነም አስታውቀዋል ፡፡ ህገ መንግስቱ ሰራዊቱ ከፖለቲካ ገለልተኛ መሆን አለበት፤ በፖለቲካ ጉዳዮች እጁን አያስገባም ፣የፖለቲካ አዋላጅም መሆን እንደሌለበት በግልጽ ያስቀመጠ ቢሆንም ቀደም ባለው ጊዜ ሰራዊቱ የሚገነባበት የፖለቲካ ኢንዶክትሪኔሽን ህገ መንግስቱ ካስቀመጠው ከሰራዊቱ ዓላማና የግንባታ መርሆዎች አንጻር በተጻራሪው በአብዮታዊ ዴሞክራሲ አስተሳሰብ ፤ በአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ርዕዮተ ዓለም ላይ የሚያተኩርና የሚያጠነጥን እንደነበር አመልክተዋል ። የተለያዩ ርዕዮተ ዓለም እና አመለካከቶች ያላቸው ፓርቲዎች ህገ መንግስታዊ እውቅና አግኝተው እየተንቀሳቀሱ ባሉበት አገር፤ ሰራዊቱን በአንድ ፓርቲ ፕሮግራም ላይ፣ በአንድ ፓርቲ ርዕዮተ ዓለም ላይ መቅረጽና መገንባት ተገቢ እንዳልነበር ጠቁመዋል፡፡ በሪፎርሙ ከተከናወኑ ስራዎች አንዱ እና ትልቁ ሰራዊቱ የሰራዊት ግንባታ ዓላማ እና የሰራዊቱ ተልዕኮ ከየትኛውም የፓርቲ ፕሮግራም ወይም ርዕዮተ ዓለም በላይ እንዲሆን ማድረግ ነው ብለዋል ፡፡በሪፎርሙ ሰራዊቱ በህገ መንግስቱ የተሰጠውን ተልእኮ በግልጽ አውቆ ለህገመንግስቱ ብቻ ታማኝ እንዲሆን በሚያስችል አስተሳሰብ እንዲገነባ ተደርጓል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ፣ የሰራዊቱ ህገ መንግስታዊ ተልዕኮ እጅጉን የገዘፈ ፤ከአንድ ፓርቲ ፕሮግራምና ዓላማ በላይ የሆነ ፣ የተከበረ፤ የአገርን ሉዓላዊነት፤ የሕዝብ ደህንነት ላይ መሰረት ያደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል። “ኢትዮጵያን እኔ ከሌለሁ ትፈርሳለች ወይም እኔ ካልተጠቀምኩ እናፍርሳት የሚለው አካል ሁል ጊዜ ቢናገርም፤ በእኔ በኩል ኢትዮጵያን የምትፈርሰው መጀመሪያ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ላይ የሚያምኑት ሕዝቦቿ እና መሪዎቿ ከሌሉና ከሌሉ ብቻ ነው ፡፡ ከዛ በላይ ኢትዮጵያ የምትፈርሰው የመከላከያ ኃይላችን፣ የፀጥታ ኃይላችን፣ የደህንነት ኃይላችን ሲፈርስ፤ ወይም እሱ መስዋዕት ሆኖ ሲሸነፍ ብቻ ነው:: ስለዚህ አሁን ያለን የሪፎርም ስራዎች የአገራችንን ገናናነትና ሉዓላዊነት የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርግ ስርዓት መፍጠር ላይ ያተኮረ ነው፤ የሰራዊት ግንባታውም እንዲሁ ፡፡ በአስተሳሰብም በተግባርም ኢትዮጵያን የበለጠ የሚያጠናክር ስራ ነው እየተሰራ ያለው” ብለዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 18/2012 ወንድወሰን ሽመልስ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35947
7392ec68f61734b486515b3a602b4bf1
29a3ca6fe64130b8ae9da47b7bfb9a71
በኮሮና ምክንያት ችግር የደረሰባቸው 30 ሺ 87 ዜጎች ከስደት ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል
አዲስ አበባ ፤ በተለያዩ ሀገራት በስደት ላይ የነበሩ እና በኮሮና በሽታ ምክንያት ችግር ውስጥ የወደቁ 30ሺህ 87 ኢትዮጵያውያን ወደሀገር ውስጥ መመለስ መቻሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ ዜጋ ተኮር የመንግስት ፖሊሲ ተግባራዊ በመደረጉ በኮሮና ምክንያት ለችግር የተጋለጡ እና በስደት የነበሩ 30ሺህ 87 ኢትዮጵያውያንን ወደሀገራቸው መመለስ ተችሏል። በፍቃደኝነት ወደሃገራቸው የተመለሱ ዜጎች በአብዛኛው ከገልፍ እና ከጎረቤት ሀገራት የመጡ ናቸው።አምባሳደር ዲና እንደገለጹት፤ በተለይ በአረብ ሀገራት እና በጎረቤት ሀገሮች በስደት የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በኮሮና በሽታ ወቅት ስራ በማጣት ጎዳና ላይ ሲወድቁ በየሀገራቱ የሚገኙ ቆንስላዎች ክትትል አድርገዋል። በተለይ በቤይሩት ከስራ ተባረው እና በመንገድ ላይ ተጥለው የነበሩ ኢትዮጵያውያንን በቆንስላው አማካኝነት ድጋፍ በማድረግ በፍቃደኝነት መመለስ ተችሏል። በዚህ መሰረት ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ከተደረጉ 30ሺ በላይ ዜጎች መካከል ከቤይሩት 656 ዜጎች፤ ከአቡዳቢ 72፤ ከሳዑዲ አረቢያ 3ሺህ 539፣ ከኩዌት ደግሞ 1 ሺህ 23 ዜጎች እንዲሁም በድንበር በኩል ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት 4ሺህ 792 ዜጎች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።እንደ አምባሳደር ዲና ከሆነ፤ መንግስት በሚከተለው የዜጋ ተኮር ፖሊሲ መሰረት አሁንም በስደት ላይ ለእንግልት የተዳረጉ ዜጎች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ጥረት እየተደረገ ይገኛል። ለአብነት በየመን የቆየ ጦርነት በመኖሩ ምክንያት የት እንዳሉ እና ምን ያክል ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ ከተባበሩት መንግስታት እና ከተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ጋር ክትትል እየተደረገበት ይገኛል። በመሆኑም በቀጣይ ከተለያዩ ሀገራት የሚመለሱ ዜጎች ይኖራሉ። ወደሀገራቸው በፍቃደኝነት ከተመለሱ በኋላም እንዲቋቋሙ ይደረጋል። በዚህ ረገድ ቀጣይነት ባለው መልኩ የማቋቋም ስራው መሰራት እንዳለበት በመንግስት ደረጃ አቅጣጫ ተይዟል።በሌላ በኩል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በአባይ ግድብ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ የዘንድሮው የክረምት ዝናብ ውሃ ከፍተኛ መጠን ነበረው። በዚህም ምክንያት የግድቡን የመጀመሪያ ዙር ውሃ ሙሌት ከታሰበው ጊዜ በፊት ማጠናቀቅ ተችሏል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 18/2012ጌትነት ተስፋማርያም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35961
afc158fa6d5c0f8ce12cc341aadb11ac
4445dba796870b36dd5a52fcd576a6cf
«የስፖርት ፖሊሲው መከለስ አለበት» – አቶ ባዘዘው ጫኔ የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽነር
እኔም አመሰግናለሁ። ክልላችን የበርካታ ስፖርቶች ጸጋ ያለው ሲሆን፤ ዘርፉም እንደየትኛውም የልማት ሥራ በስትራቴጂክ ዕቅድ ይመራል። በአንድ በኩል የክልሉ ህዝብ በስፖርቱ ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በማድረግ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለሃገራዊ ዘርፉ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት በሚያስችል አኳኋን እየተንቀሳቀስንም እንገኛለን። በአጠቃላይ 22 ስፖርቶች ሲዘወተሩ፤ ከዚህ መካከል ከክልሉ ልዩ ባህሪ፣ የአየር ንብረትና የቦታ አቀማመጥ አኳያ ምቹ የሆኑት ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን። እነዚሀም አትሌቲክስ፣ ውሃ ዋና እና ብስክሌት ሲሆኑ፤ የወጣቱ ተሳትፎም እየጨመረ ነው። እንደ ሃገርም ክልላችን ምርጥ ስፖርተኞችን በማበርከት ሲታወቅ፤ ከዓመት ዓመት ዕድገት በማሳየት ላይም ይገኛል። በስፖርት መሰረተ ልማትም በእያንዳንዱ ቀበሌ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ እንዲኖር፣ በወረዳና ዞኖች መካከለኛ ስታዲየሞች እንዲሁም በትልልቅ ከተሞች ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች እንዲገነቡ ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል። ከትልልቆቹ መካከልም የክልሉ መንግሥት የሚያስገነባው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀውና 50ሺ ተመልካቾችን በመያዝ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የባህር ዳር ስታዲየም ይነሳል። በክቡር ዶክተር ሼህ መሃመድ አሊ አላሙዲ የተገነባውና ከሁለት ዓመት በፊት የተጠናቀቀው የወልዲያ ስታዲየምም እንዲሁ። የመጀመሪያው ነገር ፖሊሲውም የሚጠቁመው ስፖርቱን ህዝባዊ ማድረግ ነው። ከዚህ አንጻርም የተሳካልን ህዝቡ ስፖርቱን እንዲመራ እንዲሁም ሀብት በማሰባሰብና በስፖርቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው። ለምሳሌ መላው የክልላችን አርሶ አደር በክፍያ ለስፖርቱ አስተዋጽኦ ያበረክታል። የመንግሥት ሠራተኛውም ከደሞዙ በፍቃደኝነት ይከፍላል፤ በእርግጥ አሁን መቀዛቀዝ አለ። እንደ አጠቃላይ ግን ከስፖርቱ ልማት ተጠቃሚ የሚሆነው ህዝቡ ራሱ በመሆኑ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደርጋል። ሌላው የሚያኮራው ተግባር የክልላችን ህዝብ በየትኛውም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርገው ድጋፍ ነው። በዚህ ዓመት በስፖርታዊ ጨዋነት የተሻለ ነገር ታይቷል። በአማራና ትግራይ ክለቦች መካከል በነበረው ችግር በራሳቸው ሜዳ እንዳይጫወቱ መደረጉ የሚታወስ ነው። የፌዴራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ስፖርት ኮሚሽን፣ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ስፖርት ቢሮዎች፣ ክለቦች እንዲሁም ደጋፊ ማህበራት በቅንጅት ባደረጉት እንቅስቃሴ የሁለቱ ክልል ክለቦች በየሜዳቸው በጨዋነት ሲጫወቱ ቆይተዋል። በክልላችን የተካሄዱት ጨዋታዎችም አስተማማኝ ጸጥታ ነበር። ይህም በዚህ ዓመት ውጤታማ ከሆንባቸው ሥራዎች መካከል ይጠቀሳል። ክልላችን ለአትሌቲክስ ስፖርት በጣም ምቹ ነው፤ ስለሆነም ልዩ ጸጋ ያላቸውን ስፍራዎች ለይተን ስምንት የሚሆኑ የአትሌቲክስ ማዕከላትን በመገንባት ላይ እንገኛለን። የደብረ ብርሃን፣ ቲሊሊ፣ ደጋ ዳሞት፣ ኮን፣ ጉና፣ ደባርቅ፣… ማዕከላት ተጠቃሽ ሲሆኑ፤ ተስፋ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች ከፕሮጀክት ተመልምለው ይሠለጥኑበታል። ቀደም ብሎ የተቋቋመው የደብረብርሃን ማዕከል በየዓመቱ 40 ታዳጊዎችን በመቀበል የሚያሰለጥንና ብቃት ያላቸው አትሌቶችን እያፈራ ይገኛል፤ ሌሎቹም ወደዚሁ መስመር እየገቡ ነው። በውሃ ዋና ስፖርትም ጸጋው ባለባቸው አካባቢዎች፣ ለምሳሌ ባህርዳር ዙሪያ፣ ጎንደር እና ኮምቦልቻ አካባቢ ክለቦችን በማቋቋም ምርጥ ስፖርተኞችን የማሳደግ ሥራ እየተከናወነ ነው። ሌላው በክልሉ ትልቅ አቅም ያለው የስፖርት ዓይነት ብስክሌት ነው። በባህር ዳር እንደሚታወቀው ብስክሌት ሳይዝ የሚንቀሳቀስ ወጣት የለም። ይህ ደግሞ ትልቅ ዕድል ነው፤ ከዚህ አኳያም ጥረት የሚባል አንድ ክለብ አለን። በቂ ባይሆንም ሌሎች ክለቦችን ለማቋቋም እሠራን እንገኛለን። ስፖርቱ እንዲዘወተርና የክልሉ መገለጫ እንዲሆንም ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ላይ ነን። እውነት ነው፤ በክልሉ ትልቅ ጸጋ አለ። ከክልሉም አልፎ ለሃገርም ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ስፖርተኞችን ማፍራት ይቻላል። በመሆኑም በቅድሚያ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እያከናወንን ነው። አሁን አሁን ከከተማ ባለፈ በገጠሩ አካባቢም ህበረተሰቡ ለመጓጓዣነት እየተጠቀመ መሆኑ መልካም ዕድል ነው። በመሆኑም ይህንን መለያው እንዲያደርግ ግንዛቤ እያስጨበጥን ነው። ሌላው ከዚህ ቀደም የተቋቋመውን የጥረት ክለብ የማጠናከር ሥራ ነው። በእርግጥ አሁን አሁን አንዳንድ ጥያቄዎች እየተነሱ በውይይት ላይ ነው ያለነው። ጥረት ከአቅም በላይ እንደሆነበትና ወደ ሌላ የልማት ሥራ መዞር ስላለበት ክለቡን ወደ ሌላ እንዲዞርለት አስታውቋል። እኛም ይህ መሆን እንደሌለበትና ክለቡ የህዝብ በመሆኑ የሚከፈለውን ዋጋ ከፍሎ ይዞ እንዲቀጥል አሳስበናል። ሦስተኛው ሥራችን ደግሞ ቁሳቁስ የማሟላት ነው፤ ዘመናዊ ብስክሌቶች አስፈላጊ በመሆኑ ከዚህ ቀደም ገዝተን ነበር። አሁንም በድጋፍ ከፍተኛ ወጪ አውጥተን ከውጭ ዘመናዊ ብስክሌቶችን አስገብተናል። እነዚህ በቂ ናቸው ማለት አይደለም፤ በቀጣይም የሚመለከታቸውን አካላት በማስተባበር ድጋፉን እንቀጥላለን። የውስጥ ውድድሮችን ለማዘጋጀት እንዲሁም ሃገር አቀፍ ውድድሮች ላይ ለምናደርገው ተሳትፎ ትኩረት እንሰጣለን። በዚህ ሂደትም ምርጥ ስፖርተኞችን የማውጣትና የመለየት እንዲሁም ተሳትፎውን የማሳደግ ስራ እየተከናወነ ነው። በዓመቱ በተካሄዱ ሃገር አቀፍ ተሳትፎዎች ያስመዘገብነው ውጤትም መልካም በመሆኑ ደረጃችንን እንዳሻሻልን ማንሳት ይቻላል። ሃገር አቀፍ ውድድሮች ላይ ለመድረስ ከታች መጀመር አስፈላጊ ቢሆንም፤ በወረዳዎችና ዞኖች የገንዘብ እጥረት ስለሚያ ጋጥም የማይሳተፉባቸው አጋጣሚዎች አሉ። በመሆኑም ማስተካከያ ማድረግ እንደ ሚያስፈልግ ለይተናል። ሌላው በአንዳንድ ስፖርቶች ላይ በሚኖረን የውድድር ተሳትፎ በቂ ስፖርተኞችን አለማሳተፍ ይታያል ይህንንም ማስተካከል ይገባናል። እስከአሁን ያልተፈታውና መንግሥትም ትኩረት ቢሰጠው የምለው ስፖርት ከፍተኛ ሀብት የሚጠይቅ እንደ መሆኑ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ብቻ ማሳደግ አይቻልም። በመሆኑም መንግሥት ዘለቄታዊ መፍትሔና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። የስፖርት ፖሊሲውም መከለስ አለበት። ከ20 ዓመት በላይ የቆየ በመሆኑ አሁን ከደረስንበት ደረጃ አኳያ መከለስ ይኖርበታል። ይዘቱ በዚያን ወቅት መልካም ቢሆንም፤ አሁን ስፖርቱ የደረሰበትን እንዲሁም ሃገሪቷ ያለችበትን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የዕድገት ደረጃ ግምት ውስጥ አስገብቶ በድጋሚ መቀረጽ አለበት። ብዙ ጥረት የሚጠይቀው ሌላው ሥራ አደረጃጀትን የሚመለከት ነው። እኔ ወደዚህ ቦታ ከመጣሁ እንኳ ስፖርቱ አንዴ ራሱን ሲችል ሌላ ጊዜ ከሌላው ጋር ሲለጠፍ ቆይቷል፤ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም። በእርግጥ አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ሁሉ አደረጃጀት መታየት አለበት፤ ነገር ግን ለውጥ በመጣበት ጊዜ ሁሉ ይህንን ማድረግ ሴክተሩን የሚያሳድግ መስሎ አይሰማኝም። በመሆኑም ወጥበት ኖሮት እንዲቀጥል ማድረግና ትኩረት መስጠት ይገባል። የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በያሉበት ከልሎ ማልማትም ያስፈልጋል፤ ለዚህም አስገዳጅ የህግ ማዕቀፍ ያስፈልጋል። የፍቃደኝነት ሥራ ካደረግነው ረጅም ጊዜ ይወስድብናል፤ እንደ ውሃ እና መብራት ማዘውተሪያ ስፍራዎችም አስገዳጅ ማዕቀፍ ሊኖራቸው ይገባል። ይህንንም በፌዴራል ደረጃ እያነሳን እንገኛለን። የመጀመሪያውና ትኩረት ልንሰጠው ያቀድነው የህዝብ አደረጃጀትን ማጠናከር ነው። ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ ህዝባዊ አደረጃጀቶችን የማጠናከርና ባለቤት ሆነው እንዲመሩት ያስፈልጋል። የማዘውተሪያ ስፍራዎች በስታንዳርዱ መሰረት በሁሉም አካባቢ ህጋዊ ሆነው እንዲለሙና እንዲስፋፉ ማድረግም ሌላኛው ነው። የስፖርት ዘላቂነትን ካሰብን ተተኪዎች መኖር ይገባቸዋል። የፕሮጀክት ስልጠናን አጠናክሮ በመያዝና ውጤታማ በሆነ አኳኋን መምራት ስለሚያስፈልግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንሠራለን። ክለቦች ከሌሉ ስፖርተኛን በተናጥል አንቀሳቅሶ ውጤታማ መሆን ያስቸግራል። በመሆኑም በሁሉም ስፖርት ክለቦችን ለማቋቋም ተቋማትን፣ ባለሀብቶችን፣… ለማሳተፍ ጥረት ይደረጋል። የመጨረሻው ደግሞ ሀብት ማሰባሰብ ነው፤ እንደሚታወቀው ስፖርት ከፍተኛ ሀብት የሚፈልግ ዘርፍ ነው። በመሆኑም ይህንን መሸከም የሚችል ሀብት ማሰባሰብ ትኩረት ሰጥተን የምንሠራው ነው።አዲስ ዘመን ሰኔ 17/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13143
e31020afdc079ae0710033d0dfcd0989
48e3deeca13a23c29b78b84459da045a
በአፍሪካ ዋንጫ የዛሬ ምድብ ጨዋታዎች
በውድድር ጊዜው እንዲሁም በተሳታፊ ሃገራቱ ብዛት ላይ ለውጥ በማድረግ እየተካሄደ ያለው 32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ አራተኛ ቀኑ ላይ ደርሷል። ዛሬ በሁለት ምድቦች ጨዋታዎች የሚከናወኑ ሲሆን፤ ምድብ አራት ኮትዲቯርን ከደቡብ አፍሪካ ያገናኛል። ከምድብ አምስት ደግሞ ቱኒዚያ ከአንጎላ እንዲሁም ማሊ ከሞሪታኒያ የሚጫወቱ ይሆናል። ከምድብ አራት ኮትዲቯርና ደቡብ አፍሪካን ለሚያገናኘውም ጨዋታ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷል። ይህንን ውድድር ለማዘጋጀት ፍላጎት አሳይታ ያልተሳካላት ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ ዋንጫ መድረክ ስኬትን ያስመዘገበችው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። እአአ በ1996 ባስተናገደችው ውድድር ዋንጫውን በሃገሯ ካስቀረች ወዲህም ሻምፒዮን ልትሆን አልቻለችም። ዝሆኖቹ በበኩላቸው እአአ በ1992ቱ የሴኔጋል እንዲሁም እአአ በ2015ቱ የኢኳቶሪያል ጊኒ የአፍሪካ ዋንጫዎች ላይ አሸናፊ በመሆን ከተጋጣሚያቸው የተሻለ ውጤት አላቸው። ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም የተገናኙባቸው ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ የበላይነት የተጠናቀቀ ቢሆንም፤ የዚህ ጨዋታ የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ግን ወደ ዝሆኖቹ አድልቷል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በካይሮ በሚገኘውና 30ሺ ሰዎችን በሚይዘው አልሰላም ስታዲየም የሚከናወን ይሆናል። በአውሮፓ ክለቦች በሚጫወቱ ወጣቶች የተዋቀረው የኮትዲቯር ብሄራዊ ቡድን ዘንድሮ ለዋንጫ ይደርሳል የሚል ቅድመ ግምት ባያገኝም ጠንካራ ከሚባሉት ቡድኖች መካከል ይጠቀሳል። የመጨረሻ የወዳጅነት ጨዋታቸውን ከዩጋንዳ ጋር ያደረገው ቡድኑ 1ለ0 በሆነ ውጤት ነበር የተረታው። ሆኖም በዛሬው ጨዋታ አሸናፊ ለመሆን የሚጫወቱት ዝሆኖቹ ዋንጫውን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ አቅደው ተሳትፏቸውን እያደረጉም ይገኛሉ። ባፋና ባፋናዎች እአአ 2015 እና 2017 የአፍሪካ ዋንጫዎች ላይ ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገቡ መሆኑን ተከትሎ በዚህ ውድድር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚጫወቱ መሆኑን የቡድኑ አባላት ይገልጻሉ። ሞሮኮ፣ ኮትዲቯርና ናሚቢያ ከተደለደሉበት ምድብ የሚገኘው ቡድኑ የረጅም ጊዜ የዋንጫ ረሃባቸውን ለማስታገስ ወደ ግብፅ እንደተጓዙም አስታውቀዋል። በቤልጂየም በሚገኘው ክለብ የሚጫወተው ፔርሲ ታኡ ከቢቢሲ ባደረገው ቆይታ፤ ምድቡ ጠንካራ የሚባል ቢሆንም ቡድናቸው ግን ከዚህ ቀደም ካስመዘገበው ውጤት የተሻለ ነገር ለማስመዝገብ የሚጫወት መሆኑን ጠቁሟል። አሰልጣኝ ስትዋርት ባክስተር ቡድኑን ከተቀላቀሉ በኋላም በቡድኑ የራስ መተማመን ስሜት እንደጎለበተም ተጫዋቹ ጠቅሷል። እኛም የአሰለጣጠኑን እንዲሁም አጨዋወቱን ተከትለን በመጫወት የተሻለ ውጤት እንደምናስመዘግብ እናምናለን። እርሱ ቡድኑን ከያዘ ጀምሮም ቡድኑ ለውጥ በማሳየት ላይ ይገኛል ሲልም አክሏል። በምድብ አምስት ሁለት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን፤ ቱኒዚያ ከአንጎላ እንዲሁም ማሊ ከሞሪታኒያ ይገናኛሉ። በዚህ ምድብ የተሻለ ግምት የሚሰጠው ብሄራዊ ቡድንም የቱኒዚያ ነው። የካርቴጅ ንስሮች በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ቡድኑ እአአ በ2004 ዋንጫውን በሃገሩ ማስቀረቱ የሚታወስ ነው። አንጎላ በመድረኩ የሚጠቀስ ውጤት የሌላት ከመሆኑ ባሻገር በምድቡ አስፈሪ ሊባል የሚችል ቡድን ባለመኖሩ ቱኒዚያ በቀላሉ ከምድቧ ማለፍ እንደምትችል ይጠበቃል። በፊፋ ማስጠንቀቂያ ሲሰነዘርባት የቆየችው ማሊም በመድረኩ አዲስ ገቢ የሆነችውን ሞሪታኒያን ታስተናግዳለች። እአአ 1972 ለፍጻሜ የደረሰችው እንዲሁም 2012 እና 2013 ሦስተኛ በመሆን ውድድሯን ያጠናቀቀችው ማሊ አዲሲቷን ሃገር በቀላሉ ልትረታ እንደምትችልም ይገመታል። በነገው ዕለትም የምድብ ስድስቶቹ ሻምፒዮናዋ ካሜሩን ከጊኒ-ቢሳዋ እና ጋና ከቤኒን የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።አዲስ ዘመን ሰኔ 17/2011 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13146
c75fd5f862a25a28d05eb4ca761faaf0
186529f7b60d89b46b4ce0fea00acab4
የወርቃማዎቹ እንስቶች የዳይመንድ ሊግ ፍጥጫ
 ውድድር ዓመቱ የዳይመንድ ሊግ ፉክክሮች እየተጋመሱ መጥተው የአሜሪካዋ ዩጂን ከተማ ደርሰዋል፡፡ ዩጂን ዛሬ በተለያዩ ርቀቶች በርካታ ፉክክሮችን ስታስተናግድ በሴቶች መካከል የሚካሄደው የሦስት ሺ ሜትር ውድድር ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ሆኗል፡፡ የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮኗ ኢትዮጵያዊት አትሌት አልማዝ አያና ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ውድድር ተመልሳ የመጀመሪያ ፉክክሯን ዩጂን ላይ ታደርጋለች፡፡ አልማዝ ወደ ውድድር መመለሷ ለፉክክሩ ድምቀት የሰጠው ሲሆን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ ምድር በርካታ የዓለማችን ድንቅ አትሌቶች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡ ከነዚህም መካከል አልማዝን ጨምሮ ገንዘቤ ዲባባ፣ሔለን ኦቢሪ፣ሲፈን ሃሰን፣ካስተር ሲሜንያና ሌሎችም ድንቅ የመካከለኛና የረጅም ርቀት አትሌቶች ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። በውድድር ዓመቱ አምስት ሺ ሜትርን በበላይነት ተቆጣጥራ የያዘችው ኬንያዊቷ ኮከብ አትሌት ሔለን ኦቢሪ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የዳይመንድ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ ለመሆን የምታደርገውን ጉዞ በዩጂን አጠናክራ እንደምትቀጥል ይጠበቃል። የሃያ ዘጠኝ ዓመቷ ኦቢሪ የዓለም ቻምፒዮን ከመሆኗ ባሻገር በዘንድሮው ዓመት በአገር አቋራጭ ቻምፒዮና ወርቅ ማጥለቅ ችላለች፡፡ ባለፈው ሪዮ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ካጠለቀች ወዲህም በለንደን አትሌቲክስ ቻምፒዮና ወርቅ ማጥለቋ ይታወሳል። ከ1500 ሜትር ሯጭነት ተነስታ በረጅም ርቀት ኮከብ አትሌት መሆን የቻለችው ኦቢሪ እኤአ 2013 ላይ በዚሁ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ድንቅ ብቃት አሳይታለች፡፡ 2014 ላይም በአሜሪካ ምድር የምን ጊዜም ፈጣን ሰዓት የሆነውን 3፡57፡05 ማስመዝገቧ በዛሬው ውድድር ከፍተኛ የአሸናፊነት ግምት እንዲሰጣት አድርጓል፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን 2015 ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የዳመንድ ሊግ ውድድር አሸናፊ መሆኗ የሚታወስ ሲሆን በ2016 አሜሪካ ፖርትላንድ የቤት ውስጥ የዓለም ቻምፒዮና ወርቅ ማጥለቅ ችላለች፡፡ ሲፈን ያለፈውን የ2017 ውድድር ዓመትን በተለያዩ ሦስት ርቀቶች ከምርጥ አምስት አትሌቶች ውስጥ መካተት ችላለች። ከ8 መቶ ሜትር እስከ 5 ኪሎ ሜትር ድንቅ ብቃት ማሳየት የቻለችው ሲፈን ባለፈው የውድድር ዓመት በ5ኪሎ ሜትር ሁለተኛና በ1500 ሜትር ሦስተኛ ሆና ማጠናቀቅ ችላለች፡፡ ዘንድሮም ሲፈን በድንቅ አቋም ላይ የምትገኝ አትሌት መሆኗ በዩጂን ለአሸናፊነት ከሚጠበቁ አትሌቶች አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡ ከፆታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ውዝግብ ውስጥ የምትገኘው ደቡብ አፍሪካዊት ካስተር ሲሜንያ በዩጂን ዳይመንድ ሊግ መካተቷ ውድድሩን በተወሰነ ደረጃውን ከፍ እንዲል አድርጓታል፡፡ የሁለት ኦሊምፒክና ሦስት የዓለም ቻምፒዮና አሸናፊዋ ሲሜንያ በ8መቶ ሜትር ለሰላሳኛ ጊዜ ያለመሸነፍ ጉዞዋን ማስጠበቅ በመቻሏ አድናቆትን አትርፋለች። ከለመደችው የመወዳደሪያ ርቀት ከፍ ብላ በሦስት ሺ ሜትር የምታደርገውን ፉክክርም በተደጋጋሚ ማሸነፍ እንደምትችል ማሳየቷን ተከትሎ ለርቀቱ ኮከቦች ፈተና እንደምትሆን ይጠበቃል፡፡ የ28 ዓመቷ ድንቅ የመካከለኛና ረጅም ርቀት አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ከሰባት በላይ የዓለም ክብረወሰኖችን መያዝ የቻለች ሲሆን በዩጂን ባለፉት ሦስት የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች የተፎካከረችው በ5 ሺ ሜትር ነው፡፡ በተለይም 2015 ላይ በዚሁ በ5ሺ ሜትር 14:19.76 በመሮጥ በአሜሪካ ምድር የምንጊዜም ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ ችላለች። ገንዘቤ ባለፈው ዓመት በዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና በ1500ና 3 ሺ ሜትር ጥምር ወርቅ በማጥለቅ የመጀመሪያዋ የዓለማችን አትሌት መሆን ችላለች። በዘንድሮው ዓመት 1500 ሜትርን 359፡08 አስመዝግባ ማሸነፍ የቻለች ሲሆን በ3 ሺ ሜትር ደግሞ በዶሃ ዳይመንድ ሊግ ኬንያዊቷ ኦቢሪን ተከትላ 8:26.20 ሰዓት ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ ከጉዳት ተመልሳ የመጀመሪያ ውድድሯን የምታደርገው አልማዝ በሪዮ ኦሊምፒክ 10ሺ ሜትርን 29፡17፡45 በሆነ የዓለም ክብረወሰን ሰዓት ማሸነፏ የሚታወስ ሲሆን 2016 ላይ የ5ሺ ሜትር የዳይመንድ ሊጉ አጠቃላይ አሸናፊ ነበረች። በ2015 የቤጂንግ የዓለም ቻምፒዮና የውድድሩን ክብረወሰን በማሻሻል በ5ሺ ሜትር ስታሸንፍ በ2017 የዓለም ቻምፒዮና በ10ሺ ሜትር ወርቅ ማጥለቋ አይዘነጋም፡፡ ካለፈው አንድ ዓመት በላይ ግን አልማዝ በጉዳት ከውድድር ርቃ ቆይታለች። ይህም በክረምቱ መጨረሻ ኳታር ለምታዘጋጀው የዓለም ቻምፒዮና አትደርስም የሚል ስጋት ፈጥሮ ነበር፡፡ አልማዝ አሁን ልምምዷን በተገቢ ሁኔታ እያከናወነች ሲሆን የዩጂን ዳይመንድ ሊግም ድንቅ ብቃቷን ታሳይበታለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በ2015 የቤጂንግ የዓለም ቻምፒዮና የ5ሺ ሜትር ውድድር በበርካቶች ዘንድ አሁንም ድረስ ይታወሳል፡፡ በዚያ ውድድር አልማዝ አያና ከሦስት ሺ ሜርት በኋላ አፈትልካ በመውጣት ውድድሩን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ በሁለተኛነት የማጠናቀቅ ሰፊ እድል የነበራት ገንዘቤ ዲባባ ነበረች፡፡ ይሁን እንጂ ገንዘቤ ውድድሩን ለመጨረስ ከሃምሳ ሜትር ያነሰ ርቀት በቀራት ወቅት ሰንበሬ ተፈሪ ከኋላ መጥታ የብር ሜዳሊያውን ማጥለቋ ይታወሳል፡፡ ሰንበሬ በዩጂኑ ውድድር እነዚሁን የአገሯን ልጆች ጨምሮ ሌሎች ኮከቦች በሚፎካከሩበት ዳይመንድ ሊግ ተካታለች፡፡ ለተሰንበት ግደይና ፋንቱ ወርቁ በዚህ ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ናቸው፡፡አዲስ ዘመን ሰኔ 23/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13329
b1d8f8ea0b21287c8d35dcb50a3267bd
077088a66213e3bade2344cea1c4e6d1
የአፍሪካ ወርቃማ እግሮች
በአፍሪካ አህጉር የእግር ኳስ ታላቁ ድግስ ከተጀመረ ሁለተኛ ሳምንቱን አስቆጥሯል። ግብጽ 32ኛውን አፍሪካ ዋንጫ ድግስ በካይሮ፣ አሌክሳንድሪያ፣ ኢስማኤሊያ እና ስዊዝ በተባሉት ከተሞቿ እያስተናገደችው ትገኛለች። በአውሮፓ ሊጎች ስመ ጥር የሆኑት፤ ሞሃመድ ሳላህ፣ ሳዲኦ ማኔ፣ ናቢ ኬታ፣ ሪያድ ማህሬዝ፣ ሃኪም ዚያክ፣ ኒኮላስ ፔፔ፣ ዊልፍሪድ ዛሃ፣ ሙሳ ማሬጋ፣ ካሊዱ ሉሊባሊ እና ቶማስ ፓርቴን የመሳሰሉ ተጫዋቾችም በውድድሩ በመፋለም ላይ ይገኛሉ። በርካታ አዳዲስ ነገሮች የታዩበትን የዘንድሮውን የአፍሪካ ዋንጫ፤ ለአሸናፊነት ከሚደረገው ፍልሚያ ባሻገር አህጉራቸውን ተሻግረው በሌላው ዓለምም ተጽእኖ መፍጠር የቻሉ አንጋፋ ተጫዋቾች እያደመቁት ይገኛሉ። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ ሰባት የአህጉሪቷን ባለ ወርቃማ እግር ተጫዋቾች በአምባሳደርነት ሰይሟል። በአፍሪካ የምንጊዜም ታላላቅ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ተርታ ከሚሰለፉት መካከል አንዱ የውድድር አዘጋጇ ሃገር ግብጽ የቀድሞ ተጫዋች ሞሃመድ አል ቃቲብ ነው። አንጋፋው ተጫዋች እአአ በ1983 ፈርኦኖቹ የመጀመሪያውን ዋንጫ ሲያነሱ ከቡድኑ አባላት መካከል ነበር። «ቢቦ» በሚል ቅጽል የሚጠራው ተጫዋቹ ሃገሩ አዘጋጅታ ሻምፒዮን የሆነችበትን እአአ የ1986 የአፍሪካ ዋንጫን አንስቷል። በአፍሪካ ዋንጫ ግብ በማስቆጠር ቀዳሚውን ስፍራ የተቆናጠጠው ካሜሩናዊው ሳሙኤል ኤቶም በዚህ ውድድር በአምባሳደርነት የተገኘ ተጫዋች ነው። በባርሴሎና እና ኢንተርሚላን የተሳካ ጊዜ ማሳለፍ የቻለው ኤቶ ለአራት ጊዜያት (እአአ በ2003፣ 2004፣ 2005 እና 2010) የካፍ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ የተመረጠ ታሪካዊ ተጫዋች ነው። ኤቶ ከካሜሩን ብሄራዊ ቡድን ጋር በመሆንም እአአ የ2000 እና 2002 የአፍሪካ ዋንጫዎችን አንስቷል። ኮትዲቯራዊያኑ ያያ ቱሬ እና ዲድየር ድሮግባም በውድድሩ በአምባሳደርነት ተሰይመዋል። በሌላው ዓለምና በሃገሩ ከምርጥ ተጫዋቾች መካከል ተጠቃሽ የሆነው ያያ ቱሬ፤ ካፍ በተከታታይ ለአራት ዓመታት (እአአ ከ2011-2014) ምርጥ ተጫዋች ሲል መርጦታል። ሃገሩ እአአ በ2015 ሻምፒዮን ስትሆንም ተጫዋቹ ከቡድኑ ጋር ነበር። ሌላኛው የሃገሩ ልጅ ተወዳጁ ዲድየር ድሮግባ በአምስት የአፍሪካ ዋንጫዎች (እአአ 2006፣ 2008፣ 2010፣ 2012 እና 2013) ሃገሩን ወክሎ ለፍጻሜ በቅቷል። በታወቀበት የእንግሊዙ ክለብ ቼልሲ እንዲሁም ለሃገሩ ብሄራዊ ቡድን ባበረከታቸው አስተዋጽኦዎች ስሙ የሚወሳው ድሮግባ እአአ በ2006 እና 2009 የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋች በሚል ተመርጧል። እአአ በ1990 አልጄሪያ የአፍሪካ ዋንጫን በምድሯ አሰናድታ ዋንጫውን ያስቀረችበት ቡድን አባል የሆነው ራቤህ ማጀር፤ በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ ካፍ በአምባሳደርነት ከሾማቸው የወርቃማ እግር ባለቤቶች መካከል አንዱ ነው። ተጫዋቹ በተለይ በፖርቹጋሉ ክለብ ፖርቶ ያደርግ በነበረው እንቅስቃሴ ስሙ የሚነሳ ሲሆን፤ እአአ በ1987 ለአፍሪካ ክብር በቅቷል። ዋንኮ ካኑ ሌላኛው ከናይጄሪያ ተገኝቶ በአፍሪካ አህጉር ደምቀው ከታዩት ኮከቦች መካከል የሚገኝ ነው። እአአ ከ2000 – 2010 በተካሄዱት ስድስት የአፍሪካ ዋንጫዎች የተሳተፈው ይህ ተጫዋች እአአ 1996 እና 1999 የካፍ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ነው። በካሜሩን ብሄራዊ ቡድን ከፍተኛ ስፍራ ያለው አል ሃጂ ዲዩፍም ከአምባሳደሮቹ መካከል አንዱ ነው። እአአ በ2000 አካባቢ በዓለም ዙሪያ ስመጥር የሆነውና ወርቃማው ትውልድ በሚል የሚታወቀው ቡድን አባል የሆነው ዲዩፍ እአአ በ 2001 እና 2002 የአፍሪካን ክብር ሊቀዳጅ ችሏል። አዲስ ዘመን ሰኔ 24/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13367
62c402752184cfad438c1784eab0de44
13d2c48a2cd4e4fa3592edecfcaae8c6
የስነ – ዜጋ እና ስነ-ምግባር ትምህርት ለወጣቶች የህግ የበላይነትን የማስገንዘብ ክፍተት እንዳለበት ተገለጸ
አዲስ አበባ፡- የስነ-ዜጋ እና ስነ-ምግባር ትምህርት በሃገራችን ለሚገኙ ወጣቶች የህግ የበላይነትን የማስገንዘብ ክፍተት እንደነበረበት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተው ችግር ማሳያ እንደሆነ ተገለጸ። በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለምአቀፍ ትምህርት መምህር እና የትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም የስነምግባር መምህር የሆኑት ዶክተር ሞገስ ደምሴ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የስነ – ዜጋ እና የስነ-ምግባር ትምህርት በሀገራችን ለሚገኙ ወጣቶች የህግ የበላይነትን የማስገንዘብ ክፍተት ነበረበት። ተጨባጭ ማሳያውም ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተው ችግር ነው።ስነ – ዜጋ እና ስነ – መግባር ትምህርት እንደሌሎች የትምህርት ዓይነቶች በንድፈ ሃሳብ ላይ ብቻ ያተኮረ ስለነበር፤ በተግባር የተማሪዎችን ባህሪይ ከመጀመሪያው ጀምሮ ኮትኩቶ በማሳደግ እና በመቅረጽ ውስንነቶች እንደነበሩበት ያመለከቱት ዶክተር ሞገስ፤ ወጣቶች ህግን ያለማክበር፣ ለስነምግባር ተገዥ ያለመሆን እና የማህበረሰቡ እሴት የኔ ናቸው ብሎ ያለማሰብ እና ከስነምግባር ያፈነገጡ ችግሮች በስፋት እየታየባቸው መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም ለክፍተቱ ማሳያ እንደሚሆን ተናግረዋል። በዋነኛነትም ስርዓተ ትምህርቱ ለገዥው ፓርቲ አስተሳሰብ ማስፈፀሚያ ነው ብሎ ህብረተሰቡና ተማሪዎች የማሰብ ዝንባሌ ስለነበር ወጣቶች ለትምህርቱ የሚሰጡት ቦታ ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጎታል ያሉት ዶክተር ሞገስ፤ በቦታው በቂ ስልጠና የነበራቸው መምህራንም አለመኖር የታሰበውን ትምህርት መስጠት እናዳልተቻለ አስታውቀዋል። መምህራን በትክክል የዴሞክራሲን መርሆችን ሲያስተምሩ እና ወጣቱ ለህግ የበላይነት መታገል ሲጀምር መንግሥት እናንተ ያልሆነአጀንዳ እያሰረፃችሁ ነው በሚል መምህራኑን ስለሚከስ ትምህርቱን በልበ ሙሉነት እንዳያስተምሩ ማድረጉን አመልክተዋል።በእነዚህ እና ተያያዥ በሆኑ ሌሎች ችግሮች ቀደም ሲል ይሰጥ የነበረው የስነዜጋ እና የስነምግባር ትምህርቱ ለወጣቱ የህግ የበላይነትን ማስገንዘብ እንዳልቻለ ተጨባጭ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም ወጣቱም ለህግ የበላነት ያለው አመለካከት ዝቅተኛ እንዲሆን ማድረጉን አመልክተዋል።ወጣቱ ለህግ የበላይነት ያለውን አመለካከት ለመቀየር የስነ ዜጋ እና ስነምግባር ትምህርት እንደ ሌሎች የትምህርት ዓይነቶች በንድፈ ሃሳብ ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑ ቀርቶ በተግባር የተደገፈ እና ስርዓተ ትምህርቱም መቀየር እንደሚኖርበት ጠቁመዋል። በዚህም ወጣቱ ሃገራዊ እሴቱን የተገነዘበና ዝም ብሎ የሚገፋ ሳይሆን መጠየቅ የሚችል ብሎም ለህግ የበላይነት መቆም የሚችል ዜጋ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የስነ ዜጋ እና ስነ ምግባር ትምህርት ጄኔራል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ለገሰ ነጋሻ በበኩላቸው የስነ ዜጋና ስነመግባር ትምህርት የነበሩበት ክፍተቶች በጥናት ተለይተው እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች መኖራቸውን አስታወቀዋል።የስነ ዜጋ እና ስነምግባር ትምህርት የሚለው ግብረገብ እና ዜግነት ትምህርት ወደሚል እንደተቀየረ የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ በቀጣይ ተማሪዎች እራሳቸውን እና ህብረተሰባቸውን የሚገልጹበት፣ ሃገራዊ እሴቶቻቸውና መርሆዎች ላይ ትኩረት አድርገው የሚሄድበት ሁኔታ ይኖራል ብለዋል። ግብረገብነት የሚባለው ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ ስድስተኛ ክፍል ለብቻው እራሱን ችሎ እንዲሰጥ፣ የዜግነት ትምህርቱ ደግሞ ከሰባተኛ ክፍል ጀምሮ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል እንዲሰጥ የሚያስችል ስርዓተ ትምህርት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል። በዚህም የወጣቱን ስነምግባር መቀየር እንደሚቻል አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 13/2012አሸብር ኃይሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35711
c06c62122ec53090b6e581b79a10858e
d15f30bcb6e72f469cccfb6b74adf3cd
«የኦሮሞ ትግል ፍሬ እንዳያፈራ ትልቁ ተግዳሮት የነበረው ኦነግ ሸኔ ነው»- አቶ ታዬ ደንደኣ፣ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
 አዲስ አበባ፦ የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ፍሬ እንዳያፈራ ትልቁ ተግዳሮት የነበረው ኦነግ ሸኔ መሆኑን የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ አስታወቁ። ህወሓት ኦነግ ሸኔን በአደባባይ እንደ ጠላት እየፈረጀ በተግባር ግን የኦሮሞን ትግል ለማክሰም እንደ መሣሪያ ይጠቀምበት እንደነበረም አመለከቱ።አቶ ታዬ ደንደኣ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ያካሄደው የፍትህ የእኩልነትና የነፃነት ትግል ፍሬያማ እንዳይሆን ኦነግ ሸኔ ከህወሃት ጋር የነበረው ከሕዝብ የተሰወረ ህብረት ዋንኛ ምክንያት ነው ብለዋል። ኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ታጋዮች አንድ ወጥመድ ሆኖ ለህወሃት ሲያገለግል እንደነበርም አመልክተዋል።ብዙዎች ኦነግ ሰፊ የሕዝብ ድጋፍ እያለው የዚህ ድርጅት ትግል ለምንድን ነው ወደፊት ገፍቶ የማይመጣው? የሚል ጥያቄ ነበራቸው። በርካታ ወጣቶች እና ምሁራን እንዲሁም መምህራንም ይሄንኑ ይጠይቁ እንደነበር አመልክተው፣ የኦነግ ትግል እውነተኛ የነፃነት ትግል ነው ብለን በማመን ትግሉን ከተቀላቀልን በኋላ ግን ኦነግ ሸኔ እና ህወሓት አብረው እንደሚሰሩ መገንዘብ ተችሏል። ኦነግ ሸኔ የህወሓት መጠቀሚያ ዕቃ መሆኑንም መረዳት ተችሏል ብለዋል። «የኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት ይፈልጋል (ኦሮሞ ብቻም ሳይሆን ኢትዮጵያውያንም ነፃነት ፈልገው ዋጋ ሲከፍሉ ነበር)፤ ይሄን ነፃነት ማን ያመጣልኛል ብሎ ሲያስብ ደግሞ አንድ በነፃነት ስም የተደራጀ ድርጅት አለ ብሎ በማመን የትግሉ አካል ይሆን ነበር። ይሄ ድርጅት ግን ጭንቅላቱ በህወሓት በመያዙ እና ይህንን ሕዝቡ በሚገባ ባለማወቁ ብዙ ዋጋ ከፍሏል ሲሉ አስታውቀዋል። «ህወሓት ኦነግ ሸኔን ሆን ብሎ በዚያ ደረጃ የኦሮሞ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ወጣት፣ የኦሮሞ ምሑር የሌለ ነገር እንዲጠብቅ፤ በሴራ ያስቀመጠው ድርጅት ነው» ያሉት አቶ ታዬ፣ በዚህ መልኩም ለሃያ ዓመታት ያህል ተጠቅመውበታል፤ በተለይም አቶ ገላሳ ዲልቦ ከሥልጣን ወርደው የአሁኑ የሸኔ ሊቀመንበር ሥልጣን ከያዘ በኋላ በቀጥታ ትብብሩ ውስጥ እንደነበሩም አመልክተዋል። «ኦህዴድ ውስጥ ሆነህ ኦሮሞ ላይ ጉዳት ደርሷል ብለህ ካነሳህ ኦነግ ትባላለህ። የኦሮሞ ባለሀብት ሆነህ ሊዘርፉህ ከፈለጉ ኦነግ ይሉሃል። ይሄን የሚያደርጉት ደግሞ ኦነግ የሌለ ከሆነ የሚፈርጁበት ስለሌለ ስለሚቸገሩ ነው። ስለዚህ ኦነግ እንደሌለና በእነርሱ ስር እንዳለ ቢያውቁትም፤ በኦነግ ስም ተማሪን ለመደብደብም፣ መምህራንን ለማሰርም፣ ነገ ይገዳደረኛል ብሎ የሚያስቡትን ለመግደልም ይጠቀሙበታል፤ ህወሓት በዚያ ደረጃ በኦነግ ሸኔ ተጠቅሟል ሲሉም ተናግረዋል።ከዚያም በላይ ኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ታጋዮች አንድ ወጥመድ ሆኖ አገልግሏል የሚሉት አቶ ታዬ ደንደኣ ፣ ለምሳሌ እኔ ሁለት ጊዜ ታስሬያለሁ። አስር ዓመት እስር ቤት ቆይቻለሁ። ሁለቱንም ጊዜ ያሳሰረኝ የኦነግ ሸኔ አባል ነው። ያሳሰረኝ ኦህዴድ አይደለም፤ ህወሓትም ራሱ ፈልጎ አላገኘኝም። ለህወሓት የሰጠኝ ኦነግ ሸኔ ነው። አብረው ስለሚሰሩ በገንዘብም ይሸጡሃል። እንዲያውም አንዳንዴ አደራጅተውና የኦነግን ባንዲራ አስይዘው አሳልፈው ለህወሃት ይሰጡሃልም ብለዋል። ለምሳሌ፣ ግርማ ጥሩነህ የሚባል የሸኔ ተወካይ 2008 አካባቢ ቦሌ ላይ 20 ሰዎችን ማህበር ብሎ በአንድ ጊዜ አደራጅቶና የኦነግ ሸኔ ባንዲራ አስቀምጦ ደህንነትን ጠርቶ አስይዟቸዋል ያሉት አቶ ታዬ፣ እናም በዚያ ደረጃ ነው በሰው የሚነግዱት ይላሉ። ከተያዝክና ከታሰርክ በኋላ ደግሞ ጀግና ታሰረ ብለው ውጪ ያሉት አባሎቻቸው በስደት እያሉ የሕዝቡን ነፃነት ከሚፈልጉ የዋሆች ላይ ገንዘብ እንደሚሰበስቡም አመልክተዋል። ከዚያ ባሻገር እነሱ የመሸጉበት ሶሎሎ የሚባል አካባቢ አለ። እዚህ መከራ ሲያይ፤ ሲታሰርና ሲገረፍ የተቸገረ ሰው በቃ ሄጄ ታጥቄ ልታገል ብሎ ወደዚያው ይሄዳል። እዚያም ይታይና ሃሳብ ያለው ከሆነና ጀግንነት ያለው ከሆነ እዚያው ይገደላል፤ ወይ ይቃጠላል። ይሄን የሚያደርጉት ደግሞ ይህ ሰው ነገ አብዮት ሊያመጣ ይችላል ብለው ስለሚሰጉ እንደሆነም ጠቁመዋል። እንደ አቶ ታዬ ማብራሪያ፤ ህወሓትና ኦነግ ሸኔ ከዚህም ባለፈ መረጃም የሚለዋወጡ ናቸው። ለአብነት፣ ኅብረተሰቡ ሲያምጽ የወያኔ መልስ ጥይት ነው፤ ግድያ ነው። በተለያየ ጊዜ በተማሪ ደረጃ፣ በወጣት ደረጃ፣ በ2006 ዓ.ም ከዚያም በፊት በ1998፣ በ1996 እና በተለያየ ጊዜ የተለያዩ አመጾች በተለይ በኦሮሚያ ክልል ተደርገዋል። በጣም የሚያሳዝንህ ግን በዚህ ውስጥም የሴራ ፖለቲካ እንዲታይ ሆኗል። በሴራውም ህወሓት በአጠቃላይም የኢህአዴግ መንግሥት ንጹሃን ኦሮሞዎችን ገድሏል፤ ሰብዓዊ መብትም ተጥሷል በሚል በዓለምአቀፍ ደረጃ (በአምነስት ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማን ራይትስ ዎችና ሌሎችም) ክስ ይቀርብበታል። ይህ ክስ ሲቀርብ ህወሓት የሚያደርገው ነገር በእኔ ትዕዛዝ ነው ሕዝቡ ያመጸው በልና መግለጫ አውጣ ብሎ የሚያነበውን መግለጫ ጽፎ ለኦነግ ሸኔ ይልክለታል። ኦነግ ሸኔም አስመራ ላይ ሆኖ በህወሓት ተጽፎ የቀረበለትም መግለጫ ያነብባል።  የእኛ ትግል ነው ብሎ ያነበበውን የእርሱን መግለጫም እነ ቪኦኤና ዶቼቬሌ ጭምር ያስተላልፉታል። ህወሓት/ኢህአዴግ ደግሞ ይሄንን ተጠቅሞ እንቅስቃሴው የሕዝብ አልነበረም፤ የአሸባሪው ኦነግ ነው ብሎ ራሱን ለመከላከል መልስ ይሰጣል። እናም በዚህ ደረጃ በረቀቀ መልኩ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ አብረው ሲሰሩ እንደነበርም አስታውቀዋል። ይሄንን በደንብ ለመረዳት በኢሬቻ ጊዜ በርካታ ዜጎች ሕይወታቸው አልፏል። በተቃውሞ ጊዜም በተለይ «ግራንድ ራሊ» ተብሎ በተደረገው ትልቅ ሰልፍ የብዙ ወጣቶች ሕይወት አልፏል። የኦሮሞ ሕዝብ በአብዲ ኢሌ እና በህወሓት ሴራ በሚሊዮን የሚቆጠር ከሶማሌ ክልል ተፈናቅሏል፤ ሞቷልም። እንግዲህ ተኩስ ቢያስፈልግ ያን ጊዜ ጀግና ወጥቶ መተኮስ ነበረበት። ወጣቱ በሰላማዊ መንገድ ወጥቶ ባዶ እጁን መንገድ ላይ ሲረግፍ ኦነግ ሸኔ የሚባለው አንድ ጥይት አይደለም ወደጠላት ወደ ሰማይ አልተኮሰም ብለዋል። ይሁን እንጂ እነ ጌታቸው አሰፋ ከሥልጣን እንደወረዱ ጫካ ታይቶታል። ይህ ምን ማለት ነው? ትግሉ የነፃነት ነው ወይስ ፀረ ነፃነት ነው? ያኔ ሕዝቡ ለነፃነት ሲታገል የት ነበሩ? አዲስ አበባ፣ አማራ ክልል፣ ኦሮሚያ ክልል፣ ደቡብ ክልል፣ ሶማሌ ክልል ሕዝቡ መከራ ሲያይ፣ ሲገረፍ፣ በግፍ ሲረግፍና ሲገደል አንድ ጥይት ለመተኮስ እንዳልሞከሩ አመልክተዋል። በወቅቱ ከእነርሱ ጋር የነበረ ኮሎኔል አበበ ገረሱ እንደምንም ለዚህ ሕዝብ እንድረስለትም ብለው ሲጠይቃቸው፣ አይ ኢትዮጵያን ሶሪያ አናደርጋትም፣ ተኩስ እዚያ ቢካሄድ ሶሪያ ነው የምትሆነው፤ ኅብረተሰቡ በራሱ ጊዜና በራሱ መንገድ በሰላማዊ መንገድ ቢታገል ነው የሚሻለው ነው ያሉት። ታዲያ ትጥቅ፣ ተኩስና ግድያ ከዚያ በኋላ ለምን አስፈለገ? የሚገድሉት ደግሞ እግር የቆረጠውን፤ ያኮላሸውን፤ ጥፍር የነቀለውናና ሌላም ግፍ ያደረሰውን አይደለም። ትናንት ይሄን ያደረገው ዛሬ የእነርሱ ወዳጅ ነው። አብረው ነው የሚሰሩት። እንዲያውም ሎጀስቲክስም ስትራቴጂም ከዚያ ነው የሚቀበሉት። ስለዚህ ግንኙነታቸው ከድሮም ጀምሮ ያለ እንደነበር አመልክተዋል። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ የሚገባው እና በተለይም የኦሮሞ ሕዝብ ሊነቃበት የሚገባው የኦነግ ሸኔ ፕሮፖጋንዳ የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ጭራቅና ገዳይ እንዲታይ፤ እንደ ሰይጣን እንዲፈራ እና እንዲጠረጠር የሚያደርግ ነው ያሉት አቶ ታዬ ደንደኣ፣ የኦሮሞ ሕዝብ የተለየ ጥያቄ እንዳለው እና ኦሮሞ ከኢትዮጵያ የተለየ እንደሆነ እንጂ፤ ከሌሎች ጋር ተስማምቶ ያለ እና ተመሳሳይ ጥያቄና ችግር ያለው፣ መፍትሄውም በጋራ ብንታገልና በጋራ ብንሰራ ነው የምናገኘው፤ የሚል አስተሳሰብ እንዲመጣ እንደማይፈልግም አስታውቀዋል። በዚህም በኦሮሞና ሶማሌ ነዋሪዎች መካከል ትንሽ እንኳን የግጦሽ ሳር ግጭት ብትፈጠር የፍረጃ ወሬን በማጋጋል ኦሮሞና ሶማሌን የሚያቃቅር፤ በተመሳሳይ በሲዳማና ኦሮሞ አዋሳኝ ላይ ትንሽ ግጭት ቢፈጠር እሱኑ አጋግሎ በኦሮሞና ሲዳማ መካከል ትልቅ ጥርጣሬ እንዲፈጠር ማድረግ ትልቁ ሥራቸው እንደሆነ ጠቁመዋል። ራሳቸው በፈጠሩት ግርግር በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ አካባቢዎች ጉዳት በደረሰ ጊዜ የሚጠቀማቸው ቃላት ለሌሎች ማህበረሰቦች እጅግ ፀያፍ፤ የሚያበሳጩና ግጭትና ቁርሾን የሚያባብሱም እንደነበሩ አመልክተው፣ በዚህ ደረጃ ይሄን አቃፊ እና የኢትዮጵያ ትልቅ መሠረት የሆነውን ማህበረሰብ፤ ኢትዮጵያውያንን ወዶና አፍቅሮ አብሮ ኢትዮጵያን የመሠረተ እና አብሮም ለማሳደግና ለማሻገር የሚፈልገውን ማህበረሰብ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር እንዳይስማማ፤ እነርሱ በሚሰሩት የፕሮፖጋንዳ ሴራ ሌሎች እንዲጠራጠሩት እየሆነ ነው ብለዋል። ይሄን ማድረግ ደግሞ የህወሓት ባህሪ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ በራሱ የህወሓትና ኦነግ ሸኔ ግንኙነት የት ድረስ እንደሆነ የሚያሳይ እንደሆነም አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ሀምሌ 14፣ 2012  ወንድወሰን ሽመልስ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35769
69cc4e7669f5fc061c140913fe953f20
941a4214f109f29dab24df081714ddcb
በቀጣይ አስር ዓመት 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤቶች ይገነባሉ
አዲስ አበባ፡- በአገሪቱ ከተሞች እየታየ ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት በቀጣይ አስር ዓመት ውስጥ በተያዘው የቤቶች ልማት መርሃግብር 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤቶች እንደሚገነቡ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ። ቤቶቹ የሚገነቡት በመንግሥት ብቻ እንዳልሆነ አመለከተ። በሚኒስቴሩ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ታደሰ ከበበ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ የቤቶች ልማት መርሃግብር ሪፎርም ያስፈልገዋል ተብሎ በጥናት ከተለየ በኋላ በሚቀጥሉትአስር ዓመታት 4 ሚሊዮን 4 መቶ ሺ አንድ መቶ ቤቶች ለመገንባት እቅድ ተይዟል። ግንባታውም በአገሪቱ ሁሉም ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል። እርሳቸው እንዳሉት፤ ከሚገነቡ 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤቶች ውስጥ የመንግሥት ሚና 20 በመቶውን ብቻ ነው። በዚህ ውስጥ 10/90፣ 20/80 እንዲሁም 40/60 ግንባታቸው ይቀጥላሉ። 10/90 አዲስ አበባ ላይ ቆሞ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን በጥናት በመለየቱ የሚቀጥል ይሆናል። ቀሪዎቹ በፊትም ያሉና አሁንም የሚቀጥሉ ናቸው።እንደ አዲስ የተጨመረው የኪራይ ቤቶች በስፋት የሚገነቡ መሆናቸው መሆኑን ጠቅሰው፣ በተቻለ መጠን ሰዎች በገቢ ልካቸው ሊከራዩ የሚችሏቸውን ቤቶች መንግሥት እንዲገነባ ይደረጋል ብለዋል። በዚህም በመንግሥት የሚገነቡ ቤቶች ወደ አራት ደረጃ ከፍ እንደሚል አብራርተዋል። በሁለተኛ ደረጃ የተያዙት የማህበራት ቤቶች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ዜጎች በማህበር ተደራጅተው የሚገነቡት ቤት ይገነባል ተብሎ ከተያዘው ከ4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤት 35 በመቶ ያህሉን መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል። በግለሰቦች አሊያም በማህበራት ለሚገነባው ቤት መንግሥት የማደራጀት እና መሬት የማቅረብ ድጋፍ እንደሚያደርግም አመልክተዋል። አቶ ታደሰ እንደገለጹት፤ በሦስተኛ ደረጃ የግለሰቦች ቤት ሲሆን፣ ግለሰቦች በራሳቸው ነባር ይዞታ ላይ ወይም  መንግሥት በሚያወጣው የሊዝ ጨረታ ላይ ተሳትፈው ቤቶችን መገንባት እንዲችሉ አቅጣጫ ተቀምጧል። በእነሱ እንዲገነባ በእቅድ የተያዘው የቤት መጠን ደግሞ ወደ 15 በመቶ ያህል ነው። በአራተኛ ደረጃ የተቀመጠው አማራጭ በመንግሥትና በግል አጋርነት የሚገነባው ቤት ሲሆን፣ በዚህም 15 በመቶ ያህል የሚገነባ እንደሆነ ተናግረዋል። በአምስተኛው አማራጭነት የተቀመጠው ሪልስቴት ሲሆን፣ ባለሀብቶች በዚህ ዘርፍ በስፋት እንዲገነቡ መንግሥት ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም የሚገነባው 10 በመቶ ያህሉ ነው ብለዋል። ሪል ስቴትን ለመደገፍ አዋጅ እያዘጋጁ መሆኑንም ጠቁመዋል። እርሳቸው እንዳብራሩት፤ በመንግሥትና በግል ባለሀብቱ ብሎም በግሉ ዘርፍ የሚመደብ በሽርክና የሚሰራ የቤት ግንባታ እንደሚኖር ይታመናል። ስለዚህ በመንግሥት ብቻ 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤት ሊመጣ አይችልም። ይህ በመሆኑ በስትራቴጂው የተቀመጠ ሲሆን፣ ስትራቴጂው በሚኒስቴሩ ደረጃ ውይይት ተካሂዶበት ጸድቋል፤ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲያጸድቁት ደግሞ ተልኳል። የተቀናጀ የቤቶች ልማት መርሃግብር የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ የሚባለው በ1996 ዓ.ም ተጀምሮ ወደየክልሎች እንዲሰፋ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን፣ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት ብቻ እስካሁን ባለው መረጃ ከ400 ሺህ ቤቶች በላይ መገንባቱ ይታወቃል።አዲስ ዘመን ሀምሌ 14፣ 2012  በአስቴር ኤልያስ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35764
12633cc79b5b02528ce2fe6aa79fdc41
813251c63b364137cca3c13626b1fc2c
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወደ ሥራ ገብቶ ማየት የዘወትር ምኞታቸው መሆኑን ነዋሪዎች አመለከቱ
አዲስ አበባ፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሁሉም የኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት እንደመሆኑ መጠን ወደ ሥራ ገብቶ ለማየት የዘወ ትር ምኞታቸው መሆኑን አመለከቱ። በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን አባተ እንደተናገሩት፡- የአባይ ግድብ የኛ ጉዳይ ነው። ከጎረቤት ሀገር ጋር ሰላማዊ የሆነ ግንኙነት እንዲኖር ለማድረግ ካልሆነ በስተቀር የራሳችንን ጉዳይ በራሳችን ነው መወሰን ያለበት። አሁን ላይ መንግሥት የያዘው አቋም ትክክለኛና አግባብነት ያለው በመሆኑ የውሃ ሙሌትም ጊዜውን ጠብቆ መሞላት አለበት እንጂ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም ብለዋል። ኢትዮጵያ ህልውናዋን፤ ክብሯን፤ ነፃነቷን ለማስከበር በፍጹም አትደራደርም የሚሉት አቶ ሰለሞን፤ የራሳችን የሆነውን አባይ ገድበን ለመጠቀም የማንንም ፈቃድ መጠየቅ የለብንም። እስከአሁን ግብፅ ብቻዋን ስትጠቀም የነበረውን አባይ በጋራ ለመጠቀም የጋራ የሆነ የሚያግባቡ ሁኔታዎች ሲኖሩ ነው መደራደር የሚቻለው ካልሆነ በራሳችን ንብረት ወደኋላ የምንሸሽበት ምክንያት የለም። እኛ ኢትዮጵያውያን የሰውን ንብረት አንነ ካም የራሳችንን አሳልፈን አንሰጠም ሲሉ አቶ ሰለሞን ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያን የጋራ ተጠቃሚ የሚያደርጉን ጉዳዮች እስካሉ ድረስ ከጎረቤትና ከውጭ ሀገራት ጋር ተግባብቶ የመኖር ባህል መሆኑን ጠቁመው፤ የአባይ ጉዳይ የኢትዮጵያ የልማትና የህልውና ጉዳይ ነው። ‹‹ግድቡ ሲጠናቀቅ ለልጅ ልጆቻችን ልማትና ተጠቃሚነትን በመስጠት ከድህነት የምንወጣበት አንዱ መንገዳችን ይሆናል›› ብለዋል። ለግድቡ መጠናቀቅ ከሌላው ጊዜ በይበልጥ አንድነታችንና አብሮነታችንን በማስጠበቅ የጋራ ርብርብ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ ሰለሞን፤ ከሀገራችን ጎን በመቆም የውስጥና የውጭ ሰላማችን እንዳይደፈርስ ጠብቀን ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ አብረን በመጓዝ ውሃው ተሞልቶ ሥራ መጀመር እንዳለበት አመልክተዋል። ወይዘሮ መንበር መቋጫ በበኩላቸው፡- ግብፅ አባይ ብቻዋን ለዘመናት ስትጠቀም መቆየቷን የራሷን አድርጋ እንደትቆጥር ያደረጋት መሆኑን ጠቁመው፤ ግድቡ የኢትዮጵያውያን እንጂ የግብፅ ወይም የሌላ የውጭ ሀገር ንብረት አይደለም። የግድቡ ውሃ ሙሌት ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ ሳይሆን በቶሎ ውሃው ተሞልቶ ከውሃ ሀብታችን ተጠቃሚ የመሆን መብት እንዳለን መታወቅ አለበት ብለዋል። ‹‹ እኔ ባለኝ አቅም ከምንሠራው ትንሽ ሥራ አጠራቅሜ ቦንድ ገዝቻለሁ፤ የልጅ ልጄም ቦንድ እንዲገዛ አድርጌያለሁ›› የሚሉት ወይዘሮዋ፤ ከዚህም በላይ ለግድቡ ግንባታ የበኩላቸውን መወጣታቸውን ገልጸዋል። አባይ ህይወታችን መጦሪያ ቅርሳችን ነውም ብለዋል። እሳቸው የሚጦሩበት ልጆቻቸው የሚከብሩበት የአባይ ግድብ ተገድቦ ተጠቃሚ ለመሆን መጓጓታቸውን በመግለጽ፤ የግድቡ ሙሌት እውን እንዲሆን መንግሥት የያዘውን አቋም አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ህልውና ጉዳይ የሆነውን የግድቡን ውሃ መሌት ለማደናቀፍ በማሰብ በውጭ ገንዘብ ድጋፍ ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚጥሩ የውስጥም ሆነ የውጭ ኃይሎች መኖራቸ ውን ገልጸው፤ የግድቡ የልማት ሥራዎች በእነሱ ድርጊት የማይቋረጥ መሆኑን አውቀው አርፈው በመቀመጥ ከእኩይ ድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ህዝቡ ሀገር ለማፍረስ የሚጥሩ ኃይሎች ምንም ጊዜ እንደማያንቀላፉ አውቆ ብልጥ በመሆን ለእነሱ ዕድሉን መስጠት የለብንም። ሁሉም ዜጋ ይህንን አውቆ የተሰማራበትን ሥራ ጠንክሮ በመሥራት ግድቡን ወደ ፊት ማስኬድ እንዳለበት አመልክተዋል። ከአባይ የምንጠብቀው ወጣቱ ትውልድ መስኖ እያለማ ሀገሩን በማበልጸግ የሥራ ዕድል የሚያገኝበት እንዲሆን ነውም ሲሉ ተናግረዋል። አባይ የሁላችንም አሻራ ያለበት ነው። ሁሉም ሰው የሚችለውን በማድረግ የተሳተፈበት በመሆኑ ግድቡን መድረስ ያለበት ቦታ ደርሶ እስከሚጠናቀቅ ድረስ እያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቅበትን መወጣት እንዳለበት ጠቁመዋል። ሁላችንም ተባብረን አባይን የእኛ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል። ‹‹ ግድቡ ተጠናቅቆ ለኔም ደርሶ ይረዳኛል ብዬ ተስፋ አድርጋለሁ›› የሚሉት አቶ ኋሊት ከሊል በበኩላቸው፤አባይ የህልውናችን መሠረት በመሆኑ ማንም እንዳንገድብ ሊያደርገን አይገባም። ግድቡ ድሮም ለግብፅ እየፈሰሰ እኛ የምንሞገስበት ሀብታችን ቢሆንም፤ አሁንም ደግሞ ተገድቦልን እኛም ከግድባችን ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባን አመልክተዋል። ምንም እንኳን አባይ ለረጅም ዘመናት ሳይገደብ በመኖሩ ቢቆጩም ዛሬ ላይ ተገድቦ ለማየት ተስፋ የጣሉበት በመሆኑ የግድብ የውሃ ሙሌት መጀመር እንዳለበት ጠቁመው፤ ህዳሴው ግድብ ተጠናቆ ሥራ እስኪጀምር ድረስ ሁሉም ያለውን አቅም ተጠቅሞ ግድቡን እውን ለማድረግ መሥራት ይጠበቅበታል ብለዋል።አዲስ ዘመን ሀምሌ 14፣ 2012  በወርቅነሽ ደምሰው
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35765
79ebecdb99d97d8cc2109bada1afbbeb
36111acd5363a101c29ed1160bf1fdc3
ትከሻ አጉባጩ የዋጋ ንረት
ሸማቹ ማህበረሰብ ላይ በየቀኑ ዋጋ ካልጨመሩ ምድርና ሰማይ ይገለባበጣል የሚባልላቸውና በኢ-ሰላማዊ ወቅት ድሃውን ኅብረተሰብ የሚበዘብዙ አካላት ዛሬም የብዝበዛ ጦራቸውን ሰብቀዋል። በከተማ ደረጃም ሆነ በክልል በሚፈጠር ግጭት ምክንያት ድሃው የኅብረተሰብ ክፍል በግብይት ምክንያት እየተጎዳ ይገኛል። ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ድንገተኛ ግድያ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ አለመረጋጋት፣ እጥረት ተፈጥሮ ነው በሚል ሰበብ በሽንኩርት (ቀይና ነጭ)፣ ቲማቲም፣ ቃሪያ፣ ድንች፣ የጎመን ዓይነቶችና ሌሎች ፍራፍሬዎችም ላይ የተደረገው ጭማሪ ዜጎችን ለተጨማሪ ወጪ ከመዳረጉ ባሻገር፤ መደበኛ አኗኗራቸው ላይም ተጽእኖ መፍጠሩ ተሰምቷል። በአዲስ አበባ ያነጋገርናቸው አንዳንድ ነዋሪዎች ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ የአትክልት ዋጋ በእጅጉ ማደጉ ከሌሎች ወጪዎች ጋር ተዳምሮ ቤተሰብን ለማስተዳደር መቸገራቸውን ይናገራሉ። በአትክልት የዋጋ ንረት ሕይወታቸው ላይ ጫና ካሳረፈባቸው የአዲስ አበባ ኗሪዎች መካከል ወይዘሮ ትርንጉ ጉታ አንዷ ናቸው። በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚኖሩት ወይዘሮ ትርንጎ ለበርካታ ዓመታት የመስተንግዶ ሥራ በመስራት ቤተሰቦቻቸውን ሲያስተዳድሩ ከርመዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን «የኑሮ መወደድ ከአቅሜ በላይ ሆኖ እያንገዳገደኝ ነው» ይላሉ ሰሞነኛውን የአትክልት ዋጋ ንረት እንደ አብነት በማንሳት። ወይዘሮ ትርንጎ የሦስት ልጆች እናት ሲሆኑ ሁሉም ልጆቻቸው በትምህርት ላይ ናቸው። የሚያሳድጓቸውም ያለ አባት ነው። አሁን ላይ በየጊዜው የሚጨምረውን የኑሮ ውድነት መቋቋም ባለመቻላቸው መጪው ጊዜ ፈተና ሆኖባቸዋል። የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆኑት ወይዘሮ ትርንጎ፤«ኅብረተሰቡ በመጀመሪያ ደረጃ ምርጫው ከሚያደርጋቸውና ለምግብነት የሚጠቀማቸው የአትክልት ምርቶች ዋጋው በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ በተለይ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ላለነው የኅብረተሰብ ክፍሎች አትክልት ገዝቶ ለመብላት ፈተና ሆኖብናል» ይላሉ። አሁናዊው ሁኔታ መጪውን ጊዜ ይበልጥ እንዲፈሩት ያደረገው ወይዘሮ ትርንጎ፤ በኑሮ ውድነቱ ተስፋቸው ከዕለት ወደ ዕለት እንዲሟጠጥ ተጨማሪ ምክንያት የሆናቸው ደግሞ እርሳቸውን ለመሰሉ ከኑሮ ጋር እልህ አስጨራሽ ግብግብ ለገጠሙ ሰዎች በፖለቲካ ልሂቃን ዘንድ ብዙም ትኩረት እየተሰጠ አለመሆኑ ጭምር ነው። እንደ ወይዘሮ ትርንጎ ገለጻ፤ ጉዳዩ ከፍ ሲልም፤ የብሔር ጉዳይን እያራገቡ የራሳቸውን ሥልጣን ለማመቻቸት የድሃውን ጉዳይ ልብ ያላሉትንም ትዝብት ላይ ጥሏቸዋል። በመሆኑም ፖለቲከኞች የራሳቸውን ጉዳይ ከማስፈፀም ወጥተው ውስጥን የሚነካና ስለኑሮ ጉዳይ ትኩረት የሚሰጥ አጀንዳ ቀርጸው ከመንግሥት ጋር መስራት ይጠበቅባቸዋል። ከወይዘሮ ትርንጎ ሀሳብ ጋር በሚስማማ መልኩ አስተያየት የሰጡት ሌላኛው የመዲናዋ ነዋሪ አቶ ተስፋዬ ጸጋዬ፤ አጠቃላይ የኑሮ ውድነት ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መምጣቱን በከፍተኛ ምሬት ይናገራሉ። ቀደም ሲል ከነበረው አመጋገብ በጥራትና በመጠን ባነሰ ሁኔታ ለመመገብ መገደዳቸውንና የኑሮ ውድነቱ ከመሻል ይልቅ በየጊዜው እየናረ መምጣቱን በመግለጽ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባታቸውንም ገልጸዋል። በቅርቡ በአትክልት ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በአብዛኛው ከእጥፍ በላይ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ተስፋዬ፤ በጃንሜዳ አትክልት ተራ አንድ ኪሎ ከ20 ብር በታች ይሸጥ የነበረው ቀይ ሽንኩርት በአሁኑ ወቅት እስከ አርባ ብር እየተሸጠ መሆኑን፤ እስከ አስር ብር ይሸጥ የነበረው ቲማቲም አሁን ላይ ከ20 እስከ 25 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ለአብነት ጠቅሰዋል። ዋጋ መጨመሩ ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ምርቶችን ከአምስት ኪሎ በታች መግዛት ስለማይቻል ችግሩን አግዝፎታልም ይላሉ። በግብይቱ አቅም ያላቸው ያሻቸውን ቢገዙም ድሃው የኅብረተሰብ ክፍል ግን «በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ» ስለሆነበት ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ከገበያው ተሰውሯል። » ይላሉ። በአትክልት ንግድ ላይ የተሰማሩት አቶ ተረፈ ሰለሞን በበኩላቸው፤ የዋጋ ግሽበትን ተከትሎ የተከሰተው የኑሮ ውድነቱ እንዳለ በማመን፤ በዚህም ሁሉም ባይሆኑም አንዳንድ ነጋዴዎች በአገሪቷ የተከሰተውን አለመረጋጋት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የማይፈታ ችግር እስከሚመስል ዋጋ በመጨመር ይበልጡንም በየጊዜው የኑሮ ውድነቱ እንዲባባስ ማድረጋቸውን ይናገራሉ። ቢሆንም በታማኝነት ያለዋጋ ጭማሪ የሚሰሩ ነጋዴዎች እንዳሉም ጠቁመዋል። አንዳንድ ስግብግብ ነጋዴዎች አላግባብ የዋጋ ጭማሪ ማድረግን እንዲያቆሙና መንግሥትም ጉዳዩን በትኩረት ሊመለከተው እንደሚገባም አስገንዝበዋል። አዲስ ዘመን ጋዜጣ በአትክልትና ፍራፍሬ ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን አስመልክቶ «ምን እየተሰራ ነው?» የሚለውን ለማጣራት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጋር በተደጋጋሚ ቢደውልም ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።አዲስ ዘመን ሀምሌ 14፣ 2012  በአዲሱ ገረመው
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35767
b1a3501fdd8fd3d50121f7be2e154380
5e195906ff398d9e9986d06ce04419a1
ሶስቱ ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀሉ ክለቦች
በሶስቱም ምድቦች ተከፍሎ በሚካሄደው የከፍተኛ ሊግ ውድድር በመጪው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን የሚቀላቀሉ ሶስት ክለቦች ታውቀዋል። ሰበታ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕናም የሊጉ ተሳታፊ ክለቦች መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በከፍተኛ ሊጉ ምድብ «ሀ» የሚገኘው ሰበታ ከተማ ከተከታዩ በሳምንቱ መጨረሻ ለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ባደረገው ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ያጠናቀቀ ሲሆን፣ አንድ ጨዋታ እየቀረውም ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን ያረጋገጠ ክለብ ሆኗል። ለሊጉ አዲስ ያልሆነው ሰበታ በተሳትፎው ተፎካካሪ መሆን ቢችልም በኋላ ኋላ አቋሙ በመውረዱ በ2003 ዓ.ም ፕሪሚየር ሊጉን መሰናበቱ ይታወሳል። ዳግም ወደ ሊጉ ለመመለስም ስምንት የውድድር ዓመታትን መጠበቅ ግድ ያለው ሲሆን፣ በመጨረሻም ይህ ፍላጎቱ ሰምሮለታል። በምድብ «ለ» የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ ሌላው በመጪው ዓመት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከምንመለከታቸው ክለቦች አንዱ መሆኑን ያረጋገጠ ክለብ ነው። ከሜዳቸው ውጪ ከነገሌ አርሲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ አቻ መውጣት አሊያም የመድንን ነጥብ መጣል ብቻ መጠባበቅ ግድ ያላቸው ወልቂጤዎች፤ ጨዋታውን በአቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል። ውጤቱን ተከትሎም እንደ ሰበታ ከተማ ሁሉ ወልቂጤም አንድ ጨዋታ እየቀራቸው በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ የሚያደርጋቸውን ትኬት ቆርጠዋል። በምድብ «ሐ» ሲወዳደሩ የቆዩት ሀዲያ ሆሳዕና ወይንም ነብሮቹ በቀጣዩ ዓመት ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፈው ሶስተኛው ክለብ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ሃዲያ ሆሳዕናዎች ይህን ማሳካት የቻሉትም በሜዳቸው ከከምባታ ሺንሺቾ ጋር ያደ ረጉትን ጨዋታ 3ለ0 በማሸነፍ ሆኗል። ውጤቱም ሁለት ጨዋታ እየቀራቸው በቀጣዩ ዓመት የሊጉ ተሳታፊ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል። እንደ ሰበታ ሁሉ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዲስ ያልሆኑት ሀዲያ ሆሳዕናዎች በ2008 ዓ.ም የውድድር ዓመት በሊጉ ተፎካካሪ ክለብ ማስመልከታቸው አይዘነጋም። የዘንድሮው ከፍተኛ ሊግ እንደከዚህ ቀደሙ ለበርካታ ጊዜያት ሳይቆራረጥ በመካሄዱ ሶስቱ ክለቦች ከወዲሁ ፕሪሚየር ሊጉን ተቀላቅለዋል። በአሁኑ ወቅት ዋናው የሊግ ውድድርም በቀጣዩ ዓመት ከማይሳተፉ ክለቦች መካከል አንዱን በይፋ ተዋውቋል። በወቅታዊ የሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በአስ ራሶስት ነጥብ የመጨረሻው ደረጃ ላይ የተቀመጠው ደደቢት በቀጣዩ ዓመት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የማይሳተፍ መሆኑን ቀድሞ ያረጋገጠ ክለብ ሲሆን፤ ከደደቢት ከፍ ብለው የተቀመጡት ደቡብ ፖሊስ እና ስሁል ሽረ የወራጅነት አደጋ ያንዣበበባቸው ሆነዋል። ከሁለቱ ከለቦች በተጓዷኝ በሂሳባዊ ስሌት መሰረት መከላከያ፤ ወላይታ ዲቻ ኢትዮጵያ ቡና ከሊጉ የመውረድ አደጋ ከተጋረጠባቸው ክለቦች ተርታ ስማቸው ተያይዟል። ቀሪ ሶስት የሊጉ ጨዋታዎችም ደደቢትን ተከትሎ በቀጣዩ ዓመት በሊጉ የማንመለከታቸውን ክለቦች ያሳውቃል። የከፍተኛ ሊግ አሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ድሬዳዋ ላይ እንደሚከናወን ታውቋል። ምድባቸውን በአንደኝነት የሚያጠናቅቁት ቡድኖች እርስ በእርስ ጨዋታ አድርገው ከፍተኛ ነጥብ የሰበሰበው ቡድን የከፍተኛ ሊጉ አጠቃላይ አሸናፊ መሆኑን ያረጋግጣል።አዲስ ዘመን ሰኔ 11/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12697
503d3348ba0eb478096501949fd92364
a0010468390f91ccc8a329efcb21ffdb
በሻምፒዮናነት ግስጋሴው – መቐለ ሰባ እንደርታ ሰከን ሲል- አጼዎቹ ለሻምፒዮናነት ተቃርበዋል
የኢትዮጵያ ቡና እና የመቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም ተከናውኗል። ጨዋታው የተካሄደው በብዙ ውጥረትና አወዛጋቢ ውሳኔ በኋላ ነው፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም በሰኔ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በዘጠኝ ሰዓት መካሄድ እንዳለበት ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ነበር ሊካሄድ የበቃው። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከሁለት ሳምንት በፊት በ26ኛው ሳምንት በአዲስ አበባ ስታዲየም መካሄድ የነበረበት ቢሆንም «የፀጥታ ስጋት» በሚል ሳይካሄድ ቀርቷል። የጨዋታው አለመካሄዱን ተከትሎ በስፖርት ቤተሰቡ፣ በክለብ አመራሮችና ደጋፊዎች፣ በመገናኛ ብዙኃን በኩል ሰሞነኛ አብይ ጉዳይ በመሆን ብዙ ሲባልልት ቆይቷል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከቀናት የውጥረት ቆይታ በኋላ የተካሄደው ጨዋታ፤ ያለምንም ግብ በአቻ ተጠናቋል።በጨዋታው ነጥብ የተጋሩት መቐለ ሰባ እንደርታዎች ከሻምፒዮናነት ግስጋሴያቸው ሰከን ሲሉ አጼዎቹን ለሻምፒዮናነት አቅርቧቸዋል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በአስደማሚ ድባብ የተከናወነው የኢትዮጵያ ቡናና መቐለ ሰባ እንደርታ ጨዋታ በርካታ የግብ ሙከራዎች ታይተዋል። በሁለቱም ክለብ ተጫዋቾች በኩል ኳስን ከመረብ ለማገናኘት የቻለ ግን አልነበረም። ቡናማዎቹ በጨዋታ እንቅስቃሴ የበለጠ ጫና ፈጥረው ሲጫወቱ ፤ መቐለ ሰባ እንደርታ ነጥብ ተጋርቶ ለመውጣት ጥረት ሲያደርጉ ተስተውለዋል። በዚህ መሠረት የተስተካካይ ጨዋታው ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ለመጠናቀቅ ችሏል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2011 ዓ.ም ዋንጫ የሻምፒዮናነት ሚዛኑ ወደ ሦስት ክለቦች በማመዘን ሊጠናቀቅ የሦስት ሳምንታት ጨዋታዎች ብቻ ቀርተውታል። የሻምፒዮናነት ክብሩንም ለመጎናጸፍ አጼዎቹ በ52 ነጥብ አንደኛና ቀዳሚ ዕድል ይዘዋል። በዛሬው ጨዋታ ነጥብ ተጋርቶ ወሳኙን ሦስት ነጥብ ያጣው መቐለ ሰባ እንደርታ በ50 ነጥብ ሁለተኛ በመሆን የአጼዎቹን ሽንፈት ይጠባበቃል። ከመቐለ ሰባ እንደርታ በመቀጠል 49 ነጥብ በመሰብሰብ በአንድ ግብ ተበልጦ ሦስተኛ የሆነው ሲዳማ ቡና ሌላ የሻምፒዮናነት ፍርቱና ከተጎናጸፉት ቡድኖች ተርታ የሚመደብ ሆኗል። የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮናነት ክብር ለማግኘት ሚዛን ደፊ ዕድል የያዙት ሦስቱ ክለቦች፤ከፊት ለፊታቸው የሚጠብቋቸው ሦስት ጨዋታዎች ምላሽ ይሰጣሉ። ይሁንና ክለቦቹ ቀጣይ ከሚጫወቱት ክለቦች አቋምና የጥንካሬ ዳራ በመነሳት የሻምፒዮናነት አሸናፊው መገመት አስቸጋሪ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል። የሆነው ቢሆንም፤የሊጉ አናት ላይ የሰፈሩት አጼዎቹ የሚኖራቸው ጨዋታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አዳማ እና ስሁል ሽረ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የአጼዎቹን እግር የሚከተለው መቐለ ሰባ እንደርታ በበኩሉ ከድሬዳዋ፣ደቡብ ፖሊስ እንዲሁም ከመከላከያ ከፊት ለፊቱ የሚጠብቁት ወሳኝ ጨዋታዎች ናቸው። ሲዳማ ቡና ደግሞ ከድሬዳዋ፣ ከደደቢት እና ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚጫወት ይሆናል። በእነዚህ ሦስት ጨዋታዎች የሻምፒዮናነት ክብር ወዴትኛው ክለብ እንደሚያርፍ የሚለይ ይሆናል። ለሻምፒዮናነት በሚደረገው ግስጋሴ ውስጥ ደግሞ ደቡብ ፖሊስ በሃያ ስምንት ነጥቦች አስራ አራተኛ፤ ስሁል ሽረ በሃያ ሰባት ነጥቦች አስራ አምስተኛ እንዲሁም ደደቢት በአስራ ሦስት ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ በመያዝ፤ ለመውረድና ለመውጣት የሚያደርጉት እልህ አስጨራሽ ጨዋታ እንደሚሆን ይጠበቃል። የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ፉክክር የመቀሌው አማኑኤል ገብረሚካኤልና የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በአስራ አምስት ግቦች አንደኛ ሁለተኛ ሲሆኑ፣ የፋሲሉ ሙጂብ ቃሲም በአስራ አራት ግቦች ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል።አዲስ ዘመን ሰኔ 12/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12738
343cd7cf047ced2d2bb12bd652c6d2a2
e4da8385218b54a4aa19deeb7c96aef8
የአፍሪካ ዋንጫ አይረሴ አጋጣሚዎች 
ተወዳጁ የአፍሪካ ዋንጫ ተወዳጅነቱ እየተሸረሸረ መጥቶ ለሰላሳ ሁለተኛ ጊዜ በፈርኦኖቹ መንደር ሊጀመር የሃያ አራት ሰዓታት እድሜ ይቀረዋል፡ ፡ ከዓለም ዋንጫ ቀጥሎ በብሔራዊ ቡድኖች መካከል የሚካሄድ ታላቅ የእግር ኳስ መድረክ የሆነው የአፍሪካ ዋንጫ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሚሰጠው ትኩረትና ተወዳጅነቱ አሁን ላይ አብሮት ነው ለማለት አይቻልም፡፡ እኤአ ከ1957 ጀምሮ በአራቱ መስራች አገራት (ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ግብፅና ደቡብ አፍሪካ) አማካኝነት ተጀምሮ ባለፉት ሃምሳ ስድስት ዓመታት የተሳታፊ አገራትን ቁጥር እየጨመረ መጥቶ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሃያ አራት አገራት መካከል ይካሄዳል፡፡ በነዚህ ዓመታትም በርካታ አይረሴ አጋጣሚና ታሪኮችን በእግር ኳስ አፍቃሪው ዘንድ አኑሯል፡፡ ጥቂቶቹን እንመልከት፡፡ የአፍሪካ ዋንጫ ከተጀመረ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ቢሆነውም በቴሌቪዥን መስኮት ለተቀረው ዓለም መድረስ የቻለው ሰላሳ ዓመታትን ዘግይቶ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዥን የተላለፈው የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን አስተናጋጅነት የተካሄደው ሲሆን በበርካታ የስፖርት ቤተሰቦች ተወዳጅነትን ለማግኘት መሰረት ያገኘበት የተለየ አጋጣሚና ታሪክ ሆኖ ይታወሳል፡፡ አፍሪካ ዋንጫ በመጣ ቁጥር በበርካታ የመለያ ምት የተጠናቀቀውና ‹‹ማራቶን የመለያ ምት›› ተብሎ የተሰየመው የፍፃሜ ጨዋታ አይዘነጋም፡ ፡ እኤአ 1992 ሴኔጋል ባስተናገደችው የአፍሪካ ዋንጫ ጋና ለአራተኛ ጊዜ ቻምፒዮን ከሆነች አስር ዓመታት በኋላ ለአምስተኛ ጊዜ ዋንጫውን ለማንሳት ከጎረቤቷ ኮትዲቯር ጋር ለፍፃሜ ደርሳለች፡፡ ኮትዲቯር በበኩሏ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ለመሳም ከጫፍ ደርሳለች፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በመቶ ሃያ ደቂቃዎች የሜዳ ላይ ፍልሚያ ኳስና መረብን ማገናኘት አልቻሉም፡፡ አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት መሄድ የግድ ሆነ፡፡ ኮከባቸው አቢዲ ፔሌን ጥለው የገቡት ጋናዎች በእግር ኳስ ታሪክ ረጅም ከሆነው የመለያ ምት በኋላ 11ለ10 በመሸነፍ ለአዲሱ ቻምፒዮን ዋንጫውን አሳልፈው ሰጡ፡፡ እኤአ 1957 የመጀመሪያው አፍሪካ ዋንጫ ላይ በአፓርታይድ ሥርዓት ከውድድር ውጪ የሆኑት ደቡብ አፍሪካዎች በ1996 የአፍሪካ ዋንጫ የፖለቲካ ባህላቸው ተለውጦ እግር ኳስ ለውህደታቸው ቁልፍ ሚና የተጫወተበት አጋጣሚ በመሆኑ ብዙዎች አይረሱትም፡፡ አገሪቱ ከአፓርታይድ ሥርዓት ተላቃ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማድረግ ከሁለት ዓመት በኋላ ኬንያ ባሰናዳችው አፍሪካ ዋንጫ ቀርባለች፡፡ ለፍፃሜ የቀረበችው ቱኒዚያን ሁለት ለምንም በማሸነፍም እስካሁን የመጀመሪያዋ የሆነውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች፡፡ ለዚህም ድል የወቅቱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንትና የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ለባፋና ባፋናዎቹ አምበል ኔል ቶቬይ ከፍፃሜው ጨዋታ በኋላ ዋንጫውን በክብር አስረክበዋል፡፡ ናይጄሪያ የአፍሪካ ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ አስተናግዳ ለመጀመሪያ ጊዜ ቻምፒዮን ከሆነች አስራ አራት ዓመታት በኋላ ወርቃማ የእግር ኳስ ትውልዷ ታሪክ የሰራበት አጋጣሚ እኤአ 1994 ላይ ተከሰተ፡፡ በእርግጥ ወርቃማው የእግር ኳስ ትውልድ የአህጉሪቱን እግር ኳስ በበላይነት መቆጣጠር የጀመረው ከሌጎሱ ድል በኋላ ቢሆንም በድል የታጀበ አልነበረም፡፡ 1988ና 1992 ላይ በአፍሪካ ዋንጫው ለፍፃሜ ደርሶ አልተሳካለትም፡ ፡ 1994 ላይ ግን በምንጊዜም ከዋክብቶቹ ራሺድ ያኪኒና ኢማኑኤል አሙኒኪ ምትሃተኛ ብቃት ታጅበው ዋንጫውን የሳሙበት አጋጣሚ አሁንም ድረስ በብዙዎች ይታወሳል፡፡ ሰባ ስድስት ሺ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያለው የአልጄሪያ ስቴድየም በ1990 የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ በማይታመን መልኩ ከመቶ ሺ በላይ ተመልካቾችን አምቆ መያዝ ችሏል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፍፃሜው ተፋላሚ አልጄሪያና የወቅቱ የአህጉሪቱ አስፈሪ ስብስብ ናይጄሪያ ናት፡፡ በዚህ ጨዋታ አልጄሪያ አንድ ለምንም በማሸነፍ ዋንጫውን ስታነሳ በስቴድየም የነበረው ድባብ በየትኛውም የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ያልታየና የማይረሳ ሆኖ ይታወሳል፡፡ በዘፋኝነት ጭምር ብዙዎች የሚያስታውሱት የደቡብ አፍሪካው ኮከብ ቤኒ ማካርቲ በየትኛውም የእግር ኳስ መድረክ በየትኛውም ኮከብ ለመፈፀም የማይቻል የሚመስለውን ታሪክ በ1998 የአፍሪካ ዋንጫ መፈፀም ችሏል፡፡ በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ማካርቲ ናሚቢያ ላይ በአስራ ሦስት ደቂቃዎች ውስጥ አራት ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ አይረሴ ታሪክ ሰርቷል፡፡አዲስ ዘመን ሰኔ 13/2011ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12832
3ff251d9576bacb395f85ed0000cb1dd
7d6f71976e9f5b884a8ae31256a3d801
የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ከ30 በላይ ሜዳዎች እየሠራ ነው 
አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ከማዘውተሪያ ስፍራ ጋር ተያይዞ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ ከሰላሳ በላይ ጥርጊያ ሜዳዎች እየሰራ መሆኑን ገለጸ። የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ በመዲናዋ በስፖርቱ ዘርፍ በስፋት ከሚነሱ ችግሮች የማዘውተሪያ ስፍራ ምልኡ አለመሆን በዋነኛነት ይጠቀሳል። በተለይ ደግሞ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠናው ላይ በስፋት ከሚስተዋሉት ችግሮች ዋነኛው የማዘውተሪያ ቦታ መሆኑን ኮሚሽኑ ያስጠናው ጥናት ውጤት አመልክቷል። ከጥናቱና ከተጨባጭ እውነታው በመነሳት ችግሩን ለመቅረፍ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ፤በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከ30 በላይ ጥርጊያ ሜዳዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። ሜዳዎቹ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ክቡር ከንቲባው ባሉበት ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ይደረጋል ብለዋል። ኮሚሽኑ በተመሳሳይ የሚታዩትን ጉድለቶች ለመሙላት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ፤ስፖርቱ ከታች ጀምሮ በሙያተኛው አለመመራቱ ለዘርፍ ውጤት አልባ መሆንና ውጥረት እንዳያመጣ ቁልፍ ምክንያት እንደሆነ ሲነገር ነበር። ስፖርቱን የማያውቁት ሰዎች ናቸው የሚቀመጡት፣ ስፖርቱን ከመምራት ይልቅ ሌላ ስራ ነው የሚሰሩት የሚሉና መሰል ትችቶች የሚነሱ መሆኑን የገለጹት አቶ ዮናስ፤ ሃሳቡ በስፖርት አዋቂዎችና ቤተሰቡ በኩል በስፋት ሃሳብ ሲሰነዘርበትም ጭምር መቆየቱን አስታውሰዋል። በመሆም በስፖርት ኮሚሽኑም በኩል ይሄንኑ በመፈተሽ ስፖርቱ በባለሙያ መመራት አለበት የሚል አቅጣጫ አስቀምጧል። ስፖርቱ እታች ላይ በሹመት ተመድቦ ሲመራ የነበረውን የጽፈት ቤት ኃላፊነት መደብን በስፖርት ሙያተኞች እንዲመራ ተደርጓል። በስፖርት ሳይንስ የጨረሱ ሙያተኞች በማሰባሰብ ነባር ቀበሌዎችንና ቀጣናውን በማስተባበርና በመምራት ስፖርቱ መሰረታዊ ለውጥና ውጤት እንዲያመጣ ያስችላል የሚል እምነት መኖሩን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ እንዲህ አይነትና መሰል እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ በቀጣይ ውጥኖችን የያዘ መሆኑን ገልጸው ፤ ህብረተሰቡ በመኖሪያ አካባቢ የማስ ስፖርት እንዲያዳብር ፣ተማሪው በትምህርት ቤቱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ፣ በወይኒ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ የሚያስችሉ ሰፊ ስራዎችን ለማድረግ ውጥን መያዙን ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ሰኔ 13/2011ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12835
e6c3da8d61cab711913f33ca7301eaaa
5fe4fbe76d67c5baf14c462789a0e8e1
ከባህር ማዶ የነገሠው የኢትዮጵያዊያን ድምፅ
ሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2012 ምሽት በኢትዮጵያ ሰምይ ስር አንድ ክፉ ጥላ አጠላ። ሀገርን ወደ ትርምስ ለመክተት ባሰቡ ወንጀለኞች እኩይ ተግባር አዲስ አበባ ገላን አካባቢ አስደንጋጭ ዜና ተሰማ። ስለ ህዝቦች መብት የሚሟገተው የኦሮሚኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ ሀጫሉ ሁንዴሳ መሞት ኢትዮጵያዊያን በኀዘን ስሜት ተቀባበሉት። የዚህ ታላቅ አርቲስት በሴረኞች መገደል ሰምተው ልባቸው በኀዘን የተሰበረው አይናቸው በእንባ የራሱት ኢትዮጵያዊያን ሌላ አስደንጋጭ ድርጊት ባልጠበቁት መልኩ ገጠማቸው። በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች የህዝብን አብሮነት በሚንድ ለዘመናት ጠብቆ ያቆየውን እሴት በተቃረነ መልኩ የጥፋት ኃይሎች በህዝብ ላይ ባደረሱት ጥቃት የንፁሐን ህይወት ተቀጠፈ፤ ይህች ታዳጊ አገር ከሌላት ላይ ቆንጥራ የገነባቻቸው የልማት አውታሮች ወደሙ። ዜጎች ለፍተው ጥረው ያፈሩት ንብረት እንደ ዘበት ዶጋመድ ሆነ።ይሄኔ መንግሥት የሀገር ህልውና ከስጋት ወደቀ፤ ዜጎች የመኖር መብታቸው በሴረኞች ታወከ ብሎ ህግ የማስከበሩ ዕርምጃ መውሰድ ግድ አለው። በዚህም አገሪቱ እንድትበታተን፣ ዜጎች ሰላማቸው እንዲደፈርስ የተመኙና የሞከሩ ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰድና በአገር ላይ የተጋረጠውን አደጋ መቆጣጠር ቻለ። የመንግሥት ህግ የማስከበር ዕርምጃ በተፈጠረው ችግር የራሳቸውን ዓላማ ማሳካት የፈለጉ ኃይሎች ቢቃወሙትም የአገርን ህልውና የሚፈልጉ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት መንግሥት የጀመረውን አገር የማዳንና የህግ የማስከበር ሥራ አጠንክሮ እንዲቀጥል በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሚገኙ የዓለም ታላላቅ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ድጋፋቸውን ለመንግሥት በመግለጽ ላይ ናቸው። ሰሞኑን በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲስ፣ ላስ ቬጋስ፣ በእንግሊዝ ለንደን፣ በኖርዌይ ኦስሎ በሌሎችም የአውሮፓና የአሜሪካ ከተሞች ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተፈፀሙ ግድያዎችና የንብረት ውድመትን የተቃወሙ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግሥት አሁን የጀመረውን የህግ ማስከበር ዕርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል። ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን በዋሽንግተን ዲሲ በጠሩት ህዝባዊ ትዕይንት ላይ ተገኝተዋል። አስተያየታቸውን የሰጡት የሰልፉ አስተባባሪና ተሳታፊ አቶ ቴድሮስ ካብትይመር እንዳሉት ኢትጵያዊያን በአንድ በመቆም በአገሪቱ ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለማውገዝና የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመረውን ህግ የማስከበር ዕርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ለመጠየቅ ህዝባዊ ትዕይቱ ተዘጋጅቷል ብለዋል። ሰልፈኞቹ በዚሁ ወቅት በአገር ጉዳይ አንደራደርም፣ መንግሥት እየወሰደ ያለው የህግ ማስከበር ሥራ አጠናክሮ ይቀጥል፣ በኢትዮጵያ ላይ የመጣ ማንኛውም ኃይል እንቃወማለን፣ ወንጀለኞች ለህግ የማቅረቡ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥል የሚል መፈክር ይዘው ሲያስተጋቡ መዋላቸውን የሰልፉ አስተባበሪዎች ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በላኩት መልዕክት ገልጸዋል። በአሜሪካ ቨርጂንያ ከተማ ሰልፍ የወጡት ደግሞ መንግሥት የወሰደውን ህግ የማስከበሩን እርምጃ እንሚደግፉትና ኢትጵያዊያን በማንኛውም ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪ የሆኑንት አቶ ሰለሞን ጀማነህ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በላኩት መልዕክት አስታውቀዋል። በእንግሊዝ ዋና ከተማ ሎንደን በተካሄደው ሰልፍ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን መንግሥት እያደረገ ያለውን ህግ ማስከበር እርምጃ እንደሚደግፍ የገለጹ ሲሆን፤ በአገሪቱ ላይ እንቅፋት ለመፍጠር የሚሞክሩ ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጠይቀዋል። በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የጥላቻ መልዕክት በማሰራጨት ላይ የሚገኙ አካላት ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። በኖርዌይ ኢትዮጵያዊያን በጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በርካታ ህዝብ መገኘቱን የገለጹት የሰልፉ አስተባባሪ አቶ ጌታቸው በቀለ ኢትዮጵያዊያኑ የመግሥትን የህግ ማስከበር እርምጃ እንደሚደግፉና የጥፋት ኃይሎች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈጸሙ ያሉት ግድያ አውግዘው ጥፋተኞች ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የመንግሥንት ህግ የማስከበር እርምጃ በመደገፍ የድጋፍ ሰልፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።አዲስ ዘመን ሐምሌ 12/2012ተገኝ ብሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35653
12b096e877b27fec85c73055f10ca6cc
0d69ccf7a74bc0214664a4891123265c
ኢንስቲትዩቱ ከውጭ ገበያ ከ37 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
አዲስ አበባ፡- የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በበጀት ዓመቱ ባለፉት 11 ወራት ወደ 30 ሀገራት የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ(ኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክስ) ምርቶችን ልኮ 37 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።የኢንስቲትዩት የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፊጤ በቀለ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በዓለም አቀፉ ገበያ ውስጥ ተሳትፎ ካደረጉ 18 ኩባንያዎች የኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ምርት በመላክ በአስራ አንድ ወራት 37 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። የምርቶቹ የገበያ መዳረሻ ከጎረቤት አገራት ጀምሮ እስከ አውሮፓና አሜሪካ በመዝለቅ በዕቅድ ዘመኑ 30 አገሮች የሀገራችንን ምርቶች ተቀባይ ለማድረግ ተችሏል። እንደ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ገለፃ፤ የ2012 በጀት ዓመት የአስራ አንድ ወራት ዕቅድ 55 ሚሊዮን 748 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ እንደ መኪና፣ ሞባይል፣ አልሙኒየም፣ ቆርቆሮ እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ወደ ተለያዩ አገሮች ለመላክ ግብ በማስቀመጥ ወደ እንቅስቃሴ የገባ ሲሆን፤ ከተላከው ምርት ከ37 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ችሏል።በመሠረታዊ ብረታ ብረት በአገር ውስጥና በውጭ ባለሀብት 14 ሚሊዮን 500 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለመላክ ታቅዶ 3 ሚሊዮን 409 ሺህ ዶላር ተገኝቷል። በኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክስ 41 ሚሊዮን 247 ሺህ ታቅዶ በአፈፃፀም 33 ሚሊዮን 593 ሺህ በላይ መላክ ተችሏል። በአጠቃላይ ከሐምሌ 2011 እስከ ግንቦት 2012 ዓ.ም ባለው ወቅት በመሰረታዊ ብረታ ብረት ፣ በኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ከ37 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ዋጋ የሚያወጡ የተለያዩ ምርቶችን ወደ 30 ሀገራት መላክ ተችሏል። ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የኤክስፖርት ምርቱ ቀንሷል ያሉት ዳይሬክተሩ ቀደም ሲል የምንዛሬ እጥረት በመኖሩ ምክንያት ኢንዱስትሪዎቹ የአቅማቸውን ያህል አምርተው ለገበያ እያቀረቡ እንዳልነበረ አስታውሰዋል። የኩባንያዎቹ ግብአት ከውጭ የሚመጣ በመሆኑም በተለያየ ምክንያት የሚፈለገውን ያክል ምርት ማምረት አለመቻሉን ገልጸዋል። የጥሬ ዕቃና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ኮሮና ቫይረስ ጋር ተደማምሮ ኢንዱስትሪዎቹ ከአቅም በታች ያመርቱ እንደነበር አስታውሰው ያም ሆኖ ግን ለውጭ ገበያ እና ለአገር ውስጥ ለግልና ለመንግሥት ምርት እያቀረቡ ናቸው።በብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ንዑስ ዘርፍ በ2006 ዓ.ም እጅግ ዝቅተኛ በሆነ የወጪ ንግድ አፈፃፀም የተጀመረ ቢሆንም በየዓመቱ በምርት ዓይነትና በተሳታፊ ኢንዱስትሪዎች ብዛት እንዲሁም በገበያ ተደራሽነት ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች አሳይቷል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 12/2012ዳግም ከበደ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35684
a8824924086bf70241bf9d44830bd684
fc4d8d99328e028effe26b6a4c41d917
ኮሚሽኑ ማህበረሰብን የማደራጀትና የሆቴሎች ድንገተኛ ፍተሻ መጀመሩን አስታወቀ
 ማህበረሰቡ ለማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ተቀጣሪዎች በዓመት ከ25 ሚሊዬን ብር በላይ ይከፍላልአዲስ አበባ፡- የከተማውን ደህንነትና ጸጥታ ለመጠበቅ በህጋዊ መንገድ ማህበረሰቡን የማደራጀትና የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ሆቴል፣ ፔንሲዮንና መሰል ቤቶችን ድንገተኛ ፍተሻ እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቁ። ማህበረሰቡ በከተማው ጸጥታና ደህንነት እንዲረጋገጥ በዓመት ለማህበረሰብ አቀፍ ተቀጣሪ ጠባቂዎች ከ25 ሚሊዬን ብር በላይ ይከፍላል።በኮሚሽኑ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ኃላፊ ኮማንደር ሰለሞን ፋንታሁን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በከተማዋ የሚታየውን ድንገተኛ ችግሮች ለመፍታት ፖሊስ ብቻውን የሚያደርገው እንቅስቃሴ አጥጋቢ ባለመሆኑ የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎቱን ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ሥራ እየተሠራ ነው። በአሁን ወቅት ድንገተኛ ችግሮች ጠንከር እና ውስብስብ እየሆኑ ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ሥራ ለማከናወን በየአካባቢው ራሳቸውንና አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ በአስሩም ክፍለ ከተሞች እውቅና ያለው ማህበረሰብን የማደራጀት ሥራ ተጀምሯል። ሆቴሎች ቀደም ሲል በየቀኑ የሚያድሩ ሰዎችን ማንነት በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት እንደሚያቀርቡ የገለጹት ኮማንደሩ፤ አሁን ላይ እየተፈጠሩ ካሉ ችግሮች ስፋትና ክብደት አንጻር ይህንን ማድረጉ ብቻ በቂ አለመሆኑን ጠቅሰዋል። በመሆኑም በከተማዋ የመኝታ አገልግሎት በሚሰጡ ሆቴሎች፣ ፔንሲዮንና መሰል ሥራ ውስጥ በተሰማሩት ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ይደረጋል። በተመሳሳይ በፈቃዳቸው የተደራጁ የአካባቢ ጠባቂዎችንም በቅርበት ክትትል እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። ከከተማው ስፋትና ከወንጀሎች ውስብስብነት አንጻር በቀጠና ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ላይ አንድ ኦፊሰር እንደሚመደብ የተናገሩት ኮማንደር ሰለሞን፤ይሄ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥም ሆነ ለሚፈጠረው ችግር ለመድረስ እጅግ ፈታኝ ነው። ስለሆነም በየደረጃው የተለያዩ አደረጃጀቶች ተፈጥሮው እየተሠራ ይገኛሉ። ሆኖም ወቅታዊ ችግሮች ሲመጡ ከበድ ስለሚል ፈጣንና ወቅታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ በዋናነት በሁለት መልኩ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል። ኮማንደር ሰለሞን እንዳሉት፣ ነዋሪው አካባቢውን እንዲጠበቅ ማድረጉ ችግር የሚፈጥረውን አካል ወዲያው አግኝቶ ዕርምጃ እንዲወሰድ ከማድረጉም በላይ የፖለቲካ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ሲሉ የተደራጁ አካላትን ለማስቆም ያግዛል። በተመሳሳይ ማህበረሰቡን ከአደጋ ለመጠበቅም ፍቱን መፍትሔ ነው። የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎቱን በዚህና መሰል መንገዶች የማጠናከርሥራው ይቀጥላል ብለዋል። በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ማህበረሰቡ ተሳትፎውን በተለያየ መልኩ እያሳየ መሆኑን የጠቀሱት ኮማንደር ሰለሞን ፤ ከዚህ ውስጥ በዓመት በከተማው የጸጥታና ደህንነት እንዲረጋገጥ ለማድረግ ለጥበቃ ቅጥር ከ25 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ አድርጎ እንደሚሸፍን አስታውቀዋል። የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎቱ በከተማ ደረጃ በ2005 ዓ.ም ቢጀመርም ብዙ ተግዳሮት አለበት ያሉት ኮማንደሩ በውጤት የተደገፈ ነው ለማለት ያስቸግራል። ሆኖም በ2011 መጨረሻ ችግሮች ተለይተው በተሻለ ሁኔታ እየተሠራና ለውጦች እየታዩ ነው። ማህበረሰቡም ፖሊስን እያመነውና አብሮ ለመሥራት ፈቃደኝነቱን እያሳየ መጥቷል። በዘንድሮ ዓመት ብቻ ለአካባቢ ጥበቃ ቅጥር ከ25 ሚሊዬን ብር በላይ አውጥቶ ደመወዝ ከፍሏል። ማህበረሰቡ ከኮሮና ጋር እየተሟገተ ባለበት በዚህ ወቅት ሳይቀር ድጋፉን ከማድረግ ወደኋላ እንዳላለ የሚገልጹት ኮማንደሩ፤ ዘንድሮ ብቻ 33 ደረጃቸውን የጠበቁ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት መስጫ የቀጠና ማዕከላት ተገንብተው ሥራ ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፤ ለዚህም 11 ሚሊየን 711 ሺህ 611 ብር ወጪ መደረጉን ገልጸዋል። በዚህ ዓመት ብቻ 3 ሺ 472 የሚሆኑ ጥበቃዎች የተቀጠሩ ሲሆን፤ ነባር 8 ሺ122 አሉ። እስከአሁን ማህበረሰቡ 12 ሺ 494 የሚሆኑትን ቅጥር ጥበቃዎች ደሞዝ ይከፍላል። በከተማ አስተዳደሩ 60 ፖሊስ ጣቢያ፣ 121 ወረዳና 833 ቀጠና አለ፤ በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊሲ አገልግሎት ይሰጣል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 12/2012ጽጌረዳ ጫንያለው
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35654
cbb6d556e6758607bf8aad3c366ff2e0
88bbd09339e9195dd63b91ce8632c840
ህዝብን ከህዝብ ለማባላት የታቀደው ሴራ በአዳባ
ወይዘሮ የዝና ጨርቆሴ፣ የአዳባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ፤ ከሰሞኑ ተከስቶ በነበረው ሁከት ቤት ንብረታቸውን ብቻ ሳይሆን ባለቤታቸውን አቶ ዘውዱን እና የልጃቸውን ባል አቶ ሰለሞንን በሞት ተነጥቀዋል። ሌላው ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰብ አቶ ካሳሁን ተሾመ በበኩላቸው እንደሚሉት፤ በዕለቱ ንጋት ላይ የጀመረው ሰልፍና ሁካታን ተከትሎ የሰው ንብረት ማውደም መጀመራቸውን የሰሙት ከቤት ሆነው ነበር። ችግሩ እየከፋ መሄዱን ሲገነዘቡም ሆቴላቸውን ሊመለከቱ ይወጣሉ። በስፍራው ሲደርሱ ግን ነገሮች ተቀይረዋል፤ ሆቴሎቻቸውም በእሳት ተያይዘው፣ ግርግሩም በዝቶ አገኙት። በወቅቱም እንኳን እየተቃጠለ ያለውን ንብረታቸውን ሊያድኑ ቀርቶ፤ራሳቸውንም ማዳን እንደማይችሉ በመገንዘባቸው የሚቃጠሉ ሆቴሎቻቸው ወደአመድነት እየተቀየሩ እያዩም ቢሆን አካባቢውን ትተው ይሄዳሉ።ይሄን መሰል ጥቃት ሲደርስባቸው ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ካሳሁን፤ በዚህኛው የሀጫሉን መገደል ምክንያት አድርገው ወጡ እንጂ አካሄዳቸው አንድም ብሔርን ካልሆነም ሃይማኖትን ተገን አድርገው ኅብረተሰቡን እርስ በእርስ ለማባላት የሚፈጸም የጽንፈኛ አመለካከት ባለቤቶች የሚከውኑት ተግባር መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም አሁን ላይ አንድም ንብረታቸው በመውደሙ፤ ሁለተኛም ለህይወታቸው በመስጋታቸው በቤተክርስቲያን ተጠልለው እን ዳሉ በመጠቆምም፤ ይሄን ዓይነት ተደጋጋሚ ጥቃቶች በከተማዋ እየተበራከቱና እየተደጋገሙ በመምጣታቸው ህዝቡ በስጋትና ሰቀቀን እየኖረ እንደመሆኑ መንግሥት መኖሩን በተግባር ሊያሳየን ይገባል ይላሉ። ይህ አካባቢ በተደጋጋሚ የሰላም፣ የህግና ፍትህ ችግር የሚስተዋልበት እንደመሆኑ፤ አሁን በተፈጠረው ችግርም ያንን ማድረግ ባለመቻሉ ህዝቡ ንብረቱን ብቻ ሳይሆን ውድ ህይወቱን በግፍ እያጣ ይገኛል። እናም እነዚህ ወገኖች ችግሮች ተደጋግመው የሚፈጸሙባቸው እንደመሆኑ ከምንም በላይ ድምፃቸውን የሚያሰሙበት የመገናኛ አውታር አብዝተው የሚናፍቁ ናቸው። ምክንያቱም ብዙዎች ተጎድተው የሚያነቡ እንደመሆኑ እንባቸውም ለህዝብና ለመንግሥት የሚያደርስላቸው ይሻሉ፤ ዘወትር በስጋትና በፍርሐት ውስጥ እንደመሆናቸውም ይሄን ጭንቀታቸውን ሰምቶ የሚደርስላቸው የመንግሥት አካል አብዝተው ይናፍቃሉ። በመሆኑም ህዝቦች እንባቸው እንዲታበስ፤ በሰላም ወጥተው እንዲገቡ፤ ሠርተው ንብረት እንዲያፈሩ ብቻ ሳይሆን የንብረታቸው ባለቤትም ተጠቃሚም እንዲሆኑ መንግሥት ጆሮ ሰጥቶ የሲቃ ጩኸታቸውን ሊያዳምጥና ምላሽ ሊሰጥ ይገባል።የአዳባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙስጠፋ ዑመር እንደሚሉት የተፈጠረው ችግር ከባድና ጠላት ተዘጋጅቶበት በቅንብር የተፈጸመ ነው። በወቅቱ ኀዘኑን ለመግለጽ የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍ የሚመስል ቢሆንም፤ በሂደቱ አቅጣጫውን ሲቀይር ችግሩን ለመከላከል በአገር ሽማግሌና የሃይማኖት አባቶች ጭምር በመታገዝ ጥረት ተደርጓል። ሆኖም ነገሮች ከአቅም በላይ ሆነው በሆቴሎች፣ በሱቆችና በመኖሪያ ቤቶች ጭምር በተፈጸመ ጥቃት ከባድ የንብረት ውድመትና ከአራት ያላነሱ ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል። ይህ ከሆነ በኋላ ግን አመራሩም፣ የጸጥታ ኃይሉም በጋራ ተሠርቶ ችግሩን ለመቀነስ የተሞከረ ሲሆን፤ በየቤቱ እየሄዱ በሰዎች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ እንደመሆኑ ችግሩን በሚፈለገው ፍጥነት መግታት አልተቻለም።እንደ አቶ ሙስጠፋ ገለጻ፤ ይህ ጥቃት አንድም ሃይማኖትን፣ ሁለተኛም ብሔርን ለይቶ ለማጥቃት የተፈጸመ ለማስመሰል ተሞክሯል። የተጎዱ ወገኖችን ባሉበት ሁኔታ ለመደገፍም ሆነ የጠፋባቸውን ንብረት ለመተካት የሚያስችሉ ሥራዎች በህብረተሰቡ በራሱ ተነሳሽነት እየተሠሩ ይገኛሉ። ከዚህ ባለፈም አሁን የሆነው ነገር ጠላት አቅዶበት ያደረገው እንደመሆኑ አስተዳደሩ ሳይዘጋጅ የተፈጠረና ውድመትም ሞትም ያስከተለ ነው፤ በዚህ ጥፋት ላይ ተሳታፊ ናቸው ተብሎ የተጠረጠሩ ከ102 ሰዎች በላይ ተይዘዋል። በቀጣይም ህብረተሰቡ ያለበትን ስጋት ለማስወገድና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ለማድረግ መንግሥት ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ እየሠራ ይገኛል።የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ቀደም ሲል እንደጠቀሱት በኦነግ ሸኔ፣ በህወሓት ጥገኛ ቡድንና በውጭ ኃይሎች ቅንጅት አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በሴራ በማስገደል በቀሰቀሱት ሁከት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት ሲያልፍ ከፍተኛ ግምት ያለው ሀብትና ንብረትም ወድሟል። ከዚህም ጋር ተያይዞ አጥፊዎችን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢውን ፍርድ እንዲያገኙ የማድረግና የመንግሥት መዋቅሩንም በመፈተሽ የማጽዳት ሥራ እየተሠራ መሆኑን መገለጻቸው ይታወሳል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 13/2012ወንድወሰን ሽመልስ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35714
ee0f2c55059b18629be2aa76652a8dd9
3b230700ecd26f47779536d4ac20ef1f
ወጣት የቴክኖሎጂ የፈጠራ ባለሙያዎች ኢትዮጵያን ወደፊት እንደሚያሻግሯት ተገለጸ- የፈጠራ ባለሙያው ወጣት ናኦል ዳባ ሁለት ድሮኖችን አስተዋወቀ
 አዲስ አበባ፡- ወጣት ባለሙያዎች የሚፈጠሯቸው ችግር ፈች ቴክኖሎጂዎች ኢትዮጵያን ወደፊት እንደሚ ያሻግሯት የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የፈጠራ ባለሙያው ወጣት ናኦል ዳባ ሁለት ሰው አልባ በራሪዎች(ድሮች)ና አንድ የሙቀት መለኪያ ማሻን አስተዋውቋል፡፡የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ትናንት በሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተካሄደው የወጣቱ የፈጠራ ሥራዎች ማስተዋወቂያ መድረክ ላይ እንደገለጹት፤ የኢኮኖሚ ልማትን ለማፋጠንና የሥራ ዕድልን ለመፍጠር ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ እንደ ወጣት ናኦል ዓይነት የፈጠራ ባለሙያዎች ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ወደፊት የሚያሻግሯት ይሆናሉ፡፡በኢትዮጵያ በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙትን 26 ሚሊዮን ተማሪዎች ሁሉ መንግሥትና የግሉ ዘርፍ ሥራ መፍጠር እንደማይችል የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ተማሪዎች እንደ ናኦል ዓይነቱን የብሩህ አዕምሮ ባለቤት ወጣት ተምሳሌት በማድረግ ለአገራቸውና ለራሳቸው በሚጠቅምና ሌሎች ሥራ የሚፈጥር የፈጠራ ሥራ ላይ መስማራት እንደሚኖርባቸው መክረዋል፡፡መንግሥት ወጣቶች በተለያዩ የሙያ መስኮች ክህሎትና እውቀት ይዘው እንዲወጡ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኘ አመልክተው፣ የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት የወጣት የፈጠራ ባለሙያዎችን ሥራዎች በመግዛት ሊያበረታቷቸው እንደሚገባም አስገዝበዋል፡፡ወጣት የፈጠራ ባለሙያው ናኦል ዳባ ያስተዋወቃቸው የፈጠራ ሥራዎች የፀረ፣አረምና ፀረ ተባይ መርጫ ድሮን፣የህዝብ መልዕክት ማስተላፊያ ድሮንና የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የሙቀት መለኪያ ማሽን ናቸው፡፡ ወጣት ናኦል የሙቀት መለኪያው አዳማ መመረት መጀመሩን ጠቁሞ፣ ሆቴሎችና ባንኮች ግዥ ፈጽመው እየተጠቀሙበት እንደሚገኘ አስታውቋል፡፡ ለድሮኖቹ ለማምረትና አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል ፈቃድ እንዳገኘ ለገበያ እንደሚቀርቡ አመልክቷል፡፡ወደፊትም በድሮን ቴክኖሎጂና መሰል የፈጠራ ሥራዎችን በኢትዮጵያ በማምረት ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካና በዓለም ገበያ የማቅረብ ዕቅድ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ፤የተቀላጠፈ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የፈጠራ ሥራዎችን ማበረታታት ተገቢናአስፈላጊ እንደሆነ አስታውቀዋል።የትራንስፖርት ሚኒስቴር በስሩ በሚገኘው የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በኩል ለድሮን ቴክሎጂና በረራ ፍቃድ ለመስጠት የሚያስችሉ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝም በቅርቡም ተግባራዊ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።ለድሮን ቴክኖሎጂና በረራ ፍቃድ ለመስጠት እየተሠራ ያለው ሥራ ለናኦል ሆነ ሌሎች በዚህ የሙያ መስክ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ዜጎች ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን አመልክተዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 13/2012
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35718
5abcf8144ec79ac98c5ac27b6da47c26
36a666236ac8d51d151c3dda951b6b60
«አባይን በሚመለከት መንግሥት የመደራደሪያ ሳይሆን የመረጃና ማስረጃ ሕጋዊ ሰነድ ማዘጋጀት አለበት” -ዶክተር ብርሃኑ ግዛው ከፍተኛ የኢነርጂ ዘርፍ ባለሙያና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር አባል
አዲስ አበባ፡- መንግሥት በውጭ አገራት የሚኖሩ ዲፕሎማሲዎችና ዲያስፖራዎችን ጨምሮ ማንኛውም ዜጋ በቀላሉ አግኝቶ እውነተኛ መረጃ የሚሸምትበት የመደራደሪያ ሳይሆን የማስረጃ አንድ ወጥ የሆነ የአባይ ግድብ ሕጋዊ ሰነድ ማዘጋጀት እንደሚገባው ተገለጸ። በማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ የኢነርጂ ዘርፍ ኤክስፐርት የነበሩትና ለበርካታ ዓመታት በአውሮፓ ቆይተው የተመለሱት፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በተለያዩ ማህበራዊ መስኮች በአማካሪነት እየሠሩ ያሉት ዶክተር ብርሃኑ ግዛው በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳሉት፤ መንግሥት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ዲፕሎማቶች፣ ዲያስፖራዎችና በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ላይ ተመሳሳይና ወጥ እውቀትና እውነተኛ መረጃ እንዲኖራቸው ማድረግ የሚያስችል ሰነድ ማዘጋጀት እንደሚገባው ተናግረዋል። ሰነዱ በተለያዩ የአገሪቱ ቋንቋዎች እና በውጭ አገር(እንግሊዝኛ ፣አረብኛና ሌሎች በርካታ ቋንቋዎች) እንዲተረጎም በማድረግ ማንኛውም ዜጋ በአገር ውስጥም ሆነ በየትኛውም ዓለም ሆኖ በቀላሉ ከድረ-ገጽ በማውረድ ስለሕዳሴው ግድብ ፕሮጀክት ከትክክለኛው አካል እውነተኛ መረጃ በማግኘትና ግንዛቤውን በማስፋት ወጥ አቋም መያዝ እንደሚያስችለውም ገልጸዋል።አገሪቱ ለምን አባይን መገደብ እንዳስፈለጋት፣ የአባይን የውኃ አስተዋጽኦ ድርሻ በግልጽ የሚያመላክት፣ ከዓለም አቀፍ ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች የውኃ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ፣ ከአገሪቱ ገጸ ምድር እና ከኃይል አጠቃቀም ጋር በተያያዘ፣ የሌሎቹን የተፋሰሱን አገራት ጥቅም የሚያስጠብቅ እንጂ የሚጎዳ እንዳልሆነ የሚያሳይ፣ የድሕነት ደረጃን የሚገልጽ፣ይሄን ዘመናዊ የኃይል ምንጭ(ኢነርጂን) ማስፋፋት በተዘዋዋሪ ለስነምህዳሩ ያለውን አበርክቶ የሚገልጽ የሕዳሴ ግድብ ሰነድ መኖር እንዳለበት አብራርተዋል። ሁሉም የመሰለውን እና የተሰማውን ከሚያቀርብ ይልቅ አንድ ወጥ የሆነ ሕጋዊ የአባይ ሰነድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በመስኖ፣ ውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አማካኝነት ተዘጋጅቶ ለዜጎች መድረስ እንደሚገባውም ነው ዶክተር ብርሃኑ የጠቆሙት። በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ብዥታ ያለባቸው፣ ዓላማና ፋይዳውን ያልተረዱ፣ ለስብሰባም ሆነ ለስልጠና የሚፈልጉት ኢትዮጵያውንም ሆኑ ሌሎች የውጭ አገር ዜጎች እንዲህ አይነት መረጃዎችን በቀላሉ ከድረገፅ አውርደው ትክክለኛ መረጃ ሊያገኙ ይችላሉ ሲሉም ተናግረዋል።መንግሥት የሕዳሴውን ግድብ አስመልክቶ የሚያዘ ጋጀውን ወጥ ሕጋዊ ሰነድ ለተለያዩ አገር መንግሥታት በሚገባቸው ቋንቋ አስተርጉሞ ማቅረብ እንዳለበት የተናገሩት ዶክተር ብርሃኑ፤ በዚያ ሰነድ ላይ ብቻ የተመሰረተ ግንዛቤ በመፍጠር ወጥ አቋም እና እውነታውን እንዲይዙ ያስችላል። እያንዳንዱ ምሁርና እያንዳንዱ ዜጋም በያለበት የሥራ ደረጃና በሚገኝበት የዓለም ጫፍ ሆኖ ይሄን ሕጋዊ የሕዳሴ ግድብ ሰነድ የማስተዋወቅና የማስረዳት ሃገራዊ ግዴታ እንዳለበት አስረድተዋል።ዜጎች የሕዳሴ ግድብን የተመለከቱ መረጃዎች ከተደራዳሪዎች ብቻ እንዲያገኙ መፍቀድ አይገባም የሚሉት ዶክተር ብርሃኑ፤ መንግሥት በዚህ ሰነድ አማካኝነት እውነተኛውን መረጃ፣ በቁጥሮች (ስታስቲክስ) አስደግፎ ካቀረበ ለሚፈልገው አካል ግልጽ ይሆንለታል። ሌሎች አገራት በራሳቸው ጉዳይ ስለሚወጠሩ፣ፍላጎታቸውም ያን ያህል ጉጉት ኖረም አልኖረም ለሚፈልገው አካል እውነተኛ መረጃ የሚሰጥ አገርን የሚወክል የመደራደሪያ ሳይሆን የማስረጃ ሰነድ አዘጋጅቶ ማቅረብ ያስፈልጋል ብለዋል። ይህ ሲሆን ለዘመናት በተንሻፈፉ አመለካከቶች እና እሳቤዎች የተጠለፉ አካላት መስመር ይይዛሉ፣ በእውነተኛ መረጃ ላይ ይቆማሉ፣ አቋም መያዝ ይችላሉ፣ ለመከራከር፣ ለማስረዳትና ለመሞገት አቅም ያገኛሉ የሚል እምነት እንዳላቸውም ዶክተር ብርሃኑ አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 13/2012ሙሐመድ ሁሴን
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35706
36a5b1eaf04cf9142ca937474fc771de
4114dbb50fc80f1c0b5eb0e5ca2580b1
«ኢትዮጵያ ግድቡን ውሃ ሞልታ በመጠቀሟ የምትጥሰው አንዳች የዓለም አቀፍ ህግ የለም» ደጀን የማነ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል የዓለም አቀፍ ህግ መምህር
አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ ከታችኞቹ የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ጋር ስምምነት ሳትደርስ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ውሃ ሞልታ በመጠቀሟ የምትጥሰው አንዳች የዓለም አቀፍ ህግ አለመኖሩን በወሎ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል የዓለም አቀፍ ህግ መምህር አስታወቁ። ግብፆች ዓለም አቀፍ ህጎችን በመጣስ ወንዙን ሲጠቀሙ መቆየታቸውንም ገለጹ።በወሎ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል የዓለም አቀፍ ህግ መምህር ደጀን የማነ በታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ኢትዮጵያ፣ በግብፅና ሱዳን መካከል ሲካሄድ የነበረው ድርድር መቋረጡን አስመልክቶ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ ሦስቱ ሀገራት በ2015 በተፈራረሙት የመርሆዎች ስምምነት መሰረት ሀገራቱ በግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ዙሪያ የመደራደር ግዴታ ስላለባቸው ኢትዮጵያም በዚሁ ስምምነት መሰረት ስትደራደር ቆይታለች። “የመደራደር ግዴታ ማለት ግን የመስማማት ግዴታ ማለት አይደለም” ያሉት የዓለም አቀፍ ህግ መምህሩ፤ በአንድ ጉዳይ ላይ ድርድር ተካሂዶ ሳይስማሙ ማቋረጥም አንዱ የድርድር ውጤት ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ከግብፅና ሱዳን ጋር ስምምነት ላይ እስክትደርስ የመደራደር ግዴታ እንደሌለባትም አመልክተዋል።ኢትዮጵያ ከሁለቱ ሀገራት ጋር ስምምነት ሳትደርስ ውሃ በመሙላት ኃይል ማመንጨት በመጀመር የምትጥሰው አንዳችም የዓለም አቀፍ ህግ የለም ያሉት መምህር ደጀን፤ ይልቁንም የውሃ ሙሌቱን በአፋጣኝ ጀምራ ኃይል ማመንጨት መጀመሯ በዓለም አቀፍ ህግ የተጣለባትን ግዴታ ለመወጣት እንደሚያስችላት ተናግረዋል።እንደ መምህር ደጀን ማብራሪያ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦች ብሎ በ2030 እኤአ ለማሳካት የያዛቸው ግቦች አሉ። አንዱ ደግሞ ህዝብን ከድህነት ማውጣት ነው። የኢትዮጵያን ህዝብ ከድህነት ማውጣት የኢትዮጵያ መንግሥት ግዴታ ነው። ኢትዮጵያ እነዚህን ግዴታዎቿን መወጣት የምትችለው እና ህዝቦቿን ከአስከፊ ድህነት ማውጣት የምትችለው የተፈጥሮ ሀብቶችን በአግባቡ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም ስትችል ነው። ለዚህ ደግሞ ታላቁን የአባይን ወንዝ ማልማት ለነገ የማይባል የቤት ሥራዋ ነው።ግብጽ ዓለም አቀፍ ህጎችን በመጣስ ወንዙን አለግባብ ስትጠቀም ኖራለች ያሉት መምህር ደጀን፤ በተለይም በዓለም አቀፍ ህግ የልማዳዊ ህግ ደረጃ የደረሱ መርሆዎችን እንዲሁም አካባቢን የሚያስተዳድሩ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን በመጣስ ወንዙን ስትጠቀም ኖራለች ብለዋል። አሁንም እነዚህን ዓለም አቀፍ ህጎችን በመጣስ እየተጠቀመችበት ነው። ይህንን አካሄዷን ለማስቀጠል ፍላጎት እያሳየች መሆኗን አብራርተዋል።እ.አ.አ በ997 የተፈረመ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዓለም አቀፍ ስምምነት መኖሩን አመልክተው፣ የዓለም አቀፍ የልማዳዊ ህግ ደረጃ ላይ የደረሱ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች መርሆዎች አንዱና የመጀመሪያው መርህ ምክንያታዊና የፍትሐዊ ተጠቃሚነት መርህ መሆኑን ገልጸዋል። ሁለተኛው ደግሞ ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ መርህ መሆኑንም አመልክተዋል።የአባይ ተፋሰስ ሀገራት የስምምነቱ ፈራሚ ባይሆኑም በተለያዩ አህጉራት ውስጥ የሚገኙ ሀገራት ስምምነቱን መፈረማቸውን የሚያነሱት መምህር ደጀን፤ ይህ ስምምነት በዓለም አቀፍ ህግ የልማዳዊ ህግ ደረጃ ላይ የደረሱ መርሆዎችን መያዙን ያብራራሉ። አንድ መርህ የዓለም አቀፍ የልማዳዊ ህግነት ደረጃ ላይ ከደረሰ ደግሞ ሀገራት የስምምነቱ አባል ቢሆኑም ባይሆኑም ለመርሆዎቹ የመገዛት ግዴታ እንዳለባቸው አስታውቀዋል።ምክንያታዊና ፍትሐዊ የውሃ አጠቃቀም ማለት ሀገራቱ ከሚያዋጡት የውሃ ድርሻ፣ ሀገራቱ ውሃውን በመጠቀም ከሚያለሙት ልማት አንጻር፣ ተፋሰሱ የሚያርፍበት የጂኦግራፊክ ስፋት፣ የወንዙ ፍሰት በማየት፣ በወንዙ ጥገኛ የሆኑ ህዝቦች ብዛት የሚሉትን ጉዳዮችን ታሳቢ ይደረጋል። ኢትዮጵያ ለናይል ወንዝ 86 በመቶ ውሃ የምታበረክት ሀገር መሆኗን ያስታወሱት መምህር ደጀን፤ ምክንያታዊና ፍትሐዊ አጠቃቀም ከተባለ ኢትዮጵያ ውሃውን በማዋጣት የአንበሳው ድርሻ ስላላት በውሃ ተቃሚነት ላይም የአንበሳው ድርሻ ሊኖራት እንደሚገባ ገልጸዋል። ከዚያ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ካላት ህዝብ ብዛት፣ በድህነት ከሚኖረው ህዝብ ብዛት አንጻርም እንዲሁም ኢትዮጵያ ያላት አብዛኛው ውሃ የገጸ ምድር ውሃ እንደመሆኑ መጠን ኢትዮጵያ ከወንዙ ውሃ የአንበሳውን ድርሻ ልትጠቀም ይገባ እንደነበር አንስተዋል።ግብፅ ለወንዙ አንዳች ጠብታ ውሃ የማታበረክት ሆና ሳለ እ.አ.አ ግብፅ የወቅቱ የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ቅኝ ገዥ ከነበረችው እንግሊዝ ጋር በተፈራረመችው ስምምነት በአባይ ላይ የወሳኝነት ስልጣን ተሰጥቷል። ይህንን ስምምነት በመጠቀም ግብፅና ሱዳን የአባይን ውሃ ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም እና የተረፈው ውሃ በግብፅ በረሃዎች ላይ በትነት እንዲባክን እና በደቡብ ሱዳን በሚገኙ ረግረጋማ መሬቶች ላይ ጠልቆ እንዲቀር ማድረጋቸውን ያብራራሉ። እንደ መምህር ደጀን ማብራሪያ፤ ለወንዙ አብዛኛውን ውሃ የምታበረክተውን ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ምንም ሳይተው ግብፅና ሱዳን ወንዙን ለሁለት መከፋፈላቸውና የቀረውን ለትነትና ለረግረጋማ መሬት ሲሳይ እንዲሆን መተው ፍትሐዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነት የሚለውንና ጉዳት አለማድረስ የሚለውን ዓለም አቀፍ ህግ መጣስ ነው። ለላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ምንም ዓይነት ድርሻ አለመተው እና ወንዙን እንዳይጠቀሙ መከላከል ጉልህ ጉዳት ከማድረስ አልፎ ፍጹም ጉዳት ማድረስ እንደሆነም አመልክተዋል። አፍሪካዊያን በቅኝ ግዛት ዘመን በገዢዎቻቸው የተፈረሙ ስምምነቶችን በመተው ነፃ ከወጡ በኋላ በራሳቸው ጉዳይ ላይ እንደገና ተደራድረው መፈራረም እንዳለባቸው በማመን ሀገራት በጉዳዮቻቸው ላይ እንደገና እየተፈራረሙ ቢሆንም ግብፅ ግን በአባይ ወንዝ ላይ የቅኝ ግዛት ዘመን ውል እንዲተገበር እየወተወተችና ጫና እያሳደረች ነው ብለዋል። ይህ የግብፅ ፍላጎትም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሀገራት ሉዓላዊ እኩልነት የሚባለውን መርህ የሚጥስ መሆኑን አብራርተዋል።በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት የአንድ ሀገር ሉዓላዊነት ከሌላው ሉዓላዊነት አይበልጥም ያሉት መምህር ደጀን፤ ስለዚህ ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ ከኢትዮጵያ የተለየ ሉዓላዊነት ልትጠይቅበት የምትችልበት የህግ መሰረት የለም ብለዋል።እንደ መምህር ደጀን ማብራሪያ፤ ግብፅ ውሃን በብዛት የሚጠቀሙ ምርቶችን በማምረት፣ አካባቢን የሚያስተዳድሩ ዓለም አቀፍ ህጎችንም ስትጥስ ኖራለች። አሁንም እየጣሰች ነው። አግባብነት በጎደለው የውሃ አጠቃቀሟ በብዝሃ ህይወት፣ በተፋሰሱ እና በስነምህዳር ላይ ጉዳት እያደረሰች ቆይታለች። ግብፅ ዓለም አቀፍ ህጎችን በመጣስ ወንዙን እየተጠቀመች መቀጠል የለባትም ያሉት መምህር ደጀን፤ ኢትዮጵያ የላይኛውን ተፋሰስ ሀገራትን ይዛ የታችኞቹን ተፋሰስ ሀገራት በተለይም ግብፅ፣ በተፋሰሱ፣ በስነምህዳር እና በስነ ህይወት ላይ ስታደርሰው ለኖረችው ጉዳትና ኢ ፍትሐዊ አጠቃቀም በዓለም አቀፍ ተቋማት ወይም በአፍሪካ ህብረት ተጠያቂ እንድትደረግ ሊሠራ እንደሚገባም አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 13/2012መላኩ ኤሮሴ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35715
4a79e07aff0ddb9307e86ddf958f566b
921bef205ccd9288bf3c762bcb93140c
የህግን የበላይነትን ለማረጋገጥ ህብረተሰቡ ከመንግሥት ጎን መሆን እንደሚገባው ተገለጸ
አዳማ፡- የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሰላምን ለማስ ፈን ህብረተሰቡ ከመንግሥት ጎን በመሆን የሚሠራውን ሥራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንዳንድ የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።ሰሞኑን ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዳሳ ህልፈተ ህይወት ጋር ተያይዞ የተከሰተ ሁከትና ግጭት አስመልክቶ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት፣ መንግሥት የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሰላምና ደህንነትን በማስፈን ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። ህብረተሰቡ ከመንግሥት ጎን በመሆን አጥፊዎችን በማጋለጥ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ መሥራት እንዳለበትም አመልክተዋል። የከተማዋ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጌቱ ጎሳ እንደተ ናገሩት፤ መንግሥት ከዚህ በፊት ህግ በማስከበር በኩል ቸልተኝነት ያሳየ መሆኑን ጠቁመው፤ አሁን ላይ የዜጎችን ደህንነት በማስጠበቅ ሰላም እንዲሰፈን በርካታ ሥራዎች እየሠራ ነው ብለዋል። ህብረተሰቡም የህግ የበላይነትን እንዲረጋገጥ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ፤ አጥፊዎች በማጋለጥና የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ የሚሠራውን ሥራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል። በሰሞኑ በተከሰተው ጥፋት የበርካታ ዜጎች ክብር የሆነ ህይወት ማለፉና የንብረት ውድመት መከሰቱ እጅግ እንዳሳዘናቸው ገልጸው፤ አርቲስቱን በመግደልና የሰው ህይወት ማጥፋት እንዲሁም ንብረት በማውደም የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሰር መዋላቸው የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ተግባር መሆኑን አመልክተዋል።የጥፋት ኃይሎች ሰሞኑን ወጣቱ በድጋሜ ለመቀስቀስ የተለያዩ መልዕክቶችን ያስተላለፉ መሆኑን ጠቁመው፤ እነዚህ ዓይነት የሀገር ሰላም የማይፈልጉ ኃይሎች ላይ እየተወሰደ ያለ ዕርምጃ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አስታውቀዋል። ወጣቱም አሁን ላይ ለፖለቲካ መጠቀሚያ መሆኑን አውቆ በመንቃት የእነዚህን የጥፋት ኃይሎች ድርጊት መቃወም እንደሚገባው ጠቁመው፤ ሰላም ወዳዱን ህብረተሰብ ሰላም በማስጠበቅ እየሠራ ያለውን ሥራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል። ህብረተሰቡ ንብረታቸው የወደመባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መልሶ እንዲቋቋሙ በማድረግ አብሮነቱን ማሳየት እንዳለበትም ጠቁመዋል። ሌላኛው የከተማ ነዋሪ ወጣት ተስፋዬ አበራ በበኩሉ፣ የንጹሐን ህይወት እንዲጠፋና ንብረት እንዲወድምና ሰላምና መረጋጋት እንዲደፈርስ ያደረጉ የጥፋት ኃይሎች ላይ መንግሥት እየወሰደው ያለው ዕርምጃ የህግን የበላይነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ጠቁሞ፤የዜጎች ወጥቶ ለመግባት ያለባቸውን ስጋት ሊቀርፍ የሚችል በመሆኑ ህብረተሰቡ ከመንግሥት ጎን በመሆን የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አመልክቷል። የአንድ ባለሀብት ንብረት ሲቃጠል ብዙ ዜጎች ናቸው ሥራ አጥ የሚሆኑት የሚለው ወጣት ተስፋዬ፤ ጥያቄ ያለው አካል ካለ ጥያቄውን የህግ አግባብ በመከተል ማቅረብ ይኖርበታል እንጂ የፖለቲካ ቁማርተኞች መጠቀሚያ መሆን እንደሌለበት አመልክተዋል። አገር ወዳድ የሆኑ ዜጎች ሀገርን ከጥፋት ኃይሎች ነቅቶ መጠበቅ እንዳለባቸው አሳስቧል። አሁንም ውጭ ሀገር ሆነው የሀገርን ሰላም ለማደፈረስና ሰው በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ የተለያዩ የሽብርና የስጋት ወሬዎች የሚያናፍሱ ኃይሎች መኖራቸው ጠቁመው፤ መንግሥት እነዚህን አካላት ለህግ ማቅረብ እንዳለበት አመልክቷል። በሰላም እየኖረ ባለው ህዝብ መካከል ግጭትና ሁከት በመፍጠር ህዝብን ከህዝብ በማጫረስ ሀገር ለማፈረስ ሲሠራ የነበረው ሴራ ምንም እንኳን የከሽፈ ቢሆንም፤ ህብረተሰቡም ከመንግሥት ጋር በመተባበር ሰላም ለማስፈን የሚሠራውን ሥራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መክሯል። ሰሞኑን በተከሰተው አለመረጋጋት ዜጎች ህይወታ ቸውን አጥተዋል ንብረት በመውደሙ በእጅጉ ማዘናቸውን የገልጹት ወይዘሮ ሀሊማ ቃበቶ በበኩላቸው፤ መንግሥት ዕርምጃ ባይወስድ ኖረ የጥፋት ኃይሎቹ ወጣቱን መጠቀሚያ በማድረግ ትልቅ ጥፋት ያደርሱ እንደነበር ጠቁመዋል። እነዚህን የጥፍት ኃይሎች የማጋለጥ እና ለህግ የማቅረብ ኃላፊነት የህብረተሰቡም መሆን እንዳለበት አሳስበዋል። አሁንም ውጭ ሀገር ሆነው አገር ለማተራመስ ሌት ተቀን እየሠሩ ያሉ አካላት አሉ የሚሉት ወይዘሮዋ፤ ህዝቡ ደህንነቱን ተጠብቆ በሰላም ወጥቶ ሠርቶ እንዳይገባ የሽብር ወሬ በመንዛት ህዝቡን ስጋት ውስጥ የሚከትቱ አካላት ከድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸው አስታውቀዋል። መንግሥትም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ህዝብን በሚያሸብሩ የጥፋት ኃይሎች ላይ ዕርምጃ በመውስድ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል።ህዝቡም የሚናፈሱ ያልተረጋገጡ መሠረተ ቢስ ወሬዎች ከመስማት ይልቅ ከትክክለኛው ምንጫቸው የተረጋገጥ መረጃዎች መውስድ እንዳለበት ጠቁመው፤ በህዝቡ መካከል ስጋትና ሽብር የሚፈጥሩ ግለሰቦችንም ሆነ ቡድኖችን ለህግ አሳልፎ በመስጠት የበኩሉን ኃላፊነት በመወጣት የህግ የበላይነት እንዲኖር ማድረግ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 13/2012ወርቅነሽ ደምሰው
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35716
bf4785edf5d54c2bca7dd844b9312270
f0a6ebba2ff1eb47e69c617e1c3367ec
ቅሬታ የፈጠረው የሴቶችና የወንዶች እግር ኳስ ተጫዋቾች የክፍያ ወጣ ገባነት
ዛሬ ዓለም ላይ የሴቶች እግር ኳስ ተመልካችና ተደማጭነት እያገኘ መጥቷል፡፡ የሴቶችን የዓለም ዋንጫ ውድድር አንድ ቢሊዮን ተመልካቾች እንዳሉት ይጠበቃል፡፡ ከወንዶች እግር ኳስ ውድድር ጋር ሲነጻፀር የሴቶች እግር ኳስ ተጫዋቾች ክፍያና ሽልማት ግን እየጨመረ ሊመጣ አልቻለም፡፡ የአሜሪካ የሴቶች እግር ኳስ ድል ባለቤት ሆፕ ሶሎ እንደገለጸችው፤ በወንዶችና በሴቶች እግር ኳስ ቡድኖች የሚሰጠው የሽልማት ልዩነት አሁንም የወንዶች የበላይነትን አጉልቶ የሚያሳይ ነው ስትል የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን የበላይ አመራሮች ትወቅሳለች፡፡ ለአብነትም ፊፋ እኤአ በ2015 በሴቶች የዓለም እግር ኳስ ውድድር ለተሳተፉ ቡድኖች ለሽልማትና ለተሳትፎ በአጠቃላይ 30 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ሲያደርግ፤ በአንጻሩ ለወንዶች የዓለም ዋንጫ ውድድር ተሳታፊዎች ሽልማትና ማበረታቻ 400 ሚሊዮን ዶላር ወጪ አድርጓል፡፡ ይህም ከሴቶች ጋር ሲነጻፀር ከፍተኛ ልዩነት ያለው መሆኑን ታነሳለች፡፡ የሽልማት ገንዘቡም ለቡድኑ አባላት ሲከፋፈል ለእያንዳንዳቸው የሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች 800 ሺህ ዶላር ሲደርሳቸው፤ ለወንዶች ግን አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር ያገኛሉ ስትል ልዩነቱ ምን ያህል ሰፊ መሆኑን ገልጻለች፡ ፡ ይህም የሴቶችና የወንዶች እግር ኳስ ቡድኖች የሚያገኙትና የሚያመነጩት ገንዘብ ልዩነት ያለው መሆኑን ነው፡፡ ፊፋም የሴቶች እግር ኳስ ውድድር ከሌሎች ውድድሮች ገቢው ተለይቶ የሚታይ አለመሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡ ፊፋ የሚከፍለው የሽልማት ገንዘብ ለተጫዋቹ የሚሰጥ ሳይሆን ለብሄራዊ ቡድኖቹ መሆኑን ገልጿል፡፡ ስለዚህ የፋይናንስ ክፍፍሉ የፊፋ ሳይሆን የብሄራዊ ቡድኖቹ ጉዳይ ነው የሚል ሀሳብ ሰንዝሯል፡፡ እናም የእግር ኳስ ተጫዋቾቹ ተወያይተው መፍትሄ የሚሰጡት እንጂ ለህዝብ ይፋ የሚሆን አጀንዳ አይደለም ብሏል የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን፤ የአስትራሊያ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ከሚያደርገው ውድድር የሚገኘውን ገንዘብ 30 በመቶ ለተጫዋቾቹ እንደየተሳትፎኣቸው የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል፡፡ በሌላ በኩል ሌሎች ብሄራዊ የሴቶች እግር ኳስ ቡድኖች በዚህ ነጠላ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ “እንዲያም ተባለ እንዲህ ብሄራዊ የሴቶች እግር ኳስ ተጫዋቾች ለሽልማት ሆነ ለማበረታቻ የሚከፈላቸው ገንዘብ ከወንዶች እግር ኳስ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ የሴቶች እግር ኳስ ስፖርት ቡድኖች በስፖንሰርና በደመወዛቸው ላይ የተንጠለጠለ ነው›› ስትል የአሜሪካ እግር ኳስ ቡድን ታሪክ ጸሀፊ ካትሊን ሙሪይ ገልጻለች፡፡ የዓለም እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር መረጃ እንደሚያመላክተው በአሁኑ ጊዜ በምስራቅ አውሮፓ የእግር ኳስ ቡድኖች የሚጫወቱ ሴት ተጫዋቾች ወርሀዊ ክፍያ በአማካይ ከአንድ ሺህ እስከ ሁለት ሺህ ያገኛሉ፡፡ከብሄራዊ ቡድናቸው ደግሞ የቀን ዓበል ከ50 እስከ 100ዶላር ይከፈላቸዋል፡፡ምርጥ ተጫዋቾች ከፍተኛውን ክፍያ ተከፍይ ናቸው፡፡በታዳጊ አገራት የሚገኙ ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ግን በጣም አነስተኛ ክፍያ እንደሚከፈላቸው ገልጧል፡፡ በእግር ኳስ ውድድሮች ለሴቶችና ለወንዶች ተጫዋቾች ለሽልማትና ለማበረታቻ የሚከፈለው ገንዘብ ከፍተኛ ቢሆንም፤ ለሴቶች ቡድኖች የሚከፈለው ገንዘብም በዚህ ዓመት በእጥፍ መጨመሩን ካትሊን ሙሪይ ሳትጠቅስ አላለፈችም፡፡ ይህ ለሴት የእግር ኳስ ተጫዋቾች ወሳኝ የተስፋ ምዕራፍ ነውም ብላለች፡፡ የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን በበኩሉ፤ የሴት እግር ኳስ ቡድኖችን ለማበረታታት ተጨባጭ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ነው የገለጸው፤ የሽልማት ገንዘቡ አንዱ ነጠላ ጉዳይ ነው፤ ግን ፊፋ የሴቶች እግር ኳስ ቡድኖች እንዲጠናከሩና እንዲስፋፉ ሁለተናዊ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል፤ ያሉት ደግሞ በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና የሴቶች ቢሮ ሀላፊ ሳራ ባርሜን ናቸው፡፡ በቀጣይ ሶስት ዓመታትም ፊፋ ለሴቶች እግር ኳስ ውድድሮች 400 እስከ 500 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ለማድረግ ማቀዱን ይፋ አድርገዋል፡፡ ተቋሙ ባላፈው ዓመት ግን 28 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ወጪ ማድረጉን አውስተዋል፡፡ የአሜሪካ ብሄራዊ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን እኩል ክፍያ ጥያቄን በአገሪቱ ህግ መሰረት እንደሚጠይቅ አስታውቋል፡፡ የአዉስትራሊያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር በበኩሉ ደግሞ የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለወንዶችና ለሴቶች እግር ኳስ ተጫዋቾች እኩል ክፍያ ጥያቄ እንዳቀረበ አስታውቋል፡፡ የናይጀሪያ ሴት የእግር ኳስ ቡድን አባላት እኤአ በ2016 የአፍሪካ ሴቶች እግር ኳስ ዋንጫን መውሰዳቸውን ተከትሎ በሆቴላቸው ባደረጉት አመጽ ክፍያቸው በተወሰነ መልኩ ተሻሽሏል። ኒውዚላንድ እኤአ በ2018 ለሴቶችና ለወንዶች ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድኖች እኩል ከፍያና ሽልማት ገንዘብ በመክፈል በዓለም የመጀመሪያዋ አገር ለመሆን በቅታለች፡፡ እኤአ በ2020 የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሴቶችና ለወንዶች ብሄራዊ እግር ኳስ ተጫዋቾች እኩል የሽልማት ክፍያ ለመፈጸም ስምምነት መደረሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡አዲስ ዘመን ሰኔ 5/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12405
4b49ecabac24cbbc523fbb25a3efe318
cc7bda1fc9765c465d5ba8811cd6dfed
በአማራ ክልል በአንድ ቀን ከ190 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ተተከለ
አዲስ አበባ፡- በአማራ ክልል በሚገኙ አስራ አምስት ዞኖች በተደረገ የችግኝ ተከላ ዘመቻ በአንድ ጀንበር ከ190 ሚሊየን በላይ ቸግኞች መተከላቸውን የክልሉ መንግሥት ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አስታወቀ። በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው እንግዳየሁ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት፤ በአንድ ጀንበር ሊተከል ታሰቦ ከነበረው 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኞች ውስጥ ሀምሌ ዘጠኝ ቀን በተደረገው ዘመቻ ብቻ 190 ሚሊየን 734 ሺ 799 ችግኝ ተተክሏል።የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ የአረንጋዴ አሻራ ወቅት እንደመሆኑ በዓመቱ ወደ 174 ሺ ሄክታር መሬትን ለደንና ለጥምር ደን አገልግሎት በሚውሉ ችግኞች ለመሸፈን ታስቦ እንቅስቃሴ ሲደረግ መቆየቱን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ በበጋ ወቅት ሲሠራ የቆየውን የሰነ ህይወታዊ ሥራ በስነ አካላዊ ለመሸፈን በተከናወነ ተግባር በድምሩ ወደ 1 ነጥብ 68 ቢሊዮን ችግኝ የማፍላተ ሥራ መሠራቱንም ጠቁመዋል።ግንቦት 28 በተወሰነ መልኩ የተጀመረው የችግኝ ተከላ ሥራ ዝናብ በደንብ መዝነብ ሲጀመር ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸው፣ ከሁሉም የላቀው በአንድ ቀን ተከላ ከማለዳው አስራ ሁለት ሰዓት እስከ ምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ድረስ የእቅዱን 93 በመቶ ማሳካት መቻሉን አስረድተዋል። በዘመቻውም ቀን በአጠቃላይ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ መሳተፉን ገልጸው፣ በአማራ ክልል አስራ አምስቱም ዞኖች በተለይም ዝናብ በደንብ እየዘነበ በሚገኝባቸው ወረዳዎች በአጠቃላይ በአንድ ቀን ተከላ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን አስታውቀዋል።“በዘመቻው የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት የመሬት ባለቤት የሆኑት ገበሬዎች ቢሆኑም አንድም ያልታሳተፈ አካል የለም” ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ከክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር ጀምሮ ትልልቅ የሃይማኖት አባቶች፤ በየአካባቢው ያሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፤ የክልሉ ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላት፣ ተማሪዎችና አጠቃላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ መሆናቸውን አመልክተዋል። በቀጣይ በተጀመረው አግባብ የችግኝ ተከላ ሥራውን የማጠናቀቅ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፣ በበጋውም ወራት የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ሥራው ሳይቋረጥ የሚቀጥልበት ሁኔታ እንደሚኖርም ተናገረዋል። እንደ አቶ ጌታቸው ገለጻ ወቅቱ ኮሮና ወረሽኝ የተከሰተበት ወቅት እንደመሆኑ “ኮረናን እየተከላከልን ችግኝ እንተክላለን” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላው እየተከናወነ ይገኛል። በከተማም ሆነ በገጠር የሚገኝ የህብረተሰቡ ክፍል፤ አንድ ዛፍ ለመትከል የሚያስችል ቦታ ያለው ሰው እንኳን ሳይቀር በችግኝ ተከላው ይሳተፋልም ብለዋል።በክልሉ አስከአሁን ከ4 መቶ ሚሊየን በላይ ችግኝ መተከሉንም ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 13/2012አስመረት ብስራት
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35717
f5635fbf6df2afd2084f5f77f91f9325
38b1b6c715f12794fec8e2adb8be35e8
ቅርጫት ኳስ በዞን አምስት ለመወዳደር እጅ አጥሮታል
ሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ በቅርቡ ለምታዘጋጀው መላ አፍሪካ ጨዋታዎች ለመሳተፍ ኢትዮጵያ በተለያዩ ብሔራዊ ስፖርት ፌዴሬሽኖቿ አማካኝነት ዝግጅት ከጀመረች ሰንብታለች በተለይም ዓመቱን ሙሉ በመርሐግብር መሰረት የሊግ ውድድሮችን የማያደርጉና የማጣሪያ ውድድር የማያስፈልጋቸው ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ባለፈው ወር የኢትዮጵያ ቻምፒዮናን በተናጠል በማካሄድ ወደ ሞሮኮ ይዘው የሚጓዟቸውን የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች መርጠው በዝግጅት ላይ ናቸው በዓመታዊ መርሐግብር የተለያዩ ውድድሮችን የሚያካሂዱ ፌዴሬሽኖች የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችን ለመምረጥ ስለማይቸገሩ የውድድሮች ቀን ሲቃረብ ዝግጅት መጀመራቸው የተለመደ ነው ከእነዚህ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች መካከል የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን አንዱ ነው ፌዴሬሽኑ ለመላ አፍሪካ ጨዋታ ዝግጅቱን ለመጀመር የማጣሪያ ውድድር ማድረግ ይጠበቅበታል ለዚህም እቅድ አውጥቶ የሚያስፈልገውን በጀት እንዲፈቀድለት ለሚመለከታቸው የኢትዮ ጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ያቀረበው ጥያቄ እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘ የፌዴሬሽኑ የፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ይመር ሃይሌ ለአዲስ ዘመን አስታውቀዋል እንደ አቶ ይመር ገለፃ፣ የቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን የመላ አፍሪካ ጨዋታን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና ከፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ጋር ስብሰባ ባደረገበት ወቅት ስፖርቱ በአገሪቱ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገበት የሚገኝ በመሆኑ ኢትዮጵያ በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ከምትሳተፍባቸው ስፖርቶች አንዱ ሆኖ ተመርጧል በተመረጠበት ማግስትም የውድድሩ ቀን ባይደርስም የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ኮሚቴ አሰልጣኞችን መርጦ እንዲያሳውቅ በማድረግ ማስታወቂያ አውጥቶ አሰልጣኞች ተቀጥረዋል አሰልጣኞቹም ተጫዋቾች እንዲመርጡና እቅዳቸውን እንዲያቀርቡ ተደርጓል ፌዴሬሽኑ በዚህ ሂደት ውስጥ እያለ መላ አፍሪካ ጨዋታ ላይ ከመሳተፉ በፊት የአፍሪካ ዞን አምስት የቅርጫት ኳስ የማጣሪያ ውድድር መሳተፍ ስለሚኖርበት ከዞን አምስት በደብዳቤ ጥያቄ መጥቶለታል የዞን አምስት የማጣሪያ ውድድሩ ከአስር ቀናት በኋላ ተጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን በዚህ ውድድር ለመሳተፍ ፌዴሬሽኑ እቅዱን ከዞን አምስት ከመጣለት ደብዳቤ ጋር አያይዞ የሚያስፈልገውን ወጪ እንዲሸፍኑ የውድድሩ ባለቤቶች ለሆኑት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን አቅርቧል ያም ሆኖ ከሚመለከታቸው አካላት እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ እንዳላገኘና የተመረጡት አሰልጣኞችም ተጫዋቾች መልምለው ዝግጅት ለማድረግ እንዳልቻሉ አቶ ይመር ይናገራሉ የማጣሪያ ውድድሩ ሊጀመር ጥቂት ቀናት በቀሩበት በዚህ ወቅት የኦሊምፒክ ኮሚቴና የስፖርት ኮሚሽን አገርን ወክለው በማንኛውም ውድድር ላይ የሚሳተፉ ብሔራዊ ቡድኖችን ወጪ መሸፈን እንዳለባቸው አቶ ይመር ያብራራሉ ‹‹በፌዴሬሽኑ በኩል የምናደርገው ይሄ ነው፣አገራዊ ውድድሮች ላይ ስንሳተፍ ወጪውን መሸፈን ያለባቸው እነዚህ አካላት ናቸው፣ ተተኪ ወጣቶችን በስፖርቱ ለማግኘትም ሆነ አገር ለማስጠራት እንዲሁም ክለቦች የሚጠናከሩበትን መን ገድ ለመፍጠር እንደ መላ አፍሪካ አይነት ጨዋታዎች ላይ መሳተፍ አለብን፣ ካለበለዚያ ፌዴሬሽኑ መኖሩ ትርጉም የለውም›› ይላሉ ፌዴሬሽኑ ደብዳቤ አስገብቶ እስካሁን መልስ አላገኘም ማለት የሚያዘጋጃቸው ብሔራዊ ቡድኖች እንዳይወዳደሩ ማለት ነው ሲሉ ያስረዳሉ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ታምራት በቀለ በበኩላቸው፤ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች አገርን ወክለው በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ለመወዳደር በቅድሚያ የማጣሪያ ውድድሮችን በራሳቸው ማድረግ እንዳለባቸው ይናገራሉ ማጣሪያውን ማለፍ ከቻሉ ግን ሙሉ ሃላፊነቱን ኦሎምፒክ ኮሚቴና ስፖርት ኮሚሽን ይረከባሉ እነዚህ ፌዴሬሽኖች የማጣሪያ ውድድሮችን በሚያደርጉበት ወቅት አቅም ካነሳቸው ድጋፍ የሚጠይቁበት ሁኔታ መኖሩን ያመለክታሉ ከቅርጫት ኳስ ጋር በተያያዘ መላ አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ ሦስት በሦስት በሚባለው ውድድር ለመሳተፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እቅድ ውስጥ መካተቱትን ይጠቅሳሉ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን የዞን አምስት ውድድርን በተመለከተ ያነሳው ነገር እንደሌለም ይጠቁማሉ ወደ ፊት ድጋፍ የሚጠይቁ ከሆነ ግን በኮሚቴው ሥራ አስፈፃሚ በኩል የሚታይ መሆኑን ያስገነዝባሉየፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን የኮሙ ኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ናስር ለገሰ እንደሚሉት፤ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ለዓለም አቀፍ ውድድሮ በሚያደርጉት የማጣሪያ ጨዋታዎች ኦሎምፒክ ኮሚቴም ይሁን ስፖርት ኮሚሽን ወጪያቸውን ይሸፍናል ተብሎ የተቀመጠ ነገር የለም ፌዴሬሽኖች ከኮሚሽኑ የሚያገኙትን የድጎማ በጀት አብቃቅተው የሚጠቀሙበት ሁኔታ አለ እጥረት ሲገጥማቸው ግን ተጨማሪ ድጋፍ ይጠይቃሉ ጥያቄው አሳማኝና ውጤት ይመዘገብበታል ተብሎ ሲታመንም ተጨማሪ ድጎማ ይደረጋል ፌዴሬሽኖች ስፖርቱን እንዲመሩ እስከ ተቋቋሙ ድረስ በጀቱንም መምራት ይኖርባቸዋል አገርን ወክለው ሲወዳደሩ ሃላፊነቱን መውሰድ አለባቸው በሌላ በኩል ግን እግር ኳስ፣ አትሌቲክስና ሌሎችም አገርን ወክለው ሲወዳደሩ በራሳቸው በጀት ነው የሚንቀሳቀሱት ‹‹ስፖርት ኮሚሽን ሃያ ዘጠኙም ፌዴሬሽኖች ውጪ ሄደው የማጣሪያ ውድድር ሲያደርጉ ወጪ የቻልንበት አጋጣሚ የለም›› ያሉት አቶ ናስር፣ ማጣሪያውን ማለፋቸው ሲረጋገጥ ግን ከዝግጅት ጀምሮ ሙሉ ድጋፍ እንደሚ ደረግላቸው ይገልፃሉ የማጣሪያ ውድድር የማያስፈልጋቸው ነገር ግን ውጤት ይመጣባቸዋል ተብሎ የታመነባቸው እንደ አትሌቲክስ፣ ቦክስና ወርልድ ቴኳንዶ አይነት ስፖርቶች ለመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ሆቴል ገብተው ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ ኦሊምፒክ ኮሚቴና ስፖርት ኮሚሽን የማጣሪያ ውድድር ማድረግ የሚጠበቅባቸው የኳስ ስፖርቶች ማጣሪያውን ማለፋቸውን ካረጋገጡ በኋላ ወደ ሆቴል ገብተው ዝግጅት ያደርጋሉ የሚል እምነት አላቸው በጉዳዩ ላይ አንድ ወጥ የሆነ መተዳደሪያ ደንብ ባለመኖሩ ሦስቱ አካላት ማለትም ፌዴሬሽኑ፣ ኮሚቴውና ኮሚሽኑ የጋራ ስምምነት ላይ በቅርብ ቀን መድረስ ይችላሉ ማለት ከባድ ነው እነዚህ አካላት በቅርብ ቀን ተግባብተው መስራት ቢችሉ እንኳን በቅርጫት ኳስ የማጣሪያውን ጨዋታ ለማድረግ ከቀረው ቀን አንፃር የማይቻል ነው ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ከኦሊምፒክ ኮሚቴና ስፖርት ኮሚሽን የበጀት ድጋፉን በቅርብ ቀን አግኝቶ፣ አሰልጣኞች በቀሪው አስር ቀን ውስጥ ተጫዋች መልምለውና ተዘጋጅተው በማጣሪያ ውድድሩ ምን አይነት ውጤት ሊያስመዘግቡ ይችላሉ? የሚለው የስፖርት ቤተሰቡ ጥያቄ ነው የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት በመሆናቸው ጉዳዩን በቅርበት ያውቁት እንደሆነ በስልክ ለማነጋገር ብንሞክርም ሊሳካልን አለመቻሉን መግለፅ እንወዳለንአዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 8/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12517
026f9b18f1e7ba863d8790e8807310c7
7133d1185f582d813a2f72d7f3b5a1ba
የኢትዮጵያውያን ከዋክብቶች የሁለት ማይል ፍልሚያ
በመካከለኛና ረጅም ርቀት ውድድሮች ተስፋ የተጣለበት አትሌት ሰለሞን ባረጋ በስታንፎርድ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ያለፈው ዓመት ክብሩን ለማስጠበቅ በሁለት ማይል ርቀት ይወዳደራል፡፡ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚካሄደው ውድድር የዓለማችን ከዋክብት አትሌቶች የሚያደርጉት ፉክክር ከወዲሁ ትኩረት ስቧል፡፡ የ2016 የዓለም ከሃያ ዓመት በታች ቻምፒዮኑ ሰለሞን ባለፈው ዓመት ባሳየው ድንቅ ብቃት በአምስት ሺ ሜትር የዳይመንድ ሊጉ አጠቃላይ አሸናፊ ለመሆን በቅቷል፡፡ በውድድር ዓመቱ በአምስት ሺ ሜትር ያስመዘገበው12:43.02 በታሪክ አራተኛው ፈጣን ሰዓት መሆን ችሏል፡፡ ሰለሞን ካስመዘገበው ሰዓት በፊት የተመዘገቡት ሦስት ፈጣን ሰዓቶች ከዚህ ቀደም ሦስት ጊዜ የርቀቱ የዓለም ክብረወሰን ሲመዘገብ የተያዙ ሲሆን ሁለቱ ሰለሞን ከመወለዱ በፊት የተመዘገቡ ናቸው፡፡ አስራ ዘጠነኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው ሰለሞን ባለፈው የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና ላይ አምስተኛ ደረጃን ይዞ ቢያጠናቅቅም በኢትዮጵያ ቻምፒዮና ለመጀመሪያ ጊዜ በአስር ሺ ሜትር ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ በዚህኛው የውድድር ዓመትም አምስት ሺ ሜትርን የዓመቱ ፈጣን ሰዓት በሆነው 12:53.04 ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ እያሳየ የሚገኘው ድንቅ አቋም በስታንፎርድ የአሸናፊነቱን ግምት እንዲሰጠው አድርጓል፡፡ ሰለሞን ባለፈው ዓመት ባሸነፈበት የሁለት ማይል ተመሳሳይ ውድድር ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ የቻለው ኬንያዊው ፖል ቼሊሞ ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ቼሊሞ እኤአ በ2007 ማት ቲገንካምፕ ያስመዘገበውን 8:07.07 የሆነውን የሰሜን አሜሪካየርቀቱ ክብረወሰን ለማሻሻል እንደሚሮጥ ተናግሯል፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊው የባህሬን አትሌት ብርሃኑ ባለው በውድድሩ ከሚጠበቁ ኮከቦች አንዱ ሲሆን ባለፈው ዓመት ሰለሞንን በዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ያሸነፈ ብቸኛው አትሌት ነው፡፡ ሰለሞን ባረጋና ዮሚፍ ቀጄልቻ እልህ ተጋብተው በመጠላለፍና በመያያዝ በወደቁበት የዳይመንድ ሊግ አጋጣሚ ብርሃኑ አፈትልኮ ማሸነፉ አይዘነጋም፡፡ ሰለሞን ባሸነፈበት የሁለት ማይል ውድድርም ብርሃኑ ሦስተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ የ2017 የዓለም አገር አቋራጭ ቻምፒዮና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊው ኢትዮጵያዊ አትሌት አባዲ ሃዲስ በዘንድሮው የሮም ዳይመንድ ሊግ ውድድር በአምስት ሺ ሜትር 12:56.48 የሆነ የራሱ ምርጥ ሰዓት ያስመዘገበ ሲሆን በዚሁ ዓመት በግማሽ ማራቶን 58፡44 የሆነ ሰዓት ማስመዝገቡ በስታንፎርድ ዳይመንድ ሊግ ከጠንካራ አትሌቶች መካከል እንዲካተት አድርጎታል፡፡ የኦሊምፒክ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊው ሐጎስ ገብረሕይወት በሁለት ማይል ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወዳደር ሲሆን ባለፉት የሮምና የሻንጋይ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች በአምስት ሺ ሜትር ሦስተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ በዚሁ ዓመት ስቶክሆልም ላይ በአስር ሺ ሜትር ሁለተኛ ሆኖ ፈፅሟል፡፡ ሐጎስ በሁለት ማይል ውድድር ልምድ ባይኖረውም በሌሎች ርቀቶች የሚያሳየው ድንቅ ብቃት ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚያደርገው ይጠበቃል፡፡ ሌላኛው ጠንካራ አትሌት ጌታነህ ሞላ ባለፈው የዱባይ ማራቶን ለመጀመሪያ ጊዜ በርቀቱ በሮጠ አትሌት የተመዘገበውን ፈጣን ሰዓት በ2፡03፡34 አስመዝግቦ ካሸነፈ ወዲህ ወደ መካከለኛ ርቀት ተመልሶ በሁለት ማይል ውድድሩ ተፎካካሪ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 8/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12521
46ecc9af62dd60b2c7d212b1d2c316ba
be66af359400254cd5edd5c42b0a5c52
አወዛጋቢው ጨዋታ ለማክሰኞ ተላለፈ
 የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የነበረው የኢትዮጵያ ቡና እና መቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ ሳይካሄድ ከቀረ በኋላ መቼ ፣ የት እና በምን ሁኔታ ይደረግ የሚለው ጉዳይ ዕልባት ሳያገኝ መቅረቱ ይታወቃል። ፌዴሬሽኑ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ በጁፒተር ሆቴል በሰጠው መግለጫ ጨዋታው ትናንት በአዲስ አበባ ስታድየም በዝግ እንዲካሄድ ወስኖ ነበር፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ ቡና በዝግ ስታድየም የሚጫወትበት ምንም አይነት የህግ አግባብ እንደሌለ በመግለፅ ጉዳዩን እስከ ፊፋና የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት እንደሚያደርሰው አሳውቆ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትናንት ሌላ ተጨማሪ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ተገዷል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ 70 እንደርታ የሚያደርጉት ጨዋታ ወደ ማክሰኞ ተዘዋውሮ አዲስ አበባ ላይ በክፍት ስታድየም እንዲካሄድ ወስኗል፡፡ በፀጥታ ስጋት ምክንያት በተደጋጋሚ ሳይካሄድ የቆየው ይህ ጨዋታ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ በሚገኘው ፈተና ምክንያት በፀጥታ አካላት ላይ ጫና በመኖሩ ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ ጨዋታው እንዲካሄድ ፖሊስ በመጠየቁ ለማክሰኞ መዘዋወሩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ አስታውቀዋል። ፖሊስም ሆነ የእግር ኳስ ክለቦቹ ኃላፊነት የሚወስዱ መሆናቸውን በመግለፃቸው ጨዋታው ደጋፊዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታድየም እንደሚካሄድም አክለዋል ።‹‹ጨዋታው እንዲቋረጥ የተደረገው በጸጥታ አካላት መሆኑ ይታወቃል፣ ከዛም የወሰነው ውሳኔ ደንብ እና መመሪያውን የተከተለ ነው፤ በእርግጥ በአሰራር ላይ የተፈጠረ ክፍተት አለ፤እያንዳንዳችን የየራሳችን ክብር አለን ሚዲያ የቤቴ ጓዳ ጎድጓዳን ግን ገብቶ ሊያወራ አይችልም ፤ በመጀመሪያው ዙር መቐለ ላይ የተፈጠረውን አላየሁም ብሎ ሪፖርት ያደረገው ኮሚሽነር ላይ እርምጃ ባለመውሰዳችን ይቅርታ እጠይቃለሁ›› በማለት የተናገሩት አቶ ኢሳያስ፣ የኢትዮጵያ ቡና በመቐለ ስታዲየም የደረሰበት ኢ-ስፖርታዊ ድርጊት በጊዜ ውሳኔ ባለማግኘቱ ይቅርታ ከመጠየቅ ባሻገር በጥቂት ቀናት ውስጥ በመቐለ 70 እንድርታ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አብራርተዋል፡፡አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 8/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12523
b82136734e1a4fc21fda800110716c96
36e01f2ee457216bb1bef6fbb6e11393
ከፍተኛ ሊግ “ለ” መድን ወደ ፕሪምየር ሊግ የማደግ እድሉን አጨልሟል
በከፍተኛ ሊግ ምድብ “ለ” ወልቂጤን እየተከተለ ያለው መድን እና ላለመውረድ እየተጫወተ የሚገኘው ዲላ ከተማን ያገናኘው ጨዋታ በዲላ መሪነት 2-0 በዝናብ ተቋርጦ በቀጣዩ ቀን ረፋድ ቀሪው 45 ደቂቃ በመቀጠል በዲላ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ተመሳሳይ የአጨዋወትን መንገድ የተከተሉት ሁለቱም ክለቦች ረጃጅም ኳሶችን ወደ ፊት ተሰላፊዎቻቸውን በመጣል ያለመ እንቅስቃሴ ያደረጉ ሲሆን የዲላ ከተማዎች ደግሞ ይበልጥ የተሳካ ነበር። በተለይ በቀኝ በኩል ተሰልፎ ሲጫወት የነበረው ዘመድኩን ሽርኩ ከእግር ሲነሱ የነበሩት ኳሶች ለመድን ተከላካዮች ፈተና ሲሆን ተመልክተናል። መድኖች 6ኛው ደቂቃ ላይ ሳሙኤል በለጠ ከቀኝ ማዕዘን ያሻገረውን ኳስ አቤል ማርቆስ ቢያገኛትም በቀላሉ ያመከናት የመጀመሪያዋ ሙከራ ስትሆን 9ነኛው ደቂቃ አምበሉ ምስጋናው በግራ የዲላ የግብ ክልል ወደ ግብ ያሻገራት ኳስ አብዱለጢፍ ሙራድ ጋር ደርሳ ተጫዋቹ ወደ ግብ ቢመታውም ግብ ጠባቂው ዳግም ተፈራ ይዞበታል። ዳግም ኳሷን ከያዘ በኋላ በረጅሙ ሲለጋው ሀብታሙ ፍቃዱ ጋር ደርሳ ተጫዋቹ ጥሩ አቋቋም ላይ ለነበረው ዳዊት ተረፈ ሰጥቶት አማካዩ የመድን ግብ ጠባቂ ጆርጅ ደስታን አቋቋም ተመልክቶ ከሳጥን ውጪ ግሩም ግብ አስቆጥሮ ዲላን መሪ ማድረግ ችሏል። ሁለተኛ ግብ እስኪያክሉ ድረስ በይበልጥ ረጃጅም ኳስ ላይ ትኩረት ያደረጉት ዲላዎች 22ኛው ደቂቃ ተጨማሪ ጎል አስቆጥረዋል። ዘመድኩን ሺርኮ በቀኝ አቅጣጫ በረጅም ወደ መድን የግብ ክልል ያሳለፋትን ኳስ አጥቂው ኤደም ኮድዞ በደረቱ አብርዶ ሲያመቻችለት አማካዩ ፋሲል አበባየሁ ከመጀመሪያው ጋር ተመሳሳይ የሆነ ግብ አስቆጥሮ ዲላን ወደ 2-0 ከፍ ማድረግ ችሏል። ግብ ከተቆጠረባቸው በኋላ ወደ ጨዋታ ለመመለስ የተከላካይ ክፍላቸውን ወደ አማካይ ክፍሉ አማካዮቹን ወደ አጥቂዎቹ በማስጠጋት አጥቅተው ለመጫወት የሞከሩት መድኖች በርካታ አጋጣሚን እያገኙ ወደ ግብ መለወጥ አልቻሉም። 29ኛው ደቂቃ ጀሚል ያዕቆብ በረጅሙ አሻግሮ ምስጋናው በግንባር ገጭቶ ለጥቂት አግዳሚው ሙየን ነክታ የወጣችበት እና አጥቂው አብዱለጢፍ ሙራድ ከግብ ጠባቂው ዳግም ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ ዳግምን አልፎ በቀላሉ ያመከናት ለብልጫቸው ማሳያዎች ናቸው። የመጀመሪያው አጋማሽ በዲላ 2-0 ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ እረፍት ቢያመሩም ሜዳው በጎርፍ በመሞላቱና ለጨዋታ እጅጉን ምቹ ባለመሆኑ በእለቱ ዋና ዳኛ ቢኒያም ወርቅአገኘሁ እና በረዳቶቹ አማካኝነት የሁለቱም አምበሎች እና ቡድን መሪዎች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ጨዋታው ወደ ሰኔ 3 ቀን 4 ሰዓት ተቀይሮ ሁለተኛው አጋማሽ ተካሂዷል። ጨዋታው ቀሪ ደቂቃ ከመደረጉ በፊት መድኖች ሜዳው ለጨዋታ ምቹ አይደለም በሚል ቅሬታን ያቀረቡ ቢሆንም ሜዳዉ ደረቅ እስኪል ድረስ 45 ደቂቃዎችን ዘግይቶ ነበር ሊጀመር የቻለው። መድኖች በድጋሚ ጨዋታው ሊጀመር ሲል የዲላ ከተማ ቡድን መሪ አለመገኘቱን በመጥቀስ በሌላ መለወጡ አግባብ እንዳልሆነ በመግለፅ ክስ ያስመዘገቡ ሲሆን የእለቱ ኮሚሽነር ቡድን መሪው በድንገተኛ ችግር ምክንያት በደብዳቤ መለወጡን አሳውቀውናል በማለት ምላሽ ከሰጡ በኋላ በእለቱ ዳኛ ቢኒያም መሪነት ጨዋታው ተጀምሯል። ከመጀመሪያው እንቅስቃሴያቸው በተለየ በሙሉ የማጥቃት ኃይላቸው ወደ ሜዳ የገቡት መድኖች በዲላ ላይ ፍፁም የሆነ ብልጫን ወስደዋል። ዲላዎች ደግሞ አልፎ አልፎ በመልሶ ማጥቃት ከሚያደርጉት አጋጣሚዎች በስተቀር የኋላ መስመራቸውን በማስጠበቁ ተጠምደው ውለዋል። መድኖች በርካታ ጊዜያቸውን በዲላ የሜዳ ክፍል ውስጥ ባሳለፉበት ጨዋታ 49ኛው ደቂቃ ዮናታን ብርሀነ በቀኝ በኩል የላካትን ኳስ ጀሚል ያዕቆብ ቢያገኛትም በቀላሉ አምክኗታል። ሜዳው ኳስን ለማንሸራሸር ምቹ ካለመሆኑ የተነሳ ረጃጅም ኳሶች ከመመልከት ውጪ በቅብብሎሽ የሚገኙ እድሎችን መመልከት አልቻለም። በተለይ ተጫዋቾች ኳስን ሲይዙ ሜዳው አቅጣጫን ሲያስታቸው የነበረበት ሂደት ተመልካችን ያዝናናም ነበር። መድኖች 52ኛው ደቂቃ ላይ ከመሀል ሜዳ የተገኘችውን የቅጣት ምት ኪዳኔ ተስፋዬ በረጅሙ ሲያሻማ ከተከላካይነት ወደ አጥቂ ስፍራ ላይ ተስቦ ሲጫወት የነበረው ሂደር ሙስፋ በግሩም አጨራረስ አስቆጥሮ መድኖች ማንሰራራት እንዲ ችሉ አድርጓል። መድኖች አቻ ለመሆን ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ሲሆን አማካዩ ሚካኤል ለማ ከርቀት ሁለት ጊዜ አክርሮ መትቶ ግብ ጠባቂው ዳግም ተፈራ በተመሳሳይ መንገድ ያወጣበት የሚጠቀሱ አስቆጪ ሙከራዎች ናቸው። 81ኛ ደቂቃ ጀሚል ያዕቆብ በአየር ላይ በግሩም ሁኔታ ያቀበለውን ኳስ አብዱለጢፍ ሙራድ በግንባር ገጭቶ ወደ ውጪ ለጥቂት የወጣበት፣ የጨዋታው መጠናቀቂያ ጭማሪ ሰዓት ላይ በቅጣት ምት ጀሚል አሻምቶ አጥቂው አቤል ማርቆስ በግንባር ገጭቶ የግቡን ቋሚ ታካ የወጣችበትም የሚጠቀሱ ናቸው። መድኖች ምንም እንኳን የበላይነትን ቢያሳዩም በጥብቅ መከላከል ላይ ትኩረት ያደረጉት ዲላዎች ተሳክቶላቸው ጨዋታው 2-1 በባለሜዳው አሸናፊነት ተደምድሟል። ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ በመድን በኩል ድንቅ እንቅስቃሴን በማድረግ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ተከላካዩ ሂደር ሙስፋ በእንባ ከሜዳ ሲወጣ የተመለከትነው ሲሆን በርካቶችም ወደ ተጫዋቹ ተጠግተው ለክለቡ ያሳየውን ተግባር በማፅናናት በጭብጨባ አድናቆት እንደተቸረው በሶከር ኢትዮጵያ ዘግ ቧል። አዲስ ዘመን ሰኔ 9/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12570
dfa9279d22a0ba9f3908e980264f6348
1f4a39b37c5994c9447cb0dd7cd02629
የካፍ ፕሬዚዳንት እስር እና ሌሎች የአፍሪካ እግርኳስ መረጃዎች
 ባለፈው ዓመት የካፍ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ማዳጋስካራዊ አህመድ አህመድ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፓሪስ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። የፊፋ ስብስባ ለመገኘት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ወደ ፓሪስ ያመሩት ፕሬዚዳንቱ ከስብሰባው መልስ ባሪ በተባለ ሆቴል እያሉ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት። አንድ በፈረንሳይ የሚገኝ ተሰሚነት ያለው ሚድያ እንደገለፀው አህመድ አህመድን በሙስና የጠየቀው በፀረ ሙስና የሚሰራ (OCLIF) የተባለ ተቋም ሲሆን ፕሬዚዳንቱን ያስጠየቀው ጉዳይም ከጀርመኑ የትጥቅ አምራች ፑማ ጋር የፈፀሙት ውል ነው ብሏል። ውሉን ለማዋዋል የማይገባቸው 739 ሺ ይሮ ተቀብለዋል ተብለው የተጠረጠሩት ፕሬዚዳንቱ በፓሪስ ከመታሰራቸው ውጭ እስካሁንም ይፋዊ ዝርዝር ሃሳብ አልተሰጠም። በቀጣይ ቀናት በዋይዳድ ካዛብላንካ እና ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ ጉዳይ ከዋይዳድ ጋር በካስ ፍርድ ቤት ይፋጠጣል እየተባለ ያለው ካፍ ከወዲሁ በብዙ ብልሹ አሰራሮች ጋር እየተጠረጠረ ይገኛል። በካፍ ቻምፒዬንስ ሊግ ያሸነፉት ዋንጫ እና ሜዳልያ እንዲመልሱ የታዘዙት ኤስፔራንሶች የካፍን ውሳኔ በፅኑ በመቃወም ጉዳዩን ወደ ካስ እንደሚወስዱት አስታወቁ። ክለቡ በይፋዊ የትዊተር ገፁ እንደገለፀው ከሆነ በቀጣይ ቀናት አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ የተወሰነለት ውሳኔ ለማስቀየር እና መብቱን ለማስከበር ካፍን በዓለምአቀፍ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ለመገተር እንደተዘጋጀ ገልፀዋል። የፍፃሜው ጨዋታ ከአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በደቡብ አፍሪካ ለማድረግ የወሰነው ካፍ ጨዋታው በአውሮፓውያን ዳኞች እንዲመራም ውሳኔ አስተላልፏል። የቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ ላይ እንዲደገም መወሰኑ ያልተዋጠላቸው የቱኒዝያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሱፍ ቻማድ ውሳኔውን በመቃወም በቱኒዝያ ደህንነት ጥርጣሬ ገብቷቸው ጨዋታውን ገለልተኛ ሜዳ እንዲደረግ የወሰኑትን ወርፈዋል። ” የደህንነት ኃይላችን በዓለም እንደ አብነት የሚጠቀስ ነው” ብለዋል። የክለቡ ደጋፊዎችም ውሳኔው በተወሰነበት የፈረንሳይዋ ዋና ከተማ ፓሪስ ሰልፍ ማድረጋቸው ተገልጿል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ካፍ በሞሮኮ ሮያል እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፋውዚ ሌካ ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል። ፕሬዚዳንቱ ከሳምንት በፊት በተካሄደው የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ፍፃሜ ላይ የእለቱ ዳኛ በዓምላክ ተሰማ ላይ ጥቃት አድርሰዋል በሚል ነው። በዛማሌክ እና ሬነሰንስ በርካኔ መካከል የተካሄደውን ጨዋታ ዛማሌክ በመለያ ምቶች አሸንፎ ዋንጫ ማንሳቱ የሚታወስ ነው። ከሳምንታት በፊት በአፍሪካ ዋንጫ የሚዳኙ ዳኞችን የለየው ካፍ ስማቸውን ዛሬ ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያዉያኑ በዓምላክ ተሰማ (ዋና) እና ተመስገን ሳሙኤል (ረዳት) ስማቸው ከተካተቱት መካከል ናቸው። የአዳማ ከተማው ግብ ጠባቂ ሮበርት ኦዶንካራ የዩጋንዳ ዝግጅትን ዘግይቶ ተቀላቅሏል። ከሴባስቲያን ድሳብር የ27 ተጫዋቾች ስብስብ ውስጥ የተካተተው ኦዶንካራ ከቀናት በፊት ወደ አቡ ዳቢ ለዝግጅት ያመራውን ቡድን በትናንትናው ዕለት ነው የተቀላቀለው።ምንጩ ሶከር ኢትዮጵያ ነው።አዲስ ዘመን ሰኔ 9/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12573
e6045e4a33fa0a8fd6e8828e283f48c2
8076900c45493649a511aee069d0f595
ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ ሰባ እንደርታ የሚያደርጉት ጨዋታ ወደ ማክሰኞ ተዘዋወረ
  ባሳለፍነው አርብ ዕለት ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ ሰባ እንደርታ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በመጪው ማክሰኞ እንዲካሄድ ተወሰነ። በፀጥታ ስጋት ምክንያት በተደጋጋሚ ሳይካሄድ የቆየው ይህ ጨዋታ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ስታድየም ይካሄዳል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር።ሆኖም በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ በሚገኘው ፈተና ምክንያት በፀጥታ አካላት ላይ ጫና በመኖሩ ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ ጨዋታው እንዲካሄድ ፖሊስ በመጠየቁ ለማክሰኞ መዘዋወሩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ አስታውቀዋል። ፖሊስም ሆነ የእግር ኳስ ክለቦቹ ኃላፊነት የሚወስዱ መሆናቸውን በመግለፃቸው ጨዋታው ደጋፊዎች በተገኙበት ማክሰኞ በ10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታድየም ይካሄዳል።አዲስ ዘመን ሰኔ 9/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12576
601ef199e02bdce87acc5c74433ee14c
168f3fc5ee39e2b6c9cd012f823b6f06
ከስፖርት ማህደር- ቁጥሬ ዱለቻ
በርካታ አትሌቶች በመካከለኛ ርቀት ላይ በመሳተፍ ለዘመናት የዘለቀ ድል ማግኘት ባይችሉም ከ1980ዎቹ አንስታ የማይዘነጉ ድሎችን ያጣጣመች አንድ ጀግና አትሌት ግን አለች። ይህቺ አትሌት ቁጥሬ ዱለቻ ትባላለች። የመካከለኛው ርቀት ሩጫ ፈር ቀዳጇ ቁጥሬ ዱለቻ ከፌዴራል ማረሚያ ቤት ጋር ውጤታማ ጊዜን ለአምስት ዓመታት አደረገች። «ሰው የዘራውን ያጭዳል» እንደሚባለው ብሂል እርሷም ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ የምታደርጋቸው ውድድሮች ላይ ውጤታማ መሆን ጀመረች። በክለቦች ውድድር ላይ ጎልታ መውጣት ቻለች። በዚያው ዓመት በ800 ሜትር እና በ1ሺህ 500 ሜትር የመካከለኛ ርቀት የክለቦች ውድድር ላይ ሁለቱንም ወርቅ አጠለቀች። ይህ ድል ክለቧን ከማስጠራቱም በላይ ብዙዎች አይናቸውን እንዲጥሉባት አደረጋት። በዚያው ዓመት በድጋሚ የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ውድድር ሲደረግ ከላይ በጠቀስናቸው ርቀቶች ሁለት ወርቅ በማስመዝገብ የድል ጉዞዋን በአራት ወርቅ «ሀ» ብላ ጀመረች። ቁጥሬ የመጀመሪያውን ከአገር ውጭ ውድድር ያደረገችው በኬንያ ነበር። በአገር ውስጥ በ1986 ዓ.ም ድል በአደረገችበት ጊዜ በተመሳሳይ በኬንያ የ1ሺህ 500 ሜትር ርቀት ላይ አምስተኛ ወጥታ ጥሩ ልምድን ወስዳለች። ይህ ዓመት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በብዛት ያደረገችበት ነበር። በአልጄሪያ በተካሄደው የአፍሪካ ወጣቶች ሻምፒዮና ላይ በመካፈል በ1ሺህ 500 ተሳትፋ የብር ሜዳሊያን አጠለቀች። ይህ ውድድርም በፖርቹጋል ላይ በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን ወክላ እንድትሄድ እድሉን ከፈተላት። በፖርቹጋል 1ሺህ 500 ሜትር በተመሳሳይ የተወዳደረችው አትሌት ቁጥሬ የነሀስ ሜዳሊያን ለአገሯ አስመዘግባለች። በርቀቱ ፈር ቀዳጅ ከመሆኗም በላይ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በ1996 ዓ.ም በሀንጋሪ ቡዳፒስት በ1ሺህ 500 በአራት ደቂቃ 06 ሰከንድ40 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት በመሆን ታሪክ ሰርታለች። አትሌት ቁጥሬ ዱለቻን ለዓመታት በስም ብናውቃትም ያስመዘገበቻቸው ውጤቶችን በማስታወስ እንደሌሎቹ አንጋፋ አትሌቶች ስናመሰግናት ግን አይታይም። የዛሬ የአዲስ ዘመን የስፖርት ማህደር አትሌት ቁጥሬ ዱለቻን እንዲህ አስታውሷታል።አዲስ ዘመን ሰኔ 9/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12578
59158cb5cabfc2a687af805c65d7f610
abe8d756a556fe7ee904d1004bff0b34
በዳይመንድ ሊጉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባለድል ሆነዋል
በሳምንቱ መጨረሻ በሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ ርዕሰ መዲና ራባት በተካሄደው የ2019 ስድስተኛው ዙር የዳይመንድ ሊግ ውድድር በተለያዩ ርቀቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባለድል ሆነዋል። 52 ሺህ ተመልካች በሚያስናግደው የልዑል ሙላይ አብደላህ ስታዲየም በተካሄደው የ 1ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ባለድል ሆናለች። ገንዘቤ ውድሩን በቀዳሚነት ለማጠናቀቅ የወሰደባት ሰዓትም 3ደቂቃ ከ55 ሴኮንድ ከ47 ማይክሮ ሴኮንድ ሆኖ ተመዝግቧል። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና ለኔዘርላድ የምትሮጠው ሲፋን ሃሰን 3 ደቂቃ ከ55 ሴኮንድ ከ93 ማይክሮ ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ገንዘቤን በመከተል በሁለተኝነት ውድድሩን አጠናቃለች። ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች። ውድድሩን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ሰዓትም 3 ደቂቃ 57 ሴኮንድ ከ40 ማይክሮ ሴኮንድ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ይህም የሯሷን ምርጥ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦላታል። አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ከውድድሩ በኋላ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠችው አስተያየትም፤ ‹‹በአፍሪካ ምድር ባሳየሁት የምሽቱ አቋሜ በጣም ደስታ ተሰምቶኛል፤ለዓለም ሻምፒዮናውም ዝግጁ መሆኔ ይስማኛል ስትል» ተደምጣለች። አትሌት ገንዘቤ እ.አ.አ በ2015 በፈረንሳይ ሞናኮ በተካሄደ የ1 ሺህ 500 ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር 3 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ ከ8 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት በርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት መሆኗም አይዘነጋም። ገንዘቤ ባሳለፍነው ግንቦት ወር መጨረሻ በጣልያኗ መዲና ሮም በተካሄደው አራተኛው የዳይመንድ ሊግ ውድድር በ1 ሺህ 500 ሜትር 3 ደቂቃ ከ56 ሴኮንድ ከ28 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት የ2019 የርቀቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል። በ1 ሺህ 500 ሜትር ወንዶች ኬንያዊው አትሌት ቪንሰንት ኪቤት አሸናፊ ሆኖበታል። በውድድሩ ሰፊ የማሸነፍ ግምት አግኝቶ የነበረው ኢትዮጰያዊው አትሌት ታደሰ ለሚ አስረኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል። በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ወንዶች አትሌት ጌትነት ዋለ በቀዳሚነት አጠናቋል። 8ደቂቃ 06 ሴኮንድ 01 ማይክሮ ሴኮንድ ሆኗል። ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጫላ በዮ 8ደቂቃ 06 ሴኮንድ 48 ማይክሮ ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆኖ ገብቷል። ኬንያዊው ቤንጃሚን ኪገን 8ደቂቃ 07ሴኮንድ 25 ማይክሮ ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ውድድሩን ሶስተኛ በመሆን አጠናቋል። በ800 ሜትር ሴቶች በተካሄደ ውድድር ኬንያውያኑ አትሌቶች ኔሊ ጄፕኮስጌይ በቀዳሚነት አጠናቅቃለች። አትሌቷ ውድድርን ያጠናቀቀችበት ሰዓትም 1ደቂቃ ከ59 ሴኮንድ 50 ማይክሮ ሴኮንድ ሆኗል። አትዮጵያዊቷ አትሌት ሀብታም ዓለሙ1ደቂቃ ከ59 ሴኮንድ 90 ማይክሮ ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ሁለተኛ እንዲሁም ዩክሬናዊቷ አትሌት ኦልሃ ላያኮቫ2 ደቂቃ ከ00 ሴኮንድ ከ35 ማይክሮ ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ሆነው ውድድሩን አጠናቀዋል። በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች መካከል የተካሄደው ውድድርም ኬንያዊው አትሌት ኤድዋርድ ዛካዮኪ ቀዳሚ ሲሆን የገባበት ሰዓትም13ደቂቃ ከ11ሴኮንድ ከ49 ማይክሮ ሴኮንድ ሆኖ ተመዝግቧል። ኢትዮጰያዊው አትሌት ሰለሞን በሪሁ ሁለተኛ ሆኖ ሲጨርስ 13ደቂቃ ከ16ሴኮንድ ከ08 ማይክሮ ሴኮንድ ውድድሩን ያጠናቀቀበት ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል። የሞሮኮው አትሌት ሱፊያን ቦካንተር ሶስተኛ የወጣ ሲሆን ፣ 13 ደቂቃ ከ17 ሴኮንድ ከ26ማይክሮ ሴኮንድ ውድድሩን ለማጠናቀቅ የፈጀበት ሰዓት ሆኗል። በአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና ሰሜን አሜሪካ በሚገኙ 14 ከተሞች የሚካሄደው የ2019 የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለሰባተኛ ጊዜ ከአስራ ሁለት ቀናት በኋላም በአሜሪካ ኢውጂን ከተማ ይካሄዳል። ዳይመንድ ሊጉ በቀጣዩ ጳጉሜን መጀመሪያ በቤልጂየም መዲና ብራሰልስ በሚካሄደው ውድድር የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በዘንድሮው የዳይመንድ ሊግ ውድድር በአጠቃላይ የስምንት ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ሽልማት ማዘጋጀቱ ይታወሳል። በሁለቱም ጾታዎች በተመሳሳይ በ16 የተለያዩ የውድድር አይነቶች በእያንዳንዱ ርቀት የአጠቃላይ አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶች የ50 ሺህ ዶላር እና የዳይመንድ ሽልማት ያገኛሉ። ከዚህም በተጓዳኝ በዳይመንድ ሊግ ውድድሮቹ ላይ የ100 ሺህ ዶላር ሽልማትም የተዘጋጀ ሲሆን በተጨማሪም በእያንዳንዱ ርቀት አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶች ከመስከረም 17 እስከ 26 ቀን 2012 ዓ.ም በኳታር መዲና ዶሃ ለሚካሄደው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያለማጣሪያ የሚያልፉ ይሆናል።
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12694
8e4847b826e6ab54dbd2e8292c8b2906
d5452d73106cb64de636ef4537ad90bf
በእግር ኳሱ ጉዳይ የመንግሥት ዝምታ እስከ ምን ድረስ ነው?
አንዳንድ ምሁራን ፖለቲካን ‹‹መጥፎ ጨዋታ ነው›› ሲሉ ይገልፁታል፡፡ በተቃ ራኒው የስፖርቱ ዓለም ተወዳጅ መድረክ የሆነው እግር ኳስ በአፍቃሪዎቹ ዘንድ ውብና ማራኪ ጨዋታ እንደሆነ ይገለፃል፡፡ በሁለት ፅንፍ የቆሙት ሁለት መስኮች በአንድ ላይ ሲቀላቀሉ የሚፈጥሩት ውህድ ግን ከፖለቲካውም የከፋ መዘዝ እንደሚያስከትል በበርካታ አጋጣሚዎች መታዘብ ይቻላል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ እግር ኳስ በተለይም በፕሪሚየር ሊግ ተጋጣሚ ክለቦች መካከል እየተፈጠረ የሚገኘው ቀውስም የዚህ ማሳያ ነው፡፡ ሌሎቹን ጨዋታዎች ትተን ካለፉት ሁለት ሳምንታት በላይ ሲያወዛግብ የቆየው የኢትዮጵያ ቡና እና መቐለ 70 እንደርታ 27ኛ ሳምንት ጨዋታ ፖለቲካ ወደ እግር ኳስ ሰተት ብሎ መግባቱን ያረጋገጠ ነው፡፡ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በደጋፊዎች መካከል ከእግር ኳሳዊ ምክንያቶች ይልቅ ሜዳ ላይና ከሜዳ ውጪ በግልፅ በሚታይ ፖለቲካዊ ምክንያት የቱን ያህል እንደተካረረ አላየሁም አልሰማሁም የሚል ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ የሁለቱ ክለቦች ጉዳይ በማሳያነት ተነሳ እንጂ በፕሪሚየር ሊጉ ሰላሳ ጨዋታዎች የፀጥታ ስጋት የሌለባቸው ሁለት ጨዋታዎችን እንኳን መጥቀስ ከባድ እየሆነ መጥቷል። የፀጥታ ስጋቱ በእግር ኳሳዊ ምክንያት አለመሆኑ ከጨዋታ በፊትም ይሁን በኋላ ለፀጥታ አስከባሪዎች ፈተና ከመሆኑ ባሻገር የራሱን ሰንሰለት ዘርግቶ ወደ ፊትም በእግር ኳስ ሜዳዎች ዙሪያ አደጋ እንዲያንዣብብ አድርጓል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ የ2011 ዓ.ም መርሃግብር ሊቋጭና ቻምፒዮኑ ሊታወቅ የሦስት ሳምንት መርሃግብር እድሜ ብቻ ይቀረዋል፡፡ ቻምፒዮን ለመሆን ከሚደረገው ፉክክር ባሻገር ላለመውረድ የሚደረገው ትንቅንቅ በራሱ ከፍተኛ መሆኑ የፖለቲካው ትኩሳት ሳይገባበት ኳሱን እንዲፋጅ ያደርገዋል፡፡ በተቀሩት የዓመቱ መርሃግብር የመጨረሻ ጨዋታዎች በተለይም በሃያ ዘጠነኛው ሳምንት መቐለ 70 እንደርታ ከመከላከያ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ የፀጥታ ስጋት ሊኖር እንደሚችል የሰጉም ብዙዎች ናቸው፡፡ ለዚህም ጨዋታው አዲስ አበባ ስታድየም መከናወኑን ከግምት በማስገባት የመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎች ባለፈው ማክሰኞ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የነበራቸው ጨዋታ ወቅት የተፈጠሩ ግርግሮችን መነሻ አድርጎ በዚህም ጨዋታ የፀጥታ ችግር ሊኖር መቻሉ የስጋታቸው ምንጭ ነው፡፡ ሰላም በራቃቸው የስፖርት ማዘው ተሪያዎች መደበኛ የውድድር መርሐ ግብሮች መተማመኛ ማግኘት እየቻሉ አይደለም። እግር ኳሳዊ ክንውኖች በሚደረጉባቸው ሜዳዎችና የሰላም ትርጉም ለዘርፉ ያለው ፋይዳ ለብዙዎች የገባቸው በማይመስልበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንደ ብሔራዊ ተቋም በሙሉ እግሩ ረግጦ መንቀሳቀስ እየቻለ እንዳልሆነ የሚናገሩ የፌዴሬሽኑ የስራ ሃላፊዎች አሉ። መደበኛ መርሐ ግብሮች በይፋ በተነገሩ ማግሥት ‹‹ተራዘሙ›› የሚሉ ዜናዎች እግር በእግር እየተከተሉ ክለቦችን ጭምር ግራ በማጋባት ላይ ናቸው፡፡የክለብ ደጋፊዎች እነዚህን ክፍተቶች በመጠቀም ይመስላል፣ በሚፈጥሯቸው አምባጓሮች ወደ ብሔር ተኮር ግጭት እየተቀየሩና ጉዳት እስከ ማድረስ እየደረሱ የሚገኙት፡፡ እንዲህ ያለውን የሜዳ ውስጥና ከሜዳ ውጪ የሚከሰት ደም አፋሳሽ አምባጓሮ ከእንጭጩ ማስቀረት እየተቻለ አለመሆኑ ማሳያዎቹ ብዙ ናቸው። በደጋፊዎች መካከል ‹‹እኛ ጋ ስትመጡ ያገናኘን›› የሚሉ ዛቻዎችና ግጭቶች ምክንያት የቀጣዩን የጨዋታ አሸናፊ ማን ይሆን? ከሚለው የስፖርቱ ቤተሰብ የእግር ኳስ ክርክሮች ይልቅ በሚፈጠረው ረብሻ ሊመጣ የሚችለውን አደጋ በመተንበይ የሚጠመዱበት ሥርዓት ሚዛን መድፋቱ መደበኛ መርሐ ግብሮች እንዳይካሄዱ ሰበብ ሲሆን መመልከት የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ በአገሪቱ የደፈረሰው ሰላም ለስፖርቱም ዋናው እርሾ እየሆነ በመታየቱ በተለይ በክልል እግር ኳስ ክለቦች መካከል የሚከ ናወኑ ጨዋታዎች ከእግር ኳሳዊ ትንቅቁ ይልቅ የሥጋት ምንጭነታቸው አይሏል፡፡ በዚህም የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ መደበኛ ውድድሮች በተያዘላቸው ቀንና ጊዜ እንዳይከናወኑ ምክንያት ሆኗል፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የፌዴሬሽኑ የቅርብ ሰዎች እንደሚናገሩትም፣ ጉዳዩ ከተቋሙ አቅም በላይ ሆኗል፡፡በክልል የሚካሄዱ ጨዋታዎች በፖለቲካ ትኩሳት ሳቢያ ተጨማሪ ራስ ምታት እየሆኑ መምጣታቸውን በዚሁ የውድድር ዓመት ለመታዘብ ተችሏል፡፡ ለታኅሣሥ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. የታሰበው የወላይታ ድቻና የሲዳማ ቡና ጨዋታ አንዱ ማሳያ ሲሆን፣ ሌላው በዚሁ የፖለቲካ ትኩሳት በይደር የቆየው መቐለ 70 እንደርታ ከፋሲል ከተማ፣ እንዲሁም ባህር ዳር ከተማ ከስሑል ሽረ እንደስላሴና ሌሎችም ይጠቀሳሉ። ክለቦች በክልሉ በተዟዙሮ የሚያደርጉት ጨዋታ ከወጪውም አኳያ ቀድሞውንም ባይደግፉትም ፖለቲካው ባመጣው ጣጣ አንዳንዶቹ እየተዟዟሩ ለመጫወት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቆይተዋል፡፡ቀደም ሲል የወላይታ ድቻና የሲዳማ ቡና የጨዋታ መርሐ ግብር ሲወጣ አንዳችም ተቃውሞ አልነበረም፡፡ ይሁንና የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንደሚካሄድ ሲጠበቅ፣ ከሲዳማ ቡና ለፌዴሬሽኑ በተላከ ደብዳቤ ጨዋታውን ወላይታ ድቻ ላይ ሄዶ መጫወት የሚያስችል ሁኔታ ባለመኖሩ ጨዋታው እንዲራዘም ተደርጓል። የመቐለ እና የፋሲል ከተማን ጨዋታ በተመለከተም ፋሲሎች ከሜዳቸው ውጪ ለሚያደርጉት ጨዋታ ዝግጅታቸውን አጠናቀው እንደነበረ፣ ሆኖም ባህር ዳር ከተማ ላይ የሚደረገው የባህር ዳርና የስሑል ሽረ እንደስላሴ ጨዋታ ፀጥታውን የበለጠ አስተማማኝ ለማድረግ በሚል ከክልሉ የፀጥታ ኃላፊዎች ለፌዴሬሽኑ በቀረበ ጥያቄ መሠረት እንደሆነም በወቅቱ መነገሩ ይታወሳል፡፡ በዚሁ ሳቢያ የፋሲል ቡድን ወደ መቐለ የሚያደርገውን ጉዞ ለመሰረዝ መገደዱ ይታወቃል፡፡በእነዚህና በሌሎችም ተያያዥ ምክንያቶች አጣብቂኝ ውስጥ የገባው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የክልል አመራሮችን ማነጋገር የጀመረው ቀደም ሲል ጀምሮ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ያም ሆኖ ጨዋታዎች መሰረዛቸውና የፀጥታ ስጋት መኖሩ አልቀረም፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ፌዴሬሽኑ በካፍ መርሃግብር መሰረት የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ክለቦችን ለማሳወቅ እየተጣደፈ ነው፡፡ የዘንድሮው መርሃግብር እንደምንም ቢጠናቀቅ እንኳን በቀጣይ ዓመት ፕሪሚየር ሊጉ እንዲህ በአስጨናቂ ሁኔታዎች ታጅቦ ይቀጥላል? ወይስ ሌላ መላ ይበጅለታል የሚሉ ጥያቄዎች ከስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ከምንጊዜውም በላይ ተጠናክረው እየተነሱ ይገኛሉ፡፡ በእግር ኳሱ እየታየ ለሚገኘው ቀውስ የመንግስት ዝምታስ እስከምን ድረስ ነው የሚሉ ቁጥራቸው ትንሽ አይደለም፡፡ መንግስት የኳሱ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ቢገባ ከፊፋ ጋር በተያያዘ ችግሮች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ የሚያነሱ ወገኖች አሉ፡፡ ይሁን እንጂ የፊፋ ህግም ቢሆን በኳሱ ምክንያት አገር መታመስና ዜጎች መጎዳት አለባቸው ብሎ እንደማያምን ይታወቃል፡፡ ፊፋ የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ከእግር ኳሱ አመራሮች ሹም ሽረት ጋር በተያያዘ እንጂ ከፀጥታ ጋር በተያያዘ መንግስት ጣልቃ ገብቶ ለሚያሳልፈው ውሳኔ የቅጣት ብትሩን እንደማያነሳ በስፖርቱ ውስጥ ያሉ ሰዎች ይናገራሉ፡፡ ስለዚህም መንግስት በእግር ኳሱ ዙሪያ ዝምታውን መስበር እንዳለበት በአፅኖት ያስቀምጣሉ፡፡የእግር ኳሱን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ወደ ቀደመው ለመመለስ ፕሪሚየር ሊጉ ከተጀመረበት ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ.ም. አስቀድሞ በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ ወደ ሁሉም ክልሎች በመንቀሳቀስ ውይይት ያደረገው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጥረት ፍሬ ማፍራት አልቻለም፡፡ እግር ኳሱን ምክንያት በማድረግ የሚስተዋለውን አደገኛ አዝማሚያ መቀነስ የሚቻለው ውድድሮችን በዞን ማከናወን ሲቻል ብቻ እንደሆነ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች ያምናሉ፡፡ ይህ የሚስተዋለውን አምባጓሮ ከመቀነሱም በላይ ተዟዙሮ በመጫወት ይባክን የነበረውን የክለቦች ፋይናንስ ይታደጋል የሚል እምነትም አላቸው፡፡አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 15/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12982
57f41fc31df1130fa5a7888d76e3de40
251f89ff7764667782d8fe7005257607
የዓመቱ ምርጥ የአምስት ሺ ሜትር ፍልሚያ
የውድድር ዓመቱ የዳይመንድ ሊግ ፉክክሮች ሰባተኛ መዳረሻ ከተማ በሆነችው ስታንፎርድ ከሳምንት በኋላ ይቀጥላሉ፡፡ በዚህ ውድድር በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች ተፋላሚ እንደሚሆኑም ይጠበቃል፡፡ ከሁለት ሳምንት በኋላ በስዊዘርላንድ መዲና ሉዛን የዓመቱ ስምንተኛው የዳይመንድ ሊግ ፉክክር ሲካሄድ በወንዶች መካከል የሚደረገው የአምስት ሺ ሜትር ፉክክር ከወዲሁ ትኩረት ስቧል፡፡ ይህ ውድድር የዓመቱ ምርጥ የአምስት ሺ ሜትር ፍልሚያ የሚል ስያሜም ከወዲሁ ተችሮታል፡፡ይህን ውድድር ትኩረት እንዲያገኝ ያደረጉት ምክንያቶች መካከል በዋናነት ሁለቱ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጥላሁን ሃይሌና ሰለሞን ባረጋ ሲሆኑ በውድድር ዓመቱ በርቀቱ ፈጣን ሰዓት ያስመዘገቡ አምስት አትሌቶች መካተታቸው በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡በረጅም ርቀት ኢትዮጵያ ተስፋ ከጣለችባቸው አትሌቶች መካከል ግንባር ቀደም የሆነው ጥላሁን በዘንድሮው የውድድር ዓመት 5ሺ ሜትርን 12፡52፡98 በመሮጥ ስሙ በቀዳሚነት የተቀመጠ ፈጣን አትሌት ነው፡፡ ጥላሁን በሉዛኑ ውድድር ከሦስት ሳምንት በፊት ሮም ላይ በጠባብ ልዩነት ያሸነፈውን ሰለሞን ባረጋን ዳግም ይገጥማል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የ5ሺ ሜትር ውድድሮችን እየተቆጣጠረ የሚገኘው ሰለሞን ሮም ላይ 12:53.04 ሰዓት አስመዝግቦ ለጥቂት በጥላሁን መሸነፉ ይታወሳል፡፤እንግሊዛዊው ሞፋራህን ከበርካታ ዓመታት በኋላ ከ5ሺ ሜትር ንግስናው ያወረደው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሙክታር ኢድሪስ በሉዛኑ ውድድር የሚጠበቅ ሲሆን ትውልደ ኢትዮጵያዊው የባህሬን አትሌት ብርሃኑ ባለው በፉክክሩ ውስጥ ተካቷል፡፡ ሮም ዳይመንድ ሊግ ላይ ጥላሁንና ሰለሞን ተከታለው በገቡበት ፈጣን ውድድር 12:56.48 የሆነ ሰዓት ያስመዘገበው አባዲ ሃዲስ እንዲሁም የኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ባለቤቱ ኬንያዊ ፖል ቼሊሞ ፉክክሩን ከሚያደምቁ አትሌቶች መካከል ይገኙበታል፡፡አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 15/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12985
eb2121a4c33e5de4c0475fe922dce1bf
1c3c611ccc61c81dffeab8e3e4fba672
የኢትዮጵያ የስፖርት ፖሊሲ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው ተጠቆመ
የኢትዮጵያ የስፖርት ፖሊሲ ውጤታማ ባለመሆኑ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው ኢንተርናሽናል የቮሉቦል አሰልጣኞች ኢንስትራክተር አለማየሁ ሸዋታጠቅ ለአዲስ ዘመን ገለጹ።የኢትዮጵያ የስፖርት ፖሊሲ ያላፉት 21 ዓመታት ከ1990 እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ አፈጻጸሙ ውጤታማ አይደለም።በመሆኑም ፖሊሲውን መለወጥና ዳግም መፈተሽ ያስፈልጋል። ለስፖርቱ ውጤት ማሽቆልቆል፤ለእንቅስቃሴው መቀዛቀዝና መዳከም የፖሊሲው ችግር ነው ብለዋል ። የኢትዮጵያ ስፖርት አደረጃጀት በርካታ እንከኖችና ድክመቶች እንደሚታይበት ገልጸው ፤ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በብዙ ድክመቶች ታጥሮ መጓዙን ገልጸዋል። በአሠራርና በአመራር ጉድለቶች ምክንያትም የሁሉም ስፖርቶች ውጤት ሊያሽቆለቁል መቻሉን አመልክተዋል ። የኢትዮጵያ ህዝባዊ ስፖርት ምክር ቤት የኢትዮጵያ የስፖርት አዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ኃላፊነቱን ባለመወጣቱና ተግባሩም በመንግሥታዊ አካሉ በመሸፈኑ በስፖርት እንቅስቃሴዎች አርኪ የዕድገት ውጤት አልታየም። በፖሊሲ ችግር፣በስፖርት አደረጃጀት ክፍተት እና የህዝባዊ ስፖርት ምክር ቤት ሀላፊነቱን ባለመወጣቱ ምክንያት በሁሉም የስፖርት አይነቶች የረባ ውጤት ሊገኝ አልቻለም፡፡በመሆኑን ተገቢ ጥናትና ሙያዊ ምርምር በማድረግ ለችግሮቹ መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢው ኢንስትራክተር አለማየው ሸዋታጠቅ በኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን የቴክኒክ ኃላፊና የብሔራዊ ቡድኖች በወንዶችና በሴቶች ከፍተኛ ዋና አሰልጣኝነት ፣የትምህርት ሥልጠና መምሪያ ኃላፊነት ፣የኢትዮጵያ ስፖርት ፖሊሲ አርቃቂ ግብረ ሀይል ሰብሳቢነት፣ የኢትዮጵያ ስፖርት አደረጃጀት አጥኚ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ በመሆን አገልግለዋል ፡፡አዲስ  ዘመን ሰኔ 19/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13071
7fbb6acc3339aaf4b8150ef8d7652d9c
f51f3c7d98a87a1c681f77005c2aab06
በአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ሁለት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኞች ተተከሉ
 አዲስ አበባ፡- በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስጀማሪነት ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ በይፋ በተከፈተው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እስከ አሁን ሁለት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኝ መተከሉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃ እና አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ታደሰ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ በይፋ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከአሁን ሁለት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኝ ተተክሏል። በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ አምስት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኞች ተፈልተው አምስት ነጥብ አራት የችግኝ መትከያ ጉድጓዶች መቆፈራቸቸውን ያስረዱት ዳይሬክተሩ አስቀድሞ ጉድጓድ መዘጋጀቱ ተከላውን ለማፋጠን እንዳገዘና በዚህ ዓመትም የተሻለ አፈፃፀም እንደተገኘ ተናግረዋል። እስከአሁንም የዕቅዱን ከ50 በመቶ በላይ ማከናወን መቻሉን አቶ ተፈራ ገልጸው ‹‹ኮሮናን እየተከላከልን እንተክላለን›› በሚል መርሕ እየተተገበረ ያለው የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ በየቀበሌው የችግኝ ተከላ ቡድን በማቋቋም ኮሮናን ለመከላከል በሚያስችል መልኩ የአረንጓዴ አሻራ ሥራው በውጤታማነት እየተከናወነ ነው። የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ከተረጋጋ በኋላ ዘመቻው በአዲስ መልክ ተጠናክሮ መቀጠሉን ዳይሬክተሩ አስረድተው፤ በተለይም ለአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ማስታወሻ በሚል የተከሉት ችግኞች አፈጻጸሙን ከፍ እንዳደረጉት ጠቁመዋል። ‹‹በሐምሌ ወር መጨረሻ በሁሉም ቦታ ዘመቻው ይጠናቀቃል›› ያሉት አቶ ተፈራ፤ ቀድመው የሚጨርሱ አካባቢዎች ቢኖሩም የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻው እንደ አገር ሐምሌ 30 እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል፡፡ዕቅዱም መቶ በመቶ እንደሚሳካና ከመትከሉም በሻገር ‹‹ችግኝ መትከል ግብ አይደለም›› በሚል መርህም በቀጣይ ለክብካቤና ክትትል ሥራ ሰፊ ትኩረት እንደሚሰጥም ጠቁመዋል። ባለፈው ዓመት አራት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ችግኝ ተተክሎ ሦስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ችግኝም መጽደቁን አስታውሰዋል።አዲስ ዘመን ሀምሌ 14፣ 2012  በዋለልኝ አየለ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35766
d6713ca753bd47ed3ea5aaa49c0cb81e
f0f94b877edb83bd2cc9aea524db43e7
ፕሬስ አረንጓዴ አሻራውን አሳረፈ
አዲስ አበባ፡- መንግሥት ከያዘው የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ጋር በዘላቂነት ሊጣጣም በሚችል መልኩ የችግኝ ተከላ በማካሄድ የአረንጓዴ አሻራውን እያሳረፈ መሆኑን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አስታወቀ። ድርጅቱ በትናንትናው ዕለት በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የራሱን ቦታ በመረከብ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሂዷል። የድርጅቱ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወንድም ተክሉ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ ድርጅቱ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ጋር በመነጋገር በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የራሱን ቦታ ተረክቦ ትናንት ባካሄደው የችግኝ ተከላ 100 ሺህ ብር በሚጠጋ ወጪ አንድ ሺህ የሚሆኑ የሀገር በቀል ዛፎችና ፍራፍሬ ችግኞችን ተክሏል። በመርሃ ግብሩም ከ200 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞቹ ተሳትፈዋል። እንደ ምክትል ሥራ አስኪያጁ ገለፃ፤ ድርጅቱ በፓርኩ ውስጥ የራሱን ቦታ ተረክቦ ችግኞችን መትከሉ በቀጣይ ለችግኞቹ የሚያደርገውን እንክብካቤ ታሳቢ ያደረገ ነው። ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ግብ ተቀምጦለት እየተካሄደ ከመሄዱ አኳያም ድርጅቱ ለዚሁ ግብ መሳካት የራሱን አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል። ድርጅቱ ከሚሰጠው የሚዲያ አገልግሎት ጎን ለጎን የማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝም ሥራ አስኪያጁ ጠቅሰው፤ ሠራተኛው በየወሩ ከደመወዙ በማዋጣት ለኤች.አይ.ቪ ታማሚዎች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል። በተጨማሪም በኑሮ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖችም ከተቋሙ በጀት በመመደብና ሠራተኛውም እንዲያዋጣ በማድረግ እርዳታ እያደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል። ዘንድሮም ድርጅቱ የተመሰረተበትን 79ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ ፕሮግራም ማከናወኑና ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ሥራ በሀገር አቀፍ ደረጃ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ ማውጣቱን ገልፀዋል። ትናንት ያካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃግብርም የዚሁ ማህበራዊ ኃላፊነት አንዱ አካልና ሙያዊ ሥራን ከመስራት ባሻገር እጁን አስገብቶ የሰራው ሥራ መሆኑን ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል። በቀጣይም ችግኞቹን የመንከባከቡ ሥራ በድርጅቱሠራተኞች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልፀው፤ በተለይ ተደራጅተው ችግኞችን ካቀረቡና ጉድጓድ ከቆፈሩ የአካባቢው ወጣቶች ጋር እጅና ጓንት በመሆን እንደሚሰራ ተናግረዋል። የተለያዩ የፍራፍሬ ዝርያ ያላቸው ችግኞች መተከላቸው ደግሞ ቢያንስ የአካባቢውን ሰው መቀለብ የሚችልና በሰፊው አርሶ አደሩ ሲያመርት ደግሞ ወደ ውጭ ሀገር በመላክ የውጭ ምንዛሪ የሚገኝበት መሆኑንም አቶ ወንድም አስታውቀዋል። የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የፋይናንስና አስተዳደር አገልግሎት ኃላፊ አቶ ሲሳይ አስፋው በበኩላቸው እንዳሉት፤ በሀገሪቱ የአምስት ቢሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃግብርን መሠረት በማድረግ በፓርኩ ውስጥ በሁለት ምዕራፍ የተከፈለ የችግኝ ተከላ እየተካሄደ ይገኛል። በዚሁ መሠረት በርካታ መስሪያ ቤቶች ወደፓርኩ በመምጣት አረንጓዴ አሻራቸውን እያሳረፉ ይገኛሉ። እስካሁን ባለው ሂደት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ጨምሮ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን የተውጣጡ ሠራተኞች በፓርኩ ውስጥ 43 ሺህ 500 ችግኞችን መትከላቸውን ኃላፊው ገልፀው፤ በእቅድ ደረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 100 ሺህ ችግኞችን ለመትከል ፕሮግራም መያዛቸውን ጠቅሰዋል። በዚሁ መሠረት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 1 ሺህ 500 የችግኝ መትከያ ጉድጓዶች መዘጋጀታቸውንም ጠቀሰው፤ ለጊዜው በ1 ሺህ ጉድጓዶች ችግኞቹ መተከላቸውንና በቀሪዎቹ 500 ጉድጓዶች ውስጥ ደግሞ ቀሪዎቹ ችግኞቹ እንደሚተከሉባቸው ኃላፊው ጠቁመዋል። በቀጣይም የድርጅቱ ሠራተኞች ችግኞቹን የመንከባከብ ሥራቸውን እንደሚቀጥሉና ችግኙ የተተከለበት ቦታም በድርጅቱ ስም ታጥሮ እንክብካቤ እንዲያገኝ በማድረግ ፍራፍሬዎችን አምርቶ ራሱም እንዲጠቀም የአካባቢውን ነዋሪ እንዲመገብ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል። በባለፈው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 28 ሺህ ችግኞች ብቻ መተከላቸውን ያስታወሱት ኃላፊው፤ ለዘንድሮ ከተያዘው ግብ አንፃር ችግኞች በፓርኩ ውስጥ በስፋት እየተተከሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡አዲስ ዘመን ሀምሌ 14፣ 2012  በአስናቀ ፀጋዬ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35768
6706e216c2fbb63a91d26611d24e594e
8e68edbb6cdb3362bb0b8bb7555da82d
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጧል
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የወንዶች ፕሪምየር ሊግ ውድድር እንዲቋረጥ ውሳኔ አስተላልፏል። ለሊጉ መቋረጥ ምክንያት የሆነውም የፀጥታ ሥጋት መሆኑን ፌዴሬሽኑ አስታው ቋል።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪምየር ሊግ ቀሪ ጨዋታዎች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ውሳኔ አስተላልፏል። በሊጉ 27ኛ ሳምንት መካሄድ የነበረበት የኢትዮጵያ ቡና እና መቀሌ ሰባ እንደርታ ጨዋታ በፀጥታ ምክንያት አለመካሄዱ በሊጉ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ በጥልቀት በመወያየትና በመመርመር ውሳኔዎችን አሳልፏል። የመጀመሪያው ውሳኔም፤ የሊግ ኮሚቴው በ27ኛ ሳምንት በኢትዮጵያ ቡና እና መቀሌ ሰባ እንደርታ መካከል ያለው ጨዋታ ዛሬ በ29/2011 ዓ.ም እንዲካሄድ የወሰነው የጨዋታ መርሐ ግብር እንዲሻርና ጨዋታው እንዳይካሄድ የሚያደርግ ነው። ሌላኛው ውሳኔም፤ ቀጣይ የፕሪምየር ሊግ ውድድሮች በተገቢው መንገድ እንዲካሄድ ከክለቦችና ከተለያዩ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግረን እና ተወያይተን ዘላቂ መፍትሄ እስኪሰጥ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የወንዶች ፕሪምየር ሊግ እንዲቋረጥ የሚያሳስብ ነው። የተለያዩ ወጪዎችና ሌሎች ጉዳዮች በደንቡ መሰረት የሚነሱ ጥያቄዎች በፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን መመሪያ የውድድር ደንብ መሰረት እንዲታዩ ማድረግም ሌላኛው የኮሚቴው ውሳኔ ነው። ግንቦት 25/2011 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በፀጥታ ሥጋት ምክንያት መሰረዙ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎም የሊግ ኮሚቴው፤ ግንቦት 27/2011 ዓ.ም በአዳማ አበበ ቢቂላ በዝግ ስታዲየም እንዲካሄድ ወስኖ ነበር። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ቡና ክለብ በመቃወሙ እንዲሁም ከመንግሥት የፀጥታ ኃይል በደረሰ መረጃ በድጋሚ ለውጥ ተደርጓል። በዚህም ዛሬ ግንቦት 29/2011 ዓ.ም በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ያለ ተመልካች እንዲካሄድ ከውሳኔ መደረሱ ይታወሳል። በተያያዘም ለ69ኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የፊፋ ኮንግረስ ላይ ኢትዮጵያ ቀጣዩን ኮንግረስ እንድታስተናግድ ተመርጣለች። ትናንት በፓሪስ ዋና ከተማ ፓሪስ በተጀመረው የፊፋ አባል አገራት ኮንግረስ በተደረገ ውይይት 70ኛውን ኮንግረስ እንድታስተናግድ መመረጧን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። በኮንግረሱ ላይ በተካሄደው የፊፋ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫም ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በድጋሚ ተመርጠዋል። የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ተክተው እ.ኤ.አ በ2016 ወደ ሥልጣን የመጡት ኢንፋንቲኖ፤ እ.ኤ.አ እስከ 2023 ድረስ የሚቆዩም ይሆናል። በኮንግረሱ ላይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጂራ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ኮሎኔል አወል አብዱራሂም እንዲሁም የጽህፈት ቤት ኃላፊው ዶክተር እያሱ መርሐ ጽድቅ ኢትዮጵያን ወክለዋል። በፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እንዲሁም የብሔራዊ ሴቶች እግር ኳስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሶፊያ አልማሙንም ትናንት ማምሻውን ወደ ስፍራው አቅንተዋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 29/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12068
84d062b1322a8bdceaf3ee609a44a61e
ca2a50b4cff5a8c86ca3bca6e7ea7a7a
ጥቂት ስለ ግብጽ የአፍሪካ ዋንጫ
በዓለም ላይ ለእግር ኳስ ገበያ ከደቡብ አሜሪካ እና የአውሮፓ አገራት በተጨማሪ የአፍሪካ አገራትም ተመራጭ ናቸው። በርካታ አፍሪካዊያን ተጫዋቾችም ባህር አቋርጠው በአውሮፓ ሊጎች በመጫወት ላይ ይገኛሉ። ሊጎቹ ከሚቀዛቀዙባቸው አጋጣሚዎች መካከል አንዱ አህጉር አቀፍ ውድድሮች እንደመሆናቸው፤ አፍሪካ ዋንጫን የመሳሰሉ ጨዋታዎች ክለቦችን ያሳስቧቸዋል። ምክንያታቸው ደግሞ፤ ግብጻዊውን ሞሐመድ ሳላህ፣ ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ፣ አልጄሪያዊው ሪያድ ማህሬዝ፣ ጊኒያዊው ናቢ ኬታ፣ ዩጋንዳዊው ዴኒስ ኦኒያንጎ፣ ሞሮኳዋዊው አክራፍ ሃኪሚ፣ ኮትዲቯራዊው ዊልፍሬድ ዛሃ፣ ኬንያዊው ቪክቶር ዋኒያማ፣ የመሳሰሉ ቁልፍ ተጫዋቾቻቸውን ስለሚያጡ ነው። በመጪው የሰኔ ወር አጋማሽ የሚጀመረው 32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ግን ከዚህ ሥጋት ነፃ ያወጣቸው ይመስላል። በፊፋ መሪነት ከሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ጋር እንዳይጋጭ ጎዶሎ ቁጥር ባላቸው ዓመታት የሚካሄደው ይህ ውድድር፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀድሞ ይካሄድ ከነበረው ግማሽ ዓመት ወደ ክረምቱ እንዲመጣ ተደርጓል። አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ሊጎች በተጠናቀቁበት እንዲሁም ተጫዋቾች በእረፍት ላይ በሚሆኑበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ደግሞ ለአውሮፓዊያኑ ክለቦች መልካም እድል ፈጥሮላቸዋል። ወቅቱ ክለባቸውን በየትኞቹ ተጫዋቾች እንደሚያደራጁ የሚያስቡብት እንደመሆኑም ለተጫዋቾች ግዢ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይታመናል። እ.ኤ.አ በ1957 በሦስት አገራት የተጠነሰሰው የአፍሪካ ዋንጫ፤ ስድስት አስርት ዓመታትን በተሻገረ ዕድሜው ተሳታፊዎቹን በማበራከት የአሸናፊነት ፍልሚያውን ዘንድሮ በ24 ቡድኖች መካከል ያደርጋል። በውድድሩ ተሳታፊ የሆኑ አገራትም፤ ከአገር ውጭ እና በአገር ውስጥ ላሉ ተጫዋቾቻቸው ጥሪ አድርገዋል። አብዛኛዎቹም ብሔራዊ ቡድኖቻቸውን አሳውቀው በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ። የአህጉሪቷን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራው ካፍ ዘንድሮ የተሳታፊ ቡድኖቹን ቁጥር ቢጨምርም፤ የሽልማት ገንዘቡንም ከመጨመር ወደ |ላ አላለም። በዚህም መሰረት ሻምፒዮን የሚሆነው ቡድን ከዋንጫው ባሻገር 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚበረከትለት ይሆናል። ሁለተኛ ደረጃን የሚይዘው ቡድን 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር፤ ለግማሽ ፍፃሜው የሚደርሱ ቡድኖች ደግሞ 2 ሚሊዮን ዶላር ያገኛሉ። ሩብ ፍፃሜውን የሚቀላቀሉት 800 ሺ ዶላር ሲወስዱ፤ ተሳታፊዎች በበኩላቸው 600 ሺ ዶላር ይደርሳቸዋል። የእግር ኳስ ቤተሰቡም በስድስት ምድብ ተከፍለው ከሚፋለሙት ቡድኖች ስብስብ እና በገቡበት ቡድን ተመስርተው አሸናፊ ይሆናሉ የሚሏቸውን ቅድመ ግምት ከወዲሁ በማስቀመጥ ላይ ይገኛሉ። እንደ ጎል ዶት ኮም ቅድመ ግምት ከሆነም፤ አዘጋጇ ግብጽ፣ ሴኔጋል እና ናይጄሪያን በከባድ ሚዛን የሚቀመጡና ለዋንጫውም ቀዳሚ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ነው። ከዋንጫ ከራቁ ዓመታትን ያስቆጠሩት ሞሮኮ፣ ጋና እና ቱኒዝያም ዋንጫውን በማንሳት ድል ለማጣጣም በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ሲሆን፤ ደቡብ አፍሪካ እና ኮትዲቯርም ተፎካካሪ ቡድኖች እንደሚሆኑ ገምቷል። የሞሮኮን ብሔራዊ ቡድን ለሁለተኛ የአፍሪካ ዋንጫ የሚመሩት ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ሄርቬ ሬናርድ ደግሞ የዘንድሮው ዋንጫ የማንሳት ብቃት የካሜሩን መሆኑን ጠቁመዋል። ከሁለት ብሔራዊ ቡድኖች ጋር ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማንሳት የቻሉት የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ፤ ግብጽ፣ ሴኔጋል፣ ኮትዲቯር፣ ናይጄሪያ እንዲሁም ሻምፒዮኑ ካሜሩን የተሻሉ ቡድኖች መሆናቸውን ከካፍ ድረ ገጽ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልፀዋል። ከዓለም ምርጥ ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀሰው ሞ ፋራህን የያዘችው የውድድሩ አዘጋጅ ግብጽ በበርካቶች ዘንድ የአሸናፊነት ግምት አግኝታለች። ቡድኑ ካካተታቸው ተጫዋቾች ባሻገር በመድረኩ ባለው የበላይነት እንዲሁም ሀገሩ ላይ የሚጫወት መሆኑ እንደሚያግዘውም ነው የሚገመተው። መቀመጫቸውን በአውሮፓ ክለቦች ያደረጉ በርካታ ተጫዋቾችን ያቀፈው የሴኔጋል ቡድንም በአሸናፊነት ዋንጫውን የሚያነሳ እንደሚሆንም ይጠበቃል። ቡድኑ ዓለም አቀፍ እግር ኳስን በሚመራው የፊፋ አገራት ደረጃ መሰረትም የተሻለ ስፍራ ላይ ይገኛል። ባለፈው ወር በወጣው የደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት ሴኔጋል ከዓለም 23ኛ ከአፍሪካ ደግሞ ቀዳሚዋ አገር ናት። ከሴኔጋል ባሻገር ሻምፒዮኑ ካሜሩን፣ ኮትዲቯር፣ ቱኒዚያ፣ ናይጄሪያ፣ ዋንጫውን ለማንሳት የሚያስችል አቋም ላይ እንዳሉም ተጠቅሷል። ለካሜሩን የተሰጠው ይህ 32ኛው የዓለም ዋንጫ ሊካሄድ ወራት ሲቀረው በዝግጅት ማነስ ምክንያት ካፍ መንጠቁ የሚታወስ ነው። በቀሪው አጭር ጊዜም ውድድሩን ማዘጋጀት የሚችልና ፍላጎት ላላቸው አገራት በተደረገው ጥሪ፤ ደቡብ አፍሪካን በማሸነፍ ግብጽ አዘጋጅ መሆኗም ይታወቃል። በአዘጋጅነቱም ቁንጮ የሆነችው አገሪቷ የዘንድሮውን ጨምሮ ለአምስት ጊዜያት በአገሯ አፈር ውድድሩን አሰናድታለች። አዘጋጇ አገር ግብጽ በአፍሪካ ዋንጫ ከሌሎች የላቀና በድል የተንቆጠቆጠ ታሪክ ጽፋለች። በሦስት አገራት (ግብጽ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ) መካከል የተካሄደውን የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ድል ያነሳችው ግብጽ፤ በዚህ ውድድር በርካታ ዋንጫዎችን በመሰብሰብ የተሻለ ታሪክ አላት። ሰባት ዋንጫዎችን በማንሳትም ቀዳሚ ናት። እ.ኤ.አ በ1959፣ 1974፣ 1986 እና 2006 አዘጋጅ በነበረችባቸው ጊዜያትም ሦስቱን ዋንጫዎች ማስቀረት የቻለች ብቸኛዋ አገርም ናት። አዘጋጅነቱን የተነጠቀችው ካሜሩን ለአምስት ጊዜያት እንዲሁም ጋና ለአራት ጊዜያት አህጉር አቀፉን ዋንጫ በማሸነፍ ግብጽን የሚከተሉ አገራት ናቸው። በከፍተኛ ደረጃ እግር ኳስ የሚከወንባት አገር ናይጄሪያ ለሦስት ጊዜያት የዋንጫ ባለቤት ስትሆን፤ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዲሁም ኮትዲቯር ሁለት ሁለት ዋንጫዎችን ማንሳት የቻሉ አገራት ሆነዋል። በስድስት ምድብ የተከፈለው ጨዋታው በእያንዳንዱ ምድብ አራት ቡድኖችን የሚያፋልምም ይሆናል። በዚህ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ የመሆን ታሪክ ያፃፉት ሦስት አገራት፤ ማዳጋስካር፣ ብሩንዲ እንዲሁም ሞሪታኒያ ናቸው። የእነዚህ አገራት ወደ ውድድር መግባት ያልተጠበቀ ቢሆንም እስካሁን ግን ከካፍ አባል አገራት 12 የሚሆኑት በታሪካቸው በዚህ ውድድር የመሳተፍ ዕድል ቀንቷቸው አያውቅም። አዲስ ዘመን ግንቦት 29/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12070
0e778bb4358793a43ba3ad1afa08ced2
fcdbcafa1ad0d59d9309b9ff2f0aca08
«የክለቦች አሰያየም ትክክል በሆነ አካሄድ ላይ አይገኝም» አቶ ተድላ ዳኛቸው የእግር ኳስ ክለቦች ፍቃድ አሰጣጥ ማናጀር
ከቃለ ምልልሱ አስቀድሞም ስለ ማናጀሩ ጥቂት ነገር እናንሳ። አቶ ተድላ በሰውነት ማጎልመሻ መምህርነት የስራ ዓለምን የተቀላቀሉ ሲሆን፤ በመስኩ በዲግሪ ደረጃ ትምህርት መሰጠት ሲጀምር በኮተቤ መምህራን ማሰልጠኛ ገብተው በ1988ዓ.ም ዲግሪያቸውን ወስደዋል። በቀጣዩ ዓመትም በአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሲሰሩ ቆዩ፤ ከ1996ዓ.ም ጀምሮም በአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል። በዚሁ ጊዜ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ዳይሬክተር በመሆን እስከ 2007ዓ.ም ቆይተዋል። ከ2009 ዓ.ም ጀምሮም በፌዴሬሽኑ የክለቦች ህጋዊነት ፍቃድ አሰጣጥ ማናጀር ሆነው እያገለገሉ ሲሆን፤ በስፖርት ማኔጅመንት የሶስተኛ ዲግሪያቸውን ለማጠናቀቅ የመመረቂያ ጽሁፍ በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ። በመጀመሪያ ደረጃ ታሪኩን በደንብ መያዝ ያስፈልጋል፤ እንዴት ነበርን የሚለውን ለማወቅም ከጊዜ ጋር ማነጻጸር ይገባል። የዚያኔ የነበረው የእግር ኳስ እድገት ምን ይመስላል ስንል፤ በወቅቱ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ቢመስልም ከገንዘብ ጋር የተያያዘ አልነበረም። ይልቁኑ ለስፖርቱ ፍቅር፣ ለማሊያ እንዲሁም የወከሉትን አካል ለማስጠራት የሚደረግ ውድድር ነበር፤ አመራሩም በዚህ ውስጥ የተካተተ ነው። አሁን ስፖርቱ ትልቅ ኢንዱስትሪ ሆኗል፤ በመሆኑም ትክክለኛ የስፖርት አመራር ይፈልጋል። ዓለም ተቀይሯል አንድ ወደ መሆኑም ነው፤ ኢትዮጵያም በዚህ መንገድ መጓዝ ይገባታል። 86 የሚሆኑ ክለቦች አሉ፤ እነዚህ ክለቦች በፕሪሚየር ሊግ፣ ከፍተኛ ሊግ እና አንደኛ ሊግ የሚጫወቱ ናቸው። ክልሎች የሚያወዳድሯቸው ሌሎች የዲቪዚዮን ክለቦች አሉ፤ በፌዴሬሽኑ የተመዘገቡት ግን እነዚህ ናቸው። ይህ መሰረታዊ ጥያቄ ሲሆን፤ አንድ ክለብ፤ ክለብ ለመሰኘት አምስት መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅበታል። እነርሱም የመወዳደሪያ ቦታ መያዝ፣ የወጣቶች ልማት፣ የሰው ሀብት አስተዳደራዊ መዋቅር፣ የፋይናንስ ሥርዓት (የገቢ እና ወጪ ሥርዓት) እንዲሁም ህጋዊነት ናቸው። የትኛውም ክለብ የጸደቀ የልማት ፕሮግራም እንዳለው በቅድሚያ መታየት አለበት። ቀስ በቀስም የሜዳ ባለቤት መሆን ይኖርበታል፤ ካልቻለም በኮንትራት መጠቀም ይገባዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ጥራት መሰረታዊ ጉዳይ እንደመሆኑ ቢያንስ ሜዳው የተከለለ፣ መልበሻ ክፍሎችና መጸዳጃ ቤቶች ያሉት መሆን አለበት። ይህ ካልሆነ ግን ከመስፈርቱ አፈንግጧል ማለት ነው። የሰው ኃይል አደረጃጀቱ ምን ይመስላል በሚለው ስርም፤ ቋሚ ጽህፈት ቤት፣ ማናጀር፣ የክለብ ኃላፊ፣ የጸጥታ ክፍል፣ … እያለ የሚቀጥል መስፈርት ይገኛል። የክለቡ መተዳደሪያ ምንድነው፤ ወጪና ገቢውስ ምን ይመስላል የሚለውም መታየት አለበት፤ እስካሁንም በፌዴሬሽናችን ያልተሰራበት ነገር ይህ ነው። ክለቦች እንዲጠይቁም ሆነ ተጠያቂ እንዲሆኑ ህጋዊ መሆን ይገባቸዋል። እነዚህን የሚያሟላ ከሆነም አንድ ክለብ አቋሙ የተስተካከለ ነው ለማለት ያስችላል። አሁን በዚህ ላይ እየሰራን ሲሆን፤ የመጀመሪያው የፕሪሚየር ሊግ ክለቦችን ህጋዊ ማድረግ ነው፤ በቀጣይም በየደረጃው ስራው ይቀጥላል። የማያሟሉ ከሆነም ከውድድር እንዲወጡ ይደረጋል። እስከ ሰኔ 30 ድረስ ክለቦች መታየት አለባቸው። ያሉበትን ሁኔታ የማወቅ ስራውም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፤ ከ16ቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አስር የሚሆኑት ታይተው የሚቀሩት ስድስቱ ብቻ ናቸው። አሁን ክለቦቻችን በምን ላይ እንደሚገኙና ምን እንደሚመስሉ በመገምገምና በመፈተሽ ላይ እንገኛለን። የእዚህን ሪፖርትም የመጀመሪያው ውሳኔ ሰጪ አካል ይመለከተውና ሙሉ ፍቃድ ሊሰጠው፣ በገደብ ሊሰጠው አሊያም አይችልም ሊል ይችላል። ይሄ ገና በሂደት ላይ ያለ ነው፤ ነገር ግን የሚያስከፋ አይደለም። ነገ ከነገ ወዲያ ሊሻሻሉ እንደሚችሉም ማሰብ ተገቢ ነው። በአደረጃጀት በኩል ጥሩ ነገር እንዳላቸው ማየት ይቻላል፤ በሜዳ በኩል ከማዘጋጃ ቤት ጋር የተያያዘ ነገር ነው፤ በመንግስት በኩልም ጥሩ ነገር እየተሰራ ይገኛል። ይህ መስፈርት በ2006ዓ.ም ነው ከፊፋ የወረደው፤ የትኛውም የስፖርቱ ተሳታፊ የሆነ አካልም ወስዶ ተግባራዊ ያደርገዋል። ከዚህ ቀደም የክለብ ፈቃድ አሰጣጥ ውይይት ተደርጎበት የፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ ላይ እንዲካተት ተደርጓል። በእኛ በኩልም ለክለቦች መስፈርቶቹን እንዲያሟሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ቴክኒካዊ ድጋፍም እናደርጋለን በዚህም ደስተኞች ናቸው። ፍቃዱ በየሁለት ዓመቱ የሚታደስ ከመሆኑ ጋር በተያያዘም መሻሻል መኖሩ ተገምግሞ ነው የሚሰጠው። ክለቦች ምን ያህል ገንዘብ አላቸው? ለውድድር ዓመቱስ ይበቃቸዋል? የሚለው በትክክል አለመታወቁ ነው ችግር የሚፈጠረው። አንዳንድ ጥሩ ስራ የሚያከናውኑ ክለቦች አሉ፤ ነገር ግን ይህንን ጠበቅ አድርገው እና በሰነድ አጅበው የሚይዙት ጥቂቶቹ ናቸው። ይህ የሚሆነውም ክለቡን የሚመራው አካል የስፖርት ሳይንስ ባለሙያ ሲሆን ነው። ስራውን አንድን ክለብ ክለብ ለማሰኘት ብለን ሳይሆን፤ ክለቡ በዚህ አደረጃጀት ውስጥ መግባት አለበት ብለን ነው የምንሰራው። ችግሩ ገቢ ሳይኖር እንደ ላሜ ቦራ ገንዘቡን ዝም ብሎ ማፍሰሱ ነው። ስለዚህ ክለቦች የራሳቸውን ገቢ እንዲያመነጩ ማድረግ ይገባል። በእርግጥ በአንዳንድ ክለቦች ገቢ ለማመንጨት እየሞከሩ ነው፤ ነገር ግን በትክክለኛው ሰዓት ሁሉም በዚህ መካተት አለባቸው። በክለቡ፣ በተጫዋቾች በደጋፊዎች እንዲሁም በስፖርቱ ትልቅ ለውጥ ያስከትላል። በትክክል እነዚህ መስፈርቶች ቢተገበሩና በትክክለኛው የስፖርት አስተዳደር ቢመሩ ደግሞ አሁን የሚታየው የክለቦች መፍረስ እና ፖለቲካዊ ችግሩ ባልታየ ነበር። የክለቦች በመንግስት ላይ መንጠልጠል አሁን የጀመረ ባይሆንም አሁን የአመሰራረታቸው ስልት ፈር እየለቀቀ ነው። የክለቦች አሰያየም ትክክል በሆነ አካሄድ ላይ አይገኝም። እንበልና ትግራይ ፖሊስ እና ደቡብ ፖሊስ ተጫውተው አንዱ ሌላኛውን አሸነፈ ቢባል ተሸናፊው ምን ሊሰማው ይችላል? በቀደመው ጊዜ የነበሩ ለአብነት ያህል የመከላከያና የፖሊስ ክለቦች፤ መቻል፣ አየር ኃይል፣ ኦሜድላ፣… የሚል ስያሜ ነበራቸው። ይህ በወቅቱ አመራር የነበሩት አካላ – እስካሁን የውድድር ፈቃድ እንጂ የህጋዊነት ፍቃድ አልሰጠንም። ከዚህ በኋላ ወደዚያ የምንግባ ቢሆንም፤ አሁንም ትልቅ የቤት ስራ አለብን። ክለቦቻችን ምን ዓይነት ስም ይዘው ይምጡ የሚለው በጥናት ላይ በተመረኮዘ አካሄድ አንድ ነገር ላይ እንደሚደርስ ተስፋ አደርጋለሁ። እግር ኳሱ ከፖለቲካ የጸዳ መሆን አለበት፤ እግር ኳስ የሰላምና ፍቅር መድረክ እንጂ በምንም ዓይነት የድብድብ መድረክ መሆን የለበትም። ስፖርቱን የሚመራው አካልም ከዚህ የጸዳ መሆን ይገባዋል። ይህ የኢትዮጵያ እግር ኳስ እንደመሆኑ የኢትዮጵያዊነትን ስሜትን እንዳይነካ ያሉት ህጸጾች በሙሉ መጽዳት አለባቸው። እኔም አመሰግናለሁ፤ በተለይ ክለቦቻችን ምን ይመስላሉ የሚለውን በማንሳታችሁ ደስተኛ ነኝ። ት የተጠቀሙት ስልት ነው፤ የተመልካችን ስሜታዊነትም ይቀንሳል። አሁን ያለው ስያሜ ግን ስጋት ነው፤ ለፌዴሬሽኑም ትልቅ የቤት ስራ ነው። ዓለም አቀፎቹ አካላትም በብሄር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖትና በመሳሰለው የሚመሰረቱ ክለቦች ተቀባይነት የላቸውም፤ ከኦሊምፒክ መርህም ውጪ ነው። በመሆኑም የክለቦች ስያሜ ከዚህ እሳቤ የጸዳ መሆን ይገባዋል። ፌዴሬሽኑም እንዲህ ዓይነት ስሞችን የሚያስቀር ይመስለኛል። በእኛ በኩል ክለቦች ሲመሰረቱ እንዲህ ዓይነት ስሞች ባይሰጡ የሚል ግብዓት ለጽህፈት ቤቱ እንሰጣለን፤ ልክ እንደ ውጪዎቹ ክለቦች በከተማ መሰየምም ይቻላል። ከዚህ ባሻገር ያለው የጎሳ ስም በመያዝ የሚመሰረት ክለብ ትክክል አይደለም። ፌዴሬሽኑም በጥናት ላይ በተመረኮዘ አካሄድ መፍትሄ የሚሰጠው ይመስለኛል።አዲስ ዘመን ሰኔ 3/2011 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12303
462753dd9150f6a9c2a0ee752a1c7912
162946e5652e3a2f923a9c24cfbc4080
የበጋ ወራት ውድድሮች በአጓጊ ፍልሚያዎች ይጠናቀቃሉ
ባለፉት ስድስት ወራት በሠራተኛው መካከል ሲካሄድ የቆየው የበጋ ወራት ውድድር የፊታችን እሁድ ይጠናቀቃል። ከአስር በላይ በሆኑ ስፖርታዊ ውድድሮች ሠራተናውን ሲያፋልም የነበረው የስፖርት መድረክ ከሌላው ጊዜ በተለየ በአጓጊ ውድድሮች እንደሚፈፀም የኢሰማኮ የስፖርት ክፍል ሃላፊ አቶ ዮሴፍ ካሳ ተናግረዋል። በፍፃሜው ውድድሮች በተለይም በአንደኛ ዲቪዚዮን እግር ኳስ እሁድ ዕለት አሸናፊውን ለመለየት የሚካሄዱት ሁለት ጨዋታዎች በጉጉት የሚጠበቁ ናቸው። አስራ ስድስት ነጥቦችን ይዞ የደረጃ ሰንጠረዡን እየመራ የሚገኘው ኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ጥዋት 2፡30 ላይ በጎፋ ሜዳ አስር ነጥብ ካለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። በተመሳሳይ ሰዓት ኢትዮ ቴሌኮም አስራ ሦስት ነጥብ ይዞ አስራ ሁለት ነጥብ መሰብሰብ ከቻለው ሙገር ሲሚንቶ ጋር ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል። የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ጨዋታውን ማሸነፍ ከቻለ በአስራ ዘጠኝ ነጥቦች የሌሎችን ውጤት ሳይጠብቅ ቻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል። ኢትዮ ቴሌኮም ተጋጣሚውን አሸንፎ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ከተሸነፈ ሁለቱም ቡድኖች በእኩል አስራ ስድስት ነጥብ ላይ ስለሚቀመጡ ቻምፒዮኑን ለመለየት ሌላ የፍፃሜ ጨዋታ ማስፈለጉ አይቀርም። ስለዚህ የእሁዱ ጨዋታ ለሁለቱ የሠራተኛ ቡድኖች ወሳኝና በጉጉት የሚጠበቁ ሆነዋል። በሁለተኛ ዲቪዚዮን እግር ኳስ ውድድር የፍፃሜ ተፋላሚዎቹ የተለዩ ሲሆን ጠዋት 4፡30 በጎፋ ሜዳ በሚደረገው ጨዋታ ቻምፒዮኑ ይለያል። አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክና ቃሊቲ ብረታብረት ፋብሪካ የፍፃሜው ጨዋታ ተፋላሚዎች መሆናቸውን ቀደም ብለው አረጋግጠዋል። የእግር ኳስ ውድድሮች እሁድ ቢጠናቀቁም የቤት ውስጥ ውድድሮች ቀደም ብለው ቅዳሜ ዕለት በተለያዩ ሜዳዎች ይቋጫሉ። በሴቶች ቮሊቦል 8፡ 00 ላይ በሙገር ሜዳ የፍፃሜ ጨዋታ ይኖራል። በዚህ የፍፃሜ ፍልሚያም አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካን የሚገጥም ይሆናል። በተመሳሳይ ሜዳ ከሴቶቹ የፍፃሜ ጨዋታ በኋላ በወንዶች መካከል ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ከብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪከ ጋር የፍፃሜ ጨዋታ ያደርጋሉ። በጠረጴዛ ቴኒስ ሴቶች አንደኛ ዲቪዚዮን የፍፃሜ ውድድር ኢትዮ ቴሌኮም አንበሳ አውቶብስን 8፡00 ላይ በብርሃንና ሰላም ሜዳ ይገጥማል። በተመሳሳይ በወንዶችም ኢትዮ ቴሌኮም ብርሃና ሰላም ማተሚያ ድርጅትን የሚገጥም ይሆናል። በሁለተኛ ዲቪዚዮን ጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር ደግሞ አዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ከብርሃና ሰላም ማተሚያ ጋር እንደሚገጥም ታውቋል። ህብረተሰቡ በሚኖርበትና በሚሠራበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማዘውተር ጤናማ እንዲሆን የስፖርት ፖሊሲው ይደነግጋል። ሠራተኛው ማህበረሰብ በብዙ ተቋማት በሚሠራበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በስፋት ሲሳተፍ ባይስተዋልም ዓመታዊ የሠራተኞች ስፖርት ውድድሮች ላይ ሲሳተፍ ይታያል። ይህም የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) በዓመት የተለያዩ መርሐ ግብሮች የሚያከናውናቸው የተለያዩ የስፖርት መድረኮች ናቸው። ከነዚህ የኢሠማኮ የስፖርት መድረኮች ትልቅ ትኩረት የሚሰጠውም ዓመታዊው የሠራተኞች የበጋ ወራት የስፖርት ውድድር በጉልህ ተጠቃሽ ነው። የሠራተኞች የበጋ ወራት የስፖርት ውድድር በአገራችን ስፖርት ታሪክ መካሄድ ከጀመረ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረና አንጋፋ ከመሆኑ ባሻገር አገርን ወክለው የመካከለኛና ምስራቅ አፍሪካ (ሴካፋ) ዋንጫን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ መድረኮች መሳተፍ የቻሉ ስፖርተኞችን ያፈራ ስለመሆኑ ይነገራል።አዲስ ዘመን ግንቦት 29/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12065
39552206c9f0e8c4939c85a2668ea08c
93a41c39d94927a79cfaff131c81e809
ንስሮቹ አራተኛ ዋንጫቸውን ለማንሳት አነጣጥረዋል
ዘንድሮ በአዲስ መልክ 24 ብሄራዊ ቡድኖችን የሚያሳትፈው የአፍሪካ ዋንጫ ሊጀመር ከሁለት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ይቀረዋል። በጉጉት እየተጠበቀ በሚገኘው በዚህ ውድድርም ከተንታኞች፣ አሰልጣኞችና ተመልካቾች፤ ዋንጫውን ማን ያነሳል በሚል ከተሰበሰበው ቅድመ ግምት መካከል የናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን አንዱ ነው። የክለቡ አምበል ጆን ኦቢ ሚካኤልም ቡድኑ ዋንጫውን ለማንሳት ወደ ግብጽ እንደሚጓዝ ከሰሞኑ ከጎል ዶት ኮም ጋር ባደረገው ቆይታ አስታውቋል። በአፍሪካ የከፍተኛ ኢኮኖሚ ባለቤቷ ናይጄሪያ፤ በዓለም ላይ እግር ኳስ በስፋት ከሚዘወተርባቸው ሀገራት ከቀዳሚዎቹ ተርታ እንደምትሰለፍ ጥናቶች ይጠቁማሉ። «ንስሮቹ» በሚል የሚታወቀው ብሄራዊ ቡድኗም በአህጉሪቱ ጠንካራ ከሚባሉት መካከል አንዱ ነው። ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ ለሶስት ጊዜያት መንገስ የቻለ ሲሆን፤ እአአ በ1980 ናይጄሪያ ባስተናገደችው ውድድርም የመጀመሪያውን ዋንጫ በሀገሩ ማስቀረት ችሏል። ቱኒዚያ ባዘጋጀችው እአአ የ1994ቱ የአፍሪካ ዋንጫም፤ ንስሮቹ ዛምቢያን 2ለ1 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ሁለተኛ ዋንጫቸውን አንስተዋል። እአአ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይም ንስሮቹ ቡርኪና ፋሶን አንድ ለምንም በሆነ ውጤት ሶስተኛ ድላቸውን አጣጥመዋል። ከዚያ በኋላ በተካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ግን ቡድኑ ከውጤት በእጅጉ መራቁ ነበር የተስተዋለው። የቀድሞው የቼልሲ ተጫዋችና የአሁኑ የሚድልስቦሮ የአማካይ ጆን ኦቢ ሚካኤል፤ ከሩሲያው የዓለም ዋንጫ በኋላ ከብሄራዊ ቡድኑ ተለይቶ ቆይቷል። በአፍሪካ ዋንጫው ንስሮቹን የተቀላቀለው አምበሉ ለሀገሩ አራተኛውን ዋንጫ ለማስመዝገብ መነሳቱም በዘገባው ተጠቁሟል። ለዚህም የአካል ብቃት ወሳኝ መሆኑን ነው ተጫዋቹ ያስታወቀው፤ «የአካል ብቃት በውድድሩ ከፍተኛውን ድርሻ ይጫወታል፤ የጨዋታው 80 ከመቶ የሚሆነውም በአካል ብቃት እንደሚሸፈን አስባለሁ» ብሏል በአሳባ በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ። «በ2013 ዋንጫውን ስናነሳም ቡድናችን በአካል ብቃት በኩል የተሻለ እንደነበር ማስታወስ ይቻላል። ይህንንም ያመጣነው ጠንካራ ልምምድ በማድረግ ሲሆን፤ አሁንም ይህንኑ እናደርጋለን። ልምምዳችንንም በቀን ሁለት ጊዜ እንሰራለን፤ በግብጽ ዋንጫውን ለማንሳትም እንደቀደመው መስራት የግድ ነው» ሲል የቡድን አጋሮቹን አሳስቧል። በተለይ በወጣት የቡድን አባላቱ ዘንድ በሚስተዋለው ዋንጫ የማንሳት ጥማት ደስተኛ እንደሆነም ጠቁሟል። «እያንዳንዱ የቡድን አባላት በሚያደርጉት ነገር ደስተኛ ነኝ፤ ሁላችንም ለፍጻሜው ደርሰን ዋንጫውን የማንሳት ፍላጎት አለን። ማወቅ ያለብን ግን እኛ ከሁሉም የተሻልን አለመሆናችንን ነው፤ ስለዚህም ማድረግ ያለብንን እያደረግን ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይገባናል። ልምድ ትልቅ ቦታ ቢኖረውም በወጣቶች መዋቀርም ትልቅ ሚና ይጫወታል። ቡድናችንም ወጣቶችንና ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች ያቀፈ ነው» ሲልም አብራርቷል የ31ዓመቱ ተጫዋች። ናይጄሪያ በውድድሩ በምድብ ሁለት ከብሩንዲ፣ ማዳጋስካር እና ጊኒ የተደለደለች ሲሆን፤ ቡድኑ ከምድቡ የተሻለ ዕድል ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል። ቡድኑ ትናንት ከዝምቧቡዌ ብሄራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደረገ ሲሆን፤ በቀጣይም ከሴኔጋል ጋር ለመጫወት አቅዷል።አዲስ ዘመን ሰኔ 3/2011ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12306
63a8a6e8fc55df4e59d433358fc706c0
106228677f9262c6463de62749d993ef
ወሳኝና ውሳኔ ያላገኘው የሊጉ እጣ ፈንታ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2011 ዓ.ም ዋንጫ ሊጠናቀቅ የሶስት ሳምንታት ጨዋታዎች እየቀሩት የትኛው ቡድን ሻምፒየን እንደሚሆን ፍንጭ ባልሰጠበት ፉክክርም በሂሳባዊ ስኬት መሰረት ሶስት ክለቦች ፋሲል ከነማ፣ መቀሌ 70 እንደርታና ሲዳማ ቡና የተሻለ ዕድል ያላቸው መስሏል።ይሁንና በ27ኛው ሳምንት ኢትዮጵያ ቡና እና በመቀለ 70 እንደርታ መካከል በአዲስ አበባ ስቴድየም ላይ መካሄድ የነበረበት ጨዋታ ሊያካሂድ ባለመቻሉ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘሙ ምክንያት ሆኗል። ከዚህ ቀደም ከነበሩት ውድድሮች በተለየ መልኩ የሊጉን መርሃ ግብር በታቀደለት ጊዜ ያጠናቀቃል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ በአዳማው የአበበ ቢቂላ ስታድየም በዝግ ይካሄድ በሚል ቢወስንም ኢትዮጵያ ቡናዎች ግን የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ሳይቀበሉት ቀርተዋል። ጉዳዩን ወደ ለዓለም ዓቀፉ የስፖርት ግልግል ችሎት (ካስ) እንደሚወስዱት ወደ ማስታወቅም ተሻግረዋል። ይህን ተከትሎም በጉዳዩ ላይ ለመወሰን የተቸገረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ታዲያ የፕሪሚየር ሊጉ አጠቃላይ ቀሪ ጨዋታዎች ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይካሄዱ የሚል ውሳኔን ምርጫው አድርጓል። ይሁንና ፌዴሬሽኑ ውድድሩን ለማቋረጥ የወሰነበት ዋናው ምክንያት ይህ ነው ብሎ አለማሳወቁና እንዲሁ ብቻ በፀጥታ ስጋት በሚል ሰበብ ውድድሩ መቆሙ በጣም የሚያስገርምና የሚያሳዝን ሆኖም ተገኝቷል። ጉዳዩን ይበልጥ አነጋጋሪ ከማድረግ ባለፈ ፌዴሬሽኑንም ትዝብት ላይ ጥሎታል። የፌዴሬሽኑ ውሳኔ በተለይ በመሪዎቹ ክለቦች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲነሳ ምክንያት ሆኖ ታይቷል። ከዚህ በተጓዳኝ ሊጉን ማቋረጥ አግባብ ነው አይደለም የሚሉ በሁለትጎራ የተሰለፉ የስፖርት ቤተሰቦችን አስተያየትም ማስተናገድ ግድ ብሎታል። ከስፖርት ቤተሰቡ አስተያያት ሰጪዎች መካከልም፤ «ጨዋታዎቹ ላልተወሰነ ጊዜ በሚል እንዲቋረጥ የተደረገበት ሁኔታ በጣም ያሳዝናል፤ ፌዴሬሽኑ የሁለቱን ክለቦች ጨዋታ ማካሄድ ሲያቅተው አጠቃላይ የሊጉን ውድድር ላልተወሰነ ጊዜ ብሎ ማቆሙ ድክመትን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል›› የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ቁጥር ልቆ ታይቷል። በዚህ መልክ በአንድ ጨዋታ ምክንያት አጠቃላይ ፕሪሚየር ሊጉ መቋረጡ እጅጉን አሳፋሪ መሆኑን የሚገልፁ የመኖራቸው ያህል፤ በተለይ እግር ኳሱና ፖለቲካው ባልተለየበት ሁኔታ ፕሪሚየር ሊጉ ላልተወሰነ ጊዜ መቋረጡ እውነትና ትክክል ነው» የሚሉም አልጠፉም። ፌዴሬሽኑ የሊጉን ውድድር ከማቋረጥ ይልቅ ግጥሚያዎቹን በምንና በጥሩ መልኩ መምራት እንዳለበት ከሁሉም የባለድርሻ ጋር መምከር እንዳለበት የሚያስገንዝቡም ቁጥራቸው በርካታ ሆኗል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ መራዘምና የሊጉ መርሃ ግብር መቋረጥ የስፖርት ቤተሰቡን ብቻም ሳይሆን ፌደሬሽኑ ውስጥ የሚገኙ አመራሮች ሳይቀር በሁለት ጎራ ከፍሎ እያነታረከ ይገኛል። ይሁንና ከሳምንቱ መጨረሻ አንስቶ እስክ ትናንት ድረስ የተሰሙ ዜናዎች፤ የፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር እንዲጀመር መወሰኑን እያስተጋቡ ይገኛሉ። ይሁንና የሊጉ አወዳዳሪ በጉዳዩ ዙሪያ በይፋ መግለጫ አልሰጠም። ሊጉ ይቀጥላል ተባለ እንጂ መቼ የሚለው ገና አልተወሰነም። የኢትዮጵያ ቡና እና መቀሌ 70 እንደርታ ጨዋታም በዚህ ሳምንት እንደሚካሄድ በጭምጭምታ ደረጃ እንደተገኘ መረጃው ያመላከተ ሲሆን፣ ጨዋታው መቼና እንዴት ይካሄድ የሚለው ቁርጡ አልተረጋገጠም። ጨዋታው ለተመልካች ክፍት ሆኖ ወይስ በዝግ ስታዲየም ይካሄዳል የሚለውም እልባት አላገኘም። በእርግጥ የሊጉ መርሃ ግብር በይፋ ቀጣይ እጣ ፈንታ አለመታወቅ መርሐ ግብሩን ለማሟላት ብቻ ለሚጫወቱ ክለቦች ፋይዳው እዚህ ግባ ላይባል ይችላል። ይሁንና ለሊጉ ዋንጫ ክብር የሚጫወቱ ክለቦች ላይ የሚያሳድረው ጫና ነጋሪ አያሻውም። ከተጨማሪ የፋይናስ ወጪ አንስቶ በተለይ በመሪነቱ ቦታ ለዋንጫ በሚፋለሙ ክለቦች የአሸናፊነት ስነልቦና ላይ የሚያሳድረው ጫና መዘንጋት አይኖርበት። ከዚህ ባለፈ እንደ ባለፈው የውድድር ዓመት ሊጉ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ መጠናቀቅ አልሆንልህ ብሎት፤ ጨዋታዎች በክረምት ወራት በዶፍ ዝናብ፣ ጭቃና ውሃ ባዘለ ሜዳ መካሄዳቸውና ተጫዋቾች ሜዳ ገብተው ሲንቦራጨቁ መመልክታችን አይቀሬ ነው። በመሆኑም ወሳኝና ውሳኔ ያላገኘው የሊጉ እጣ ፈንታ አስታዋሽ ይፈልጋል፡፡አዲስ ዘመን ሰኔ 4/2011 ታምራት ተስፋዬ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12356
de709ab5abed4cc189fafbdaaa1d53fa
0aeaf80cc81ed713803cef9b31141877
በአስመራ ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ሁለተኛ ወጣ
በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ በተካሄደ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ታደሰ አሰፋ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ። ከምስራቅ አፍሪካ የተወጣጡ አትሌቶች፤ የተካፈሉበት የማራቶን ውድድር ባሳልፍነው እሁድ አስመራ ጎዳና ላይ ተካሂዷል። ከኤርትራ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኬንያ፣ ከኡጋንዳ፣ ከደቡብ ሱዳንና ከታንዛኒያ የተወጣጡ አትሌቶች በተሳተፉበት ውድድርም አዘጋጇ ኤርትራ ቀዳሚ ሆና አጠናቃለች። አትሌት መሃሪ ፀጋዬ ውድድሩን በቀዳሚነት ሲጨርስ፤ ኢትዮጵያዊው አትሌት ታደሰ አሰፋ በሁለተኛነት ውድድሩን አጠናቆል። ሌላኛው ኤርትራዊ አትሌት ፔትሮ ማሞ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ገብቷል። አትሌት ታደሰም ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ በኤርትራ ምድር በተካሄደ ማራቶን በመሳተፍና ባለድል በመሆን ታሪክ መፃፍ ችሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በመወከል ወደ ስፍራው ያቀኑት አሰልጣኝ ታደለች ቢራ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለዓመታት የዘለቀው ቁርሾ በተወገደበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት ውድድሩን በመታደማቸው ልዩ ደስታን እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል። አሸናፊዎቹ አትሌቶችም እንደየቅደም ተከተላቸው፤ ከስድስት ሺህ፣ አራት ሺህ እና ሶስት ሺህ ዶላር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የባህልና ስፖርት ኮሚሽነሩ አምባሳደር ዘመዴ ተካም ለአትሌቶቹ የተዘጋጀውን ሽልማት በስፍራው ተገኝተው አብርክተዋል። ከማራቶን ውድድሩ በተጓዳኝ 20 ሺህ ተወዳዳሪዎች የተሳተፉበት የጎዳና ላይ ሩጫም ተካሂዷል። ዘገባው የኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ነው።አዲስ ዘመን ሰኔ 4/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12359
5e8cd4db1e330752f23c38d724efdae9
9d7876a23ffd6a9a936c8000f43a3d71
የኳስ ጠቢቡ በአዲስ ቤት ለሌላ ታሪክ
በእግር ኳሱ መንደር የፍልሚያ ሜዳ ሲታይ ቁመቱ አጭር ግን ጠንካራ፣ መሮጥ የማይታክተው፤ ፈጣንና ጉልበታም ተጫዋች ነው። ተመልካች አድናቂዎቹም«እርሱ የምርጥነት ምልክት፤ አንድ ለሻምፒዮናነት የሚጫወት ክለብ ሊኖረው የሚገባውም ወሳኝ ተጫዋች ነው »ሲሉም ስለችሎታው ይመስክሩለታል። ሙሉ ስሙ ኤዲን ሃዛርድ ይባላል። እኤአ 1991 የተወለደው ይህ ቤልጄየማዊ በጥበበኛ እግሩቹ ብቻም ሳይሆን በፀባዩም ይታወቃል። የዓለማችን እግር ኳስ ሶስተኛው ኮከብ ብለው የሚጠሩትም በርካታ ናቸው። አመለ ሸጋው ተጫዋች በእግር ኳሱ የፍልሚያ ሜዳ ከዳኛ ከተጫዋችና ደጋፊ ጋር በመነጫነጭና በእሰጣ አገባ ጊዜውን አያጠፋም። ትኩረቱ ሁሉ ኳሱና ኳሱ ላይ ብቻ ነው። ስራውን በሚገባ የሚያውቅ ታታሪ ሰራተኛ፤ በሽንፈትና በአቻ ውጤት ወቅት ደጋፊውን ከማክበሩ የተነሳ ቀና ብሎ ለማየት የማይደፍር ሽንፈት ውስጡ ድረስ ዘልቆ የሚሰማው መሆኑ ይነገርለታል። ከስነምግባሩ ባሻገር ስለድንቅ የአግር ኳስ ጥበብ ክህሎቱ ተናግረው፣ የማይጠግቡም፤ የእርሱ በሜዳ ላይ መገኘት ብቻውን የአንድን ጨዋታ ውጤት ይወስናል፤ 90 ደቂቃ እርሱን ሜዳ ውስጥ መመልከት ብቻውን ደስታን ያጭራል ሲሉ ያሞካሹታል። በሁለት እግሩ ከሚጫወት ኤዲን ሃዛርድ ጋር የቡድን አጋሩ ከመሆን በተሻለ እርሱን በተቃራኒ መለያ መግጠም እጅግ አድካሚና ፈታኝ እንደሆነም ያምናሉ። በተክለሰውነት፣ በአካል ብቃትና በቴክኒክ ተሰጥኦ የታደለው ኤደን ሀዛርድ የእግር ኳስ ህይወት ይበልጥ ያማረና ወደ ከፍታው ማማ የተንደረደረው ከፈረንሳይ ነው። በተለይ በ2011/12 የውድድር ዓመት የፈረንሳይ ሊግ አንድ የሊል 20 ግቦችን በማስቆጠር16 ግቦችን ለቡድን አጋሮቹ ማቀበል የቻለ ሲሆን፤ የውድድር ዓመቱ ምርጥ ተጫዋችነት ክብርንም ተጎናጽፏል። ተጫዋቹ በፈረንሳይ ቆይታ በተለያዩ የአውሮፓ ሃያል ክለቦች አይን ውስጥ መግባት የቻለ ሲሆን ከሁሉ ቀድመው የግላቸው ማድረግ የቻሉት ግን ቼልሲዎች ናቸው። እኤአ በ2012 ሰማያዊዎቹን ሲቀላቀልም በወቅቱ ከለቡን የተቀላቀለበት የዝውውር ዋጋ 32 ሚሊየን ፓውንድ ሆኖም ተምዝግቧል። ሃዛርድ የቼልሲዎችን ስብስብ ከተቀላቀለ ወዲህም በተለይ ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒዮም እኤአ በ2013 ስታንፎርድ ብሪጅ መድረሳቸውን ተከትሎ ይበልጥ ብቃቱን ማስመስከር ችሏል። ጆዜ ይከተሉት ለነበረው የ 4-2-3-1 የጨዋታ ፍልስፍና ይበልጥ ምቹ በመሆን የክለቡን የመልሶ ማጥቃት በማቀላጠፍ ስሙ ቀድሞ የሚነሳ ተጫዋች ለመሆን አልተቸገረም። በዚህ ብቃቱም ሰማያዊዎቹ በፕሪሚየር ሊጉ ዳግም እንዲያንሰራሩና በተከታታይ ድልና ወጥ በሆነ አቋም የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሱ የእርሱ ተሳትፎና ሚና ከማንም ተጫዋች ገዝፎ ታይቷል። በቼልሲ ቤት ቆይታው ብዙዎች ስለ ችሎታው እንዲመሰክሩና ከመቀመጫቸው ተነስተው እንዲያጨበጭቡ ያስገደደው ሃዛርድ፤ በጣሊያናዊው አስልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ እንዲሁም በማውሪዚዮ ሳሪ ጨዋታ ፍልስፍናም ከቋሚና ቀዳሚ ተመራጭ ተጫዋቾች እንጂ ተቀያሪ አልነበረም። በቼለሲዎች ቤት ላለፉት ሰባት ዓመታት የቆየው ሃዛርድ በየዓመቱ ድንቅ ብቃቱን እያስመሰከረና በብሪጅ ተመልካቾች ዘንድም ተወዳጅነቱን በማስጠበቅ የሰማያዊዎቹ ጥንካሬ ሚስጥር መሆን የቻለ ሲሆን፤ በተለይ ባሳልፍነው የውድድር ዓመት የ28 ዓመቱ ቤልጄማዊ ጥበበኛ በማውሪዚዮ ሳሪ ስር 16 ግቦችን አስቆጥሮ 15 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ አቀብሏል፡፡ በምዕራብ ለንደኑ ክለብ የነገሰው ሃዛርድ በሚያሳየው ድንቅ ብቃት የፕሪሚየር ሊጉ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋችነት ክብርም ከመቋደስ ባለፈ፤ የባሎንዶር እንዲሁም የፊፋ ቤስት አዋርድ እጩ ውስጥ በተደጋጋሚ በእጩነት ስሙን አሰጥርቷል። ከዚህም ባለፈ ተጫዋቹን የግል ማድረግ የሚፈልጉ የዓለማችን ታላላቅ ክለባት ቁጥርም እንዲያይልም አድርጓል። በተለይ የስፔኑ ሃያል ክለብ ለተጫዋቹ የነበረው ፍቅር ከሁሉ ልቆ ታይቷል። ስሙ ከሎስ ብላንኮዎቹ ጋር የተዛመደው ሃዛርድ ከሰማያዊዎቹ ጋር የአንድ ዓመት ኮንትራት ቢቀረውም፤ በስታንፎርድ ብሪጅ ቆይታው ግን ከሚቀጥለው የውድድር ዓመት በኋላ እንደማይቀጥል በተደጋጋሚ ሲገለፅም ቆይቷል። ቼልሲዎቹ አርሰናልን በማሸነፍ የዘንድሮውን የአውሮፓ ሊግ ዋንጫ ባነሱበት ምሽት ሁለት ግቦችን ያስቆጠረው ሃዛርድ፤«የስንብቴ የመጨረሻ ቀን ይመስለኛል፤ በፕሪሚዬር ሊግ የመጫወት ህልም ነበረኝ፥ ላለፉት ሰባት ዓመታትም በአውሮፓ ታላቅ ከሆነው ቼልሲ ጋር ይህን አሳክቻለሁ፤ አሁን ሌላ አዲስ ፈተና በሌላ ሊግ ለመሞከር ተዘጋጅቻለሁ»ሲል ተደምጧል። ተጫዋቹ ከቼልሲ ለመልቀቅ ወስኖ ከሆነ ማረፊያው ሪያል ማድሪድ እንደሚሆን በተገመተው መሰረትም ባሳለፍነው ሳምንት ተጫዋቹ ሎስ ብናኮዎቹን በይፋ በመቀላቀል ሌላ ደማቅ ታሪክ ለመፃፍ ወደ ስፔን አቅንቷል። ከዊጋን ጋር የመጀመሪያ የሰማያዊ ማለያውን ጨዋታ ያደረገ ሲሆን፤ የመጨረሻ ጨዋታውም አርሰናል ሆኗል። የምእራብ ለንደኑ ክለብም የብዙዎች ዓይን ያረፈበትን እንቁ ልጃቸውን አሳልፈው ለመስጠትም ብዙ ቢማገቱም፤ በመጨረሻ ውድ ልጃቸውን አሳልፈው ለመስጠት ወስነዋል። በጥበበኛው ልጃቸው ምትክም 130 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ካዝናቸው አስገብተዋል። ተጫዋቹ በሳንቲያጎ በርናባው አምስት ዓመታትን ለመቆየት የሚያስችለውን ኮንትራት መፈረሙ ታውቋል። በሰባት ዓመታት የክለቡ ቆይታ በ352 ተጫታዎች ላይ ተስልፎ የተጫወተ ሲሆን 110 ግቦችንም ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ሁለት የፕሪሚየር ሊግ፣ የአውሮፓ ሊግ፤ የኤፍ ኤና ሊግ ካፕ ዋንጫን ዋንጫን ከፍ አድርጎ መሳም ችሏል። ሃዛድ ይህን መሰል ታሪክ የሰራበትን ክለቡን መቀላቀሉን አስምልከቶም«አሁን ሪያል ማድሪድን መቀላቀሌ በይፋ ታውቋል፤ አንድ የማይካድ ነገር ቢኖር ደግሞ በእግር ኳስ ህይወቴ በወጣትነቴ የመጀመሪያዋን ግብ ካስቆጠርኩበት ጊዜ አንስቶ ለማድሪድ የመጫወት ህልም ነበርኝ»ሲል በማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ አስፈሯል። ቼልሲዎችን መሰናበት እጅጉን ከባድና ፈታኝ የውይወቱ ክስተቶች ሆኖቦት እንደነበርና ሆኖም ግን በአዲሱ ጎጆውም በብሪጅ የነበረው እያንዳንፈዱ ትዝታ አብሮት እንደሚጓዝ ሳይጠቁም አላለፈም። የቼልሲ ዳይሬክተር ማርያና ክራኖፋስኪያ፤ ከኤዲን ጋር መለያያት እጅግ አሳዛኝና ከባድ ነው። እኛ ከአርሱ ጋር ለመለያያት ፍላጎት አልነበረንም፤ ይሁንና ተጫዋቹ በሌላ አዲስ ፈተናና አዲስ አገር የልጅነት ራእዩን ለማሳካት የወሰነውን ውሳኔ እናካብራለን፤ በክለባችን ላበረከተው አስተዋፆኦም ምስጋናችን የላቀ ነው፤ ወደ ፊት ወደ ስታንፎድ ብሪጅ መመልስ ከፈለገም በራችን ሁሌም ለእርሱ ክፍት ነው ሲሉ»ተደምጠዋል። የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ፕሬዚዳንት ሮማን ካልዴርኖም«ሃዛርድ በሁለት እግሩ መጫወት የሚችል ልዩ ተጫዋች ነው፤ በሜዳ ላይ ጥበብ እጅግ የተካነ ነው፤ ክለቡ ካስፈረማቸው ተጫዋቹች መካከልም ምርጡ ነው፤ በቀጣዩ ዓመት የአሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ስብስብ ውስጥ ልዩነትን ማምጣት ይችላል»ብለዋል። በበርካቶች ዘንድ የሪያል ማድሪዶች ተስፋ መሆኑ የተሰመረበት ቤልጄማዊ ጥበበኛ ዛሬም በይፋ የማድሪዶች ተጫዋች መሆኑን በማረጋጋጥ ከደጋፊዎቹ ጋር እንደሚተዋወቅ ይጠበቃል። የኳሱ ጠቢቡ በአዲስ ቤት ለሌላ ታሪክ ቀጣዩን የውድድር ዓመት በናፍቆት ይጠብቃል።አዲስ ዘመን ሰኔ 4/2011 ታምራት ተስፋዬ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12363
c9dcebc7d4f32844e0f0d301266b8b37
ecc398da937989fe9ec922285a7b610a
‹‹የህዳሴ ግድብ ፍሬውን ልናይ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሆንን እየተሰማን ነው››
 ‹‹ግብጽ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስቆም እስከመጨረሻው እየታገለች ነው። እኛም የጀመርነውን ግንባታ ለመጨረስ እየታገልን ነው። በጉጉት ዘጠኝ አመት የተጠበቀው የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ፍሬውን ልናይ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሆንን እየተሰማኝ ነው›› በማለት አስተያየቱን የሰጠን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ወጣት ሚካኤል ማንደፍሮ ነው።ወጣት ሚካኤል የሲቪል ኢንጂነሪንግ ምሩቅ ነው ፤በተማረው ሙያ ተቀጥሮ እየሰራ ይገኛል።አባይ ነገ እንደርሱ ተምረው ለማደግና ሀገራቸውን ለመለወጥ ጥረት ለሚያደርጉ ወጣቶች ትልቅ ትርጉም አለው ብሎ ያስባል።የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ሀገራቸውን ጥለው የሚሰደዱ ብዙ ወጣቶች በሀገራቸው ተስፋ እንዲኖራቸው ያደርጋቸዋል።ግድቡ ኢትዮጵያን አሳንሰው ለሚያዩዋት ሁሉ አንገቷን ቀና እንድታደርግ የሚያደርጋት መሆኑን  ይናገራል።በመሆኑም እርሱን ጨምሮ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ግድቡን እውን በማድረግ ታሪክ መሥራት አለበት ብሎ ያምናል።እርሱ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነው።‹‹ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በእኔ አእምሮ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በህፃናትም ልብ ውስጥ ገብቷል።በመገናኛ ብዙሃን ሲቀርብ እንደሰማሁት ግብጾች አባይ በደማቸው ውስጥ ነው።እኛም በደማችን ውስጥ እንደሆነ ልናሳውቃቸው ይገባል››በማለት አስተያየታቸውን የሰጡን ሌላው የከተማዋ ነዋሪ አቶ በለጠ መንግሥቱ ፤ ግብጽን መከታተል የዕለት ተዕለት ተግባር መሆን አለበት ብለው ያምናሉ።እንደ አቶ በለጠ ገለጻ፤ ግብጽ በሀሰት ሌላውን ዓለም ለማሳመን ጥረት ስታደርግ ኢትዮጵያ እውነት ይዛ ለዚያውም ፍትሐዊ አጠቃቀም እንዲኖር ደጋግማ እየተናገረች ተቀባይነት አታገኝም ለማለት ያዳግታል ።ግብጽ ግንባታውን ለማስቆም የምታደርገው እንቅስቃሴ  ለኢትዮጵያ የበለጠ ጥንካሬ ይሰጣት እንደሆን እንጂ ወደኋላ አይመልሳትም። የግድቡ ሥራ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሶ ይቆማል ማለት ዘበት እንደሆነም አቶ በለጠ ተናግረዋል። በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ በአንድ የግል ህንፃ ውስጥ ተከራይተው የተዘጋጁ አልባሳት በመሸጥ የሚተዳደሩት ወይዘሮ ትግስት አስመላሽ በበኩላቸው፤ አሁን መስማት የሚፈልጉት ታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተገነባ ነው የሚለውን ሳይሆን፣ አልቋል የሚለውንና አልቆም የጥቅሙ ተጋሪ ሲሆኑ ማየት እንደሆነ ይገልጻሉ።እርሳቸው እንዳሉት የንግድ ሥራቸው በመብራት ነው የሚደምቀው።መብራት ሲጠፋ ሱቃቸው ይቀዘቅዛል።የመብራት አገልግሎት ይቆራረጣል።የጀነሬተር ወጪ ደግሞ ከባድ በመሆኑ ይቸገራሉ።ግድቡ ተጠናቅቆ ችግራቸው እንደሚቃለል ተስፋ አድርገዋል።በከፍለከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ አበበ ተካ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ከዳር እንደምታደርስ ባይጠራጠሩም የግብጽን ጉዳይ በቀላሉ ማየት እንደማያስፈልግ ይገልጻሉ።በሀገር ደረጃ የዲፕሎማሲ ሥራው መጠናከር እንዳለበትና በድርድሩም አሸናፊ ሆኖ መገኘት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።መንግሥት ከማሳመኑ ጎን ለጎን ግድቡን ማሳከት እንዳለበትም ተናግረዋል። እርሳቸውን ጨምሮ ሁሉም ከመንግሥት ጎን ካልቆመ ግብጽ የፈለገችውን ለማሳካት እንደምትጠቀምበትም አመልክተዋል።አቶ አበበ እንዳሉት፤ በተለያየ ጊዜ በሀገሪቷ የሚስተዋሉት አለመረጋጋቶች ግብጽ ለምትፈልገው ዓላማ ምቹ እንዳይሆን ይሰጋሉ።ይህ እንዳይሆን ግን ከወዲሁ ማሰብ እና የሚቆጭ ታሪክ እንዳይሰራ መጠንቀቅ እንደሚገባም ካለው ነባራዊ ሁኔታ ተገንዝበዋል።የግድቡ ግንባታ ሲጀመር ለግንባታ ሥራው ይደረግ የነበረው የገንዘብ ድጋፍና ግድቡ ተጠናቅቆ ለማየት የነበረው ፍላጎት የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላልፈዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 16/2012 ለምለም መንግሥቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35853
b615fbc5f8e6d027668793670258af86
9fce5efd482d4ba4de2203f9caa83ed5
“የመጀመሪያው የውሃ ሙሌት መጠናቀቅ፣ የመቻላችን ማሳያ ነው” ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ
አዲስ አበባ፡- መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በታላቅ ጉጉትና በብዙ ተስፋ የሚጠብቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመጀመሪያው ውሃ ሙሌትመጠናቀቅ ኢትዮጵያውያን አትችሉም ላሉን የመቻላችን ማሳያ መሆኑ ተገለፀ።አዲስ ዘመን ጋዜጣ ያነጋገራቸው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፤ የመጀመሪያው የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን ተከትሎ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የመጀመሪያ ውሃ ሙሌቱ መጠናቀቅ የኢትዮጵያውያንን ማንነት ያስመሰከረ የግብፅንም ልክ ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል። ይህ ስኬት ለኢትዮጵያውያንም ሆነ ለሌሎች ያለው እንድምታ ቀላል የሚባል አይደለም ያሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ እንዲህ አይነት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ ማጠናቀቅ ፈተናው ከባድ ቢሆንም ኢትዮጵያውያን ይህን በመቻላችን ስኬታማ ነን ብለዋል። ይህም አትችሉም ሲሉን ለነበሩት ሁሉ ትልቅ መልእክት ነው ብለዋል። በተለይም እስከዛሬ ድረስ ማንም ጠያቂ ሳይኖርባቸው የዓባይ ውሃ ለኛ ፈጣሪያችን ነው እስከማለት የደረሱትን የግብፆች ጫና ተቋቁሞ ለዚህ መድረስ ትልቅ ስኬት መሆኑን ተናግረዋል። ግብፅ የዓባይን ውሃ በብቸኝነት ለመጠቀም ባላት ጉጉት ስታስፈራራ መቆየቷንም አስታውሰዋል። ይህ ትልቅ ድል በመሆኑ ግብፆች ከዚህ በላይ የትም ሊሄዱ አይችሉም ድርድሩም ይቀጥላል ብለዋል።ግብፅ በቀጣይ በሚደረገው ድርድሮች አክብራ እንድትሄድ ማሳያ መሆን የሚችል እንደሆነ የጠቆሙት ፕሮፌሰር በየነ፤ በታሪክም ቢሆን ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር ከፍተኛ ግንኙነት ያላት እና ጎረቤት አገር ብንሆንም እስካሁንም የውስጥ ችግሮቻችንን ተጠቅመው ሲያሸብሩና ሲያስፈራሩ መቆየታቸውን አመልክተዋል። ይሁንና አሁን የመጀመሪያው የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ ማስፈራራታቸው እንደማያዋጣና ልካቸውን እንዲያውቁ ያስችላል ብለዋል።ይሁን እንጂ ድል አድርገናል በማለት ብዙም መኩራራት አይገባም ያሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ ቀጣይ ለምናከናውነው ግንባታም ድርድሮች የሚቀጥሉ መሆናቸውን አብራርተዋል። ስለዚህ ሁሉንም ነገር በፍቅርና በውይይት ማድረግ ተገቢ መሆኑንም አመልክተዋል። በቀጣይም አቅም እስከፈቀደ ድረስ ሌሎች ግድቦችን በመገንባት ኢትዮጵያን ወደተሻለ ከፍታ ማምጣትና ህዝቦቿን ከድህነት ማውጣት የግድ ነው ያሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ ይህን ተግባራዊ ማድረግ የሚቻለውም የተጀመረውን ሥራ አጠናክሮ በመቀጠል በመስኖ እርሻና በሀይል ማመንጫዎች በመሆኑ እነዚህን ሁለት ከድህነት መውጫ መንገዶች አጠናክሮ መቀጠል ተገቢ ነው በማለት አብራርተዋል።አሁን የተገኘው ድል ለቀጣዩ ተግባር ስንቅ ከመሆን በላይ በጉልበት እናስቆማለን በማለት ሲፎክሩ ለነበሩትም ሆነ በዲፕሎማሲም ሊያዳክሙን ለሞከሩት በሙሉ አሁን መጠናቸውን እና ልካቸውን እንዲያውቁ አድርጓል። የድሉ ባለቤት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ቢሆንም በተለየ መልኩ በጉዳዩ ድርድር ሲያደርጉ ለነበሩ ሁሉ ታላቅ ምስጋና እና ክብር ይገባቸዋል። መንግስትስም “ሙያ በልብ ነው” እንዲሉ። ብዙ ጫጫታዎችን ችሎ በታቀደው መሰረት የግድቡን ውሃ ሙሌት ተግባራዊ እንዲሆን በማድረጉ እውቅና ሊሰጠውና ሊመሰገን ይገባል። ይህም ጨዋነት ነው ብለዋል፤ በቀጣይም እያንዳንዱ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 16/2012ፍሬህይወት አወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35851
c0a645d99b364a6bbd891db61a16e49b
3e647a3e29e38599d698dce047383070
ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች በአፍሪካ ዋንጫ በኮሚቴነት መሳተፋቸው ልምድ ለመቅሰም እንደሚያግዝ ተጠቆመ
በግብጽ አስተናጋጅነት በሰኔ ወር በሚካሄደው 32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተለያዩ ኮሚቴዎች የሚሳተፉ ሙያተኞች ዝርዝር ውስጥ ኢንስትራክተር አብርሀም መብ ራቱ መካተታቸው እውቀቱና ልምድ ለመቅሰም እንደሚያግዝ ተጠቆመ፡፡ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ድረገጽ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ውድ ድሩን በዳኝነት ከሚመሩት የጨዋታው ዳኞች ኢንተርናሽናል ባምላክ ተሰማ እና ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ተመስገን ሣሙኤል በተጨማሪ፤ ኢትዮጵያ በኢንስትራክተር አብ ርሀም መብራቱ መወከሏ በዘርፉ እው ቀትና ልምድ ለመቅሰም እንደሚያግዝ ተጠ ቁሟል፡፡ የ2019ኙን የአፍሪካ ዋንጫ በተለያዩ ዘርፎች የሚያገለግሉ ሰላሳ ኮሚቴዎችና 224 የኮሚቴ አባላት ይፋ ሲደረጉ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ የውድድሩ ቴክኒክ ኮሚቴ የጥናት ቡድንን ተቀላቅሏል ሲል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡ ይህ ቴክኒካል የጥናት ቡድን 15 አባላት ያሉት ሲሆን፤ በዋነኛነት የውድድሩን ኮከብ ተጫዋች ይመርጣል፤ የአፍሪካን የእግር ኳስ ደረጃን እና ቴክኒካል ነገሮችን ይገመግማል፡፡ ከውድድሩ የተገኙ አዳዲስ ነገሮችንም በሪፖርቱ ያቀርባል። ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ ካፍ ስለሰጣቸው ሀላፊነት ሲናገሩ፤ “ከብዙ አገሮች ጋር ያገናኛል፤ እውቀቱንም ልምዱንም ለመቅሰም ይረዳናል፤ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማመቻቸት ይጠቅመናል፤ ይህንን እድል በማግኘቴ እኔ እዚህ ለመድረሴ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ያደረጉትን ሙያተኞች፤ የስፖርት ቤተሰቡን፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን እና ካፍን ከልብ አመሰግናለሁ” ብለዋል። በዚህ ቡድን ውስጥ ኤሊት ኢንስትራክተሮች፤ በከፍተኛ ደረጃ የመጫወት ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ጋር በማካተት የእውቀት ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ የታሰበ ነው።አዲስ ዘመን ሰኔ 5/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12402
586cfe7894f2f53195a582ac6e26e0c1
6df26ea46e01af3c91f37e45c29fb074
ሰባት የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ዳግም ወደ ኢትዮጵያ በረራ ጀመሩ
አዲስ አበባ፡- የኮሮና በሽታ ከተከሰተ በኋላ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የመንገደኞች በረራ አገልግሎት መነቃቃት በማሳየቱ ሰባት የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ወደ ኢትዮጵያ መብረር መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ክብረአብ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ከተከሰተ በኋላ በርካታ ሀገራት በረራቸውን አቋርጠው ቆይተዋል። በአሁኑ ወቅት ግን በአየር ትራንስፖርት የመንገደኞች በረራ አገልግሎት መነቃቃት በማሳየቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ሰባት ደርሰዋል። በአማካይ በቀን ሰባት የውጭ ሀገራት አየር መንገድ አውሮፕላኖች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ላይ ናቸው።እንደ ኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሽመልስ ገለጻ፤ ኮሮና በሽታ በዓለም ላይ ከተስፋፋ በኋላ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ መብረር ከጀመሩ አየር መንገዶች መካከል የዱባይ ፣ የቱርክ፣ የኳታር፣ የግብጽ፣ የሱዳን፣የኬንያ እና የጅቡቲ አየር መንገዶች ይገኙበታል። በአሁኑ ወቅትም በአማካይ ሁለት መደበኛ በረራ እና አምስት መደበኛ ያልሆኑ የመንገደኛ አገልግሎት የሚሰጡ አውሮፕላኖች ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ እየበረሩ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንም እየጨመረ የመጣውን የአየር በረራውን አገልግሎት እና የአውሮፕላኖች ቁጥር መሰረት በማድረግ የቁጥጥር ስራ ለማከናወን የሚችሉ በቂ ሰራተኞችን ማሰማራቱን አቶ ሽመልስ ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው፤ በኮሮና በሽታ መስፋፋት ምክንያት እረፍት ላይ የነበሩ ሰራተኞቹን ጭምር በመጥራት በ24 ሰዓት ውስጥ በሶስት ፈረቃ የሚሰሩ 45 የአየር በረራ ቁጥጥር ባለሙያዎችን በአሁኑ ወቅት ተሰማርተዋል። በቀጣይ ቀናትም ወደ ኢትዮጵያ የሚበሩ እና ከኢትዮጵያ የሚነሱ አውሮፕላኖች ቁጥር እንደሚጨምር በመገመቱ ተጓዳኝ በሽታ ከሌለባቸው ሰራተኞች ውጪ ያሉ እና 90 በመቶ የሚሆኑትን የባለስልጣኑ ባለሙያዎችን በማሰማራት የቁጥጥር ስራውን ለመከወን ታቅዷል። የኮሮና በሽታ በተስፋፋበት ወቅት እንኳን ኢትዮጵያ የአየር ክልሏን እንዳልዘጋች የተናገሩት አቶ ሽመልስ፤ በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያን አየር ክልል አቋርጠው ወደሌሎች ሀገራት የሚያልፉ አውሮፕላኖች ላይ ቁጥጥር ሲደረግ እንደነበረ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ወደአቋረጠባቸው ቦታዎች ዳግም መብረር በመጀመሩ በየቀኑ ወደአውሮፓ እና ሌሎች ክፍላተ ዓለማት የሚያደርገውን በረራ 50 ማድረስ መቻሉን ጠቁመዋል። በመሆኑም ባለስልጣኑ ከ50 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት አውሮፕላኖች እንቅስቃሴ ላይ በየቀኑ ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን መረጃ የኮሮና በሽታ ከመስፋፋቱ በፊት ወደ ኢትዮጵያ የሚበሩ 22 የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ሲኖሩ በየቀኑ ከ300 በላይ በረራዎች በኢትዮጵያ ይስተናገዱ ነበር።አዲስ ዘመን ሐምሌ 18/2012ጌትነት ተስፋማርያም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35966
1c1bce546b7f3ed93f150fafbd4f15d1
b101b0868b18be1bd47e3cd2edb0236a
የግድቡ ውሃ ሙሌት መከናወኑ መንግስት ለግድቡ ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል
 አዲስ አበባ፦ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት በታቀደለት ጊዜ መከናወኑ መንግስት በግድቡ ግንባታ ላይ ያለውን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑ ተገለጸ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የመንግስት ዋነኛ አላማ የህዳሴው ግድብ ግንባታ በተሻለ ጥራት እና ፍጥነት አጠናክሮ መቀጠል ነው። የውሃ ሙሌቱም ተግባር ቢሆን ከግንባታ ስራው ጋር የተያያዘ ሲሆን፤ አሁን ላይ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት መካሄዱ የመንግስትን በግድቡ ግንባታ ላይ ያለውን ቁርጠኝነት ማሳያ አድርጎ መውሰድ ይቻላል። እንደ አምባሳደር ዲና ከሆነ፤ በግድቡ ዙሪያ የሚከናወነው ውይይት ባሻገር መንግስት ግንባታው ጥራቱን እና ፍጥነቱን በጠበቀ መልኩ ሳያቋርጥ መቀጠሉ በዋናነት ለግንባታው ያለውን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው። ግንባታው ሲታሰብ የውሃ ሙሌቱ አንድ አካል በመሆኑ መንግስት እያከናወነ የሚገኘው የግድቡ ስራ ላይ ምንም አይነት እምነት ማጣት ሊኖር አይገባም። ግንባታው በተሻለ ሁኔታ በፍጥነት እየተከናወነ በመሆኑ አሁን ላይ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት ተካሂዷል ። ኃይል ለማመንጨት የሚያስችሉ የተለያዩ ግንባታዎች እና ሙያዊ ተግባራት በሚፈለገው ልክ እየተከናወኑ በመሆኑ መንግስት ግንባታው ላይ ያለውን የማያወላዳ አቋም መገንዘብ ያስችላል ብለዋል ። ኢትዮጵያ ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ግንባታውን እያከናወነች ቢሆንም በቀሪ ጉዳዮች ላይ የጋራ ተግባቦት ለመፍጠር ከግብጽ እና ሱዳን ጋር ድርድሯን እንደቀጠለች መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ዲና፤ ይህም ኢትዮጵያ የተፋሰሱን ሀገራት ጥቅም ሳትነካ የተፈጥሮ ሃብቷን መጠቀም እንደምትችል ያላትን አመኔታ ማሳያ እንደሚሆን አስረድተዋል። የውሃ ሙሌቱም የታችኞቹን ተፋሰስ ሀገራት ጥቅም በማይጎዳ መልኩ መሙላት የኢትዮጵያ መብት ነው። በታችኛው የወንዙ ተፋሰስ ላይ የሚገኙ ሀገራት በግንባታው ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ ለማስወገድ ከውይይቱ ባሻገር ግድቡ ሙያዊ አሰራሩን በተከተለ መልኩ የሚከናወንበትን መንገድ ኢትዮጵያ አጠናክራ እንደምትቀጥልም አስታውቀዋል። መንግስትም የተፋሰሱ ሃገራትን በማይጎዳ መልኩ ወንዙን ለመጠቀም በሚያስችል የትብብር መንፈስ የግድቡ ግንባታን እያከናወነ መሆኑ በግድቡ ላይ ያለውን የዜጎች አመኔታ እንደሚጨምረው ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ሀብት መምህርና የህዳሴው ግድብ የቴክኒክ ቡድን አባል ዶክተር በለጠ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በኩል ደጋግሞ እንደተገለጸው የህዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገው ውይይት ከውሃ ሙሌቱ ጋር አይገናኝም፤ ይልቁንም ሙሌቱ የግንባታው አንድ አካል ነው። ነገር ግን የግድቡ ግንባታ ደረጃውን ጠብቆ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት መካሄዱ መንግስት ለግንባታው ያለውን ቁርጠኛነት ማሳያ አድርጎ መውሰድ ይቻላል። እንደ ዶክተር በለጠ ከሆነ፤ ግብጾች በሚያነሱት የትርክት መረጃ አማካኝነት ውሃ ሙሌቱ ቢከናወን አደጋ እንደሚያመጡ ሲናገሩ ቆይተዋል። ይሁንና ውሃ ሙሌቱ የድርድሩ አካል ባለመሆኑ ከግንባታው ጋር ደረጃ በደረጃ እንደሚከናወን ያውቃሉ። ኢትዮጵያም የግንባታውን ሙያዊ ሂደት በተከተለ መልኩ ሙሌቱን ማከናወኗ ሊጠበቅ የሚችል ጉዳይ ነው። በማንኛውም ጊዜ ግንባታው እንደቀጠለ ሁሉ የውሃ ሙሌቱም ሙያዊ ደረጃውን ተከትሎ መከናወኑ ተገቢ ነው። ይህንንም ኢትዮጵያ በግንባታው ላይ ያላት ቁርጠኝነት በቀጣይም እንደሚቀጥል ማሳያ ነው። የተለያዩ የድርድር መድረኮች በሚከናወኑበት ወቅትም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች የግድቡ ግንባታ ሳይቋረጥ መቀጠሉ ትልቁ የመንግስትን ቁርጠኛነት ያሳያል ብለዋል ።እንደ አንድ የውሃ ዘርፍ ኤክስፐርት እና የግድቡ ተደራዳሪ አካል መግለጽ የምችለው የግብጾች ማስፈራሪያ ከሚዲያ ያለፈ አይሆንም የሚሉት ዶክተር በለጠ፤ የማህበረሰባችንን ስነ ልቦና ለመረበሽ የሚያደርጉት ጥረት አካል መሆኑን ማወቅ እንደሚገባ ገልጸዋል።ይልቁንም ግድቡ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የሚሰጠው ጥቅም መልካም ቢሆንም ድርድሩ ላይ እየተካፈሉ የሚገኙት ጥቅማቸውን ከፍ ለማድረግ ነው ያሉት ዶክተር በለጠ፤ ኢትዮጵያ ለህዝቦቿ ተጠቃሚነት ግንባታውን ትቀጥላለች ይህም ቁርጠኝነቷን ያሳያል ብለዋል ።አዲስ ዘመን ሐምሌ 16/2012ጌትነት ተስፋማርያም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35852
3343adcb03f0f4834595e7b918b85b2c
75780de815016ac2a1887d16b3c2e09d
የህዳሴው ግድብ ውሃ ሙሌት የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ስኬት ማሳያ መሆኑን ምሁራን አስታወቁ
 ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ግንባታ ላይ የነበረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ አፈፃፀሙ 74 ከመቶ ደርሷል፡፡ በ2012 ዓ.ም መያዝ የሚገባውን ውሃ ሙሌትም ሙሉ ለሙሉ መያዙን ተከትሎ ለኢትዮጵያ ብስራት ሲሆን ለግብፅ ልብ ስብራት ሆኗል፡፡ የግድቡ ውሃ ሙሌት በታሰበለት ጊዜ ውስጥ መከናወኑ ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ጥረት ፍሬ ማፍራቱን ማሳያ መሆኑን የተለያዩ ምሁራን ለአዲስ ዘመን ተናግረዋል፡፡ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን መምህር የሆኑት አቶ ገዛኸኝ በርሄ እንደሚሉት፤ ግድቡ በመጀመሪያው ዙር መያዝ የሚገባውን ውሃ በመያዙ የተሰማው ብስራት የኢትዮጵያ ጥንካሬና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል እየተሰሩ ያሉ የዲፕሎማሲ ተግባራት የውሃ ሙሌቱ በታቀደው መልኩ ኢትዮጵያ ማከናወን መቻሏ ግብፆች እስካሁን የመጡበትን አካሄድ ዳግም ለማየት እንደሚገደዱና ቀሪውን የውሃ ሙሌት ለማዘግየት የተቻላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ የኮሙኒኬሽን መምህሩ ያስረዳሉ፡፡በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ሀብት ምህንድስና አስተዳደር መምህር ኢንጅነር አብዱልዋሃብ አቤ እንደሚሉት፤ ቀደም ሲል በአገሪቱ የነበረው አንድ የውሃ ምህንድስና ትምህርት ቤት በአሁኑ ወቅት በ12 ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ መሆኑ በቀጣይ ኢትዮጵያ የውሃ ሃብቷን ከዚህ በበለጠ ለመጠቀም ዕድል እንዳላትና ይህም ዓባይን ጨምሮ በሌሎች ወንዞች ላይ የመጠቀም መብቷን ለመጎናፀፍ እውቀት እያካበተች መሆኑን አመላካች ነው፡፡ ግብፆች ይህም ራስ ምታታቸው ሲሆን ለኢትዮጵያ አይበጅም የሚሉትን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም፡፡ እንደ ኢንጅነር አብዱልዋሃብ ገለፃ፤ ግብፅ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ከስትራቴጂክ ጠቃሜታ፤ ወታደራዊ ኃይል፤ አገሪቱ ካላት የተማረ የሰው ኃይል እና በዲፕሎማሲ ረገድ የትኛው አዋጭ ነው ብለው አጢነው የሚንቀሳቀሱ ሲሆን አሁን ባለው ሁኔታ በብዙ መንገድ ሽንፈት እየገጠማቸው ነው፡፡ አሁን እየተበለጡ ሲሆን ይህንን ለማካካስም ሌላ ተንኮል ላይ መጠመዳቸው አይቀሬ መሆኑን ማጤን አስፈላጊ መሆኑንና ለዚህ ሁሉ ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡በተለይም በዲፕሎማሲ ሥራ የተናበበ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሥራዎችን ማከናወን፤ በዓለም ላይ ኢ-ሚዛናዊ ዘገባ እያካሄዱ ያሉ ሚዲያዎችም ላይ በመቅረብ እውነታውን ማስረዳት ይገባል፡፡ ግድቡ ውሃ መያዝ መጀመሩ አንዱ ድል ቢሆንም በቀጣይም በርካታ የቤት ሥራዎችም መኖራቸውን በመጠቆም፤ የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ እጅጉን በተናበበ መንገድ ግድቡ ቀጣይ ምዕራፎች ላይ ማተኮር አለባቸው ብለዋል፡፡ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ህግ መምህር የሆኑት አቶ ይበልጣል መሥዕዋት እንደሚሉት፤ የአሜሪካና የአረብ ሊግ ውሳኔን በመፃረር ብሎም የግብጽን ፉከራ በመተው ግድቡ ውሃ ሙሌት መጀመሩ የኢትዮጵያን ተሰሚነት በእጅጉ የሚጨምርና ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ አሸናፊ እየሆነች መምጣቷን አመላካች ነው፡፡ግብፅ ቀደም ሲል ግድቡ እንዳይገነባ በዲፕሎማሲ ጫና፣ የፋይናንስ ምንጮችን በመዝጋት ብዙ ሄዳ አዋጭ ባይሆንላትም በቀጣይ የዓለም ባንክን፣ ኢንተርናሽናል ሞንተሪ ፈንድንና ሌሎች የገንዘብ ምንጭ የሆኑ ተቋማት ሌላ ቀጣይ ልማት እንዳትሰራ ብድርና እርዳታ ለማስከልከል ብዙ ዕርቀት ልትጓዝ እንደምትችል ያላቸውን ስጋት አስቀምጠዋል፡፡ግብፆች እስካሁን የመጡበት አካሄድ በኢትዮጵያ ውስጥ እጅ አዙር የብጥብጥ ሤራ አዋጭ እንዳልሆነ በቅርቡ በኢትዮጵያ ታቅዶ የከሸፈው ሴራ ሁነኛ ማሳያ ነው የሚሉት ምሁሩ፤ ህብረተሰቡም ሴራውን በሚገባ ተረድቷል፡፡ በቀጣይ የአገር ውስጥ ፖለቲካ ከተስተካከለ፣ ሙስና እና ምዝበራ ከተወገደ እና የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት እየተጠናከሩ ከሄዱ በዓባይ ላይ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ለማከናወን አንዳች የሚያግድ ኃይል እንደሌለም አቶ ይበልጣል ይነገራሉ፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 18/2012ክፍለዮሐንስ አንበርብር
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35974
e4cabdc849b4981eb5c0308748eb7658
75e712d1e0d394716a5a5fb6a231b08c
ካሳዬ አራጌ ለኢትዮጵያ ቡና ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተመርጧል
ኢትዮጵያ ቡና የቀድሞ የክለቡ ተጫዋች እና አሰልጣኝ የነበረውን ካሳዬ አራጌን ለቀጣዩ የውድድር ዘመን አሰልጣኝ አድርጎ መምረጡን በይፋዊ ገፁ አስታውቋል። የውድድር ዓመቱን በፈረንሳዊው አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜስ መሪነት ጀምሮ በገዛኸኝ ከተማ ጊዜያዊ አሰልጣኝነት ሊያገባድድ የተቃረበው ኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ኦፕሬሽንና ቴክኒክ ኮሚቴን በአዲስ መልክ ማዋቀሩ የሚታወስ ሲሆን የአሰልጣኝ ምርጫ እንዲያከናውን በተሰጠው መመሪያ መሰረት አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን ምርጫው ማድረጉን የሶከር ስፖርት ድረ ገፅ አስነብቧል። “ኢትዮጵያ ቡና የሚታወቅበትን የጨዋታ ዘይቤ በጥልቀት ይረዳል.” በሚል መነሻነት እንደተመረጠም ክለቡ ጨምሮ ገልጿል። አሰልጣኝ ካሳዬ ከሚኖርበት ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከስምምነት ላይ ከደረሰ ቀጣዩ የቡና አሰልጣኝ ሆኖ የሚሾም ይሆናል ተብሏል። ከ1979 ጀምሮ ለኢትዮጵያ ቡና የተጫወተው ካሳዬ አራጌ በ1994 መጨረሻ ከእግርኳስ ዓለም ከተገለለ በኋላ የክለቡ አሰልጣኝ ሆኖ የሰራ ሲሆን እስከ 1996 አጋማሽ በነበረው ቆይታ የጥሎ ማለፍ ድል ሲያስመዘግብ ኢትዮጵያ ቡናን በጂኬ አጨዋወት ፍልስፍናው የወቅቱ መነጋገርያ ቡድን አድርጎት ነበር።አዲስ ዘመን ዛሬግንቦት 25/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11899
b418ad8a665ecae2ee21bcddb6902032
d1defe089487d502909c542ccf627a79
እግር ኳስ ጥበብ ወይስ….?
የሰው ልጅ ሰፊውን የስሜቱን ክፍል በጥበብ እንደሚገለጥ በጉዳዩ ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በእርግጥም ሙዚቃ፣ ስዕል እና ሌሎች የጥበብ ዘርፎች በሰው ልጅ እያንዳንዱ ድርጊት ላይ ሰፊ ቦታ ይዘው እንመለከታለን። ስለዚህ እንዲህ እንጠይቃለን። እግር ኳስ በጥበብ ውስጥ የምትገለፅ እውነት? ወይስ በራሷ መልህቅ ላይ በነፃነት እንደምትንሳፈፍ አይነት? ይህን ለመጠየቅ ያስደፈረን ሁለት ተቃራኒ ሀሳቦች በዚህ ጉዳይ ላይ ስለሚንሸራሸሩ ነው። አንዱ ወገን ክቧን ኳስ «አስደናቂ ጥበብ፤ነገር ግን ቦታ ያልተሰጣት» በማለት ሲገልፃት። ሌላኛው ደግሞ «ከሰሞነኛ ስሜት የማታልፍ ድርጊት» ናት በማለት፤ ጥበባዊ ፋይዳዋን ይነጥቃታል። ለዚህም ይመስላል ታላላቅ የዓለም እና የአገራት ታሪኮች ሲፃፉ ስፍራ የማይሰጧት። የአንድን አገር ሉአላዊነት፣ ባህል እና ወግ ወለል አድርጎ በሚያሳየው የታሪክ መዝገብ ላይ እግር ኳስ ስፍራ ሲያጣ የምንመለከተው። ይህ ማለት ግን ወዳጆቿ እስከነ ውበቷ ወደ ቀጣዩ ትውልድ አያሻግሯትም ማለት አይደለም። ነገር ግን የቡድን ስብስብ ማንነት አንዱ መገለጫ እንደመሆኗ መጠን በታሪክ መዝገብ ላይ ማግኘት የሚገባት ክብር በትከሻዋ ላይ አልተደረበላትም። እግር ኳስን በፈላስፋው በሬኒ ዴካርት አስተሳሰብ ተመልክተናት ፋይዳዋን ለማየት እንይ እስቲ፤ ዴካርት «I think, therefore I am» በማለት በአፈጣጠሩ ላይ ምንም ጥርጣሬ እንደሌለው ሊያመላክተን ይሞክራል። ይሄን እሳቤ «I play therefore I am» ወደሚለው እናምጣው እና የክቧን ኳስ ሚስጢር ለመፍታት እንሞክር። ታዲያ እንሞክር ነው ያልነው። በእግር ኳስ ጨዋታ አንድ ቡድን የሚይዘው የአጨዋወት ስልት የቡድኑን ስብእና ይበይናል። “አጨዋወትህን ንገረኝ እና ማን እንደሆንክ እነግርሀለሁ” አይነት። ላለፉት በርካታ ዘመናት የሰው ልጆች እግር ኳስን በተለያየ የአጨዋወት ስልት ለመግለጥ እና አዳዲስ ፈጠራዎችን ለማስተዋወቅ ሙከራ አድርገዋል። ልፋታቸውም መና አልቀረም ዛሬ ላይ ደርሰዋል። ታሪክ በዚህ ላይ ምን ይለናል? እግር ኳስ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአዳዲስ የአጨዋወት ፍልስፍናዎችን እየዳበረ ይመጣል። ለዓመታት በአንድ መንገድ የሚጓዝ አይደለም። በስፖርቱ ፍቅር አቅላቸውን የሳቱ እና በህልማቸውም ጭምር ከኳስ ጋር የሚያድሩ ባለሙያዎች እግር ኳስን ለማሻሻል ይጠበባሉ። በአንዱ ዘመን የመጣው ፋሽን ትንሽ ሲቆይ ያልፍበታል። ደግሞ አዲስ ይፈጠራል። ወቅቱ 1872 ነበር። በጊዜው በእግር ኳስ ታሪክ የመጀመሪያው ኢንተርናሽናል ጨዋታ በሁለት አገራት መካከል ተደረገ። ጨዋታውን ያደረጉት እንግሊዝ እና ስኮትላንድ ነበሩ። በዚያን ጊዜ ነበር «አሰላለፍ» ወይም ቦታን መሰረት አድርጎ ቡድንን ማዋቀር እንደ ህግ ሆኖ የተጀመረው። ተጫዋቾች በአሰኛቸው ስፍራ እና መንገድ ወደ ተጋጣሚያቸው ግብ በመድረስ እና የግብ ክልላቸው እንዳይደፈር በመከላከል ይጫወቱ ነበር። የመጀመሪያው የእግር ኳስ ማህበር ዋና ፀሐፊ ቻርልስ አልኮክ በመፅሐፉ ላይ እንዳሰፈረው «በወቅቱ ሰባት አጥቂዎች የባላጋራ ክልል ላይ ግብን ያነፈንፉ ነበር። ሶስቱ ደግሞ ግብ እንዳይቆጠርባቸው በተቃራኒው ይጠብቁ ነበር። በእርግጥም የመጀመሪያው መስመር ላይ የሚኖረው በረኛው ብቻ ነው» በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ የእግር ኳስ ህግ እና ፍልስፍናን ተከትሎ ጨዋታዎችን ማድረግ እንደተጀመረ፤ እንግሊዝም ባላጋራዋን ስትገጥም 1-2-7 አሰላለፍ ወይም «formation» ይዛ እንደቀረበች፤ ስኮትላንድ በአንፃሩ 2-2-6 አሰላለፍን እንደመረጠች ይናገራል። በወቅቱ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ምንም ግብ ሳይቆጠርበት ነበር የተጠናቀቀው። ከሁለቱ አገራት ፍልሚያ በኋላ አሰላለፍን መሰረት አድርጎ መጫወት አዋጪ እንደሆነ የእግር ኳስ ባለሙያዎች መገንዘብ ጀመሩ። በሌላ በኩል የእንግሊዙ ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ እና ኖቲንግሀም ፎረስት በጊዜው የ2-3-5 አሰላለፍን በእግር ኳሱ ላይ ለማስረፅ ጥረት እያደረጉ ነበር። ከዚህም ሌላ ቀስ በቀስ በባላጋራ ክልል ላይ ግብ ለማግባት የሚራኮቱ አጥቂዎችን የመቀነሱ ተግባር ፋሽን ሆነ። እ.አ.አ በ1960 በዩክሬኑ የዳይናሞ ኬቭ የእግር ኳስ ክለብ ተደናቂ ታሪክ ያለው አሰልጣኝ «ቪክቶር ማስሎቭ» እግር ኳስን እንደ «አውሮፕላን» መስሎ በማቅረብ አዲስ የጨዋታ ፍልስፍናን አስተዋወቀ። ባላጋራን ለመርታት አጥቂዎችን መቀነስ፣ የተከላካይ እና የመሀል ክፍሉን ማጠናከር ተገቢ መሆኑን አመላከተ። ይህ ሂደት እስካሁንም ድረስ ቅርፁን እየቀያየረ አዳዲስ ፍልስፍናዎችን እያካተተ መጓዙን ቀጥሏል። ለሬኔ ዴካርት ማሰቡ መኖሩን ካረጋገጠለት። ወይም መኖሩ እንዲያስብ ካደረገው፤ እኛም ክቧ ኳስ በጥበብ ትገለፃለች፤ ኧረ እንዳውም እግር ኳስ ራሱ ጥበብ ነው የሚል ድምዳሜ እንሰጣለን። ይህን ስንል ግን ግብዝ ሆነን አይደለም። አዲስ ነገር መፍጠር ማሰብን አሊያም ለየት ያለ ጥበብን የሚጠይቅ ከሆነ፤ እግር ኳስ ጥበብ መሆኑን ለመደምደም ያን ያክል የሚከብድ ነገር አይደለም። መካድ የማንችለው ሀቅ ግን አንዳንድ ግብዞች እግር ኳስን ያለ ስፍራዋ ሲያስቀምጧት፣ አንዴ ዝቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ያለቅጥ ከፍ እንደሚያደርጓት ነው። ስታዲዮሞች የክቧን ኳስ ታሪክ በመያዛቸው ብቻ ዝም ብለው እንኳን ይጮሀሉ። ይህን ጩኸት ለመስማት ደግሞ ዝም ማለት ብቻ በቂ አይደለም። በተጨማሪ የክቧን ኳስ የደስታ እና የስቃይ ዘመናት ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል። «ባዶነት እራሱ በስታዲዮሙ ውስጥ ባዶ ይሆናል። ይህ የሚሆነው ግን ፍፁም ከእግር ኳስ የራቃችሁ እና በስታዲዮሙ ውስጥ ቅንጣትም ትውስታ የሌላችሁ ከሆነ ብቻ ነው» ስታዲዮም ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መግባት ብቻ የታሪኩ አካል አያደርግም። ወደ ሌላኛው ጥጋት ስንመለከት ደግሞ ክቧ ኳስ ደስታን ብቻ ሳይሆን የጠለቀ ሀዘንን ይዛ ከተፍ እንደምትል እናስተውላለን። ነፍሳችንን ሀሴት ለማድረግ ቋምጠን በግልባጩ መሪር ሀዘን ውስጥ ትጨምረናለች። ሞኛሞኝ ሆነን ከክቧ ኳስ ደስታን ብቻ ከጠበቅን «በእግር ኳስ ግጭትና ጥላቻ አይፈጠርም፤ መሀረብም እንባን አይጠርግም» ብለው እንደሚነታረኩት አይነት እንሆናለን ማለት ነው። አይናችንን ከከፈትን በዚህኛው ጥግ ላይ ሌላ ሞኛ ሞኝነት እንመለከታለን። የክቧ ኳስ አፍቃሪዎች እንደተዘነጉ ያስባሉ። ታሪክ ጥቂት ስፍራ፤ ቢያንስ እንኳን አንዳች ጥጋት አልሰጠንም ሲሉ ያጉረመርማሉ። ይህን የሚሉት ግን ክቧ ኳስ የሁለት ቢሊዮን ሰዎችን አይን በአንድ የቴሌቪዝን ሳጥን መክተቷን የዘነጉ ሰዎች ናቸው።አዲስ ዘመን ዛሬግንቦት 25/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11890
95c49d3e8943e47848c20d3418e08e65
abec54975c5013314169269043f1b798
«መንግሥት የኢትዮጵያን አጀንዳ ይዞ እስከቀጠለ ድረስ በማንም አይሸነፍም»- ዶክተር ገበያው ጥሩነህ የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ፕሬዚዳንት
አዲስ አበባ፡- ‹‹ሀገርን የሚመራው መንግሥት በፍትሐዊነት፣ ሁሉንም ብሄር ብሄረሰቦች በእኩልነት እስከመራ እና የኢትዮጵያን አጀንዳ ይዞ እስከቀጠለ ድረስ ማንም አያሸንፈውም›› ሲሉ የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ፕሬዚዳንት ዶክተር ገበያው ጥሩነህ ገለጹ።ዶክተር ገበያው ሰሞኑን ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደተናገሩት መንግሥት ትክክለኛና ኢትዮጵያን ወደፊት የሚያራምድ አጀንዳ እስከያዘ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ ከመንግሥት ጎን ይቆማል። ኢትዮጵያን ለማፍረስም ሆነ ለማበጣበጥ የሚፈልጉ አካላትም ይሄንን በደንብ ቢረዱ መልካም ነው ብለዋል። ሀገርን በመምራት ላይ ያሉ አካላትም የህዝብን ፍላጎት በመጠበቅ እና ያለአድሎ ሀገሪቱን በመምራት መገለጥ ይኖርባቸዋል ያሉት ዶክተር ገበያው፤ መንግሥት ፍትሐዊ የሆነ ሁሉንም ብሄር ብሄረሰቦች እኩል የሚያስተዳድር አስተዳደር እየፈጠረ፣ ኢትዮጵያን ዋነኛው አጀንዳ አድርጎ መቀጠል አለበት። ይሄንን ካደረገ ህዝብ ከመንግሥት ጋር እንደሚቆም ጠቅሰው ህዝቡ ከመንግሥት ጋር እስከ ቆመ ድረስ ደግሞ ኢትዮጵያ ወደታለመላትና ወደሚፈለገው ብሩህ ጎዳና ትሄዳለች ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ አሁን ያለችው መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው የሚሉት ዶክተር ገበያው በተለይ ባሳለፍናቸው ሁለት ዓመታት የሚታዩ በጣም ብዙ መልካም ነገሮች በአንድ በኩል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ ስጋቶች መኖራቸውን ገልጸዋል። ‹‹ኢትዮጵያ ያለችበት አጣብቂኝ ከዚህ በፊት በነበሩ ክፍለ ዘመናት ያልነበረ፣ ጠንከር ያለና አስቸጋሪ ነው። በአንድ በኩል ከግብፅ ጋር ተያይዞ ያለው ጂኦፖለቲክስ እንዲሁም በሀገራችን ለብዙ ዓመታት የተዘራው ጫፍ የወጣው የዘር ፖለቲካ አመለካከት አለ። በዚያ ላይ ደግሞ ኮቪድ 19 ተጨምሯል።›› ያሉት ዶክተር ገበያው የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የሥራ አጥ ቁጥሩ መብዛት፣ ከኢኮኖሚ ዕድገቱ ጠንክሮ አለመሄድ ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ በርካታ ችግሮች መታየታቸውን አስታውቀዋል። በለውጥ ጉዞው በጣም ጥሩና እጅን በአፍ ላይ የሚያስጭኑና የሚያስደምሙ አስደናቂ ነገሮች መታየታቸውን ገልጸው፤ የፖለቲካ ምህዳሩን ከማስፋት ጀምሮ በልማት ሥራ ላይ የሚታዩ መልካም ነገሮች አሉ። ሰፋፊ ሥራዎች በረጅም ዓመት በማያልቁበት ሀገር በወራት ፕሮጀክቶች እየተጠናቀቁም ነው። በብዙ ራዕይና ተስፋ ኢትዮጵያን ወደነበረችበት ከፍታ የሚመልስ ዓይነት አቅጣጫ እየታየም ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።ዶክተር ገበያው እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ ጠላቶች እርስ በእርስ በሚኖረን ግጭትና አለመግባባት ኢትዮጵያዊነት የሚሸነፍ ይመስላቸዋል። ይህችን ሀገር ለማበጣበጥና ለማፍረስ የሚሠራው አካልም ይሄንን የተረዳ አይመስለኝም። ‹‹ደርግ ኃይለስላሴን አሸንፎ አይደለም። ያሸነፈው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። ህዝቡ አገዛዙን ስለጠላ ነው ለውጡን የተቀበለው እንጂ ከኢትዮጵያውያን ጋር ውጊያ አድርጎ ያሸነፈ የለም። ወያኔም አሸንፎ ሳይሆን ህዝብ ደርግን ስለጠላው ብቻ ነው የተቀበለው። አሁን የታየው ለውጥም ህዝቡ ከኢህአዴግ ጋር ስላልቆመ የመጣ ነው።›› ያሉት ዶክተር ገበያው ሰሞኑን ይሄንን ችግር ሲፈጥሩ የሰነበቱ ሰዎችና ቡድኖች የሚስቱትም ይሄንን ነው ብለዋል። አሁን ያለውን መንግሥት ህዝብ ከጎኑ ከሆነ ማንም ሊያሸንፈው አይችልም። ህዝብ በጠላው የኢህአዴግ መንግሥት ላይ ይሄንን ወጣት አነሳስተን ድል አግኝተናልና አሁንም ያንን እንደግማለን ማለት መሳሳት ነው ሲሉም ገልጸዋል።እርስ በእርስ የሚደረግ ግጭት በጣም የሚያሳዝን ነው ያሉት ዶክተር ገበያው በተለይ በአሁኑ ወቅት የውጭ ችግር ይገጥመናል ብለን በምንሰጋበት ጊዜ የእርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር የሚያደርጉ አካላት ለውጭ ኃይሎች በር መክፈት መሆኑን በመገንዘብ ከስህተታቸው ሊታረሙ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል። ዶክተር ገበያው እንዳሉት፤ በታሪካችን በመሳፍንት ተከፋፍለን በኖርንበት ዘመን እንኳን እርስ በእርስ ሊዋጉ ተፋጥጠው የነበሩት መሳፍንት ከውጭ ጠላት መጣ ሲባል የሚዘምቱት አብረው ነው። ያንን ታሪካችንን በዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ልንደግመው ይገባል። ሁልጊዜም ቢሆን ወጣቱ ተቃውሞውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማድረግ አለበት። አሁን ደግሞ ይሄንን ለማድረግ የሚያስችል ምህዳርን ያሰፋ ስርዓት አለ። የተገኘውን ነፃነት ይዞ ወደፊት መግፋት ይገባል እንጂ በጡንቻ ማሰብ በ21ኛው ክፍለ ዘመን መቆም አለበት ሲሉም ተናግረዋል። ወጣቱ ለሚያነሳው ጥያቄ ምክንያታዊ መሆን እንዳለበት የተናገሩት ዶክተር ገበያው አባቶቻችን ‹‹እህን ጨምርበት›› የሚሉት አባባል ነበራቸው። ‹‹እህ›› ማለት አዳምጥ፣ አሰላስል ፣አገናዝብ ፣ ሁሉም ጉዳይ ይግባህ ማለት ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ግን አንዳንድ ወጣቶች አንድን ነገር ሲሰሙ ወደፊትና ወደኋላ አገናዝበው አይመለከቱም። እውነታውንም አያረጋገጡም፤ እንዳውም ከሰማውም በላይ ጨምሮ ለሌላው ይናገራል። ስለዚህ ከዚህ ባህል መውጣት አለበት። መንገድ የምዘጋው ፣ንብረት የማወድመው፣ ሰው የምገድለው ለምንድነው ? ይህን አድርግ ያለው ማን ነው ? ውጤቱስ ምንድነው ብሎ ማገናዘብ ይገባል ሲሉም መክረዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 19 ቀን 2012 ዓ.ም በ አልማዝ አያሌው
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36041
e281b5f5857d82bef0158a17b336e949
bb8063d372bd132ae67dc0433177175a
ዓመታዊው የስፖርት ጥናት ምርምር ጉባኤ ተካሄደ
የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በየዓመቱ የሚያደርገው የስፖርት ጥናት እና ምርምር ጉባኤ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ትላንት ተጠናቋል። በጉባኤው ላይ በተለያዩ ስፖርት ዘርፎች ላይ ሳይንሳዊ ጥናት እና ምርምር ያደረጉ ምሁራን ስራዎቻቸውን አቅርበዋል። በአካዳሚው የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ በርካታ የስፖርት ባለሙያዎች እና የበርካታ ዓመታት ልምድ ያላቸው አሰልጣኞች የተገኙ ሲሆን ስፖርቱን በሳይንሳዊ መንገድ የሚያድግበትን እና ውጤታማ የሚሆንበት ጉዳዮች ላይ ምክረ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ አንበሳው እንየው በየዓመቱ የሚደረገውን ጉባኤ በማስመልከት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ላይ እንደገለፁት አካዳሚው በተሰጠው ተግባር እና “ኃላፊነት መሰረት በየዓመቱ በርካታ ጥናትና ምርምሮችን ከምሁራን እና ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመሆን እየሰራ ያቀርባል። ሁሉም የስፖርት ዘርፉ ባለድርሻ አካላት ከጥናቱ የሚገኘውን ውጤት ተግባር ላይ ለማዋል ሊረባረቡ ይገባል። ሳይንሳዊ መፍትሄ አመላካች ምርምሮችን ወደ መሬት ማውረድ በየጊዜው ለሚያድገው እና ለሚለዋወጠው የስፖርቱ ዘርፍ አማራጭ የሌለው ነው። በባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር የስፖርቱ ዘርፍ ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ በበኩላቸው እንደገለፁት በስፖርቱ ዘርፍ የሚታየውን ማነቆ ለመፍታት የሚደረጉትን ጥናት እና ምርምሮች ከመደርደሪያ ላይ እንዳይቀሩ ጥብቅ ስራ መሰራት ይኖርበታል። ይህ እንዳይሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል። አካዳሚው በሁሉም የስፖርት ዘርፎች ላይ የሚታዩትን ችግሮች ለመፍታት መፍትሄ የሚያመላክቱትን ጥናቶች ሊያዳብራቸው እና በየጊዜው እያሻሻለ ወደ መሬት የሚወርዱበትን መንገድ ሊያመቻች ይገባል፡ በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የተገኙ ሲሆን የረጅም ዓመት ልምዳቸውን በመድረኩ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች አካፍለዋል። በተለይ የኤሽያ አህጉር አገራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሳይንሳዊ ምርምር በማድረግ በስፖርቱ ዘርፍ ውጤታማ መሆን መቻላቸውን ገልፀዋል። በየመን በነበራቸው ቆይታም በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የተቋቋሙ አካዳሚዎች ሳይንሳዊ መንገድ በመከተላቸው ውጤታማ እንደነበሩ መታዘባቸውን ተናግረዋል። በተለይ ኢትዮጵያ በአላት እምቅ በስፖርቱ ላይ ማተኮር እና በእነዚህ ውስን ስፖርቶች ላይ መስራት ተገቢ መሆኑን አስምረውበታል። አዲስ ዘመን ዛሬግንቦት 25/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11893
92f3954fa37c6d0ec93c405c3c107ca6
b96570e382d186f19c30ddf844a5ce4e
የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ቀንሷል
የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ይታወቃል። ይኸውም ስፖርቱን ከማስፋፋት ይልቅ ወደ ማገድ፣ ህዝቡንም ከማቀራርብ ይልቅ ወደ ማራራቅ የሚመራ መሆኑ ታይቷል። አሳሳቢ የሆነውን ይህንን የስፖርታዊ ጨዋነት ችግርም በጥናት የመለየት ስራ ሲሰራ ቆይቷል። የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽንም ከፌዴሬሽኑ ጋር በመተባበር በሳይንሳዊ መንገድ ችግሮቹ እንደተለዩ በተለያዩ መድረኮች ተገልጿል። በተለየው መንስኤና የመፍትሄ አቅጣጫ መሰረትም መግባባት ላይ የሚያደርስ ግኝት በመያዝ በየደረጃው ከባለድርሻ አካላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጥ እና ሁሉም የየራሱን ሚና እንዲጫወት አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደ ስራ መገባቱን፤ በኮሚሽኑ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ናስር ለገሰ ይገልጻሉ። ወደ ስራ ከተገባ በኃላም በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል የሚለውን ለማወቅም ከሰሞኑ በአዳማ ከተማ መድረክ ተዘጋጅቷል። በመድረኩም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አጠቃላይ አፈጻጸሙን እንዲሁም የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ሚናውን በምን መልኩ እንዳከናወነ ሪፖርት መቅረቡን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። በቀረበው የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት መሰረትም የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ካለፈው ዓመት አንጻር መቀነሱ ታይቷል። ችግሮቹ ፖለቲካዊ ይዘትም ስለነበራቸውም ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ከላይ እስከታች የተሳተፉበት ነበር። በተለይም በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካከል የነበረውን ችግር በመፍታት ክለቦች በሜዳቸው እንዲጫወቱ መደረጉ በመልካም ጎን ተነስቷል። በተለይ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ስፖርታዊ ጨዋነትን በማስፈን ረገድ የተሻለ በመሆኑ በመድረኩ ከተገኙ አካላት ምስጋና ተችሮታል። ክለቡ በተለይ ከመቀሌ ሰባ እንደርታ ጋር በነበራቸው ጨዋታ በራሳቸው ተነሳሽነት ኃላፊነት ለመውሰድ ያሳዩት ዝግጁነት እንዲሁም ደጋፊዎች ሰላምን ለማስፈን የሚያደርጉት ጥረት ተደንቋል። ሌሎችም የክለቡን አርዓያ በመከተል የውድድር ስፍራዎች የስጋት ቀጠና ሳይሆን፤ ህብረተሰቡ ያለ ሃሳብ የሚዝናናበት ስፍራ እንዲሆን ጥሪ መቅረቡንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ስፖርታዊ ጨዋነትን ለማስፈን ተጨባጭ ስራ የሚሰሩ የመኖራቸውን ያህል ጠንክረው መስራት እንደሚገባቸው የታዩ መኖራቸውም ተመልክቷል። በአንድ ክልል ውስጥ ሆነውም ያልተፈታ ችግር ያለባቸው መኖራቸውም ተጠቅሷል፤ ለአብነት ያህልም በሃዋሳ ከተማ እና ወላይታ ድቻ፣ በኮምቦልቻ እና ደሴ ከተማ መካከል እንዲሁም በትግራይ ባሉ የክለብ ደጋፊዎች መካከል አለመግባባቶች መኖራቸውም ተጠቅሷል። ይህም ችግሩን ከመቀነስ ባሻገር ሙሉ ለሙሉ እንዳይፈታ አድርጎታል። አሁንም ያልተሰሩ ቀሪ ስራዎች መኖራቸው የተነሳ ሲሆን፤ ስፖርታዊ ጨዋነትን ለማስፈን ያልተዳሰሱ መንገዶች መኖራቸውም ከመግባባት ላይ ተደርሷል። በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰራር ላይም ችግሮች መኖራቸውም ተስተውሏል። የፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት በቂ የሰው ኃይል እንዲኖረው ከማድረግ ጀምሮ ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴዎችን በድጋሚ የማደራጀት እንዲሁም አሰራሩን የመፈተሽ ስራም አስፈላጊ ነው። በመሆኑም ይህንኑ ከክለቦች ጋር የጋራ ለማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ አቶ ናስር ያብራራሉ። ፌዴሬሽኑ ውሳኔዎችን ተከትሎ የሚመጣውን ቅሬታ ለማስቀረት በሰነድ ደረጃ አሳድጎ ለሚመለከታቸው አካላት በማሰራጨት ላይ ይገኛል። ፌዴሬሽኑ ሌሎች ችግሮችንም በአሰራር ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑም ተመልክቷል። ይህንኑ በየደረጃው ግንዛቤ በማስጨበጥ የህግ ክፍተት እንዳይኖርም ተጨማሪ ስራዎችን ማከናወን እንዳለባቸው ተመልክቷል። ሌላው የደጋፊዎችን ግንዛቤ በማሳደግና ደጋፊዎች የአባልነት መታወቂያ እንዲያገኙ የማድረግ ስራ አስፈላጊ መሆኑም ተነስቷል። የጸጥታ አካሉም አጠቃላይ የውድድር ቦታን ደህንነት በማስጠበቅ እና የውድድር ሁኔታን አስቀድሞ በማወቅ ቅድመ ሁኔታ በማድረግ ለትንኮሳ የሚገቡትን በመፈተሽ፣ በመለየትና የማውጣት ላይ እንዲሰሩ። በዚህ ስራ ላይ የጸጥታ ክፍሉ በሌሎች ላይ ጉዳት ላለማድረስ በሚያደርገው ጥረት በራሱም ላይ ችግር እየደረሰ መሆኑ የተሰመረበት ጉዳይ ሆኗል። በክለቦች ዘንድ አጥፊዎችን በማጋለጥ ላይ ችግር ስላለ ለስፖርቱ እድገት ሲባል በዚህ ላይ ጠንካራ ስራ መሰራት አለበት። በመገናኛ ብዙሃን ዘንድም ለስፖርታዊ ጨዋነት መስፈን ጉልህ ሚና ያላቸውን ያህል ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ በማሰራጨት አባባሾች መኖራቸውም ተነስቷል። በመሆኑም ተቀራርቦ በመስራት ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ነው። በመድረኩ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል፤ በዚህም ሁሉም አቅዶ በስፖርታዊ ጨዋነት መስፈን ላይ መስራት እንደሚገባ መጠቆሙን አቶ ናስር ይገልጻሉ። በስፖርቱ ጥራት ላይ መስራት እንደሚገባ፤ በዳኞች አቅም በማሳደግ፣ በስፖርተኞች ምልመላ፣ የክለብ ተጫዋቾች ክፍያ ወጥነት፣ አድሎአዊ ከሆነ አሰራር በመውጣት፣ ጸጥታ ክፍሉም ጠንክሮ እንዲሰራ፣ የተሻለ ስራ የሰሩ ክለቦች ተሞክሮም ሌሎች እንዲጋሩ፣ … ከስምምነት ላይ ተደርሷል።አዲስ ዘመን ግንቦት 26/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11936
e97c869a3b995a8c69020a39960b933f
1e3c578f8ea401a22955f7f3d386c355
ክለቦቹ በጋራ ራሳቸውን በገቢ ለማጠናከር ተስማሙ
 የፋሲል ከነማ እና ባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ከለቦች በጋራ የፋይናንስ አቅማቸውን ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለፀ፡፡ ክለቦቹ በባህርዳር ከተማ በተደረገ ልዩ ዝግጅት ላይ ስምምነት ማድረጋቸውን የዘገበው ሶከር ኢትዮጵያ ነው፡፡ በናኪ ሆቴል በተደረገው ዝግጅት የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ሙሉቀን ዓየሁ፣ የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሙሉቀን አዳነ (ዶ/ር)፣ የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ማኅበር ፕሬዚዳንቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር። በፕሮግራሙ ሁለቱን የክልሉ የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦችን ፋይናንስ በዘለቄታዊነት ለማጠናከር የታሰበን ፕሮጀክት አስመልክቶ ገለፃ እና ማብራሪያ የተደረገ ሲሆን በዋናነት ክለቦቹ ከመንግሥት በየዓመቱ ከሚበጀትላቸው በጀት ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ የታሰበ መሆኑ ተነግሯል። ምንም እንኳን የስምምነቱ ዋና ዓላማ ክለቦቹን ከመንግሥት ጥገኝነት ለማላቀቅ ቢሆንም በአጭር ጊዜ እቅድ ክለቦቹን ህዝባዊ ማድረግ፣ ደጋፊዎችን ያማከለ ስራ መስራት፣ የታዳጊ ማሰልጠኛ ማዕከላትን መገንባት እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን ያለመ መሆኑ ተነግሯል። ገንዘቡን የመሰብሰብ ኃላፊነት የየክለቦቹ ደጋፊ ማኅበራት የሚያከናውኑት መሆኑ የተነገረለት ይህ ፕሮጀክት ፋይናንሱን የተመለከተ የወጪ ጉዳዮች ክለቦቹ በሚያዋቅሯቸው ኮሚቴዎች እንደሚሰራ ተብራርቷል። በተለያዩ ፕሮግራሞች የሚሰበሰበውን ገንዘብ እኩል ለመካፈል የተስማሙት ሁለቱ ክለቦች በጋራ ደጋፊዎቻቸውን በማሰልጠን ገቢዎች ከየአቅጣጫው እንዲሰበሰቡ እንደሚያደርጉ ተገልፃል። ከስድስት ወር በላይ እንደፈጀበት የተገለፀው ፕሮጀክቱ የተለያዩ ጥናቶች እና ምክክሮች ሲደረጉበት እንደቆየ ተጠቁሟል። ከገለፃው በኋላ ሁለቱ ክለቦች በበላይ ጠባቂዎቻቸው አማካኝነት የስምምነት ፊርማ ያኖሩ ሲሆን የጋራ የባንክ አካውንት ከነገ ጀምሮ ተከፍቶ ስራዎች እንደሚጀመሩ በመጨረሻ ተገልጿል።አዲስ ዘመን ዛሬግንቦት 25/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11902
b3972abdaa58b3c6b27428ca44b086ca
ff38b82547e2d32215846698aa6128a9
የኦሊምፒክ ሳምንት ዝግጅት ቀጥሏል
 የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ «ኦሊምፒክ ለሰው ልጆች ክብር አንድነትና ሰላም» በሚል መሪ ሀሳብ ለሚያዘጋጀው የኦሊምፒክ ሳምንት የሚያደርገውን ዝግጅት ቀጥሏል። ኮሚቴው ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ያደረጉ የውጪ ዲፕሎማቶችና አምባሳደሮች ተሳታፊ እንዲሆኑ ከኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ምክክር አድርጓል። ዘመናዊው ኦሊምፒክ የተመሰረተበት ቀን በመጪው ሰኔ ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበር ሲሆን፤ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎችም በተለየ መልኩ ይከበራል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን በከፍተኛ ትኩረት በዓሉን ለማክበር ማቀዱን አስታውቋል። ከዕቅዶቹ መካከልም ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ያደረጉ የውጪ ዲፕሎማቶችና አምባሳደሮች እንዲሁም ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ከገዢው ፓርቲ ጋር የሚያገናኝ የእግር ኳስ ጨዋታ ነው። በዚህም መሰረት ኮሚሽኑ ከኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በመሆን ከኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በዝግጅቱ ዙሪያ መወያየታቸውን የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን በድረገጹ አስነብቧል። በምክክሩም ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፤ የኦሊምፒክ ሳምንት መርሀ ግብሮችን አድንቀዋል። በውጪው ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ያለውን ሰላምና ምቹ ሁኔታን፣ መቀራረብን፣ መደማመጥንና ሰላማዊ የስፖርት መድረክን የሚያስተምር በመሆኑ፤ በምን መልኩ መሄድ እንዳለበት በጋራ አጭር ሰነድ በማዘጋጀት ቀጣይ ተግባራቶች እንዲከናወኑ ከመግባባት ላይ ተደርሷል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እና የከተማዋ ስፖርት ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋይ፤ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተገኝተውም በገዢው ፓርቲ እና በተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል የእግር ኳስ ጨዋታ ለማካሄድ መታሰቡን ለሰብሳቢዋ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አብራርተዋል። ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳም የኦሊምፒክ ሳምንት መርሀ ግብሮችን አድንቀዋል። በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል መቀራረብን፣ መደማመጥንና የሰላማዊ የስፖርት መድረክን የሚያስተምር መሆኑን ጠቅሰዋል። በቀጣይም መርሃ ግብሩ በምን መልኩ መሄድ እንዳለበት በጋራ አጭር ሰነድ በማዘጋጀት ቀጣይ ተግባራቶች እንዲከናወኑ መድረክ በመፍጠር እንደሚሰሩም ጠቁመዋል። የኦሊምፒክ ሳምንቱ ከ23 – 30/ 2011 ዓ.ም ድረስ በሃገር ዓቀፍ ደረጃ፤ በአትሌቲክስ እና እግር ኳስ ውድድሮች፣ በኮንሰርት፣ በሲምፖዚየም እንዲሁም በአባላት ምዝገባ ይከበራል። አከባበሩን አስመልክቶም ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ ስፖርት ኮሚሽነሮች፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ፕሬዚዳንት፣ የክልል መንግስታት እና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የአፈጻጸምና አተገባበር ሰነድ ምክክር በቢሾፍቱ ከተማ መካሄዱ ይታወቃል። የኦሊምፒክ ሳምንቱ መከበር የኦሊምፒዝም መርህ እና እሴቶች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል። ከዚህ በተጓዳኝም በኦሊምፒክ ጽንሰ ሃሳብ መሰረት ሰላምን፣ አንድነትን፣ የህዝቦች መፈቃቀርና መተሳሰብን ለማጎልበት ይረዳል። በተጨማሪም በመጪው ዓመት ለሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ 200ሚሊዮን ብር የሚያስፈልግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም፤ ህብረተሰቡ ከተሳትፎው ጎን ለጎን ስፖርቱን የሚያግዝበትን ሁኔታም ያመቻቻል።አዲስ ዘመን ግንቦት 26/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11939
ad10b3da15fc6fa6553cde4f1da22374
8ae6b2ccb21de8c35d94226523bba21b
በሊጉ መርሃ ግብር ፋሲሎች ወደ ዋንጫው ሲጠጉ፤ ሲዳማዎች ሩጫቸውን አቀዝቅዘዋል
 እንደ ባለፈው ዓመት ሁሉ ዘንድሮም ሻምፒዮን የሚሆነውን ክለብ ቀደም ብሎ ማሳወቅ ያልቻለው የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቋጫውን ሊያገኝ ሶስት ጨዋታዎች ብቻ ቀርተውታል።የሊጉ 27ኛው ሳምንት መርሀ ግብርም በሳምንቱ የእረፍት ቀናት በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ሲካሄድም በተለይ ለዋንጫው የተሻለ እድል አላቸው የተባለላቸው ክለቦች ብርቱ ትንቅንቅ አድርገዋል።ያልተጠበቁ ውጤቶቹም የዋንጫ ትንቅንቅ ይበልጥ እንዲፋፋም አድርገውታል።በ27ኛው ሳምንት መርሀ ግብር ቅዳሜ ግንቦት 24 የተካሄደውና መከላከያን ከሲዳማ ቡና ያገናኘው ጨዋታም ያልተጠበቀ ውጤት የተመዘገበበት ሆኗል።በ24ተኛው ሳምንት መሪው መቀሌን ማሸነፍ የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች፤ በ25ተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ቡናን በሜዳና በደጋፊው ፊት 2ለ0 እንዲሁም ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ደርቢ ደቡብ ፖሊስን አራት ለሁለት ማሸነፋቸው ይታወሳል።ካለፉት ሶስት ጨዋታዎች ሁሉንም ማሸነፍ የቻሉት ሲዳማዎች፤ አንደኛና ሁለተኛ ከተቀመጡት ፋሲልና መቀሌ እኩል 49 ነጥብ በመያዝ በግብ ክፍያ ብቻ ተቀድመው ሶስተኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ የዋንጫ ጉዞአቸውን በእጅጉ ማሳመራቸውም አይዘነጋም።ከወቅታዊ የመከላከያ አቅምና አቋም አንፃር ጨዋታው ለሲዳማዎች ፈታኝ እንደማይሆን ቢገመትም፤ ሜዳ ላይ የሆነው ግን የተገላቢጦሽ ነው። ባለሜዳዎቹ ሲዳማ ላይ አራት ግቦችን ሲያስቆጥሩ አንድ ግብ ብቻ ተቆጥሮባቸዋል።ጨዋታውን አሸንፈው ቢሆን ኖሮ ቢያንስ ለ24 ሰዓት ሊጉን በቀዳሚነት መምራት የሚያስችላቸውን አጋጣሚ አሳልፈው የሰጡት ሲዳማዎች፤ያጧቸው ሶስት እጅ ወሳኝ ነጥቦች በዋንጫ ትንቅንቅ ላይ ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው ታምኖበታል። ሲዳማዎች በቀጣይ በዋንጫ ትንቅንቅ ሻምፒዮን ለመሆን የግድ ቀሪ ጨዋታዎችን ሙሉ ለሙሉ ማሸነፍና የየተከታዮቻቸውን መሸነፍ መጠበቅ ግድ የሚላቸው ሆኗል። ሲዳማዎች በአጠቃይ ድሬዳዋና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲና ደደቢትን የሚፋለሙ ይሆናል።በጨዋታው ወቅታዊ አቋም እያደር መዋዠቅና በውጤት ቀውስ የመውረድ አደጋ እንደተጋረጠበት መከላከያ በ26ተኛ ሳምንት መርሃ ግብር በስሁል ሽረ ከደረሰበት ሽንፈት አገግሞ ሲዳማ ላይ ያስመዘገበው ውጤትም ከወራጅ ቀጣናው እንዲወጣ አስችሎታል።ጦሩ በደረጃ ሰንጠረዝ፤ በ29 ነጥብ 13ተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ተሸናፊው ሲዳማ ቡና በአንፃሩ በ49 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃው ላይ ተቀምጧል።በአማራ ደርቢ ፋሲል ከነማን ከባህር ዳር ከተማ አገናኝቷል።ባለሜዳዎቹ ፋሲሎች፤ በ25ተኛ ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር የአምናውን የሊጉ ሻምፒዮን ጅማ አባጅፋርን 6 ለ1 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ሲረከቡም በ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ወደ ሶዶ አቅንተው በወላይታ ዲቻ ያልተጠበቀ የ2ለ1 ሽንፈትን ማስተናገዳቸው ይታወሳል።በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም የተካሄደው የሁለቱ ክለቦች ፍልሚያም፤ ለዋንጫ እንደሚፋለም ክለብ ድንቅና ወጥ አቋም ያሳዩት ፋሲሎች አራት ለባዶ ማሸነፍ ችለዋል።ከውጤቱ ባገኙት ውድ ሶስት ነጥብ የሊጉ መሪነታቸውን አስጥብቀዋል። የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውሰድ በመንደርደር ላይ ያሉት አፄዎቹ፤ይህን ታሪክ ለመስራት ደግሞ ከፊታቸው ከቅዱስ ጊዮርጊስ፤አዳማና ስሁል ሽረ ጋር ብርቱ ፍልሚያ ይጠብቃቸዋል።የጨዋታውን ተሸናፊ ባህር ዳርቻዎች በአንፃሩ በመጀመሪያው የሊጉ መርሃ ግብር ድንቅ ብቃት ማሳየት ቢችሉም፤በሁለተኛው የሊጉ መርሃ ግብር መዳከማቸውን የሚያስመሰክር ውጤትን አስመልክተዋል።የጣና ሞገዶቹን ያለፉት ሁለት ጨዋታዎች ስንመለከት እንኳን በ25ተኛ ሳምንት በሊጉ የደረጃ ግርጌ ላይ በሚገኘው ደደቢት የ 5 ለ2 ያልተጠበቀ ሽንፈት ሲደርስባቸው ከወልዋሎጋር ነጥብ ተጋርተዋል።በየደረጃው ሰንጠረዥም በ37ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።ሌላኛው ተጠባቂ የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ቡናን ከመቀሌ 70 እንደርታ አገናኝቷል። ይሁንና የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከጸጥታ ጋር በተገናኘ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ተደርጓል። ጨዋታው ባለመካሄዱ መቀሌ በ49 ነጥብ በነበረበት ሁለተኛነት ሲቀጥል፤ ኢትዮጵያ ቡና በ34ነጥብ አስራ አንደኛ ደረጃን ይዟል። በ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብርም ወደ ጅማ አቅንተው፤2ለ 2 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተው የተመለሱት መቀሌዎች፤የፋሲል መሸነፍ መሪ ለመሆን የሚያግዛቸው ቢሆንም ከጨዋታው አንድ ነጥብ ብቻ ማግኘታቸውን ተከትሎም በግብ ክፍያ ተበልጠው በነበሩበት የሁለተኝነት ደረጃ ለመቀጠል መገደዳቸው ይታወሳል።በተለይ በሁለተኛ የሊጉ መርሃ ግብር በሌሎች ውጤት ላይ ሳይመሰረት ሻምፒዮን ሊያደርጉት የሚችሉ ወሳኝ ጨዋታዎች ላይ ነጥብ የጣለው መቀሌ፤ የሊጉን ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውሰድ ከፊቱ፤ከድሬዳዋ ከነማ፣ ደቡብ ፖሊስ፣ መከላከያ ጋር የሚያደርገውን ፍልሚያ ማሸነፍ የግድ ይለዋል።ይህም በመሪው ፋሲል ነጥብ ማጣት ላይ ተጨማሪ መሰረቱን የሚያደርግ ይሆናል።ሌላኛው መርሃ ግብር ደደቢትን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሲያገናኝ ጨዋታው በፈረሰኞቹ የሶስት ለሁለት አሸናፊነት ፍፃሜውን አግኝቷል።በ23ተኛ ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብርም በሸገር ደርቢ ከኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም በ24ተኛው ሳምንት ከደቡብ ፖሊስ እንዲሁም በቀጣይ ከመከላከያ ጋር ነጥብ የተጋሩት ፈረሰኞቹ፤በ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብርም በሜዳና ደጋፊያቸው ፊት ድሬዳዋን አስተናግደው 2ለ0 ማሸነፋቸው ይታወሳል።ደደቢቶች በአንፃሩ በ25ተኛው ሳምንት መቀሌ ላይ በትግራይ ስታዲየም ባህር ዳርን ሳይጠበቁ 5ለ2 ቢያሸንፉም 26ኛ ሳምንት መርሃ ግብርም በአዳማ ከተማ አራት ለባዶ ተሸንፈው በቀጣዩ ዓመት የሊጉ ተፋላሚ እንደማይሆኑ ማረጋገጣቸው ይታወሳል።የጨዋታው አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአሁኑ ወቅት ከመሪው ፋሲል በስድስት ነጥብ ዝቅ ብሎ በ46 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።።በ27ኛው ሳምንት መርሀ ግብር የተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ወላይታ ዲቻን ከጂማ አባጅፋር ያገናኘው ነው። ባሳልፈነው ሳምንት የሊጉን መሪ ፋሲል ሁለት ለአንድ ያሸነፉት ዲቻዎች፤ በዚህ ሳምንት ደግሞ የአምናውን የሊጉን ሻምፒዮንበፎርፌ ማሸነፍ ችለዋል፡፡ የወራጅ ስጋት ተጋርጦባቸው የነበሩት ዲቻዎች በሊጉ ሁለተኛ አጋማሽ ባሳዩት ድንቅ አቋም በፍጥነት ከወራጅ ቀጣና ስጋት መላቀቅ ችለዋል።በአሁኑ ወቅትም በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ነጥባቸውን ወደ 34 ከፍ በማድረግ በደረጃ ሰንጠረዡ 12ተኛ ላይ ተቀምጠዋል።የአምናው ሻምፒዮና ጅማ አባጅፋር በአንፃሩ በ40 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።ሌላኛው የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዪኒቨርሲቲን ከአዳማ ከተማ አገናኝቷል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታም በአንድ አቻ ውጤት ተጠናቋል።26ኛ ሳምንት መርሃ ግብርም በሜዳውና በደጋፊው ፊት ደደቢትን አስተናግዶ 4ለ0 ማሸነፋቸው ተከትሎ፤ ከወራጅ ቀጣናው ስጋት መለቀቁ አይዘነጋም።ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች በአንፃሩ፤ባሳልፈነው ሳምንት ወደ ባህር ዳር አቅነተው ካለምንም ግብ ነጥብ ተጋርተው መመለሳቸው ይታወሳል።በደረጃ ሰንጠረዙ አዳማ በ34 ነጥብ አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ከቢጫ ሰርጓጆቹ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች በአንፃሩ፤በ37 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ሌላኛው የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር ደቡብ ፖሊስ ከሃዋሳ ከተማ አገናኝቷል።በደቡብ ደርቢ በሁለቱ  ክለቦች መካከል የተካሄደው ጨዋታም በባለሜዳው ሶስት ለሁለት አሸናፊነት ተጠናቋል።በ25ተኛው ሳምንት መርሃ ግብር መቀሌን 1ለ0 ያሸነፉት ሃዋሳዎች፣ 26ኛ ሳምንት መርሃ ግብርም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ካለምንም ግብ ነጥብ መጋረታቸው ይታወሳል።በ26ስተኛ ሳምንት በሲዳማ ቡና የተሸነፉት ደቡብ ፖሊሶች በአንፃሩ በዚህ ሳምንት ሃዋሳ ምርታታቸውን ተከትሎ ከሊጉ ወራጅ ቀጣና ለማውጣት የሚያደርጉትን ጥረት የሚያግዝ ውጤት አግኝተዋል።ደቡብ ፖሊሶች አሁን ላይ በ28 ነጥብ በሊጉ 14 ተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ፤ ሃዋሳዎች በአንፃሩ በ38 ነጥብ 8ተኛ ደረጃ ይዘዋል።ድሬዳዋን ከስሁል ሽረ ያገናኘውም ሌላኛው የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር ነው። የሁለቱ ከለቦች ጨዋታም በአንድ አቻ ውጤት ተጠናቋል።በሊጉ ሁለተኛ ዙር ድንቅ አቋምና ውጤት በማሳየት ደረጃቸውን በእጅጉ በማሻሻል ከወራጅ ቀጣናው ክለቦች ተርታ ስማቸውን ለማስወጣት እየጣሩ የሚገኙት ስሑል ሽረዎች፤በ26ተኛ ሳምንት መርሃ ግብር መከላከያን አስተናግደው 2ለ1 ማሸነፋቸው ይታወሳል።ብርቱካናማዎቹ ድሬዳዋዎች በአንፃሩ፤በ26ተኛ ሳምንት መርሃ ግብር አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ለባዶ መሸነፋቸው ይታወሳል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ፤ ከወራጅ ቀጣናው የሚላቀቁበትን እድል ማግኘት ያልቻሉት ስሁሎች፤ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዝ በ27 ነጥብ 15ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ድሬዳዋዎች በአንፃሩ፤ በ35 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዘዋል።የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ፋሲል ከነማ ሃምሳ ሁለት ነጥቦች በመሰብሰብ በቀዳሚነት ይመራል።መቀሌ ሰባ እንደርታና ሲዳማ ቡናም በተመሳሳይ አርባ ዘጠኝ ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበልጠው ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነዋል።የሊጉን ወራጅ ቀጣና ስንመለከት፤ደቡብ ፖሊስ በሃያ ስምንት ነጥቦች አስራ አራተኛ፤ስሁል ሽረ በሃያ ሰባት ነጥቦች አስራ አምስተኛ እንዲሁም ደደቢት በአስር ሶስት ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘዋል።የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ፉክክር የመቀሌው አማኑኤል ገብረሚካኤልና የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በአስራ አምስት ግቦች አንደኛ ሁለተኛ ሲሆኑ የፋሲሉ ሙጂብ ቃሲም በአስራ አራት ግቦች ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 27/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11976
f32df55938f5b066760efbafd36d8be8
3916c5b34bf8d02ca6aae021d0b306f3
የቀያዮቹ ስኬት ቁልፍ
ሊቨርፑሎች ከምንጊዜውም በላይ ዘንድሮ በግል ሚዛን የሚለካ፤ በግል መነጽር የሚታይ፤ በግል አይምሮ የሚተረጎም ሳይሆን ማንኛውንምና ሁሉንም የሚያስማማ ለውጥ አሳይተዋል። የቀያዮቹ ተጫዋቾች፤በታላቅ ተመስጦ የሚመለከቱት፤በታላቅ ንፃሬ በብዙዎች የሚደነቅ ድንቅ ውበት ያለው እግር ኳስ መጫወትና ማሳየት ችለዋል። እያንዳንዱን ጨዋታ አሸንፈው ለመውጣት ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ የሚያደርጉት በአንፊልዱ ሜዳ ከሚታዩት ደማቁ ኮከቦችም መካከል፤ቨርጂል ቫንዳይክ የመከላከል ስራውን በትጋት ሲወጣ በርካቶች«ግብፃዊው ሜሲ»በሚል ቅፅል የሚጠሩት መሃመድ ሳላህ የግብ ማምራት ሀላፊነቱን በአግባቡ ተወጥቷል።አሊሰን ቤከርም የቀያዮቹን የግብ ክልል በንቃት ጠብቋል።በ2016 ከሳውዝሃፕተን ለቆ ቀዮቹን የተቀላቀለው ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ የተቃራኒ ተከላካዮችን ሲያስጨንቅ ብሎም ግቦችን ሲያስቆጥር ጆርዳን ሃንደርሰን የመሃል ሜዳ ክልሉን ሚዛን በመጠበቅ የክለቡን የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ሲያቀላጥፍ ታይቷል።ከሊቨርፑሎች የዘንድሮ ውጤታማ ጉዞም ጀርባ ታዲያ እ ኤ አ በ 2015 ማገባደጃ በመርሲሳይድ ደርቢ ሊቨርፑል ከኤቨርተን 1 ለ 1መለያየቱን ተከትሎ አንፊልድን የተሰናበቱት አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ እግር ተክተው ቀያዮቹን ማሰልጠን የጀመሩት ጀርመናዊ አሰልጣኝ ጀርገን ክሎፕ ዋነኛውን ሚና ይወስዳሉ። ፈጣን መልሶ ማጥቃት የታጀበ የኳስ ፍልስፍናን የሚከተሉት የርገን ክሎፕ ሊቨርፑሎችን ከመምራታቸው በፊት ቦርሲያ ዶርትሙንድን ከ2008 እስከ 2015 እንዲሁም ሌላኛውን የጀርመን ክለብ ሜንዝን ከ1989 እስከ 2001 አሰልጥነዋል።ክሎፕ በቡንደስሊጋው በነበራቸው ቆይታ በተለይ ከቢጫማዎቹ ጋር ድንቅ ዓመታትን ያሳለፉ ሲሆን ፕሪሚየር ሊጉን ከተቀላቀሉና ቀዮቹን ከተረከቡ ወዲህም በአንፊልሮድ ሜዳ የለውጥ ድባብ ገኖ መታያት ጀምሯል።በተለይ ዘንድሮ ድንቁን ሊቨርፑል የተመለከቱት አንፊልዳውያንም ለዚህ ያበቃን፣በውጤታማው የለውጥ ጎዳና የወሰደን ሹፌር እርሱ ነው ሲሉ አሰልጣኝ እውቅና ይሰጡታል።የአንፊልድን ድባብ ለተጋጣሚ ቡድኖች ሲኦል የሚያደርጉት ታማኞቹ የክለቡ ደጋፊዎችም ለአሰልጣኙ ያላቸው ክብርና ፍቅር ከሁሉ የተለዩ ሆኖ ታይቷል።አሰልጣኙ ጨዋታ ከማንበብ ብቃቱ በተጓዳኝ አልፎ አልፎ በሜዳ የሚያሳያቸው አስቂኝና አወዛጋቢ ተግባራት የመዝናናታቸው ብቻም ሳይሆን የፍቅርና ስስታቸው ምክንያት ስለመሆኑም ያምናሉ።ተጫዋቾቹም ቢሆኑ በአሰልጣኙ የጨዋታ ፍልስፍና መማረካቸውን ብቻም ሳይሆን እያሳቀ የሚገስፅ እርሱን ብቻ ማየታቸውን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይመሰክራሉ።አሰልጣኙ የርገን ክሎፕም ለ29 አመት የዘለቀውን የክለቡ የፕሪምየር ሊግ የዋንጫ ጥማት ፍጻሜ ለማበጀት ዘንድሮ ከጫፍ ቢደርሱም በአንድ ነጥብ ተበልጠው ዋንጫውን አጥተዋል።ይሁንና በፕሪሚየር ሊጉ ያሳዩት ድንቅ ብቃት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግም ማሳየት ችለዋል። የአውሮፓው መድረክ ተሳትፎአቸው ግን እንደፕሪሚየር ሊጉ አመድ አፋሽ አላደረጋቸውም።ባሳልፈነው ዓመት በአውሮፓው ታላቅ መድረክ ለፍፃሜ ደርሰው በሎስ ፕላንኮዎቹ የተሸነፉት ቀያዮቹ፤ የዘንድሮውን የሃያላን ክለቦች ፍልሚያ ከቶትንሃም ጋር ለፍፃሜ በመድረስ በሁለት ለባዶ በድል አጠናቀዋል፡፡የዘንድሮውን ሲጨምር በአጠቃላይ ለስድስተኛ ጊዜ የአውሮፓ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ከፍ አድርገው መሳም ችለዋል።ምንም እንኳን ክሎፕ ብቻውን ለዚህ ስኬት ምክንያት ነው ብሎ መደምደም ባይቻልም እንደ መሪ ከደጋፊውና ከተጫዋቾቹ በላይ የእርሱ ሚና ግዙፍ እንደነበር በርካቶች መስክረዋል። የቀያዮቹ ተጫዋቾቹም «ለስኬት የሚያበቁ ድንቅ መመሪያዎችን ሰጥቶናል፤ ህብረታችን ጠንካራ እንዲሆን አንድነታችን እንዲያስፈራ በማድረግ የእርሱ ሚና ገናና ነው ሲሉ ባለውለታቸውንና የስኬታቸውን ቁልፍ አሞካሽተውታል።አዲስ ዘመን ግንቦት 27/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11979
7829605aed5717455527eb87508ed1aa
ea9ee4c32daedd909149824d13b5ab5d
ወርቅ ሳይሆን ልብ ማሸነፍ
 ከዓለም እስከ አህጉር፣ ከአህጉር እስከ አገር፣ ከአገር እስከ መንደር ከዚያም ማህበረሰብ እስከ ግለሰብ፣ በስፖርት ልቡ ያልተሳበና በፍቅሩ ያልተንበረከከ የለም።ስፖርት ሰላም ፣ፍቅር ፣የአብሮነትና የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የወንድማማችነት ልዩ መገለጫ ነው። ስፖርት ዘር፣ሃይማኖት፣ ፆታና ቀለምን አይለይም።ሁለት የተለያዩ አገራት ያወዳጃል። በአገር ፍቅር ስሜት ያስተሳስራል።ያፋቅራል።በእርግጥ አንዳንዶች ውጤትን ከስፖርታዊ ጨዋነት አስበልጠው የግል ጥቅማቸውን ሲያስቀድሙ ይስተዋላል። ከዚህ በአንፃሩ የግል ፍላጎታቸውን ችላ በማለት በስፖርታዊ ስነ ምግባር የታነፁ መኖራቸው የማይካድ ሃቅ ነው።በአትሌቲክሱ የውድድር ፍልሚያ ኬንያውያን በተለያዩ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ውድድሮች ላይ በርካታ ወገኖችን አስደንቀዋል።አስጭብጭበዋል።በውድድር አሸናፊ ሆነው የታዩትን ያህልም ከአንዴም ሁለት ጊዜ በስፖርታዊ ጨዋነትና ሰብዓዊነት ተግባር የታነፁ ስለመሆናቸውም አስመስክረው የሚሊየኖችን ልብ ሲያሸንፉ ታይተዋል።።የምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር አትሌት ከሰሞኑም ይህን በስፖርታዊ ጨዋነት መርህ የታነፀ ሰብዓዊነት ተግባር ደግሞ አሳይቷል።ትዕይንቱ የተከሰተው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር የነሃስ ሜዳሊያ በሚሰጠውና ከቀናት በፊት በተካሄደው የናይይጄሪያ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ነው።የታሪኩ ባለቤት ሲሞን ቺፕሮት ይባላል።ኬንያዊ የረጅም ሩጫ አትሌት ነው።በዚህ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ሲሳተፍ አራተኛው ሲሆን፣ ከሶስት ዓመት በፊት ደግሞ ባለድል መሆን ችሏል።ባሳለፍነው አመት ደግሞ ሁለተኛ ሆኖ ጨርሷል።ክስተቱ እንዲህ ነው። ሲሞን ቼፐሮት የዘንድሮውን ውድድር እየመራ ለመጨረስ የተወሰኑ ሜትሮች ብቻ ቀርተውታል።ውድድሩን ለሁለተኛ ጊዜ በማሸነፍ የመጀመሪያው የሚሆንበትን ታሪክ ለመፃፍ ማንም ሊያቆመው አይቻለውም።ይሁንና በዚህ ቅፅበት ሌላኛው የአገሩ ልጅና ብርቱ ተቀናቃኙ የሆነው ኬኔት ኪፕኬሞይ ድንገት ሲዝለፈለፍ ይመለከታል።ክስተቱን ያስተዋለው ሲሞን ቼፕሮት ግን የአገሩን ልጅ ጥሎት ለመግባት አልወሰነም።ውድድሩን አሸንፎ አንደኛ የመባል ስሜቱን አላዳመጠም።ውድድሩን ለሁለተኛ ጊዜ በማሸነፍ የመጀመሪያው የሚሆንበት ታሪክ ለመጻፍ አልቸኮለም።አትሌቱ የተፎካካሪውን ውድቀት እንደ መልካም አጋጣሚ ከመጠቀም ይልቅ ብዙዎቹን ባስገረመ መልኩ ሩጫውን በማቋረጥ ጓደኛውን ከወደቀበት ደግፎ አንስቶ ልባዊ ወንድምነቱን በማሳየት በርካታ ወገኖችን አስደምሟል። ሁለቱ አትሌቶችም ቀስ ብለው በመሮጥ ውድድሩን 15ኛ እና 16ኛ ሆነው የፈፀሙ ሲሆን አንደኛ መውጣት የሚችለው ሲሞንም ተሸንፏል።አትሌቱ ከፊቱ የሚጠብቀውን የወርቅ ሜዳሊያና የአሸናፊነቱን ሽልማት ገንዘቡን በመተውና ይህ ሁሉ ከሰው እንደሚያንስ በማሳብ የፈፀመው መልካም ተግባር በሚሊየን የሚቆጠሩ ልቦችን ማሸናፍ ችሏል።የወርቅ ሜዳሊያውን ትቶ ከወርቅ በላይ የሆነ ጀብዱ በመፈፀም፤ ከወርቅ ሜዳሊያው ይልቅ ሰብአዊነት እንደሚልቅ ለመላው ለዓለም   አሳይቷል።ሜዳሊያ ሳይሆን ልብ ያሸነፈውና በውድድሩ ስፍራ ሆነው ውድድሩን የተመለከቱትን በሺዎች የሚቆጠሩ ብቻም ሳይሆን በአህጉር ዓቀፍ ደረጃ በቴሌቪዥን መስኮት የሚመለከቱትን ያስደነቀ አትሌት ፤ማሸነፍ ማለት ሁሌ አንደኛ መውጣት ማለት አይደለም፤ሁሌ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኛት አይደለም። አንዳንዴ ተሸንፈህ አሸናፊ ትሆናለህ፣ መጨረሻ ወጥተህ ክብርን ጀግንነትን ትጎናፀፋለህ አሰኝቷል።‹‹በአንድ ወቅት አባቴ፤ በመንገድህ ላይ የታመመ ሰው ስትመለከት አልፈኸው ጉዞህን አትቀጥል፤ ይልቅ እርዳው፤ ብሎኝ ነበር፤ የአገሬውን ልጅ ወድቆ ስመለከተው ይህ ወደ አእምሮዬ መጣ፤ እናም ለራሴ ሳላስብ ልረዳው ወሰንኩ ››ያለው አትሌቱ፤ መሰል ተግባሩም ለመጪው ትውልድ አርእያነት ያለው ስለመሆኑ ተናግሯል።የአትሌቱ ተግባርም የወርቅ ሜዳሊያ ከማግኘት ይልቅ ወርቃማ ልብ መያዝ ይበልጥ ያነግሳልና ይህም እውነተኛው የስፖርት ጽንሰ ሃሳብ መገለጫ ነው አሰኝቷል። በዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበር የናይጄሪያ ተወካይ ማይክ ልቴሟግቦር አትሌቱን ‹፣ጀግናችን››ሲሉ አሞካሽተውታል፡፡ለፈፀመው የሰብዓዊነት አኩሪ ገድልም አንድ ሚሊየን ሽልንግ አበርክተውለታል።የቺፕሮትን ተግባር በማወደስ፤ ተረጂው አትሌት በበኩሉ፤ ‹‹ሁሉም አትሌት ይህን መሰል ተግባር አይፈፅምም፤ሲሞን መልካም ሰው ነው፤ በውድድሩ እኔን ለማርዳት ያሰው መልካምነትም እጅጉን አስድንቆኛል›› ሲል ተደምጧል። አሸንፎ ሜዳሊያውን ከወሰደው ኢትዮጵያዊ በላይ ሲሞን ጀግና ተብሎ ዘላለማዊ ስምና ዝናን አትርፏል።አዲስ ዘመን ግንቦት 27/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11981
02b21004538a5faf81b7c28639575139
ca4c9543e9f594143f31bf322d8486c1
‹‹ ቁስልን ማመርቀዝ እና አመርቅዞ እንዳይድን ማድረግ የታሪክ አላማ አይደለም ›› – የታሪክ መምህር እና ደራሲ ታዬ ቦጋለ
አዲስ አበባ :- ቁስልን መጫር፣ ጭሮ መቧጨር፣ ቧጭሮ ማቁሰል፣ አቁስሎ ማመርቀዝ እና አመርቅዞ እንዳይድን ማድረግ የታሪክ አላማ አይደለም ሲሉ የታሪክ መምህር እና ደራሲ ታዬ ቦጋለ ገለጹ። ህወሓት/ ትህነግ ስልጣን ዘመኑን ለማርዘም አማራና ኦሮሞን እንደማህበረሰብ ማጋጨትን እንደ አንድ ስልት አድርጎ ይዞት እንደነበረም አስታወቁ ። የታሪክ መምህር እና ደራሲ ታዬ ቦጋለ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ቁስልን መጫር፣ ጭሮ መቧጨር፣ ቧጭሮ ማቁሰል፣ አቁስሎ ማመርቀዝ እና አመርቅዞ እንዳይድን ማድረግ የታሪክ አላማ አይደለም፤ የታሪክ ትርክቶች ከታሪክ ዓላማ ውጪ ከሆኑ የታሪክ ትርክቶች ሳይሆኑ የፖለቲካ ፈጠራ ናቸው ብለዋል።የፖለቲካ ፈጠራ የታሪክ ትርክቶቹ መነሻቸው አገር ማፍረስ እና በማህበረሰብ መካከል ግጭት መፍጠር እንጂ ለአሁኑ ትውልድ ዳቦ አይሆኑም ያሉት አቶ ታዬ ቦጋለ፤ የታሪክ ትምህርት ዓላማው ያለፈውን ለማጥራት፣ ዛሬን በጥሩ መሰረት ላይ ለማነጽ እና ነገን በብሩህ ሁኔታ ለመገንባት መሆኑንም ተናግረዋል። “ህወሓት/ ትህነግ ሲቋቋም በጥቂቶች የተመሰረተው ቡድን ነው። ይሄ ስርዓት ውስብስብ ባህሪያት ያሉት ነው። በፖለቲካ ቋንቋ መግለጽ ያስቸግራል። አንደኛው መለስ ዜናዊ በነበረበት ረጅም ጊዜ በአንድ በኩል ሞኖክራሲ ነበር። ሞኖክራሲ ማለት የአንድ ሰው አምባገነን አገዛዝ ነው። የኢኮኖሚ ባህሪያቱን ስንመለከት ደግሞ አሪስቶክራሲ (ኦሊጋርኪ) ነው። የጥቂቶች የበላይነት የሚንጸባረቅበት ስርዓት ነው። ይሄ ስርዓት በባህሪው መቆየት እንደማይችል፣ አምባገነን እንደሆነ፣ በፍርሃት የተከበበ ስሜት ይዞ ስለተነሳ እንዲቆም አማራና ኦሮሞን እንደማህበረሰብ ማጋጨትን አንድ ስልት አድርጎ ይዞ ነበር” ብለዋል ። አማራውን ትምክህተኛ፣ ኦሮሞን ጠባብ፣ ደቡቡን የስብዕና መሸርሸር ያለበት፣ አርብቶ አደር አካባቢ፤ ሱማሌ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ሐረሪን ደግሞ አብዮታዊ ዴሞክራሲን ለመሸከም የሚያስችል ቁመና የሌላቸው አጋር ሆነው የሚቀጥሉ በማድረግ ስርዓቱ እንዲቀጥል ማድረጉን አመልክተዋል። ምሁራንን የቀለም አብዮተኞች፣ የሻዕቢያ ተላላኪዎች፣ የግብጽ ተላላኪዎች፣ ወጣቱን የጎዳና ላይ ነውጠኞች በሚል እያንዳንዱ ታፔላ ተለጥፎበት እንደነበረም አስታውሰዋል። ዛሬም የምናየው የግጭት ምንጭ ይሄንን ነው። ሲዳማን ከወላይታ ጋር፣ ስልጢን ከጉራጌ ጋር ከመጀመሪያው ከመለያየት ጀምሮ ሰዎች አብረው ተያይዘው እንዳያድጉ በማድረግ እስከ ሰፈር ድረስ የከፋፍሎ ግዛት ስልት እንደነበረው ገልጸዋል። ህወሓት በሰፊው ስልጣን ላይ እንድትቆይ በአለም ታሪክ ውስጥ ተፈጽመው የማይታወቁ ግን አስከፊ ወንጀሎች ተፈጽመዋል ሲሉም ተናግረዋል። ለምሳሌ ህወሓት የዘር ጭፍጨፋ አድርጓል። መንግስታዊ ሽብርተ ኝነትን ፈጽሟል። የተለያዩ ማህበረሰቦችን የማውረድ ነገር ተጠቅሟል። ከፋፍሎ መግዛትን አድርጓል። ያልተገቡ ጨረታዎች፣ የባንክ ብድሮች፣ የተደራጁ ዘረፋዎችን አካሂደዋል ሲሉም ከሰዋል። በማረሚያ ቤት በሰው ልጅ ላይ ሊፈጸም ይችላል ብለን የማናስበው ጥፍር መንቀል፣ የወንድ ብልት ላይ ኮዳ ማንጠልጠል፣ በሴቶች ማህጸን ብረት መክተት፣ በወንዶች ብልት ጫፍ ብረት መክተት፣ ገልብጦ መግረፍና የመሳሰሉትን እጅግ አስከፊ ነገሮችን ማድረጉንም ገልጸዋል። የኦሮሞ ፖለቲከኞችም ሁለቱን ህዝቦች በማጋጨት በግርግር ወደ ስልጣን መምጣት እንደሚፈልጉ አመልክ ተው፣ ግብጽ የአባይን አጠቃላይ ግድብና የአባይ ተጠቃሚነታችንን ማፍረስ የምትችለው ሁለቱን በማጋጨት እንደሆነም ጠቁመዋል ። ወደ አናርኪ ከማምራት በውይይት የአመለካከት ለውጥ ማምጣት የመጀመሪያ መፍትሄ ማድረግ ጠቃሚ መሆኑንም አመልክተዋል። የወንድማማችነት ‹‹እርታ ልርታ›› ስሜት በሚገባ መዳበር ይገባዋልም ብለዋል። “ለችግሮቻችን መፍትሄ የሚሆነው አባቶቻችን የኖሩ በትን ፍቅር መመለስ ነው። በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብሎ መወያየት ነው። የኦሮሞ ጥቅም የት ጋር ነው የተነካው? የአማራ ጥቅም የት ጋር ነው የተጎዳው? የሶማሌ ጥቅም የት ጋር ነው ያነሰው? የሌላው የት ነው እንጀራው በአንድ በኩል አይወፍር ብሎ ቁጭ ብሎ በሰከነ መንገድ መወያየት ነው” ብለዋል ።አዲስ ዘመን ሐምሌ 20/2012 ዘላለም ግዛው
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36096
6462ccf811609ac33952c06dcef7bcd1
f238c2c4eadfd61dedb60ba691f0b5c3
የዛሬውን ፍፃሜ ጨዋታ በዓምላክ ተሰማ ይመራዋል
ዛሬ የ2018-19 ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ፍፃሜውን ሲያገኝ በግብፁ ዛማሌክ እና የሞሮኮው በርካኔ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ በዓምላክ ተሰማ እንዲመራ በካፍ መመደቡን የሶከር ኢትዮጵያ ድረ ገፅ አስነብቧል። ከሳምንት በፊት በሞሮኮ በተደረገው የመጀመርያ ጨዋታ ባለሜዳው አር ኤስ በርካኔ በመጨረሻ ደቂቃ ኮጆ ላባ ባስቆጠረው ጎል ማሸነፍ የቻለ ሲሆን የመልሱ ጨዋታ በአሌክሳንድሪያው ቦርግ አል አረብ ስታድየም ዛሬ ምሽት ይካሄዳል። ይህን ጨዋታም ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማ በመሐል ዳኝነት ይመራዋል። ደቡብ አፍሪካዊው ዛኪይ ሲዎሊ እና የሴኔጋሉ አልሀጂ ማሊክ በረዳትነት ሲመሩ ቱኒዚያዊው ሳዶክ ሴልሚ በአራተኛ ዳኝነት ተመድቧል። በሞሮኮ የተካሄደውን የመጀመርያውን ጨዋታ የመራው ጃኒ ሲክዌዜ ደግሞ ከሱዳናዊው ዋሊድ አህመድ እና ሴኔጋላዊው ጋብሬል ካማራ ጋር በመሆን የVAR ዳኝነቱን ይመራል።አዲስ ዘመን ግንቦት 18/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11507
7f75aa875d26b0379c0b6352f8d0afdb
8664eeb073fe58019f706a462bd08ec1
ዛሬም ያልተፈታው የከተማችን ትራንስፖርት ችግር
 ክረምቱ ጨክኗል ጠዋት ማታ የሚጥለው ዶፍ ለመንገደኞች፣ በተለይ ትራንስፖርት ለሚጠቀሙ ወገኖች አዳጋች መሆን ጀምሯል፤ ወቅታዊው የኮቪድ 19 ስጋት ደግሞ እንደቀድሞው አማራጭ የሚሰጥ አልሆነም። በርካቶች ማልደው በሚቆሙበት ጎዳና ብቅ የሚል ታክሲና አውቶቡስን እየናፈቁ ያንጋጥጣሉ፤ መጨረሻቸውን ለማግኘት በሚያታክቱ ረጃጅም ሰልፎች የተደረደሩ ተሳፋሪዎች ያለመታከት ሰዓታትን ቆመው ይገፋሉ በሰልፉ መሀል ነፍሰጡሮች፣ ህፃናት የያዙ እናቶች ፣ አቅመ ደካማዎችና ሌሎችም ይታያሉ። ተራ ጠብቀው የሚደርሱ አንዳንድ ታክሲዎች እልፍ ሆነው ከተደረደሩት ጥቂት ያህሉን ብቻ ዘግነው እብስ ይላሉ፤ ቀጣዩን የሚጠብቁ ሌሎች ደግሞ በቀደሟቸው ተሳፋሪዎች ዕድለኝነት እየጎመጁ የራሳቸውን ዕጣ ፈንታ ይናፍቃሉ፡፡ ታክሲዎች እንደታሰበው በጊዜው አይደርሱም ይሄኔ በዳመናው መክበድ የሰጉ ሰልፈኞቹ ተስፋ ይቆር ጣሉ፣ ከፊት ያለው ሳይሸኝ ከኋላ በኩል ያለው ሰልፍ በእጥፍ ይጨምራል። አቶ አሰፋ ቢተው የግል ድርጅት ተቀጣሪ ናቸው። በርካቶች ቤት በዋሉበት በዚህ ዘመን እሳቸው ይህን ማድረግ አልተቻላቸውም፤ የሥራ ባህሪያቸው ከቤት የሚያውል አይደለም። ይህ እንኳን ባይሆን እጃቸውን ናፍቀው ለሚያድሩ ልጆቻቸው የዕለት ዳቦ ሊያጎርሱ ግድ ይላል። በሚኖሩበት የቱሉዲምቱ አካባቢ በርካታ አውቶቡስና ታክሲዎች አገልግሎት ይሰጣሉ። እሳቸው አብዛኛውን ጊዜ በሚጠቀሙበት የታክሲ ትራንስፖርትም በረጃጅም ሰልፎች ላይ መቆምን ልምድ አድርገዋል። አሰፋ ይህ እንዳይሆን ማልደው ይወጣሉ እንዳሰቡት ሆኖ ግን ከችግሩ ማምለጥ አይቻላቸውም፤ ጠዋት ማታ በረጃጅም ሰልፎች ታድመው ከቤት ወደ ሥራ፣ ከሥራም ወደ ቤት ለመመላለሰ ተገደ ዋል። የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ በኋላ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። በርካታ ሠራተኞችም ቤት ሆነው ሥራዎቻቸውን እንዲከውኑ ተወስኗል። እንዲህ መደረጉ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ታሰቦ ነበር። ዛሬም ግን ‹‹ቤትህ ተቀመጥ›› የተባለ ነዋሪ ኑሮ አስገድዶት ወደውጪ በመውጣቱ ትራንስፖርቱና የሰው ቁጥር ሊመጣጠን አልቻለም፤ እንዲህ መሆኑ ደግሞ እንደ አቶ አሰፋ በመሰሉ ለፍቶ አዳሪዎች ላይ እያሳደረ ያለው ተጽዕኖ ላቅ እንዲል አድርጎታል። እሳቸውን ጨምሮ ሌሎች ተጠቃሚዎች እንደሚሉት የትራንስፖርት ዋጋውና የተጠቃሚዎች ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል። መፍትሔ የለሹ የከተማችን የትራንስፖርት ጉዳይም እልባት ካልተበጀለት የችግሩ ስፋት በአሳሳቢነቱ ይቀጥላል። ከጀሞ አየር ጤና፣ ወደ ጦር ኃይሎች በየቀኑ የሚመላለሱት ወይዘሮ ወርቅነሽ በርካቶች የሚያነሱትን ችግር ይጋራሉ። ከጡረታ በኋላ በጥቂት ክፍያ ተቀጥረው የሚሠሩበት የግል ድርጅት ከኮቪድ መከሰት በኋላ ተዘግቶ ቢቆይም በቅርቡ ሥራ ጀምሯል፤ ይህ መሆኑ እሳቸውን ጨምሮ ሌሎች ሠራተኞች በትራንስፖርት እጦት እንዲንገላቱ አስገድዷቸዋል። ወይዘሮዋ ቀደም ሲል ለታክሲ በቀን ይከፍሉት የነበረው ሰባት ብር አሁን ላይ በእጥፍ ጨምሮ ሃያ ስምንት ብር እያስወጣቸው መሆኑን ይናገራሉ፤ በሰዓቱ ለመድረስና ተመልሶ ለመምጣትም የሚገጥማቸው ውጣውረድ በእጅጉ እየፈተናቸው ነው። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮማንደር አህመድ መሐመድ ከኮቪድ መከሰት በኋላ ህብረተሰቡ ቤቱ እንዲቀመጥ መወሰኑን ያስታውሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ በርካታው የከተማ ነዋሪ ያለማቋረጥ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ መሆኑም በትራንስፖርት አቅርቦቱና አጠቃቀሙ ላይ ከፍተኛ ችግር እያስከተለ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡እንደ ኮማንደር አህመድ ገለጻ ከወረርሽኙ መከሰት በኋላ የታክሲዎች የመጫን አቅም በሃምሳ ፐርሰንት መቀነሱ ለረጃጅም ሰልፎች መፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡ ከክረምቱ ጋር ተያይዞ የሚኖረው የመንገድ መዘጋጋትም የታክሲዎች ምልልስ እንዲቀንስና በተጠቃሚው ላይ ተጽዕኖ እንዲፈጠር አድርጓልቀደም ሲል ህብረተሰቡ ቤት የመዋል ልምድን አዳብሮ እንደነበር ያስታወሱት ኃላፊው፣ በአሁኑ ጊዜ አብዛኞቹ መስሪያቤቶች ሥራ ከመጀመራቸው ጋር ተያይዞ በርካታ ሠራተኞች ትራንስፖርት ፈላጊዎች ሆነዋል፡፡ ይህ እውነታም ቀደም ሲል በነበረው ልክ እንቅስቃሴው እንዳይ ቀጥልና የሚስተዋለው ችግር እንዲባባስ አስገድዷል። በአሁኑ ጊዜ ከተለያዩ ቦታዎች ወደ መሀል ከተማ የሚገቡ ሰዎች መበራከታቸውን የገለጹት ኮማንደሩ እነሱን ጨምሮ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከወትሮው በባሰ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች መሆናቸው ለችግሩ መባባስ በምክንያትነት የሚጠቀስ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ ያለውን የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ቁጥር መፍትሔ ለመስጠት ጥናት በመደረግ ላይ መሆኑን የተናገሩት ኮማንደር አህመድ፣ በቅርበት በመቀመጥ ካለው ስጋት ይልቅ ተጠጋግቶ በመቆም የሚመጣው ችግር እንደሚብስ በመታመኑ በጉዳዩ ላይ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል፡፡በሃምሳ ፐርሰንት መሆኑ ቀርቶ በወንበር ልክ ይጫን የሚለው ሃሳብ የህብረተሰቡ ጥያቄ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው ጉዳዩ አሳማኝ በመሆኑ ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተወያበት መሆኑን ተናግረዋል። በቅርብ ጊዜ ተጨማሪ አስር የከተማ አውቶቡሶች ርክክብ መካሄዱን የተናገሩት ኮማንደር አህመድ ይህ መሆኑ የትራንስፖርቱን ችግር ለማቃለል በቂ እንደማይሆንና ቀደምሲል የተጀመረውን የሦስት ሺህ አውቶቡሶች ግዢን የማጠናቀቅ ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። በአሁኑ ጊዜ በተወሰኑ አካባቢዎች ለአውቶቡስ መጓጓዣነት ብቻ የተለዩ መንገዶችን በመጠቀም የሚስተ ዋለውን መጨናነቅ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው። ችግሩ በዘላቂነት እስኪፈታ ሕብረተሰቡ ሊተባበር ይገባል ያሉት ኮማንደር አህመድ በተለይ አሽከርካሪዎች በእነዚህ መንገዶች ላይ መኪና ባለማቆም፣ የተበላሹትን ፈጥኖ በማንሳትና በተመሳሳይ ሰዓት ባለመውጣት የመንገዱን መጨናነቅ ሊቀንሱ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 20/2012መልካምስራ አፈወርቅ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36125
e3989077cc99c110fbedfdb77f552e62
dffbe733f67039bbd24f45be8bb43a77
የህብረተሰቡ መዘናጋት የኮሮ ቫይረስ ስርጭት እንዳያስፋፋው ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
ድሬዳዋ፡- በከተማዋ እየተስተዋለ የሚገኘው የህብረተሰቡ መዘናጋት የኮሮ ቫይረስ ስርጭት እንዳያስፋፋው ስጋት እያሳደረ መሆኑን የከተማው መስተዳድር ጤና ቢሮ አስታወቀ። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር የጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ቢሮ አስተባባሪ ወይዘሮ ስንታየሁ ደባሱ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መምጣቱ፤ በሽታው በማህበረሰቡ ውስጥ እየተሰራጨ መምጣቱ የሚያመላክት በመሆኑ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው መሆኑን ያሳያል ነገር ግን አሁን ላይ እየታየ ያለው የህብረተሰቡ መዘናጋት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እንዳያስፋፋው ስጋት እየሆነ ይገኛል ፡:ምርምራ በሚካሄድበት ወቅት ብዙ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው እንዲሁ በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች መገኘታቸው ቫይረሱ እየተሰራጨ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመው፤ ህብረተሰቡ መጀመሪያ አካባቢ ያሳይ የነበረውን የመከላከልና የጥንቃቄ ስራ በመተው የመላመድ ሁኔታዎች እየታዩ መሆናቸውን አመልክተ ዋል። ምርምራውን ለማስፋት ወደ ጤና ተቋማትና ሆስፒታሎች ከሚመጡ ታማሚዎች እንዲሁም ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ካላቸው ሰዎች ናሙና በመውሰድ የምርመራ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን አስተባባሪዋ ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ያለው የመመርመሪያ ጣቢያ አንድ ሲሆን በሁሉም ጤና ጣቢያዎች በላብራቶሪ ባለሙያዎች አማካይነት ናሙና የሚወሰድ መሆኑን ጠቁመው፤ ለላብራቶሪ ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት ናሙና የሚወስድበት ሁኔታ የተመቻቸ መሆኑን አመልክተዋል። አክለውም፤ ድሬዳዋ በጁቡቲ መንገደኞች በኩል የስጋት ቀጠና በመሆኗ፤ ከሌሎች ከተሞች በተለየ መልኩ የተለያዩ የመከላከል ስራዎች የሚሰሩ ሲሆን በድንበሮች ፣ የትራንስፖርት መግቢያና መውጫዎች አካባቢዎች ከሹፌሮች ናሙና እየተወሰደ የሚገኝ መሆኑን አመልክተዋል። እንደ አስተባባሪዋ ገለጻ፤ የጅቡቲ ተመላሽ ዜጎች ደወሌ ለይቶ ማቆያና ህክምና ማዕከል ምቹ ባለመሆኑ ወደ ድሬዳዋ እንዲዘዋወሩ ተደርጓል። እንዲዘዋወሩ የተደረጉትም ቫይረሱ የተገኘባቸው፤ ገና ከጁቡቲ የገቡ ምርመራ የተደረገላቸውንና ያልተደ ረገላቸው መሆናቸውን አመልክተዋል። በዚህም በአንድ ቀን ከተወሰደ 80 ናሙና ውስጥ 78 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን 75 ሰዎች ከደወሌ ለይቶ ማቆያ የመጡ ሲሆን ሌሎች 3 ሰዎች ከማህበረሰቡ መገኘታቸው እጅግ አስደንጋጭ ክስተት መሆኑን አስታውሰዋል። ምርመራውን ለማስፋት ተጨማሪ መመርመሪያ ማሽን የተጠየቀ መሆኑን ጠቁመው፤ አሁኑ ግን ባለው አቅምና የሰው ሃይል ተጠቅሞ ለመመርመር ጥረት በማድረግ ናሙና የመውሰዱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሚደረገው የቤት ለቤት ልየታ ስራ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በኤሌክት ሮኒክ ሥርዓት በመታገዝ የቤት ለቤት የሙቀት ልየታ የሚሰሩ መሆኑን ጠቁመው፤ ዳታ አያያዝ ሥር ዓቱን በማዘመን በታብሌት የተደገፈ መረጃን በመሰብሰብ የሪፖርት አሰጣጥ ሥርዓቱ የተናበበና የተሳለጠ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ የተፈጠረ መሆኑን አመልክተዋል። ህብረተሰቡም ጥንቃቄ ሳይለየው ኮሮናን በመከላከል አጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን የሚጠቁሙት አስተባባሪዋ፤ ከዚህ ጎን ለጎን ሌሎች የህክምና የክትባት አገልግሎቶች በአግባቡ እየተሰጡ ይገኛሉ በመሆኑ ህብረተሰቡም ያለምንም ስጋት ጤናውን መከታተል እንዳለበት አመልክተዋል። በድሬዳዋ ከዚህ ሌላ ተጨማሪ እንደ ወባ ያሉ ስጋቶች መኖራቸውን ጠቁመው፤ የመከላከል ስራ አብሮነትን የሚጠይቅ በመሆኑ ህብረተሰቡም ሆነ ባለድርሻ አካላት የጤና ስራውን ማገዝ እንደ ሚጠበቅባቸው ጥሪ አቅርበዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 20/2012ወርቅነሽ ደምሰው
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36117
9344b5b6f7f645a42c5fdd1de3a04d61
9cff5ee80a7b092e34ff05d54d2abd15
የፕሪሚየር ሊጉ ዳኞች የአካል ብቃት ፈተና ወስደዋል
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የብሔራዊ ዳኞች በአዲስ አበባ ስታዲየም በ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግን እየመሩ ለሚገኙ 28 ዋና እና 34 ረዳት ዳኞች የአካል ብቃት ፈተና መስጠቱን አስታውቋል፡፡ በዕለቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ዋና ፀሐፊ አቶ ሰለሞን ገብረሥላሴ የተገኙ ሲሆን ምዘናው በየውድድር ዓመቱ በፊፋ ሕግ መሠረት በየሦስት ወሩ ከሚካሄደው የዳኞች የአካል ብቃት መመዘኛ ፈተናዎች መካከል የ3ኛው ዙር የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ እና የፊፋ ኤምኤ ዳኞች የአካል ብቃት ኢንስትራክተር በሆኑት በአቶ ቸርነት አሰፋ እንዲሁም በብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ አባላት መካሄዱን ፌዴሬሽኑ በድረ ገፁ አስነብቧል፡፡ በፈተናው ከ28ቱ ዋና ዳኞች 4ቱ ፈተናውን ያላለፉ ሲሆን በረዳት ዳኝነት የተፈተኑት 34ቱም ፈተናውን በብቃት አጠናቀዋል፡፡ የአካል ብቃት ፈተናውን ያላለፉ ዳኞች በቀጣይ 6 ወራት እራሳቸውን በማዘጋጀት በድጋሚ የሚፈተኑ ሲሆን ይህንን እስኪያጠናቅቁ ድረስ በዳኝነት እንደማይሠሩ እና ፈተናውን በድጋሚ ተፈትነው ማለፍ ካልቻሉ ከፕሪሚየር ሊጉ በደረጃ ዝቅ በማለት የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎችን እንዲመሩ ይደረጋሉ፡፡ ይህ ዓይነቱ ምዘና በየሦስት ወሩ የሚሰጥ በመሆኑ ቀደም ሲል በዳኞች ላይ ይደርስ የነበረውን የተለያዩ የጤና እና መሰል ችግሮች ለመቅረፍ እንዲሁም ባለሙያዎቹ በተወሰነ ጊዜ ከዳኞች ጋር በመገናኘት ያሉበትን ደረጃ ለማየት እና ጥሩውን ለማበርታት እንዲሁም ዝቅተኛ ውጤት ያመጡትን በማንቃት የተሻለ መሥራት እንደሚገባቸው ለማድረግ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ የሚገኝ መሆኑን እና ያሉትን የዳኝነት ችግሮች በሰፊው ለመቅረፍ በተለያዩ እርከኖች የሚከናወኑ ውድድሮች በወንድም በሴትም የሚመሩ ዳኞች ተተኪዎች ላይ በተለይ የሴት ዳኞች ችግር ከፍተኛ በመሆኑ ጠንክሮ መሥራት የቀጣይ የቤት ሥራችን አድርገን እንሠራለን ሲሉ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ቸርነት አሰፋ ገልጸውልናል፡፡አዲስ ዘመን ግንቦት 18/2011ዳግም ከበደ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11509
77fe4c09c5fb343adce6ce26703bad2d
27b6ffbe278d3ade1e2c5cf192168259
ከተማ አቀፍ የስፖርት ፌስቲቫል ተካሄደ
አዲስ አበባ፡- ከተማ አቀፍ የስፖርት ፌስቲቫል ትላንት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተካሄደ። “ዘረኝነት ይብቃ” በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው ይህ ፌስቲቫል አላማ ህብረተሰቡ በሚማርበት፣ በሚሠራበት እና በሚዝናናበት አካባቢ ጤና ተኮር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተሳታፊ እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። ከዚህም ባሻገር ከዘረኝነት አስተሳሰብ የፀዳ፣ በመቻቻል በመግባባትና በመከባበር መልካም እሴቶችን የሚያከብር፣ ከአደገኛ ሱሶች የራቀ ህብረተሰብ መፍጠርን አላማ ያደረገ እንደሆነም በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡ በፌስቲቫሉ ላይ ከባህላዊ ስፖርቶች መካከል የፈረስ ጉግስ የቀረበ ሲሆን ከዘመናዊ ደግሞ የመኪና፣ የብስክሌትና የመሳሰሉ ስፖርታዊ ክንዋኔዎች መርሐ ግብሩን አድምቀውታል። የአካል ጉዳተኞች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ፣ የውሹ፣ ቴኳንዶናየእጅ ኳስም ተካሂዷል። የፌስቲቫሉ ተሳታፊዎች ስፖርታዊ እንቅስ ቃሴዎችን በማድረግ ጤናቸውን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ለአንድነት ፀር የሆነውን ዘረኝነት መከላከል ላይ እንዲያተኩሩም ጥሪ ቀርቧል። ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ስፖርታዊ እንቅስቃሴው ቀጣይነት እንዲኖረው ይሠ ራል። ምክትል ከንቲባው ባለዕድል ለሆኑ የፌስቲቫሉ ተሳታፊዎች የብስክሌት ሽልማት ሰጥተዋል። በዚሁ መሰረት 95 ብስክሌቶች በኩፖን ለደረሳቸው ባለ ዕድለኞች ተከፋ ፍለዋል። በዚህ ፌስቲቫል ላይ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ የተለያዩ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ታዳጊ ህጻናት፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶችና በእድሜ የገፉ አረጋዊያን በፌትቫሉ ላይ የተሳተፉ ሲሆን የተለያዩ የኤሮቢክስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን አድርገዋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 19/2011በጋዜጣው ሪፖርተር
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11568
5d184f68fa60bec2c03f6f2ebbb42d99
9e5650a5dd348cc73f6ecb3fad679943
የዩጂን ዳይመንድ ሊግ የዓለም ሴት ከዋክብትን ያፋልማል
በአሜሪካዋ የኦሪጎን ግዛት የምትገኘው የዩጂን ከተማ «የዓለም የመም እና የሜዳ ስፖርቶች መቀመጫ» የሚል ቅጽል ስም ይከተላታል። እአአ የ2021 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አስተናጋጅ በመሆንም በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ተመርጣለች። በጥበብ ሥራዎችና ስፖርት የምትታወቀው ከተማዋ በመጪው የፈረንጆቹ ወር መጨረሻ ደግሞ የዓለም ምርጥ ሴት አትሌቶችን ልታፋልም ቀጠሮ ይዛለች። የዳይመንድ ሊግ መዳረሻዎች ከሆኑት መካከል በአሜሪካ አፈር ላይ የሚካሄደው ውድድር ከሌሎቹ በተለየ የሴቶች 3ሺ ሜትር ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል። ሩጫውን ከወዲሁ አጓጊ ያደረገው የዓለምና የኦሊምፒክ ሻምፒዮን የሆኑ አትሌቶች ተሳታፊነታቸውን በማረጋገጣቸው ሲሆን፤ «እስከአሁን ከታዩ ውድድሮች ታላቁ» የሚል ስያሜም ተሰጥቶታል። ኢትዮጵያዊያኑን ጨምሮ በኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በሆላንድ አትሌቶች መካከል ከፍተኛ የአሸናፊነት ፍልሚያ እንደሚደረግም ይጠበቃል። በየትኛውም ዓለም የሚካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮችን ደረጃ ከሚጨምሩት መካከል አንዱ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቶች ተሳትፎ ነው። ኦሊምፒክን ጨምሮ በዓለም ሻምፒዮናዎች እንዲሁም በሌሎች የመምና የጎዳና ላይ ሩጫዎች ውጤታማ የሆኑት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶችም ቅድሚያ ተጠቃሽ ናቸው። ይህንን ውድድር እጅግ አጓጊ ካደረጉት ተሳታፊ አትሌቶች መካከልም ኢትዮጵያዊቷ ገንዘቤ ዲባባ ተካታለች። የ28ዓመቷ ገንዘቤ ለሰባት ጊዜያት የራሷን ክብረወሰኖች እንዲሁም ፈጣን ሰዓቶች በማሻሻል አቻ ያልተገኘላት አትሌት ናት። የእርሷን ክብረ ወሰን ልዩ የሚያደርገውም በሌሎች ሊደፈር እና ሊሻሻል ያልቻለ መሆኑንም ዳይመንድ ሊግ በድረገጹ ጠቁሟል። እአአ በ2015 በአሜሪካ ምድር ባደረገችው የ5ሺ ሜትር ውድድር 14 ደቂቃ ከ19 ሰከንዶች ከ76 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት የግሏን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ፤ የዓመቱ የዓለም ምርጥ አትሌት በመባል መመረጧም ይታወሳል። ያለፈው ዓመት በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናም በ1ሺ 500 እና 3ሺ ሜትር ውድድር ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ያጠለቀች የመጀመሪያዋ አትሌት መሆኗ የሚታወስ ነው። በተያዘው ወር መጀመሪያ በተሳተፈችበት የዶሃ ዳይመንድ ሊግም በ3ሺ ሜትር ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች። ከዚህ ባሻገር ገንዘቤን በዚህ ውድድር ተሳታፊ የሚሆኑትን ምርጥ አትሌቶች ታስከነዳለች የሚል ግምት ሊያሰጣት የቻለው ደግሞ በርቀቱ ያላት ፈጣን ሰዓት ነው። 8 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ ከ60 ማይክሮሰከንድ የሆነ የግሏ ምርጥ ሰዓት ያላት ገንዘቤ በ4 ሰከንድ ከ08 ማይክሮ ሰከንድ ከሌሎቹ የፈጠነ መሆኑም ድረገጹ አመልክቷል። በሪዮ ኦሊምፒክ 10ሺ ሜትር ለሁለት አስርት ዓመታት በቻይናዊቷ አትሌት ተይዞ የቆየውን ሰዓት በማሻሻል የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ አልማዝ አያናም የቦታው ድምቀትና የውድድሩ ፈተና ከሚሆኑት መካከል ተገኝታለች። በዚያው ዓመት በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ በ5ሺ ሜትር አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ነበረች። አልማዝ በርቀቱ ለኢትዮጵያ ቀዳሚ ስትሆን በዓለም ደግሞ ሁለተኛዋ ፈጣን አትሌትም ናት። እአአ በ2015 በ5 ሺ ሜትር የዓለም ቁጥር አንድ አትሌትነት ማዕረግን ስታገኝ፤ በ2016 እና 2017 ደግሞ በ10ሺ ሜትር አቻ ያልተገኘላት አትሌትነቷን አረጋግጣለች። ያለፈው ዓመት ግን በጉልበት ጉዳት ምክንያት ከውድድር ርቃ ነበር የቆየችው። ከረጅም ጊዜ ማገገም በኋላም አንድ ወር ብቻ ለሚቀረው የዩጂን ዳይመንድ ሊግ ጠንካራ ልምምድ ስታደርግ ቆይታለች። ይህም በአዲስ ጉልበት የምትሳተፍበት ውድድር እንደመሆኑ ተፎካካሪዎቿን በማስከተል የተለመደ ድሏን ታስመዘግባለች በሚል እንድትጠበቅ አድርጓል። ሌላኛዋ የዚህ ውድድር ተካፋይ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሰምበሬ ተፈሪ ናት። በጎዳና ላይ ውድድሮች በተለይ የምትታወቀው አትሌቷ በአሜሪካ የሚኖራት ተሳትፎ የመጀመሪያዋ የመም ውድድር ነው። በ5ሺ ሜትር ባስመዘገበችው ሰዓት ከዓለም የምንጊዜም አትሌቶች መካከል ዘጠነኛ ስፍራ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት በግማሽ ማራቶን ውድድርም ተሳታፊ ነበረች። የ21 ዓመቷ ወጣት አትሌት ለተሰንበት ግደይም በዚህ ውድድር ከተፎካካሪዎቹ ተርታ ተካታለች። በቅርቡ በተካሄደው የዓለም ሃገር አቋራጭ ሻምፒዮና የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚዋ ለተሰንበት በ5ሺ ሜትር ባላት ሰዓት በዓለም ስምንተኛዋ ፈጣን አትሌት ናት። በ5ሺ ሜትር የኢትዮጵያ ሻምፒዮናዋ ፋንቱ ወርቁም በዚህ ውድድር ተሳታፊነቷን አረጋግጣለች። አትሌቷ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በተሳተፈችበት 3ሺ ሜትር ያስመዘገበችው ፈጣን ሰዓትም በዓለም ስድስተኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጣት በመሆኑ በዚህ ውድድር የተሰጣትን ግምት አንሯል። በአምስት ሺ ሜትር የዓለም ቁንጮ የሆነችው ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪም በዚህ ርቀት ተካፋይ መሆኗን ያረጋገጠች ሌላኛዋ አትሌት ናት። የ29 ዓመቷ አትሌት በተከታታይ ለሁለት ዓመታት የዳይመንድ ሊግ አሸናፊ ስትሆን፤ የውድደሩን ደረጃ ከፍ ከሚያደርጉና ፈታኝ ከሆኑት አትሌቶች መካከል ተጠቃሽ ናት። አትሌቷ ወደ ሩጫ የገባችው በ1ሺ 500 ሜትር ርቀት ሲሆን፤ እአአ በ2013ቱ የዓለም ሻምፒዮና የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ነበረች። በሪዮ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ብታስመዘግብም፤ በለንደኑ ሻምፒዮና ግን መንገሥ የቻለች አትሌት ናት። የመምና የጎዳና ላይ አትሌቷ ኦቤሪ የምትታወቅባቸው ርቀቶች 1ሺ500፣ 3ሺ እንዲሁም በ5ሺ ሜትሮች ነው። እአአ በ2012፣ 2014 እና 2018 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናዎች ላይ በ3ሺ ሜትር ተሳትፎዋ፤ አንድ የወርቅ እና አንድ የብር ሜዳሊያ ስታጠልቅ አንድ ጊዜ አራተኛ ደረጃን አስመዝግባለች። በተያዘው የፈረንጆቹ ወር በተካሄደው የዶሃ ዳይመንድ ሊግ የሦስት ኪሎ ሜትር እንዲሁም በዓለም ሃገር አቋራጭ ሻምፒዮና በአዋቂ ሴቶች ውድድር አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል። አትሌቷ በቅርቡ በተለያዩ ውድድሮች ተሳትፎዋ አሸናፊ መሆኗ እንዲሁም በርቀቱ ያላት ልምድ ተዳምሮም የዚህ ውድድር ፈታኝ አትሌት ብቻም ሳትሆን የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ትሆናለች የሚል እምነትም ተጥሎባታል። የሁለት ጊዜ የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ ደቡብ አፍሪካዊቷ ካስተር ሰመኒያ በውድድሩተሳታፊ ከሆኑ ተፎካካሪ አትሌቶች መካከል አንዷ እንደምትሆን ይጠበቃል። በ800 ሜትር የሦስት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮናዋ ሰመኒያ በርቀቱ ተሳታፊነቷን ያረጋገጠች ሲሆን፤ በዚህ ርቀት እምብዛም ባትታወቅም ለአሸናፊነት እንደምትፋለም ቅድመ ግምቱን አግኝታለች። ያለፈው ዓመት ምርጥ ሴት አትሌት ተመራጭ የሆነችው አትሌቷ፤ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ካወጣው የውድድር ደንብ ጋር በተያያዘ ውዝግብ ውስጥ መቆየቷ ይታወቃል። አትሌቷ ከወራት በፊት በሃገሯ በተካሄደ ሻምፒዮና ላይ በ5 ኪሎ ሜትር ውድድር ተሳትፋ ቀዳሚ መሆን ችላለች። በሌላ ውድድርም በተመሳሳይ ተሳትፎዋ የግል ሰዓቷን ማሻሻሏ ደግሞ ለዚህ ውድድር የምታደርገውን ዝግጅት ሊያሳይ የሚችል ነው። በአሜሪካ እአአ በ2017 እና 2018 ዳይመንድ ሊግ ውድድሮች በ800 ሜትር ተሳትፎዋ ድል ያስመዘገበች መሆኗም ውድድሩ አዲስ እንደማይሆንባትም ነው የተነገረው። በትውልድ ኢትዮጵያዊት በዜግነት የሆላንዳዊት የሆነችው የ26 ዓመቷ ሲፈን ሐሰንም በዚህ ውድድር ተሳታፊ ከሆኑት አትሌቶች አንዷ ናት። አትሌቷ እአአ የ2015 ዳይመንድ ሊግ በ1ሺ 500 ሜትር የዋንጫ ተሸላሚ ስትሆን፤ በቀጣዩ ዓመት በተካሄደው የቤት ውስጥ ሻምፒዮናም በዚሁ ርቀት የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ነበረች። እአአ በ2017 በተለያዩ ርቀቶች በተሳተፈችባቸው ሦስት ውድድሮች ላይ ያስመዘገበቻቸው ሰዓቶችም ከአምስት ምርጥ አትሌቶች ተርታ አሰልፈዋታል። ያለፈው ዓመትም በተመሳሳይ አስደማሚ ብቃት ይዛ የቆየችው ሲፈን፤ በ1ሺ500 ሜትር እና 5ሺ ሜትር ከቀዳሚዎቹ መካከል ልትገኝ ችላለች። በተያዘው ዓመትም በተመሳሳይ ብቃቷን አሳድጋ ወደ ውድድር የገባች ሲሆን፤ ከወራት በፊት በተካሄደው የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ 14 ደቂቃ ከ44 ሰከንድ በመግባት የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ሆናለች። በግማሽ ማራቶን ተሳትፎዋም ከኬንያዊያን አትሌቶች ውጪ ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበጭ አትሌት ተሰኝታለች። በጆርዳን በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫም አሸናፊ መሆኗ የራስ መተማመኗን ያሳደገ ከመሆኑም ባሻገር በዳይመንድ ሊጉም ብርቱ ተፎካካሪ እንደምትሆን ነው የሚጠበቀው። በዚህ ውድድር ላይ ተካፋይ መሆናቸውን ካረጋገጡት አትሌቶች መካከል 15 የሚሆኑት ከዘጠኝ ደቂቃ በታች የሆነ ሰዓት ያላቸው መሆኑ ከፍተኛ ፍልሚያ እንደሚያስተናግድ መገመት ይቻላል። በአትሌት ገንዘቤ ዲባባ ቀዳሚነት የሚመራው የአትሌቶቹ የግል ፈጣን ሰዓት የሚበላለጠው በሰከንዶች ብቻ መሆኑም፤ ከፉክክሩ ባሻገር ፈጣን ሰዓት አሊያም የርቀቱ ክብረወሰን ሊመዘገብ እንደሚችልም ይጠበቃል።አዲስ ዘመን ግንቦት 19/2011ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11561
b5e3ce79903c74e6f3eb2c83f4560c39
e6542717f568a4670fc79f716c623fcc
የኦሊምፒክ ሳምንት በአዲስ አበባ
የኦሊምፒክን ጽንሰ ሃሳብ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚያሰርጽና መርሁን ማዕከል ያደረገው የኦሊምፒክ ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ መርሐ ግብሮች ይካሄዳል። እአአ ለ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ የገቢ ማሰባሰቢያም ይካሄዳል። በመጪው ሰኔ ወር ዘመናዊው ኦሊምፒክ የተመሰረተበት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ይታሰባል። በኢትዮጵያም ዘንደሮ ለየት ባለ መልኩ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች በተለያዩ ስፖርታዊ ሁነቶች ይከበራል። «ኦሊምፒዝም ለሰው ልጆች ክብር፣ ሰላምና አንድነት» በሚል መሪ ቃል የሚከበረው፤ የኦሊምፒክ ሳምንቱ የኦሊምፒክን መርህ እና እሴቶች ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ለሀገሪቷ ሰላምና አንድነት እንዲሁም በህዝቦች መካከል መፈቃቀርና መተሳ ሰብን ለማጎልበት የሚጫወተው ሚናም ከፍተኛ ነው። የኦሊምፒክ ሳምንቱ ከሚከበርባቸው የሃገሪቷ ክፍሎች መካከል አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። መርሐ ግብሩም በከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበላይነት እንደሚመራም ጋዜጣዊ መግለጫው በተሰጠበት ወቅት ተጠቁሟል። አከባበሩን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በቅንጅት እየሠራ ሲሆን፤ የተለያዩ ክንውኖች እንደሚኖሩም ተገልጿል። ለተያዙት መርሐ ግብሮችም እየተደረገ ያለው ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽነር ዮናስ አረጋይጠቁመዋል። 60 ትምህርት ቤቶችን የሚያሳትፈው የተማሪዎች ሩጫ አንዱ ሲሆን፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ኮተቤ ሜትሮ ፖሊታንት ዩኒቨርሲቲ ምሁራንን ያሳተፈ የፓናል ውይይትም ይካሄዳል። በአንጋፋ ክለቦች መካከል ከሚካሄደው ባሻገር ታዋቂ ሰዎችን፣ ዲፕሎማቶችን እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃንን የሚያሳትፉ የእግር ኳስ ውድድሮችም ይኖራሉ። የኢትዮጵያ ሴት ብሄራዊ ቡድን(ሉሲዎቹ) ከሴት ሚኒስትሮች እንዲሁም ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ከገዢው ፓርቲ ጋር የሚያገናኝ የእግር ኳስ ጨዋታ ለማካሄድም ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑንም ኮሚሽነሩ ጨምረው ገልጸዋል። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፤ የኦሊምፒክ ሳምንቱ በሁሉም ከተሞች የሚከበር መሆኑን ጠቅሰዋል። በሃገር አቀፍ ደረጃም በአትሌቲክስ እና እግር ኳስ ውድድሮች፣ በኮንሰርት፣ በሲምፒዚየም እንዲሁም በአባላት ምዝገባ እንደሚከበርም ጠቁመዋል። አከባበሩ ስፖርት ለሰላም ያለውን ሚና ከማሳየት ባሻገር ስፖርቱን ለመደገፍም ያለመ ነው። በመጪው ዓመት ለሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ 200 ሚሊዮን ብር የሚያስፈልግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም፤ ህብረተሰቡ ከተሳትፎው ጎን ለጎን ስፖርቱን እንዲያግዝም ፕሬዚዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል። የኦሊምፒክ ሳምንቱ ከመጪው ሰኔ 16/2011 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን፤ ኮሚቴውን ለመደገፍ አባል ለመሆን የሚያስችል ምዝገባ መጀመሩ ይታወሳል። ለምዝገባው በተከፈተው ድረገጽ አማካኝነት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ስፖርት ቤተሰብ በመሆን በሃሳብ፣ በዕውቀት እንዲሁም በገንዘብ እገዛ ማድረግ ይቻላል።አዲስ ዘመን ግንቦት 19/2011ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11571
8abb0c501bb3f26ebe4633a5fb1e0a7a
b5f894be70c3a41d50d52f8379e60440
ከማንችስተር ሲቲ ስኬት በስተጀርባ 
በቅርቡ በተጠናቀቀው የ2018/19 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ማንችስተር ሲቲ ዋንጫ አንስቷል፡፡ ይህ የፕሪሜር ሊግ ፍጻሜ ማንቸስተር ሲቲን በልዩ ክብር ሲያነግስ ተቀናቃኞችን አስቆጭቷል፡፡ ክለቡ ሰሞኑን የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫም ባለቤት ሆኗል፡፡ ክለቡ በሻምፒዮንስ ሊጉ ለድል ባይበቃም ጥሩ ተፎካካሪነቱን አሳይቷል። በዚህ የተነሳም የተወሰኑ ተቀናቃኝ ክለቦችና የእግር ኳስ ስፖርት ተንታኞች ማንችስተር ሲቲ የድል ባለቤት የሆነው በገንዘብ ኃይል ነው ይላሉ። የቢቢሲ የእግር ኳስ ስፖርት ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን ግን ሲቲዎች የተሻለ ቡድንና አመራር ስለነበራቸው የድል ባለቤት ቢሆኑም፤ በውድ ዋጋ የገዟቸው ተጨዋጮችም ለድሉ መሳካት ጉልህ ሚና ነበራቸው ይላል፡፡ በተለይ በእንግሊዝ ውስጥ ያሉት ሚዲያዎች ማንችስተር ስቲ ለድል የበቃው ያለቅጥ ከፍተኛ ዋጋ በወጣባቸው ተጫዋቹ አማካኝነት መሆኑን ሰፊ ሽፋን ሰጥተው ዘግበዋል፡፡ በአንጻሩ የማንችስትር ሲቲ ሊቀ መንበር ካለዶን አል ሙባረክ፤ ሲቲ ለድል የበቃው በጣም በውድ ዋጋ በገዛቸው ተጨዋጮቹ ነው በሚለው ሀሳብ አይስማሙበትም፡፡ “ይህን የሚያወሩት በክለባችን ስኬት በቅናት ያረሩ ባላንጣዎቻችን ናቸውም ይላሉ። “ስለዚህ ሀሳቡ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ነው” ሲሉ አጣጥለውታል፡፡ ምክንያታቸውም የዓመቱ ስፖርታዊ ዝውውሮች ሲታዩ ይህን እውነታ አያመለክቱም፡፡ በውድድር ዓመቱ ክለቡ ለተጫዋጮች ግዥ ያወጣው ወጪ ከሌሎች አቻ ክለቦች አንጻር ሲታይ ከፍተኛ የሚባል አይደለም ሲሉ በማስረጃ ይሞግታሉ፡፡ ክለቡ በዓለም ላይ በእግር ኳስ 10 ከፍተኛ የዝውውር ዋጋ ካስከፈሉ የተጫዋች ፊርማ ስምምነቶች አንዱ እንኳን የለውም። ለአብነት ያህል፤ በውድድር ዓመቱ የእንግሊዝ የፕሪሜር ሊጉ ተፎካካሪ ክለቦች ከሚባሉትና ከ10 ከፍተኛ የተጫዋጮች ዋጋ ዝውውር ከአደረጉ ክለቦች መካካል አንዱ የማንችስተር ዩናይትድ ክለብ ነው፡፡ ይህ ክለብ ፖል ፖግባና ሮሜሉ ሉካኩን 89 ሚሊዮን እና 75 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ አድርጎ አዘዋውሯል፡፡ ሊቨርፖልም ቢሆን ቨረጅ ቫን ዳይክን በ75 ሚሊዮን ዮሮ አስፈርሟል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ክለባችን ማችስተር ስቲ ሪያድ ማርቲዝን ከሌስተር ሲቲ እኤአ 2018 ሀምሌ ወር መጨረሻ ላይ በ60 ሚሊዮን ዮሮ አዛውሯል። አይማሪክ ላፖርትን፤ ኪቨን ዲ በሩንና ቤንጃሜን ሜንዲ እንደ ቅድም ተከተላቸው 57፣55፣52 ሚሊዮን ዮሮ አውጥቶ አስፈርሟል፡፡ ስለዚህ ማንችስተር ስቲ በውድ ዋጋ በተገዙ ተጫዋቾች ነው ለስኬት የበቃው እየተባለ በተቀናቃኝ ወገኖች የሚናፈሰው ወሬ ውሃ የሚቋጥር አይደለም፤ ምንጩም ቅናት ነው ሲሉ ሙባረክ ኮንነውታል፡፡ “በዓመቱ የውድድር ዘመን ከተደረጉ ከአስሩ ውድ የተጨዋጮች ፊርማ ማንቸስተር ስቲ አይገኝበትም፡፡ ክለቡ በተጋነነ ሽያጭ የተዘዋወሩ ተከላካይ፣ አጥቂና ግብ ጠባቂ የለውም” የሚሉት ሊቀ መንበሩ ውድድሩ ቀላል ባይሆንም፤ እውነታው ግን ክለቡ ሁለገብ ስልት በመጠቀምና በአነስተኛ ኢንቨስትመንት ለድል ሊበቃ መቻሉን ይናገራሉ፡፡ “በተለይ የቡድን ስራና ውሳኔ ነው ክለባችን ለዚህ ስኬት የበቃነው” ሆኖም አሉ ሙባረክ፤ “ማንችስተር ሲቲ ለድል የበቃው በውድ ገንዘብ ባስፈረማቸው ተጫዋጮቹ አማካኝነት ነው የሚለው የቅናትና የአሉባልታ ወሬ በመሆኑ እንደ ጨዋታው አካል እንወስደዋለን” ብለዋል፡፡ እርሳቸው ይህን ቢሉም ሲቲ በውድ ዋጋ ተጨዋጮችን ያዘዋውራል የሚለውን ትችት ተቀናቃኞቻቸው ብቻ ሳይሆን የአውሮፓ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ይጋራዋል፡፡ የማንችስተር ሲቲ ክለብ የገንዘብ አጠቃቀሙ ፌዴሬሽኑ በገንዘብ አጠቃቀምና በፍትሀዊነት ዙሪያ ያወጣውን መመሪያ የሚጥስ መሆኑን ይጠቀሳል፡፡ የላሊጋው ፕሬዚዳንት ጃቪር ቴባስ ሲቲ ክለብ በአቡ ዳቢ ዩናይትድ ግሩፕ ስር መሆኑ በእግር ኳሱ ውድድር በገንዘብ ኃይል ያላግባብ እየተዘወረ ነው ሲሉ ይወቅሳሉ፡፡ ሚስተር ሙባረክ የፕሬዚዳንት ጃቪር ቴባስን ሀሳብ በፍጹም አይቀበሉትም። እንዲያውም “ሀሳቡ ዘረኝነት የሚጸባረቅበትና ሚዛናዊነት የጎደለው ነው” ይላሉ፡፡ ምክንያቱም የፕሬዚዳንቱ ትችት ወደአንድ ወገን ብቻ ያጋደለው ነው፡፡ ለምሳሌ፤ ከዚህ ቀደም ሀያሉ የስፔን ክለብ ሪያል ማድሪድ ታወቂ ተጫዋቾችን ያዘዋወረበት ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን ያወሳሉ፡፡ ፖርቹጋላዊ ሊዊስ ፊጎና የፈረንሳዩን አማካይ ዚኒዲን ዚዳን፤ እንዲሁም የብራዚሉን አጥቂ ሮናልዶና የእንግሊዙን አንበል ዴቪድ ቤካም ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ አድርጎ ማዘዋወሩን ነው ያወሱት፤ ይህ የሚያሳየው የፕሬዚዳንቱ ሀሳብ ሚዛናዊነት የጎደለው መሆኑን ነው ባይ ናቸው፡፡ ከአውሮፓ ፕሪሚር ሊጎች አንዱ ጠንካራና ብዙ ተመልካች ያለው የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ አንዱ ነው፡፡ ማንችስተር ሲቲም ከእነዚህ ጠንካራ ክለቦች አንዱ ነው፡፡ ይህ ክለብ በቀጣይም ተመጣጣኝ ኢንቨስትመንት ወጪ በማድረግ ክለቡን የተሻለ ተፎካካሪ ለማድረግ ይሰራል እንጂ፤ ትልቅ ኢንቨስትመንት የማውጣት ዓላማ የለንም ብለዋል። የክለቡ ሊቀመንበር፤ ሁለቱ የስፔን ታዋቂ ክለቦች ባርሴሎናና ሪያል ማድሪድ በከፍተኛ ወጪ ተጨዋቾችን የሚያዘዋውሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ ሲቲ ብቸኛው ከፍተኛ ተከፍይ ተጨዋቾችን የሚያስፈርም ክለብ አይደለም ብለው ሞግተዋል፡፡ እሳቸው ይህን ቢሉም ብዙዎች ማንችስተር ሲቲ ለድል የሚበቃው ለተጫዋቾች ዝውውር ከፍተኛ ወጪ በማውጣቱ ነው ብለው ይከራከሩ እንጂ፤ ቸልሲና ማንችስተር ዩናይትድ በአንጻሩ ለተጫዋቾች ዝውውር ከፍተኛ ወጪ ቢያደርጉም ለድል መብቃት አልቻሉም፡፡ ከአራት ዓመታት በፊት በሼክ መንሱር ባለቤትነት ከተያዘ በኋላ በ800 ሚሊዮን ፓውንድ ኢንቨስትመንት የተደራጀው ማን ሲቲ ዘንድሮ የፕሪሚዬር ሊጉን ዋንጫ አንስቷል፡፡ ሲቲ ከአራት ዓመት በፊት ለተጨዋቾች ደመወዝ በዓመት 54 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ የነበረው ሲሆን፤ ባለፉት ሁለት ዓመታትም ወጪው 174 ሚሊዮን ፓውንድ በመድረስ በእንግሊዝ የምንጊዜም ከፍተኛው የደመወዝ ከፋይ ክለብ አድርጎታል፡፡ ማንችስተር ሲቲ የፕሪሜር ሊጉን ዋንጫና የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫም ማንሳት የቻለው በእውቁ አስልጠኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ጭምር ተመርቶ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክራሉ፡፡አዲስ ዘመን ግንቦት 21/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11673
177e4c10440b65bd12fc052c75091f41
e7a1c8346e96e25e3cd20d5999121715
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመዲናዋና በክልል ከተሞች ነገ እና እሁድ ስምንቱም ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ እሁድ ግንቦት 24 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ አስር ሰዓት ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ 70 እንድርታ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚያደርጉት ፍልሚያ የሊጉ የሳምንቱ ትልቁ ጨዋታ ነው፡፡ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ያሉ ክለቦች የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት በሚያደርጉት ትንቅንቅ በክለቦቹ መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት መጥበቡን ተከትሎ በፕሪሚየር ሊጉ ፉክክሩ እየተፋፋመ መጥቷል። በመሆኑም ነገ በሊጉ መርሐ ግብር መሰረት ሶስት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከአዳማ ከተማ እና ወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስ ከሀዋሳ ከተማ በተመሳሳይ ሰዓት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት የሚፋለሙ ይሆናል። ወራጅ ቀጣና ላይ የሚገኘው መከላከያ ከሲዳማ ቡና በአዲስ አበባ ስታዲየም በዚሁ እለት ምሽት 11 ሰዓት ግጥሚያቸውን ያከናውናሉ። ሊጉ እሁድ እለት ቀጥሎ ሲውል አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡ ወራጅ ቀጣና ውስጥ የሚገኘው ደደቢት ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ወላይታ ድቻ ከጅማ አባ ጅፋር፣ ድሬዳዋ ከተማ ላለመውረድ ከሚታገለው ከስሑል ሽረ እንዲሁም በአማራ ክልል ደርቢ አፃዎቹ ፋሲል ከነማ ከጣና ሞገዶቹ ባህርዳር ከተማ በተመሳሳይ ሰዓት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት የሚፋለሙ ይሆናል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን አፃዎቹ ፋሲል ከነማ በ49 ነጥብ ሲመራ፤ መቐለ 70 እንደርታና ሲዳማ ቡና በእኩል 49ነጥብ በአፄዎቹ ፋሲል ከነማ በጎል ክፍያ ተበልጠው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ይከተላሉ። በአንፃሩ መከላከያ፣ ደቡብ ፖሊስ እና ደደቢት ደግሞ ከ14ኛ እስከ 16ኛ ያሉትን የመጨረሻዎቹን ሦስት ደረጃዎች ይዘው ወራጅ ቀጣና ውስጥ ይገኛሉ፡ የፕሪሚየር ሊጉን ኮከብ ጎል አግቢነት የመቐለ 70 እንደርታው አማኑኤል ገብረሚካኤል እና የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በእኩል 15ጎሎች ሲመሩ፤ የፋሲል ከነማው ሙጂብ ቃሲምና የደቡብ ፖሊሱ ሄኖክ አየለ በእኩል 12ጎሎች ይከተላሉ። እንዲሁም የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ በ11 ጎሎች ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን እየተከተለ ይገኛል።አዲስ ዘመን ግንቦት 22/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11771
b419327f34d6505a74819dfff483ccaf
4fdde919bec4570460949e0df8656569
ዛማሊክ በታሪኩ የመጀመሪያውን ዋንጫ አነሳ
ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማ በመሐል ዳኝነት በመሩት የ2018/19 ካፍ ኮንፌዴሬሽን የፍፃሜ ጨዋታ የግብፁ አንጋፋ ክለብ ዛማሌክ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፒዮን ሆነ። የ2018/19 ካፍ ኮንፌዴሬሽን የፍፃሜ ጨዋታ በሞሮኮው ሬኔይሳንስ ስፖርቲቭ ዴ ቤርካኔ እና በግብፁ ዛማሌክ መካከል ተካሂዷል። ሁለቱ ክለቦች ከሳምንት በፊት ባካሄዱት ጨዋታ በጭማሪ ሰዓት ቶጓዊው ኮድጆ ፎ -ዶህ- ላባ ለቤርካኔ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ዛማሊኮች መሸነፋቸው ይታወሳል። የመልሱ ጨዋታ ባሳለፍነው እሁድ በአሌክሳንድሪያው ቦርግ አል አረብ ስታድየም ሲካሄድም የመጀመሪያ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫቸውን ከፍ ለማድረግና ለ16 ዓመታት የዘለቀውን አህጉራዊ የዋንጫ ረሃባቸውን ለመግታት በሜዳቸውና ደጋፊያቸው ፊት ተፋልመዋል። በጨዋታውም በፈጣን መልሶ ማጥቃት ትፅነው የተጫወቱት ዛማሊኮች ከእረፍት መልስ በቪዲዮ እገዛ በተካሄደ ዳኝነት ውሳኔ (VAR) የተሰጣቸው ፍፁም ቅጣት ምት ማሃሙድ አላ ወደ ግብ በመቀየር አንድ ለዜሮ እንዲያሸንፉ ያስችላቸዋል። ጨዋታው በዚህ ውጤት ሲጠናቀቅ ሁለቱም ክለቦች አንድ አቻ መሆናቸውን ተከትሎ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የፍፅም ቅጣት ምት ዛማሊክ 5 ለ3 በሆነ ውጤት ባለድል ሆኗል። እኤአ በ1911 እንደተመሰረተ የሚነገርለት ዛማሊክ፤ ከአፍሪካ ክለቦች በርካታ ዋንጫዎች በማነሳት ተከታይ እንጂ ቀዳሚ የለውም። ክለቡ በአህጉር ደረጃ ካሳካቸው ክብሮች መካከልም 5 የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ 3 የካፍ ሱፐር ካፕ ወይንም የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን ይጠቀሳሉ። ክለቡ እኤአ በ2003 የአፍሪካ ሱፐር ካፕ ዋንጫን ካሳካ በኋላ ከአህጉራዊ ዋንጫ ጋር ተራርቆ የቆየ ሲሆን፤ የዘንድሮው ድሉም ከአስራ ስድስት ዓመታት በኋላ መሆኑ ታውቋል። የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በማንሳት ደግሞ በታሪኩ የመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቦለታል።። ከዚህ ቀደም ሁለት ተከታታይ የቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜዎችን እና ከወራት በፊት በዶሀ የተከናወነውን የካፍ ሱፐር ካፕ ጨዋታን መምራት የቻለው ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማም፤ 86ሺ ተመልካቾች በሚያስተናግደው ስታድየም የተካሄደውን የፍፃሜ ጨዋታም በብቃት መወጣቱም ታውቋል። የ2018/19 የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አሸናፊው ዛማሊክ 1ነጥብ 25 ሚሊዮን ዶላር ሲሸለም፤ ተሸናፊው ቤርካኔ በአንፃሩ 625 ሺ ዶላር አግኝቷል። የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የተጀመረው እኤአ በ2004 ነው።አዲስ ዘመን ግንቦት 20/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11611
74f99b837c2123444214a20d33d8bfed
e2b267c1ffb6fa161b8588339d43599c
ለ20 ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ግብ ተይዟል
 አዲስ አበባ፡- በቀጣይ 10 ዓመት በሚተገበረው መሪ ዕቅድ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በኮንስትራክሽን፣ በአገልግሎት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ(አይሲቲ)ና በሌሎች መስኮች ለ20 ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ግብ መያዙን የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ገለጸ። ኮሚሽነሩ ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ ለብሄራዊ የኢንቨስትመንትና የስራ ዕድል ኮሚቴ የ10 ዓመቱን መሪ የልማት ዕቅድ ሲያቀርቡ እንዳስታወቁት፤ ለ20 ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር የተጣለውን ግብ ለማሳካት ኢትዮጵያ በየዓመቱ በአማካይ ሁለት ሚሊዮን ስራ አጥ ዜጎች ስራ መፍጠር አለባት። የአስር ዓመቱ መሪ የስራ ፈጠራ መስክ የልማት ዕቅድ በየዓመቱ የሚመጣውን አዲስ የስራ ፈላጊ ሀይል ያገናዘበ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ኤፍሬም፤ እቅዱን ማሳካት የሚያስችሉ የስራ ፈጠራን የሚያበረታቱ ምቹ ፖሊሲዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል። ኢንተርፕራይዞች ለብዙ ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥሩና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልን የሚያሰፍኑ መሆን እንዳለባቸው ገልጸው፣እነዚህ ተቋማትን አስፋፍቶ ለማስቀጠል የሚያጋጥማቸውን ችግር ከወዲሁ መፍታት እንደሚገባም አስገዝበዋል። ይበልጥ የስራ ዕድል በሚፈጥሩ የስራ መስኮች ላይ መረባረብ ያስፈልጋል ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ከመንግሥት ጠባቂነት ወደ ማህበረሰብ ኃላፊትና ወደ ግሉ ዘርፍም ማተኮርና መሳተፍ ያስፈልጋል ብለዋል። ስራናሰራተኛን የማገናኘት አሰራርን፣የፋይናንስ አሰራርና አደረጃጃትን ማሻሻልና ማዘመን እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። እስካሁንም 385 ሚሊዮን ዶላር ለስራ ዕድል ፈጠራ ከተለያዩ የልማት አጋሮች መገኘቱን ጠቅሰው፣ ሀብት የማሰባሳብ ስራው በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል። ባለፈው በጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ሦስት ሚሊዮን 387ሺህ 079 የአጭር ጊዜ እና ዘላቂ የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸውን የጠቀሱት ዶክተር ኤፍሬም፤በበጀት ዓመቱ ከተፈጠረው የስራ ዕድልም አንድ ሦስተኛው ጊዜያዊ መሆኑንም ጠቅሰዋል። እንደ ዶክተር ኤፍሬም ገለጻ፤የአዲስ አበባ አስተዳደር፣አማራ፣አፋርና ኦሮሚያ ክልሎች ከዕቅዱ በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ክልሎች ናቸው። ደቡብ ፣ትግራይና ጋምቤላ ክልሎች እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ከ90 በመቶ በላይ ዕቅዳቸውን አሳክተዋል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ዘርፎች፣መስኖ፣ደን ልማት፣ማዕድንና የቱሪዝም ስራዎች ላይ የተሻለ የስራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ አብራርተው፣ 330ሺህ የሥራ ዕድሎች በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት መክሰማቸውን ተናግረዋል። በአዲሱ በጀት ዓመትም ለሦስት ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ዕቅድ መያዙን ጠቁመዋል። በሚቀጥለው አምስት ዓመትም ለአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር የሚችሉ አዳዲስ ፕሮጀክቶች መጀመራቸውንም ጠቁመዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 21/2012ጌትነት ምህረቴ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36180
a80e2979b454fba929ef0249776ee9fd
266e7433b163eeb8b12af5fa7f2a8c01
ባንኩ በ2012 በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ማትረፉን አስታወቀ
 አዲስ አበባ፡- የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በ2012 በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ማትረፉን አስታወቀ። ከባንኩ ብድር ወስደው ሲሰሩ የነበሩና የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጠረው አለመረጋጋት ጉዳት ለደረሰባቸው ተቋማት እገዛና እርዳታ ለመስጠት የማጣራት ስራ እያካሄደ መሆኑም ተጠቁሟል። የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ደርቤ አስፋው የባንኩን የ2012 በጀት ዓመት አፈጻጸም አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት፤ በ2012 በጀት ዓመት ባንኩ ከመጠባበቂያና ከእቃ እርጅና በፊት ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ አትርፏል። ከታክስ በፊት የተጣራ ትርፍ ደግሞ 1 ነጥብ 527 ቢሊየን ብር ነው። ይህ ትርፍ በባንኩ ታሪክ ከፍተኛ ነው። ከሀገሪቱ ባንኮችም ሶስተኛው ትርፋማ ባንክ ያደርገዋል። በ2011 በጀት ዓመት ከግብር በፊት 767 ሚሊየን ብር ትርፍ መገኘቱን ያብራሩት ፕሬዚዳንቱ፣ የዘንድሮው ትርፍ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር እጥፍ መሆኑን አብራርተዋል። ከትርፉም ባሻገር በ2011 ዓ.ም ከነበረው 41 ነጥብ 79 ቢሊየን ብር አጠቃላይ የባንኩ ሀብት የ11 ነጥብ 13 ቢሊየን ብር ጭማሪ በማሳየት በ2012 ዓ.ም 52 ነጥብ 92 ቢሊየን ብር መድረሱን ጠቁመዋል። እንደ አቶ ደርቤ ማብራሪያ፤ ባንኩ በ2012 በጀት ዓመት ብቻ 9 ነጥብ 34 ቢሊየን ብር በማሰባሰብ የባንኩን አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡን 45 ነጥብ 52 ቢሊየን ብር አድርሷል። በተጨማሪም በዓመቱ 31 አዳዲስ ቅርንጫፎችን የከፈተ ሲሆን፣ በአጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ብዛት 420 አድርሷል። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተፈጠረው አለመረጋጋት ባንኩ ብድር የሰጣቸው በርካታ ተቋማት የመቃጠልና የመውደም አደጋ እንደደረሰባቸው የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፤ ተቋማቱ ወደ ስራቸው እንዲመለሱና ስራቸውን እንዲያስቀጥሉ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። በአሁኑ ወቅት ባንኩ ብድር በሰጣቸው ተቋማት ላይ የደረሰውን የውድመት መጠን የማጥናት ስራ እየተሰራ መሆኑን ያብራሩት አቶ ደርቤ፣ ለተቋማቱ አስፈላጊውን እርዳታ በመስጠት ባንኮቹ ወደ ስራቸው እንዲመለሱና በቀጣይ ጊዜያትም ከባንኩ የወሰዱትን ብድር መመለስ እንዲችሉ ባንኩ የበኩሉን እንደሚወጣ አብራርተዋል። እንደ ፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ ፤ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱንም በመወጣት ላይ ይገኛል። በኮቪድ 19 ምክንያት ሊጎዱ ይችላሉ ተብለው የታሰቡትን በመለየት እስከ 5 በመቶ የሚደርስ የብድር ወለድ ቅነሳ አድርጓል። ከ 8 ሚሊየን ብር በላይ በሀገርና በክልል ደረጃ በተደራጁ የሃብት ማሰባሰቢያ ኮሚቴዎች በኩል ለግሷል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 21/2012 መላኩ ኤሮሴ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36188
26c6a5b4ce9f75c2b94f09e3159ad678
47e5dcd86df984d89ab6b0f04a3aa8b5
አቶ ልደቱ አያሌው ፍርድ ቤት ቀረቡ
 አዲስ አበባ፦ የኢዴፓ አመራር አቶ ልደቱ አያሌው ትናንት በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀረቡ። በወቅቱም ፖሊስ በሰኔ 23 ቀን 2012 ዓመተ ምህረት በቢሾፍቱ ለወጣቶች ገንዘብ በመስጠት ለብጥብጥ እና አመፅ በማነሳሳት በሚል ወንጀል እንደጠረጠራቸው አስታውቋል። ፖሊስ ባለፈው ዓርብ አራት ሰዓት ላይ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው እና በወቅቱም ሁለት ሽጉጦች ማግኘቱን አስታውቋል። የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ለማቅረብም የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜንም ጠይቋል። አቶ ልደቱ በበኩላቸው፣ ቋሚ አድራሻቸው በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ መሆኑን በመግለጽ መቅረብ ያለብኝ ፌደራል ፍርድ ቤት ነው በሚል መቃወሚያ አሰምተዋል። የአስም በሽተኛ እና የዛሬ ዓመት የልብ ቀዶ ጥገና ወዳ ደረጉበት ሀገር ትናንት 4 ሰዓት ላይ መጓዝ እንደነበረባቸው እና ትኬት መቁረጣቸውን፣ የእስር አያያዙም ለኮቪድ-19 እንዳያጋልጠኝ እሰጋለሁ በማለት በዋስ የመፈታት መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል። መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ የእስር አያያዛቸው ምቹ እና ጥንቃቄ ያለው መሆኑን ገልጾ፣ ከእስር ቢፈቱ ማስረጃ እንደሚሸሽበት በማሳወቅ ዋስትናውን ተቃውሟል። የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ ጉዳያቸው በዚያው በቢሾፍቱ አይታይ በሚል ላቀረቡት መቃወሚያም ወንጀሉ የተፈፀመው በቢሾፍቱ በመሆኑ እና መኖሪያቸውም በዚያው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን እዚያው የማየት ስልጣን እንዳለው በማስረዳት ጉዳዩ በችሎቱ መታየት እንደሚቀጥል ትእዛዝ ሰጥቷል። የዋስትና ጥያቄውንም ውድቅ በማድረግ ለመርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። የአቶ ልደቱ ጠበቃም የክልሉን የጥብቅና ፍቃድ ባለማቅረባቸው ጥብቅና ሳይቆሙላቸው ቀርተዋል። ፍርድ ቤቱም ፍቃድ ከሌላቸው ማማከር እንደማይፈቀድላቸው ገልፆላቸዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 21/2012
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36187
6f1b9d729365bddd29bcd3eae5d2e8f3
1e146e8edd85b39e76c11f9955591f08
ኮሚሽኑ በክልሉ ለከፋ ችግር ለተጋለጡ ዜጎች የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ:- የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ህልፈተ ህይወትን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተ አለመረጋጋት ለከፋ ችግር ለተጋለጡ ዜጎች የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የብሄራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። በኮሚሽኑ የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ዳይሬክተር ወይዘሮ አልማዝ ደምሴ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ህልፈተ ህይወትን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተ አለመረጋጋት 8ሺ 368 ዜጎች ለከፋ ችግር የተጋለጡ ሲሆን፤ ኮምሽኑም አደጋው ከተከሰተበት ማግስት ጀምሮ ለሰባት ሺ 342 ዜጎች የምግብና ለስምንት ሺ 368 ዜጎች የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። እንደ ዳይሬክተሯ ማብራሪያ፤ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ህልፈተ ህይወትን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተ አለመረጋጋት የከፋ የሚባል ጉዳት ደርሷል፡፡ በዚህም በክልሉ በሚገኙ ስምንት ወረዳዎች 224 ቤቶች በቃጠሎና 18 ቤቶችን ደግሞ በማፍረስ በድምሩ 242 ቤቶች በመውደማቸው ስምንት ሺ 368 የሚሆኑ ወገኖች ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል፡፡ ኮሚሽኑም አደጋው ከተከሰተ ማግስት ጀምሮ ለሰባት ሺ 342 ዜጎች የምግብና ለስምንት ሺ 368 ዜጎች ደግሞ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የጠቆሙት ወይዘሮ አልማዝ፤ በክልሉ ለሰባት ሺ 342 ዜጎች አንድ ሺ 101 ነጥብ ሦስት ኩንታል እህል፣ 33 ነጥብ አራት ኩንታል ዘይት፣ 115 ነጥብ 64 ኩንታል አልሚ ምግብ፣ 973 ነጥብ 76 ካርቶን ብስኩት፣ 14 ነጥብ 69 ኩንታል ቴምር እና 770 ነጥብ 44 ኩንታል ፓስታ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል። በሻሸመኔ ከተማ ጉዳት የደረሰባቸው 96 ቤቶች በአሁኑ ወቅት መልሰው እየተገነቡ እንደሚገኙ ወይዘሮ አልማዝ ጠቁመው፤ በክልሉ ለስምንት ሺ 368 ዜጎች ሦስት ሺ 347 ነጥብ 2 ብርድልብስ፣ 1673 ነጥብ 6 ብረት ድስት፣ 1006 ነጥብ ስድስት ማንቆርቆሪያ፣ 3347 ነጥብ 2 የፕላስቲክ ኩባያ፣ 3437 ነጥብ ስድስት የፕላስቲክ ሳህን፣ 1006 ነጥብ 6 የፕላስቲክ ጀሪካን፣ 1006 ነጥብ ስድስት የፕላስቲክ ጆግና 1673 ነጥብ ስድስት የፕላስቲክ ሸራ መሰራጨቱን ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 22/2012ሶሎሞን በየነ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36255
f3a4eca970bdc8a9e448ff815135fd4c
081efe8573b26e6f9e6f6f265bb338a3
በኦሊምፒክ ሳምንት አከባበር ላይ ምክክር ተደረገ
ዘመናዊ ኦሊምፒክ ጨዋታ የተመሰረተበትን ቀን ለማሰብ በመጪው ወር አጋማሽ በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚከበረው የኦሊምፒክ ሳምንት አስመልክቶ፤ በእቅድ አተገባበር ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደረገ። የኦሊምፒክ ሳምንቱ በእግር ኳስ ጨዋታ፣ በሩጫ፣ በሲምፖዚየምና በተለያዩ ኮንሰርቶች ይከበራል። «ኦሊምፒዝም ለሰው ልጆች ክብር፣ ሰላምና አንድነት» በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የኦሊምፒክ ሳምንት፤ ዘንድሮ ለየት ባለ መልኩ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተለያዩ ስፖርታዊ ኩነቶች እንደሚካሄዱ ኮሚቴው አስታውቋል። በዚህም የኦሊምፒዝም መርህ እና እሴቶች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና ለሀገሪቷ ሰላም፣ አንድነት፣ የህዝቦች መፈቃቀርና መተሳሰብን ለማጎልበት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው። በእቅድ አተገባበር ምክክሩ ላይ፤ ክቡር አቶ ሀብታሙ ሲሳይ የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር  ወልደጊዮርጊስ ተገኝተዋል። ከባለድርሻ አካላት መካከልም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የተመረጡ የአዲስ አበባ 8 የእግር ኳስ ክለብ ተወካዮች እንዲሁም የአርቲስት ተወካዮች ተካፍለዋል። የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክቡር ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፤ የኦሊምፒክ ሳምንት ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ኩነቶች ሲከበር ዓላማ አድርጎ የተነሳው የኦሊ ምፒክ መርህና ጽንሰ ሃሳብን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል። ስፖርት ለሀገርና ለህዝቦች ስላም እንዲሁም አንድነት ያለውን ፋይዳ በማስገንዘብ ህዝቦች በአንድነት እንዲቆሙ ለማስቻል፣ የስፖርት ችግሮችና መፍትሄዎች ዙሪያ መግባባትን ለመፍጠር ነው። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለአህጉርና በዓለም አቀፍ ውድድሮች የሚያደርጋቸውን ተሳትፎዎችንና ውድድሮችም በብቃት ለመወ ጣት ህዝቡ በባለቤትነት ስሜት ማገዝ እንዲችል ሁኔታዎችን ለማመቻቸትና በፋይናንስ ራሱን እንዲያጠናክር ለማድረግ መታለሙንም ፕሬ ዚዳንቱ ጠቁመዋል። ለዚህ ዓላማ ስኬት  የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ህብ ረተሰቡን በኦሊምፒክ እንቅስቃሴ ማሳተፍ እንደሚጠበቅም አሳስበዋል። የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሀብታሙ ሲሳይ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ይዞ የተነሳው ዓላማ አስፈላጊና ጊዜውን የጠበቀ መሆኑን አመላክተዋል። ህብረተሰቡ በዓመት አንድ መቶ ብር ከፍሎ በመመዝገብ የኦሊምፒክ አባል በመሆን ስፖርቱን በባለቤትነት እንዲደ ግፍና እንዲያግዝ የተመቻቸ ዕድል ተፈጥሯል። የሚገኘው ገቢም መልሶ የስፖርት ልማት ሥራዎችን በመስራት መንግሥት ያለበትን የፋይናንስ ጫና ከማቃለል አንጻር ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ነው የገለጹት። በመድረኩ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት፤ ኮሚቴው የጀመረው እንቅስቃሴ ወቅቱን የጠበቀና ሀገሪቷ ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል። ለተግባራዊነቱም ሁሉም በቁርጠኝነት ለመስ ራትና መደጋገፍ ስለሚገባ በፍጹም ቁርጠኝነት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ መግለጻቸውን ኮሚቴው በድረ ገጹ አስነብቧል።አዲስ ዘመን ግንቦት 7/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=10824
9f9dcab3480fee6eab75f4b510db867e
0883eee91baf2f8807baca815fb6c091
«ለውድድር የሚሆን የማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረት የለብንም» በኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ፋሲሊቲ ዳይሬክተር ኢንጂነር አዝመራው ግዛው
በኢትዮጵያ ስፖርት ውስጥ እንደ ውስንነት ከሚጠቀሱ ጉዳዮች መካከል አንዱ የማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረት ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህም በሁሉም የሃገሪቷ ክፍል በተሰጠው ልዩ ትኩረት ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ከጠበቁ ትልልቅ ስታዲየሞች ጀምሮ በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በመገንባት ይገኛሉ። በመኖሪያ አካባቢ ባሉ የማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረት ላይ ተደጋጋሚ ቅሬታዎች መነሳቱ ግን አልቀረም። በመንግሥት ደረጃ ከፍተኛ ወጪ የተደረገባቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች ጥራት ላይም ችግር መኖሩ ይጠቀሳል። አዲስ ዘመን ጋዜጣም በዛሬው እትሙ እነዚህን ጉዳዮች የሚዳስስ ቃለ ምልልስ፤ ከኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ፋሲሊቲ ዳይሬክተር ኢንጂነር አዝመራው ግዛው ጋር እንደሚከተለው አድርጓል። እኔም አመሰግናለሁ። ከዚህ ቀደም የነበረው ስራ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ማስፋፋት ላይ ነበር። ይህንን ለማድረግ ደግሞ ያሉትን በቁጥር ማወቅ ይጠይቃል፤ ለዚህም ወደ ክልሎች ቅጽ ሲላክ በግምት ተሞልቶ ይላክ ነበር። አሁን አሰራሩን በመቀየር ከወረዳ ጀምሮ ተቆጥሮ፤ ስማቸውና የሚገኙበት ስፍራ በተጨባጭ ዝርዝር መረጃ እንዲያዝ ተደርጓል። ይህንን ሥራ የሚያከናውን ግብረ ኃይል ተቋቁሞም እየተሰራ ይገኛል። አንዱ ችግር የክልል ስፖርት ኮሚሽነሮችን፣ የፍትህ አካላትን፣ የማዘጋጃ ቤት ኃላፊዎችን፣ የከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን፣… ያካተተ ምክክር ከባለድርሻ አካላት ጋር አድርገናል። ክልሎችም ተመሳሳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲያደርጉ አቅጣጫ አስቀምጠን ነበር፤ ይሁን እንጂ ሁሉም ክልል በእኩል በመውሰድ ላይ ክፍተት ነበረ። ስራውን በተሰጠው ስልጠና መሰረት የሚያከናውኑ የመኖራቸውን ያህል አንዳንዶች ደግሞ እንደተለመደው ይሞሉ ነበሩ። ይህም እንዳሰብነው በተመሳሳይ ሁኔታ ሊሄድልን አልቻለም። ሆኖም ማዘውተሪያዎቹ እንደተቀመጠው በትክክል በስማቸውና ባሉበት ቦታ እንዲመዘገቡ የማድረግ ስራ ተከናውኗል። አጠቃላይ ውጤቱ ከደረሰን በኋላም በተያዘው ወር መጨረሻ በጋራ የምንገመግመው ይሆናል። ቆጠራው ሲካሄድ በሚሞላው ቅጽ መሰረት ደረጃውን የመለየት ስራው ይካሄዳል። በመረጃ ላይ ተመስርተን ደረጃ የመስጠቱን ስራም እዚህ እናከናውናለን። የደረጃ መለያ መስፈርቱ የተዘጋጀው፤ በ2004ዓም የማዘውተሪያ ስፍራዎች አስተዳደር አዋጅ በወጣበት ወቅት ነው። ይህም ዓለም አቀፍ ተሞክሮና የሃገሪቷን ተጨባጭ ሁኔታ በመቀመር የተዘጋጀ ነው። ከዚህ በመነሳትም በሚሰጡት አገልግሎት ደረጃው ይሰጣቸዋል። ደረጃ አንድ የሚባሉት የማዘውተሪያ ስፍራዎች ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ማስተናገድ የሚችሉት ሲሆኑ፤ ደረጃ ሁለት ላይ የክልል ውድድሮችን የማዘጋጀት አቅም ያላቸው እንዲሁም ሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ጥርጊያ ሜዳዎች ናቸው። የደረጃ መለያ መስፈርቱ ለጂምናዚየሞችና ሌሎች ማዘውተሪያዎችም የተዘጋጀ ነው። በመጨረሻ ደረጃ የሚገኙት ማዘውተሪያዎች ደግሞ የተከለሉ እንዲሁም የመጸዳጃ፣ የመታጠቢያ እና መልበሻ ቤት እንዲኖራቸው ይጠይቃል። አይቻልምም፤ ይቻላልም። እንደሚታወቀው ኢንተርናሽናል ስታዲየሞች እየተገነቡ ይገኛሉ፤ እነዚህ ደግሞ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የማስተናገድ አቅም አላቸው። ይህ ደግሞ አማካሪው ዲዛይኑን ከመስራት ጀምሮ የፊፋን ደረጃ ማሟላት አለማሟላቱን ያረጋግጣል። የዓለም አቀፉን አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር እንዲሁም የካፍን ደረጃ እንዲያሟላም ስለሚደረግ ነው። አያሟላም የሚያስብለው ደግሞ፤ እንዲያሟላ የተቀመጠለት ደረጃ የሃገር በመሆኑ ነው። እያንዳንዱ ሃገር የራሱ ደረጃ ያለው ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ መስፈርቶችን ሲያስቀምጥ ለኢትዮጵያ ነው። ትልልቆቹ ማዘውተሪያዎች የዓለም አቀፍ ማህበራትን ደረጃዎችን ማሟላት ቢጠበቅባቸውም እዚህ የተቀመጠው ሃገሪቷ ላለችበት ተጨባጭ ሁኔታ እንዲመች ሆኖ ነው። ከቻን ጋር ያለው ነገር ከደረጃ ጋር ሊያያዝ አይችልም። ከመጀመሪያው ስነሳ ቻን ወደዚህ ሲመጣ የትኞቹ ስታዲየሞች ማስተናገድ ይችላሉ የሚለው ነው የታየው። ሁሉም ስታዲየሞች ላይ በተደረገው ግምገማም አራቱ ተመረጡ፤ ብሄራዊው፣ ባህርዳር፣ መቀሌ እና ሃዋሳ ስታዲየሞች። የተመረጡትም በዲዛይኖቻቸው ላይ ካፍ የሚጠይቃቸውን መስፈርቶች በማሟላታቸው ነው። የካፍ የቅኝት ቡድንም በተለያየ ጊዜ በመምጣት ማጣራቱን አካሄዱ። የኢትዮጵያ በጀት ከአምስት ዓመት እቅድ ጋር የተያያዘ መሆኑ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎም ቡድኑ ባደረገው ምልከታ በፕሮጀክቶቹ ላይ ልዩነት አልተመለከተም። የሜዳ፣ የቴክኖሎጂ፣ የውሃ፣ … ሌሎች መስተካከል አለባቸው የተባሉ ብዙ ነገሮች ቢኖሩም የበጀት ችግርም ነበር። ስራው በተለያየ ዙር የሚከናወን ቢሆንም የተጀመሩ የማስተካከያ ስራዎች ግን ነበሩ። በእነርሱ ምልክታ በአንድ ዓመት ውስጥ ምን ያህል ሊሰራ ይችላል የሚለውን በመገምገም፤ እንጂ በደረጃ ችግር አልነበረም አዘጋጅነቱ የተወሰደው።ልክ ነው፤ እኔም ከቡድኑ ጋር ነበርኩ። ለምሳሌ የአዲስ አበባ ስታዲየም ከተገነባ ረጅም ጊዜ ስለሆነው ሜዳው በፊፋ የምስክርነት ማረጋገጫ ባላቸው ባለሙያዎች በድጋሚ አሰሩት ነው የተባለው። ሌሎች ስታዲየሞች ላይም ያሉት ሁለት ሁለት መልበሻ ክፍሎች እስከ 30አባላት ላሉት አንድ ቡድን በቂ ባለመሆኑ አፍርሳችሁ አስፉት ነው የተባለው። በሃገሪቷ በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶች በመሰራት ላይ ይገኛሉ። ከዚህ ባሻገር የእኛ ፕሮጀክቶች በዙር እንደሚሰሩ ባለማወቃቸው፤ ተጀምሮ እንደቆመ ነው የሚገነዘቡት። አመራሩ የወሰነውም ችግሩን በመውሰድ የቀሩትን ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ በሌላ ጊዜ መጠየቅ ይሻላል በሚል ነው። ይሄ ትንሽ የተወሳሰበ ነው። ነገር ግን በየትኛውም ክልል የሚወጣው ገንዘብ የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት ነው። የትኛውም ማዘውተሪያ ሲገነባ ታዋቂ ስፖርተኞችን ለማፍራትና ትልልቅ ውድድሮችን ለማስተናገድ ነው። ተጨባጭ ወደሆነው ነገር ስንገባ ግን የተወሳሰበ ነው። ለአብነት ያህል የጋምቤላ ስታዲየም 65 በመቶ ቢደርስም በበጀት ችግር ቆሟል። የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ደግሞ የጋምቤላ ክልል ምክር ቤትን በጀት መድበው እንዲጨርሱ ማድረግ ይችላል ወይ? የለውም። ገፍተን የማንሄድባቸው ነገሮች ቢኖሩም ግን ቴክኒካዊ ድጋፍ እናደርጋለን፤ የትኞቹም ስታዲየሞች ሲገነቡ እኛ ጋር መጥተው አማክረውን ነው። በተመሳሳይ የጅግጅጋ ስታዲየም ዲዛይን ተሰራ፤ አፈር ጠረጋ ተከናወነ፣ የግንባታ ቁሳቁስም ተቀመጠ ከዚያ ስራው ቆመ። በኮንትራት አስተዳደር ችግር ማለት ነው፤ ለምን ይህ ተደረገ ብለን በቀጥታ መጠየቅ ግን አንችልም። ምክንያቱም የእኛ ግንኙነት ከክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ጋር ነው። ሌላው በኃላፊዎች መቀያየር የሚፈጠር የመረጃ ክፍተት የሚከሰት ነው። ለውድድር የሚሆን የማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረት የለብንም። ይህ ከቆጠራው ጋር የሚያያዝ ነው፤ በእያንዳንዱ ወረዳ ቢያንስ በትምህርት ቤት ደረጃ ማዘውተሪያዎች አሉን። ነገር ግን መረጃውን ይዞና በትክክል አውቆ መጠቀም ላይ ችግር አለ። በየትምህርት ቤቱ በርካታ ደረጃቸውን የጠበቁ የሦስት በአንድ ሜዳዎች ይገኛሉ፤ በየተቋማቱም በተመሳሳይ። ማዘውተሪያ የለም የምንለውም በአንድ ወረዳ ላይ ምንም ከሌለ ነው። ለምሳሌ በአዲስ አበባ በአማካይ ቢታይ ማዘውተሪያ የሌለው በአንጻሩ ደግሞ ብዙ ያለበት ወረዳ ይኖራል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ደግሞ ክፍት ቦታዎችን ለስፖርት እንዲሆኑ በማመቻቸት ላይ ክፍተት ይኖራል፤ እንጂ ችግር ይኖራል የሚል እምነት የለኝም። በሁሉም የስፖርት ዓይነቶች ለውድድር የሚሆኑ ማዘውተሪያዎች አሉ፤ ነገር ግን ለህጻናት፣ ወጣቶችና አዋቂዎች የሚሆን በማዘጋጀት ላይ ግን ቀሪ ስራ አለ። አንዱ ክፍተት የማዘውተሪያ ስፍራዎችን እንዴት እናስተዳድር የሚለው ነው። በእርግጥ አዋጁ ብቻ ለዚህ በቂ ነው፤ የእኛ ችግር ነው እንጂ። አዋጁ ላይ በግልጽ የተቀመጠውን ማስፈጸም ላይ ስፖርቱን የሚመራው አካል ከወረዳ እስከ ፌዴራል የቁርጠኝነት ችግር አለ። በመሆኑም ደንቡን በማውጣት ለኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ተልኳል፤ ከዚያም በሚኒስትሮች ምክር ቤት አስተያየት ተሰጥቶ ከጸደቀ በኋላ ወደ ተግባር የሚገባ ይሆናል። ነገር ግን የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት በራሱ ችግሩን አይፈታውም፤ የአመራርና ፈጻሚን ቁርጠኝነት ይጠይቃል። ማዘውተሪያ ስፍራ ማለት ለመጪው ትውልድ የምናስተላልፈው ሃብት ነው። አሁን ያለው ሁኔታ እየተቀየረ ይሄዳል፤ አሁን በየወረዳው ያሉ ከተሞች በፍጥነት እያደጉ የቦታ ጥበት ይከሰታል። የአሁኑን እየወቀስን ነገ ከዚህ የባሰ እንዳይመጣም ህብረተሰቡ ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ይጠብቅ፣ ይንከባከብ፣ ያለ አግባብ ሲወሰድበትም ለህግ አካላት ያሳውቅ። በሁሉም ደረጃ ያሉ፤ የመሬት አስተዳደር አካላትም መሬትን አሳልፎ ለሌላ ኢንቨስትመንት መስጠት ሃገርን አያሳድግም። የሃገር እድገት የሚመጣው ጤነኛ ማህበረሰብን መፍጠር ሲቻል ነው፤ ዜጎችን እየገደሉ ህንጻ መገንባትም ሃገርን ስለማያሳድግ ትኩረት ይደረግበት ስል አሳሰባለሁ።አዲስ ዘመን ግንቦት 12/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11093
131eb2abc10eb290a6dfe04f6fcddc76
39a270d08078e6fc1d62f5699463e314
አዳ ሄገርበርግ የቢቢሲ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባለች 
የሊዎኗ የፊት መስመር ተጫዋች አዳ ሄገርበርግ በቻምፒዮንስ ሊጉ የፍጻሜ ጨዋታ ሀትሪክ በሰራች ማግስት በስፖርቱ ህይወቷ ለታላቅ ሽልማት በቅታለች። አዳ በአለም ዙሪያ በሚገኙ ደጋፊዎች በተሰበሰበ የሕዝብ አስተያየት ድምጽ የ2019 የቢቢሲ የዓመቱ ምርጥ የሴቶች እግር ኳስ ተጫዋች ሆና ተመርጣለች። አዳ የቢቢሲ ሬድዮ ዓለም አቀፍ አገልግሎት ያበረከተላትን ሽልማት አስመልክታ ‹‹ለማመን የሚከብድ ነው፤ ለዚህ ስኬት እበቃለሁ ብዬ አልጠበኩም ፤ በጣም ጥልቅ ስሜት ተሰምቶኛል›› ስትል ሽልማቱ በተበረከተላት ወቅት ተናግራለች። ለዚህ ሽልማት አምስት ተወዳዳሪ እጩዎች የቀረቡ ሲሆን ጃፓናዊቷ የሊዮን የመሀል ተከላካይ ሳኪ ኩማጊና አሜሪካዊቷ የመሀል ሜዳ ተጫዋች ሊንድሴይ ሆርራን ተካተውበታል። የ 23 ዓመቷ ኖሮዌያዊት አዳ በ2017(እኤአ) ይህን ሽልማት ማሳካት ችላለች። በዘንድሮውም ዓመት ዳግም በማሸነፍ ለሁለተኛ ጊዜ ይህን ክብር ተቀብላለች። አዳ ሌሎች እጩ ተፎካካሪ ተጫዋቾችን አስመልክቶ ሽልማቷን በተቀበለችበት ወቅት ‹‹ሳኪ በጣም የምቀርባት ጓደኛዬ ናት።የሷን ብቃትና ችሎታ ለክለቧም የምታበረክተውን ከፍተኛ አገልግሎት ጠንቅቄ አውቃለሁ። የጃፓን የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አምበልም ናት። ይህ ሁሉ የሚያሳየው ድንቅ ተጫዋች መሆኗን ነው ስትል›› ለቡድን አጋሯዋ ያላትን አድናቆት ገልጻለች። ሳምና ፔርኒሌ ከሊንድሴይ ባሻገር ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው ተጫዋቾች መሆናቸውንም አዳ አልሸሸገችም። አዳ ለሁለተኛ ጊዜ ይሄን ክብር በመቀዳጀቷ የተሰማትን ስሜት  ለመግለጽ ቃላት እንዳጠራት አብራርታለች። ቢቢሲ በድረ ገጹ እንዳስነበበው በአለም ዙሪያ የተጫዋቿ አድናቂዎች ባለፉት አመታት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የተጫዋቿ ማሕበራዊ ድረገጽ የሚያሳይ ሲሆን፤ የመጀመሪያዋ የአለማችን የሴቶች ባላንዶር አሸናፊ ለመሆን በቅታለች። የሄግበርግ የሕዝብ መግለጫ ባለፈው አመት ጨምሯል, ለዚህም በከፊል የሴቶች የቡላንዶር እና የእርሷ ግቦች ስታትስቲክስ ለራሳቸው ይናገራሉ። እ.ኤ.አ በ2017 እስከ 18 በእድገት ወቅት ሁሉንም ውድድሮች ለሊዮን አስቀመጠች። በወቅቱ በ 33 ጨዋታዎች በ 29 እግር ግቦች ውስጥ መቆየት ችላለች። ምንም እንኳ የባርሴሎና ውድድር በተካሄደው የቅዳሜው የመጨረሻ ደረጃ ላይ የ16 ደቂቃ የእርሷ ውድድር የቢቢሲው የምርጫ ድምጽ ከተዘጋ በኋላ ብቅ ብቅ ብሏል።እሷ እንዲህ ትላለች ‹‹አንዳንድ ጊዜ ‘እንዲህ ማድረግ የምችል ይመስለኛል’ ብዬ አስባለሁ።”ይሁን እንጂ ሁሉንም ነገር በዓይነ ሕሊናቸው መሳል እስከዚያ ጊዜ ድረስ ይመራናል.”ብላለች። እ.ኤ.አ. በ 2017 አዳ ሄገር በርግ በኖርዌይና በዓለም አቀፋዊ ደረጃም በተለይም ለወጣት ልጃገረዶች እኩልነት አለመኖሩን በመቃወም እራሷን ከቡድኑ አግልላም ነበር። ይህ ማለት በዚህ ሰመር በፈረንሳይ በሚደረገው የአለም ዋንጫ ውድድር ውስጥ የኖርዌይ ቡድን አካል አይደለችም ማለት ነው። “እነዚህን ሁሉ አሸናፊዎችና እነዚህን ሁሉ ስኬቶች ማሸነፍ ድምጽ ይሰጡሀል” ብላለች። “እኔ ስለእኔ አይደለም የምናገረው።ይህ ስፖርት ብዙ አይነት ለውጦችን በማምጣት ላይ ነው። ሌሎችንም ማነሳሳት አለበት ትላለች አዳሄገር በርግ።.”ሁላችንም በዚህ ላይ ስንቆም, ስፖርታችንን በትክክለኛው አቅጣጫ ለማምጣት, እኛ በጣም ጠንካራ እንሆናለን.” ስትል አክላለች።አዲስ ዘመን ግንቦት 15/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11219
4d1cc21f224086e9d334dec36b5df66d
b174627c160c53b9ef6cd0f5271eca7c
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመዲናዋና በክልል ከተሞች ነገ እና ዕሁድ ሁሉም ስምንቱም ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ የሊጉ የሳምንቱ ትልቁ ጨዋታ ነገ ግንቦት 17/2011 ዓ.ም በጅማ ስታዲየም ጅማ አባ ጁፋር ከመቐለ 70 እንድርታ ከቀኑ አስር ስዓት ላይ ይፋለማሉ። በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ያሉ ክለቦች የሊጉን ዋንጫ ለማንስት በሚያደርጉት ትንቅንቅ በክለቦቹ መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት መጥበቡን ተከትሎ በፕሪሚየር ሊጉ ፉክክሩ እየተፋፋመ መጥቷል። በመሆኑም ነገ በመርሐ ግብሩ መሰረት አራት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ወላይታ ድቻ ከአፄዎቹ ፋሲል ከነማ፣ ሲዳማ ቡና ወራጅ ቀጠና ውስጥ ከሚገኝው ደቡብ ፖሊስ እንዲሁም ሃዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ ስዓት ከቀኑ ዘጠኝ ስዓት የሚፋለሙ ይሆናል። ሊጉ ዕሁድ እለት ቀጥሎ ሲውል አራት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኝው ስሑል ሽረ ከመከላከያ፣ አዳማ ከተማ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ከሚገኘው ከደደቢት እና የጣና ሞገዶቹ ባህር ዳር ከተማ ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ስዓት ከቀኑ ዘጠኝ ስዓት የሚፋለሙ ይሆናል። እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከድሬዳዋ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም በዚሁ ዕለት ምሽት አስር ስዓት ግጥሚያቸውን ያከናውናሉ።የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን አፄዎቹ ፋሲል ከነማ በ49 ነጥብ ሲመራ፤ መቐለ 70 እንደርታ በ48 ነጥብ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጧል። ሲዳማ ቡና በ46 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ይከተላል። በአንፃሩ ደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረ እና ደደቢት ደግሞ ከ14ኛ እስከ 16ኛ ያሉትን የመጨረሻዎቹን ሦስት ደረጃዎች ይዘው ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ፡ የፕሪሚየር ሊጉን ኮከብ ጎል አግቢነት የመቐለ 70 እንደርታው አማኑኤል ገብረሚካኤል እና የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በእኩል 15 ጎሎች ሲመሩ፤ የፋሲል ከነማው ሙጂብ ቃሲም በ12 ጎሎች ይከተላል። እንዲሁም የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ በ11 ጎሎች ሦስትኛ ደረጃን ይዞ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን እየተከተለ ይገኛል።አዲስ ዘመን ግንቦት 16/2011ሶሎሞን በየነ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11353
5919794d8f3c565156a512f83237b6a0
13a78ecb4b3a62e7e0e91650e690d44f
የዳርት ስፖርት ማሰልጠኛ ማንዋል ተዘጋጀ
 የኢትዮጵያ ዳርት ስፖርት የዳኝነት ስርዓትን በፌዴራል ደረጃ ወጥ በሆነ መልኩ ለማከናወን የሚያስችል የማሰልጠኛ ማንዋል ዝግጅት ተጠናቆ ሥራ ላይ መዋሉ ተገለጸ።የኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን ለአዲስ ዘመን እንደገለጸው፣ ማንዋሉ በአዲስ መልክ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ይህም እስከዛሬ የነበረውን የተዘበራረቀ አሰራር በማስቀረት ወጥ አሰራርን ለመዘርጋት ያግዛል። ከዚህ በኋላም በማንኛውም ደረጃ የሚካሄዱ የዳርት ውድድሮች፣ ግጥሚያዎችና ጨዋታዎች ወጥ በሆነ መንገድ የሚመሩት በዘርፉ ባለሙያዎች በተዘጋጀና ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን ባካተተ መልኩ በተዘጋጀው ማኑዋል ነው።ማኑዋሉ ከዳኝነት ስልጠና ባሻገር በርካታ ነባር ችግሮችን እንዲፈታ የተዘጋጀ መሆኑንም ፌዴሬሽኑ ይጠቁማል። ለሁሉም ክልሎች በአጋዥ መሳሪያነት፤ በተለይም በፅንሰ-ሀሳብ ብያኔ፣ ነጥብ አሰጣጥ፣ ሪኮርድ አያያዝ እና ሌሎች ችግሮችን ከመፍታት አኳያም በወጥነት እንዲያገለግል ሆኖ የተዘጋጀ መሆኑንም አመልክቷል።የኢትዮጵያ ዳርት ስፖርት ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን አላምረው እንዳብራሩት፤ ማኑዋሉ ከዚህ በፊት የነበረውን ሙሉ ለሙሉ በመከለስና የዓለም አቀፍ ዳርት ፌዴሬሽንን ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ከአገሪቷ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ የተዘጋጀ ነው። ከዚህ በኋላ የዳርት ውድድሮችን፣ የዳኝነት ሥነ-ሥርዓቱን፣ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሂደትንና መሰል ጉዳዮችንም ዓለም አቀፍ ህጉን መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲስተናገዱ ከማድረግ አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ታምኖበታል።የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ጎይቴ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ላይ ቀርቦ ይሁንታ ማግኘቱን ይገልጻሉ። ከዛሬ ጀምሮም ወደ ተግባር እንዲሸጋገር የተወሰነው ይህ ማኑዋል የዳርት ስፖርትን ተወዳጅና ተዘውታሪ ከማድረግ፣ ከማዘመን፣ ስፖርታዊ ጨዋነትን ከማስፈን፣ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ከማቀላጠፍ፣ በክልል ፌዴሬሽኖች፣ ማህበራትና ሌሎች ክበባት መካከል የጋራ ግንዛቤን ከማዳበር አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን እ.አ.አ በ2015 የዓለም አቀፉ ዳርት ፌዴሬሽን (WDF) አባል መሆኑ ይታወሳል።አዲስ ዘመን ግንቦት 12/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11095
a1b1c3e1c8d3b7231e03d78777fac762
7936b0b6f88f27518ea27822b8da7496
የሲዳማና ወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለቦችን የሚያቀራርብ ውይይት እየተካሄደ ነው
 በሲዳማ ከተማና በወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ መካከል የተከሰተውን ስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ችግር አስመለክቶ ሶስት ታላላቅ ውይይቶችን በማዘጋጀት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት እና የደቡብ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር እንደሚመክሩ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። መረጃው እንዳመለከተው ቀደም ሲል በደቡብ ክልል በተካሄደው መድረክ ላይ የሁለቱ ክለቦች በስፖርት መርህ መሰረት ስፖርቱን ማካሄድና ማህበረሰቡን ማቀራረብ በሚገባውአግባብ መፈጸም ሲገባቸው ያልተገባ ሁኔታዎች በመከሰቱ ችግሩም ቀላል ባለመሆኑ የውይይት መድረኮች መዘጋጀት እንደሚገባ ቃል መገባቱ ይታወሳል። ዛሬ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት በሚገኙበት የጋራ መድረክና ሰኞና ማክሰኞ በተናጥል በተለያዩ ቦታዎች ሲካሄዱ የነበሩ የጋራ መድረኮች ማጠቃለያ ይካሄዳል። በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ርስቱ ይርዳ እንዲሁም የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ እና የደቡብ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች ይሳተፋሉ። በውይይት መድረኩ የሁለቱ ክለቦች ችግሮቻቸውን በመፍታት የህዝብ ለህዝብ ቅርርቡን በማጠናከር ሰላማዊ የሆነ የውድድር ጊዜ እንደሚሆን ይጠበቃል።አዲስ ዘመን ግንቦት 15/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11222
6c76b923b802714e20d660f15612b970
4af238b0c01a8a7bfeb8d67da20c8f11
በአዲስ አበባ ‹‹ዘረኝነት ይብቃ›› በሚል መሪ ቃል የቦክስ ሻምፒዮና ተጀምሯል . ከ60ሺ ሰዎች በላይ የሚሳተፉበት ‹‹የማስ ስፖርት›› ዕሁድ ይካሄዳል
‹‹ዘረኝነት ይብቃ›› በሚል መሪ ቃል 7 ክለቦችና ከ60 በላይ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት የቦክስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም ማካሄድ መጀመሩን የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ አርአያ ብርሃኔ እንዳሉት፤ የቦክስ ሻምፒዮናው በትናንትናው ዕለት መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ እስከ መጋቢት 18 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል፡፡ ውድድሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቷ እየታየ ያለውን የጥላቻ ፖለቲካ እንዲበቃ ለማድረግና በከተማዋ የቦክስ ስፖርት እንዲስፋፋ በማድረግ ቀጣይነት ባለው መልኩ ወንድማማችነትንና ማኅበራዊ ግንኙነቶችን በማጠናከር ስፖርታዊ ጨዋነት የተላበሰ ብቁ ተወዳዳሪ ‹‹ኤሊት›› ስፖርተኞችን ለማፍራት ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡ በዓይነቱ የተለየ የመጀመሪያው የቦክስ ውድድር ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን፤ስፖርት ሁሉን አቃፊ በመሆኑ በውድድር መድረኩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃለፊዎችን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦችም እየታደሙበት ይገኛል፡፡ ስፖርት ለጤንነት፣ ለወዳጅነት ብሎም ለሰላም የሚለውን መርህ ተከትሎ የታለመለትን አላማ በሚያሳካ መልኩ መጀመሩንም ነው ከአዘጋጆቹ መረዳት የተቻለው፡፡ በውድድሩ 6 ክለቦችና አንድ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የሴቶች ቡድን የሚሳተፉ ሲሆን፤ ዓላማውን በመደገፍ አዲስ አበባ ፖሊስ ፣ፌዴራልማረሚያ፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ፣ማራቶን ቦክስ፣ማራቶን ቦክስ ክለብ እና ተጋባዡ የድሬዳዋ ከነማ ቦክስ ክለብ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡ በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ሜዳ በድምቀት የተጀመረውን ውድድር የአላማውና የስፖርቱ ደጋፊዎች በሙሉ በቀሪው የውድድር ቀናት እንዲታደሙ በፌዴሬሽኑ በኩል ጥሪ ተደርጓል፡፡ እንደ አቶ አርአያ ገለጻ፤ ስፖርት የጥላቻ ፖለቲካዊ አስተሳሰብን ይሰብራል ተብሎ የተዘጋጀው የቦክስ ሻምፒዮናው፤ ስፖርት የአንድነት መፍጠሪያ መድረክ መሆኑን በመገንዘብ የመተጋገዝ ባህልን ለማጎልበት፣ ስፖርት ለሰላምና ለአንድነት ያለውን ፋይዳ በህብረተሰቡ ዘንድ ለማስረጽ፣ የአጋርነት ስሜትን በማጎልበት ተነሳሽነትን ለመፍጠር፣ በነፃነት ማግስት የተጀመሩ አንጸባራቂ ልማቶችን በስፖርቱ ዘርፍ አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ ሀገራዊ ትውፊቶችን በኃላፊነት ተረክቦ ለቀጣይ ትውልድ የሚያስረክብ ዜጋ ለማፍራት፣ ወጣቶችን በስፖርት እንቅስቃሴ በማሳተፍ አገሪቷ በስፖርቱ እቅድ የያዘችውን ፖሊሲና ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ክለቦችን በስፖርት ውድድር በማሳተፍ ጤንነታቸው እንዲጠበቅና ከስፖርቱ ጋር በማላመድ ባላቸው አቅም እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ፤ ተተኪና ምርጥ ተወዳዳሪ ስፖርተኞች ለፌዴሬሽኑ፣ ለከተማውና ለክለቦች ማፍራት፤ በክለብ ስፖርት በስፋት ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል፤ በስፖርት ውድድሩ የባህል ልውውጥ እንዲካሄድ በማድረግ ክለቦች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻልና የአገሪቷን ብሎም የከተማውን ህብረተሰብ ፍላጎት በማርካት የቦክስ የስፖርት ህዳሴን ማረጋጋጥ፤ ዘረኝነትን የሚጠየፍ ትውልድና ስፖርተኛ ማፍራት እንዲሁም በቦክስ ስፖርት ከተማ አስተዳደሩንና አገርን የሚወክሉ ስፖርተኞችን ማፍራት የውድድሩ ተቀዳሚ ግብ መሆኑንም አቶ አርአያ አስታውቀዋል፡፡ በተያያዘ መረጃ፤ በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ60ሺ በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያሳትፍ የማስ ስፖርት የፊታችን ዕሁድ ይካሄዳል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ሥልጠና ተሳትፎና ውድድር ዳይሬክተር አቶ በሀይሉ በቀለ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በማስ ስፖርቱ በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ የሚሆኑበት ሲሆን መርሃ ግብሩ የፊታችን ዕሁድ በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል፡፡በያዝነው ሳምንት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በከተማዋ የማስ ስፖርትን በይፋ ለማስጀመር በተዘጋጀ መድረክ ላይ ከዘርፉ ከተውጣጡ 33 ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንቶችና 3 አሶሴሽን ሥራ አስፈፃሚዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በመድረኩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከስፖርት ማህበራት ጋር በመሆን የስፖርቱን ዘርፍ ለማሳደግ እና በተግባር ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት እንደሚሠራና ስፖርት ዘረኝነትንና ቂምን በማስወገድ ፍቅር፣ አንድነትንና መቻቻልን የሚያመጣ አንዱ መሳርያ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የዚህ ዓይነቱ መርሃ ግብር ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተጨማሪ የስፖርቱ ዘርፍ እንዲያድግ የሚረዳ በመሆኑ በተከታታይነት እንደሚካሄድም ተናግረዋል፡፡ መርሃ ግብሩ ህብረተሰቡ በሚማርበት፣ በሚሠራበትና በሚዝናናበት አካባቢ ጤና ተኮር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተሳታፊ እንዲሆን፣ ከዘረኝነት አስተሳሰብ የፀዳ ፣ በመቻቻል በመግባባትና በመከባበር መልካም እሴቶችን የሚያከብር ፣ ከአደገኛ ሱሶች የራቀ ህብረተሰብ መፍጠርን አላማው ያደረገ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡ በኢንጂነር ታከለ ኡማ አነሳሽነት በሚካሄደው በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ፣ ምሁራን ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የካቢኔ አባላት፣ አርቲስቶች፣ የስፖርት ማህበራት፣ የእግር ኳስ ደጋፊ ማህበራትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተካፋይ ይሆናሉ፡፡አዲስ ዘመን ግንቦት 16/2011አዲሱ ገረመው
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11348